📌የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ
የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙያዊ ውይይት ተካሂዷል።
ዝግጅቱ በአካዳሚው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ የእንኳን በደህና መጣችሁ ንግግር የተከፈተ ሲሆን አካዳሚው ይህንን መሰል ለፖሊስ ግብዓትነት የሚጠቅሙ እና ሙያዊ ተዋስዖዎችን ለመፍጠር አበክሮ እንደሚሠራ አስታውሰዋል፡፡
ውይይቱ በፕሮፌሰር ዘላለም ልየው እየተመራ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ እና አቶ ይኩኖ አምላክ መዝገቡ፥ የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ ሊኖረው ስለሚገባው ሚና እና የመማርና ማስተማር ሥርዓት የመነሻ ሐሳቦቻቸውን በማቅረብ ከታዳሚያን ጋር ሰፋ ያለ የውይይት ጊዜን አሳልፈዋል፡፡
በዚህ ዝግጅት ላይ የአካዳሚው ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የአካዳሚው አባላት፣ ተመራማሪዎች፣ ፖሊስ አውጪዎች እና በጉዳዩ ላይ ፍላጎት ያላቸው ታዳሚያን በአካልና በበይነ መረብ ታድመዋል፡፡
የዚህ ውይይት ሙሉ ቪዲዮ ከጥቂት ቀናት በኋላ በአካዳሚው የዩቲዩብ ቻናል እና የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተጭኖ ለተመልካች ይቀርባል፡፡
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

👍7❤5👏4
  📌"ቼኑ" ጥናታዊ ፊልም ጥቅምት 3 ይመረቃል 
"ቼኑ" ጥናታዊ ፊልም የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይመረቃል።
"ቼኑ" ጥናታዊ ፊልም ደጀኑ በቀለ በሚባል እና ቄራ ሰፈር ተወልዶ ስላደገው አንድ ኢትዮጵያዊ የ60 ዓመት ጎልማሳ ግለሰብ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ነው።
"ቼኑ" ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታትና 6 ሚሊየን ብር ገደማ ፈጅቷል። ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ አቀራረብና ዝግጅት ይዞ የቀረበው ፊልሙ ለሀገርም ለወገንም ታሪክን ሰንዶ ማስቀመጥ ያለውን ከፍተኛ ሀገራዊ ሚና የሚያሳይና ውድ የሆነ የህይወት ልምድን ለአሁኑ ትውልድ አስተምሮ የሚያልፍ ጥናታዊ ፊልም ነው ሲሉ የፊልሙ ባለታሪክ አቶ ደጀኑ በቀለ ተናግረዋል።
"ቼኑ" ፊልም በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ፊልም ሲሆን፣ የ2 ሰዓት ርዝመት ያለው ዶክመንተሪ ፊልም መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ጥናታዊ ፊልም ለመስራት መነሻው ምክንያት የደጀኑን አስገራሚ ህይወት ለሌሎች ማስቃኘት ነው ያለው የፊልሙ ዳይሬክተር ይድነቃቸው ዓይኔ፥ ታሪኩ የሚያስተምርና ፋይዳው ለማህበረሰቡ ላቅ ያለ ነው ብሏል።
ማስታወሻ: የዚህን ጥናታዊ ፊልም ምረቃ የመግቢያ ትኬት ለ10 ቤተሰቦቻችን በክብር እንሸልማለን።

❤21👍6🔥2
  📌አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመረቀ
"አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ" የተሰኘ ባለ 15 ወለል የሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመረቀ ።
በ24,000 ካ.ሜ ላይ ያረፈው "አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ" ባለ አራት ወለል የመኪና ማቆሚያ 592 ህፃናትንና 887 አዋቂዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የሲኒማ አዳራሾችን ከሙሉ መገልገያዎች ጋር የያዘ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርብ ጊዜ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን አስመርቆ እንደነበር ይታወሳል።

❤10
  📌የደራሲ አዳም ረታ ተወዳጅ መጽሐፍ ተተረጎመ 
ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው የደራሲ አዳም ረታ መጽሐፍ "እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ" የተሰኘው መጽሐፉ ነው።
ወደ እንግሊዝኛ ስትረጎመም "Couch grass" በሚል ርዕስ እንደሆነም ሰምተናል።
መጽሐፉን በእንግሊዝኛ ቋንቋ በተርጓሚነት የምታቀርበው ቤተልሄም አትፊልድ ትባላለች።
በማህበራዊ ትስስር ገጿም "እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ የተሰኘው የደራሲ አዳም ረታን መጽሐፍን "Couch grass" በሚል ርዕስ ተርጉሜ በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚታተም ሳበስራችው ደስ ብሎኛል" ብላለች።
በተጨማሪም ተርጓሚዋ አራት ተረኮችን እንዳካተተችም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ" መጽሐፍ በውስጡ ከአጭር ልቦለድ ከፍ ከረጅም ልቦለድ ዝቅ ያሉ 7 ታሪኮችን ይዟል።
ከዓመታት በፊትም በአብርሃም ገዛኸኝ አዘጋጅነት "የሎሚ ሽታ" በሚል ርዕስ ወደ ፊልም ተቀይሮ ለተመልካቾች ቀርቧል።
ደራሲ አዳም ረታ ደራሲ "መዝሙረ ሄላዊ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርባለው ካለ አንድ ዓመት አልፎታል።

❤22🥰2
  📌ሀጅ ዑመር ኢድሪስ (ሙፍቲ) በጠና ታመሙ 
ሀጅ ዑመር ኢድሪስ (ሙፍቲ) በጠና መታመማቸው ተሰምቷል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሀጅ ዑመር ኢድሪስ (ሙፍቲ) የጤና እክል ገጥሟቸዉ ለህክምና ወደ ቱርክ ሀገር መሄዳቸውም ተነግሯል።
ሀጅ ዑመር ኢድሪስ ያጋጠማቸው የጤና እክል ምንነት እስካሁን በይፋ አልተነገረም።
የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሀጅ ዑመር ኢድሪስ (ሙፍቲ) ከገጠማቸው የጤና እክል አላህ አፊያ እንዲያረጋቸው ዱአ እንዲደረግላቸው ጥሪ ቀርቧል።
Via ነጃሺ ቲቪ

🙏26😭9❤6👍5🥰4👏1
  📌የአንጋፋው ሰዓሊ ወርቁ ማሞ ልጅ በሆነቸው በወጣቷ ሰዓሊ ገብርኤልዋ ወርቁ ማሞ የተዘጋጁ የሥዕል ስራዎች ብቻ የሚቀርቡበት "ከልብስ ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው።
ይህ የሥዕል አውደርዕይ ጥቅምት 8 2018 ዓ.ም በአርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።
ሠዓሊዋ በዚህ የሥዕል አውደርዕይዋ ላይ "የሰው ልጅ ከልብሱ በላይ ዋጋ የለውም ወይ?" በማለት ጠይቃለች።
ጥቅምት 8 የሚከፈተው አውደርዕይው እስከ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
ይህ የሥዕል አውደርዕይ ጥቅምት 8 2018 ዓ.ም በአርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።
ሠዓሊዋ በዚህ የሥዕል አውደርዕይዋ ላይ "የሰው ልጅ ከልብሱ በላይ ዋጋ የለውም ወይ?" በማለት ጠይቃለች።
ጥቅምት 8 የሚከፈተው አውደርዕይው እስከ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
👍13❤10
  📌OBN የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግን በነፃ አሳያለሁ አለ
የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ውድድር በነፃ ለተመልካች እንደሚያስመለክት በይፋ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከዚህ በፊት በዲኤስቲቪ በክፍያ ሲተላለፍ የቆየ ሲሆን በቀጣይ በነፃ ለተመልካች ይደርሳል።
OBN የውጭ እና ሀገር ውስጥ ሚዲያዎችን ተወዳድሮ በማሸነፍ የሊጉን የስርጭት መብት መግዛቱን በይፋ አሳውቋል።
ዲኤስቲቪ በመጨረሻ የሊጉ አመታት ቆይታው በ OBN የፕሮዳክሽን መሳሪያዎች ተከራይቶ ሊጉን ሲያሳይ እንደነበር ይታወቃል።
በርካታ ተመልካቾች ያሉት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀገራችን ሚዲያ በነፃ መቅረቡ ለስፖርቱ ተመልካቾች መልካም ዜና ሆኗል።
በስምምነቱ ዙሪያ ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

😁16❤7😍3👎2🤣2👍1👏1💩1
  📌 የኃይሉ አመርጋ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ታወቀ 
ድምጻዊ ኃይሉ አመርጋ ከተራራው ማዶ፣ እንግዳ፣ ይነጋል፣ ማርዬ፣ ይገርማል የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ አስር ያህል ሥራዎችን በጃኖ ባንድ በኩል መዋጮ አድርጎ።
ከጃኖ ባንድ ባንድ መፈርስ በኃላ ከኃይሉ አመርጋ በቀር 3ቱ የባንዱ ድምጻዊያን በየፊናቸው የራሳቸውን የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች አቅረበዋል።
በሙዚቃ ወዳጆችም ዘንድ የኃይሉ አመርጋ የሙዚቃ አልበም መቼ ነው የሚለቀቀው የሚሉ ጥያቄዎች ለድምጻዊው ሲቀርቡ ቆይተዋል።
ለዚህም ጥያቄ በመጨረሻም አልበሙ ለአድማጮች የሚቀርብበት ቀን ታወቋል።
ድምጻዊው በግሉ የሰራው የመጀመሪያ አልበሙ ጥቅምት 21 2018 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአልበሙን ስራ ለመከውን ስድስት ዓመታት እንደፈጀ የተነገረለት አልበሙ "አሁን " የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።
ከመለቀቁ በፊትም ጥቅምት 18 2018 ዓ.ም የሙዚቃ ማድመጭ መሰናድ እንደተዘጋጀለትም ሰምተናል።

❤36🔥6
  📌ታላቁ አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ አረፉ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት የክብር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት የክብር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
😢45💔7❤6😭3
  📌"ጀሚላ" የተሰኘ ፊልም ዛሬ ይመረቃል 
በዜማ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በካብ ኢንተርቴይመንት አቅራቢነት ለእይታ የሚቀረበው ይህ ፊልም ድርሰትና ዝግጅቱ የደራሲና ዳይሬክተር ፀጋ ካህሳይ (ጃምቦ ) ነው።
የፊልሙ ጭብጡም እንደ ሃገር እንደ ቤተሰብ በፍቅር ተዋዶና ተፈላልጎ የመኖር ነባር ቤተሰባዊ ባህላችንን በማጠናከር ዙሪያ የሚያጠነጥን የፍቅር ፊልም ነው።
የ“ጀሚላ” ፊልምን ስራዎችን ለመከወን ከሁለት አመት በላይ እንደፈጀ የተነገረ ሲሆን 1:35 ደቂቃ የሚፈጅ የቆይታ ጊዜ አለው።
በትወና አዳዲስና ነባር ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን ሄኖክ አለማየሁ፣ነፃነት አንበርብር
ምህረት በለጠ ፣ቁምላቸው አዱኛ(ከድር ሰተቴ) ሌሎችም ተሳታፈዋል።
ጀሚላ ፊልም ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 10 2018 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዓለም ሲኒማ ከ11:00 ጀምሮ ይመረቃል።

❤5👍4
  📌ታሪካዊው አንበሳ መድሐኒት ቤት ፈረሰ
አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ የሚገኘዉ እድሜ ጠገቡ አንበሳ ፋርማሲ መፍረሱን ቅዳሜ ገበያ በስፍራው ተገኝታ አረጋግጣለች።
እየፈረሰ ያለው አንበሳ ፋርማሲ ከተመሰረተ 80ኛ ዓመቱን የያዘና ጥንታዊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በጀርመናዉያን ሁለተኛ እና በሦስተኛ ትዉልድ እየተንቀሳቀሰ የነበረው አንጋፋዉ አንበሳ መድሐኒት ቤት የመድሐኒት ሽያጭና ቅመማ ብቻ ሳይሆን የሕክምና ቁሳቁስ አስመጭና አገር ውስጥ አከፋፋይም ነበር ።
ከዓመታት በፊት አንበሳ ፋርማሲ ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የጀርመን ኤምባሲ የአንበሳ መድሐኒት ቤትን ድጋፍ መስጠትን ይመለከታል በሚል ለአዲስ አበባ ከተማ የወቅቱ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፃፈዉ ደብዳቤ አዲስ አበባን ብሎም ኢትዮጵያን የጀርመን የመዋለ ንዋይ ፍሰት መዳረሻ ለማድረግ እንደሚያበረታታ አንድ ኤምባሲ፤ ጉዳዩ ሕጋዊ መንገድን መከተል አለበት ብለን እናምናለን። ምክንያቱም በእድሜ ጠገቡ የአንበሳ መድሐኒት ቤት ላይ አስተዳደሩ ይወስዳል የተባለዉ ርምጃ ሌሎች የጀርመን ባለ ኃብቶችን ሊያሸሽ ይችላል ሲል ደብዳቤ ማግባቱ በወቅቱ ተዘግቧል።
 
አንበሳ ፋርማሲ የሚገኝበት አነስተኛ ህንጻ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሆን ከአመታት በፊት ከአካባቢ ልማት ጋር በተያያዘ ፋርማሲው ይፈርሳል ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ፍጹም ከእውነታው የራቀና መሰረተ ቢስ መረጃ ነው ሲል ኮርፖሬሽኑ ማስተባበሉ የሚታወስ ነው።
Via ቅዳሜ ገበያ

😭6❤3
  📌የጋዜጠኝነት ስልጠና ለሰልጣኞች 
ጋዜጠኝነትን መማርና ጋዜጠኛ መሆን ህልማችሁ ከሆነ ልጠቁማችሁና ወደሴጅ ጎራ በሉ።
ደግሞ 6 ወር ብቻ በቂ እንደሆነ ሰምቻለሁ።
ስልጠናው ልምድ ባላቸውና የሚዲያውን ዓለም በሚያውቁት መምህራን ይሰጣል። ተጋባዥ እውቅ ጋዜጠኞችም ከልምዳቸው ያካፍላሉ።
9ኛ ዙር ላይ ደርሰው አሁንም ለ10ኛ ዙር አዳዲስ ሰልጣኞችን እየመዘገቡ ነውና እንዳያመልጣችሁ።
ጋዜጠኝነቱን ለይቼ ጠቆምኳቹ እንጂ ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከ30 በላይ በሆኑ ዘርፎች ስልጠና ይሰጣል።
ሴጅ ላለፉት ዓመታት በማሰልጠን በሙያ ምዘና ብቃት አስመዝኖ በማብቃት ለገበያው ተወዳዳሪ የሆነ ባለሙያዎች በማበርከት ላይ የሚገኝም ተቋም ነው።
ከታች ካሉት አድራሻዎች በተጨማሪ በማስፈንጠሪያዉም ጎብኟቸው።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Threads: https://www.threads.net/@sage_training_institute

❤11👍3👎2
  📌 አሻም ቴሌቪዥን ታሸገ
በአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የሚተዳደረው "አሻም ቴሌቪዥን" ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም እንደታሸገ ኤቨንት አዲስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የቴሌቪዥን ጣቢያው በምን ምክንያት እንደታሸገ ለጊዜው አልታወቀም።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የሚተዳደረው "አሻም ቴሌቪዥን" ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም እንደታሸገ ኤቨንት አዲስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የቴሌቪዥን ጣቢያው በምን ምክንያት እንደታሸገ ለጊዜው አልታወቀም።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
🙊8❤5😱2
  📌 "ኑ እንጫወት ልብ እንጠግን" ልዩ መርሐግብር 
በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል እየተጫወትን የህጻናትን ልብ ለመጠገን ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ ፈስቲቫል ለሕፃናት እና ለታዳጊዎች ተዘጋጅቷል።
ፌስቲቫሉ ልባቸውን ለመታከም ወረፋ በመጠበቅ ላይ ላሉ ሕፃናት ገቢ ለማሰባሰብ እና ለማህበረሰብ ደሞ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዓላማ ያደረገ ነው።
ለሕጻናት እና ለታዳጊዎች የተዘጋጀው ፌስቲቫሉ ቅዳሜ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በአምባሳደር ፓርክ ከጠዋት 4፡00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል እየተጫወትን የህጻናትን ልብ ለመጠገን ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ ፈስቲቫል ለሕፃናት እና ለታዳጊዎች ተዘጋጅቷል።
ፌስቲቫሉ ልባቸውን ለመታከም ወረፋ በመጠበቅ ላይ ላሉ ሕፃናት ገቢ ለማሰባሰብ እና ለማህበረሰብ ደሞ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዓላማ ያደረገ ነው።
ለሕጻናት እና ለታዳጊዎች የተዘጋጀው ፌስቲቫሉ ቅዳሜ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በአምባሳደር ፓርክ ከጠዋት 4፡00 ጀምሮ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
❤7👍2
  📌ጥበብና የአእምሮ ጤና አውደርዕይ መዝጊያ 
በሜታል ሄልዝ አዲስ የተዘጋጀውና የአእምሮ ጤና ላይ ትኩረት ያደረጉ የሥዕል ስራዎችየቀረቡበት አውደርዕይ በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ውስጥ ሲካሄድ ቆይቷል።
በዚህ "Art inspired by mental health" በሚል ርዕስ በተካሄደ አውደርዕይ ላይ የሠዓሊ ሶሎሜ ጌታቸው፣ የሠዓሊ አለማየሁ ደረሰማ ሥዕሎች ቀረበዋል።
ይህ የሥዕል አውደርዕይ አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች የመዝጊያ ሥነሥርዓቱ ይከናወናል ተብሏል።

❤6
  📌በጣቢያው ባለቤት የታሸገው አሻም ቴሌቪዥን 
አሻም ቴሌቪዥን ከትላንትና ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጣቢያው ባለቤቶች እንደታሽገ ጣቢያው ከአሰራጨው መግለጫ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።
አሻም በመግለጫው "የቴሌቪዥን ጣቢያው ከረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የጣቢያውን መደበኛ ስርጭት ማከናወን አልተቻለም።ችግሩን ለመቅረፍ የሚዲያው አስተዳደር ጥረቶች እያደረገ ይገኛል:: ያጋጠመው ችግር እስኪስተካከል በሚል አስተዳደሩ በካሜራና መሰል የሚዲያው ንብረቶች እንዳይንቀሳቀሱ ፤ የውስጥ ንብረት ክፍሉን አሽጓል" ሲል አስታውቋል።
ጣቢያው ይህንን ይበል እንጂ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያው ሰራተኛ ከቅርብ ወራት ወዲህ በጣቢያው ምን እንደተፈጠረ እንዲህ ሲል ያብራራል "ከቅርብ ግዜ ( ከ5 ወይ 6 ወር ) ወዲህ ምን እንደሆነ ባናዉቅም (የሚነገረን ምክንያት ብር የለንም ብቻ ነበር ) ቤቱ የሰራተኛን ደሞዝ በማቆየት እና ከዛም ባለፈ እስከ 2 ወራት ባለመክፈል ቆይቷል።
እኛም የገጠመውን ችግር በመረዳት በተደጋጋሚ ደሞዙን ሳይጠይቅ በገባለት ሰዓት ጠብቀናል። በሚዲያው ዉስጥ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ፣ ተከራይ እና ብዙ ወጪዎች ያሉበት ሰራተኛ እንደመኖሩ ለወራት በችግር አሳልፈናል። የሆነዉ ሆኖ ነገሮች ተስተካከሉ ስንል እየባሱ በመምጣታቸዉ በድጋሜ በመስከረም ወር ጀምሮ የሁለት ወር ደሞዛችን እንዲገባና ጥያቄ ብናቀርብም '' በዚህ ሰዓት መክፈል አንችልም፣ከዚህ በኋላ ለአንድ ወር ጠብቁ '' የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።ከዚህ ባለፈ የሰራንበትን የስራ ልምድ ብንጠይቅም ሊሰጡን አልቻሉም" ሲል ተናግሯል።

❤20🤔5😁2
  📌የዶቸ ቬለ ዘጋቢዎች እንዳይዘግቡ ለጊዜዉ ታገዱ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለዶቸ ቬለ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ዘገባ እንዳይሰሩ ለጊዜዉ አገዱ።
ዶቸ ቬለ ከ1980ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ ዘጋቢዎች አማካኝነት የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሐብታዊና ማሕበራዊ ጉዳዮችን እና የአፍሪቃ ሕብረትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ አካባቢያዊ፣ አሐጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ተቋማትና ማሕበራትን እንቅስቃሴና ክንዋኔዎችን ሲዘግብ ቆይቷል።
ዓለምአቀፉ ማሰራጪያ ጣቢያ ከ 2010 ጀምሮ የወኪሎቹን ቁጥር በማሳደግ መቀሌ፣ ባሕርዳር፣ ደሴ፣ አዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋና አሶሳ በሚገኙ 9 ወኪሎቹ አማካይነት መረጃዎችን በማሰባሰብ ገለልተኛ፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ ዘገባዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያሰራጫል። ይሁንና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ በፃፈዉ ደብዳቤዉ ዶቼ ቬለና ወኪሎቹን የኢትዮጵያን ሕግና ደንብ ጥሰዋል፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን አያከብሩም በማለት ወቅሷል።
ከዛሬ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚገኙ የዶቸ ቬለ ዘጋቢዎችን የሥራ ፈቃድ ለጊዜዉ ማገዱን አስታዉቋል። ባለሥልጣኑ «ጊዚያዊ» ያለዉ እግዳ ሥለሚቆይበት ጊዜ የገለፀዉ ነገር የለም።

❤4🤔4👍2
  📌አቤ ከቤ ከአሰላ እውቅና ተሰጠው
በተለያዩ የሬድዮ ጣቢያዎች እና የሬዲዮ ፕሮግራሞች ላይ በንቁ ተሳታፊነቱ ዝነኛ የሆነው አቤ ከቤ ከአሰላ በትውልድ ከተማው አሰላ በOptical Art Acadamy አማካኝነት የዕውቅና ሰርተፍኬትና ሜዳሊያ ተበርክቶለታል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በተለያዩ የሬድዮ ጣቢያዎች እና የሬዲዮ ፕሮግራሞች ላይ በንቁ ተሳታፊነቱ ዝነኛ የሆነው አቤ ከቤ ከአሰላ በትውልድ ከተማው አሰላ በOptical Art Acadamy አማካኝነት የዕውቅና ሰርተፍኬትና ሜዳሊያ ተበርክቶለታል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
❤20👏5👍4
  📌የአንጋፋው አርቲስት ተክሌ ደስታ የመኖሪያ ቤት በዕዳ ምክንያት የሐራጅ ጨረታ ወጣበት 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአርቲስት ተክሌ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ጨረታ ያወጣባቸው ሚድ ትሬዲንግ ለሚባል ድርጅት ለወሰደው ብድር ቤታቸውን መያዣ በማድረጋቸውንና ድርጅቱ ብድሩን በአግባቡ ባለመመለሱ ነው።
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጠቢብ ተክሌ ደስታ " ድመቷን ማን ገደላት? " የሚል ተወዳጅ የቴሌቪዥን ድራማ ደራሲ የአንድን መ/ቤት መዝገብ ቤት አይጥ አስቸግሮ ድመት ሊገዛ ተፈልጎ " ድመቷ በየትኛው የመ/ቤቱ ህግ ትተዳደር ? በምን መዝገብ ላይ ትስፈር ? ለቀለቧ በጀት እንዴት ይያዝ ? " አይነት ሀሳቦች የተነሱበት የምን ጊዜም ምርጥ ሥራ ይታወቃሉ።
©️ድሬቲዩብ

😢29❤2👍1
  📌'ባልቻ አባነፍሶ' ተውኔት ወደ መድረክ ሊመለስ ነው
የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ተውኔት ማሳየት ሊጀምር እንደሆነ ተሰምቷል።
ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ባልተለመደ መልኩ ከተውኔት ደራሲያን እና ከተውኔት አዘጋጆች ጋር ልዩ ልዩ ስምምነቶችን ሲፈፅም የኤቨንት አዲስ ሚዲያ አዘጋጆች ተመልክተናል።
በዚህ የስምምነት ሥነሥርዓት ላይ ከተሰሙ ጉዳዮች በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ከዓመታት በኃላ ተውኔት ማሳየት ሊጀምር እንደሆነ የተገለጸበት ጉዳይ አንደኛው ነው።
የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ወደ ወደ መደበኛው ስራ ሲመለስም የ"ባልቻ አባነፍሶ" ቴአትርን ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ አምርቶ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለተመልካች እንደሚያቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"ባልቻ አባነብሶ" ታሪካዊ ተውኔት እንዲዘጋጅም ስምምነት ተፈጽሟል። የዚህ አዲስ ድርሰት መራሔ ተውኔት በመሆን አዘጋጅ ዶ/ር ተሻለ አሠፋ የስምምነት ፊርማውን አስፍሯል።
ሌላ በኩል የደራሲ መልካሙ ዘሪሁን ድርሰት የሆነው "ወህኒ አምባ" የተባለውን አዲስ ወጥ ተውኔትን ወደ መድረክ ለማምጣት ስምምነት ተፈጽሟል።
ለዚህ አዲስ ድርሰት መራሔ ተውኔት በመሆን አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ የስምምነት ፊርማውን አስፍሯል። የዚህ ተውኔትም ልምምድ በይፋ ተጀምሯል።'ወህኒ አምባ' ተውኔት በሦስት ወራት ውስጥ ተሠርቶ እንደሚጠናቀቅ ተነግሯል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በ2018 ዓ.ም ለተመልካች የሚያቀርበውን የኦሮምኛ "ሰዴተ" የተሰኘ የሙሉ ጊዜ የኦሮምኛ ተውኔት ለመመድረክ ተስማምቷል።

❤18👏3✍1