Telegram Web Link
Audio
23) የትጉኃን መማክርት መመሪያ እና ትምህርት ክፍል 1
ሐምሌ 25/2012 ዓ.ም
Audio
24) የትጉኃን መማክርት መመሪያ እና ትምህርት ክፍል 2
ሐምሌ 29/2012 ዓ.ም
27👏1
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
24) የትጉኃን መማክርት መመሪያ እና ትምህርት ክፍል 2 ሐምሌ 29/2012 ዓ.ም
👆👆👆📌 የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም አዲስ ነውና ዛሬም ነገም ልክ እንደ ትላንቱ ልናዳምጠው፡ ልንመከርበት፡ ልንጽናናበት ይገባል !
43👏4
💚💛❤️ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የሐዋርያት ጾም አደረሳችሁ አደረሰን!

ጾሙን የበረከትና የንስሐ ፍሬ የምናፈራበት ያድርግልን።

🟩 🟩 🟩
🟨 🟨 🟨
🟥 🟥 🟥
ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር፤
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም፤
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
www.tg-me.com/christian930
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
42
ሩሲያ ድሮኖቿን በዩክሬን ከተሞች ላይ አዘነበች !!

ሩሲያ በ 24 ሰዓታት በ206 ድሮኖችና በ9 ሚሳኤሎችን በመላክ በ ሰሜናዊ ምስራቅ፣ በሰሜንና በሁለቱ ሀገራት አቅራቢያ በሚገኙ ዩክሬይን ከተሞች ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተነግሯል ፡፡

በዚህ ከሳምንት በፊት ዩክሬን ለፈፀመችው የአፀፋ ምላሽ እንደሆነ በተነገረው 206 ድሮኖችን ሚሳኤሎች በተሳተፉበት ጥቃት የዩክሬይን 2ተኛ ትልቋ ከተማ የሆነችው ካርኪቭን ጨምሮ የዩክሬን በርካታ ከተሞች ላይ የተፈፀመ ሲሆን በጥቃቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መዉደማቸዉ ተዘገቧል ።

የዩክሬይን አየር ሀይል ባወጣው መግለጫ ዛሬ ሩሲያ 206 ድሮኖችንና 9 ሚሳኤሎችን ወደ ሃገሪቱ መላኳን ከእነዚህም መካከል 87 ድሮኖችን ማክሸፍ መቻሉን ከተላኩትም መካከል 48 ኢራን ሰራሽ መሆናቸዉን አስታውቋል፡፡

እንደመግለጫው ከሆነ በዛሬው 17 ስፍራዎች ኢላማ ዉስጥ በማስገባት በተፈፀመ ጥቃት 80 ድኖሮችን ደግሞ በኤሌክትሮኒክ ሲስተም ከራዳር ውጭ መቻሉን፣ ስድስት ክሩዝ ሚሳኤሎችንና አንድ ኢስካንደር ሚሳኤልን፣ በአየር መቃወሚያ በመጣል ሊደርስ የነበረዉን የከፋ አደጋ ማስቀረቱን አስረድቷል፡፡

የዩክሬይን አየር ሀይል እንደ ወጣዉ መረጃ ከሆነ በዛሬው ጥቃት ሩሲያ በ10 ቦታዎች ላይ ኢላማዋን አሳክታ ጥቃት የፈፀመች ሲሆን በተጨማሪ ሰባት ቦታዎች ደግሞ በአየር መቃወሚያ የተመቱት ጦር መሳሪያዎች ስብርባሪዎች ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ብሏል ።

በዛሬው ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ የተመታችው የዩክሬይን 2ተኛ ትልቋ ከተማ የሆነችው ካርኪቭ ከንቲባ ኢጎር ተረኮቭ ስለጥቃቱ ሲናገሩ ‹‹ይህ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ጠንካራው የሚባል ጥቃት ደርሶብናል›› ብለዋል፡፡

ሞስኮ እንደገለፀው አርብ ጥቃቱ የተፈፀመው የዩክሬን ለፈፀመችው "የሽብር ድርጊት" በሩሲያ የተሰጠ ምላሽ ነው ። ጥቃቶቹም ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ። ሲል አሳዉቋል ።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በበኩላቸዉ ብሄራዊ ጥቅማችንን፣ ደህንነታችንን እና የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ ይመለከታል። “ለእኛ ይህ የህልውና ጉዳይ ነው” በማለት የአፀፋ ምላሹን አስፈላጊነት አስረድተዋል ።
25🔥5
🟢🟡🔴
ሰኔ 2 | #ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ እና #ቅዱስ_ኤልሳዕ_ነቢይ ፍልሠተ ዐፅማቸው ኾነ፨

የቅዱስ ዮሐንስ ራስ በአንድ አርዮሳዊ እጅ ሳለች፥ መጥምቁ ዮሐንስ ለአባ አንያኖስ ተገለጠለትና ራሱ የምትገኝበትን ቦታ ነገረው። እንደዛሬው ባለ ዕለት ግንቦት 30 ቀን ከዚያ አወጣት፡፡ ይህም የካቲት 30 ቀን ከአገኟት በኋላ ዳግመኛ ከነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ ያገኙበት ነው፡፡

በ350 ዓ.ም አካባቢ ክፉ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር። ለዚህ እንዲረዳው በ70 ዓ.ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት።

ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ አውጥተህ አቃጥል" አሉት።

ሲቆፈር የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው ሰኔ 2 ቀን ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል። እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል።

በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤ/ክናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል። በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል።
🍀

በዚችም ቀን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የአክስት ልጅ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ እሳት ከሰማይ አውርደው በፈንታሌ ተራራ ላይ ሰሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ 473,000 አጋንንት በአንድ ጊዜ ያጠፉ ታላቁ #አቡነ_ቀውስጦስ_ዘመሐግል መታሰቢያቸው ነው።

የታናሽ ወንድማቸው የዐፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ ዐፄ አምደ ጽዮን የአባቱን እቁባት በማግባቱ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሄደው ንጉሡን ቢገሥጹት በግዞት ወስዶ ጎናቸው በጦር ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡

ልደታቸውም ሆነ ዕረፍታቸው ከእመቤታችን ልደትና ዕረፍት ጋር አንድ ቀን ነው።

T.me/Ewnet1Nat
40🙏1
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

🥢 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ የትዕቢተኛዎችንም ኵራት አዋርዳለሁ።
ትንቢተ ኢሳያስ 13፡11

በ 3/10/2017 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
33
Audio
የእህታችን ወለተ ሥላሴ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
በወንድሟ ገብረ ማርያም የቀረበ
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
3/10/2017 ዓ.ም


👉 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫ እና መመስገኛ ምድር
👉 ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
👉 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
👉 ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ
20250609_231825
Your recordings
የእህታችን ወለተ ጻድቅ ልጆች እጹብ ድንቅ ምስክርነት
በእናታቸው ወለተ ጻድቅ የቀረበ
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
3/10/2017 ዓ.ም


👉  ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም
👉 ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ሀገር አይድንም
👉 ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ቤተሰብ አይድንም ።
20250609_233533
Your recordings
የእህታችን ወለተ ጻድቅ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስተ ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
3/10/2017 ዓ.ም


👉 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫ እና መመስገኛ ምድር
👉 ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
👉 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
👉 ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ
21
2025/07/12 13:53:15
Back to Top
HTML Embed Code: