Telegram Web Link
📌"ከራሚ ከራማ" የግጥም መድብል ለንባብ በቃ

በገጣሚ ዳንኤል ወዳጄ የተዘጋጀው ፤ 96 ግጥሞችን  242 ገጽ የያዘው  "ከራሚ ከራማ"   በውስጡ  በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስንኞችን አካቶ  ለንባብ በቅቷል።

ገጣሚው እንደሚለው "ከራሚ "የሚለው ቃል ግዕዝም አማርኛም አንድምታ አለው። "ግዕዙ ወይን ጠጅ ጠማቂ ማለት ሲሆን ፣ አማርኛውም አልፋን ኦሜጋንም ያጠቃለለ ነው"ይለናል።

በመግቢያው በደንብ እንደተጠቀሰውም የገጣሚው ምኞት በሥራው ኦሜጋ መሆን ነው። በተለያዩ ግጥሞቹም ይህ አልፎም የመታወስ ምኞት ተንፀባርቋል።
በሌላ በኩል "ከራማ የሚያጠናግረው ክፉው አውሊያ ሳይሆን ቅኔን ለአበው የሚነግረው መንፈስ ነው"ም ይለናል።

"ከራሚ ከራማ " ሐሙስ ማለትም በ27/06/2017 ዓም በዋልያ መጻሕፍት  ታላላቅ እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅም ገጣሚው አስታውቋል።

መጽሐፉ ጃፋር (ለገሐር)  እና ኤዞፕ(ፒያሳ) መጻሕፍት መደብር ላይ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ዓድዋና ኪነጥበብ" የተሰኘ ውይይት ነገ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበበት ማዕከል 129ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ "ዓድዋ እና ኪነጥበብ" የተሰኘ ልዩ ሙያዊ የውይይት መድረክ ሐሙስ የካቲት 20 2017 ዓ.ም. በ10:00 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እሸቱ ጮሌ አዳራሽ አሰናድቷል።

ውይይቱን ዕውቁ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሽፈራሁ በቀለ ይመሩታል።ሰአሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን (ዓድዋና ሥነጥበብ)፣ትዕግሥት ዓለማየሁ - (ዓድዋና ቴአትር እና ሲኒማ፣ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር) - (ዓድዋና ሥነጽሑፍ) ሰርጸ ፍሬስብሃት - (ዓድዋና ሙዚቃ)በየዘርፋቸው መወያያ ሐሳቦችን ያጋራሉ።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በኢትዮጵያ ዕይታዊ ጥበባት ወዳጆች ማህበር የተሰናዳ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ዕይታዊ ጥበባት ወዳጆች ማህበር የተዘጋጀውና በሠዓሊና ቀራጺ "የሚያጤሰው ጠረጴዛ " የሥነጥበብ ሥራ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የምክክር መርሐግብር እና በሠዓሊ እና የአለ የሥነጥበብ እና ዲዛይን ት/ቤት መስራች የክቡር አለ ፈለገሰላም ህሩይ አንድ መቶኛ ዓመት የልደት በዓል መታሰቢያ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአለ የሥነጥበብ እና ዲዛይን ት/ቤት ውስጥ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ ዕይታዊ ጥበባት ወዳጆች ማህበር በ2007 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ ጀምሮ በዕይታዊ ጥበባት ዘርፎች ላይ ተቆርቋሪ በሆኑ ከተለያየ ሙያ የተውጣጡ የጥበብ ወዳጆች አንድ የጋራ መድረክ እንዲፈጠር ለማስቻል የተመሠረተ ማህበር ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።

የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።

"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።

በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

አርዕስት መረጃዎች:

1.24 ዓመታት በኢትዮጵያ ቆይታ ባደረገ ጃፓናዊ የባህል ጥናት ተመራማሪ የተጻፈ መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ።

2.በዝነኛዋ አርቲስት መስከረም አበራ ፕሮዲዩስ የተደረገ ተውኔት ለመድረክ ሊበቃ ነው።

3.ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ እጩ በመሆን የቀረበበት ትሬስ የሙዚቃ ሽልማት ተካሄደ።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/nMWNd8zY-ls?si=KjgVmy8IQ5luu-Lb

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ሆሊውድ መንደር ተንቀጠቀጠ

ትናንት ምሽት፣ የካቲት 23/ 2017 ዓ.ም የኦስካር ሽልማት በተካሄደባት ሆሊውድ መንደር የርዕደ መሬት ተከስቶ እንደነበር ተዘገቧል።

ርዕደ መሬቱ የተከሰተው የኦስካር ሽልማትን ተከትሎ ታዋቂው ቫኒቲ ፌይር መጽሄት በሚያዘጋጀውና በርካታ ታዋቂ ሰዎች ድግስ ላይ ተሰባስበው በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።

3.9 ሬክተር ስኬል የተመዘገበው ርዕደ መሬት ስላደረሰው ጉዳት የተገለጸ ነገር የለም።

በፊልሙ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የኦስካር ሽልማትን በሆሊውድ ይዘግቡ የነበሩ የቢቢሲ ጋዜጠኞች ድንገተኛው የመሬት ርዕደ መሬት ሲከሰት በስፍራው ላይ የነበሩ ሲሆን፤ በርካቶች በድንጋጤ መጮሃቸውን በዘገባቸው ላይ ጠቅሰዋል።

#Arts

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የገጣሚ ዳንኤል ወዳጄ "ከራሚ ከራማ" የግጥም መጽሐፍ  የፊታችን ሐሙስ ይመረቃል።

የገጣሚ ዳንኤል ወዳጄ "ከራሚ ከራማ " የተሰኘ መጽሐፍ የፊታችን ሐሙስ የካቲት 27 2017 ዓም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በአራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

በገጣሚ ዳንኤል ወዳጄ የተዘጋጀው 96 ግጥሞችን 242 ገጽ የያዘው "ከራሚ ከራማ"  መጽሐፍ በውስጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ይዟል።

ገጣሚው እንደሚለው "ከራሚ "የሚለው ቃል ግዕዝም አማርኛም አንድምታ አለው። "ግዕዙ ወይን ጠጅ ጠማቂ ማለት ሲሆን አማርኛውም አልፋን ኦሜጋንም ያጠቃለለ ነው"ይለናል።

መጽሐፉ ጃፋር (ለገሐር)  እና ኤዞፕ(ፒያሳ) መጻሕፍት መደብር ላይ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ በወዳጆቹ ተሸለመ

የትዝታው ንጉስ ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ለሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ላደረገው አስተዋፅዖ ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት ከወዳጅ እና ቤተሰቦቹ ከልብ የመነጨ አድናቆትን አግኝቷል።

በፕሮግራሙ ላይ ለታዋቂው ድምፃዊ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ለበርካታ አመታት ላበረከቱት ትሩፋት ያላቸውን ጥልቅ አክብሮት እና ምስጋና የሚገልጽ የወርቅ ሃብል ተበርክቶለታል።

ድምፃዊዉ ዘመን እና ጊዜ የማይሽራቸውን ስራዎችን በመስራትየሚታወቀው ማህሙድ አህመድ የሀገሪቱን የባህልና የሙዚቃ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአፍሪካ ወጣቶች ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ወጣቶች በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ያላቸውንተሳትፎ ማሳደግን አላማው ያደረገ የአፍሪካ ወጣቶች ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከተባበሩት መንግስታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ
ዶክተር ራሚዝ አልካባሮቭ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ተመድ የአፍሪካ ወጣቶች ፌስቲቫልን በጋራ ማካሄድ በሚችሉበትሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ፌስቲቫሉ ወጣቶች ሰላም የሰፈነባት አፍሪካን በጋራ ለመገንባት የበኩላቸውን
አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማነሳሳትና የፓን አፍሪካኒዝምን እሳቤ ማጠናከርን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

ኹነቱን ሚኒስቴሩ ከተመድ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትጋር በመተባበር በልዩ ልዩ መርሐግብሮች ለማካሄድ እየሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌“የሕይወት ትውስታዬ” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የኮሎኔል ይልማ መንግስቱ “የሕይወት ትውስታዬ”መጽሐፍ ዛሬ አርብ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል የሚመረቅ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)፣ ደራሲ ገነት አዬለ እና መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ንግግር ያደርጋሉ።በተጨማሪም የሀርመኒክ ባንድ አባላት በቫዮሊን ጣዕመ ዜማ ያሰማሉ።

ከመጽሐፉ ባሻገር የኮሎኔል ይልማ ታሪክ በሦስት ሰዓት በድምጽ ዘጋቢ ፊልም ተሠርቶ በተወዳጅ ሚዲያ ቲዩብ ላይ የሚጫን ሲሆን በዕለቱም የ29 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም በምረቃው ላይ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

የ92 አመቱ ኮሎኔል ይልማ ከልጅነት አንስቶ በሥራ ዓለም ያሳለፉትን አስገራሚ ህይወት በ368 ገጽ አቅርበውታል።

በደርግ መንግስት አስተዳደር ወቅት በሕዝብ ደህንነት መስሪያ ቤት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በሠሩበት ጊዜ ሰዎች ያለአግባብ እስር እንዳይደርስባቸው ብሎም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ በማድረጋቸው ይመሰገኑ የነበሩት ኮሎኔል ይልማ መንግስቱ፥ በመጽሐፋቸው ከፖሊስ ሰራዊት አባልነት ተነስተው ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ድረስ ያሳለፉትን ረጅም የሥራ እና የግል ህይወት ተርከዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" ሰባተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት  ይካሄዳል።

ባለፉት ስድስት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ ስድስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም ገጣሚ ፊርማዬ አለሙ የምትዘከረ ሲሆን ክብርት አስቴር ዘውዴ የዕለቱ ተጋባዥ የክብር እንግዳ በመሆን እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የመጀመሪያው የብራዲያል ኤክስፖ ተዘጋጅ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እንደሆነ የተገለጸው የብራዲያል ኤክስፖ ሊካሄድ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ኤክስፖው መጋቢት 6 እና 7 2017 ዓ.ም በቦናንዛ አዲስ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን በመረኃግብሩም ፋሽን ሾውና የመፀሀፍ ምረቃትን ጨምሮ ከ13 በላይ ዘርፎች ይቀርቡበታል። እንዲሁም ከ40 በላይ ሻጮች ይገኙበታል ተብሏል።

በመርኃግብሩም ድንቅ የፋሽን ትዕይንቶች፣ ምርጥ ዲዛይነሮች የሰርግ ጋውንን፣ የሙሽራ ቀሚሶችን እና የሙሽራ ልብሶችን በማሳየት ዘመናዊና ዘመኑን የዋጁ የሙሽራ ስብስቦችን ይቀርቡበታ፣ የቀጥታ ትዕይንቶችን የኬክ ቅምሻዎችን ፣ የአበባ ዲኮር ዝግጅት ማሳያዎችን ፣የጠረጴዛና ወንበር አቀማመጥ፣ ለይአውቶችን እና የሰርግ መዝናኛ ቅድመ እይታዎችን ይቀርባሉ ተብሏል።

ይህም በአይነቱ ለመጀመሪያ ግዜ ወደር በማይገኝለት ሁኔታ ቅንጦትን ከውበት ጋር አሟልቶ የያዘ እንዲሁም እውቅ የሰርግን ጣጣ ነገር ልቅም አርገው የሚያውቁ የሠርግ እቅድ ባለሞያዎችን በተጨማሪም ለሰርግ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ያሳያል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ጦቢያ ግጥምን በጃዝ በመላው አውሮፓ ከተሞች ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ትዕይንቶችን ሊያቀርብ ነው፡፡

ላለፉት 13 ዓመታት በኪነ - ጥበብ መድረክ ከፍተኛው ዕውቅናን ያተረፈው ጦቢያ ግጥምን በጃዝ “ኢትዮ-አውሮፓ የባህል፣ የኪነ-ጥበብ እና የህዝብ ግንኙነት” በሚል መጠሪያ ልዩ የጥበብ ዝግጅቱን ለማቅረብ እንዲያስችለው መሠረቱን በጀርመን ሀገር ካደረገው ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፑፒልስ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በስምምነቱ ሁለቱም ወገኖች የኢትዮጵያን እና የአውሮፓ የባህል እንዲሁም የስነ ጥበብ ግንኙነት ለማሳደግ ማለማቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ዓላማቸውም የኢትዮጵያውያን እና የአውሮፓውያን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር እንደሆነ የድርጅቶቹ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ገልፀዋል፡፡

የጦቢያ ዋና ስራ አስኪያጅ ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈ እንደገለፁት ኢትዮጲያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያውያን በመድረክ ዝግጅቱ ሲገኙ ከመዝናናት ባለፈ ለተቸገሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦም እያደረጉ እንደሆን እያሰቡ ዝግጅቱን እንዲታደሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፑፒልስ በኢትዮጲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዘውዱ ገዛኸኝ በበኩላቸው በዚህ ስምምነት ዜጎች በእንደዚህ ያሉ የመዝናኛ ሁነቶች ለሀራቸውና ለህዝባቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስቻል ለድርጅቱ ዓላማ መሳካት ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ብለዋል፡፡

ይህን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በሚዲያ አጋርነት አርትስ ቴሌቪዥን የሚሰራ ሲሆን ስምምነቱም በአርትስ ቢሮ ውስጥ ተፈጽሟል፡፡

መረጀው የአርትስ ቴሌቪዥን ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።

የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።

"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።

በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

አርዕስት መረጃዎች:

1. ዝነኛው "አበበ በሶ በላ" አረፍተ ነገር ዘንድሮ ሃምሣ ዓመት ሆነው። ምን ? በዝርዝር እንነግራችኋለን።

2.የፍቅር እስከ መቃብር ገፀባህርያት በሥዕል የሚገልጡበት አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው።

3.አስራ ዘጠኝ ቃልጠየቆች በአንድ የተሰባሰቡበት የጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

4.ተዋናይነት ፀደይ ፋንታሁን በአዘጋጅነት ብቅ ያለበችበት ቴአትር ለመድረክ በቃ።

5.ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት የተነገረው አዲስ ሀገርኛ ፊልም የፊታችን ሰኞ ለእይታ ይበቃል።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/P34DCnMhAsI?si=iXlqG3A0l8Yb_3v7

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ማዕዶት" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በደራሲ ከፈለኝ ዘለለው የተዘጋጀው "ማዕዶት" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ እንቁላል ፋብሪካ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው "ፅጌረዳ አዳራሽ" ውስጥ ይመረቃል።

"ማዕዶት"የደራሲው አምስተኛ መጽሐፍ ሲሆን ከዚህ ቀደም የሻማ ብርሃን፣ አገልፋኖ፣ አሞዛ እና ሐዋዝ የተሰኙ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የበገና ዜማ የህክምና አገልግሎት ላይ እየዋለ ነው

የበገና ዜማ በኢትዮጵያ ለህክምና አገልግሎት  እየዋለ መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የሆነው ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የዜና አውታሩ  ባቀረበው ዘገባ በአዲስ አበባ በሚገኘው ግሬስ ነርሲንግ ሆም የበገና ህክምና እየተሰጠ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡

የ60 አመቱ አቶ ሰለሞን ዳንኤል በዊልቸር የሚንቀሳቀሱ ሲሆን በዚህ ህሙማን ማቆያ ሁለት አመታትን አሳልፈዋል፡፡

የበገናን ዜማ ድምፅ ሲሰሙ ጭንቅላታቸውን እየወዘወዙ መመሰጣቸውን መመልከቱን ዘገባው አስረድቷል፡፡

የበገና ድምፅ ሲሰሙ ሰላም እንደሚሰማቸው የተናገሩት አቶ ሰለሞን ጨምረውም ‹‹እግዚአብሄርን ስትፈልጉት በተለያየ መንገድ ታገኙታላችሁ፡፡ እኔ በገና ስመለከት እግዚአብሄር የሚያናግረኝ መስሎ ይሰማኛል›› ብለዋል፡፡

ከግሬስ ነርሲንግ ሆም መስራቾች አንዱ የሆኑት ዶክተር ናትናኤል ሀይሉ ህሙማኑ በገናን ሲሰሙ በሚያሳዩት ስሜት መገረማቸውን ገልፀዋል፡፡

ህሙማኑ በበገናው ድምፅ በሽታቸውን እንደሚረሱትና እንቅልፍ ውስጥ እንደሚገቡ የጠቆሙት ዶክተር ናትናኤል ጨምረውም ‹‹ህሙማኑ በገና ሲሰሙ የደም ግፊታቸው ይቀንሳል፣ የልብ ምታቸው ይረጋጋል፡፡ ከሌሎች ሙዚቃ መሳሪያዎች በተለየ በገና ትክክለኛ የመረጋጋት ስሜትን ይፈጥራል‹‹ ብለዋል፡፡

በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የልብ ሀኪምና መምህር የሆኑት ዶክተር ቡክማን በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ለማድረግ ሰሞኑን በዚህ ህሙማን ማቆያ መገኘታቸውን የዜና አውታሩ አስረድቷል፡፡

እሳቸውም ሁኔታውን ከተመለከቱ በኋላ የበገና ዜማ በተለይ በፅኑ ህመም ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች መልካም ተፅእኖ የመፍጠር ሀይል እንዳለው መናገራቸውን ገልጿል፡፡

📌መረጀው የዘሐበሻ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን የሥነጥበብ ትርዒት ተጀመረ

69ኛው የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ሸማ የሥዕል አውደርዕይ ፣የፋሽን ትርኢት እና የዕውቅና መርሐግብር ከየካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳፋየር አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ "ጥበብ ለሴቶች" በተሰኘ መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው መርሐግብር በሠዓሊ ራስ በረከት የተሳሉ፣ የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን የባህል ግንኙነቶችን የሚያሳዩ እንዲሁም ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ 40 የሥዕል ስራዎች ቀርበዋል።

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠናከር እና የባህል ቁርኝነትን ለማሳደግ መሰል የኪነጥበብ መርሐግብሮች በተከታታይ መከናወቸው ፋይዳው የጎላ መሆኑን አዘጋጁ ራስ በረከት አንዳርጌ ገልጿል።

በአውደርዕዩ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች፣የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ አርበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የሴቶችን ህይወት ለመለወጥ እና በአርአያነት የሚጠቀሱ ኢትዮጵያውያን እና ደቡብ ሱዳናዊያን እንስቶች እውቅና ተከርክቶላቸዋል።

ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል ለጎብኚዎች ከፍት እንደሚሆን ተገለጿል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ቢክ እስኪብርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊመረት ነው

አልሳም ኃላ/የተ/የግል ቢክ እስኪብሮቶን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ከኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ጋር ዛሬ የካቲት 29 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

አልሳም ከማምረቱ በተጨማሪ የምርቱ ስርጭትም ለምስራቅ አፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ለጅቡቲ፣ ለሶማሊያና ለኤርትራ የሚያከፋፍል ይሆናል።

የቢክ እስክብርቶ በኢትዮጵያ መመረት በአከባቢው ካለው የገበያ ስፋት አንፃር ለአገራችን የቴክኖሎጂ ሽግግር ይፈጥራል፣ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል፣ ለዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

በቀጣይ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የተገለጸው።

አልሳም ኃላ/የተ/የግል ማህበር ከተመሰረተ 25 ዓመታት ያለፉት ሲሆን በአስመጪነት፣ በላኪነት፣ በአገር  ውስጥ ንግድ፣ በሪል ስቴትና በማኑፋክቸሪንግ የሥራ ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ኮንሰርት

ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ(አርዲ) በሀገረ እስራኤል የመጀመሪያ የሙዚቃ ኮንሰርቱን በቅርቡ እንደሚያካሂድ ይፋ አድርጓል።

አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) ከዚህ ቀደም "እናትዋ ጎንደር" እና "ካሲናው ጎጃም" በተሰኙ ሙዚቃዎች ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቷል።

በተጨማሪም ባሳለፍነው ዓመት ጥር ወር በለቀቀው "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነትን አትርፏል።

ድምጻዊው ከ2 ወራት በፊት ያወጣው "አሞራው ካሞራው" የተሰኘውና በጀግናው አሞራው ውብነህ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የሠራው ነጠላ ዜማው በዩቲዩብ ከ7 ሚሊዮን በላይ ተመልካች እንዳስገኘለት ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌 ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ተዘከረ

ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የተዘከረበት" የካቲት ወርሐ ገብረክርስቶስ "የተሰኘ ልዩ መርሐግብር ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በስሙ በተሰየመው ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ውስጥ እንደተካሄደ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዕለቱም የገብረክርስቶስ ግጥሞችና ስለእሱ የተገጠሙ ግጥሞች ተነበዋል።በተጨማሪም ገብረክርስቶስን በሕይወቱ የመጨረሻዎቹ ቀናት ያገኙ ሰው በቪዲዮ ምስክርነት ሰጥተዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን ሐሙስ ይካሄዳል

መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት ላይ አንጋፋው የተውኔት አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/09 00:14:02
Back to Top
HTML Embed Code: