📌ተዋናይነት ፀደይ ፋንታሁን በአዘጋጅነት ብቅ ያለበችበት "ጥቁር እንግዳ" ተውኔት ለመድረክ በቃ
በደራሲ ውድነህ ክፍሌ የተደረሰው "ጥቁር እንግዳ" ተውኔት ሐሙስ የካቲት 27 2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ለመድረክ በቅቷል።
በተውኔት ላይ ሱራፌል ተካ፣ደምሴ በየነ፣ፀደይ ፋንታሁና ማርታ ግርማ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።
የ"ጥቁር እንግድ" ተውኔት ዋና አዘጋጅ ዶ/ር ተሻለ አሰፋ ሲሆን ተዋናይነት ፀደይ ፋንታሁን በረ/አዘጋጅነት የመጣችበት ተውኔት ሆኗል።
ተውኔቱ በቋሚነት ዘወትር ሐሙስ በ12:00 በዓለም ሲኒማ ለቴአትር አፍቃሪያን እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌የፍቅር እስከ መቃብር ገፀባህርያት በሥዕል የሚገልጡበት አውደርዕይ ዛሬ እይታ ይበቃል።
በሠዓሊ ምዕራፍ ግሩም የተዘጋጀውና የፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ ገፀባህርያት በሥዕል የሚገለጡበት "የደራሲው ሥዕል" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አውደርዕይ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በሠዓሊ ምዕራፍ ግሩም የተዘጋጀውና የፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ ገፀባህርያት በሥዕል የሚገለጡበት "የደራሲው ሥዕል" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አውደርዕይ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ጎዶን ጥበቃ" ተውኔት ዛሬ በክብር ይሰናበታል
በሳሙኤል ቤኬት ተደርሶ በሀይከል ሙባረክ የተተረጎመውና በዳግም ሲሳይ የተዘጋጀው "ጎዶን ጥበቃ" የተሰኘ ተውኔት ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በክብር ከመድረክ እንደሚሰናበት ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"ጎዶን ጥበቃ"ተውኔት ከነሐሴ 2 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 8 ወራት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለቴአትር አፍቃሪያን ሲቀርብ ቆይቷል።
በተውኔቱ ላይ አልዓዛር አበበ፣ ግሩም አስፋው ፣ዘላለም አለማየሁ፣ሙሉብርሃን በለጠ፣ናሆም ቢኒያም በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

📌የአንዱዓለም ጎሳ ባለቤት ህልፈት
የድምፃዊ አንዷለም ጎሳ ባለቤት ቀነኒ አዱኛ በድንገት ሕይወቷ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ የቀነኒን አሟሟት በተመለከተ ፖሊስ ምርመራ ላይ እንዳለ አሳውቋል ።
ቀነኒ አዱኛ ፤ ከመሞቷ ከ12 ሰዓታት በፊት በቲክቶክ የማኀበራዊ የመገናኛ ድረገጽ ላይ ደስተኛ ሆና በመጨፈር ቪዲዮ ለቃ ነበር ።
ለድምፃዊ አንዷለም ጎሳ፣ ለቤተሰቦቿ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶች ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥልን ።
Via ይድነቃቸው ከበደ

📌ታዋቂው ሙዚቀኛ አቶ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋጭነታቸው የሚታወቁት ሙዚቀኛው አለማየሁ ፋንታ ስራቸውን የጀመሩት ሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት በመቀጠር ነው፤ እዚያም ለ10 ዓመታት ሰርተዋል፡፡
ለ40 ዓመታት ያህል በ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሙዚቀኛው፤ በዕድሜአቸው መጨረሻ ጡረታ ከውጡ በኋላ በዚሁ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ማገልገላቸውን የሙዚቀኛው የቅርብ ሰው ሆኑት ታዋቂው የበገና መምህር መጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ነግረውናል፡፡
ባህላዊዎቹን የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያዎች በገናን በመደርደር፣ ክራርና መሰንቆን አሳምረው በመጫወት ይታወቁ እንደነበር ከመጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ሰምተናል፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ የቀለም ትምህርትን የተማሩ እንዲሁም የድቁና ትምህርትም የነበራቸው ነበሩ፡፡
ሙዚቀኛው ከ6 ወራት በፊት በድንገት ወድቀው እግራቸው በመሰበሩ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትናንትናው እለት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈፀምም ሰምተናል፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ባለ ትዳርና 6 ልጆች አባት ነበሩ፡፡
📌Via ሸገር 102.1

Event Addis Media
Photo
📌ከድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ እጮኛ ቀነኒ አዱኛ ህልፈት ጋር በተያያዘ እስካሁን ያሉ መረጃዎች
የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ እጮኛ ሞትን በተመለከተ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት የት ነበረች? የድምጻዊው ማናጀር ስለልጅቷ ተናግሯል።
በኢንጂነሪንግ ድግሪ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀችው ቀነኒ በሞዴሊንግ በማስታወቂያ ሥራዎች በማኅበራዊ ሚድያ ዝናን አትርፋለች።
በሚቀጥለው ቅዳሜ ልደቷን ለማክበር በሚል ፎቶዎች እየተነሳች እንደነበር ከቅርብ ሰዎቿ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ልጅቱ ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት የት ነበረች?
ልጅቱ ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት ለልደቷ ፎቶ ስትነሳ እንደነበር በወቅቱ ፎቶ ያነሳት የነበረው የወንዴክስ ስቱዲዮ ባለቤት ወንድወሰን ጋሻው ተናግሯል ።
ፎቶግራፈሩም "በፎቶግራፍ ስራዎች ካፈራዋቸው ወዳጆቼ መካከል የቀኝ እጄ የምላት እህቴ ቀነኒ አዱኛ መካሪዬ ጎደኛዬ የክፉ ቀን ወዳጄ ነበረች።
ትላንት መጋቢት 1 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ የልደት ፎቶዎች ሳነሳት ነበር ማታ 1:00 በሰላም ተለያየትን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 2 2017 ዓ.ም ጠዋት ማረፏን አረዱኝ" ብሏል።
በተጨማሪም ትላንትና መጋቢት 1 2017 ዓ.ም አመሻሹን ቀነኒ አዱኛ ከእጮኛዋ ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ ጋር በመዝናኛ ስፍራ አብረው እንዳሳለፉም ከተለያዩ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሣ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግሯል።
"ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።
ቦሌ አራብሳ ከዓመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።
ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።
ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።
ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።
ፖሊስ ምን አለ?
የልጅቱ አሟሟት ምን እንደሆነ የምርመራ ስራ ተሰርቶ እስኪገለጥ ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግሥት ይጠብቅ በሌላ በኩል አንዳንድ ግለሰቦች ተገቢ ካልሆነ ትንታኔ ይታቀቡ ብሏል።
📸ፎቶው ትላንት ለልደቷ የተነሳችው ፎቶ ነበር።
@EventAddis1

📌ሆቴሎችን የጎዳው የአሜሪካ እርዳታ መቋረጥ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ድጋፍ በመቋረጡ በሆቴሎች የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች መቀነሳቸው ተገለጸ።
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በተለያዩ መንገዶች ለአገሮች ሲያደርገው የነበረውን ድጋፍ በማቋረጡ ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሆቴሎች ይካሄዱ የነበሩ ሥልጠናዎች፣ ስብሰባዎችና አጫጭር ዓውደ ጥናቶች መቀነሳቸውን የሆቴል ዘርፍ ተዋናዮች ተናገሩ፡፡
እ.ኤ.አ. በ2024 ብቻ ወደ 38 ቢሊዮን ዶላር በጀት በመላው ዓለም ወጪ ማድረጉ የሚነገርለት ዩኤስኤአይዲ ለኢትዮጵያ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ግዙፍ የተራድኦ ድርጅት መሆኑ ይነገርለታል፡፡
በከተማው ውስጥ ከሚገኙ ሆቴሎች ይህ ድጋፍ በመቋረጡ የገጠማቸውን ችግር በተመለከለተ ሪፖርተር ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የማርኬቲንግ ባለሙያ፣ እ.ኤ.አ. በመጋቢትና በሚያዝያ 2025 ብቻ ለሆቴላቸው ይገባ የነበረ 25,000 ዶላር በፕሮግራሙ መታጠፍ ምክንያት መሰረዙን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ምክንያት የማይገኘውን ገንዘብ ለማካካስ ከዚህ ቀደም ከነበረው የሆቴሉ ዋጋ ባነሰ ገንዘብ የሚመጡ ፕሮግራሞችንና እንግዶችን የመቀበል፣ እንዲሁም በማርኬቲንግ ባለሙያዎች አማካይነት ወደ ድርጅቶችና ተቋማት በመሄድ የማካካሻ እንግዳና የመሳብ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በካዛንቺስ አካባቢ የሚገኝ አንድ የሆቴል አዳራሽ ባለሙያ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ የሆቴሉ አዳራሽ በሳምንት ሦስቴ አንዳንዴም ለአምስት ቀናት በሙሉ ተይዘው የነበረበት ጊዜ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን የሚደረጉ ስብሰባዎች ቁጥር መቀነሱን ገልጸዋል፡፡
Via ሪፓርተር ጋዜጣ (ሲሳይ ሳህሉ)

📌 ‘ናኦታ’ የልጆች መጽሔት ለንባብ በቃች
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአፋን ኦሮሞ ያዘጋጃት ‘ናኦታ’ የልጆች መጽሔት ለንባብ በቅታለች።
‘ናኦታ’ የተሰኘችዉ የልጆች መጽሄት ባለ 40 ገጽ እና ባለ ሙሉ ቀለም ህትመት ያላት ወራዊ መጽሄት ስትሆን፤ ከየካቲት ወር ጀምሮ በገበያ ላይ ትገኛለች፡፡
መጽሔቷ ትዉልዱን በመልካም ስነ ምግባር እና እውቀት ማነጽን ታሳቢ ያደረገች ናት።
በዋናነት በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ባህልና ታሪክ፣ ተፈጥሮ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ጉዳዮች የተካተቱባት ነች።
በዚህም ልጆችን እያዝናናች በስነ መግባር የምታንጽ፣ የንባብ ልምድን የምታዳብር እንዲሁም ልጆችን ከሳይንስና ጋር የምታስተዋዉቅ መጽሄት ተደርጋ የተዘጋጀች ሆናለች።
ከ3 እስከ እና 15 ዓመት የሚገኙ ልጆች የመጽሄቷ ዋና ታላሚ አንባቢያን ናቸዉ።

📌ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣርና እሑድ ይካሄዳል
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር እና ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት በመጪው እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡
‘ቁርዓን - የእውቀትና የሰላም ምንጭ’ በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ የማጣሪያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ቁርዓን በሁሉም መስክ የሰዎችን ሕይወት በቀና መንገድ በመምራት ለማህበረሰብ ከፍታ መሰረት መሆን የቻለ ነው።
በዚህ አግባብ ውድድሩ ይህን የቁርዓን ክብርና ከፍታ ለመግለጥ የተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ውድድሩ ቁርዓንን በልቦናቸው የተሸከሙ ሃፊዝ ወጣቶችን ለማበረታታትና ቀጣይ ተተኪ ትውልዶችን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።
ዋናው ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር እሑድ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ አመልክተዋል፡፡
በዚሁ ቀን በርካታ አማኞች የሚታደሙበት ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሥነ ሥርዓት ‘ከኢፍጣር እስከ ቁርዓን’ በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በሁለቱ ታላላቅ መርሐ ግብሮች ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
©️ FMC

📌የድምጻዊት የማ የሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ
ድምጻዊት የማርያም ቸርነት(የማ) "ስንት ነው?" ለተሰኘው የሙዚቃ ሥራዋ ያስናዳችው የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዩቲዩብ ቻናሏ በኩል ለአድማጮች ደርሷል።
ድምጻዊት ስለዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"የደጋ ሰው አልበም ከተለቀቀ አንድ ዓመት የሆነው ሲሆን በዚህ መካከል በነበሩኝ 70 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የመድረክ ስራዎች እና ዝግጅቶች ምክንያት የቪዲዮ ስራ ሳላቀርብ ቆይቻለሁ።
በቅርቡ በአዲስ አበባ በመድረክ የምንገናኝ ሆኖ ከዚህ አልበም ውስጥ “ስንት ነው? “የተሰኘውን የሙዚቃ ቪዲዮ በየማ (YEMa) YouTube channel ስለተለቀቀ እንድትመለከቱት እና ከወደዳችሁት እንድታጋሩት እጋብዛለሁ" ብላለች።
በዚህ የሙዚቃ ላይ ጎላ ጎህ በግጥም የተሳትፈ ሲሆን በዜማ፣ ቅንብር፣ ቀረፃ እና ድምፅ ውህደት ኢዩኤል መንግስቱ ተሳትፏል።

📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
አርዕስት መረጃዎች:
1.ተወዳጁ "ባቢሎን በሳሎን " ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው።
2.ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ 13 ቀናት በእስር ቤት እንዲቆም ተወሰነበት።
3.ከ30 ዓመታት በላይ እንደወሰደ የተነገረለት የአንጋፋው የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ዘጋቢ ፊልም ተሰርቶ ተጠናቀቀ።
4.አስር ሁለቱ እንግዶች" የተሰኘ ተውኔት የፊታችን እሁድ ለመድረክ ይበቃል።
5."ስሜ ደበላ ታላቁ የግብርና ምርምር ሥርዓት መሪ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/FL6kxm4BGNw?si=mErTv7NAFWzE0nY1
📌መልካም ምሽት

📌"ብስክሌት አዲስ" የተሰኘ ፌስቲቫል ነገ ይካሄዳል
ነፍ ኮምኒኬሽን እና ኤቨንት ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ከወራት በፊት የጀመረውና ዓመቱን ሙሉ የወሩ የመጨረሻ እሁድ የሚካሄደው "ብስክሌት በአዲስ" ወርሀዊ ፌስቲቫል 3ኛው ዙር ነገ እሁድ መጋቢት 07 ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ እስከ 7:00 ድረስ ከ4ኪሎ ቀበና ባለው ጎዳና ይካሄዳል።
የፌስቲቫሉ ዋና ዓላማ የብስክሌት ልምድን መፍጠር በመሆኑ ከውድድር ፍፁም ነፃና ከህፃናት እስከ አዛውንት ድረስ ተሳታፊ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

📌"ባቢሎን በሳሎን"ተውኔት ወደ መድረክ ይመለሳል
በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተስፋዬ ገ/ሐና የተዘጋጀውና በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "ባቢሎን በሳሎን" ተውኔት ከሁለት ዓመት በኃላ ለአጭር ጊዜ ወደ መድረክ ሊመለስ እንደሆነ አርትስ ስፔሻል ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"ባቢሎን በሳሎን" ተውኔትን በአውሮፓ ለሁለተኛ ጊዜ ለማሳየት እንቅስቃሴዎች እንደተጀመሩ የተገለፀ ሲሆን ተውኔቱ ወደ አውሮፓ ከመጓዙ በፊት ለአጭር ጊዜ በዓለም ሲኒማ እንዲታይ ከሲኒማ ቤቱ አስተዳደር ጋር ንግግር እንደተጀመረ እና በቅርቡ በድጋሚ ለመድረክ እንደሚበቃ ውድነህ ክፍሌ ለአርትስ ስፔሻል ተናግሯል።
ተውኔቱ ወደ መድረክ መቼ ይመለሳል የሚለው ጥያቄ የበርካታ ቴአትር አፍቃሪን ጥያቄ እንደሆነ የገለፀው ደራሲው "ባቢሎን በሳሎን" ወደ መድረክ እንዲመለስ "የዓለም ሲኒማ ኃላፊዎችም ያሻነውን ቀን እንደሚሰጡን ቃል ገብተውልናል" ብሏል።
"ባቢሎን በሳሎን" ተውኔት ወደ መድረክ ሲመለስ አርቲስት አለማየሁ ታደሰን ጨምሮ ሁሉም ተዋናዮች እንደሚኖሩም ተገልጿል።
ለ22 ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ሲቀረብ የቆየው "ባቢሎን በሳሎን" ተውኔት ከሁለት ዓመት በፊት ከመድረክ መሰናቱ ይታወሳል።
📌 ArtsSpecial

📌በኩናማ ሙዚቃው የሚታወቀው ኪዳኔ ኃይሌ አረፈ
"ኦማኒንዳ ጉዳ"በተሰኘው የኩናማ ሙዚቃው በበርካቶች ዘንድ የሚታወቀው ድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ የኩናማ ሙዚቃ ኤልያስ መልካ ካቀናበራቸዉ አልበሞች "ብፍቅሪ ሸፊተ" አልበም ውስጥ የሚገኝ ሙዚቃ ነው።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"ኦማኒንዳ ጉዳ"በተሰኘው የኩናማ ሙዚቃው በበርካቶች ዘንድ የሚታወቀው ድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ የኩናማ ሙዚቃ ኤልያስ መልካ ካቀናበራቸዉ አልበሞች "ብፍቅሪ ሸፊተ" አልበም ውስጥ የሚገኝ ሙዚቃ ነው።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ
ኪዳኔ ሃይሌ ፀባየ ሸጋ ቀልድና ጨዋታ አዋቂ፣ በኩናማ ዜማና ግጥም ድርሰት ከፊት የሚቀመጥ፣በተጨማሪም ድምፃዊና ሳክስፎኒስት ነበር።
ቤተሰቦቹን ጥየቃ ሸራሮ በሄደበት በአደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ መጋቢት 06 ቀን 2017 ዓ.ም. ሕይወቱ አልፏል።
ኤልያስ መልካ በቅንብር የተሸለመበትን የኩናምኛ ዘፈን ድርሰትን ግጥሙን የፃፈው፣ ዜማውን የደረሰውና በድምፅ ያቀነቀነው ኪዳኔ ነበር።
ድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ - "ኦማኒንዳ ጉዳ" በተሰኘው የኩናማ ሙዚቃው በበርካቶች ዘንድ ይታወቃል።
የድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ የኩናማ ሙዚቃ ኤልያስ መልካ ካቀናበራቸዉ አልበሞች "ብፍቅሪ ሸፊተ" አልበም ውስጥ የሚገኝ ሙዚቃ ነው።
በ1956 ዓ.ም የተወለደው ኪዳኔ ኃይሌ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።
ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 2:00 ሰዓት ላይ በመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

አንጋፋው አርቲስት መርዓዊ ስጦት አረፈ
አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው መርዓዊ ሥጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ክላርኔት በመጫወት የሚታወቀው አርቲስት መርዓዊ፤ ከሙዚቀኛነቱ ባለፈ በትወና መድረክ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሏል፡፡
አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ቦታ ከሚይዙ አንጋፋ ሙዚቀኞች መካከል አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡
ከ55 ዓመታት በላይ በቆየበት የሙዚቃ ሕይዎቱ፤ በድምጻዊነት፣ በክላርኔትና አልቶ ሳክስ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነት፣ በሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲነት እንዲሁም በአቀናባሪነት እና ሌሎች ተዘርፎች ማገልገሉ ይታወሳል፡፡

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለአጭር ጊዜ ድርጅትዎን በነፃ ያስተዋውቁ!
የእርስዎን ፍላጎት በአንድ ላይ የሚያገናኝ መድረክ!
በርካታ ዘርፎች እና የአገልግሎት ሰጪዎችን ለማግኘት ቀላል መድረክ፣ኪራዮች፣ህጋዊ አገልግሎቶች፣የውበት አገልግሎቶች፣ጉዞ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎችም 🙏
Download now!
App store:
https://apps.apple.com/us/app/meda-app/id6657988238
Google Play:
https://play.google.com/store/apps/details?id=come.meda.app
Instagram:
https://www.instagram.com/medamobileapp?igsh=MzRlODBiNWFlZA==
Telegram:
https://www.tg-me.com/medamobileapp

📌"ኑ ታላቅ እናክብር" የተሰኘ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል
አንጋፋው የሥነጽሑፍ ባለሞያ አስፋው ዳምጤ የሚመሰገንበት "ኑ ታላቅ እናክብር" የተሰኘ ዝግጅት ነገ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ይካሄዳል።
በዝግጅቱ ላይ አንጋፋ ደራሲያን፣ ሠዓሊያን፣የጥበብ ሰዎች ይገኙበታል ተብሏል።
የደራሲ አስፋው ዳምጤን 90ኛ ዓመት የልደት በዓል ለማክበር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተሰናዳው በዚህ ዝግጅት ላይ ልዩና በውድ ዋጋ የታተመ መጽሔት ለጥቂት ሰዎች ብቻ እንደሚታደልም ተነግሯል።