📌"የተመለሱ እይታዎች" አውደርዕይ ተከፈተ
የሠዓሊ ኪሩቤል ተፈሪ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "የተመለሱ እይታዎች" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ትላንትና ረቡዕ መስከረም 7 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።
ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥቅምት 3 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

❤7
📌ሸገር ጋዜጠኞቼ ከታሰሩ 17 ቀናት ሆናቸው አለ
የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች፣ አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው፣ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቁጥጥር ስር ከዋሉ 17 ቀን ሆናቸው።
የፌዴራል ፖሊስ፣ ጋዜጠኞቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፣ ያሰራጩት ዘገባ በሕግ የተከለከለ ይዘት ያለውና የሽብር ድርጊት ነው ብሎ እንደሆነ፣ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቅድለት፣ ባቀረበው ማመልከቻ ጠቁሟል፡፡
የሕክምና ባለሞያዎች፣ ለመንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ፣ የጤና ሚኒስቴር በሰርኩላር ያስተላለፈውን መፍትሄ፣ እንዴት እንደሚመለከቱት፣ የሕክምና ባለሞያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ ነሐሴ 24 በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ፣ ዜናው ተላልፎ ነበር፡፡
በዚሁ ዜና ምክንያት የፌዴራል ፖሊስ፣ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ፀጋውን፣ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ፣ ምክንያቱን ዘርዝሮ፣ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በመጠየቁ፣ ፍርድ ቤቱ ዘጠኝ ቀን ፈቅዶለት ነበር፡፡
በቀጣዩ ቀጠሮ፣ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ፣ የገንዘብ ዝውውራቸውን እና ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስን ምክንያትና ከጋዜጠኞቹ የቀረበውን መከራከሪያ ያዳመጠው፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ፣ ጋዜጠኞቹ በ50,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በትዕዛዙ መሰረት፣ መስከረም 7/2018 ከሰዓት በኋላ፣ አስፈላጊው ፎርማሊቲ ተሟልቶ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ደርሶታል፡፡
ይሁንና፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሳኔ በይግባኝ፣ ወደ ፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመወሰዱ፣ ለመስከረም 12/2018 ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

❤9🤬3👍1👎1🤔1😢1
📌 አዳብና ፌስቲቫል በሁለት ከተሞች ይከበራል
የ2018 የክስታኔ አዳብና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እና ኬላ ከተሞች በድምቀት እንደሚከበር ተነገረ።
አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት አዳብና በፌስቲቫል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ይካሄዳል።
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ ጥቅምት 02 2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ቀደም ብሎ መስከረም 24 2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ተነግሯል።
የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ሥነሥርዓት ሲሆን 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።
አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
መላው ኢትዮጵያውያን መስከረም 24 ኬላ እና ጥቅምት 02 በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን ፌስቲቫል ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርበዋል።

❤9
የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1. አንጋፋዋ ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዓመታት በኃላ በልዩ የሙዚቃ ድግስ በአዲስ አበባ ከአድናቂዎቹ ልትገናኝ ነው።
2.ሙዚቀኛ ጆኒ ራጋ "ቁልፉን ስጪኝ" የተሰኘው አልበሙን በለቀቀ በ20 ዓመቱ በተመሳሳይ ቀን ሁለተኛ አልበሙን ለአድማጮች ሊያቀርብ ነው።
3.ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍትን በማዘጋጀትና በማሳተም ለማሰራጨት የሚያስችለውን “ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ” የተሰኘ አሳታሚ ድርጅት ማቋቋሙን አስታወቀ።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/pwk3_pkRRns?si=gvLwt3jpjJ05Kjhm
📌መልካም ምሽት

❤9👏7
📌ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ ነው
የሕዳሴ ግድብ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ እንደሆነ ተሰምቷል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከሰኞ መስከረም 12 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ በማድረግ መጎብኘት ይቻላል አሉ።
ሚኒስትሯ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪስት መስህቦችን ጎብኝተዋል።
በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ጎብኝዎች ሕዳሴ ግድብን በአንድ ጊዜ 50 በመሆን መጎብኘት ይችላሉ።
ምዝገባው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል እንደሚሆን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል ሲል FMC ዘግቧል።

❤7👍3🥰2👎1
📌ሶፊ ዛሬ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር ይዳኛል
ኢትዮጵያን ጨምሮ 23 ሀገሮች የሚሳተፉበት "ኢንተርቪዥን ሶንግ ኮንቴስት 2025" ላይ ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) ኢትዮጵያን ወክሎ በዳኝነት ይሳተፋል::
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የወከለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊም መሆን ችሏል::
ይህ ውድድር ዛሬ ማታ በቀጥታ ስርጭት በባላገሩ ቲቪ፣ ፌስቡክ እና ዩትዩብ ቻናል ይተላለፋል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
ኢትዮጵያን ጨምሮ 23 ሀገሮች የሚሳተፉበት "ኢንተርቪዥን ሶንግ ኮንቴስት 2025" ላይ ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) ኢትዮጵያን ወክሎ በዳኝነት ይሳተፋል::
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የወከለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊም መሆን ችሏል::
ይህ ውድድር ዛሬ ማታ በቀጥታ ስርጭት በባላገሩ ቲቪ፣ ፌስቡክ እና ዩትዩብ ቻናል ይተላለፋል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
❤14👍2
📌አሰፋ ጫቦን የሚዘክር ቤተ-መጽሐፍት ተመረቀ
"ጋሞነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ጋር ተጋጭቶብኝ አያውቅም " በሚለው ንግግራቸው የምናውቃቸው የህግ ባለሙያ፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ፣ ደራሲና ፖለቲከኛ ጋሽ አሰፋ ጫቦን የሚዘክር ቤተ-መጽሐፍት በጋሞ ባሕል ማዕከል ተመርቆ ተከፍቷል።
በመርሃግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የጋሽ አሰፋ ጫቦ ቤተሰቦች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"ጋሞነቴ ከኢትዮጵያዊነቴ ጋር ተጋጭቶብኝ አያውቅም " በሚለው ንግግራቸው የምናውቃቸው የህግ ባለሙያ፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ፣ ደራሲና ፖለቲከኛ ጋሽ አሰፋ ጫቦን የሚዘክር ቤተ-መጽሐፍት በጋሞ ባሕል ማዕከል ተመርቆ ተከፍቷል።
በመርሃግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የጋሽ አሰፋ ጫቦ ቤተሰቦች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
❤12🙏5🔥1🥰1
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቷል
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (አዲስ ዘመን፣ ጋዜጣ+፣ በሪሳ ) ለስራ ተወዳደሩ ማስታወቂያ አውጥቷል። የዚህ ተቋም ባልደረባ መሆን የምትፈልጉ ተወዳደሩ፣ ይቅናችሁ እንላለን።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (አዲስ ዘመን፣ ጋዜጣ+፣ በሪሳ ) ለስራ ተወዳደሩ ማስታወቂያ አውጥቷል። የዚህ ተቋም ባልደረባ መሆን የምትፈልጉ ተወዳደሩ፣ ይቅናችሁ እንላለን።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
❤5👍1
📌የሸገር ጋዜጠኞች ከእስር ተፈተዋል
የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛው ችሎት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በዋስ እንዲለቀቁ የስር
ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል።
ጋዜጠኞቹ በዋስ እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ከሰዓት በ21ኛ ቀናቸው ከእስር ተለቀዋል።
የፌዴራሉ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ፣ጋዜጠኞቹን ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት፣ ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ነገሩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ መስከረም 14 ቀን 2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡
ጋዜጠኞችቹ ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በቁጥጥር ስር በዋሉ 21ኛው ቀን በተለዋጩ ቀጠሮ ቀን ፣ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የስር ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ የሰጠው ውሳኔ አፅድቆ መዝገቡን ዘግቷል፡፡
በውሳኔው መሰረት ዛሬ ከሰዓት ከእስር ተለቀዋል።

❤14👏6🤔1
📌አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በአሜሪካ ኤምባሲ ልዩ እንግዳ በመሆን ይቀርባል
(መግቢያው በነፃ ነው)
በዘጠነኛው የCREATOR LAB ዝግጅት ላይ የፊልም ተዋናይ፣ደራሲ፣ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዩሰር የሆነው ሚካኤል ሚሊዮን እንግዳ በመሆን ይቀርባል።
አዘጋጆቹም ተከታዩን ብለዋል"ከሚኪ ጋር በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 20 2018 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል። ሰለሆነም በዚህ መድረክ ላይ እንዲታደሙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ተዋናይ ፤ ደራሲ እንዲሁም አዘጋጅ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ እና በሙያው ላይ ልምድ ያላችሁ ባለሙያዎች በሙሉ ይህ የመገናኛ ዕድል ለእናንተ ነው።
📍አድራሻ ፡ አሜሪካን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
📅 ቀን: ነገ ማክሰኞ - መስከረም 20 ፣ 2018
🕗 ሰዓት:ከቀኑ - 8:00
🎟 መግቢያ: ነፃ
አቅራቢ፦ ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር
በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ኢንስታግራም ገፃችንን ፎሎ ማድረግ እንዳይረሱ
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ ዐባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

❤9👍2👎1
📌የጆኒ ራጋ የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ
የድምጻዊ ጆኒ ራጋ “ውሃ እና እሳት" የተሰኘ ሁለተኛ አልበም ከ20 ዓመታት በኃላ ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም በጆኒ ራጋ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።
ጆኒ ራጋ 16 ሙዚቃዎችን በያዘው አዲስ አልበሙ ከአንጋፋ እስከ ወጣት ድምጻውያን በጋራ ሰርቷል።
ከእነዚህም መካከል ባህታ ገብረሕይወት፣ ዮሐና፣ ናቲማን፣ ልጅ ሚካኤል፣ ኤደን አይሸሸም ፣ ዮሴፍ ኤቢሶ እና ኤቨርሬጽ ተሳትፈዋል።
የ"ውሃ እና እሳት" አልበም ግጥም፣ ዜማ እና ቅንብር በራሱ በጆኒ ራጋ የተሰናዳ ሲሆን ፍቅር፣ ትዝታ፣ ፍርድ የጾታ እኩልነት እና ሕይወት በውሃ እና እሳት አልበም ከተነሱ ርዕሶች መሃል የሚጠቀሱ ናቸው።
ስቱድዮ ውስጥ የተቀረጹ መሳሪያዎችን ባካተተው በዚህ አልበም አንጋፋው ሙዚቀኛ ቶሚ ቲ (ቶማስ ጎበና) አሻራውን ያሳረፈበት ሲሆን እንደቀድሞ ሥራው ሁሉ በመላው ዓለም በጥራት መደመጥ እንዲችል ሚክሲንግ እና ማስተሪንጉ የተለያዩ አገሮች በሚገኙ የተመረጡ ስቱድዮዎች ተከውኗል።

❤15👍2
📌ያንጎ ኢትዮጵያ እና ጆኒ ራጋ ተፈራረሙ
ያንጎ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ በታላቅ ዝግጅት ተመልሶ ከመጣው አንጋፋው የኢትዮጵያ ድምፃዊ ጆኒ ራጋ ጋር "ውሃ እና እሳት" በተሰኘው አዲስ አልበሙ ላይ አብሮ መስራቱን አስታውቋል።
ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳጅ ከሆኑ ድምፃውያን መካከል የአንዱን መመለስ ከማክበሩም በተጨማሪ፣ ያንጎ የአገር ውስጥ ተሰጥኦዎችን እና የባህል መገለጫዎችን ለመደገፍ ያለውን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት ያሳያል።
በያንጎ የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ይቅናአለም አበበ ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ፥ "የጆኒ ራጋ ሙዚቃ ሁሌም የኢትዮጵያን መንፈስ እና ነፍስ የሚወክል ነው"ብለዋል።
ይህ ትብብር ከመዝናኛ በላይ የሆነው ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ጥልቅ ግንኙነት እና ያንጎን የዕለት ተዕለት ሕይወታቸው አካል ላደረጉት አሽከርካሪዎቻችን፣ ደንበኞቻችን እና አድናቂዎቻችን ያለንን ክብር የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
ጆኒ ራጋ በበኩሉ "ከያንጎ ጋር ያለው ይህ ትብብር ስለ ዳግም መመለሴ አልበም ብቻ አይደለም፤ ፅናትን፣ ማህበረሰብን እና የኢትዮጵያን ሙዚቃ ጉዞን ስለማክበር ጭምር ነው። ላለፉት 20 ዓመታት፣ የኮንሰርት ጉብኝቶቺ እና የቀጥታ ስርጭት ትርኢቶች ወቅት ከጎኔ ለነበሩኝ ታማኝ አድናቂዎቼ ምስጋና ይገባቸዋል፤ በተለይም ለአርቲስቶች መብት እና በኢትዮጵያ የሮያሊቲ ክፍያ እንዲጀመር በምታገልበት ወቅት ከጎኔ ነበሩ። አልበሜ፣ የተረጋጋ መንፈስን እና አስደሳች በዓላትን የሚተርኩ ታሪኮችን በማጋራት ለሙዚቃ ቤተሰቤ ውለታውን መመለስ እፈልጋለሁ" ብሏል።
በዚህ አጋርነት ያንጎ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን፣ አሽከርካሪዎችን እና ሰፊውን ማህበረሰብ የጆኒ ራጋን መመለስ በደስታ እንዲቀበሉ እና በ"ውሃ እና እሳት" አልበም እንዲዝናኑ ይጋብዛል።

👍7❤3
📌በጋዜጠኛ አፈወርቅ እያዩ የተፃፈው "ቻይና በጋዜጠኛው ዓይን" መጽሐፍ ለንባብ በቃ
የጉዞ ማስታወሻ ይዘት ያለው መፅሀፉ የቻይና የእድገትና ስልጣኔ ምስጢሮችን ከኢትዮጵያ አንፃር ይዳስሳል።
አፈወርቅ ወደ ቻይና ለስራ ላይ ስልጠና ተጉዞ የነበረ ሲሆን በቻይና ዴይሊ፣ ግሎባል ታይምስና ሲጂቲኤን ፅሁፎቹ ታትመዋል። ሁለት ጊዜ ወደ ቻይና የተጓዘ ሲሆንም ቁልፍ የፖለቲካ ኢኮኖሚ መድረኮች ላይ በመሳተፍ ዘገባዎችን ሠርቷል።
መፅሀፉ በሁለት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የቀረበ ነው።
በአስገራሚና አስደናቂ ገጠመኞች የተሞላውን መፅሀፍ በተለያዩ አማራጮችና በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ባለው የኢሬቻ ባዛርና ፌስቲቫል ታገኛላችሁ ተብላችኋል።
ጋዜጠኛው በምርመራ ዘገባ ሥራዎቹ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም "የተሸፈነው ሲገለጥ" ና "ማን ይጠየቅ?" የተሰኙ በዋቸሞና ጂንካ ዩኒቨርስቲዎች ላይ ያተኮሩ ዝግጅቶቹ በሚዲያ አዋርድ ሽልማት ታጭቶባቸዋል።

❤4👍2
📌የአእምሮ ጤና ላይ ያተኮረ አውደርዕይ
የአእምሮ ጤና ላይ ትኩረት ያደረጉ የሥዕል ስራዎች
የቀረቡበት "Art inspired by mental health " አውደርዕይ ባሳለፍነው ማክሰኞ ስድስት ኪሎ በሚገኘው በገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ውስጥ ተከፍቷል።
በዚህ አውደርዕይ የሠዓሊ ሶሎሜ ጌታቸው፣ የሠዓሊ አለማየሁ ደረሰማ ሥዕሎች ቀረበዋል። አውደርዕይው እስከ ጥቅምት 8 ድረስ ይቆያል ተብሏል።

❤13👍2
📌የመንሱር እና ብስራት ሬዲዮ ውዝግብ
የእግር ኳስ ስፖርት ተንታኙ መንሱር አብዱልቀኒ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ውዝግብ ውስጥ እንደገባ አስታወቀ።
ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ከሬድዮ ጣቢያው ጋር ስለተፈጠረው ውዝግብ ተከታዩን ብሏል"የብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ፓርትነር በመሆን ከጣቢያው ጋር በትብብር ''ብስራት-ስፖርት" የተሰኘውን ፕሮግራም ለ12 ዓመታት ሳቀርብ መቆየቴ ይታወቃል።
ይሁንና በእነዚህ ሁለት ቀናት (ረቡዕ እና ሐሙስ መስከረም 28 እና 29) ከእኔ የስራ ትጋት ጋርባልተያያዘ (በግሌ ልፈታው በማልችለው ምክንያት) ከጣቢያው ጋር ያልተግባባንባቸው ጉዳዮች ተፈጥረዋል።
እነዚህ ልዩነቶች መፍትሔ እስኪያገኙ ድረስ (ዛሬ በማለዳ ያስተዋወቅኳችሁን ፕሮግራም ጨምሮ) "ብስራት-ስፖርት" ከሬድዮ አየር ላይ እንደወረደ ስገልጽላችሁ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ነው" ሲል ተናግሯል።

❤14
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል
70ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር አሮን ደጎል ሀብቴ "ዳኝነት እና ፍትህ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ጥቅምት 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
70ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር አሮን ደጎል ሀብቴ "ዳኝነት እና ፍትህ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ጥቅምት 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
👍2
📌9ኛው የBCAA የፎቶግራፍ አውደርዕይ!
የBored Cellphone Addis Ababa የፎቶግራፍ አውደርዕይ ለዘጠነኛ ጊዜ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 1 2018 ዓ.ም ከረፋዱ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲ ኤም ሲ አደባባይ ፊትለፊት በሚገኘው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢያዎች በስልክ የተነሱ ፎቶግራፎች ለእይታ ይቀርባል ተብሏል።

❤4
📌የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዋና አዘጋጅ ከዓለም የፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተሸላሚዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ
ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መስራቾች አንዱ የሆነው ተስፋለም ወልደየስ፤ ዓለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት (IPI) እና ዓለም አቀፍ ሚዲያ ሰፖርት (IMS) የተባሉ ሁለት ተቋማት በትብብር ለሚሰጡት የዓለም ፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተመረጠ። የእዚህን ዓመት ሽልማት እንዲቀበሉ የተመረጡት ተስፋለምን ጨምሮ ሰባት ጋዜጠኞች እና አርታዒያን ናቸው።
ዓለም አቀፉ ሽልማት ለሚዲያ ነጻነት ወይም ያልተገደበ የዜና እና የመረጃ ፍሰት በተለይ ግለሰባዊ ደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሆኖ ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ጋዜጠኞች የሚሰጥ ነው።
ተስፋለም ለሽልማቱ የተመረጠው “ለገለልተኛ ጋዜጠኝነት ባለው የማይናወጥ ቁርጠኝነት” እንደሆነ ሸላሚዎቹ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 29፤ 2018 ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ጋዜጠኛው “ከባለስልጣናት ለሚሰነዘር ቀጥተኛ የበቀል እርምጃ” ዒላማ ከመሆኑ ባሻገር በሥራው ምክንያት “የግል ሕይወቱን በተደጋጋሚ ለአደጋ እንዳጋለጠ” ሸላሚዎቹ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። ከአንድ ዓመት በላይ የሚረዝመውን ጨምሮ ለተደጋጋሚ የዘፈቀደ እስራት የተዳረገው ተስፋለም፤ “ከጊዜ ወደ ጊዜ ለነጻ ሚዲያ አስቸጋሪ በሆነ ምህዳር ውስጥ ለሕዝብ ለሚጠቅም ጋዜጠኝነት ቦታ ለመፍጠር ባለው ቁርጠኝነት” ተሰድዶ ከነበረበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን ተቋማቱ በመግለጫቸው አመልክተዋል።
ተስፋለም “ለዚህ ታላቅ ሽልማት በመመረጤ ታላቅ ክብር ይሰማኛል” በማለት ደስታውን ገልጿል።

❤18👏2