Telegram Web Link
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 ዋዋጎ

ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍የሕይወት ታሪክ

ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የሙዚቃ ባለሞያ ተፈሪ አሰፋ አረፈ

የድራም የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ እና የነጋሪት ባንድ መስራች የሆነው ተፈሪ አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ተሰምቷል።

ተፈሪ አሰፋ የኢትዮጵይ ሙዚቃ ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ የያዘውን ሞያ በውጭ ሃገር ተምሮ እና በሚገባ አጠናቆ ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ በመመለስ የድራም አጨዋወት ሞያ በሃገራችን በብዙ ሰው  እንዲወደድ ያደረገ ታታሪ የሙዚቃ ሰው ነበር።

የሃገራችንን ሙዚቃ ድምበር ተሻጋሪ እንዲሆን እና በመላው ዓለም ተድማጭ እንዲሆን ጥናት አድርጎ የሙዚቃ አልበም በማስቀረፅ በዓለም ገበያ ላይ  እንዲውል ያስቻለ ፣የድርሻውን የተወጣ እና እየተውጣ የሚገኝ ትጉህ፣ ታታሪ፣እውቀቱን ለሌሎች አሳልፎ መስጠትን የማይሰስት፣ ብዙ የድራም ተጫዋቾችን ያፈራ፣የድራም አጨዋወት ጥበብን በሚገባ በተማሪዋቹ አዕምሮ ውስጥ ያፅነሰ፣ ቀና ፣ልበ እሩሩህ እና ከሁሉም ሰው ጋር ተግባቢ እና መልካም ሰው ነበር።

Via አክሊሉ ወልደዮሀንስ

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ነገረ መጻሕፍት" ዛሬ ይካሄዳል

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት  ዛሬ ቅዳሜ ጥር 17 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በዚህ መሰናዶ ላይ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ እና ዶ/ር አንዱዓለም አባተ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የተደበቁ እውነቶች የተጋረዱ ሀቆች" ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
📌«ማህሙድ መዝፈን አልነበረበትም፤የሙዚቃው ድግስም ዓላማውን ስቷል» የጣዕም ልኬት አዘጋጆች

የሙዚቃ ባለሙያዎቹን ሰርፀ ፍሬ ስብሃት እና ምዕራፍ ተክሌን ያጣመረው በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ  ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 6  እስከ 8 ሰዓት  የሚቀርበው "የጣዕም ልኬት" መሰናዶ በጥር 17 / 2017 ዓ.ም ቆይታው ሳምንታዊ ዳሰሳውን ያደረገው ለአንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ የተዘጋጀውን የሙዚቃ ድግስ በተመለከተ ነው።

የሙዚቃ መርሃግብሩ በቀረበበት ሳምንት በከተራና ጥምቀት በዓል ልዩ ዝግጅት ምክንያት በወቅቱስለ ኮንሰርቱ  ማንሳት እንዳልተቻለ  አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።
አዘጋጆቹ  'የሳምንቱ የሙዚቃ አምባ' ላይ ዳሰሳ ባደረጉበት የአንጋፋው ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የሙዚቃ ዝግጅት መልካም ጎኖች ቢኖሩትም ሊስተካከሉ ይገባቸው የነበሩ መሰረታዊ ነጥቦችን አስቀምጠዋል።

ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የኢትዮጵያ የሙዚቃ መልክ ተደርጎ የሚቆጠር እና የሚወደስ ታላቅ ድምፃዊ ከመሆኑ አንፃር እርሱን አክብሮ የተሰናዳ ዝግጅት መሆኑ ከመርሃ ግብሩ ጀርባ ያሉትን እንደሚያስመሰግን አዘጋጆቹ ገልፀው ከድምፃዊው የቀደሙና ዛሬ ላይ በህይወት ያጣናቸው ታላላቅ ሥራን የሰሩ ድምፃውያንን እንዲህ ባለ መልኩ ሳናከብራቸው እንደማለፋቸው  ይህ ዝግጅት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውም አንስተዋል።

መሀሙድ አህመድ በሙዚቃ ሕይወቱ የደረሰበት ደረጃ እና ከፍታ «ለዚህ ክብር የሚመጥን የጥበበ ሰው እንዲሆን ያደርገዋል» ያሉት አዘጋጆቹ ከእሱ በተጨማሪ በሥራቸው የላቀ ከፍታ ላይ ደርሰው ልክ እንደ እሱ አክብረን ላልሸኘናቸው ሁሉ 'የመንፈስ ውክልናን የሚወስድ ነው።" ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ አንፃር ለመርሃ ግብሩ መሳካት ከውጥን ጀምሮ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የደከሙት በጠቅላላ ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ያም ሆኖ ግን  ከታለመለት አላማ አንፃር ሲታይ ትልቅ ክፍተት የነበረበት ከመሆኑ ባለፈ በታሰበው ልክ መሬት ላይ ወርዷል ማለት እንደሚያዳግት የጣዕም ልኬት አዘጋጆች አንስተዋል።

ክፍተቱ የሚጀምረው መርሃ ግብሩ "የስንብት" የሚለውን ቃል መጠሪያ ከማድረጉ እንደሆነ አንስተዋል። መጠሪያው ትልቅ ክፍተት የሚፈጥር እና ከሥነ ልቦና አንፃር ሲታይ አሉታዊ ተፅዕኖው እንደሚያጋድል አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

ከዚያ ይልቅ ማክበር እንደመሆኑ መጠን ስያሜው ያንን ተንተርሶ ሊሰጥ ይገባው እንደነበር በማንሳት መድረኩ ግቡን መቷል የሚል አመኔታ እንደሌላቸው ተናግረዋል። በጣዕም ልኬት አዘጋጆች ዕይታ በሙዚቃ ድግሱ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።

👉« የመድረኩ ይዘት የተቃኘበት መንገድ ትልቅ ስህተት ነበረው፤ይህንን ያለ ይሉኝታ ማስቀመጥ ይገባል።» ብለዋል

👉ከሰዓት አከባበር ጋር በተገናኘ ትልቅ ክፍተት መፈጠሩን ተከትሎ በርካቶች ዝግጅቱን አቋርጠው ለመውጣት ከመገደዳቸው ባለፈ ጥቂት ታዳሚያን ብቻ መሀሙድ ሥራውን ሲያቀርብ መመልከታቸው  ቀዳሚው ክፍተት እንደነበር ተጠቅሷል።

👉«መሀሙድን ለማክበር የተገኙት ድምፃውያን የራሳቸውን የቀደሙ ሥራዎች እና በየምሽት ክበቡ የሚቀርቡ ሙዚቃዎችን ደግመው ማቅረባቸው ከመድረኩ አላማ ጋር የሚጋጭ ነበር። በተጨማሪም የመድረኩ ዝግጅት ላይ ምን አይነት ሥራ ይቅረብ በሚለው ዙሪያ ምንም ግንዛቤ አልነበራቸውም።»

« ከዚያ ይልቅ በእለቱ ተዋጣላቸውም አልተዋጣላቸውም ከሁሉም ድምፃውያን አንደበት የመሀሙድን ስራ ልናደምጥ ይገባ ነበር» ሲሉ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

👉 «መሀሙድ በወቅቱ ከነበረበት የጤና እክል አንፃር አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ሙዚቀኞችም ጭምር  እንዲዘፍን ፈፅሞ ማድረግ አልነበረባቸውም።»
ከእዚያ ይልቅ በመድረኩ የክብር ሥፍራ ላይ ሆኖ ቢከታተል መልካም እንደነበር አንስተዋል።

👉 የዝግጅቱ "እጥር ምጥን" ማለት አለመቻሉ ክፍተት መፍጠሩን ያነሱት የጣዕም ልኬቶች መርሃ ግብሩ ሚሊኒየም አዳራሽ የግድ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ ሌላ ስፍራ በመምረጥ የሙያ ምስክርነት፣ ዘጋቢ ፊልሞች፣ ስጦታዎችና ሌሎችም ጉዳዮች በተናበበ መልኩ ማድረግ ይቻል ነበር ሲሉ አንስተዋል። የምሽት ክለብ የመሰለ መርሃ ግብር መሆኑን ተከትሎ አዘጋጆቹ ሳይቀሩ ለመቆጣጠር ተቸግረው እንደነበር ገልፀዋል።

👉«ፕሮግራሙ ኮንሰርት የሚሰሩ ሰዎች እጅ ላይ መውደቁ ክፍተት ፈጥሯል ያሉት አዘጋጆቹ ኮንሰርት መሆኑ እና ገንዘብ ላይ ማተኮሩ የቀረቡት ድምፃውያን ከመሀሙድ አርቋቸዋል። » ሲሉ ሁኔታውን የገለፁ ሲሆን የመሀሙድን ስራ በተደጋጋሚ የተጫወቱ እንዲሁም የመሀሙድ ሙዚቃ ዘመን ተጋሪ ሆነው የሰሩ ባለሙያዎች ቢመረጡ መልካም ነበር ሲሉ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል።

ከእዚህ እና ከሌሎች ክፍተቶች እንፃር ዝግጅቱ ሀሳቡ እና መነሻው ትልቅ ተግባር ግን  አጨራረሱ  ዝቅተኛ እንደሆነ አንስተዋል።

Via ናትናኤል  ሀብታሙ( Fm Addis 97.)

ለተጨማሪው: @EventAddis1
📌ሜንታል ሄልዝ አዲስ ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል

የአእምሮ ጤና ላይ ትኩረቱን አድርጎ በየወሩ የሚካሄደው ሜንታል ሄልዝ አዲስ የሥነልቦና ውይይት ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል::

የዚህ ወር ርዕስም፡-“Understanding narcissistic presonality Disorder ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ በመሆን የሥነልቦና ባለሞያው የሆኑት ጴጥሮስ ሀጎስ የውይይት መነሻ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

54ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዶ/ር ጋሻው አይፈራም "የትውልዶች ቅራኔ በዘመነ ብዙሃ ቀውስ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የመሠረት አዛገ መጽሐፍ አርብ ይመረቃል

የመሰረት የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራች በሆኑት ወ/ሮ መሰረት አዛገ የተጻፈው "ሺ ጊዜ እንዳፈቅር" የተሰኘ የግጥም መጽሔት ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።ይህም መጽሐፍ ከነገ በስቲያ አርብ ጥር 23 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።በምርቃት ሥነሥርዓት ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌 የሎሬቱ ቤት "ቪላ አልፋ" በድጋሚ ሊከፈት ነው

የዓለም ሎሬት ሜተር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ እና ስቲዲዮ የነበረው ቪላ አልፋ ከአራት ወራት ብኋላ ለህዝብ ክፍት ሊደረግ ነው።

በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች አካባቢ የሚገኘው ቪላ አልፋ ከጣሪያው ጀምሮ ወደ ምድር የሚዘልቀው ፍሳሽ የእድሳት ጉዞውን ረጅም እና እድካሚ እንዳደረገው ታውቋል።

ነገር ግን በሁለት ወር ውስጥ ቀሪው ስራ እና የሙዚየም ስራው ተጠናቆ በአራት ወር ውስጥ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባ አያሌው ነግረውናል።

ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የአርቲስቱ መኖሪያ ቪላ አልፋ ከዛሬ ነገ በቅርቡ ክፍት ይሆናል ሲባል ቆይቷል።

ለመሆኑ ከወሰን ማካለል እና አካባቢው መኖሪያ መሃል እንደመሆኑ መጠን በዚህ ሐሳብ መንገድ ምን ተሰራ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው የሙዚየሙ አጎራባች እንደተለየና ለጉብኝት አመቺ ተደርጎ እንደታደሰ ነግረውናል።

የአለም ሊቀ ሊቃውንት የኪነ ጥበብ ባለሙያው ሰአሊ አፈወርቅ ተክሌ የእጅ ስራዎች መካከል መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የግድግዳና ጣሪያ ስዕሎች፣  የሞዛይክ ስራዎች፣ የመስኮትና መስታወት ስዕሎች፣ የዳግማዊ የምፅአት ፍርድ፣ የደመራ ስእል፣ የራስ መኮንን ሀውልት፣ የአፍሪካ ድል አፍሪካ አጠቃላይ ነጻነት፣  የመስቀል አበባ እንዲሁም እናት ኢትዮጵያ ይገኙበታል።

መረጃው  የሸገር ሬድዮ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የድምጻዊ ማሚላ ሉቃስ ‘እንደ ጊዜው’ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል።

አስራ ሶስት ትራኮችን የያዘዉ የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ ‘’እንደ ጊዜው’’ አልበም ጥር 30 2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

በሰዋሰው መልቲሚዲያ በኩል እንደሚለቀቁ ሲነገሩ ከነበሩ አልበሞች መካከል አንዱ የሆነው ‘’እንደ ጊዜው’’ የተሰኘዉ የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ አልበም ለስድስት ዓመታት የተለፋበት ሲሆን አንጋፋ እና ወጣት ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ።

በአልበሙ ላይ በግጥምና ዜማ ይልማ ገ/አብ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ፣ አለማየሁ ደመቀ እንዲሁም እራሱ ድምፃዊ ማሚላ ሉቃስን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች አሻራቸዉን አሳርፈዉበታል።

አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ካሙዙ ካሳ፣ ሚኪ ጃኖ፣ስማገኘዉ ሳሙኤል፣ፋኑ ጊዳቦ፣ሱራፌል የሺጥላ እና ጊልዶ ካሳ በሙዚቃ ቅንብሩ ተሳትፈዉበታል።

አልበሙ የፊታችን ጥር 30 ጀምሮ በሰዋሰው አፕ እና በሰዋሰዉ የዩቲዩብ ገፅ ላይ ይለቀቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 ዋዋጎ

ድርሰት: ታረቀኝ ብርሃኑ
አዘጋጅ: ጥላሁን ዘውገ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍የሕይወት ታሪክ

ድርሰትና ዝግጅት ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የድምፃዊ ዮሐና አልበም ዛሬ ተለቀቀ

የድምፃዊ ዮሐና አዲስ አልበም ዛሬ ጥር 23 2017 ዓ.ም በቀኑ 8:00 ጀምሮ ለአድማጮች ቀርቧል።

ድምፃዊ ዮሐና 'ሃሎ' የሚል መጠሪያ ያለውን እና 10 ሙዚቃዎች ያካተተውን አዲስ አልበሙን እንደለቀቀ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።

በዚህ አዲስ አልበም ዮሐና ከሰራቸው ሙዚቃዎች መካከል 'ታማ' በሚል ርዕስ ያቀነቀነው ሙዚቃ ከዮሐና ጋር ጥብቅ ቁርኝት ላላት መቐለ ከተማ የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ እንደሆነ ተነግሯል።

ግጥም እና ዜማ ሙሉ በሚባል ደረጃ ራሱ ዮሐና እንደሰራው እና አርቲስት ሳምቮድ፣ ዮርዳኖስ (ጆጆ) በአልበሙ ውስጥ ተሳትፎ ካደረጉት መካከል መሆናቸው ተገልጿል ።

በሙዚቃ ቅንብሩ እና ሚክሲንግ ሃይፐር ዜማ እና ማሩ አለማየሁ (ማርቭል) ሲሳተፉበት በማስተሪንግ ላይ ደግሞ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌መልካም ዜና: ከኤቨንት አዲስ ሚዲያ

የኤቨንት አዲስ የሐሙስ መረጃዎች አደጉ ተመነደጉ

ዘውትር ሐሙስ በኤቨንት አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሰራጭ የቆየው "የሐሙስ መረጃዎች" ልዩ ጣዕም ጨምሮ በቴሌቪዥን መስኮት መተላለፍ ጀምሯል።

የሐሙስ መረጃዎችን ዘውትር አርብ "አርትስ ስፔሻል" በሚል ርዕስ ምጥን ፕሮግራሙን ወደ እናንተ ያደርሳል።

"የአርትስ ስፔሻል" ምጥን ፕሮግራም ዘውትር አርብ ከምሽቱ 1:00 እና በድጋሚ ከምሽቱ 4:00 ላይ በአርትስ ቴሌቪዥን የዜና ሠዓት ይተላለፋል።

በተጨማሪም በሚሊዮኖች ተከታይ ባለው በArts tv World"  የዩቲዩብ ቻናል ይሰራጫል።

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ:

አርዕስት:

1.ጃፓናዊያን በአማርኛ ያዜሙበት የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ቀረበ።

2.ሠዓሊ መዝገቡ ተሰማ ሀሳቡን የሚያጋራበት ልዩ መድረክ ነገ ይካሄዳል።

3.በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የሴቶች የቁርአን ውድድር ሊካሄድ።

4.የደራሲ ሌሊሣ ግርማ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

5.ድምጻዊ አለማየሁ ሄርጶ ወደ ሙዚቃ ተመለሰ።

6."ከመስኮቶች በስተጀርባ" የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይሰሙ ሊንክ: https://youtu.be/y0XQ3babXY0?si=AFT46V5kf8BbVmUj

📌መልካም ምሽት


ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" አምስተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት  ይካሄዳል።

ባለፉት አምስት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ ስድስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም ገጣሚ ተስፋዬ ማሞ እና ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ የዕለቱ ተጋባዥ የክብር እንግዳ በመሆን እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ድምጻዊ ዘሩባቤል ሞላ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።

(መግቢያው በነፃ ነው)

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር ዘሩባቤል ሞላን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከድምጻዊ ዘሩባቤል ሞላ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን  ማክሰኞ ጥር 27 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከዘሩባቤል ሞላ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ  ማክሰኞ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌“ሺ ጊዜ እንዳፈቅር” የግጥም መድበል ተመረቀ

በገጣሚ መሠረት አዛገ “ሺ ጊዜ እንዳፈቅር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የግጥም መድብል በዋልያ መፅሐፍት ተመርቋል።

መጽሐፉ አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሥነጽሑፍ ቤተሰቦች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

በምረቃው ሥነስርዓት ላይ ጸሐፌ ተውኔትና ገጣሚ አያልነህ ሙላቱ፣  ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ፣ ደራሲና መምህር ኃ/መለኮት መዋዕልና መምህር የሻው ተሰማ በመፅሐፉ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።

እንዲሁም ወጣት ገጣሚያን ሥራቸውን አቅርበዋል፡፡

የግጥም መድብሉ በ92 ገፆች የተቀነበበና 47 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ250 ብር ለንባብ በቅቷል።

ገጣሚ መሠረት አዛገ፣ የ”መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት” መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ስትሆን፥ ላለፉት 14 ዓመታት በህጻናትና በእናቶች ድጋፍና እገዛ ላይ በሠራቻቸው ሥራዎች በርካታ ሽልማቶችን ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ማግኘት የቻለች እንስት ናት፡፡

ዘገባው የአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

📸ተክሌ ማርኮን

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ገጣሚ ምስረቅ ተረፈ በእስር ላይ ትገኛለች

በጦቢያ ግጥምን በጃዝ ፕሮግራም አዘጋጅነት የምናውቃት ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ?" በሚል በፖሊስ የተወሰደች ሲሆን ፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁ ተሰምቷል።

ፖሊስ፣ ምሥራቅን አዲስ አበባ፣ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት እንዳቀረባት፣ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል፣ "ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርባት" በሚል ለጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ተከትሎ፣ ምሥራቅ አሁን በአዲስ አበባ ፖሊስ እስር ላይ እንደምትገኝ ወዳጆቿ ገልጸዋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አስር ሺህ ሰው የሚሳተፍበት የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት በአድዋ ሙዚየም ሊካሄድ እንደሆነ ተነገረ።

ከ10 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ይሳተፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት የፊታችን የካቲት 2 2017 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ሊካሄድ ነው።

ይህ በኢትዮ ፊትነስ ዳንስ እና በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት አማካኝነት የሚዘጋጀው የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ዋና ዓላማው ሀገራችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ማስተዋወቅ ነው።

በፕሮግራሙ የከተማው ነዋሪዎች እና ከውጭ ሀገር ትውልደ ኢትዮጵያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የዳንስ ፊትነስ በከተማችን መዘጋጀቱ  ባህላዊውን ውዝዋዜ ከዘመናዊው ዳንስ ጋር በማዋሐድ የሚዘጋጅ በመሆኑ ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የማህበረሰብ ስፖርት ማስፋፊያና ማደራጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል ገልፀዋል።

የኢትዮ ዳንሰ ፊትነስ አሰልጣኝ እና መስራች ቶማስ ኃይሉ (ቶሚ ፕላስ) በበኩሉ በፕሮግራሙ ከ10ሺ በላይ ሰዎች ለማሳተፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ  ይህ ከተሳካ  በዳንስ ፊትነስ በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ እንደሚሆን አሳውቋል።

ቲሸርቱን ከኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጂም ያገኙታል፣ የመግቢያ ዋጋ በነፃ ሲሆን ለቪአይፒ የመስሪያ ቲሸርቶች ተዘጋጅተዋል። በሁሉቱም አማራጮች ለመሳተፍ በኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ድረገፅ https://www.ethiodancefitness.com ላይ መመዝገብ ያስፈልጋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ጥሎሽ ሐር ብራንድ ሾሟል!

ዝነኛዋ ቸሊና ከጥሎሽ ሐር ጋር የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርማለች።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት የሚቆየው ለሁለት ዓመት ነው።

እንዲሁም ቸሊና በጥሎሽ ሐር ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት ተፈራርማለች፡፡

ጥሎሽ ሐር የሰርግ ቀሚሶችን፣ ማስዋቢያዎችን እና የህንድ እና ተመሳሳይ ባህላዊ ቀሚሶችን የሚያቀርብ ድርጅት ነው ተብሏል።

ጥሎሽ ሐር በሠርግ ዘርፍ ውስጥ ታዋቂ እና መሰረት ያለው የንግድ ምልክት ነው።

ጥሎሽ ሐር የሠርግ አልባሳት መሸጫ እና ማከራያ ስቶር ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የሠርግ  አልባሳትን እና መገልገያዎችን በሽያጭ እና በኪራይ በማቅረብ በተጨማሪም ልዩ ልዩ ዓለምአቀፍ የሠርግ አልባሳትን እንዲሁም የተለያየ ስታይል ያላቸው የሠርግ መገልገያዎችን ወደ ገበያ ይዞ በመምጣት ላይ ይገኛል።

ጥሎሽ ሐር የሠርግ አልባሳት መሸጫ እና ማከራያ ሱቅ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 1 2017 ዓ.ም በታላቅ ሥነሥርዓት (Grand Opening ) ጋራድ ሞል ላይ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።

በጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ የተፃፈው 57 ቁም ነገር አዘል አዝናኝ ወጎች የተካተቱበት  "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" መጽሐፍ ነገ ማክሰኞ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡ 30 አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት አዳራሽ (ብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት) ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
2025/07/10 23:24:02
Back to Top
HTML Embed Code: