#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች

1, #ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, #ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።
በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, #ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, #አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. #አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, #ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, #ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, #ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
ስለ ስቅለቱ የተነገሩ ድንቅ ትምህርቶች

ቅዱስ አትናቴዎስ

1:- "ከአንድ በትር በግ ሁሉ እንደሚነዳ ሰው ሁሉ በአዳም ኃጢአት ወደ ሲዖል ይነዳ ነበር። በአንዱ ክርስቶስ የጽድቅ በትር አማካኝነት ወደ ገነት ተነዳን።"

2:- ከእንግዲህ ከፍ አድርገን የምናሳየው መፈክር ወይም ባንዲራ አለን። እርሱም የጌታችን ንጹሕ ደም ነው።

3:- እገሌ ቢሞት እናርፍ ነበር ሲባል ሰምተናል ሙት ሟችን አያሳርፍም። የክርስቶስ ሞት ለሞት ሞትን የከፈለ ለእኛ ሕይወትን የሰጠ ከዚህ በፊት ያልነበረ ወደ ፊትም የማይደገም ብቸኛ ሞት ነው።

4:- ከገነት የወጣነው በእፅ ነበር አሁንም የዳነው የዳነው ደሙ በፈሰሰበት በእፀ መስቀሉ ነው።

5:- መስቀል ለነገት ለመንግሥተ ሰማያት መወጣጫ መሰላል ሆነ።

6:-ለነፍሳችን መድኃኒትሽ እኔ ነኝ ብሎ ዕረፍትን ሰበከላት።

7:- ኖሮ ማኖር እያለ ሞቶ ማሳረፍህ ይደንቃል። የክርስቶስ ሞት ኖሮ ያሳረፈ ሳይሆን ሞቶ ያሳረፈ ሞት ነው።

8:- ሦስት ቦታዎች ላይ ወድቀን ነበር። ምድረ ፋይድ መቃብርና ሲዖል። ምድረ ፋይድን በበረት ቀደሰው መቃብርን በቅዱስ ሞቱ ድል ነሣው። ሲዖልን በቅድስት ነፍሱ መዝብሮ ወደ ገነትን አወረሰን።

9:- በብሉይ ሦስትት ነገሮች ይጠሉ ነበር። ሴት ፣ ሞትና ፣ እንጨት። ከሴቲቱ ተወልዶ የእባቡን ራስ ቀጠቀጠና ስሟን መለሰ። በሞቱ ሞትን ደፋው በእንጨት ተሰቅሎ አራቱን መዓዘን ቀድሶ ወደ ገነት አሻገረን።



✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል::  የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ?  እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ አጋሯቸው።

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
እንኳን አደረሳችሁ

ሞታችንን ሻረ

አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር ፣     
ክርስቶስ ተነሳ ከህቱም መቃብር፡፡      /፪/
           ……..አዝ
ክርስቶስ  በሞቱ ሞታችንን ሻረ ፣
ነፍሳትን አውጥቶ ሰይጣንን አሰረ ፣
የሲዖል እስር ቤት ባዶ ሆኖ ቀረ ፣
በትንሣኤው ብርሃን ሰላም ተበሠረ ፡፡
አዝ……
ሙስና መቃብርን በስልጣኑ ሽሮ ፣
የሲዖልን መዝጊያ የሞት በሩን ሰብሮ ፣
ብርሃን ተጎናፅፎ ሰላምን አብስሮ
ክርስቶስ ተነሣ አልቀረም ተቀብሮ
አዝ…….
የሰንበት ጌታዋ ክርስቶሰ ሲነሣ
መርገማችን ጠፋ ቀረልን አበሳ
እርቅ ሆነ በሰማይ እርቅ ሆነ በምድር  ፣
ነፍሳት ተሻገሩ ወደ ገነት ምድር
አዝ…….
ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው ጨለማ ፣
የጥሉ ግድግዳ የሞት ጥላ ግርማ ፣
ሸሸ ተወገደ በመስቀሉ ዓላማ ፣
የትንሣኤው ብሥራት በዓለም ተሰማ ፡፡
አዝ…….
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ!

#ውዳሴ_ትንሣኤ

"የክርስቶስ ትንሣኤ ምስጋና ይገባዋል። ውዱስ፣ ቅዱስ መባል ያስፈልገዋል። ታላላቅ ነገሥታት ቢነሡ ከድሀ ሰፈር ነው ፣ ክርስቶስ ግን ከሞት መንደር ተነሥቷል። በቤተ ልሔም እጅግ ዝቅ ያለው ፣ በትንሣኤው እጅግ የገነነው አንዱ ክርስቶስ ነው። ታላላቅ ሰዎች ከፍ ቢሉ በምክንያቶች ነው ፣ ክርስቶስ ግን በኃይሉ የተነሣ ነው። ተነሥተው የነበሩ ኃያላን በመውደቃቸው መተረቻ ሁነዋል፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ግን ዳግም ድካምና ሞት የለበትምና ሲደነቅ ይኖራል። ሌሎች ቢነሡ ለበቀል ፣ ለጥፋት ነው ፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ግን ቅዱስ ነው። ገንዘብ ላጡ ገንዘብ የሰጡ ቸር ተብለው ይመሰገናሉ ፣ ሕይወት ላጡ ሕይወት የሰጠ ክርስቶስ ሲመለክ ይኖራል። ሁሉ ቢነሡ እርሱን ሥልጣንና በኵር አድርገው ነው። እርሱ ግን በራሱ ሥልጣን ተነሥቷል ፣ በኵረ ትንሣኤ ሲባል ይኖራል። ሳይንስ ፍልስፍና ገና ያላለቀ ነውና አይታመንም ፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ግን የተፈጸመ ነውና ሊያምኑት ይገባል።"

ክርስቶስ ተነሣ! ምእመን ሆይ ለበጎ ተግባር ተነሣ!

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
#ማዕዶት

=) አባቶቼ ከትንሣኤ ማግሥት "ማዕዶት" ይባል ብለው ከሺህ ዓመታት በፊት ሰየሙ። እኔ ደግሞ ማዕዶት ይሁንልኝ ብዬ ለመንኩህ።

=) ማዕዶት ይሆን ዘንድ ልቤን ጨካኝ አድርግልኝ። ለዓለም እንስፍስፍ ለጽድቅ ቀጠሮ የማበዛ ፣ ግፍን ዛሬ ፣ ደግነትን ነገ ልሠራ ለምሻው እባክህ የቀደምክልኝ የእኔ ሙሴ ማዕዶት አድርግልኝ። እኔ "ትንሣኤና ሕይወት ነኝ" ያልከው ለመኖር አሥነሳኝ። የሕይወት መነሻው ትንሣኤ ፣ የትንሣኤ መድረሻው ሕይወት ነው። በራሴ እንዳልተነሣሁ በራሴስ እንዴት እኖራለሁ ? የትንሣኤው ጌታ ፣ የሕይወት ራስ ክርስቶስ ይህች ቀን ማዕዶት መሸጋገሪያ ትሁንልኝ። በማግስቱ ኃጢአትን እንዳልጀምር እግሬ ሳይረግጥ አሳልፈህ በጎውን አሳየኝ።

=) ማዕዶት ለአገልጋዮች ከዘረኝነት ሁሉን ወደ ምታቅፈው ወደ አምላካችን ወደ አንተ ይሁን።

=) ለሀገር መሪዎች ማዕዶት ይሁን።

=) ማዕዶት ለዘመነኞች ይሁን። ሁሉ ደንቁሮ እነርሱ ያወቁ ለሚመስላቸው ፣ የሚሊዮኖችን በረከት ብቻዬን ልዋጠው ለሚሉ ፣ ሆዳቸው ለማይሞላ ፣ ከረጢታቸው መዝጊያ ላጣ ፣ ወርቅ ላለመዱ ፣ ድህነት ሂዶም ተመልሶ ቢመጣስ እያሉ ለሚስገበገቡ ፣ መኖር ባንተ መሆኑን ረስተው መኖር በቁጥር ለመሰላቸው ፣ ድሃ ሲያዩ ድህነታቸው ትዝ እያላቸው ለሚያባርሩ ፣ ስርቆታቸው ገደብ ለሌለው፣  እባክህን ለእነዚህ ምስኪኖች ማዕዶት ይሁን

=) ማዕዶት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ይሁን።

=) ማዕዶት ወደ ሥጋና ደምህ

=) ማዕዶት ከዓለም ወደ አንተ

=) ማዕዶት ከግብጽ ወደ ከነዓን ከምድር ወደ ሰማይ ከሰማይ ወደ መንግስተ ሰማይ ከመንግስተ ሰማይ ወደ እናትህ አንተን ወደ ወለደችህ የዓለም አማላጅ ወደ ሆነች ከመላእክት ወደ መስተጋድላን አንተ ለማክበር ደማቸውን ወዳፈሰሱ ወደ ሰማዕታት ይሁን።

=) መሻገር ፣ መሸጋገር ፣ ማሻገር ይሁንልን ። ለመሻገር ፍጥነት ፣ ለመሸጋገር ሂደት ፣ ለማሻገር ፍቅር ስጠን። ለመሻገር አመንትተናል ፣ የተሻለች ምድር ብናገኝ ገነትን ለመሰረዝ ፈልገናል ። ማራናታ የሚያሰኘን የመከራው ጅራፍ ነው። እባክህን ዛሬ ማዕዶት ፣ ዓለም ከኋላችን ክርስቶስ ከፊታችን ይሁን!

https://www.tg-me.com/finote_kidusan
​​ #ከትንሣኤ_እሁድ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ

ሰኞ

👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ

👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ

👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ

👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

ዓርብ

👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ

👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ

👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን
መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

🤗በትንሳኤ ወቅት ሰላምታችን🤗
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሠይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ ፍስሐ ወሰላም

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔ
ር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
መጽሐፈ_ምስጢር_በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሰጫ_@eotc_books_by_pdf.pdf
13.3 MB
📚⛪️መጽሐፈ ምስጢር በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ📚⛪️

ተርጓሜ ፦ በመምህር ህሩይ

ይኽን
መጽሐፈ ምሥጢር በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ በታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ከዛሬ ስድስት መቶ ዓመት በፊት ተደርሶ ወደ አማርኛ በመተርጉም ለንባብ ያበቃው ጻድቁ የመሠረቱትና መጽሐፉን የጻፉበት የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ገዳም ነው፡፡
በመጽሐፉ አስደናቂ መልስ የተሰጣቸው የተወገዘ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች በጥቂቱ

➦የሰ
ባልዮስ ተግሣጽ
➦የአቡርዮስ ተግሣጽ
➦የአርዮስን ተግሣጽ
➦የንስጥሮስ ተግሣጽ
➦የፎጢኖስ ተግሣጽ
➦የአርጌንስ ተግሣጽ
➦የመለኮት ቃል ሰው ወደ መሆን ተለወጠ ለሚሉ ተግሳጽ፡፡

ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ሼር በማድረግ ለባለማህተቦች ያድርሱ እኔ ኃላፊነቴን ተወጥቼአለሁ!

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @fi
note_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
👑 መጽሐፈ ተክሊል @eotc_books_by_pdf.pdf
36.4 MB
📚⛪️መጽሐፈ ተክሊል📚⛪️

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የጋብቻ አስፈላጊነት እና በድንግልና የሚቆዩ ሰዎች በምን አይነት ሥርዓተ በተክሊል አንድ አካል መሆን እንደሚችሉ ተቀምጧል ሁላችንንም እግዚአብሔር ለዚህ ክብር ያብቃን😍!

                    •➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግ
ዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
ማቴዎስ 7፥7-8

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።  የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።

ይላል የ እግዚአብሔር ቃል
እኛ ግን በከንቱ አብዝተን እንጨነቃለን
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይደለን።


✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይደርስ ዘንድ
#Share_Please

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
"ወንጌላዊው ዮሐንስ እመቤታችንን የጠራበት መንገድ"

ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን …………“የኢየሱስ
እናት” ብሎ ጠርቷታል፡፡ ይኼ ሐዋርያ በጻፈው
ወንጌል ላይ የራሱንም ስም እንኳን አንድ ጊዜ
ያልጠራ ትሑት ሰው ቢሆንም የእመቤታችንን
ስም የጠራበት መንገድ እንዲሁ የምናልፈው
አይደለም፡፡ በወንጌሉ/በዮሐንስ ወንጌል/
እመቤታችንን ስምንት ጊዜ አንስቷታል፡፡ /ዮሐ
፪፥፩‚ ፪፥፫‚ ፪፥፭‚ ፪፥፲፪‚ ፮፥፵፪‚ ፲፱፥፳፭
‚ ፲፱፥፳፮‚ ፲፱፥፳፯/ ስምንት ጊዜ ሲጠራት ግን
አንድም ቦታ “ማርያም” ብሎ በስሟ
አልጠራትም፡፡ የጠራት “የኢየሱስ እናት” “እናቱ”
ብቻ ብሎ ነው፡፡ ቅርበት ባይኖረው ነው እንዳንል
ወንጌሉ ድንግል ማርያም በመስቀሉ ሥር
ለዮሐንስ ተሰጥታው “ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ወደ
ቤቱ ወሰዳት” ይላል፡፡ /ዮሐ ፲፱፥፳፯/ ሥጋዋን
መላእክት ነጥቀው ወደ ሰማይ ሲወስዱትም
አብሯት ተነጥቋል፡፡ ይህ ሐዋርያ በወንጌሉ ዐሥራ
አራት ጊዜ ማርያም የሚባሉ ሴቶችን ስም
ቢጽፍም አንድም ጊዜ እመቤታችንን በስሟ
አልጠራትም፡፡
ነገሩን አልን እንጂ እሱማ መጽሐፍ ቅዱስን
ስንመረምር አምላክን ከወለደች ጀምሮ
ከመላእክትም ወገን ሆነ ከሰዎች ወገን እሷን
የጠሩበት መንገድ ሲቀይሩ አይተናል፡፡አምላክን
ከመጸነሷ በፊት “ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር
ፊት ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ” ሲሉ የነበሩት
መላእክት ከወለደች በኋላ ግን “ሕጻኑና እናቱን
ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ” ሲሉ እናገኛለን፡፡ ሉቃ
፩፥፴ ማቴ ፪፥፵፫ አክስቷ ኤልሳቤጥ ልትጠይቅ
በሔደች ጊዜ ኤልሳቤጥ “የጌታ እናት አለች
እንጂ” እንደ ዝምድናዋ “ማርያም” ብላ
አልጠራቻትም፡፡ ሉቃ ፩፥፵፫
ይህ የሆነበት ምክንያት ድንግል ማርያም እጅግ
ታላቅ የክብር ስሟ “እናቱ” “የኢየሱስ እናት”
“የጌታ እናት” “የአምላክ እናት” የሚለው ስለሆነ
ነው፡፡ አንዲት እናት የታወቀ የከበረ ዝነኛ ልጅ
ካላት ለከሟ ይልቅ የእገሌ እናት ተብላ መጠራቷ
የተለመደና ተገቢ ነው፡፡ እመቤታችን ሰማይና
ምድር በእጁ የሠራው የገናናው አምላክ
ለእግዚአብሔር እናቱ ሆናለች፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው
በስሟ ከመጥራት ይልቅ በክብር ስሟ “የኢየሱስ
እናት” ብሎ ሊጠራት ወደደ፡፡ ይህን የቅዱስ
ዮሐንስ የመላእክት የቅዱሳኑ ትውፊትና የጉባኤ
ኤፌሶን ውሳኔ ይዘን እኛም ማርያም ከማለት
ይልቅ ወላዲተ አምላክ እመ አምላ እመቤታችን
እመ ብርሃን እንላታለን፡፡

የወላዲተ አምላክ ምልጃዋ ረድኤቷ አይለየን!!

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
Audio
"" ወደ ገነት ነጥቀው ወሰዱት! "" (፪ ቆሮ. ፲፪:፬)

"ገድለ ቅዱስ ያሬድ፥ ወአናሲማ"

(ግንቦት 11 - 2015)
ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
#ወዳጄ_ሆይ

በስሜት ከሰዎች ጋር ሮጠህ ደክመህ ያልደረስክበት ነገር ካለህ ወደተነሳህበት ተመልሰህ ከእግዚአብሔር ጋር እሩጥ ያኔ ካሰብክበት ብቻ ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ።

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።”
— ዮሐንስ 15፥5
✥••┈┈••● ✞ ◉●••┈┈••✥

💚 @finote_kidusan 💚
💛 @finote_kidusan 💛
❤️ @finote_kidusan ❤️
ግንቦት 27 እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጓሜውም አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
☞ይህ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በሃምሳኛው
በዐረገ በአሥራኛው ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡
☞ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከጠዎቱ ሦስት ላይ ነበር፡፡

☞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት በተናገረው
አምላካዊ ቃል መሠረት"ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ" ብሏቸው ነበር
ሰዓቱ ሲደርስ የሚያጽናኑበት ብርታት የሚሆናቸው የዕውቀት፤ የኃይል መንፈስ
ቅዱስ ሰደደላቸው፡፡
☞"በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው
ሳሉ ድንገት እንደሚቃጠል ዐውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ በሁሉም መንፈስ

ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሠጣቸው በሌላ ልሣኖች ይናገሩ
ጀመር"(የሐዋርያት ሥራ 2፥1-11)
☞ይህችንም ዕለት ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን በማለት ይጠሯታል፡፡
☞ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "መንፈስ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ ባይወርድ ኖሮ
ቤተክርስቲያን በኮሰሰች ነበር"በማለት የበዓሉን ታላቅነት መስክሯል፡፡

☞" እግዚአብሔር ይላል በመጨረሻም ቀን እንዲህ ይሆናል እንዲህ ይሆናል
ሥጋ በለበሱ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሁም ትንቢት
ይናገራሉ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ ደግሞም
በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለለሁ የሚል

ትንቢት ይናገራሉ"(ትንቢተ ኢዮኤልምዕራፍ 2ከቁጥር 28)
☞መንፈስ ቅዱስ ለምን ይወርዳል?
☞መንፈስ ቅዱስ ሊያጽናና ሊረጋጋ እንደሚወርድ በወንጌል ተነግሯል፡፡
☞"አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነ አጽናኝ እርሱ ሁሉን
ያስተምራቸው እኔም እኔ የነገረሸኅችሁን ሁሉ ያሳስባችኃል፡፡(ዮሐ 14፥25)
☞ - - - እኔ ግን እውነት እነግራችኀለሁ፤ እኔ እንድሔድ ይሻላችኅል፡፡

እኔ
ባልሔድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤እኔ ብሔድ ግን አርሱን እልክላችኀለሁ፡፡
(ዮሐ 16፥7)
☞ከዐረገ በኃላ መንፈስ ቅዱስ ሊያጽናናቸው እንሚመጣ ተናገረ፡፡
☞መንፈስ ቅዱስ ምሥጢር ሊገልጥ ይወርዳል፡፡
☞"የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን
እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኅል፡፡(ዮሐ
16፥12-13)

☞"እንዲህ አላቸው ወደ ዓለሙ ሁሉ ሒዱ ወንጌልን ለፍጥረት ስበኩ(ማር
16፥15)ብሎ በዓለም ሁሉ ያለውን ቋንቋ እንዲያውቁ አድርጎ ወንጌልን ለአለም
እንዲሰብኩ ልኳቸዋል፡፡
☞ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በወረደበት እለት የተለያዩ ቋንቋ ተገልጦላቸዋል፡፡
(ሐዋ 2፥3)
☞እኛም ጰራቅሊጦስ ለዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት፤ የቤተክርስቲያን
ልጆች መሠረት የተጣለበት ቀን በመሆኑ መንፈስ ቅዱስ ያጸናን፤ ይቀድሰን፤
ምሥጢሩን ይገልጥልን ዘንድ በማሰብና በመማፀን በዓሉን እናከብራለን፡፡

(ከመድበለ ታሪክ መጽሐፍ የተወሰደ)
☞ጰራቅሊጦስ የወርቅ ሐር ግምጃ የቅዱሳን የጌጣቸው ልብስ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ የጻድቃን የባለሟል ነታቸው የራስ ወርቅ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ያናገረ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ሐዲስ ወንጌልን ያስተማረ ዘንድ ጳውሎስን የጠቀሰ የሕይወት
መብረቅ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን የወይን ጠጅ ሳይጠጡ ያሰከረ ነው፡፡

☞ጰራቅሊጦስ በጽዮን አደባባይ በቶማስ ላይ በቅዱስ ነቢይ ፊት የበራ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ፍጹም የከበረ የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወት ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ የማይዳሰስ የእሳት ነበልባል ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ መጉደል ወይም መጨመር ሳይኖርበት በህልውናው አምላክ
ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ እንደ አብና እንደ ወልድ በሰማያትና በምድር ሁሉ ላይ መንግሥቱ
የመላ ነው፡፡

☞ጰራቅሊጦስ አሸናፊ ነው ለሰማዕታት መመኪያ የተሰበሩትን የሚጠግን ነው፡፡
☞ቅድመ ዓለም ለነበረ ፍጹም አንድነቱ ለሱ ስግደት ይገባል ዛሬም ዘወትርም
ለዘላለሙ አሜን፡፡
ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ pinned «ግንቦት 27 እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጓሜውም አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ☞ይህ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በሃምሳኛው በዐረገ በአሥራኛው ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ ☞ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከጠዎቱ ሦስት ላይ ነበር፡፡ ☞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት በተናገረው አምላካዊ ቃል መሠረት"ኃይልን…»
ጾመ ሐዋርያት

በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡

ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬)  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
 
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችንን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
 
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት  አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
 
ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ pinned «ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያት…»
አምላክ አሜን! †††

††† እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †††

=>ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

+ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

+የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

=>መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
+የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
+በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
+በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
+እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
+የጌታችንን መንገድ የጠረገ
+ጌታውን ያጠመቀና
+ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::

+ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

+" አባ ጌራን ሕንዳዊ "+

=>ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ::

+በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ (የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል) አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ::

+ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: (ምሳ. 24:16)

=>አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን::

=>ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)
2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)
3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ)
4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች)
2024/05/01 13:12:06
Back to Top
HTML Embed Code: