📌ጋሻና ድል ሲኒማ ቤቶች አገልግሎት ጀመሩ
በአድዋ ድል መታሠቢያ ሙዚየም ውስጥ ለፊልም ማሳያነት የተገነቡ ጋሻና ድል የተሰኙ 2 ሲኒማ ቤቶች በቋሚነት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
ፊልም አፍቃሪዎች ከማክሰኞ ውጪ ባሉት 6ቱም የሳምንቱ ቀናት ወደ አድዋ ድል መታሠቢያ ጎራ በማለት የተመረጡ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ፊልሞችን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ሲኒማ ቤቶቹ የወቅቱን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ በመሆናቸው ለፊልም ኢንደስትሪው መነቃቃት የሚፈጥሩ ስለመሆናቸው የፊልም ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌"አፈር ልክ" የሥዕል አውደርዕይ በእይታ ላይ ነው
የሠዓሊ አብዲ የኃላሸት የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "አፈር ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ ሰኔ 11 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 30 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
የሠዓሊ አብዲ የኃላሸት የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "አፈር ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ረቡዕ ሰኔ 11 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 30 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://www.tg-me.com/EventAddis1
"እውነት እና ፍቅር" መንፈሳዊ ተውኔት ለእይታ ይበቃል
በሄኖክ በቀለ ተደርሶ የተዘጋጀው "እውነት እና ፍቅር" የተሰኘው መንፈሳዊ ተውኔት የፊታችን ሰኔ 29 2017 ዓ.ም በቫምዳስ ሲኒማ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።
መንፈሳዊ ተውኔት የኃይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ይመረቃል።
ተውኔቱ ምንም እንኳን ኃይማኖታዊ ጭብጥ ቢኖረውም ማንም ሰው ሊያየው በሚችለው መልኩ መቅረቡንም አዘጋጆቹ ለኢቨንት አዲስ ሚዲያ መረጃውን ተገልጿል።
የ55 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ይህ ተውኔት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የንግድ ተውኔት መሆኑንም ሰምተናል።

📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌"ልጄስ" የቴሌቪዥን ድራማ ዛሬ ይፈፀማል
ልጄስ ድራማ ዛሬ ረብዕ ሰኔ 18 2017 ፍፃሜውን ያገኛል። የመጨረሻዎቹን ሶስቱ ክፍሎች ክፍል 40 ፣ 41 ፣ 42 ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በቃና ቲቪ እና በቃና የዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
እስከ አምስተኛው ክፍል ድረስ በካናል ፕላስ እና በቃና ቲቪ ዩቲዩብ ቻናል እየተላለፈ የቆየው"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል በካናል ፕላስ ሲኒማ ብቻ ሲተላለፈ እንደነበር ይታወሳል።
"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ ከክፍል አምስት በኃላ ያለው ቀጣይ ክፍል ከሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቃና ቴሌቪዥን ሲሰራጭ ቆይቷል።
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1

📌የጥበብ ቅምሻና የልምድ ማካፈያ መድረክ
(መግቢያው በነፃ ነው)
በአቢሲኒያ የሥነጥበብ ተቋም የተዘጋጀው የጥበብ ቅምሻና የልምድ ማካፈያ መድረክ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 21 2017 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው በተቋሙ ቢሮ ይካሄዳል።በዕለቱም ከ40 ዓመት በላይ በሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት የማስተማር ልምድ ያካበቱት አርቲስት አበበ ካሣዬ ስለ ዲዛይን፣ኢሉስትሬሽን፣ፊደል ጥናት፣ሲንቦልና ሎጎ ዲዛይን ያላቸውን ልምድ ያካፋላሉ ተብሏል።
ፕሮግራሙ የመለማመጃ ክፍል ስለሚኖረው እርሳስና ወረቀት ይዛችሁ መምጣት ትችላላችሁ ተብላችኋል።

📌የማ ሙዚቃዎቿን የምታቀርብበት ፌስቲቫል
(መግቢያው በነፃ ነው)
ሁለተኛው ዓለምአቀፍ የታላቁ ደቡባዊ ንፍቀ-ክበብ አገራት ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሊካሄድ ነው።
ፌስቲቫሉ ከአርብ ሰኔ 20 ጀምሮ እስከ እሁድ ሰኔ 22 ድረስ ለሶስት ቀናት እንደሚካሄድም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የጃማይካ፣ ኩባ፣ ኡራጋይ፣ቱኑዥያ፣ካሜራንና የሌሎችም ሀገራት ከያኒያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
በፌስቲቫሉ ላይ በዕለት ቅዳሜ ድምጻዊት የማርያም ቸርነት (የማ) የሙዚቃ ዝግጅቷን እንደምታቀርብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያመለክታል። የፌስቲቫሉ መግቢያ በነፃ ነው።

📌አብርሆት ቤተመጻሕፍት በጊዜያዊነት ተዘጋ
የአብርሆት ቤተመጻሕፍት በ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምክንያት መደበኛ አገልግሎቱ በጊዜያዊነት ተቋርጧል።ለሳምንታትም በጊዜያዊነት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቤተመጻሕፉም ስለዚህ ጉዳይ ተከታዩን ብሏል"አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሚሰጥባቸዉ ተቋማት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።ስለሆነም ተቋሙ ከሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለዝግጅት እና ለፈተና አገልግሎት ስለሚውል የወትሮ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን በአክብሮት ልናሳውቅ እንወዳለን"።

📌አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ የተማሪዎች ምርቃት ስነ-ስርዓት እና የተቋሙን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ያከብራል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን 75ኛ ባች ተማሪዎች ያስመርቃል።
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ ይዘከራል ተብሏል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመባል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን አፍርቷል፡፡
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን 75ኛ ባች ተማሪዎች ያስመርቃል።
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ ይዘከራል ተብሏል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመባል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን አፍርቷል፡፡
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌አንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ የጃንቦ ሪል ስቴት አምባሳደር መሆኑን ሪል ስቴቱ ይፋ አድርጓል።
በቅርቡ 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ በቅርቡ ከዚሁ ሪል ስቴት የመኖሪያ ቤት እንደተበረከተለት ይታወሳል።
ጋዜጠኛውና የሪልስቴት ተቋሙ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።
የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ደበበ ሰይፋ ጃምቦ ሪል ስቴት በጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ መወኩሉ ትርፋማ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ሪልስቴት ተቋሙ እስካሁን 700 የሚሆኑ ቤቶችን ለቤት ባለቤቶች ገንብቶ ማስረከቡን ስራ አስፈፃሚው መናገራቸውን አራዳ ሰምቷል።
የሪል ስቴት ተቋሙ እና የጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ የሥራ ስምምነት ለሦስት ዓመት ይቆያል ተብሏል።
የአምባሳደርነት ሥምምነት መፈረሜ ቀጣይ ሥራዎቼ ላይ ትኩረት አድርጌ እንድሰራ ያደርገኛል ያለው ደግሞ ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ ነው።
በህይወት ዘመኔ የምችለው እና የማውቀው ሥራ ጋዜጠኝነት ብቻ ነው ያለው ጋዜጠኛው ሙያው ግን የልፋትን የሚከፍል ባለመሆኑ ብዙ ሊሰራበት ይገባል ሲል አሳስቧል።

📌ሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል የፊታችን ሰኞ ይዘጋል
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ በቀጥታ ስርጭት ለተመልካቾች ሲያሰራጭ የቆየው ዲ ኤስ ቲቪ ሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል ከፊታችን ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከቻናሉ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም ቻናሉ የተለያዩ የስፖርት ይዘቶችን በሌሎች የሱፐር ስፖርት ቻናሎች መከታተል ትችላላችሁ ብሏል።
በያዝነው ዓመት ከወራት በፊት ካናል ፕላስ ቻናልም ከኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ ስርጭቱን አቋርጦ መውጣቱ ይታወሳል።

📌ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙና ውቢት ያረጋል የክብር እንግዳ የሆኑበት ልዩ ዝግጅት የፊታችን እሁድ ይካሄዳል
(መግቢያው በነፃ ነው)
በሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በፒያሣ ካምፓስ የሰለጠኑ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን የፊታችን እሑድ ሰኔ 22 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚያቀርቡ ሲሆን በዕለቱም ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የጋዜጠኝነት ሕይወታቸውን እና ልምዳቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል።
በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የተመራቂ ተማሪዎችን የመመረቂያ ስራዎች እንዲከታተሉ እንዲሁም ለጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል መጠየቅ የሚፈልጉትን በማንሳት በልምድ ልውውጡ ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

📌"ቢራቢሮ" ተውኔት የፊታችን ሰኞ ለመድረክ ይበቃል
በኤልያስ ቤተማርያም ተፅፎ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው “ቢራቢሮ” የተሰኘው ተውኔት ለእይታ ሊበቃ ነው።
"ቢራቢሮ" ሙዚቃዊ ተውኔት ሲሆን የፊታችን ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ለእይታ ይበቃል ተብሏል።
በተውኔቱ ላይ ሩሐማ ኃ/ሚካኤል ፣ ዮናታን መኮንን፣ እየሩሳሌም ገ/ስላሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።
የተወኔቱ ፕሮዳክሽን ማናጀሮች ሀና ታዬ(እርጎዬ) እና ሔኖክ ተሾመ ናቸው።

📌የደጃዝማች ከበደ ተሰማ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
የክቡር ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ‹‹ነበር እንዳይረሳ - ከታሪክ ማስታወሻ ባሻገር›› የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፍ በራሳቸው በደጃዝማች ከበደ ተሰማ ተዘጋጅቶ ከ52 ዓመታት በኋላ ነገ ለአንባቢያን ይቀርባል።
የመጽሐፉ የምርቃት ሥነሥርዓት በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር) ፣በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አዳራሽ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት (4፡00) ጀምሮ ይካሄዳል ።
ደራሲው ከዚህ በፊት በብዙ አንባቢያንና የታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ተወዳጅ በነበረው ‹‹የታሪክ ማስታወሻ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ይታወሳሉ፡፡
በአዲሱ መጽሐፋቸው፣ ደራሲው በሕይወተ ሥጋ እያሉ ባለፉባቸዉ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ኹነቶች ውስጥ የዐይን እማኝ የነበሩባቸውን ጉዳዮች ጨምሮ፣ ስለ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የአስተዳደር ዘይቤዎችና ልምዶች ፣ ስለ ልጅ ኢያሱ ምኒልክ አነሳስና ፍፃሜ ፣ ሰለ አፄ ኃይለሥላሴ የንግሥና ክብረ በዓል ሥርዓትና በ1953 ዓ.ም ተሞክሮ ስለከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ያዩትን ፣የነበሩበትንና የታዘቡትን ለአንባቢያን አቅርበዋል ።
በዚሁ ወቅት በመጽሐፉ አርትዖት ላይ በቀጥታ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለና ዶክተር የራስወርቅ አድማሴ ግንዛቤያቸውን ያቀርባሉ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የደራሲው ቤተሰቦችና ወዳጆች የሚታደሙ ሲኾን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዉ አጠር ያለ ውይይት ይደረጋል፡፡
መጽሐፉ በዕለቱ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለገበያ የሚውል ሲሆን በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች ይገኛል፡፡

📌ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ሊመስገን ነው
ዘንድሮ 75ተኛ ዓመት የልደት በዓሉን የሚያከብረው ተወዳጁና ተከባሪው ደራሲና መምህር ኃይለመለኮት መዋዕል ነገ በሚካሄድ ልዩ መርሐግብር ይመሰገናል።
ይህ መርሐግብር በስብሐቲዝም አዘጋጆች የተሰናዳ ሲሆን ነገ እሁድ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊው ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዕለቱም ደራሲያኑ ሣህለስላሴ ብርሃነ ማርያምና ዘነበ ወላ ሀሳቦቻቸውን የሚያጋሩበትን ጭምሮ ልዩ ልዩ መርሐግብሮች እንደሚካሄዱ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

📌"ቃል እና ቅኔ" ልዩ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል
ሙሉ ገቢው ለበጎ ዓላማ የሚውለው "ቃል እና ቅኔ" የተሰኘ ልዩ መርሐግብር ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ዘነበ ወርቅ (ኢቢሲ ማሰልጠኛ ተቋም ) ኦሮሚያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ ልዩ መሰናዶ ላይ ትላልቅ የኪነጥበብ ባለሞያዎች የሚገኙ ሲሆን የግጥም፣ ወግ፣ መነባንብን ጨምሮ የተለያዩ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል።
ትኬት መሸጥ ተጀምሯል!!
በቴሌብር
0929521135 ዳግም
0913742370 ፉአድ
በንግድ ባንክ 1000345483679 Dagim Sisay
እያስገባችሁ ደረሰኙን በዚሁ ስልክ በቴሌግራም ላኩልን።
◈ ወዳጅዎን በመጋበዝ ዓላማውን ይደግፉ!!
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
ሙሉ ገቢው ለበጎ ዓላማ የሚውለው "ቃል እና ቅኔ" የተሰኘ ልዩ መርሐግብር ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ዘነበ ወርቅ (ኢቢሲ ማሰልጠኛ ተቋም ) ኦሮሚያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ ልዩ መሰናዶ ላይ ትላልቅ የኪነጥበብ ባለሞያዎች የሚገኙ ሲሆን የግጥም፣ ወግ፣ መነባንብን ጨምሮ የተለያዩ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል።
ትኬት መሸጥ ተጀምሯል!!
በቴሌብር
0929521135 ዳግም
0913742370 ፉአድ
በንግድ ባንክ 1000345483679 Dagim Sisay
እያስገባችሁ ደረሰኙን በዚሁ ስልክ በቴሌግራም ላኩልን።
◈ ወዳጅዎን በመጋበዝ ዓላማውን ይደግፉ!!
ለተጨማሪው:https://www.tg-me.com/EventAddis1
📌በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌በዓለም ሲኒማ በዚህ ሳምንት እነዚህ ተውኔቶች ለተውኔት አፍቃሪን ይቀርባሉ።
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
መልካም መዝናኛ ይሁንላችሁ !!
https://www.tg-me.com/EventAddis1/6236
📌አፍሪካዊቷን ጋዜጠኛ “ቆንጆ ነሽ” በማለት ያደነቁት ዶናልድ ትራምፕ መነጋገሪያ ሆነዋል
በነጩ ቤተ -መንግስት ለዘገባ የተገኘችውን አፍሪካዊት ጋዜጠኛ ቆንጆ ነሽ በማለት አድናቆታቸውን የገለጹት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት መነጋሪያ ሆነዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዴሞክራቲከ ሪፐብሊክ ኮንጎንና ረዋንዳን ለማስታረቅ በተሰናዳው ስነ-ስርዓት ላይ በነጩ- ቤተ መንግሰት ለዘገባ የተገኘችውን አንጎላዊት ጋዜጠኛ ሃርያና ቬራስን ነው ቆንጆ ነሽ ሲሉ ያደነቋት፡፡
እንዳንች ያሉ ቆነጃጀት ጋዜጠኞች ቢበዙ እንዴት መልክም ነበር ሲሉም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
"ይህን ማለቴ ትክክል ላይሆን ይችላል” ቢሆንም “በጣም ውብ ናት" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
Via ebcdotstream

በቀነኒ የቲክቶክ ገፅ የተለቀቀው ፎቶ መነጋገሪያ ሆነ
ከወራት በፊት ህይወቷ ያለፈው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ በሕይወት እያለች ትጠቀምበት በነበረውና ከ636 ሺ በላይ ተከታይ ባለው የቲክቶክ አካውንቷ ጥቃት እንደደረሰባት የሚያሳይ ፎቶ ተለቋል::
በሟች የቲክቶክ ገፅ ጥቃት እንደሚደረስባት የሚያሳይ ፎቶ ከተለቀቀ በኃላም በርካቶች እየተነጋገሩበት እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ተመልክቷል።
በቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ እስር ቤት የቆየው እጮኛዋ አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ በትላንትናው ዕለት በተካሄደው የሀጫሉ አዋርድ ተሸላሚ እንደነበረ የሚታወስ ነው::