ግብፅ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ ለፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ አሰማች
ግብፅ በትናንትናው ዕለት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ “ዓለም አቀፍ ሕግን ጥሳለች” ስትል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ አቤቱታዋን አሰምታለች።
በደብዳቤው የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የህዳሴው ግድብ ምርቃት “በሕግ ሊደገፍ የማይችል ሕገወጥ የአንድ ወገን ተግባር” ነው ብለዋል።
አያይዞም “ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የህልውና ጥቅም በቀላሉ ትተዋለች ማለት ከንቱ ምኞት ነው” ሲል ገልጾ፣ “ኢትዮጵያ የጋራ በሆነው የውሃ ሃብት ላይ በብቸኝነት ቁጥጥር እንድታደርግ ግብጽ አትፈቅድም” ሲል አጽንኦት ሰጥቷል።
ካይሮ የህልውና ጥቅሟን ለማስከበር እንዲሁም በአለም አቀፍ ህግ እና በተባበሩት መንግስታት ቻርተር ስር የተፈቀዱትን ማናቸውም እርምጃዎች ለመውሰድ እንደምትችል መግለጿን የቱርኩ አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል።
ግብጽ አቤቱታዋን ያቀረበችው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ትናንት ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የቀጠናው ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በይፋ መመረቁን ተከትሎ ነው።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከተገኙ የቀጠናው ሀገራት መሪዎች መካከልም የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ይገኙበታል።

❤16
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
🟢🟡🔴
መስከረም 1 | ርእሰ ዐውደ ዓመት
#ርእሰ_ዐውደ_ዓመት
በግእዝ ዐውደ ዓመት ይባላል - ርእሰ ዐውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ተባለ።
[🌼] በዚህች ቀን ከ9ኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ የከበረ መልአክ ራጉኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል መስከረም 1 ቀን ከሊቃነ መላእክት በብርሃናት ላይ የተሾመበት ዕለት ነው።
ግንቦት 1 ቀን ለታላቁ አባት ለሄኖክ ምሥጢራትን የገለጸበት በዓሉ ነው፡፡
በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ነቢዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡
እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው።
የመልአኩ ልዩ ቃልኪዳን፦
"የራጉኤል አምላክ ይቅር በለኝ በማለት አንዲት ቃልስ እንኳን ቢናገር እንደ ወዳጄ እንደ አብርሃም፣ እንደ ባለሟሌም እንደ ይስሐቅ፣ እንደ አከበርኩትም እንደ ያዕቆብ ክብርን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ። በራሱ ላይም አክሊል አቀዳጀዋለሁ። ረጅም ዘመናት ሰፊ፣ ወራትም እሰጠዋለሁ" ሲል ቃሉን ሰጥቶታል፡፡
[🌼] ዳግመኛም በዚህች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሐዋርያ #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ በአሸዋ ከረጢት ውስጥ ተከቶ ወደ ባሕር በመጣል ምስክር ሆኖ ዐረፈ።
[🌼] በዚችም ዕለት #ጻድቁ_ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ተፈወሰ።
[🌼] ይህች ቀን የታላቁ የቊልዝም ሰው የሆነ ፍጹም ጻድቅ፣ ሰይጣንን አስሮ ዐሥራ አራት ሰው ሊይዙት የማችሉትን ደንጊያ ያሸከመው #የአባ_ሚልኪ የዕረፍት በዓሉ ነው።
#እንኳን_አደረሳችሁ።
T.me/Ewnet1Nat

❤50
🌼 🌼 🌼 እንኳን አደረሳችሁ 🌼 🌼 🌼
...ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትኾኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ›› በማለት እንዳዘዘን (፩ኛ ቆሮ. ፭፥፯) በኀጢአት፣ በተንኮል ፣ በዘረኝነት፣ እርሾ የተበከለውን ሰውነታችንን በጽድቅ ሕይወት እናድሰው፡፡
...ክፋ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርገዉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ። ገና ጥቂት ኃጢአተኛም አይኖርም፤ ትፈልገዋለህ ቦታዉንም አታገኝም፤ ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ። በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል። ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል፤ እግዚአብሔር ይስቅበታል። ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።
#መዝሙረ_ዳዊት 36(37)፥ 9-10
ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር
ኢትዮጵያ ርስት ድንግል ማርያም
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ኢትዮጵያ የዓለም ገዥ።
🌼 🌼 🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼 🌼 🌼

❤56👍1
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
🟢🟡🔴
መስከረም 2 | የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ #አጥማቂው_ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው፦
ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።
ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር። ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች። መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።
የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች። ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።
ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት። እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው።
ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ፤ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።
ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ። ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጧት። እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።
በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።
ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም አለች። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።
#እንኳን_አደረሳችሁ
◦🌿◦🌼◦🌿◦

❤25
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
🍀🌼🌼🌼🍀
ልዩ ቃልኪዳን ከገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
በወር በወሩ መጠመቅ ባይቻለው መስከረም ሁለት ቀን ይጠመቅ የሠራው ኃጢአቱ ሁሉ ፈጽሞ ይሠረይለታል፡፡
🌼🍀🍀🍀🌼
ሙሉውን ከታች የመብረቅ ⚡ ምልክቱን 👇 ተጭነው ይመልከቱ።

Telegraph
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ልዩ ቃልኪዳን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፨ የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ከፈጣሪው የተቀበለው ቃልኪዳን፦ {🌼} የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ገድል ሲነበብ ውኃ አምጥቶ በበላዩ ላይ አንብቦ፣ አስነብቦ፣ የገድሉ መጽሐፍ የተነበበበትን ውኃ የተጠመቀውን፥ በሚጠመቁ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ወደርሱ መጥቶ ፊቱን በትምእርተ መስቀል አርአያ በእርሱ ስም ዮሐንስ ብሎ ያትመዋል። እስከ ሰማኒያ ዓመት የሠራው ኃጢአቱ…
❤31
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ዋኖቻችንን እንወቅ ❗️)
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አራት (4)
(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
✨መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማነው?
🌻 ሰኔ 30 - የተወለደበት
🌻 መስከረም 2 - ያረፈበት
🌻 መስከረም 1 - ቃልኪዳን የተቀበለበት
🌻 መስከረም 26 - ፅንሰቱ
🌻 የካቲት 30 - ቅድስት እራሱ የተገኘችበት
🌻 ሚያዝያ 15 - ቅድስት እራሱ 15 ዓመታት ከሰበከች በኋላ ዐረፈች።
🌻 ጥቅምት 30 - በአርብያ ምድር እራሱ የታየችበት
🌻 ጳጉሜን 1 - የታሰረበት
🌻 ኅዳር 12 የመታሰቢያ በዓሉ
🌿 ሕይወቱና ተጋድሎው
🌻 ቃልኪዳኑና
🌹 ሰማዕትነቱ...
📌 ቁጥር 1) ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወቱን ያንብቡ👇
🫴 https://telegra.ph/መጥምቀ-መለኮት-ቅዱስ-ዮሐንስ-ማን-ነው-11-08
📌 ቁጥር 2) ከመድኃኔዓለም የተቀበለውን ልዩ ቃልኪዳን ያንብቡ👇
🫴 https://telegra.ph/ለመጥምቁ-ዮሐንስ-የተሰጡት-ልዩ-ቃልኪዳኖች-11-08
3) በትረካ (በድምፅ) ለማዳመጥ 👇
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/16080
📌 ሙሉውን ታሪክ ያስተውሉ!

ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡
ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡
የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
❤25👍6
ከኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_በተለያዩ_ጊዜያት_የተሰጡ_መግለጫዎች_ክፍል_፪_.pdf
4 MB
📩 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫዎች
በተለያዩ ጊዜያት የተሰጡ በpdf
ክፍል-፪
🔗 ክፍል-፩ በpdf ከአሁን በፊት ተዘጋጅቶ ተለቆላችኋል ይኼ ደግሞ ከዚያ ቀጥሎ ያሉት በመግለጫዎች የያዘ pdf ፋይል ነው።
ተጠቀሙበት!
2/01/2018 ዓ.ም

❤42🔥1
ሰይፍ፡በግብጽ፡ላይ፡ይመጣል፥ሁከትም፡በኢትዮጵያ፡ይኾናል፤የተገደሉትም፡በግብጽ፡ውስጥ፡ይወድቃሉ፥ብዛቷንም፡ይወስዳሉ፥መሠረቷም፡ይፈርሳል።
#ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 30:4
#ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 30:4
❤48
በአዲስ አበባ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የስድስት ወር እና የአመት ከሰባት ወር ህጻናትን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ።
በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ራዕይ ጤና ጣቢያ አካባቢ በትላንትናው ዕለት በግምቱ 9:45 አካባቢ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
አደጋው የደረሰው በሙያዋ ነርስ የሆነች እናት በስድስት ወር እና በአመት ከሰባት ወር ልጆቿ ፣ በሰራተኛዋ እንዲሁም ቡና ለመጠጣት ህጻን ወንድ ልጇን ይዛ በመጣች ጎረቤቷ ላይ ነው።

❤18😭11🔥2
መስቀል አደባባይ አደጋ‼️
በመስቀል አደባባይ ዛሬ አመሻሹን ድንገተኛ አደጋ መድረሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
በርካታ አምቡላንሶች የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እያመላለሱ ሲሆን በአካባቢው በርካታ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች እንደሚታዩ የአይን እማኞች ገልፀዋል።
የአደጋው መንስኤ በግልጽ ባይታወቅም የህዳሴ ግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ ነገ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በመዘጋጀት ላይ የነበረ መድረክ ወድቆ ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ለተጎዱ ሰዎች መልካሙን ሁሉ እንመኛለን።
(አዩዘሀበሻ)

❤14🔥5
🔆 የእግዚአብሔርን መልዕክት በሁሉም ሚድያ ለዓለም ሁሉ አድርሰናል፡ ሰሚ የለም የሚጠፋ የበዛም ለዛ ነው‼️
▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰
"እውነት አንድ ናት ወገኖቼ ፡፡ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት ፡፡ ይህቺ ናት እውነቴ ፤ ይህቺ ናት እምነቴ ፤ ይህቺ ናት ፡ ለእናንተ መዳኛ መንገድ ፡ ይህች ናት ፡ እኔን የምታገኙበት መንገድ ፤ እኔ የተከልሁት እውነት ፡ ይሄ ነው ፡፡ በዚህ ነው የምታተርፉት ብሎ ፡ ቸሩ መድኃኒዓለም አስቀምጦት ከሄድ ፡ ስንት ዘመን ተቆጠረ ወገኖቼ? በሺህ ቤት! ሰው ግን አይሰማም ፡፡ እንዲያውም ይሄንን እውነት ለማጥፋት ፡ የማያደርገው ዘመቻ የለም ፤ የማያደርገው ጥፋት የለም። ይህ ደግሞ ፡ የምታዩት ነው ፡፡ የእውነት ሰዎችን ፡ ስንቶችን አጥፍተዋል? የእውነትን መንገድ ፡ ስንቶቹ ለማጥፋት ታግለዋል? ዛሬ በግልጽ እንደምታዩት ፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ያልተሰለፈ ኃይል አለ? መንግሥታት ሁሉ በግልጽ ፡ ሽፋንም የለውም ፤ ድብቅም የለውም። ተዋሕዶን እናጠ ፋለን ፤ ይህቺ የእግዚአብሔር እውነት ናት ፤ እሷን እናጠፋለን ፤ ሕዝቡን ፡ ይሄንን ያዘለውን ሕዝብ በሙሉ እናጠፋዋለን ፤ እናፈራርሳታለን ፤ የእኛን ውሸት እንተክላለን ፤ ካቶሊኩን እንተክላለን ፤ እስላሙን እንተክላለን ፤ የዲያብሎስን መን ግሥት ፡ በግልጽ እንተክላለን ብለው ፡ ሌላውን ዓለም ፡ ሙሉ በሙሉ ሸፍነዋል ፤ ተቆጣጥረዋል ፡፡
የቀራቸው አገር የለም ፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ ናት የቀረችው ፡፡ ኢትዮጵያን ደግሞ መቆጣጠርና ማጥፊት አለብን ብለው ፡ በእራሳቸው አምሳል የቀረፁትን ፡ የሚያምኑትን ፡ ፍጹም ታማኝ ፡ የዲያብሎስ ወኪል የሆነውን መንግሥት ተክለው ፡ ዛሬ ኢትዮጵያን እንዴት እንደ አመሷት ፡ እንዴት እየፈጯት ፡ እየቆሏት እንዳለ ፡ ይህ ደግሞ ፡ የዛሬ 18 ዓመት (በፊት) ጀምረን ስንናገር ፡ ይህ እንደሚመጣ ስንናገር ፡ ልትሰሙ ስላልወደዳችሁ እንጂ ፡ ይኸው እውነቱ ዛሬ ፡ በግልጽ እየታየ ታዩታላችሁ ፡፡
እውነት አንድ ናት በቃ ፡፡ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት! እሷን የጨበጠ ፡ በእውነቷ የተመላለሰ ፡ ዲያብሎ ስን አሸነፈ ፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር አገኘ ፤ ጨበጠ ፡፡ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ አረፈ ፡፡ በልጅነት ተመዘገበ ፤ ተወደደ ፤ ከበረ ። እምነት እንዲህ ናት ፡፡ የአብርሃም እምነት ይህቺ ናት ፡፡
ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት ፡ ቃል ኪዳን የገባላት ኢትዮጵያ ፡ ያከበራት ኢትዮጵያ ፡ ብዙ ዋጋ የከፈለችው ኢትዮጵያ ከበረች ፡፡ እግዚአብሔር አከበራት ፤ ወደዳት ፤ ምልክትም ሰጠ ፤ መለያዋ እንዲሆን ፡ አረንጓዴ ፡ ቢጫ ፡ ቀዩን ፡ የቃል ኪዳን ምልክት አስጨበጠ፡፡ እግዚአብሔር እውነቱን አስጨበጠ ፡፡
እኛ ስለተናቅን አይደለም ፤ እኛ እኮ ፡ እውነት ተናግረን በዋልንበት እንውላለን ፤ በአደርንበት እናድራለን ፡፡ እግዚአብሔር በሰጠን ዕጣ ክፍላችን እንቆማለን ፡፡ ይሄን ብቻ አይደለም ፡ እግዚአብሔር አራቱን የቃል ኪዳን ምልክቶች ፡ ቃሎችን ጨብጡና ያዙ ብሎ ፡ እነሆ ሚሥጥሩን ገለጸ ፡፡
ኢትዮጵያን ስለ ወደድኳት ፡ ስለ አከበርኳት ፡ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ናት ብሎ ወሰነ ፡፡ ይሄን ገለጽን ፡፡ ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ናት ፡፡ ለተወደደችው እናታችን ፡ በሰማይም ንግሥት ፡ በምድርም ንግሥት ለሆነችው እናታችን ድንግል ፡ በፍቅር ፡ በስስት የተሰጠች ፡ ገንዘቧ ናት ፡፡ ኢትዮጵያ ማንም ሊያጠፋት አይችልም ፡፡ ይጠፋል እንጂ ፡ እግዚአብሔርን ያሸነፈ አለ እንዴ? ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ናት ፡፡
ለምን? እውነትን የጨበጠ ሕዝብ ፡ በውስጧ አዝላ ስለያዘች ፡ እውነትን የጨበጠ ፡ ዋጋ የከፈለ ትውልድ ስለሆነ ፡ እውነተኛ የተዋሕድ ኦርቶዶክስ እምነትን የጨበጠ ሕዝብ ስለሆነ ፡ ለዓለም ብርሃን ናት ፡፡ ይሄም ተወስኖ ነው፤ በእግዚአብሔር የተወሰደ ፡፡ ኢትዮጵያ በደከመችበት ልክ ፡ በለፋችበት ልክ ፡ በከፈለችው ዋጋ ልክ ፡ ልጆቿን በገበረችበት ልክ ፡ እግዚአብሔር ዓለምን አሳልፎ ሰጠ ፡፡ አሸናፊዋ እምነት ብሎ አወጀ ፡፡ እውነተኞቹ ልጆቼ ያሉባት ፡ የባረኳት ኢትዮጵያ ትንገሥ ፤ ዓለምንም ትግዛ ብሎ ወሰነ ፡፡ ይሄ እንግዲህ ፡ ሊገባው ፡ ሊቀበለው ያልቻለ ትውልድ ፡ ምን እናድርገው? አልሰማ አለ ፡፡ እንጮኻለን ፡ እንጮኻለን ፡ ዛሬ ዓለም በቴሌግራሙ (መልእክት የሚተላለፍበት ገጽ) በሉ ፡ በዩቱዩቡ (የምስል ድምፅ የሚተላለፍበት ገጽ) ፡ በፌስ ቡኩ (የፊት ለፊት ምስል የሚያሳይ መወያያ ገጽ) ፡ በዋትስአፑ ፡ በምኑ እያለ ፡ ዓለም በሙሉ ፡ ስምንቱም ቢሊዮን ሕዝብ እማያየው የለም ፤ የማይሰማው የለም ፡፡
ንቆ ስለተወው እንጂ ፡ ሁሉም ይሰማዋል ፡፡ እንግዲህ እንደምትረዱት ፡ እውነቱ ይሄ ነው ፡፡ ወዲህ ይውጣ ፡ ወዲህ ይውረድ ፤ ወዲህ ይሂድ አልተባለም ፡፡ በግልጽ ተቀምጦለት ነበር ፤ አልሰማም ። እግዚአብሔርን ፡ ምክሩን ፡ ትእዛዙን ንቀውታል ፤ ፍርዱን አቃለዋል ፡፡ እንዳሻቸው ዓለምን የሚጋልቧት የመሰላቸው ፡ ዛሬ ጭንቅ ፡ ጥብብ ብሏቸዋል ፡፡ ለምን? በቃ እግዚአብሔር ፡ በግልጽ እየመጣ ነዋ ፡፡ ፍርድን ጭኖ መጣ ፡፡ ትእዛዙን ያቃለሉትን ፡ የናቁትን ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያወጣቸው ነው ፡፡ ምልክት እየሰጠ ነው ወገኖቼ ፡፡
እንደምታውቁት ማንኛውም ነገር ፡ ምጥ የያዛት ሴት እንኳ ፡ እንዲያው ዝም ብላ መጥታ ፡ ደርሳ ውልድ አታደርግም እኮ ፡፡ ይጎረባብጣታል ፡፡ ትጨነቃለች ፤ ምጥ ይይዛታል ፤ ምልክት ትሰጣለች በቃ ፡፡ ልጅ መጥቷል ፤ ልትወልድ ነው ፡፡ እንዲህ አይደለም ሂደቱ? አዎ ፡፡
እንግዲህ ኢትዮጵያም ፡ ወደ ተመደበላት ፡ እግዚአብሔር ወደ ወሰነላት ፡ ወደ ክብሯ ማማ ለመውጣት ፡ ምልክቱ እየታየ ነው ፡፡ ዓለምም ስለ አወቀው ፡ ሁሉም ጉልበቱን አሰባስቦ ፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ፡ ይሄው ሰልፍ ይዞ ፡ በምድር ላይ ያልታየ እልቂት ፡ በኢትዮጵያ ላይ ይከናወናል ፡፡ ዓለም በሙሉ ፡ ሁሉም አንድ ስለሆነ ፡ በሐሳቡ ስለተሰማማ ፡ አንድም ሰው ስለ ኢትዮጵያ እልቂት አይተነፍስም ፡፡ አለቆች ፡ አገሮች እነ አሜሪካ ደጋሾቹ ፡ የዐመፅ ደጋሾቹ አይተነፍሱም ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ፡ ማን እንደሆነ ፡ አምላክነቱን ሊያሳያቸው ፡ ጅማሮውን ይኸው አሳይቷቸዋል ፤ ይቀጥላል ፤ ወደፊትም ይሄዳል ፡፡ ቢጠበቡ ፡ ቢጨነቁ የሚያመጡት ምንም ነገር የለም ፡፡ ከመሆን እሚያድነው ነገር የለም ። የመጥፊያቸው ምልክቶች በዝቷልና ፡ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚለው ስም ፡ ሊጠሩት አይደለም ፡ ሊሰሙት የሚያንገሸግሻቸው ፡ አባት ተብየዎች ፡ ካህን ነን ባዮች ፡ ዲያቆን ፡ መምህር ሁሉ ፡ የአንድ ወቅት የስብከት ሥራቸው ፡ አጀንዳቸው ፡ ማብጠልጠያ ፡ የዲስኩራቸው ማድመቂያ አድርገውን ባጅተውበታል ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው።
በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት የተጠቀሰው የፍርድ ቃል ፡ እየመዘነ ፡ እየለካ ለመከራው ሲያሰጣቸው ፡ አሁንም መፍትሔ የሚሹት ፡ ከሚጠፉበት የጨለማ መንገድ ነው ፤ ቀድሞም የጠፉበትን ፡ ያጠፏቸውን የነጮችን አገዛዝ መንገድ ፡ እምነት ሁሉ ፡ ያድነናል ብለው ፡ አሁንም የሙጥኝ ብለው ተጣብቀውበታል ፡፡ እንደ ፈቃዳቸው ውጤቱን ግን ሳይውል ሳያድር ያዩታል። አሁን እሚዘገይ ነገር የለም ፡፡ እሚዘገይ ነገር የለም ፡፡"
▷ ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ ፳፮ ጥር 15-2016ዓ.ም ለመላው የአዳም ዘር በሙሉ ከተላከው የተወሰደ‼️

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
መስቀል አደባባይ አደጋ‼️ በመስቀል አደባባይ ዛሬ አመሻሹን ድንገተኛ አደጋ መድረሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል። በርካታ አምቡላንሶች የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እያመላለሱ ሲሆን በአካባቢው በርካታ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች እንደሚታዩ የአይን እማኞች ገልፀዋል። የአደጋው መንስኤ በግልጽ ባይታወቅም የህዳሴ ግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ ነገ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በመዘጋጀት ላይ የነበረ መድረክ ወድቆ ሳይሆን…
በአዲስ አበባ "የደስታ" ሰልፍ ላይ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ በመስቀል አደባባይ ሲካሄድ በነበረው የደስታ ሰልፍ ላይ፣ ከባድ ዝናብን ለመጠለል በተፈጠረ መረጋገጥ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በበርካቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ከስፍራው የደረሰን አስደንጋጭ ዜና ያመለክታል። ይህ አሳዛኝ ክስተት፣ ትላንት በተመሳሳይ ስፍራ መድረክ ተሰብሮ በርካታ ሰዎች የተጎዱበትን ሀዘን የደገመ ሆኗል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የህዳሴውን ግድብ በዝማሬና በጭፈራ እያከበሩ በነበረበት ወቅት፣ በድንገት የጣለው ከባድ ዝናብ ስነስርዓቱን አመሰቃቅሎታል።
የአይን እማኞች ከስፍራው ለዘሐበሻ እንደገለጹት፣ ህዝቡ ዝናቡን ለመጠለል በአቅራቢያው ወደሚገኙ ድንኳኖችና ህንጻዎች ለመግባት ሲሯሯጥ በተፈጠረ ከፍተኛ ግፊያና መረጋገጥ አደጋው ሊከሰት ችሏል።
ይህ የዛሬው አደጋ ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው፣ ገና የትላንቱ ቁስል ሳይደርቅ መከሰቱ ነው። ትላንት ለዚሁ የድጋፍ ሰልፍ ዝግጅት ሲደረግ የነበረ መድረክ ተሰብሮ በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።
በሁለት ተከታታይ ቀናት በአንድ ስፍራ ላይ እንዲህ አይነት አደጋዎች መከሰታቸው፣ በዝግጅቱ የደህንነት ጥንቃቄ ላይ ከፍተኛ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው።
የመስቀል አደባባይ እና አካባቢው በከፍተኛ ግርግር እና የሀዘን ድባብ ውስጥ ውሏል፡። የሟቾች እና የጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ስጋት አለ። ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሱት ይዞ የሚቀርብ ይሆናል።
©️ ዘ-ሐበሻ
መስከረም 4, 2018 ዓ.ም

❤10🔥4