Telegram Web Link
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

60ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ዶ/ር ይሁኔ አየለ "ቡዳ! እውነት ወይስ ሀሰት" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ግንቦት 17  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ዛሬ ይከበራል

የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ኢትዮጵያውያን በራሳችን ወግና እሴት ብሎም የመከባበር ባህል መሰረት ኢትዮጵያዊ ቀለም ባለው መልኩ "ክብር ለአባትነት" በሚል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ግንቦት 15 በሃገር አቀፍ ደረጃ መከበር የጀመረ ቀን ነው።

ግንቦት 15 የተመረጠበት ምክንያት የጣልያን ወራሪ ኃይልን አድዋ ላይ መክተው ያሸነፉት ጀግኖች አባቶቻችን በድል አድራጊነት ወደ መናገሻ ከተማቸው የተመለሱበት በመሆኑ ብዙሃኑ አባቶች ከቤተሰብ ባሻገር ለሃገር መፅናት ላደረጉት ተግባር የሚታወሱበትና ምስጋና የሚቀርብበት ዕለት እንዲሆንም በማሰብ ነው፡፡

ላለፉት 17 አመታት በኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን ግንቦት 15 ላይ ሲያከብር በቤተሰባቸው፣ በአካባቢያቸው፣ በወዳጆቻቸው እና በዙሪያቸው ባሉ ሁሉ ስማቸው በመልካም የሚነሳ፣ አርአያ መሆን የቻሉ፣ ከቤተሰብ እስከ ሃገር በመልካም አባትነትና አበርክቶ የሚነሱ አባቶችን፤ የኢትዮጵያ አባቶች የክብር መገለጫ የሆነውን ጋቢ በመደረብ፣ ዝቅ ብሎ እግር በማጠብ፣ የዕውቅና ምስክር ወረቀት በመስጠትና ታሪካቸውን በመሰነድ ሲያመሰግን እና ሲያከብር ቆይቷል።

ግንቦት 15 እንደሌላው ዓለም ሁሉ ኢትዮጵያዊ መልክ የያዘ፣ ኢትዮጵያውያን አባቶች የሚመሰገኑበት፣ በኢትዮጵያ ካላንደር ኢትዮጵያዊ ምክንያት ኖሮት የሚከበር "የኢትዮጵያ አባቶች ቀን" ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"ሥዕልና ጃዝ" የተሰኘ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

(መግቢያው በነፃ)

"ሥዕልና ጃዝ" የተሰኘ ዝግጅት ነገ ቅዳሜ ግንቦት 16 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ መካኒሳ አካባቢ በሚገኘው ጃዝ ኮፊ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም የሥዕልና ጃዝ ፌስቲቫል እንዲሁም ሌሎች አሳታፊና አዝናኝ ዝግጅቶች ይኖራሉ ተብሏል። መግቢያው በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌ኢቢኤስ ቁጥር አንድ ብራንድ ሆኖ ተመረጠ

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚዲያ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ተቀባይነት ያለው ቀዳሚ ብራንድ ተብሎ የተመረጠው መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው ብራንድ አፍሪካ የተሰኘው ተቋም ባዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡

በዚሁ የእውቅና ዝግጅት ላይ  ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ተቀባይነት ካላቸው የመገናኛ ብዙኃን ብራንዶች መካከል ቁጥር 1 የሆነው ቢቢሲና አልጀዚራን በማስከተል መሆኑን ነው ብራንድ አፍሪካ ያሳወቀው፡፡

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚዲያ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ብራንድ ስለመሆኑ እውቅና በተሰጠበት በዚህ መድረክ ላይ የሀገርን አርማ ይዞ በመላው አለም የሚበረው አንጋፋውና ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ10 ተከታታይ ዓመታት በላይ ግዙፍ ስማቸውን ይዘው ከዘለቁ 5 ብራንዶች መካከል አንዱ በመባል እውቅና ተችሮታል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን አየር መንገዱ በአፍሪካ በአቪዬሽን ዘርፍ ካሉ ተመራጭ ብራንዶች ውስጥ ቀዳሚው በመሆን ኤምሬትስና ኳታር አየር መንገዶችን አስከትሎ የአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ ስለመሆኑ ነው በዝግጅቱ ላይ የተነገረው፡፡

Via EBS

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

1.ድምጻዊት ሀይማኖት ግርማ "ጅንኑ" ስትል የሰየመችውን የሙዚቃ አልበም ከ12 ዓመታት በኃላ ዛሬ ለሙዚቃ አድማጮች አቀረበች።ድምጻዊት ኃይማኖት "ተረስቻለሁ የሚል ስጋት አለኝ፣አደጋ አጋጥሞኝ ነበር። ሙዚቃ ባቆምኩበት ሰዓት ተመልሼ የምመጣ አልመሰለኝም ነበር" ስትል ተናገራለች ስለጉዳዩ በአርትስ ስፔሻል ትሰማላችሁ።

2.በአሜሪካውያን የተሰራው "ኢትዮጵያ" የተሰኘ ተውኔት ከ88 ዓመታት በኃላ ከሰሞኑ በዋሽንግተን ዲሲ ለመድረክ በቅቷል። ተውኔቱ በ1930ዎቹ ከተዘጋጀ በኋላ በጊዜው የአሜሪካ ፕሬዚደንት በነበሩት ቴዎዶር ሩዝቬልት አስተዳደር አማካኝነት ለህዝብ ለዕይታ እንዳይቀርብ በይፋ ታግዶ የቆየ እንደሆነ ተነግሯል።በዝርዝር እንነግራችኋለን።

3.በአዲስ አበባው የጣይቱ የባህል እና ትምህርት ማዕከል ውስጥ የፊታችን ሰኞ በማዕከሉ ታሪክ የመጀመሪያው ግዙፍ የሥነጥበብ አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው።

4.የ"ድንቅነሽ" ወይንም "ሉሲ" አጽም የተገኘበት 50ኛ ዓመት ተከበረ። እንዲሁም  በእድሳት ምክንያት ተዘግቶ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/8zfvUnde4nA?si=YcyoId-NFm08fa_g

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የሸገሩ ስንክሳር ፕሮግራም መጽሐፍ ሆነ

በጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ የተዘጋጀውና በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት "እነሆ ስንክሳር" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬድዮ ለዓመታት ሲተላለፈ የቆየው "ስንክሳር" የሬድዮ ፕሮግራም አሁን በመጽሐፍ መልክ እንደተዘጋጀም ተነግሯል።

"እነሆ ስንክሳር"መጽሐፍ የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጀ ያመለክታል።

መጽሐፉ በጃፋር እና በዕውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች በኩል ለአንባቢያን ይከፋፈላም ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ቅጽ ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከዚህ ቀደም ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

Telegram: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ወደ አየር ተመለሰ

ተወዳጁ የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ጣቢያ ለተወሰነ ጊዜ ከአየር ወርዶ እንደቆየ ይታወሳል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው ከትላንት ጀምሮ ወደ አየር እንደተመለሰም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን በDstv ቻናል 468 እና በኢትዮሳት 11605 አሁን በስርጭት ይገኛል ተብሏል።

ትኩረቱን ልጆች ላይ አድርጎ የሚሰራውና በጥቂት ጥሪት፣ የሰው ሀይል እዚህ የደረሰው የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ጣቢያ በልጆችና በቤተሰብ ዘንድ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሆነ በርካቶች ይመሰክራሉ።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌ቻናል 1 የመዝናኛ ቴሌቪዥን ሊከፈት ነው

ቻናል 1 (Channel 1) የተሰኘ አዲስ የመዝናኛ የቴሌቭዥን ጣቢያ የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ዘርፍ ሊቀላቀል እንደሆነ ተሰምቷል።

ሰኔ ወር ላይ የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀምር የተሰማዉ  ቻናል 1 ፣ ባሳለፍነዉ ሳምንት ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሳተላይት ስርጭት ፍቃድን ተረክቧል።

ቻናሉ ቀደም ብሎ በርካታ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደከረመ እና አዳዲስ የፕሮግራም ይዘቶችን ለተመልካች ይዞ ለመምጣትም ዝግጅት ላይ እንዳለ ተሰምቷል።

የቻናል 1 መስራች አቶ ሳሙኤል ደበበ፣ ከ“ወንዶች ጉዳይ” ፊልም ፕሮዲዩሰርነት ጀምሮ ለ10 ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከካሜራ ጀርባ ትልቅ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና ዳይሬክት በማድረግ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌"አስኒ" ፊልም ቀጣይ ሳምንት ለእይታ ይበቃል

በድምጻዊት አስናቀች ወርቁ ሕይወትና ስራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው "አስኒ" የተሰኘ ፊልም ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ በቬኒው ዌርሃውስ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።

ፊልሙ ከታየ በኃላም "የአስናቀች ወርቁ  ሕይወት ታሪክ: ድፍረት ፣ጥልቅ ስሜት እና ውበት በኢትዮጵያ "የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ውይይት ከፊልሙ አዘጋጅ ራሔል ሳሙኤል ጋር ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1‌‌
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

1. ተዋናይት ትዕግሥት ግርማ ከአስር ዓመት በኃላ በመድረክ ተውኔት የመጣችበት "ደጋግ ሰይጣኖች" ተውኔት ለመድረክ ሊበቃ ነው።

2.የሚዲያ፣የሥነጽሑፍ፣የቴአትርና የፊልም ባለሞያዎችን የሥራና የሕይወት ታሪክን የሰነደው"መዝገበ አእምሮ ቅጽ 2 " መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል።

3."ዳዎኤ ቡሹ" የተሰኘ ኢትዮጵያዊ ፊልም በዓለምአቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ ለእይታ ሊቀርብ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/uQpiSwNxLJM?si=_cPFvapeM4Wte1zK

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የደራሲ መዝገቡ አባተ መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

የዛሬ 50 ዓመት የተፃፈውና ዘንድሮ ለሕትመት የበቃው የጋዜጠኛና ደራሲ መዝገቡ አባተ መፅሐፍ ዛሬ ግንቦት 25 2017 ዓ.ም በድምቀት ይመረቃል።

ጋዜጠኛና ደራሲ መዝገቡ አባተ  በኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች እየተዘዋወረ  ከአካባቢው ነዋሪዎች  ጠይቆ የተረዳውን መዝግቦ ያዘጋጀው መፅሀፍ ከ400 በላይ ገፆች ያሉት ሲሆን የመፅሐፉም አርታዒ የታሪክ ባለሙያ ብርሀኑ ደቦጭ ነው፡፡

መፅሐፉ ዛሬበአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ሲመረቅ የደራሲው ልጆች፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች ይታደማሉ፡፡በተጨማሪም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የሀገር ባለውለታዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የሁነቱ አዘጋጅ ደግሞ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን መሆኑ ሲሆን የደራሲው ቤተሰቦችና መፅሀፉ የሕትመት ብርሀን እንዲያይ አድርገዋል፡፡

በመፅሀፉ ላይ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፣ ፕሮፌሰር ሰሎሞን ሙሉጌታ እና ጋዜጠኛ ማዕረጉ በዛብህ  ፣የመፅሀፍ ግምገማ የሚያቀርቡ ሲሆን ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመም የመፅሀፍ ዳሰሳው አወያይ ናቸው፡፡ የደራሲው የመዝገቡ አባተ የሕይወት ታሪክም በልጃቸው በፀሀይ መዝገቡ አባተ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ደራሲ እና ጋዜጠኛ መዝገቡ አባተ  የዛሬ 14 ዐመት ሕይወቱ ያለፈ ጋዜጠኛ ሲሆት በአገራችን በሕትመት ሚድያዎች በማገልገል የሚታወቅ ነው፡፡ከሠራባቸው የህትመት ውጤቶች መካከልም ሰንደቅ አላማችን አንዱ ነው፡፡

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አሐዱ ሬድዮና ቴሌቪዥን ስልጠና አዘጋጅ

ልዩ የጋዜጠኝነት ክህሎት የክረምት ስልጠና በአሐዱ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን

በመሠረታዊ የጋዜጠኝነት ትምህርቶች

በዜና አፃፃፍና አቀራረብ

በምርመራ ጋዜጠኝነት ምንነት እና አዘገጃጀት

በፕሮግራም ዝግጅት እና አቀራረብ

በቃለ-ምልልስ ቴክኒኮች

በማሕበራዊ ሚዲያ ይዘት አዘገጃጀት

በግራፊክስ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ

እንዲሁም በሌሎች መሠረታዊ የጋዜጠኝነት ክህሎቶች ላይ በሚዲያ ሥራ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አንጋፋ ጋዜጠኞች እና በዩኒቨርሲቲ መምህራን ስልጠና ይሰጣል፡፡

ስልጠናው ከሰኔ 15 እስከ ነሐሴ 30/2017 ድረስ የሚቆይ ሲሆን፤ በንድፈ ሀሳብና በተግባር ልምምዶች ላይ አተኩሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሰጣል!

አድራሻ፡- ሲኤምሲ (CMC) ሚካኤል የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ሕንጻ አንደኛ ፎቅ በአካል በመምጣት ይመዝገቡ!

እንዲሁም በ https://shorturl.at/aA2j5 ዝርዝር መረጃዎችን በመሙላት ይመዝገቡ!

ለበለጠ መረጃ ፡-0940 00 00 05
                         0940 00 00 09

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በዕውቀቱ ስዩም በቅኔ ቤት ዝግጅቱን ሊያቀርብ ነው

"በቅኔ ቤት" የፊታችን June 14 LONDON እና  June 15 ደግሞ በ LEEDS "የሳቅ ድግስ"  ተዘጋጅቷል። ሁለቱም መድረኮች ላይ በዕውቀቱ ስዩም በሀገረ እንግሊዝ ዝግጅቱን ያቀርባል ተብሏል።

ቅኔ ቤት - በለንደን ከተማ ውስጥ በሁለት ወራት አንዴ ቋሚ ምሽት ከጀመረ ሦስት ዓመታት አስቆጥሯል።

በእንግሊዝ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ "የሚስቶቼ ባሎች" የተሰኘ የመድረክ ተውኔት በማስመጣት ለተመልካች አቅርቧል።

በዚህኛው ዙር ዝግጅት ላይም፣ በዕውቀቱ ስዩም ፣ትዕግስት ማሞ ብርሃኔ፣ዳግማዊ ጌታቸው፣በሐይሉ ነቃጥበብ፣አስተዋይ መለሰ፣ክብሮም ገ/ማርያም፣ኒኒ አሰፋ ፣ዳዊት ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ትኬቱ ለንደን ፊንስበሪ ፓርክ የሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል የሀበሻ ሬስቶራንት እና ሊድስ ፒያሳ ባርና ሬስቶራንት ይገኛል ተብሏል።

+447305496203
+447950212404

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መፅሀፍ ተፃፈለት

የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መፅሀፍ የፃፈችሁ ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት።

ረዳት ፀሀፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲሚ  የተባለ ፀሀፊ መሆኑን ሰምተናል።

በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መፃፍ ለማሳናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሀፊዋ አስረድታለች።

አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መፃህፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተነግሯል።

ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሀይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ጠቅሳለች።

መፅሀፉ አትሌት ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፣ ፍልስፍናውን፣ የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ልጁ ሜላት ስትናገር ሰምተናታል።

ለጊዜው ''Dissecting Haile'በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መፅሀፋ ወደፊት ወደ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል።

መፅሀፉ ለገበያ የሚቀርበው በመጪው ነሀሴ ወር መሆኑንም ሰምተናል።

የአትሌት ኃይሌን የህይወት ታሪክ የሚመለከት ሌላ መፃህፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኗንም ልጁ ተናግራለች።

Via ንጋቱ ሙሉ

ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"ሰው ሙሉ ትዝታ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

በገጣሚ ኪሩቤል ዘርፉ የተዘጋጀው "ሰው ሙሉ ትዝታ /ወል -መካ/" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ በቅደመ ክፍያ ሽያጭ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።

ገጣሚውም በማህበራዊ ትስስር ገፁ"

ብትወዱ በዚህ በኩል ሸምቱ

1000247106964
kirubel zerfu zeleke

በ telebirr🌟
0987367513
ዋጋ - 400 birr 💵

👉 @ቴሌ-ግራም ላይ ስክሪን ሹት አስቀምጡልኝ ተወዳጁኝ

https://www.tg-me.com/kirubelzerfu" ብሏል።
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።

መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌 ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ

የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሏል።

በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተገንዝቧል።

ተስፋለም የመጀመሪያውን ሌሊት ካሳለፈበት እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ትላንት ሰኞ ሰኔ 2 ቀን፤ 2017 ቄራ አካባቢ ወደሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ተዘዋውሯል።

ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርቦ በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ተወስኖ ነበር። ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ተስፋለም የጠየቀውን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ተስፋለም “ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” እንደተጠረጠረ ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ በሰጠበት ደብዳቤ ላይ ሠፍሯል። የተስፋለም የዋስትና መብት እንዲከበር ከተሰጠው ትዕዛዝ በኋላ መርማሪ ፖሊስ በቃል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። ይሁንና እስካሁን በይፋ ፍርድ ቤት ይግባኝ አልጠየቀም።

የተስፋለም ዋስትና እንዲከበር ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አስፈላጊውን ክፍያ ፈጽሞ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተጻፈው ደብዳቤ በሚመለከታቸው የፖሊስ መኮንን ሳይፈረምበት ቀርቷል።

©️ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ከእስር ተፈታ

በእጮኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሶስት ወራት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ከእስር ቤት መውጣቱን ፋስት መረጃ አስነብቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የህግ ባለሙያው አበባየው ጌታ "ከአርቲስት አንዷለም ጎሳ ጠበቃ ጋር በስልክ ባደረኩት ንግግር አርቲስቱ ከእስር የመፈታቱ ዜና እውነት መሆኑን አረጋግጦልኛል" ሲል ጽፏል።

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌መቅረዝ ሥነኪን ዛሬ ይካሄዳል

መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ ማእከል “ተግባራዊ ማሳያዎችን በመጠቀም የፊዚክስ ፅንሰ-ሃሳቦችን መግለጽ” በሚል ርእስ በፊዚክስ የትምህርት ዘርፍ፤ ታዋቂና በዘርፉ ከፍተኛ የማስተማርና የምርምር ልምድ ባላቸውንና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ት/ርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ አቅራቢነት ትእይንታዊ ሳይንሳዊ ገለጻ ያካሂዳል።

መርሐግብሩ ዓርብ፣ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ይካሄዳል።

https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
2025/07/07 04:29:53
Back to Top
HTML Embed Code: