Telegram Web Link
📌 አምፊ የጥበብ ዝግጅት "በአንድ ቲኬት ህይወት እናድን" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ልዩ ፕሮግራም ቅዳሜ ይካሄዳል።

አዳማ ዩኒቨርሲቲ የስነጽሑፍ እና ትያትር ክበብ እና አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ታዋቂ የጥበብ ሰዎች የሚዘጋጅ "አምፊ ጥበባት" የተሰኘ የጥበብ ፕሮግራም ቅዳሜ የካቲት 15 ከ 9፥00 -11:30 አዲስ አበባ ከቦሌ ወደ 22 በሚወስደው መንገድ 24 ባለው መሶብ የባህል አዳራሽ  ተመርቆ ይጀመራል።

በዚህ ፕሮግራም ግጥሞች፣ ቀልዶች፣ ሙዚቃ እና ድራማ የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህን ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው፣ ከዚህ ፕሮግራም የሚገኘው ገቢ በካንሰር በሽታ እየተሰቃዩ ለሚገኙ አንድ የክበባችን አባል እናት ማሳከምያነት የሚውል ነው።

በዕለቱ መገኘት ብንችልም ባንችልም የቲኬቱ ዋጋ 250 ብር ብቻ ስለሆነ አንድ ቲኬት በመግዛት መተባበር መልካም ነው።  ለመመዝገብ  https://forms.gle/niyxbMBzW7qcZBWm8
"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ የፊታችን አርብ ይመረቃል

በደራሲ ኤደን ሀብታሙ የተዘጋጀው "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በመጪው አርብ የካቲት 14 ቀን 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

"ማለዳ ደጃፍ ላይ" የድህረ ዘመናዊ ልቦለድ (post modernism writing style) የአጻጻፍ ቅርጽ የያዘ፣ በ277 ገጾች የተቀነበበ መጽሀፍ ሲሆን በቅርጹም ሆነ በአቀራረቡ ለየት ያለ መልክ ይዞ ለመምጣት የሞከረ የልቦለድ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በ13 ምዕራፎች (በ13 ወራት በተወከሉ) በሥነቃል እና በሥነሥዕል የተሰነደ የልቦለድ ስራ ነው። አስራ ሶስቱ ታሪኮች ለብቻቸውም ሆነ አንድ ላይ በህብረት መቀናጀት የሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አንኳር ገጸባህርያትን አቅፎ የያዘ ነው።  

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በይዘቱ ከማህበራዊ፣ ጥበባዊ እና አሁናዊ (current affairs)፣ስነልቦናዊ እና ሰዋዊ (humanistic) ጉዳዮችን በጥልቅ የሚዳስስ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” አርብ የካቲት 14፣ ከቀኑ 10፡00 ሰአት ላይ የተለያዪ የክብር እንግዶች፣ የጥበብ ባለሞያዎች እና የመጽሐፍ አፍቃሪያን በተገኙበት በዋልያ መጽሐፍ መደብር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን ዛሬ ይካሄዳል

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር ለሁለት ዓመታት የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ክብረ በዓል ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አላቲኖስ የፊልም ውይይት ዛሬ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ የቀይ ካርድ ፊልም ላይ ውይይት ያካሄዳል።

በዕለቱም የቀይ ካርድ ፊልም አዘጋጅ የአብሥራ ዶጮ በክብር እንግድነት ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ’ መጽሐፍ ሦስተኛ ክፍል የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል

በጋዜጠኛ ገነት አየለ የተዘጋጀውና ‘በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታ’ የተሰኘው መጽሐፍ ሦስተኛ ክፍል የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በዋልያ መጻሕፍት ይመረቃል።

የፈረንሳይ ተወላጅ የሆነው አርኖ ሚሼል ዳባዲ ከወንድሙ ጋር ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ ያየውን፣ የተመለከተና የሰማውን ያኖረበት ይህ መጽሐፍ፥ በዋናነት በዘመነ መሳፍንት የነበረችውን ኢትዮጵያ የሚያመላክት ነው። ከዛም አልፎ መልክዓምድሩንና በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ባህል፣ ስርዓት፣ መልክ፣ ወግና ሥርዓት፣ አለባበስንም ጭምር በማራኪ ትረካ የሚያስቃኝ ነው። ይህን መጽሀፍ ለገነት ያሳተመላት ዋልያ መጽሀፍት ሲሆን ድርጅቱ በርካታ ድርሰቶች ለህትመት ማድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡

ገነት ይህን መጽሐፍ ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ በመመለስ የመጀመሪያውን እትም በ2009 ዓ.ም ለንባብ አብቅታለች። በ2013 ዓ.ም ደግሞ ኹለተኛውን ክፍል ለተደራስያን ያደረሰች ሲሆን፥ መጽሐፉ አራት ክፍሎች ያሉት መሆኑን ጠቅሳ፥ አራተኛውና የመጨረሻው የመጽሐፉ ክፍል መተርጎም መጀመሯን አሳውቃለች።

በዚህ የምርቃት መርሀ ግብር ላይ ደራሲ አበራ ለማ፣የታሪክ ባለሙያ ዶክተር ዘካርያስ አምደብርሀን ፣የፍልስፍናው ሰው ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ እና ዶክተር አውግቸው አማረ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።

ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ተርጓሚ ገነት አየለ ከዚህ ቀደመ ‘የመንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች’ እንዲሁም ‘ትንሿ ሀገር’ የተሰኙ መጽሐፎችንም ለአንባብያን አድርሳለች።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"የብሌን አንዳች" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በጋዜጠኛ እና ደራሲ ዋለልኝ አየለ የተዘጋጀው "የብሌን አንዳች" የተሰኘ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለአንባቢያን እንደቀረበ ከደራሲው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በ240 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ 24 ርዕስ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል በ400 ብር የጀርባ ዋጋም ለአንባቢያን ቀርቧል።

ሁለት ጋዜጠኞችን እና አንድ የራሱን ነፃ ሕይወት የሚከተል ፍስሐ የሚባል ወጣት ዐቢይ ገጸ ባህሪያት ያደረገው ‹‹የብሌን አንዳች›› መጽሐፍ፤ በተለይም በፍስሐ በኩል የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ይሞግታል፡፡ በሁለቱ ጋዜጠኞች በኩል ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና የፍቅር ጉዳዮችን ያስቃኘናል፡፡ አረቄ ቤትም ካፌም በመገኘት ያስተዋላቸውን ነገሮች፣ የሰዎችን የሕይወት ገጠመኞች ያስቃኛል።

የደራሲ ዋለልኝ አየለ የመጀመሪያ ሥራ የሆነው ይህ መጽሐፍ በጃዕፋር መጽሐፍት (ሜክሲኮ) በኤዞፕ መጽሐፍት መደብር (ፒያሳ) ይገኛል፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በእይታ ላይ የሚገኝ የሥዕል አውደርዕይ !

ሠዓሊ ትዕማር ተገኝ እና ሠዓሊ ፈትለወርቅ ታደሰን “Question & Assured Existence “ በሚል ርዕስ ያዘጋጁት የሥዕል ዓውደ ርዕይ ከየካቲት 10 ቀን 2017 ጀምሮ በገብረ-ክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ሙዚየም በእይታ ላይ ይገኛል።

በዚህ ሳምንት የተከፈተው የሥዕል ዓውደ ርዕይ ከሰኞ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም  እስከ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል::

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

በደራሲ ኤደን ሀብታሙ የተዘጋጀው "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ አርብ የካቲት 14 ቀን 2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

"ማለዳ ደጃፍ ላይ" የድህረ ዘመናዊ ልቦለድ (post modernism writing style) የአጻጻፍ ቅርጽ የያዘ፣ በ277 ገጾች የተቀነበበ መጽሀፍ ሲሆን በቅርጹም ሆነ በአቀራረቡ ለየት ያለ መልክ ይዞ ለመምጣት የሞከረ የልቦለድ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በ13 ምዕራፎች (በ13 ወራት በተወከሉ) በሥነቃል እና በሥነሥዕል የተሰነደ የልቦለድ ስራ ነው። አስራ ሶስቱ ታሪኮች ለብቻቸውም ሆነ አንድ ላይ በህብረት መቀናጀት የሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አንኳር ገጸባህርያትን አቅፎ የያዘ ነው።  

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በይዘቱ ከማህበራዊ፣ ጥበባዊ እና አሁናዊ (current affairs)፣ስነልቦናዊ እና ሰዋዊ (humanistic) ጉዳዮችን በጥልቅ የሚዳስስ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” አርብ የካቲት 14፣ ከቀኑ 10፡00 ሰአት ላይ የተለያዪ የክብር እንግዶች፣ የጥበብ ባለሞያዎች እና የመጽሐፍ አፍቃሪያን በተገኙበት በዋልያ መጽሐፍ መደብር ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።

የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።

"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።

በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

አርዕስት መረጃዎች:

1."እንጦጦ  ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ወደ ቀድሞ ሰሙ  "ተፈሪ መኮንን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተብሎ ተመልሷል ።

2.በ13 ወራት የተወከሉ 13 ታሪኮችን የያዘው የደራሲ ኤደን ሀብታሙ "ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

3."በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ"  መጽሐፍ ሶስተኛ ክፍል ነገ ይመረቃል።

4.ከፍተኛ ውጪ እንደወጣበት የተነገረውና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተዘጋጀው "አባ መልካ" ፊልም እይታ ሊበቃ ነው።

5."የ1966 ሕዝባዊ አብዮት እና መኢሶን አንዳንድ ማስታወሻ" የተሰኘ መጽሐፍ ላይ እሁድ ውይይት ይካሄዳል።

6.ዓለምአቀፉ የሬጌ አቀንቃኝ አልቦሮሲ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዝግጅቱን ሊያቀርብ ነው።


"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/g7fKBrVde34?si=cj0ncJ24szpqAWFz

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ተመረቀ

በደራሲ ኤደን ሀብታሙ የተዘጋጀው "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አርብ የካቲት 14 ቀን 2017 አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

በመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ በሕይወት እምሻው እና እሱባለው አበራ የመጽሐፍ ዳሰሳ የቀረበ ሲሆን አዜብ ወርቁ፣ ቸርነት ወ/ገብርኤል፣ ግሩም ተበጀ እና በሁሉም አለበል ከመጽሐፉ የውስጥ ገጾች ለታዳሚያን አንብበዋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የደራሲ ኤደን ሀብታሙ የአስረኛ ክፍል የአማርኛ መምህሯ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። መጽሐፉንም በክብር መርቀዋል።

"ማለዳ ደጃፍ ላይ" የድህረ ዘመናዊ ልቦለድ የአጻጻፍ ቅርጽ የያዘ፣ በ277 ገጾች የተቀነበበ መጽሀፍ ሲሆን በቅርጹም ሆነ በአቀራረቡ ለየት ያለ መልክ ይዞ ለመምጣት የሞከረ የልቦለድ ስራ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በ13 ምዕራፎች (በ13 ወራት በተወከሉ) በሥነቃል እና በሥነሥዕል የተሰነደ የልቦለድ ስራ ነው። አስራ ሶስቱ ታሪኮች ለብቻቸውም ሆነ አንድ ላይ በህብረት መቀናጀት የሚችሉ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አንኳር ገጸባህርያትን አቅፎ የያዘ ነው።

“ማለዳ ደጃፍ ላይ” በይዘቱ ከማህበራዊ፣ ጥበባዊ እና አሁናዊ ፣ስነልቦናዊ እና ሰዋዊ ጉዳዮችን በጥልቅ የሚዳስስ ስራ ነው።
📌 "ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተባለ

ሚያዝያ 19 1917 ዓ.ም ተመርቆ የተከፈተውና በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ሥልጠና ታሪክ ቀደምት ሥፍራ ካላቸው ተቋማት ውስጥ የሚመደበው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ስሙ ወደ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቀይሮ ሲጠራበት ቆይቷል።

እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመስራቹና በቀድሞ ስያሜው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ስም ድጋሚ እንዲሰይም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እንደነበር ተነግሯል።

"እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ"ስያሜ የተቋሙን ታሪክና ቦታ የማይወክል በመሆኑና ዘንድሮ የሚከበረውን የትምህርት ቤቱን መቶኛ ዓመት አስመልክቶ ስያሜውን በዚህ ሳምንት ወደ"ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተብሎ እንዲመለስ እንደተደረገ አርትስ ስፔሻል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ትምህርት ቤቱ ባስቆጠረው አንድ መቶ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች በማስተማርና በማሠልጠንም፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች ለነበሯት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ጉዳዮች ምላሽ የሚሰጡ ባለሙያዎችንም ያፈራ ነው፡፡

በናትናኤል ደበና

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌“አባ መልካ” የተሰኘ ፊልም ተመረቀ

በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጀው “አባ መልካ” የተሰኘ ፊልም በብሔራዊ ቴአትር አዳራሸ ለምርቃት በቃ፡፡

ፊልሙ የተመረቀው ታዋቂ አርቲስቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የፊልም አፍቃሪዎች በተገኙበት ነው።

"አባ መልካ" ፊልም በከፍተኛ ጥራት በአባለታ የትወና ማዕከል ሰልጣኞች ተሳትፎ የተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

ፊልሙ በኦሮሞ ፊልም ኢንዱስትሪ እና በፊልም እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳለውም ተገልጿል።

የፊልሙ ይዘት በኦሮሞ ህዝብ እውቀት፣ ባህልና ወግ ላይ ያተኮረ ነውም ተብሏል።

በ"አባ መልካ" ፊልም ከ100 በላይ ባለሙያዎች መሳተፋቸውም ተገልጿል።

መረጃው የFMC ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌መቅደስ ደበሳይ እና ኢቢኤስ ቲቪ ተለያዩ

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ በመሆን ስትሰራ የቆየችውና ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ድንገት የጠፋችው መቅደስ ደበሳይ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የነበራት ቆይታ ማብቃቱን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአቅራቢዋ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መቅድስ ደበሳይ በራሷ ሚዲያ ለመምጣት ማሰቧንም ሰምተናል:

ዝርዝሩን በድምጻችን ይስሙ:

https://vm.tiktok.com/ZMkTxNXG4/
📌ድምጻዊው አብዱ ኪያር "ፈተናው እየበዛብኝ ነው ሁላችሁም በፆማችሁ እና በፀሎታችሁ አስታውሱኝ" ሲል መልዕክቱን አስተላለፈ።

ድምጻዊው አብዱ ኪያር ከቀናት በፊት ሊፍት ውስጥ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ጉዳት እንደደረሰበትና ህክምና ሲደረግለት እንደቆየ መገለጹ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ወላጅ እናቱን በሞት እንዳጣቸው በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ዝርዝሩን በድምጻችን ይሰሙ:

https://vm.tiktok.com/ZMkTQykvA/
📌ድምፃዊ ታሪኩ ጋንጋሲ ወይንም ዲሽታ ጊና የሰላም አምባሳደር በሚል እውቅና ተሰጠው፡፡

ይህንን እውቅና የሰጠው የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ነው፡፡ ሽልማቱን ለመቀበል ትላንት ወደመቀሌ የተጓዘው ድምፃዊ ታሪኩ ከአውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገለት ሰምተናል፡፡

በዛሬው እለት የክብር ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት ካባ እንዲለብስ የተደረገ ሲሆን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊው ዶክተር አፅብሀ ገብረ እግዚአብሄር ‹‹በትግራይ ላይ ጦርነት ሲታወጅ በአደባባይ ሰላምን የሰበከ ነው›› በሚል አወድሰውታል፡፡

የሰላም አምባሳደር በሚል እውቅናና ሽልማት ካበረከቱለት በኋላም የሰላም ተቆርቋሪነቱን እንዲቀጥል አሳስበውታል፡፡ በዛሬው ዝግጅት ላይ ቢሮው ከድምፃዊው በተጨማሪም አምባሳደር መንገሻ ረዳን የራያን ባህል በማስተዋወቅ ላደረጉት አስተዋፅኦ በሚል የክብር ሽልማትና የአንድ መቶ ሺ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡

መረጃ የ ዘሀበሻ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ሙዚቀኛ ዳዊት ቸርነት በማዕረግ ተመረቀ

የፓስተር ቸርነት በላይ(ቸሬ) የኩር ልጅ የሆነው ሙዚቀኛ ዳዊት ቸርነት ከሰሞኑ በማዕረግ ተመርቋል።

ፓስተር ቸሬ ስለልጁ "እንኳን እግዚአብሔር ረዳ የበኩር ልጄ ዳዊት ቸርነት(ዴቮ) ሁልጊዜም እኔ አባትህ በአንተ እንደኮራው እና እንደተማመንኩኝ ነው። ይህው ዛሬም
አመሰግናለው"ብሏል።

ድምጻዊ ዳዊት ቸርነት "ህይወት" ሰው ክፍል ሁለት " የተሰኘና ከዚህ ቀደም "ሰው" ክፍል አንድ ሞት" የተሰኘ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/09 18:57:28
Back to Top
HTML Embed Code: