📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:
1.አንጋፋው አርቲስት ኪሮስ ኃይለሥላሴ በማርች ባንድ ታጀቦ ምስጋና ሊቀርብለት ነው።
2.አርትስ ቴሌቪዥን በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ አዲስ ድራማ ሊጀምር ነው።በሌላ "በሕግ አምላክ" ድራማ ምዕራፍ ሶስት የሚጀምርበት ቀን ታውቋል።
3. ተወዳጁ ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው።
4.ሁለቱ ግዙፍ የሥየጥበብ አውደርዕዮች በአንድ ሳምንት በተከታታይ ቀናት ሊካሄዱ ነው።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/3dymotNOWis?si=a9WgTbBvuj-m2cdP
📌መልካም ምሽት
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌"የደራው" መጽሔት ለንባብ በቃ
"የደራው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ዲጂታል መጽሔት ሶስተኛ እትም ለንባብ በቅቷል።
ዲጂታል መጽሔቱ በዚህኛው እትም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ ይዟል።
ከእዚህም መካከል በአዲስ አበባ በሰማይ በራሪ ታክሲዎች ፣የአሜሪካው ታሪፍ፣የቲክቶክ ውለታ፣ወደብ ማግኘት፣መርካቶ እንሂድ፣በBig Habesha የሙዚቃው ዓለም ጦርነት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ ተብላችኋል።
መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://www.tg-me.com/yederaw

👍1
የጠይም ፈረንጅ 50,000 ብር ሊሸልም ነው!!
ሙዚቀኛ ብስራት ሱራፌል ስድስት የሙዚቃ ስራዎችን የያዘው ተወዳጅ ሙዚቀኞች እና ደራሲዎች ያሳተፈው የጠይም ፈረንጅ አልበም በቅርብ ቀን ለአድማጭ ሊያደርስ ዝግጅቱን አጠናቋል!
ሙዚቀኛውም ከዚህ በፊት ተወዳጅ ሁለት አልበሞችን ቃል በ ቃል እና ማለፊያ በተጨማሪም ነጠላ ዜማዎቹ በአድማጭ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙ ናቸው::
ታዲያ የጠይም ፈረንጅን የአልበም ገፅ (Cover) ምስል የፈጠራ አቅም ላላቸው ሰዎች እድሉን ሰጥታል! ከአልበሙ መጠሪያ እና ከቀደሙት ስራዎቹ በመነሳት ይገልፃል ብላችሁ የምታስቡትን ስራ ከታች በተቀመጡት አድራሻዎች መሳተፍ ትችላላችሁ!!
ታዲያ ከሁሉም ተወዳዳሪዎች አንድ ብቻ አሸናፊ ሲኖር ሽልማቱም ሃምሳ ሺ ብር ጨምሮ በጠይም ፈረንጅ አልበም ገፅ ላይ ይሄው ምስል ይውላል!
በቴሌግራም @YeteyimFerej
(0972236767)
በኢሜል [email protected]
በመላክ መሳተፍ ትችላላችሁ!
ለተወዳዳሪዎች በሙሉ መልካም እድል!
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1

'የትዝታዬ ማሕደር' ሚያዝያ 5 2017 ዓ.ም ይመረቃል
"ዳግላስ ጴጥሮስ "በሚለው የብዕር ስሙ የሚታወቀው፣ በርካታ መፅሀፎችን እና መጣጥፎችን ያስነበበው ደራሲ ጌታቸው በለጠ 'የትዝታዬ ማሕደር' በሚል ርዕስ የሕይወት ታሪኩን ፅፎ በቅርቡ ያስመርቃል፡፡
ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለ ሲሆን በየጊዜው በሚሰጣቸው የማህበራዊ እና የኪነ ጥበባት ሂሶችም ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ሚድያዎች ላይ በመቅረብ ቃለ- መጠይቆች በመስጠት ከበሬታን ያገኘ ደራሲ ነው።
ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በጋዜጦች ላይ በመፃፍ አቅሙን ያሳየ የብዕር ሰው ነው።
ደራሲ ጌታቸው በለጠ የሚያስመርቀው መፅሀፍ፣448 ገፆች ያሉት ሲሆን ከልጅነት እስከ አዋቂነት ዕድሜ ያሳለፈውን ሕይወት በመፅሀፉ ላይ አካቷል፡፡
የደራሲ ጌታቸው መፅሀፍ 1000ብር የሚሸጥ ሲሆን በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ታዋቂ ደራሲያን፣ እና የቅርብ ወዳጆቹ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

📌ሁለት ግዙፉ አውደርዕዮች በአንድ ሳምንት
በአንድ ሳምንት በተከታታይ ቀናት የሚካሄዱት አውደርዕዮች አርት ኦፍ ኢትዮጵያ እና The Big Art Sale ናቸው።
በሸራተን አዲስ በየዓመቱ ይካሄድ የነበረውና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለአምስት አመታት ተቋርጦ የነበረው Art of Ethiopia የሥነጥበብ አውደርዕይ ዘንድሮ ተመልሷል።
ከአምስት በኃላ በተዘጋጀው በዚህ አውደርዕይ ላይ 62 ሠዓልያን የሥዕል ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሚያዚያ 2 እና 3 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ይካሄዳል።
በሌላ በኩል The Big Art Sale
በሒልተን ሆቴል ቅፅር ግቢ ውስጥ ሚያዚያ 4 እና 5 2017 ዓ.ም የሚካሄደው ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ከ200 ሠዓሊያን የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውን ለሽያጭ ይቀርባሉ።
ዝግጅቶቹን What's out Addis ከሸራተን አዲስ፣ ከሂልተን ሆቴልና ከካልቸር ክለብ ጋር በመጣመር አሰናድተውታል።

📌የአስቻለው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው
በእናትዋ ጎንደር፣ካሲናው ጎጃም፣ አሞራው ካሞራ በተሰኙ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው "አስቻለ"የተሰኘው አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለሙዚቃ አፍቃሪው ያደረሰው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ( አርዲ) የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ሀገር ሊያቀርብ እንደሆነ ገልጿል።
አርትስ ስፔሻል ከድምጻዊ እንዳገኘው መረጃ ከሆነ የሙዚቃ ዝግጅቱ ከፋሲካ በኃላ በፈረንጆቹ ሜይ 15 2025 በቴላቪብ እንደሚካሄድ ተነግሯል።
ድምጻዊ አስቻው ፈጠነ የሙዚቃ ኮንሰርት በእስራኤል ካቀረበ በኃላ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት የሙዚቃ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ ድምጻዊው ለአርትስ ስፔሻል ገልጿል።

📌አምስተኛው የጣፋጭ ሕይወት ምስጋና
በጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጅው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና ዝግጅት ዘንድሮው ለአምስተኛ ጊዜ ይካሄዳል።
አምስተኛው ምን ምን አዲስ ነገር ይዟል?ምንስ ክንውኖች ይኖሩታል ?
በዚህ መርሐግብር የጣፋጭ ሕይወት የፓናል ውይይት ሚያዝያ 30፣የቤተሰብ ፌስቲቫል ግንቦት 17 ዋናው የምስጋናና የሽልማት ቀን ግንቦት 30 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዚህ መርሐግብር መምህራን ፣የህክምና ባለሞያዎች፣አሽከርካሪዎች እና የፅዳት ባለሞያዎች፣ቤተሰቦች ይመሰገናሉ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 30 የምስጋና ቀን እንዲሆንም እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል።
በስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይም በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በህይወት ክህሎት ስልጠና ፣ በበጎ አድራጎት ፣ ዝናን ለመልካም ምግባር፣ሚዲያውን ለስነልቦና ግንባታ ፣ ማህበራዊ ሚዲያውን ለመልካምነት ለተጠቀሙት ግለሰቦች እና ተቋማት ሽልማት ይሰጣል።
በመርሃግብሩ ላይ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ንግግር እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

📌"የተቀደሱ ማሚቶዎች" የሥዕል አውደርዕይ
የሠዓሊ አለባቸው ካሣ የሥዕል ስራዎች የሚቀረቡበት "የተቀደሱ ማሚቶዎች" የሥዕል አውደርዕይ አርብ ሚያዝያ 3 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሚያዝያ 17 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

📌"ሰተቴ" ተከታታይ ድራማ ለእይታ ሊበቃ ነው
በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ "ሰተቴ" የተሰኘ አዲስ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ በአርትስ ቴሌቪዥን በቅርቡ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀመር ተነግሯል።
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
በመንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ ላይ መሠረቱን ያደረገ "ሰተቴ" የተሰኘ አዲስ ተከታታይ አስቂኝ ድራማ በአርትስ ቴሌቪዥን በቅርቡ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀመር ተነግሯል።
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
❤2
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል
በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" ስምንተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ሚያዝያ 4 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት ይካሄዳል።
ባለፉት ሰባት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ ስድስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።
በዕለቱም ደራሲ ከበደ ሚካኤል የሚዘከር ሲሆን ኃይሉ ፀጋዬ የዕለቱ ተጋባዥ የክብር እንግዳ በመሆን እንደሚገኝ ተገልጿል።
አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ እምቅ፣ ጥልቅ፣ ምጡቅ የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

📌ሁለት አጫጭር ፊልሞች ለእይታ ሊበቁ ነው
"ገብረ ጉንዳን" እና "አልባትሮስ" የተሰኙ ርዕሶች የተሰጣቸው ሁለት አጫጭር ፊልሞች ነገ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ለእይታ ይበቃሉ፡፡
ሁለቱም ፊልሞች አጭር ፊልም የመስራት ሀሳብ ላላቸው እንዲሁም አጭር ፊልም መታደም ለሚፈልጉ የፊልም አፍቃሪያን ጥሩ አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ወጣቱ የፊልም ባለሞያ ናትናኤል ማርቆስ ይታሰባል።
የመግቢያ ዋጋው 2ዐዐ ብር ሲሆን ትኬቱን ቀድማችሁ በሚከተለው 1000394090658 (CBE) 0919320448 (Telebirr)
Dawit nahusenay የቴሌብር አካውንት መቁረጥ ትችላላችሁ ወይንም ወይም በሚቀጥለው ሊንክ መመዝገብ ይቻላል።
https://forms.gle/hwduM3nEqmh31Rwh8

❤1
📌የግጥም ምሽት የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል
"Youth impact" የግጥም ምሽት አዘጋጅቷል።
ይህም የግጥም ምሽት ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው Youth impact ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"Youth impact" የግጥም ምሽት አዘጋጅቷል።
ይህም የግጥም ምሽት ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው Youth impact ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ልዑል ሲሳይ ተከታታይ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው
የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰርት የፊታችን ሚያዚያ 18 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 እስከ እኩለሌሊት 6:00 ድረስ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የተዘጋጀው ኮንሰርት እንደተጠናቀቀ ግንቦት 2 በሀዋሳ፣ ግንቦት 23 በድሬደዋ ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ከልዑል ሲሳይ በተጨማሪስካት ናቲ፣ ሃና ግርማ እና ዊሃ በዝግጅቱ ላይ በቶራ ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
በሦስቱም የኮንሰርቶች ላይ በአጠቃላይ ከ22 ሺህ በላይ ተመልካች የሚጠበቅ ሲሆን ቀድሞ ለሚገዙ ውስን የሚሆኑ ትኬቶችን 400 ብር መደበኛ 600 በዕለቱ በር ላይ 800 ቪአይፒ 2500 ብር ሲሆን ትኬቱን መግዛት የሚቻለው በቴሌ ብር ብቻ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በዘመናዊ ሙዚቃ በመጀመሪያ አልበም ከፍተኛ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ያገኘው ልዑል ሲሳይ በፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ እና ሸጋ ኤቬንትስ እና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የሙዚቃ ቱር "የልዑል ሙዚቃ ቱር" በሚል ስያሜ ያከናውናል።
ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ "ልዑል'' ሲል በሰየመው የመጀመሪያ አልበሙ ውሰጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ስልተ-ምቶችን ጨምሮ ሬጌና ፖፕ ስልቶችን አካቶ መምጣቱ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰርት የፊታችን ሚያዚያ 18 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 እስከ እኩለሌሊት 6:00 ድረስ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የተዘጋጀው ኮንሰርት እንደተጠናቀቀ ግንቦት 2 በሀዋሳ፣ ግንቦት 23 በድሬደዋ ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ከልዑል ሲሳይ በተጨማሪስካት ናቲ፣ ሃና ግርማ እና ዊሃ በዝግጅቱ ላይ በቶራ ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
በሦስቱም የኮንሰርቶች ላይ በአጠቃላይ ከ22 ሺህ በላይ ተመልካች የሚጠበቅ ሲሆን ቀድሞ ለሚገዙ ውስን የሚሆኑ ትኬቶችን 400 ብር መደበኛ 600 በዕለቱ በር ላይ 800 ቪአይፒ 2500 ብር ሲሆን ትኬቱን መግዛት የሚቻለው በቴሌ ብር ብቻ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በዘመናዊ ሙዚቃ በመጀመሪያ አልበም ከፍተኛ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ያገኘው ልዑል ሲሳይ በፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ እና ሸጋ ኤቬንትስ እና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የሙዚቃ ቱር "የልዑል ሙዚቃ ቱር" በሚል ስያሜ ያከናውናል።
ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ "ልዑል'' ሲል በሰየመው የመጀመሪያ አልበሙ ውሰጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ስልተ-ምቶችን ጨምሮ ሬጌና ፖፕ ስልቶችን አካቶ መምጣቱ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:
1.ከተማ በቃኝ ብሎ ጭልጥ ያለ ገጠር የገባው ኢትዮጵያዊ ሠዓሊ የሥዕል ሥራዎቹ በሸራተን አዲስ ሆቴል ለእይታ ቀረቡ።
2.ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ እና ድምጻዊ አለማየሁ ሂርጶ ከ20 ዓመታት በኃላ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን በአንድ መድረክ ሊያቀርቡ ነው።
3.ወጣቱ ድምጻዊ ልዑል ሲሳይ በሶስት የኢትዮጵያ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ አስታወቀ።
4.ግንቦት 30 ሀገር አቀፍ የምስጋና ቀን እንዲሆን ጥያቄ ቀረበ።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/PZ_0mMbltYk?si=xAPx2WFWhr-JJh4z

ሰይፍ ፋንታሁን ህመም ገጥሞት እንደነበረ ተናገረ
ዝነኛው የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ፕሮግራሞች አቅራቢ ሰይፉ ፋንታሁን ትንሽ ህመም ገጥሞት እንደነበረ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታወቀ።
ሰይፉ ፋንታሁን በማህበራዊ ትስስር ገፁ"ቀለል ያለውን አድርጎልኛል።እግዚአብሔር ይመስገን።በዚህ ሳምንት ወደ ስራ እመለሳለሁ" ብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
ዝነኛው የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ፕሮግራሞች አቅራቢ ሰይፉ ፋንታሁን ትንሽ ህመም ገጥሞት እንደነበረ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታወቀ።
ሰይፉ ፋንታሁን በማህበራዊ ትስስር ገፁ"ቀለል ያለውን አድርጎልኛል።እግዚአብሔር ይመስገን።በዚህ ሳምንት ወደ ስራ እመለሳለሁ" ብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"የደራው" መጽሔት አራተኛ እትም ለንባብ በቃ
"የደራው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ዲጂታል መጽሔት አራተኛው እትም ለንባብ በቅቷል።
ዲጂታል መጽሔቱ በዚህኛው እትም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ ይዟል።
ከእዚህም መካከል አንጋፋው ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ከዝነኛው ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ጋር የተጣመሩበት የ"ደጃዝማች" አልበም ጉዳይ ይገኝበታል።
የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ በደጆ ነው!!
በደራው መጽሔት በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ!
መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://www.tg-me.com/yederaw
"የደራው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ዲጂታል መጽሔት አራተኛው እትም ለንባብ በቅቷል።
ዲጂታል መጽሔቱ በዚህኛው እትም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ ይዟል።
ከእዚህም መካከል አንጋፋው ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ከዝነኛው ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ጋር የተጣመሩበት የ"ደጃዝማች" አልበም ጉዳይ ይገኝበታል።
የደራው መጽሔት በተወደደችው ቅዳሜ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ በደጆ ነው!!
በደራው መጽሔት በርካታ ጉዳዮችን በነፃ ይኮምኩሙ!
መጽሔቱን የግሎ ለማድረግ
👇👇👇
https://www.tg-me.com/yederaw
📌የፊልም ባለሞያ አንተነህ ኃይሌ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል
(መግቢያው በነፃ ነው)
የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር አንተነህ ኃይሌን ጋብዟል::
የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከአንተነህ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 7 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።
በዕለቱ ከፊልም ባለሞያው ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::
ፕሪስቴጅ አዲስ ከአንተነህ ኃይሌ ጋር የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ማክሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

📌ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቢሮ ከፈተ
በህንድ ሀገር መሰረቱን ያደረገው ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮውን ከፈተ
በውጭ ሀገራት ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን በማማከርና የጉዞ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚታወቀውና በህንድ ሀገር መሰረቱን ያደረገው ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቅርንጫፉን በይፋ እንደከፈተ አስታውቋል።
"ቫይደም ሄልዝ አለም አቀፍ ልምዱን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ከህክምና ጉዞ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው እፎይታን ለመስጠት ያለመ" መሆኑን የቫይደም ሄልዝ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ፓንኬጅ ቻንድራ ተናግረዋል።
ቫይደም ሄልዝ በህንድ፣ ቱርክ፣ ታይላንድ፣ ዱባይ፣ ጀርመን፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሲንጋፖር፣ ማሌዥያ እና ደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ ከ 8,000 በላይ ዶክተሮች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን እስካሁን ድረስም በዓለም ዙሪያ ከ 100,000 በላይ ታካሚዎች ህክምና እንዲያገኙ አስተዋጽኦ እንዳደረገም ተገልጿል።

📌 የዘሪቱ ከበደ የመድረክ አልበም
የዘማሪት ዘሪቱ ከበደ "ማዕናናትህ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና መድረክ (Live) ላይ እንደተቀረጸ የተነገረለት የመዝሙር አልበም የፋሲካ ዕለት እንደሚለቀቅ ዘማሪዋ በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
የዘማሪት ዘሪቱ ከበደ "ማዕናናትህ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና መድረክ (Live) ላይ እንደተቀረጸ የተነገረለት የመዝሙር አልበም የፋሲካ ዕለት እንደሚለቀቅ ዘማሪዋ በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
👍1
📌ሰራዊት ፍቅሬ በሲትኮም ድራማ እየመጣ ነው
ከበርካታ ዓመታት በኃላ ዝነኛው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ "ማረፊያ" በተሰኘ አዲስ አስቂኝ ድራማ ላይ ሊተውን እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የድራማው ፕሮዲዩሰር አርቲስት አሸናፊ ማህሌት በማህበራዊ ትስስር ገፁ"ይህ ቀን እንደሚመጣ አውቅ ነበር። እንዲህ ይፈጥናል ብዬ ግን አላሰብኩም ።ሁለገቡ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በተከፈተው የሚያዚያ ወር የአርቲስቶች የዝውውር መስኮት ሪከርድ በሆነ ዋጋ "ማረፊያ" የተሰኘውን ሲትኮም ድራማ ተቀላቅሏል" ብሏል።
በተጨማሪም አርቲስት አሸናፊ ማህሌት " ከወጣበት ከፍተኛ ዋጋ አንፃር በርካታ የሳቅ አና የቁምነገር ጎሎችን በማስቆጠር ተመልካቾቻችንን አርክቶ ለሲትኮማችን ብዙ ዋንጫዎችን ያመጣል ብለን እናምናለን" ሲል ተናግሯል።
አያይዘውም "ያለብንን የሳቅ ጫሪ አጥቂ ቦታ ስለሸፈንን በዚህ አመት ከንፈር የሚባለውን በረኛ አስከፍተን ጥርስን ነፃ በማውጣት ውጭ እንደምናሳድረው ለተመልካቾቻችን ቃል እንገባለን" ሲል ተናግሯል።