📌ብሔራዊ ቤተመንግሥት ለሁሉም ክፍት ሆነ
ለአራት ወራት የሙከራ አገልግሎት ላይ የነበረው የብሔራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ከዛሬ ሰኔ 10 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሕዝብ እይታ ክፍት መሆኑ ታውቋል።
የመግቢያ ዋጋዎች መደበኛ ትኬት 300 ብር እንዲሁም ልዩ ቲኬት 1,000 ብር ሲሆን የሥራ ሰዓታት ከማክሰኞ በስተቀር በየቀኑ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11 ሰዓት ክፍት ይሆናል።
በብሔራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ውስጥ የመኪና ሙዚየም፣ውድ የሆኑ እና ለብዙ ዘመናት ተጠብቆ የኖረ ቅርስ እና ሌሎችም ቅርሶች ይገኛሉ።
ደረጃውን የጠበቀ ካፍቴሪያ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የመዝናኛ አማራጮች መኖራቸዉም ተገልጿል፡፡
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236

📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌"ኖ ሞር" የተሰኘ ተውኔት ለመድረክ በቃ
በደራሲ ፍፁም ንጉሴ ተደርሶ በተሻለ ወርቁ የተዘጋጀው "ኖ ሞር" ተውኔት ባሳለፍነው አርብ በዓለም ሲኒማ ለመድረክ በቅቷል።
"ኖ ሞር" ተውኔት የኮሜዲ ዘውግ እንዳለውም ተነግሯል።በተውኔቱ ላይ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ህሊና ሲሳይ፣የምስራች ግርማና ፍሬሕይወት መለሰ ተውነውበታል።
በፍሬ መልቲሚዲያ የቀረበው "ኖ ሞር" ተውኔት በቋሚነት ዘውትር አርብ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ መታየቱን እንደሚቀጥልም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌የዶ/ር ወዳጄነህ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
በዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ የተዘጋጀውና"101 የጥበብ ጠብታዎች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።
ዶ/ር ወዳጄ ከዚህ ቀደም "የመላዕክት አለቆች በእናት ሀገር" ፣"ክልሷ ሳይኪ" እና ሌሎችንም መጻሕፍትን ለንባብ እንዳበቃ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ የተዘጋጀውና"101 የጥበብ ጠብታዎች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።
ዶ/ር ወዳጄ ከዚህ ቀደም "የመላዕክት አለቆች በእናት ሀገር" ፣"ክልሷ ሳይኪ" እና ሌሎችንም መጻሕፍትን ለንባብ እንዳበቃ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል
62ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ገጣሚ ውብአረጋ አድምጥ "አገባባዊ ድጋፍ በጋሽ ሰይፉ መታፈሪያ ግጥሞች እና ነገረ ባይራ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ሰኔ 15 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
62ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ገጣሚ ውብአረጋ አድምጥ "አገባባዊ ድጋፍ በጋሽ ሰይፉ መታፈሪያ ግጥሞች እና ነገረ ባይራ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ሰኔ 15 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የዘጋቢ ፊልም እይታ በቅብብሎሽ
(መግቢያው በነፃ ነው)
ቅብብሎሽ የተሰኘው መሰናዶ ልዩ ልዩ መርሐግብሮችን ማካሄዱን ቀጥሏል። ዛሬ ሰኔ 12 ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ "Sound track to a Coupd'etat" የተሰኘ ዘገቢ ፊልምን ጃክሮስ አካባቢ በሚገኘው ዘ ቬኒው ዌር ሀውስ ውስጥ ለተመልካች ያቀርባል።
ዘጋቢ ፊልሙ የመጀመሪያውን የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፓትሪስ ሉሙምባ አሳዛኝ የተቀናበረ ግድያና ጃዝ ሙዚቃን የዓለምአቀፍ የፖለቲካ ጥልፍልፍልፎሽ ሁነትን በረቀቀ ጥበብ ያስቃኛል ተብሏል።

📌የድምፃዊ ይሁኔ በላይ መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል
የድምፃዊ ይሁኔ በላይ የጥበብ እና የህይወት ጉዞውን የሚያስቃኝ አዲስ መጸሐፍ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ተሰምቷል።
“ፍኖተ ጥበብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው መጽሐፉ ድምጻዊ ይሁኔ በላይ ከተወለደበት ፍኖተ ሰላም እስከ አሜሪካ በሙዚቃ ህይወቱ እና በኑሮ ያሳለፈውን የሕይወት ጉዞ የሚተረክበት ነው ተብሏል።
በመጽሐፉ ዝግጅት ላይ ደራሲ አቤል ጋሼ እና መጋቢ ጥበባት አበረ አዳሙ በአርትኦት ስራ ተሳትፉበታል።
መጽሐፉ በፈረንጆቹ ሰኔ 21 2025 በአሜሪካ ሀገር የሙያ ባልደረቦቹ በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌ድምጻዊ ያሬድ ነጉ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል
(መግቢያው በነፃ ነው)
የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር ያሬድ ነጉን ጋብዟል::
የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች"ከያሬድ ጋር በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 17 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ሚዲያ ገለጸዋል።
በዕለቱ ከድምጻዊው ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::
ፕሪስቴጅ አዲስ ከያሬድ ነጉ ጋር የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ማክሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:
📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱
https://jazzio.land/register
መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!
በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ
የአርትስ ስፔሻል መረጃዎች ዋና ዋና ጉዳዮች:
1.'የትንፋሽ ውበት' የዋሽንት ኮንሰርት ነገ ይካሄዳል።
2.የደራሲ ሕይወት እምሻው መጻሕፍት በድጋሚ ታተሙ።
3.'ታላቁ ጥቁር' መጽሐፍ ላይ በነገረ መጻሕፍት ውይይት ሊካሄድ ነው።
4.የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።
5.ሶስት ሀገርኛ ፊልሞች በሀበሻ ቪው መተግበሪያ ለእይታ ይበቃሉ።
እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።
"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:
https://youtu.be/7e_TZYi6fUc?si=zXwKFb8Cq5ISWYX2
📌መልካም ምሽት

📌በ"ታላቁ ጥቁር' መጽሐፍ ዙሪያ ውይይት ይካሄዳል
በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "ታላቁ ጥቁር " የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት ንጉሤ አየለ ተካ ይገኛሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ሳምንት የተመረጠው መጽሐፍ "ታላቁ ጥቁር " የተሰኘ መጽሐፍ ሲሆን በክብር እንግዳነት ንጉሤ አየለ ተካ ይገኛሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌የዋሽንት ኮንሰርት ዛሬ ይካሄዳል
የዋሽንት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድም "የትንፋሽ ውበት" ሲል የሰየመውን የዋሽንት ኮንሰርት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 14 2017 ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በመሶብ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ያቀርባል።
በዚህ ኮንሰርት ላይ የዋሽንት ተጫዋቹ ጣሰው ወንድምና የፒያኖ ተጫዋቹ አብይ ወ/ማርያም ይጣመራሉ ተብሏል።
"የትንፋሽ ውበት" የዋሽንት ሙዚቃዊ ዝግጅት መግቢያ ዋጋውም 300 ብር እንደሆነ ተገልጿል።
በመሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ ውስጥ በዋሽንት ተጫዋችነቱ የምናውቀው ጣሰው "የትንፋሽ ውበት" የተሰኘ የዋሽንት የሙዚቃ አልበም ከአንድ ዓመት በፊት ለአድማጮች አድርሷል።

📌የሕይወት እምሻው መጻሕፍት በድጋሚ ታተሙ
ደራሲ እምሻው ሕይወት በ2007 ባርቾን በ 2010 ፍቅፋቂን በ2011 ማታ ማታና እንዲሁም በቅርቡ ለእርቃን ሩብ ጉዳይና የቡና ቁርስ የተሰኘው የወግና የአጭር ልብ-ወለዶች ስብስብ መጽሐፎችዋን ለአንባብያን አበርክታለች፡፡
ቀደሞ ብሎ ለንባብ የበቁት መጻህፍቷም ከመጻሕፍት መደብሮች መደርደሪያ ጠፋ ብለው ነበር። ትላንትም ከዓመታት በኃላ በድጋሚ ታትመው ለአንባቢያን ቀርበዋል።
ከገበያ የጠፉትን የሕይወት እምሻውን መጻሕፍት ለመሸመትና ከደራሲዋ ጋር ለመጨዋወት ዓላማ ያደረገ መርሐግብርም ሰኔ 13 2017 አመሻሹን በዋልያ መጻሕፍት ተካሂዷል።

📌"የቀራጩ ማስታወሻ " መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በቤዛኩሉ ደጀኔ የተዘጋጀው "የቀራጩ ማስታወሻ" የተሰኘ መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ ለንባብ በቅቷል።
የቤዛኩሉ ደጀን መጽሐፍ የሆነው "የቀራጩ ማስታወሻ " ለንባብ የበቃው 216 ገፆችን ይዞ ነው።
ቤዛኩሉ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የካሜራ ባለሙያ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንደ ሚዲያ ባለሙያ ሙያዊ ጉዳዮችን በሌንሶቹ ቀርጿል።
ከዚህም ባሻገር ደራሲው በዓይኑ የተመለከታቸውን እውነቶችና ትዝብቶች በጉዞ ማስታወሻነት ያሰፈረበት ነው።
ለቤዛ ኩሉ ይህ መጽሐፍ ሁለተኛው መጽሐፉ ሲሆን "የሌሊት ወፍ ድምፆች" የሚል የግጥም መድብል ከዚህ በፊት አሳትሟል።

📌ጋሻና ድል ሲኒማ ቤቶች አገልግሎት ጀመሩ
በአድዋ ድል መታሠቢያ ሙዚየም ውስጥ ለፊልም ማሳያነት የተገነቡ ጋሻና ድል የተሰኙ 2 ሲኒማ ቤቶች በቋሚነት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
ፊልም አፍቃሪዎች ከማክሰኞ ውጪ ባሉት 6ቱም የሳምንቱ ቀናት ወደ አድዋ ድል መታሠቢያ ጎራ በማለት የተመረጡ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ፊልሞችን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ሲኒማ ቤቶቹ የወቅቱን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ በመሆናቸው ለፊልም ኢንደስትሪው መነቃቃት የሚፈጥሩ ስለመሆናቸው የፊልም ባለሙያዎች ተናግረዋል።

📌"አፈር ልክ" የሥዕል አውደርዕይ በእይታ ላይ ነው
የሠዓሊ አብዲ የኃላሸት የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "አፈር ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ ሰኔ 11 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 30 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የሠዓሊ አብዲ የኃላሸት የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "አፈር ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ ሰኔ 11 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 30 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"እውነት እና ፍቅር" መንፈሳዊ ተውኔት ለእይታ ይበቃል
በሄኖክ በቀለ ተደርሶ የተዘጋጀው "እውነት እና ፍቅር" የተሰኘው መንፈሳዊ ተውኔት የፊታችን ሰኔ 29 2017 ዓ.ም በቫምዳስ ሲኒማ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።
መንፈሳዊ ተውኔት የኃይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ይመረቃል።
ተውኔቱ ምንም እንኳን ኃይማኖታዊ ጭብጥ ቢኖረውም ማንም ሰው ሊያየው በሚችለው መልኩ መቅረቡንም አዘጋጆቹ ለኢቨንት አዲስ ሚዲያ መረጃውን ተገልጿል።
የ55 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ይህ ተውኔት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የንግድ ተውኔት መሆኑንም ሰምተናል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
በሄኖክ በቀለ ተደርሶ የተዘጋጀው "እውነት እና ፍቅር" የተሰኘው መንፈሳዊ ተውኔት የፊታችን ሰኔ 29 2017 ዓ.ም በቫምዳስ ሲኒማ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።
መንፈሳዊ ተውኔት የኃይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ይመረቃል።
ተውኔቱ ምንም እንኳን ኃይማኖታዊ ጭብጥ ቢኖረውም ማንም ሰው ሊያየው በሚችለው መልኩ መቅረቡንም አዘጋጆቹ ለኢቨንት አዲስ ሚዲያ መረጃውን ተገልጿል።
የ55 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ይህ ተውኔት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የንግድ ተውኔት መሆኑንም ሰምተናል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌"ልጄስ" የቴሌቪዥን ድራማ ዛሬ ይፈፀማል
ልጄስ ድራማ ዛሬ ረብዕ ሰኔ 18 2017 ፍፃሜውን ያገኛል። የመጨረሻዎቹን ሶስቱ ክፍሎች ክፍል 40 ፣ 41 ፣ 42 ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በቃና ቲቪ እና በቃና የዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
እስከ አምስተኛው ክፍል ድረስ በካናል ፕላስ እና በቃና ቲቪ ዩቲዩብ ቻናል እየተላለፈ የቆየው"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል በካናል ፕላስ ሲኒማ ብቻ ሲተላለፈ እንደነበር ይታወሳል።
"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል ከሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቃና ቴሌቪዥን ሲሰራጭ ቆይቷል።

📌የጥበብ ቅምሻና የልምድ ማካፈያ መድረክ
(መግቢያው በነፃ ነው)
በአቢሲኒያ የሥነጥበብ ተቋም የተዘጋጀው የጥበብ ቅምሻና የልምድ ማካፈያ መድረክ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 21 2017 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው በተቋሙ ቢሮ ይካሄዳል።በዕለቱም ከ40 ዓመት በላይ በሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት የማስተማር ልምድ ያካበቱት አርቲስት አበበ ካሣዬ ስለ ዲዛይን፣ኢሉስትሬሽን፣ፊደል ጥናት፣ሲንቦልና ሎጎ ዲዛይን ያላቸውን ልምድ ያካፋላሉ ተብሏል።
ፕሮግራሙ የመለማመጃ ክፍል ስለሚኖረው እርሳስና ወረቀት ይዛችሁ መምጣት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

📌የማ ሙዚቃዎቿን የምታቀርብበት ፌስቲቫል
(መግቢያው በነፃ ነው)
ሁለተኛው ዓለምአቀፍ የታላቁ ደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ አገራት ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሊካሄድ ነው።
ፌስቲቫሉ ከአርብ ሰኔ 20 ጀምሮ እስከ እሁድ ሰኔ 22 ድረስ ለሶስት ቀናት እንደሚካሄድም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የጃማይካ፣ ኩባ፣ ኡራጋይ፣ቱኑዥያ፣ካሜራንና የሌሎችም ሀገራት ከያኒያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
በፌስቲቫሉ ላይ በዕለት ቅዳሜ ድምጻዊት የማርያም ቸርነት (የማ) የሙዚቃ ዝግጅቷን እንደምታቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያመለክታል። የፌስቲቫሉ መግቢያ በነፃ ነው።