Telegram Web Link
📌የድምጻዊት ዘቢባ ግርማ "እንደምንም" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነው

አንጋፋውና ወጣት የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት “እንደምንም" የሙዚቃ አልበም 13 ሙዚቃዎችን በውስጡ የያዘ  ሲሆን አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አምስት ዓመት እንዲወሰድባትም ተነግሯል።

ለአልበሙ ላይ የሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ በድምጻዊት ዘቢባ ግርማ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡

የሙዚቃ አልበሙ ስለ ፍቅር፤ ስለ ምስጋና እና ስለ እናት እና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

የድምጻዊት ዘቢባ ግርሓጨ"እንደምንም" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት አንድ በዘቢባ ግርማ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ለአድማጮች ይቀርባል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ አውደርዕይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ 17ኛውን ዓመታዊ የመጽሐፍ አውደ-ርዕይ ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ስድስት ኪሎ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውስጥ ያካሂዳል።

በነዚህ ቀናት በዩኒቨርሲቲው በመገኘት አውደርዕዩን ጎብኙ፣መጽሐፍት ግዙ፣ስለ ንባብ ተወያዩ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ፈስቲቫሉን ላይ በነፃ ይታደሙ

ቅዳሜ እና እሁድ ሚያዝያ 25 እና 26 2017 ዓ.ም የሚደረገው የዓለም የጥበብ ቀን እና የኢትዮጵያ ጃዝ ፌስቲቫል መግቢያ በነፃ ሆኗል።

የዓለም አቀፍ የሥነጥበብ ቀን እና የኢትዮጵያ ጃዝ ፌስቲቫል ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሚያዚያ 25 እና 26 2017 ይከናወናል፡፡ የዘንድሮው ፌስቲቫል ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ታዋቂና ተወዳጅ የሆኑ ሙዚቀኞችን ያሳተፈ እንደሆነ ተነግሯል።

በዚህ ዓመት ፌስቲቫል ላይ ለኢትዮ-ጃዝ አባት ለታዋቂው ሙላቱ አስታጥቄ በዘርፉ ላበረከቱት ፈር ቀዳጅ ሥራቸውና እና በዓለም የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ላኖሩት ሙዚቃዊ ትሩፋት ክብር የሚሰጥበት እንደሆነም ተገልጿል።

በተጨማሪም በፌስቲቫሉ ላይ ከ41 ዓመታት በኃላ አድማስ ባንድ የሙዚቃ ዝግጅቱን ያቀርባል ተብሏል።

ዝግጅቱ ቅዳሜ ሚያዚያ 25 እና እሁድ ሚያዚያ 26 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ከቀኑ 7፡00 እስከ ምሽት 1፡00  በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ይካሄዳል።

አዘጋጆቹ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚና SAY Records ናቸው።

ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

1. ድምጻዊ ብስራት ሱራፌል ለአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምህሩ ያዜመበትን ሙዚቃ ጨምሮ 6 የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘው "የጠይም ፈረንጅ" የሙዚቃ አልበምን ለአድማጮች አቀረበ።

2.ሁለት ጎራ ክፍሎ ሲያነጋገር የቆየው የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ከትላንትና በስቲያ በእስራኤል ቴላቪቭ ተካሄደ። በሌላ ድምጻዊ  ቴዲ አፍሮ በ8 ሙዚቃዎች ላይ በግጥምና የተሳተፈበት የአንጋፋዋ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ አልበም ዛሬ አመሻሹን ለአድማጮች ቀረበ።

3.በመድረክ መሪና ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ የተዘጋጀው "የመድረክ ማስታወሻ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

4.ኢትዮጵያዊቷ በአሜሪካ ትልቅ የሥነጽሑፍ ሽልማት ተሸለመች።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/c6JUGt_BOl0?si=M28Ec0VbDN6xYOBs

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮፒካር እና አሚጎስ ጥምረት

ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ጋር በመተባበር፣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዘመናዊ  መኪኖችን ለ15 ደንበኞች ማስረከባቸውን ዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮፒካር ዋና መ/ቤት በተካሄደ ሥነሥርዓት ላይ አስታውቀዋል።

በኢትዮፒካር በቀጥታ ግዢ እንዲሁም በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት እነዚህ የኤሌክትሪክ መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፤እስካሁንም  ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ፈላጊዎች ከባንክ እንዲሁም ከብድርና ቁጠባ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ውል በመግባት መኪኖቹን ማስረከቡን የኢትዮፒካር ማርኬቲንግ ኃላፊ ወወይዘሪት አቤኔዘር ደበበ ገለጸዋል።

ኢትዮፒካር መኪኖቹን የሚሸጠው ከባትሪና መለዋወጫ ዕቃዎች ዋስትና ጋር መሆኑን የጠቆሙት  የማርኬቲንግ ኃላፊዋ፤ በቻይና በ3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሞዴል መኪኖችን እንደሚያስመጣ  ተናገረዋል።

አሚጎስ ከኢትዮፒካር ጋር ስምምነት ከፈጸመ ወዲህ ቅድመ ቁጠባውን ላሟሉ 100 ደንበኞቻቸው የኤሌክትሪክ መኪኖችን ያስረከቡ ሲሆን፤ እስከ መጪው ሰኔ 30 ባለው ጊዜም 50 ለሚደርሱ ደንበኞች መኪኖችን ለማስረከብ መታቀዱም ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የሮፍናን ኮንሰርት ጋምቤላ ሊካሄድ ነው

የሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ"የኔ ትውልድ " የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 2 2017 ዓ.ም በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

ይህ የሮፍናን የሙዚቃ ኮንሰርት በጋምቤላ ስታዲየም እንደሚካሄድም ሙዚቀኛው በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ቍናማት" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በገጣሚ ሐዋዝ የሻነህ የተዘጋጀው "ቍናማት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፉ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ205 ገፆች ተቀንብቦ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚና ደራሲ ሐዋዝ የሻነህ ከዚህ መጽሐፍ አስቀድሞ "ኢካቦድ"የግጥም ስብስብ)፣ "የአዳም ፊርማ" እና "ሰውነት" የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ለጋስ አድማስ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

በገጣሚ ወልደገብርኤል ደሳለኝ(ወገደ) የተዘጋጀው "ለጋስ አድማስ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ በቅርቡ ንባብ ይበቃል ተብሏል።

"ለጋስ አድማስ" የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ350 ብር በቅደመ ሽያጭ ለአንባቢያን ይቀርባል።

መጽሐፉን መግዛት ለሚፈልጉ የባንክ ቁጥር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000530618661
ወልደገብርኤል ደሳለኝ
ቴሌ ብር ፦0992269755

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
“የአፍሪካ ቀንድ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

“የአፍሪካ ቀንድ” የተሰኘው መጽሐፍ በመጪው አርብ ገበያ ላይ ይውላል ተብሏል።

በታዋቂው የአፍሪካ ቀንድ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ በሆኑት ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፋም ተጽፎ፣ በጋዜጠኛ ኅይለመስቀል በሸዋምየለህ ወደ አማርኛ የተመለሰው ይኽ መጽሐፍ፣ በ231 ገጾች ተቀንብቦ በ450 ብር እንደሚሸጥ ሰምተናል።

መጽሐፉ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ ባሏቸው ፖለቲካዊ ግንኙነቶች ላይ አተኩሮ፣ የመጪውን የቀንዱን ዕጣ ፈንታም ይዳስሳል ተብሏል።

መጽሐፉ በኹሉም የጃፋር መጽሐፍት ቤቶች እንደሚገኝም ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ አውደርዕይ ተከፍቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የመጽሀፍ አውደ-ርዕይ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ውስጥ ከዛሬ ሚያዝያ 28 2017 ዓ.ም ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።

17ኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የመጽሀፍ አውደ-ርዕይ ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 4 ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል፡፡
 
በዚህ አውደርዕይ ላይ አዳዲስ መጻሕፍት ይመረቃሉ፣ ዳግም የታተሙ መጻሕፍት ለሽያጭ ይቀርባሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
4 የኢቤኤስ ሰራተኞች በዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ

በሽብር ወንጀል ጉዳይ ተጠረጥረው በእስር ላይ የሚገኙ አራት የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች፤ ዋስትና በማስያዝ እንዲለቀቁ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።

ሁለት የጣቢያው ሰራተኞችን ጨምሮ 16 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤት አስታውቋል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ እና ጋዜጠኛ የአብሥራ ገዛኸኝ በጂንካ ዩኒቨርስቲ ዝግጅታቸውን ሊያቀርቡ ነው

በጂንካ ዩኒቨርስቲ ልዩ ኪነጥበብ ተዘጋጅቷል።በዚህ ዝግጅት ላይ አንጋፋው ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌና የአርትስ ቴሌቪዥኑ አመለሸጋው ጋዜጠኛ የአብሣራ ገዛኸኝ በክብር እንግድነት ይገኙበታል።

በተጨማሪም ፕሮግራሙ ላይ በአቢሲኒያ የኪነጥበብ ቡድን አባላት የግጥም፣ የሙዚቃ ፣የመነባንብ ፣ጭውውትና በአጠቃላይ የኪነጥበብና የሥነጽሑፍ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ።

ዝግጅቱ ዛሬ ሚያዝያ 30 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በጂንካ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ሳይንሳዊ ጽሑፍ ከየትኛውም ሀገር በበለጠ ተሰርዟል ተባለ

በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ አዲስ ጥናት በኢትዮጵያ ተመራማሪዎች የተጻፉት ሳይንሳዊ ጽሑፎች ዓለም ውስጥ ካሉ ከማንኛውም ሀገር ተመራማሪዎች በበለጠ መጠን ተሰርዘዋል ወይም ተመልሰው ተወስደዋል ሲል አመልክቷል ።

ይህም በኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ፅሁፎች ከእውነት የራቁ ወይም ከፍተኛ የጥራት ችግር ያለባቸው በመሆናቸው ከአሳታሚዎች እንዲሰረዙ መደረጉን አመልክቷል።

በህንድ የሚገኝ የውሂብ ሳይንቲስት የሆኑት አቻል አግራዋል ባካሄዱት ይህ ጥናት፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ ስትሆን ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና እና ግብፅ በመቀጠል ከፍተኛውን የፅሁፍ መሰረዝ መጠን ያሳዩ ሀገራት ናቸው።

ተመራማሪው አግራዋል እንዳሉት፣ ይህ ሊሆን የቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ጥራት የሌላቸውን ፅሁፎች በንቃት የሚከታተሉና የሚያጋልጡ ጠንካራ የሳይንስ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ባለመኖሩ ሊሆን ይችላል።

በአንጻሩ እንደ ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት የምርምርን ታማኝነት በማረጋገጥ ረገድ ግንባር ቀደም ሲሆኑ፣ ጥራት የሌላቸውን ፅሁፎች በመለየትና በማስወገድ ረገድም ውጤታማ ናቸው ብለዋል።

ጥናቱ አብዛኛዎቹ ፅሁፎች የተሰረዙበት ምክንያት በግልጽ እንደሚታየው በሐቀኛ ስህተት ሳይሆን፣ "አብዛኛው" የሚሆነው በተለያዩ የሥነ ምግባር ጉድለቶች የተነሳ እንደሆነ ይጠቁማል። ይህም የውሸት መረጃዎችን ማቅረብ፣ የሌሎችን ስራ ያለ ፈቃድ መጠቀም (ስርቆት) ወይም በምርምር ሂደቱ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን መፈጸምን ያካትታል።

Via ካፒታል ጋዜጣ

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌 የነገረ መጻሕፍት አዘጋጆችና ታደሚያን ቅዳሜ "አበሻው " በተሰኘ መጽሐፍ ላይ ይወያያሉ

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ነገ ቅዳሜ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "አበሻው " የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት አያሌው ምትኩ ብሩ ይገኛሉ ተብሏል። የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:

1. የሙዚቃ አልበሙን ለአድማጮች ካደረሰ ሃያ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረው አንጋፋው ድምጻዊ ዳዊት መለሠ እና ሚካኤል በላይነህ የተጣመሩበት የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው።

2.ጦቢያ የኪነጥበብና የሀሳብ መሰናዶ በዘጠኝ የአውሮፓ ሃገራት በ16 የአውሮፓ ትልልቅ ከተሞች ትርዒቱን ሊያቀረብ ነው።

3.ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ከፍተኛ ወጪ አውጥቼበታለሁ ያለውን የሙዚቃ ቪዲዮ በቅርቡ ለተመልካቾች እንደሚያቀርብ ተናገረ።

4.የደራሲ አድኃኖም ምትኩ ሁለተኛ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

5.'የተሸመኑ ትውስታዎች' የሥዕል አውደርዕይ ነገ ይከፈታል።

6.ኮሜዲያን እሸቱ መለሠ የኮሜዲ ዝግጅቱን ነገ በለንደን ከተማ ያቀርባል።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/XBpZW2u7i3M?si=jPI7dBJ4hx5gLsrd

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"ጦቢያ" በዘጠኝ የአውሮፓ ሀገራት

"ጦቢያ" የኪነጥበብ ዝግጅት በ9 የአውሮፓ ሃገራት ትርዒቱን ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷል።

ይህም የአውሮፓ ጉዞ ጦቢያ ከሆፕ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው ተብሏል።ከወርሐ ሰኔ እስከ ነሐሴ ለሁለት ወራት ገደማ የሚካሄደው ዝግጅቱ የኢትዮጵያዊያንን ባህል ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም ተገልጿል።

ጦቢያ በዚህ ጉዞው በዘጠኝ የአውሮፓ ሀገራት እና በ16 የአውሮፖ ትላልቅ ከተሞች  ዝግጅቱን ያቀርባል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"የተሸመኑ ትውስታዎች" የሥዕል አውደርዕይ

በወጣቱ ሠዓሊ ብርሃኑ ማናዬ የተዘጋጁ ሥዕሎች የቀረቡበት"የተሸመኑ ትውስታዎች" የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 2 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖስት ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ”The Space Ethiopia” የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

በዳግም አበበ አጋፋሪነት የተዘጋጀው ይህ አዉደርዕይ የተለያዩ የስዕል አቀራረቦችን እንዲሁም በተለያዩ የአሳሳል ዘይቤ የተሰሩ የስዕል አይነቶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።አውደርዕዩ እስከ ሰኔ 18 2017 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"በመኖር በኩል" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የደራሲ አድኃኖም ምትኩ "በመኖር በኩል" መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 4 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመርቆ ለንባብ ይበቃል ተብሏል።

"በመኖር በኩል" መጽሐፍ አስራ ሰባት አጫጭር እና የተያያዙ ታሪኮች ያሉበትን የልብወለድ መጽሀፍ ነው።

ደራሲ አድኃኖም ምትኩ የበኩር ስራው የሆነውን "አዎ እሱ ጋ ያመኛል" የተሰኘ የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ መፅሃፍ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ለአንባብያን ያደረሰ ሲሆን መጽሀፉ ተወዳጅነትን በማትረፍ በአጭር ግዜ ውስጥ አምስተኛ ህትመት ደርሶ ከአስራ ስምንት ሺ ኮፒ በላይ መሸጥ እንደተቻለ ተነግሯል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌'ሐሙስ' ተውኔት ነገ ሐሙስ ለእይታ ሊበቃ ነው

"ሐሙስ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ተውኔት ነገ ሀሙስ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

አንጋፋው ከያኒ ተክሌ ደስታ ከዓመታት በፊት የተወነበት አስከትሎም አዘጋጅ ሆኖ ብቅ ያለበት "ሐሙስ" ተውኔት ከ20 ዓመታት በኋላ ነገ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ባልተለመደ መልኩ ከቀኑ 8:ዐ0 ላይ ለመድረክ ይበቃል ተብሏል።

"ሐሙስ" ተውኔት ድርሰቱ የስዩም ተፈራ ሲሆን አዘጋጆቹ ተክሌ ደስታና ተስፋዬ ሲማ ናቸው።

በትወናው በኩል ታሪኩ ሚፍታ ፣ ቴዎድሮስ ሙሉጌታ፣ ዕፀሕይወት አዳንከኝ፣ዮዲት ካሣሁንና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌 ማን ይመስገንልዎ? ይጠቁሙን!

የምስጋና ባህል እንዲያድግ ጥረት የሚያደርገው "ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት" ግንቦት 30 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

ይህ ምስጋና ፕሮግራም በተለያየ ዘርፍ ማለትም፣በስራ ፈጠራ፣በበጎ አድራጎት፣ማህበራዊ ሚድያውን ለመልካም ተግባር ፣ሚድያውን ለስነልቦና ግንባታ፣ዝናን ለመልካም ተግባር የተጠቀሙ ሰዎችን ያመሰግናል፣በርቱልኝ ይላል።

በስድስቱ ዘርፎች የእርሶዎ በጎ አድራጊ ማነው?

https://vote.thmediagroups.com/

ከላይ ባለው ሊንክ ይጠቁምን ግንቦት 30 በክብር እናመሰግንልዎታለን።
2025/07/07 22:44:24
Back to Top
HTML Embed Code: