📌ቻናል 1 የመዝናኛ ቴሌቪዥን ሊከፈት ነው
ቻናል 1 (Channel 1) የተሰኘ አዲስ የመዝናኛ የቴሌቭዥን ጣቢያ የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ዘርፍ ሊቀላቀል እንደሆነ ተሰምቷል።
ሰኔ ወር ላይ የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀምር የተሰማዉ ቻናል 1 ፣ ባሳለፍነዉ ሳምንት ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሳተላይት ስርጭት ፍቃድን ተረክቧል።
ቻናሉ ቀደም ብሎ በርካታ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደከረመ እና አዳዲስ የፕሮግራም ይዘቶችን ለተመልካች ይዞ ለመምጣትም ዝግጅት ላይ እንዳለ ተሰምቷል።
የቻናል 1 መስራች አቶ ሳሙኤል ደበበ፣ ከ“ወንዶች ጉዳይ” ፊልም ፕሮዲዩሰርነት ጀምሮ ለ10 ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከካሜራ ጀርባ ትልቅ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና ዳይሬክት በማድረግ ይታወቃል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌"አስኒ" ፊልም ቀጣይ ሳምንት ለእይታ ይበቃል
በድምጻዊት አስናቀች ወርቁ ሕይወትና ስራዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው "አስኒ" የተሰኘ ፊልም ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ በቬኒው ዌርሃውስ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።
ፊልሙ ከታየ በኃላም "የአስናቀች ወርቁ ሕይወት ታሪክ: ድፍረት ፣ጥልቅ ስሜት እና ውበት በኢትዮጵያ "የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ውይይት ከፊልሙ አዘጋጅ ራሔል ሳሙኤል ጋር ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።

📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
1. ተዋናይት ትዕግሥት ግርማ ከአስር ዓመት በኃላ በመድረክ ተውኔት የመጣችበት "ደጋግ ሰይጣኖች" ተውኔት ለመድረክ ሊበቃ ነው።
2.የሚዲያ፣የሥነጽሑፍ፣የቴአትርና የፊልም ባለሞያዎችን የሥራና የሕይወት ታሪክን የሰነደው"መዝገበ አእምሮ ቅጽ 2 " መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል።
3."ዳዎኤ ቡሹ" የተሰኘ ኢትዮጵያዊ ፊልም በዓለምአቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ ለእይታ ሊቀርብ ነው።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/uQpiSwNxLJM?si=_cPFvapeM4Wte1zK
📌መልካም ምሽት

📌የደራሲ መዝገቡ አባተ መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል
የዛሬ 50 ዓመት የተፃፈውና ዘንድሮ ለሕትመት የበቃው የጋዜጠኛና ደራሲ መዝገቡ አባተ መፅሐፍ ዛሬ ግንቦት 25 2017 ዓ.ም በድምቀት ይመረቃል።
ጋዜጠኛና ደራሲ መዝገቡ አባተ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች እየተዘዋወረ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቆ የተረዳውን መዝግቦ ያዘጋጀው መፅሀፍ ከ400 በላይ ገፆች ያሉት ሲሆን የመፅሐፉም አርታዒ የታሪክ ባለሙያ ብርሀኑ ደቦጭ ነው፡፡
መፅሐፉ ዛሬበአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ሲመረቅ የደራሲው ልጆች፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች ይታደማሉ፡፡በተጨማሪም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የሀገር ባለውለታዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
የሁነቱ አዘጋጅ ደግሞ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን መሆኑ ሲሆን የደራሲው ቤተሰቦችና መፅሀፉ የሕትመት ብርሀን እንዲያይ አድርገዋል፡፡
በመፅሀፉ ላይ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፣ ፕሮፌሰር ሰሎሞን ሙሉጌታ እና ጋዜጠኛ ማዕረጉ በዛብህ ፣የመፅሀፍ ግምገማ የሚያቀርቡ ሲሆን ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመም የመፅሀፍ ዳሰሳው አወያይ ናቸው፡፡ የደራሲው የመዝገቡ አባተ የሕይወት ታሪክም በልጃቸው በፀሀይ መዝገቡ አባተ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ደራሲ እና ጋዜጠኛ መዝገቡ አባተ የዛሬ 14 ዐመት ሕይወቱ ያለፈ ጋዜጠኛ ሲሆት በአገራችን በሕትመት ሚድያዎች በማገልገል የሚታወቅ ነው፡፡ከሠራባቸው የህትመት ውጤቶች መካከልም ሰንደቅ አላማችን አንዱ ነው፡፡

📌አሐዱ ሬድዮና ቴሌቪዥን ስልጠና አዘጋጅ
ልዩ የጋዜጠኝነት ክህሎት የክረምት ስልጠና በአሐዱ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን
በመሠረታዊ የጋዜጠኝነት ትምህርቶች
በዜና አፃፃፍና አቀራረብ
በምርመራ ጋዜጠኝነት ምንነት እና አዘገጃጀት
በፕሮግራም ዝግጅት እና አቀራረብ
በቃለ-ምልልስ ቴክኒኮች
በማሕበራዊ ሚዲያ ይዘት አዘገጃጀት
በግራፊክስ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ
እንዲሁም በሌሎች መሠረታዊ የጋዜጠኝነት ክህሎቶች ላይ በሚዲያ ሥራ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አንጋፋ ጋዜጠኞች እና በዩኒቨርሲቲ መምህራን ስልጠና ይሰጣል፡፡
ስልጠናው ከሰኔ 15 እስከ ነሐሴ 30/2017 ድረስ የሚቆይ ሲሆን፤ በንድፈ ሀሳብና በተግባር ልምምዶች ላይ አተኩሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ይሰጣል!
አድራሻ፡- ሲኤምሲ (CMC) ሚካኤል የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ሕንጻ አንደኛ ፎቅ በአካል በመምጣት ይመዝገቡ!
እንዲሁም በ https://shorturl.at/aA2j5 ዝርዝር መረጃዎችን በመሙላት ይመዝገቡ!
ለበለጠ መረጃ ፡-0940 00 00 05
0940 00 00 09

በዕውቀቱ ስዩም በቅኔ ቤት ዝግጅቱን ሊያቀርብ ነው
"በቅኔ ቤት" የፊታችን June 14 LONDON እና June 15 ደግሞ በ LEEDS "የሳቅ ድግስ" ተዘጋጅቷል። ሁለቱም መድረኮች ላይ በዕውቀቱ ስዩም በሀገረ እንግሊዝ ዝግጅቱን ያቀርባል ተብሏል።
ቅኔ ቤት - በለንደን ከተማ ውስጥ በሁለት ወራት አንዴ ቋሚ ምሽት ከጀመረ ሦስት ዓመታት አስቆጥሯል።
በእንግሊዝ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ "የሚስቶቼ ባሎች" የተሰኘ የመድረክ ተውኔት በማስመጣት ለተመልካች አቅርቧል።
በዚህኛው ዙር ዝግጅት ላይም፣ በዕውቀቱ ስዩም ፣ትዕግስት ማሞ ብርሃኔ፣ዳግማዊ ጌታቸው፣በሐይሉ ነቃጥበብ፣አስተዋይ መለሰ፣ክብሮም ገ/ማርያም፣ኒኒ አሰፋ ፣ዳዊት ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
ትኬቱ ለንደን ፊንስበሪ ፓርክ የሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል የሀበሻ ሬስቶራንት እና ሊድስ ፒያሳ ባርና ሬስቶራንት ይገኛል ተብሏል።
+447305496203
+447950212404

📌አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መፅሀፍ ተፃፈለት
የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መፅሀፍ የፃፈችሁ ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት።
ረዳት ፀሀፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲሚ የተባለ ፀሀፊ መሆኑን ሰምተናል።
በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መፃፍ ለማሳናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሀፊዋ አስረድታለች።
አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መፃህፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሀይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ጠቅሳለች።
መፅሀፉ አትሌት ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፣ ፍልስፍናውን፣ የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ልጁ ሜላት ስትናገር ሰምተናታል።
ለጊዜው ''Dissecting Haile'በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መፅሀፋ ወደፊት ወደ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል።
መፅሀፉ ለገበያ የሚቀርበው በመጪው ነሀሴ ወር መሆኑንም ሰምተናል።
የአትሌት ኃይሌን የህይወት ታሪክ የሚመለከት ሌላ መፃህፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኗንም ልጁ ተናግራለች።
Via ንጋቱ ሙሉ

📌"ሰው ሙሉ ትዝታ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
በገጣሚ ኪሩቤል ዘርፉ የተዘጋጀው "ሰው ሙሉ ትዝታ /ወል -መካ/" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ በቅደመ ክፍያ ሽያጭ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።
ገጣሚውም በማህበራዊ ትስስር ገፁ"
ብትወዱ በዚህ በኩል ሸምቱ
1000247106964
kirubel zerfu zeleke
በ telebirr🌟
0987367513
ዋጋ - 400 birr 💵
👉 @ቴሌ-ግራም ላይ ስክሪን ሹት አስቀምጡልኝ ተወዳጁኝ
https://www.tg-me.com/kirubelzerfu" ብሏል።

📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌 ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሏል።
በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያሳልፍ መደረጉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተገንዝቧል።
ተስፋለም የመጀመሪያውን ሌሊት ካሳለፈበት እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ትላንት ሰኞ ሰኔ 2 ቀን፤ 2017 ቄራ አካባቢ ወደሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ተዘዋውሯል።
ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርቦ በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ተወስኖ ነበር። ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ተስፋለም የጠየቀውን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ተስፋለም “ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” እንደተጠረጠረ ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ በሰጠበት ደብዳቤ ላይ ሠፍሯል። የተስፋለም የዋስትና መብት እንዲከበር ከተሰጠው ትዕዛዝ በኋላ መርማሪ ፖሊስ በቃል ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። ይሁንና እስካሁን በይፋ ፍርድ ቤት ይግባኝ አልጠየቀም።
የተስፋለም ዋስትና እንዲከበር ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አስፈላጊውን ክፍያ ፈጽሞ በፍርድ ቤቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተጻፈው ደብዳቤ በሚመለከታቸው የፖሊስ መኮንን ሳይፈረምበት ቀርቷል።
©️ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

📌ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ከእስር ተፈታ
በእጮኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው ድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሶስት ወራት ከተጠጋ ጊዜ በኋላ ከእስር ቤት መውጣቱን ፋስት መረጃ አስነብቧል።
በሌላ በኩል ደግሞ የህግ ባለሙያው አበባየው ጌታ "ከአርቲስት አንዷለም ጎሳ ጠበቃ ጋር በስልክ ባደረኩት ንግግር አርቲስቱ ከእስር የመፈታቱ ዜና እውነት መሆኑን አረጋግጦልኛል" ሲል ጽፏል።

📌መቅረዝ ሥነኪን ዛሬ ይካሄዳል
መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

📌የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ ማእከል “ተግባራዊ ማሳያዎችን በመጠቀም የፊዚክስ ፅንሰ-ሃሳቦችን መግለጽ” በሚል ርእስ በፊዚክስ የትምህርት ዘርፍ፤ ታዋቂና በዘርፉ ከፍተኛ የማስተማርና የምርምር ልምድ ባላቸውንና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ት/ርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ አቅራቢነት ትእይንታዊ ሳይንሳዊ ገለጻ ያካሂዳል።
መርሐግብሩ ዓርብ፣ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ይካሄዳል።
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መርሐግብሩ ዓርብ፣ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ይካሄዳል።
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌"የእግዜር ብቸኝነት" መጽሐፍ አርብ ይመረቃል
የገጣሚ መኳንንት መንግስቱ "የእግዜር ብቸኝነት" መጽሐፍ ነገ አርብ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።
"የእግዜር ብቸኝነት"መጽሐፍ በ138 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።ገጣሚ መኳንንት መንግስቱ ከዚህ ቀደም "ክፍት የስራ ቦታ" እና "ስንፋታ እንደግስ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አቅርቧል።

📌ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተፈታ
ጋዜጠኛ ተስፋለም ሦስት ጊዜ በዋስ ከእስር እንዲፈታ በፍርድ ቤቶች ቢወሰንም ፖሊስ ከእስር አልፈታውም ነበር።
ዛሬ አርብ ግን ከእስር ስለመፈታቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
ጋዜጠኛ ተስፋለም ሦስት ጊዜ በዋስ ከእስር እንዲፈታ በፍርድ ቤቶች ቢወሰንም ፖሊስ ከእስር አልፈታውም ነበር።
ዛሬ አርብ ግን ከእስር ስለመፈታቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:
1. ድምጻዊት የማርያም ቸርነት (የማ) የሙዚቃ ኮንሰርቷን ነገ ታቀርባለች።
2.'ከባድ ማፊያ' ፊልም በዚህ ሳምንት ለእይታ በቃ።
3.የደራሲ ሚስጥር አደራው ' እኔ' የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።
4. የሮፍናን ኑሪ ' የኔ ትውልድ' ኮንሰርት ነገ በመቀሌ ይካሄዳል።
5.የወዳጄነህ መሐረነ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ተባለ።
6.'ኖ ሞር' የተሰኘ ኮሜዲ ተውኔት ዛሬ ለመድረክ በቃ።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/xk3XyfLufi0?si=MwOW5CvFp61jhQIJ

📌የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የ60ኛ ዓመት የልደት በዓል ነገ ቅዳሜ በድምቀት ሊከበር ነው
ከጦር ሃይሎች ራድዮ አስከ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከቅዳሜ መዝናኛ፣ ከነፃ ፕሬስ እስከ አርትስ ቲቪ፣ ከ97.1 ራዲዮ እስከ ሸገር ኤፍ ኤም ድረስ ተወዳጅ ሥራዎቹን ያቀረበው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ በሚደረግ የእራት ፕርግራም የልደት በዓሉ ይከበራል ተብሏል።
በሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሚከበረው የደረጀ የልደት በዓል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ የልደት በዓሉን ለማድመቅ የሙዚቃ ዝግጅትም እንደተሰናዳ ተገልጿል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
ከጦር ሃይሎች ራድዮ አስከ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከቅዳሜ መዝናኛ፣ ከነፃ ፕሬስ እስከ አርትስ ቲቪ፣ ከ97.1 ራዲዮ እስከ ሸገር ኤፍ ኤም ድረስ ተወዳጅ ሥራዎቹን ያቀረበው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ በሚደረግ የእራት ፕርግራም የልደት በዓሉ ይከበራል ተብሏል።
በሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሚከበረው የደረጀ የልደት በዓል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ የልደት በዓሉን ለማድመቅ የሙዚቃ ዝግጅትም እንደተሰናዳ ተገልጿል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በደራሲ ሚስጥረ አደራው የተፃፈው "እኔ" የተሰኘው መፅሐፍ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሃሳቦቿንና ስራዎቿን በተለይም የትርጉም ስራዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ በማቅረብ የምትታወቀው ሚስጥረ አደራው የመጀመሪያ ስራዋ የሆነውን "እኔ" የተሰኘ መፅሃፍ ለንባብ አብቅታለች።
ሚስጥረ በብዙዎች ዘንድ የፐርሺያውን ገጣሚ የሩሚን ስራዎች ወደ አማርኛ በመቅዳትና በማቅረብ በስፋት የምትታወቅ ሲሆን አሁን የተለያዩ ታሪኮችን የያዘ መፅሃፍ ነው ይዛ የመጣችው።
"እኔ" የተሰኘው መፅሐፍ፤ ፀሐፊዋ በተለያዩ ጊዜዎች ማህበራዊና መሰል ጉዳዮች የሚፈጥሯቸውን ሸክሞችና ጭቆናዎች በማጠየቅ የራስን ነፃነት ለመፈለግ የሚደረግን በጥያቄና መልስ የተሞላን የህይወት ትግልን የምታሳይበት ነው።
በዋልያ መፅሃፍት በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይም ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን፣ አርታኢና ተርጓሚ ቴዎድሮስ አጥላው፣ አርቲስት አዳነች ወልደ ገብርኤል፣ ደራሲ ዘቢብ መልኬ፣ የስነ ልቦና እና የጤና ባለሙያ ሰላማዊት ሞሲሳን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች ዲስኩርና ስለ መፅሃፉ ምልከታቸውን ተናግረዋል።
ደራሲዋ ሚስጥረ አደራው በ Health Informatics ዲግሪ እንዲሁም በ Health Information Data analytics የማስተርስ ዲግሪዋን በመያዝ በህክምና ዘርፍ ውስጥ በመስራት ላይ ትገኛለች።
ከቅዳሜ ጀምሮ ለንባብ የበቃው "እኔ" መፅሃፍ 179 ገፆች አሉት።

📌የአፍሪካ ህፃናት ቀን በስለ እናት !
በየዓመቱ ሰኔ 9 የሚከበረው የአፍሪካ ህፃናት ቀን ዘንድሮም «የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነፅ ህፃናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን» በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ በአፍሪካ ለ35ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።
ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት የአፍሪካ የህፃናት ቀንን በድርጅቱ ግቢ ውስጥ በተለያዩ መርሐግብሮች አክብሮ ውሏል።
ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ለችግር የተጋለጡ እና የተጎዱ ህጻናትን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለመታደግ የተቋቋመ ድርጅት እንደሆነም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አብዱ ተናግረዋል።
በዕለቱም ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት አዲሱን ብራንድና የማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይፋ አድርጓል።

📌ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ መኖሪያ ቤቱን ተረከበ
በ60ኛ የልደት በዓሉ ከጃምቦ ሪል ስቴት የመኖሪያ ቤት ስጦታ የተበረከተለት አንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌበተወለደበት ባደገበትና በኖረበት በቅሎ ቤት በሚገኘው የጃምቦ ሪል ስቴት አፍሪካ ኅብረት-2 አፓርታማ ፕሮጀክት የተበረከተለትን ቤት ትላንት ተረክቧል፡፡
5ኛ ወለል ላይ የሚገኝ ፥ ባለሁለት መኝታ ፥ ኦፕን ኪችን ፥ ስቶር፥ ሰፊ ሣሎን እና በረንዳ ፥ 16.5 ሚልዮን የሚያወጣ (( ጥንቅቅ ያለ ዘመናዊ ቤት )) በመሆኑ በቦታው የተገኙ ሁሉ በደስታ ረስርሰዋል፡፡
የጃምቦ ሪል እስቴት ባለቤት ኢንጂነር ደበበ ሰይፉ እና ባልደረቦቻችው በተገኙበት፤ እንዲሁም (የደረጀ ኃይሌ እና ትዕግስት ሽፈራው ቤተሰቦች፤ ወዳጆች) "የእንኳን ደስ አላችሁ" የምሳ ግብዣ ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ ኬተሪንግ ተከናውኗል፡፡
የጃምቦ ሪልስቴት ብራንድ አምባሳደር ደረጀ ሀይሌ ከታዋቂው ሪልስቴት ድርጅት ጋር ለሦስት ዓመታት ይሰራል።