Telegram Web Link
📌"ገመሃልያ" ፊልም የፊታችን ሰኞ ይመረቃል

በኪማ ፊልምስ ተሰርቶ በፀጋ መልቲ ሚዲያ የቀረበው "ገመሃልያ" ፊልም የፊታችን ሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ በልዩ ዝግጅት ይመረቃል።

የፊልሙ ዳይሬክተር ዳይሬክተር ሳሙኤል (ባዩሽ ልጅ) ሲሆን በድርሰት ኤፍሬም ሀጎስ ተሳትፏል፣ 1 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ርዝመት ያለው ፊልሙ በፀጋ መልቲ ሚዲያ ፕሮዲውስ ተደርጓል።

በትወና ሰለሞን ቦጋለ፣ አዜብ ወንድሰን፣ ድምፃዊያን ቃልኪዳን ዳንኤል እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

ፊልሙ ለቀረፃ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የወሰደ ሲሆን ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶበታል።

የፊታችን ሰኞ መጋቢት 15 ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሞያዎች በተገኙበት በዓለም ሲኒማ የሚመርቅ ሲሆን መጋቢት 19,20,21 እና መጋቢት 26,27,28 በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል እንዲሁም በተመሳሳይ ሠዓት በአሜሪካን ሀገር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

አርዕስት መረጃዎች:

1.የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን "እሳት ወይ አበባ" የግጥም መጽሐፍ ከዓመታት በኃላ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ ሊበቃ ነው።

2.ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ለየት ባለ አጻጻፍ የመጡበት አዲስ መጽሐፋቸው ለንባብ በቃ።

3.መቼቱን በአንድ የፋሲካ ዋዜማ ምሽት ላይ ያደረገው ፊልም ለእይታ በቃ።

4.ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል።

5.ነገረ መጻሕፍት የመጽሐፍ ውይይት ነገ ይካሄዳል።

6."ገመሃልያ" ፊልም የፊታችን ሰኞ ለእይታ ይበቃል።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/OwAYLBrkeYU?si=W1TtMma0IAB7PqO5

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አል ዐይን አማርኛ ሥራ ሊያቆም ነው

ባለቤትነቱ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግሥት የኾነው አል ዐይን አማርኛ የበይነ መረብ የዜና ማሠራጫ ሥራ ሊያቆም ነው ፡፡

የዜና ማሠራጫው በአማርኛ ቋንቋ ዜናዎችንና ዘገባዎችን የሚያዘጋጁ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎቹን የቅጥር ውል አቋርጧል ፡፡

ተቋሙ የሠራተኞቹን ውል ያቋረጠው፣ የአማርኛ ዜና አገልግሎቱን አቁሞ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ለመውጣት በማሰቡ መኾኑን ዋዜማ ዘግባለች ፡፡

ዘጋቢዎቹ ሥራቸውን እየሠሩ ባሉበት ወቅት ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቂያ ሳይደርሳቸው፣ በድንገት የሥራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልዕክት በኢሜይል እንደደረሳቸው ዋዜማ ሰምታለች፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት የጀመረው አል ዐይን አማርኛ ከትናት በስትያ ጀምሮ ዜናዎችን አላሠራጨም፡፡ የዜና ድረረገጹ በዋናነት ትኩረቱን በመካከለኛው ምሥራቅ ላይ አድርጎ የአገር ውስጥና ዓለማቀፍ ዜናዎችን በአማርኛ ቋንቋ ለኢትዮጵያዊን አንባቢዎች ሲያቀርብ ነበር፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"የደራው" መጽሔት ለንባብ በቃ

"የደራው" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ዲጂታል መጽሔት የመጀመሪያው እትም ለንባብ በቅቷል።

ዲጂታል መጽሔቱ በዚህኛው እትም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዞ ይዟል።

ከእዚህም መካከል ቬሮኒካ አዳነ ከየት ወዴት፣ቢመሽም በር መዝጋት አይቻልም፣ሪቫን ልንቆርጥ ይሆን?፣መስሪያ ቤት እስር ቤት አይደለም፣Big Habesha የጠቆመን መኪና እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን በነፃ ይኮምኩሙ ተብላችኋል።

መጽሔቱን ለንባብ ሊንክ:https://www.tg-me.com/yederaw
📌ድምጻዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ትቀርባለች

(መግቢያው በነፃ ነው)

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር ፀደኒያ ገ/ማርቆስን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች "ከፀዲ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮዋን የምታካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቿ የሚቀርቡላትን ጥያቄዎች  ማክሰኞ መጋቢት 16 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቷ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከፀደኒያ ገብረማርቆስ  ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ  ማክሰኞ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
https://jazzio.land/register

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ለውጥ " የተሰኘ ዝግጅት ሊካሄድ ነው

ግለሰባዊ፣ቤተሰባዊ፣ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ "ለውጥ" የተሰኘ ልዩ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት አሊ ኢድሪስ፣ዮሐንስ ኃ.ከበደ፣እንዳለ ጫላ፣ቤተልሔም ውቡ፣ዓይናዓለም መርሴ፣ ሜላት ስለሺ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች “በሽብር ወንጀል” ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞችን፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

በሌላ በኩል የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማን ፍስሐፅዮን የብርቱካንን ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በመግለጫቸው በድርጅቱ ውስጥ እና በውጭ የተቀናጀ ሀይል ከጋዜጠኝነት መርህ ውጭ የሆነ ተግባር ተፈፅሟል ብለዋል።

የብርቱካን ጉዳይም አዘጋጆቹ ያለ በቂ መረጃ ማጣራት ያከናወኑት መሆኑን ገልጸዋል።

ዝግጅቱም ከማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የወረደው በራሷ በብርቱካን ጥያቄ መሰረት መሆኑን ነው የተናገሩት መረጃዎችን ለማጣራት ባደረጉት ጥረትም ነገሩ ውሸት ሆኖ መገኘቱን ገልጸው፣ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በዶክመንተሪው ምክንያት ለፈጠረው ችግር መላ ኢትዮጵያውያንን ይቅርታ ጠይቀዋል።

ችግሩን በፈጠሩት አካላት ላይ ድርጅቱ አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድም በተጨማሪ አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚተባበር ገልጸዋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"የያዩ ትውስታ"የመታሰቢያ ዝግጅት እየተካሄደ ነው

የአንጋፋው ሙዚቀኛ ያየህይራድ አላምረው የመታሰቢያ ዶክመንተሪ ፊልም ምርቃትና ሊሰራው በውጥን ላይ የነበረው "አስርቱ ትዕዛዛት" የተሰኘው ስራው የሚቀርብበት "የያዩ ትውስታ" ተብሎ የተሰየመው ልዩ ዝግጅት ዛሬ መጋቢት 19/2017  ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል ሲል ባላገሩ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ታዋቂው የሙዚቃ ደራሲ፣ ፕሮዲውሰርና ፕሮሞተር ያየህይራድ አላምረው የጥላሁን "ቆሜ ልመርቅሽ" ፣ የአስቴር አወቀን "ሰበቡ" እና "የሠርጌ ትዝታ" ፣ የኩኩ "ይቺ ናት ሀገሬ" ፣ የቡድን ሥራዎች የኾኑት የነ ዘሪቱ "መኖርህን ሌሎች ይሻሉ" ፣ እና የነ ጸደኒያ "ሰው ነው ነው ለሰው መድሃኒቱ" የተሰኙ ሙዚቃዎች የግጥም ድርሰቶች ጀርባ የነበረ የሙዚቃ ፕሮዲውሰርና ፕሮሞተር ጭምር ነበር ።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1."The Big Art Sale" ዓወድርዕይ ለሃያኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው።

2.ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ከዓመታት በኃላ የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች ልታደርስ ነው።

3.አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ሊመሰገን ነው።

4.በእውነተኛ ታሪክ የተመሠረተው "ቀይ ባህር ሲቀላ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/qYHu2jD5558?si=tqbzAKeyIuRkGBMQ

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ግዙፉ አውድርዕይ ለሃያኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው

በጥበብ አፍቃሪያኑና በጥበበኛው ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው ’The Big Art Sale’ ዓውደ ርዕይ በዚህ ዓመት ለሃያኛ ጊዜ  በሒልተን ሆቴል  የፊታችን ሚያዝያ 4 እና 5  2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

በአውደ ርዕዩ ከ100 በላይ ሰዓሊያንና ቀራፂያን አዳዲስ ሥራዎቻቸውን ለጎብኚዎችና ለገዢዎች ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

ከጥበብ ስራዎች በተጨማሪ ጥበብ አፍቃሪያኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚዝናኑባቸው የመጠጥና የምግብ ኮርነሮች ሲኖሩ፤ለልጆች ልዩ የመጫወቻ ሥፍራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ይህ ልዩ ዓውደ ርዕይ ጠቢብያኑ ሥራቸውን እንዲሸጡ እድል የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ገቢውም  ለበጎ አድራጎት ሥራዎች እንደሚውል ተጠቁሟል።

በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የጥበብ ዓውደርዕዩ ዋትስ አውት አዲስ ከሒልተን ሆቴል ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ነው።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"የእግዜር ብቸኝነት" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የገጣሚ መኳንንት መንግስቱ ሦስተኛ መጽሐፍ የሆነው "የእግዜር ብቸኝነት" መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፍ በ138 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚ መኳንንት መንግስቱ ከዚህ ቀደም "ክፍት የስራ ቦታ" እና "ስንፋታ እንደግስ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አቅርቧል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ሊመሰገን ነው

ደራሲ፣አዘጋጅና ተዋናይ ቢኒያም ወርቁ የሚመሰገንበት ልዩ ዝግጅት የፊታችን ሰኞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል።

መርሐግብሩ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በጥበቡ ዓለም የኖረው እና እየኖረ የሚገኘው፣ በርካቶችን ከህልምና ተሰጥኦዋቸው ያገናኘው ሁለገቡ ከያኒ ቢኒያም ወርቁ ለእስካሁን አበርክቶው፣ ትጋትና ብቃቱ በይፋ የሚመሰገንበት መሰናዶ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ይህ የምስጋና መርሐግብር የፊታችን ሰኞ መጋቢት 22 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ከ11 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከናወናል።

አርቲስት ቢኒያም ወርቁ  ከ20 በላይ ፊልሞች እና ከ7 በላይ ትያትሮችን በደራሲነት፣ በአዘጋጅነት፣ በተዋናይነት እና በዳይሬክተርነት ሰርቷል፡፡

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017

«ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017» በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከመጋቢት 19 ቀን እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን በዛሬው እለት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጸው፥ ይህ ኤክስፖ ከዚህ ቀደም ከተደረጉ የንግድ ትርኢቶች የተለየ እና ልዩ የሚያደርጉት በርካታ ዝግጅቶች ማቀዱን ገልጿል።

በዚህ ኤክስፖ ጎብኚዎች የተለያዩ የፆም ምግቦች (በብፌ መልክ) በአንድ ቦታ በ150 ብር ከነፃ የስንቅ ማልት ጋር ያገኛሉ።

ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ የሆነውን የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በኤክስፖ ላይ በልዩ ሁኔታ ይተዋወቃል።

2.8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኤሌክትሪክ መኪና እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል እንዲሁም አይቴል የሞባይል ቀፎ ለሽልማት ቀርቧል።

ከመደበኛው የንግድ ትርኢት ባለፈ የባህል፣ የትምህርት እና የመዝናኛ መድረክ የቀረበ ሲሆን የሀገራችንን ባህል እና እሴቶች የሚያንጸባርቁ ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ይኖሩታል።

ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል፡፡

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
"በመንገዴ ላይ" አውደርዕይ በእይታ ላይ ነው

በሠዓሊና ቀራጺ ሄኖክ ፀጋዬ የተዘጋጀውና "በመንገዴ ላይ" የሚል ርዕስ የተሰጠው የቅራጻቅርጽ የሥነጥበብ አውደ ርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ መጋቢት 17  2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው እንጦጦ ጋለሪ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።ይህ የሥነጥበብ አውደርዕይ እስከ ሚያዝያ 7 2017 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ስም የተሰየመው የሮያሊቲ ክፍያ ማስገኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በተወዳጁ የሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካ ስም የተዘጋጀው የሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በይፋ ተዋውቋል።

ሥርዓቱ ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ወይም (EMEMRC) የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነው።

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የሮያሊቲ ክፍያ አሰባሰብን አስመልክቶ በጋራ ያዘጋጁትን የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ለማፅደቅ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቀረበለትን ቀመር ለማፅደቅ ከሚዲያ አመራሮችና ከፈጠራ ባለሙዎች ጋር እየተወያየ ሲሆን፥ ተቋማት የሚከፍሉት የሮያሊቲ ክፍያ የገቢ አቅማቸውን መሰረት በማድረግ 24 ሠአት የሙዚቃ ውጤቶችን ይጠቀማሉ ተብሏል።

የሙዚቃ ተጠቃሚዎች በዓመትና በጊዜያዊነት ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉም ተሰምቷል።

ለአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቀረበው ቀመር መሰረት ተቋማቱ በ24 ሠአት ውስጥ 360 እነዲሁም በዓመት ደግሞ 131 ሺህ 400 ሙዚቃዎችን እንደሚያጫውቱ ተመላክቷል።

የሙዚቃ ባለሙያውም በተጫወተለት የሙዚቃ መጠን የሚከፈለው ሲሆን፥ ባለስልጣኑና ሁለቱ ማህበራት በዛሬው ዕለት የሮያሊቲ ክፍያ ቀመርን ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ዘግቧል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋሽን፣ በስነ ዉበት (ሜካፕ)፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ሴኩሪቲ እና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሰልጣኞችን ለማሰልጠን ምዝገባ እንደጀመረ ይፋ አድርጓል።

ዳማሪዮስ ተግባር ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች  የሚሰጥ ሲሆን  ከመስከረም ጀምሮ በLevel 2  ዓለም አቀፍ በሆኑ ባለሙያዎች ስልጠናዎች ይሰጣል ተብሏል በተጨማሪም ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ በተቋሙ አቅም መሰረት የፋይናንስ አገልግሎቶች እንደሚመቻችላቸው ተገልጿል።

አቅም ለሌላቸው ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ እና ከንብ ባንክ ጋር የዱቤ ብድር አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ተፈፅሟል።

በሜካፕ ትምህርት ክፍል ከMario ሜካፕ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ውል መፈፀማቸውን ገልፀው ከቆዳ ስፔሽሊስት ዶክተሮች ጋር በጥምረት አብሮ ለመስራት ውል መፈፀማቸው ተገልጿል።

አሁን ለ20 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን፣ ከRome Business School ጋር ለተማሪዎች የስኮላርሺፕ ስምምነት ተደርጓል።

ተቋሙ ቦሌ ብራስ የሚገኝ ሲሆን በ1200 ካሬ ሜትር ላይ አርፏል፣ 24 ከፍሎች ሲኖሩት፣ ዘጠኝ የመማርያ ከፍሎች፣ አንድ ቤተ መጽሐፍትን ያካተት ተቋም ነው።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ልጄስ" ድራማ ድጋሚ ለእይታ ሊቀርብ ነው

"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል ከሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቃና ቴሌቪዥን መታየት እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው ያመለክታል።

ይህ ተከታታይ ድራማ በሰማኸኝ አይችሉሁም ዳይሬክት የተደረገ ሲሆን አርቲስት ዳንኤል አሸናፊ (ፂሞ) በመሪ ተዋናይነት ተውኖበታል፡፡

እስከ አምስተኛው ክፍል ድረስ በካናል ፕላስ እና በቃና ቲቪ ዩቲዩብ ቻናል እየተላለፈ የቆየው"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል በካናል ፕላስ ሲኒማ ብቻ ሲተላለፈ እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌EBS "አዲስ ምዕራፍ" ፕሮግራም በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሰረት ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ ተወሰነ

“አዲስ ምዕራፍ” የቴሌቪዥን ፕሮግራምን በተመለከተ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ "አዲስ ምዕራፍ" በተሰኘ ፕሮግራሙ እሑድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር በመገምገም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ብሏል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ሪድስ አምስተኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ለዓመታት የልጆች የንባብ ልምድ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሪድስ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው አምስተኛ ጉባኤው ከትላንት መጋቢት 24 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በዝግጅቱ ላይ ከተለያየ ዘርፍ የተወጣጡ ባለሙያዎች ስለ ልጆች ንባብ እና ተያያዥ ሀሳቦች ላይ መነሻ ጥናታዊ ፅሁፎች እያቀረቡ ሲሆን በፅሁፎቹም መነሻነት የሃሳብ ልውውጥ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጉባኤ ላይ የልጆች ንባብ ባህልን ለማሳደግ አስተዋፅኦ ያደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና የመስጠት መርሃግብር ይካሄዳል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ሪድስ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ በሁሉም ክልሎች ከ70 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ቤተመጽሐፍትን በማቋቋም ከመንግስት እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር አብሮ እየሰራም እንደሚገኝ አስታውቋል።

የ22 ዓመታት እድሜ ያስቆጠረው ኢትዮጵያ ሪድስ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች እና ልጆችን ባለፉት ዓመታት በንባብ አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉን ገልጿል።

📸 ተክሌ ማርኮን

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ሁለገቡ ባለሞያ ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ እንግዳ የሆነበት አላቲኖስ የፊልም ውይይት ዛሬ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ "ቀለም እና ሲኒማቶግራፊ"በሚል ርዕስ ውይይት  ያካሂዳል።

በዝግጅቱ ላይ የፊልም ባለሞያዎች ባለቀለም ፊልሞችን መሰራት ከጀመሩ ወዲህ ቀለም የፊልሙን ታሪክ (Story) ለታዳሚው በተሻለ መልኩ ከማስተላለፍ አኳያ የሚጫወተውን ሚና በተመለከተ የቀለም ባለሞያው ኢ/ር ጌታሁን ሔራሞ ሀሳቡን ያጋራል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/08 08:45:49
Back to Top
HTML Embed Code: