📌አስደሳች ጉዞ ወደ ወንጪ:
Camping 🏕️ Trip To Wenchi Crater lake
ጉዞ ወደ ተወዳጁ እና የአለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር : ወንጪ : የካቲት 1እና 2/ 2017
It’s time to spend your weekends embarking on an unforgettable camping trip to Wenchi crater lake ! Explore the stunning natural beauty and live the adventure with 👉🏾 @dembeltours
Date 📅): February 8 & 9 2025
Duration(⏱): 2 days & 1 night
Departure: Mexico, Wabi Shebelle Hotel
6:00 AM @ 12:00 LT
Price(💵): 5900 ETB For Locals
Package includes
🚎 ትራንስፖርት / Transport
🥪ቁርስ / Breakfast /X2/
🍔 ምሳ / Lunch / X2 /
🥩 እራት / barbecue 🍖
🥤የታሸገ ውሃ / Bottled Water
🎫የመግቢያ ዋጋ / Entrance
🗺 የአስጎብኚ / Local Guide
🏖 ዋና / Swimming
🏕 የምሽት እሳት ዳር ጨዋታCampfire 🔥
🌊የተፈጥሮ ፍል ውሀ / Hot Spring Water & bath
⛺️ ማደሪያ ድንኳን (Tent)
📷 ፎቶግራፍ /🌅 Photograph
For more info call 📞 0919874598
@dembeltours

📌አላቲኖስ የፊልም ውይይት ዛሬ ይካሄዳል።
አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ያካሄዳል።በዕለቱም በበርካታ ፊልሞች ላይ በድምፅ ባለሞያነት የተሳተፈው ሐብታሙ አዲስ በእንግዳነት ይቀርባል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌"የጉድ ሰፈር" ተውኔት በቢሾፍቱ ከተማ
በወሰን ግዛው ተደርሶ በአማኑኤል ክፍሌ የተዘጋጀው"የጉድ ሰፈር" ተውኔት በቢሾፍቱ ከተማ የፊታችን እሁድ ለእይታ ይቀርባል ተብሏል።
በይሳኮሮ ኪነጥበባት ተቋም ተዘጋጅቶ የቀረበው "የጉድ ሰፈር" ተውኔት የፊታችን እሁድ የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው በእታለም ሲኒማ ለተመልካች እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ አስታውቋል።

📌"ዓይነ ርግብ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
በደራሲ ትዕግሥት ሳሙኤል የተዘጋጀው "ዓይነ ርግብ" መጽሐፍ ነገ አርብ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በወመዘክር (ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ)ውስጥ ይመረቃል።
በዕለቱም ልዩ ልዩ ኪነጥበባዊና የትውውቅ መርሐግብሮች እንደሚኖሩ አዘጋጆቹ አስታውቋል።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ዋዋጎ
ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍የሕይወት ታሪክ
ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌የሌሊሳ ግርማ አዲስ ዛሬ ለንባብ ይበቃል።
የደራሲ ሌሊሳ ግርማ “በታችም በምድር” የተሰኘው ወጥ የልቦለድ መፅሐፍ በዛሬው ዕለት በንባብ ይበቃል ተብሏል።
በተለያዩ መጣጥፎችና አጭር ልብ ወለድ ጽሁፎች በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሌሊሳ ግርማ፤ አሁን ደግሞ በመጀመሪያ የወጥ ልቦለድ ድርሰት መጥቻለሁ እያለ ነው፡፡
ደራሲ ሌሊሳ ግርማ፤ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በሚያቀርባቸው ጥበባዊ መጣጥፎቹም ይታወቃል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም “የንፋስ ህልም እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች”፣ “አፍሮ ጋዳ”፣ “መሬት - አየር - ሰማይ”፣ “የሰከረ እውነታ”፣ “እስቲ ሙዚቃ”፣ “ነፀብራቅ”፣ “ይመስላል ዘላለም”፣ የሚሰኙ የመጣጥፍና የአጭር ልብ ወለድ ስብስብ መድበሎችን ለአንባቢያን ማበርከቱ ይታወሳል፡፡
የመጽሐፉ አሳታሚ ዋሊያ መፅሐፍት ድርጅት ሲሆን፤ መጽሐፉ ከዛሬ ጀምሮ በከተማዋ በሚገኙ መጻሕፍት ቤቶች ሁሉ ለገበያ እንደሚውል ታውቋል ሲል አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘግቧል።

📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።
የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።
"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።
በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:
አርዕስት:
1.የድምጻዊ ዮሐና "ታማ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃ መነጋገሪያ ሆነ።
2.ዓመታዊው አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ።
3.የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ለአንድ ወር በኢትዮጵያ ሊዘክር ነው።
4.የአውሮፓ ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
5. የዝነኛው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) ያልተጠበቀ የመድረክ ሥራ ዓለምን እያነጋገረ ነው።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ: https://youtu.be/A1NyEwkdI_4?si=i2A4hF20mlJjeDHX
📌መልካም ምሽት

📌"ነገረ መጻሕፍት" ዛሬ ይካሄዳል
በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 1 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዚህ መሰናዶ ላይ አምሳሉ መሐሪ እና ቤተማርያም ተሾመ ተጋባዥ እንግዶች ናቸው።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

📌"ከራሚ ከራማ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።
በወጣቱ ገጣሚ ዳንኤል ወዳጄ የተጻፈው "ከራሚ ከራማ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚቀረብ ገጣሚው ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ አስታውቋል።
የመጽሐፍ ርዕስ የሆነው "ከራሚ ከራማ" ሲተርጉም "ከራሚ"በግዕዝ ወይን ጠጅ ጠማቂ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል"ከራሚ" ማለት የሚኖር የኖረ የተሻገረ የከረመ"ማለት እንደሆነም ገለጿል።

📌የሬጌው ድምፃዊ ራስ ብሩክ ሦስት አዳዲስ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለቀቀ
ኢትዮጵያዊው የሬጌ አርቲስት ራስ ብሩክ ፀሀይ ወይም “ራስ ባርኪ” ሦስት አዳዲስ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለቋል፡፡
እነዚህ የሙዚቃ ስራዎች በዳንስሆል እና ሬጌ ስልት የተሠሩ ሲሁኑ “ልስልስ ያለች”፣ “ይቅናህ” እና “አፍሪካን ፓርቲ” የሚሉ ርዕሶችን ይዘዋል፡፡
ራስ ብሩክ ከዚህ ቀደም በርካታ ሙዚቃዎችን ያስደመጠ ሲሆን በተለይ ከ10 ዓመት በፊት የለቀቀው “ብዙ ወሬ” የተሰኘው ዘፈኑ ተወዳጅነትን አትርፎለታል፡፡
በተጨማሪም ከተለያዩ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የሬጌ አርቲስቶች ጋር በመጣመር ሥራዎቹን አቅርቧል፡፡ ራስ ብሩክ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለረዥም ጊዜያት የሬጌ ሙዚቃ ፕሮግራም አቅራቢ ሆኖም ሰርቷል፡፡
የአዳዲሶቹ ሦስት ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ በራሱ በድምፃዊው ራስ ብሩክ የተሠሩ ሲሆን “ይቅናህ” የተሰኘው ዘፈን ቪዲዮ ዩጋንዳ ውስጥ ቀረፃው ተከናውኗል፡፡ “አፍሪካን ፓርቲ” የተሰኘው ሙዚቃ ላይ ደግሞ ሦስት ዝነኛ ዩጋንዳዊያን አርቲስቶች ተሳትፈዋል፡፡ ዘፈኖቹ በአርቲስቱ የዩቲዩብ ገፅ (Ras Biruk Tsehay) ላይ ተለቀዋል፡፡
https://www.youtube.com/@RasBirukTsehay_BarkyOfficial/videos

📌የሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ የስንብትና የመታሰቢያ ሥነሥርዓት ተካሄደ
የሙዚቃ ባለሙያው የተፈሪ አሰፋ የስንብትና የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ባሳለፍነው የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ተካሄደ።
በዚህ መርሐግብር ላይ ወ\ሮ መልካም ሰው አበበ የተፈሪ አሰፋ አጭር የህይወት ታሪክ ያነበቡ ሲሆን ህይወቱን እና ስራዎቹን የሚያሳይ አጭር ቪድዮም ለእይታ ቀርቧል።
ለሙዚቃ መምህር እና ተመራማሪ ተፈሪ አሰፋ በተዘጋጀው የስንብትና የመታሰቢያ መርሐግብር ላይ የባለቤቱ የአርቲስት አብነት አስናቀ እና የሁለት ልጆቹ የአማኑ ተፈሪ እና የረድኤት ተፈሪ መልዕክት በአቶ ያፌት ተክሌ ከተላለፈ በኋላ በአቶ አብይ ጥላሁን ግጥም ቀርቧል።
እህትና ወንድሞቹ ግርማቸው አሰፋ ፣ ሰዋሰው አሰፋ ፣ እስክንድር አሰፋ ፣ ህሩይ አሰፋ ፣ ናኦድ አሰፋ እና ቅድስት አሰፋ ስለሙዚቀኛ ወንድማቸው ስለልጅነቱና አስተዳደጋቸው ተናግረዋል።
አባ ላዕከ ማሪያም አባታዊ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ አቶ ምስጋናው ሙላት ፣ አቶ ክብሮም ብርሃኔ እና አቶ ኪሩቤል አሰፋ ከተፈሪ እሰፋ ጋር ስለነበራቸው ወዳጅነት እና ስለሙያዊ አብርክቶው ተናግረዋል።
የስመ ብዙው የሙዚቃ ሰው የተፈሪ እሰፋ አስክሬን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በብሔራዊ ቴያትር የመታሰቢያ እና የክብር ሽኝት ከተደረገለት በኋላ በቅድስት ስሥላሴ ካቴድራል የቀብር ስነ ስረዓቱ ይፈፀማል።
ሚያዚያ 15 ቀን 1964 ዓ.ም ከአባቱ አቶ አሰፋ ፀጋዬ እና ከእናቱ ወ\ሮ መንበረ ተሰማ በአዲስ አበባ ከተማ የተወለደው ሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ ህክምናውን ሲከታተል በነበረበት ሎስ አንጀለስ ከተማ በተወለደ በ52 ዓመቱ ዕረቡ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ማረፉ ይታወሳል።
©️ሚካኤል አለማየሁ

📌ዛሬ ዓለም አቀፍ የሬድዮ ቀን ነው
በዓለም ዙሪያ ከ44 ሺህ በላይ ሬዲዮ ጣቢያዎች በየዕለቱ መረጃዎችን ለዓለም ህዝብ ያደርሳሉ።
📌ከ5 ቢሊየን በላይ የሚሆኑ የዓለማችን ህዝቦች የሬዲዮ አድማጮች መሆናቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
📌 የዓለም ራዲዮ ቀን እንዲከበር በስፔን የራዲዮ አካዳሚ አነሳሽነት ጥያቄው በፈረንጆቹ በ2010 ለ(UNESCO) የስራ አመራር ከቀረበ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ጉዳዩን ተቀብሎ ዓለም አቀፍ የራዲዮ ቀን በየዓመቱ የካቲት 13(በኛ የካቲት 6) እንዲከበር ወስኗል።
📌ከ152 ዓመታት በፊት እንደተፈጠር የሚነገርለት ሬድዮ ከ100 ዓመታት በላይ ሰዎች በየዕለቱ በስራ ቦታቸው፣ በትራንስፖርት ላይ እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ያደምጡታል።
📌በሀገራችን የመጀመሪያው ሬድዮ የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስርጭት ላይ የሚገኙ ከ50 በላይ የሬዲዮ ጣቢያዎች አሉ፡፡
📌የመጀመሪያው ኤፍ.ኤም የሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ.ኤም 97.1 ነው። የመጀመሪያው የግል የሬዲዮ ጣቢያ ሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 ነው።
📌የካቲት 23 1997 ስርጭቱን የጀመረው የደቡብ ድምፅ ኤፍ ኤም 100.9 ሬድዮ ዘንድሮ 20 ዓመት ይሞላዋል።
📌ሸገር 102.1፣ ፋና ኤፍ ኤም 98.1፣ ዛሚ (የአሁኑ አዋሽ)፣ ብስራት 101.1፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8፣አሐዱ 94.3፣ አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 እና ሌሎችም በስርጭት የሚገኙ የከተማችን ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያዎች ናቸው።
📌የኢኮኖሚና ዋልታ ቡና ቡና፣ ፀሐዬ ደመቀች፣ የተስፋዬ ገብሬ ስፖርት ለጤንነት ፣የአሸናፊ ከበደ እረኛው ባለዋሽንት ክላሲካል ፣ የኢትዮጵያን እንቃኝ የኪሮስ ኃይለስላሴ ድምፅ፣የአይሬ አሆይ፣ የዘፈን ምርጫ ኢንትሮ እና ሌሎችም የማይረሱ የሬድዮ የሙዚቃ ድምፆች ናቸው።

📌የጠርሲዳ ከበደ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው።
በደራሲ ጠርሲዳ ከበደ የተዘጋጀው "ውሃዬን ሽጬ ኮዳ የገዛኹለት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ በይፋ ተመርቆ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።
መጽሐፉም በርካታ ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ይመረቃል።
በዕለቱም አርቲስት ተስፉ ብርሃኔ፣ አርቲስት ዋሲሁን በላይ ፣ ድምጻዊ አንተነህ ምናሉ፣ ገጣሚ ሒክማ ፋንቱ እና ሌሎችም በመድረኩ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

📌 ዋርካ ሬድዮ ወደ ስርጭት ሊመለስ ነው።
የዋርካ ሬዲዮ 104.1 ድጋሚ ወደ ሙከራ ስርጭት ተመልሶ በቅርቡ መደበኛ ፕሮግራሞችን ለመጀመር እንዳሰበ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከሬድዮ ባለቤቶቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮ ዋርካ የጠቅላላ ጉባኤውን መደበኛና ድንገተኛ ስብሰባዎቹን በጊዮን ሆቴል አካሂዶ ዋና ውሳኔዎቹን በቃለ ጉባኤ ማፀደቁን ተከትሎ የተለያዩ ለመጪ ጉዞው ወሳኝ የሆኑ አዳዲስ አመራሮችን አካቶ በአዲስ የተነቃቃ መንፈስ ወደስራ ገብቷል ተብሏል።
አዲሱ አመራር ስቱዲዮ ከማመቻቸት አንስቶ የታዳሚን ቀልብ ይዞ ለመዝለቅ የሚያስችለውን አዲስ የስትራቴጂ አቅጣጫ እየነደፈ በፍጥነት ወደአየር ተመልሶ ለመምጣት እየተንደረደረ እንደሆነ ተሰምቷል።
ጋዜጠኛ ስለሺ ተሰማ የኢትዮ ዋርካ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆኑም ተመርጠዋል።
ዋርካ ሬድዮ በመጪው አስርት አመታት በምስራቅ አፍሪካ የተለየ ምርጥ ሚዲያ ሆኖ ልቆ እንደሚወጣ የሚታመን እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ኩባንያው ከብዙሀን መገናኛው የሬዲዮ ስራዎች በትይዩ በጥናትና የማማከር አገልግሎት ተሰማርቶ የቢዝነስ ሞዴል ቅኝቱን እንዲያጠናክር ጉባኤው አሳሰቦ በጫረታ አሸንፎ የያዘውን ሞገድ ኤፍ ኤም 104.1 ሬዲዮን በፍጥነት ለአየር እንዲያበቃ አደራ ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የዋርካ ሬዲዮ 104.1 ድጋሚ ወደ ሙከራ ስርጭት ተመልሶ በቅርቡ መደበኛ ፕሮግራሞችን ለመጀመር እንዳሰበ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከሬድዮ ባለቤቶቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮ ዋርካ የጠቅላላ ጉባኤውን መደበኛና ድንገተኛ ስብሰባዎቹን በጊዮን ሆቴል አካሂዶ ዋና ውሳኔዎቹን በቃለ ጉባኤ ማፀደቁን ተከትሎ የተለያዩ ለመጪ ጉዞው ወሳኝ የሆኑ አዳዲስ አመራሮችን አካቶ በአዲስ የተነቃቃ መንፈስ ወደስራ ገብቷል ተብሏል።
አዲሱ አመራር ስቱዲዮ ከማመቻቸት አንስቶ የታዳሚን ቀልብ ይዞ ለመዝለቅ የሚያስችለውን አዲስ የስትራቴጂ አቅጣጫ እየነደፈ በፍጥነት ወደአየር ተመልሶ ለመምጣት እየተንደረደረ እንደሆነ ተሰምቷል።
ጋዜጠኛ ስለሺ ተሰማ የኢትዮ ዋርካ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆኑም ተመርጠዋል።
ዋርካ ሬድዮ በመጪው አስርት አመታት በምስራቅ አፍሪካ የተለየ ምርጥ ሚዲያ ሆኖ ልቆ እንደሚወጣ የሚታመን እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ኩባንያው ከብዙሀን መገናኛው የሬዲዮ ስራዎች በትይዩ በጥናትና የማማከር አገልግሎት ተሰማርቶ የቢዝነስ ሞዴል ቅኝቱን እንዲያጠናክር ጉባኤው አሳሰቦ በጫረታ አሸንፎ የያዘውን ሞገድ ኤፍ ኤም 104.1 ሬዲዮን በፍጥነት ለአየር እንዲያበቃ አደራ ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።
የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።
"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።
በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በ"Arts tv World" የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:
አርዕስት:
አርዕስት መረጃዎች:
1. "ታስፈልገኛለህ" ፊልም ለእይታ በቃ።
2."ዴጊያ" ትውፊታዊ ተውኔት ለመድረክ ሊበቃ ነው።
3.የተቃውሞ የገጠመው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ነገ በለንደን ከተማ ይካሄዳል።
4."ውሃዬን ሸጩ ኮዳ የገዛኹለት" መጽሐፍ የፊታችን ሰኞ ይመረቃል።
8. "ጥያቄ ፣ መልስ፣ መኖር" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኞ ይከፈታል።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/aV6SWpQaSRE?si=XFpyvyyxFHRsDcQk

📌"ማለዳ ደጃፍ ላይ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።
ከዚህ ቀደም አነጋጋሪ በነበረው "ከአመጿ ጀርባ" በተባለው መጽሐፏ የምትታወቀው ደራሲ ኤደን ሀብታሙ "ማለዳ ደጃፍ ላይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ እንደምታበቃ ይፋ አድርጋለች።
ደራሲ ኤደን ሀብታሙ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"ጥቂት የማትባሉ የፌስ ቡክ እንዲሁም የአካል ወዳጆቼ፡ “መቼ ነው ሁለተኛ መጽሐፍሽን የምታቀምሺን?” ባላችሁኝ መሰረት እነሆ በጣም በቅርቡ ላዳርስልችሁ ሽር ጉድ እያልኩ ነው"ብላለች።
በተጨማሪም ስለመጽሐፉ ይዘትም"ትንሽ ቆም ብሎ ላስተዋለው፣ ማለዳ ደጃፍ ላይ፣ ስስ ተስፋና አዳዲስ ህልሞች በመስኮታችን ቀዳዳ ሾልከው ይገባሉ። ህይወት ሁሌም ማለዳ ደጃፋችን ላይ ታንኳኳለች።በማለዳ በራችንን ወለል አድርጋን ከከፈትን ደግሞ የበረታ ጸሀይ ያልነካቸው፣ ብዙ ትኩስ የተስፋ ፍንጥቅጣቂዎች፣ በጸሀይ ጨረሮችን ተሳፍረው ከቤትችን ይዘልቃሉ፣ ከቀናን ከሞላልን" ብላለች።
መጽሐፉ በ277 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ500 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
መጽሐፍ በቅርቡ በታላቅ ሥነሥርዓት ተመርቆ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
አስቀድሞ ለንባብ የበቃው የደራሲዋ "ከአመጿ ጀርባ" መጽሐፍ በዛጎል መጻሕፍት ባንክ "የ2013 የዓመቱ የልቦለድ መጽሐፍ" በሚል ተመርጦ እንደነበር ይታወሳል።

📌የቴዲ አፍሮ የለንደኑ ኮንሰርት እንዴት ነበር?
ከሰሞኑ ውዝግብ መነሻ ይሁን ሌላ ምክንያት የኮንሰርቱ ስፍራ እስከመጨረሻዋ ቀን አልተገለፀም ነበር ሊቀር ይችላል በሚል የጎንዮሽ ወሬዎችም በርትተዉ ነበር።
በመጨረሻም ቴዲ ረፋድ ላይ በማህበራዊ ድህረገፁ የተጠባቂዉን ኮንሰርት ስፍራ ይፋ አደረገ እናም ከተለያዩ ከተሞች ጉዞ ወደ ለንደን ተጀመረ።
ሙዚቃን ሁሌ ሳይሆን በድንገት መርጠዉ ከሚሰሙት ዘንድ ብሆንም ባገኘሁት የተሳትፎ እድል ቴዲን መድረክ ላይ ለማየት በሠዓቴ dominion center ተገኘሁ።
ከሁለት መቶ አንበልጥም መጀመሪያ ወደ አዳራሹ የዘለቅነዉ በሂደት ግን የሰዉ ቁጥር እየጨመረ መጣ በዚህ መሀል በተደጋጋሚ ጌታቸዉ ማንጉዳይ የቴዲ ማናጀር ላይ አይኔ አርፏል።
ሁለት እጁን ኪሱ ላይ ከቶ የሰዉን መግባት ይጠባበቃል አዳራሹን ይቃኛል ከፊት ከጀርባ ይመላለሳል ደጋግሞ ይመጣል ይሄዳል በመጨረሻም በተሳታፊዎች ያለመገኘት ስጋት የተጀመረው ኮንሰርት የቤቱን አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ።
ከ1ሺ በላይ ሰዉ በተለያዩ ፕሮግራሞች ያላስተናገደዉ ሴንተር መያዝ በሚገባው ልክ ከ2000 በላይ ታዳሚ በሁሉም ቦታ አስተናገደ።
በኮንሰርቱ መሀል 2ት ግዜ የአዳራሹ ማናጀር እባካችሁ ባልኮኒዉ ላይ ያላችሁ አትዝለሉ ፕሮግራሙን እናቋርጣለን እስኪል ድረስ።
ህዝቡ በኮርኩማ አፍሪካ ተጀምሮ በጥቁር ሰዉ ሙዚቃ እስከተጠናቀቀበት 11 ዘፈኖች ከተለያዩ ከልበሞቹ ተመርጠዉ በቀረቡበት ምሽት ተደስቷል።
ቴዲ አፍሮ አንድ ቦታ ላይ ስለ ሀገሩ ሲዘፍን በስሜት አልቅሷል።የመድረክ ዝግጅት lighting sound ምናምን አይጠየቅም አንደኛ የነበረዉ ዝግጅት ደስ በሚል ትዝታ በሀገረ እንግሊዝ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ለሊት ላይ ተጠናቀቀ።
Via ጋዜጠኛ ሀብታሙ ገደቤ

📌የጠርሲዳ ከበደ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል
“ውሃዬን ሸጬ ኮዳ የገዛኹለት” በሚል ርዕስ የተፃፈው የደራሲ ጠርሲዳ ከበደ መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ የካቲት 10 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡00 ላይ በ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በይፋ ይመረቃል፡፡
የመጽሐፍ ምርቃት ኹነቱን ፤ ፊካ ሶሻል ኢንተርፕረነርስ ፤ ሲግናል ኤቨንትስ እና ሄኖክ የ'ታገኝ ልጅ በጋራ በመኾን ሸጋ አድርገው አዘጋጅተውታል፡፡
ተዋናይ እና አዘጋጅ ተስፉ ብርሃኔ ፣ ገጣሚ እና ተዋናይ ዋስይሁን በላይ ፣ መምህርና ተዋናይ ፈቃዱ ከበደ ፣ መምህርና ተዋናይ ፉአድ መሐመድ ፣ ተዋናይት ሕሊና ሲሳይ ፣ ተዋናይ ሔኖክ ዘርአብሩክ ፣ ድምጻዊ አንተነህ ምናሉ ፣ ተዋናይት ሕይወት ወንድወሰን ፣ ገጣሚ ሂክማ ፋንቱ ፣ ገጣሚ በረከት ተስፋዬ ፣ ብርኩማ ባንድ ፣ ዐራት ነጥብ የኪነጥበብ ቡድን እና ፊካ ኳየር የ 124 ደቂቃዎች የጥበብ ‘ብፌ’ ሰድረዋል። በድምሩ 70 ገደማ በየዘርፉ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉበትም ሰምተናል።
አዘጋጆቹ “ሥነ፟-ጽሑፍን ሲሉ ዋጋ ለከፈሉ ኹሉ ክብር ስንል ለፍተንበታል!” ያሉት ይኽ ኹነት ከደራሲዋ መጽሐፍ የተወሰደ የአንዲት ሴት ተውኔት ፣ የቀጥታ መድረክ ሙዚቃ እና ኮንቴምፖራሪ ዳንስ፣ ሙዚቃዊ ተውኔት ፣ ማራኪ አንቀፆች እና ግጥምን ያካተተ ኹነት አዘጋጅተው ሸጋ ምሽት ሊሰጡን ቀጠሮ አስይዘውናል፡፡
በምሽቱ ተጋባዝ እንግዶችም የሚኖሩ ሲኾን፤ በተጨማሪ ከደራሲዋ ጋር የሚኖር የመጽሐፍ ማስፈረም ዝግጅትንም ያካተተ ነው ብለዋል፡፡ ኹነቱ ሥነ፟-ጽሑፍን ለሚወዱ ኹሉ ክፍት መሆኑንም ሰምተናል።

📌የሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ የክብር ስንብት እና የሥርዓተ ቀብር ሥነሥርዓት በቀጣይ ረቡዕና ሐሙስ ይከናወናል
ተወዳጁ ሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ በሀገረ አሜሪካ በሕክምና ላይ እንዳለ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
አስከሬኑ ረቡዕ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ሀገሩ የሚመጣ ሲኾን፣ በማግስቱ፥ ሐሙስ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የክብር ስንብት መርኀ ግብር ይከናወናል።
ከክብር ስንብቱ መርኀግብር በኋላ፣ ከቀኑ 6:30 ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ይፈጸማል።
በክብር ስንብት እና በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ተወዳጁን ጥበበኛ ተፈሪ አሰፋን እንድንሰናበተው ኮሚቴው የአክብሮት ጥሪውን አቅርቧል።

📌የሽርሽር ጉዞ ወደ ላንጋኖ እና አቢያታ-ሻላ ብሄራዊ ፓርክ ከገሊላ ትራቭል ጋር 👏
📅 Date: February 22 & 23 / 2025 /
የካቲት 15 እና 16 / 2017 E.C
⏱ Duration: 2 Days & 1 Night
🚌 Departure:
📍 mexico wabi shebele
⌚️ 6:00 AM / 12:00 LT
Price(💵): 6000 ETB for Locals
Package includes:
🚎 ትራንስፖርት / Transportation
🥪 ቁርስ / Breakfast /X2/
🍔 ምሳ / Lunch /X2/
🍖 እራት / Barbecue Dinner /X1/
🥤 የታሸገ ውሃ / Bottled Water
🎫 የመግቢያ ዋጋ / Entrance Fees
🗺 የአስጎብኚ / Local Guide
🔥 የምሽት እሳት ዳር ጨዋታ / Campfire
🏕 ማደሪያ ድንኳን / Tent
📸 የፎቶግራፍ / Photography
For more information call on ☎️ 0919874598
@gelilatravel are excited to invite you to a unique and exhilarating campaign trip to Langano. This is more than just a getaway; it’s an opportunity to explore, relax, and create lasting memories.
Tiktok link:
https://vm.tiktok.com/ZMkW6bXjK/