Telegram Web Link
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት እንዴት ነበር ?

የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ትላንት እሁድ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በዱባይ ኮላኮላ አሬና ውስጥ ተካሄዷል።

በኮንሰርቱ ላይ ከታደመው ከጋዜጠኛ አቤል ገብረኪዳን ስለነበረው ዝግጅት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ አጭር መረጀ ደርሶታል።

እንደሚከተለው ይቀርባል"ኮንሰርቱ ከመግቢያው ስንጀምር የኮካኮላ አሬና ድንቅ ነው፡፡ትክክለኛ የኮንሰርት ስፍራ ነው፡፡ለታዳሚ ይመቻል፣ለአቅራቢዎቹም እጀ ሰባራ የማያደርግ ምርጥ ቦታ ነው፡፡ግዝፈቱ ስቴድየምን የሚመስለው አሬና ውስጡም በጣም ቆንጆ ነው፡፡ለዝግጅቱ የተመደበው አብዛኛው ቦታም ሙሉ ነበር፡፡ ጸጥታ አስከባሪዎች ወደ አዳራሽ መጠጥ እንዳይገባ ማድረጋቸውም ትክክለኛ ውሳኔ ሆኖ ታይቶኛል፡፡"

"ድምጻዊ #ቴዲ አፍሮ በዱባይ አቆጣጠር 3 ሰዓት ካለፈ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ "አፍሪካ" በሚለው ሙዚቃ ተጀምሮ "ጥቁር ሰው" በሚለው ሙዚቃ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከአስር የሚበልጥ ሙዚቃዎችን የተጫወተ ሲሆን አንዳንዶቹ ሙዚቃዎች በተለይ ታዳሚውን አሳብደው አሬናውን መነቅነቅ የቻሉ ነበሩ"።

"ባንዱ ገራሚ ነው፡፡በሚጫወቱት መሳሪያ ማስተር ያረጉ ሙዚቀኞች የተሰባሰቡበት ነው ማለት ይቻላል፡፡ጊታሩ፣ሳክሱ፣ማሲንቆው እና ሌሎቹ ለየብቻ በሙዚቃው መሃል የተጫወቷቸው ዜማዎች ለብቻ ሊከፈልባቸው ሁሉ የሚገባ ናቸው፡፡በጣም ድንቅ ነበሩ፡፡በእረፍት ሰአት የተጫወቱትም ኢትዮጵያውያን ዲጄዎች የኮንሰርቱ ቫይብ እንደደመቀ እንዲቀጥል ማድረግ ችለዋል"።

"በጥቅሉ ቴዲም በጥሩ አቋም ታዳሚውን እንደያዘ ያጠናቀቀ ሲሆን ህዝቡም በኮንሰርት እንደተለመደው ሳይጉላላ አብሮ ዘፍኖ እና ጨፍሮ ወጥቷል፡፡ነቅለው ለኮንሰርት የወጡት የዱባይ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን ትክክለኛ ኮንሰርት አስመስለውታል፡፡"

ለተጨማሪው: @firtunamedia
Forwarded from Prestige Addis
ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ በፕሪስቴጅ አዲስ መድረክ ላይ በመገኘት ያደረገውን ክፍል ሁለት አስደሳች እና አስተማሪ ቆይታ በዩቲዩብ ገፃችን ላይ ተለቋል

ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት መመልከት ይችላሉ

https://www.youtube.com/watch?v=91qADRMxnfg.


@preaddis
Forwarded from Prestige Addis
Beyond the Screen

Get ready to embark on a magical journey with the incredibly talented Fikeraddis Nekatibeb! This is your chance to connect with the beloved singer in an unforgettable, one-of-a-kind experience-sharing program. Fikeraddis Nekatibeb has touched countless hearts with her music, and now, she’s inviting you to join her for a special moment of inspiration and connection.

Stay tuned for more details on how you can participate in this exclusive opportunity. Don’t miss out on this chance to get closer to Fikeraddis and be part of something truly extraordinary!

#beyondthescreen #prestigeaddis
ታላቁ የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን አረፈ 

አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ ፣ ገጣሚ እና ትርጓሜ ነብይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስታውቋል።

ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ፣ ድንገት ያረፈው ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም  ረፋዱ ላይ ነው።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን ለረጅም ዓመታት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።

ነብይ መኮንን ከአዲስ አድማስ መሥራቾች አንዱ ሲሆን  በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት ስሙ ይጠቀሳል።

"ነገም ሌላ ቀን ነው" "የመጨረሻው ንግግር" እና "የእኛ ሰው በአሜሪካ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

ኤቨንት አዲስ ድረገፅ በታላቁ የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን ህልፈት ሀዘኑን ይገልጻል።ለቅርብ ቤተሰቦቹ፣ አድናቂዎቹ ከልብ መፅናናትን ይመኛል።

ለተጨማሪው:
@firtunamedia
የጊዜ ሰሌዳ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ "የጊዜ ሰሌዳ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 1 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

በዕለቱም ጸሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮተ መዋዕለ ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ አርቲስት ፈለቀ ካሣ፣ ደራሲ የዝና ወርቁ፣ ደራሲ ሮማን ተወልደብርሃን በክብር እንግድነት ይገኛሉ።

ገጣሚያኑ ቴዎድሮስ ካሣ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ ፌቤን ፋንጮ፣ መሰረት ጌታነህና ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

"የጊዜ ሠሌዳ" መጽሐፍ በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
የቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከፊታችን አርብ ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

የዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከፊታችን አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የ"ጀስቲሺያ" ፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ስትሆን አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ በፊልም ጽሑፍ ተሳትፈዋል።

ህሊና ሲሳይ ፣እድለወርቅ ጣሰው ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ቢታኒያ መስፍን ፣ኤደን ግርማና ሌሎችሞ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።

"ጀስቲሺያ" የቤት ሰራተኞን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ይዞ የተሰራ ፊልም እንደሆነ ተሰምቷል።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
                 
አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ

ተዋናይ፣ ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢው ነፃነት ወርቅነህ ለህክምና ወደ ሀገረ ህንድ መሄዱን የሚገልጽ ማስታወሻ በግል የፌስቡክ ገፁ ማጋራቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎች ለአርቲስቱ መልካም ምኞታቸውን ሲገልፁ ነበር።

ገሚሶቹ ደግሞ አርቲስቱ ላይ ያጋጠመው የጤና እክል የከፋ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ጭምር ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል።

ያም ሆኖ ግን አርቲስቱ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተጨማሪም መልካም ምኞታቸውን ለተመኙለት ምስጋናውን በማቅረብ በጥቂት ቀናት ውስጥ የህክምና ክትትሉን አገባዶ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለስ ተናግሯል።

ለተጨማሪው :@firtunamedia
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኀበር

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በጉባኤውም ያለፈው ሁለት ዓመት የሥራ ክንውን እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ግምገማ ተደርጎበታል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ማኅበሩን በፕሬዝዳንትነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ባለበት የሥራ መደራረብ ምክንያት ማኅበሩን ተተኪዎች እንዲመሩት በመጠየቁ በጠቅላላ ጉባኤው በክብር ተሸኝቷል።

በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በሥራ ላይ ያሉት የሥራ አስፈጻሚ አባላት የቆይታ ጊዜያቸው ስለተጠናቀቀ የተጓደሉትን ጨምሮ እንደ አዲስ የዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ተካሂዷል። በዚህም መሰረት ሶስት ነባር ሥራ አስፈጻሚዎችና ስምንት አዳዲስ አባላት በእጩነት ቀርበው ምርጫ ተደርጓል። በጉባኤው ለምርጫ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎች በጠቅላላ ጉባዔው በድምፅ ምርጫ ተመርጠዋል።

በጠቅላላ ጉባዔው ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተመጡት እታገኘሁ መኮነን፣ ትብለፅ ተስፋዬ፣ ሲሳይ ሳህሉ፣ሳሙኤል አባተ፣ ዳግማዊት ግርማ፣ዳዊት ታደሰ፣መርሻ ጥሩነህ፣ማናዬ እውነቱ፣ዳዊት አስታጥቄ ናቸው።

ከተመረጡት ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል በተደገው የፕሬዝዳንት የምርጫ ውድድር ጋዜጠኛ እታገኘሁ መኮነን አብላጫ ድምጽ በማግኘት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሆና ተመርጣለች፡፡

አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ የማኅበሩን ጠንካራጰ ጎኖች በማስቀጠልና ከአባላት ጋር በመተባበር ለጋዜጠኞች መብት መከበር እና ለኢትዮጵያ ሚዲያ አጠቃላይ ዕድገትና ነፃነት እንደሚሰራ ቃል ገብቷል።

ለተጨማሪው : @firtunamedia
ዕውቁ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የተዘከረበት መርሃ ግብር ተካሄደ

አብሮ አደግ በፍቅር የመረዳጃ ማሕበር ያዘጋጀው የዕውቁ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የተዘከረበት መርሃ ግብር  በተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል። በዚህ መርሃ ግብር የገነነ ስራዎች እና ሕይወት በዝርዝር መዘከሩ ተነግሯል።

መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የማሕበሩ ሰብሳቢ አቶ ቤዛው ሹምዬ ማሕበሩ ባለፉት አስር ዓመታት ስላደረጋቸው ዕንቅስቃሴ አትተዋል። አክለውም "ያለፉትን በመዘከር፣ የሰሩትን በማክበር ተተኪዎችን እንፍጠር!" በሚል መሪ ቃል ስለተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር በዝርዝር አብራርተዋል።

የገነነ መኩሪያ የሕይወት ታሪክ በንባብ የቀረበ ሲሆን፣ በሕይወት ዘመኑ ያበረከታቸው የተለያዩ ስራዎች በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ ተዘክረዋል። ከገነነ መኩሪያ "ኢሕአፓ እና ስፖርት" መጽሐፍ የተቀነጨበ ስራ ለዕድምተኞች በትረካ ቀርቧል።

በተጨማሪም፣ ለቀድሞ የእግርኳስ ተጨዋቾች ተካ ገለታ፣ ግርማ አበበ፣ እና ጌቱ መልካ፤ ለቀድሞ ቦክሰኛ ደረጀ ደሱ እና ለድምጻውያኑ ጎሳዬ ተስፋዬ እና አብዱ ኪያር፣ ለሁለገቡ የኪነ ጥበብ ሰው ዳዊት አፈወርቅ፣ ለተዋናይ ተሰማ ገለቱ፣ ለኬሮግራፈር ዳንኤል ደሳለኝ፣ ለጋዜጠኛ እንግዱ ወልዴ እና ለሕግ ባለሞያዋ ሰናይት ፍስሐ (ፕ/ር) ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እና የገነነ መኩሪያ ባለቤት ወይዘሮ አስቴር አየለ ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሃ ግብሩ ላይ ታድመዋል።

አብሮ አደግ በፍቅር የመረዳጃ ማሕበር የተመሰረተበትን አስረኛ ዓመት በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ተከብሯል።

መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው።

@firtunamedia
"የሚስቶቼ ባሎች"ተውኔት ነገ ይሰናበታል

በደራሲ አበባየሁ ታደሰ ተደርሶ በተስፋዬ ገ/ማርያም እና ይገረም ደጀኔ የተዘጋጀው " የሚስቶቼ ባሎች " ተውኔት ነገ ረቡዕ ሐምሌ 10 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ  ከዓለም ሲኒማ መድረክ በክብር እንደሚሰናበት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ሰምቷል።

በሐምሌት መልቲሚዲያ የቀረበው"የሚስቶቼ ባሎች " ተውኔት ላይ ይገረም ደጀኔ፣ ሸዊት ከበደ ፣የምስራች ግርማ ፣ ብሩክ ምናሴና ሔኖክ ብርሃኑ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።

ቴአትሩ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ እንዲሁም በሀገርፍቅር ቴአትር አዳራሽ ለእይታ ቀርቦ የነበረ ሲሆን ከዓመታት በኃላ ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ 21 2015 ዓ.ም ነበር ወደ መድረክ የተመለሰው።

@firtunamedia
የሙዚቃ አቀናባሪው ያምሉ ሞላና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ በጋራ የሰሩት ግሚስ አልበም ተለቀቀ

"አዲስ ቀለም" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና የሙዚቃ አቀናባሪው ያምሉ ሞላ እና ወጣቷ ድምጻዊት መና ወረደ የተጣምሩበት ግሚስ(EP) የሙዚቃ አልበም በስፖቲፋይ የሙዚቃ መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ተለቋል።

"አዲስ ቀለም" ግሚስ አልበም በውስጡ ምንድነው ፣ ኤሌክትሪክ፣ ማዕዘን፣ተው ተው፣አንድ ሰሞን የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎችን የያዘ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የግሚስ አልበሙ ግጥም ፣ ዜማ፣ እንዲሁም ከሙዚቃው ቅንብር እስከ ማስተሪንጉ ድረስ በያምሉ ሞላ ተሰርቷል።

በተጨማሪም በከበሮ አገረሰላም ሻፊ ፣ በመሰንቆ ሀዲንቆ፣በክራራ ፋሲካ ኃይሉ ተሳትፈዋል።

በአልበሙ ከተካተቱ ሙዚቃዎች ውስጥ "ተው ተው" የተሰኘው ሙዚቃ የበርካታ የአገራችን ሴቶች ሕይወት (የቤተሰብ ኃላፊነትን) የሚዳሰስ ሙዚቃ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ሰምቷል።

ዛሬ ማለዳ በስፖቲፋይ የሙዚቃ መተግበሪያ የተለቀቀው አልበሙ አመሸሻ ላይ በዩቲዩብ በኩልም ይለቀቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
📍 የሥነጽሑፍ ውይይት

በአዳም ረታ መጻሕፍት ላይ ውይይት

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) የሚዘጋጅው " የወር ወንበር" መሰናዶ ላይ በዚህ ወር በደራሲ አዳም ረታ መጻሕፍት ላይ ያተኮር "አዳም ከአለፍ አገደም" የአዳም ረታ ሥራዎች ጥቂት ምልከታ" በሚል ርዕስ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 13 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 በወመዘክር አዳራሽ ሥነጽሑፋዊ ውይይት ይካሄዳል።

በዚህ ሥነጽሐፋዊ ውይይት ላይ አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ መነሻ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ  https://bit.ly/3S45QS2 ይሙሉ ተብለዋል።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
📍የሥነጽሑፍ ውይይት

በ"ግርባብ ያ ደግ ሰው" መጽሐፍ ላይ ውይይት

በደራሲ ፍቃዱ አየልኝ "ግርባብ ያ ደግ ሰው" መጽሐፍ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 13 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 አራት ኪሎ በሚገኙ ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ውይይት ይካሄዳል።

በዕለቱም በመጽሐፉ ላይ ሥነጽሑፍ ዳሰሳ እና ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

አወያይ: ዮናስ ታረቀኝ

ዳሰሳ አቅራቢዎች: ምግባር ሲራጅና ዮሴፍ ይድነቃቸው

ለተጨማሪው: @firtunamedia
"ኦሎምፒክ "ኮንሰርት ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል

አንጋፋ እና ወጣት ድምጻዊያን የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርቡበታል በሚል ሲተዋወቅ የቆየው እና ዛሬ ሐምሌ 13 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ይካሄዳል የተባለው "ኦሎምፒክ 2024" የተሰኘ ኮንሰርት ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል።

ይህ ኮንሰርት ሐምሌ 6  2016 ዓ.ም ይካሄዳል ከተባለ በኃላ ወደዛሬ ሐምሌ 13  2016 ዓ.ም  እንደተራዘመ ይታወሳል።

ምናልባትም ኮንሰርቱ ሙሉበሙሉ ሊሰርዝ የሚችልበት እድል ሊኖር እንደሚችል ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከውስጥ ምንጮች ሰምቷል።

ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት ሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት እና ላላ ፕሮዳክሽን  በመተባበር ያዘጋጁት ነው።

የኮንሰርቱም ዋንኛ ዓላማ  የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶችን ለመደገፍ የተዘጋጀ ተብሏል።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
የኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍት ክፍል በስፔን ማድሪድ

በስፔን ማድሪድ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት የኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍት ክፍል እንደተከፈተ ተነግሯል።

የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ እንደገለጹት በሀገሪቱ ብሄራዊ ቤተ-መጻሕፍት ቅጥር ግቢ የተደራጀው የኢትዮጵያ ቤተ-መጻሕፍት ክፍል የኢትዮጵያን ታሪክ ባህልና ቋንቋ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንዲረዳ መደራጀቱን ገልፀዋል።

መጻሕፍቶቹ በስፔን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሚገባ እንዲጠቀሙባቸው አመች በሆነ የዲጂታል መተግበሪያዎች ሳይቀር መገኘት እንደሚችሉ ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
Forwarded from Prestige Addis
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከተወዳጇ ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ጋር ያደረግነውን ፕሮግራም በዩቱዩብ ላይ እንዲከታተሉን ስንል እንጠይቃለን.

https://youtu.be/u3zzvwJrETw?si=d80iy5kjfTBLuX9R

@prestiigeaddis
ተዋናይ ሚካኤል ሚሊዮን የተጋበዘበት  በፊልም አሰራር ጥበብ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እና ተሞክሮዎቹን  የሚያካፈልበት መሰናዶ ዛሬ ይካሄዳል።

የተለያዩ ፊልሞችን፣ ቴአትሮችን፣የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎችን ፕሮዲዉስ በማድረግ በዝግጅት እና በትወና ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው የፊልም ባለሙያ ሚካኤል ሚሊዮን ዛሬ ማክሰኞ  ሐምሌ 16 2016ዓ.ም አራት ኪሎ ኢክላስ ህንፃ ላይ በሚገኘው በልቀት ኮሌጅ ከቀኑ 11:30 ሰዓት ጀምሮ  በመገኘት በፊልም አሰራር ጥበብ ላይ ለተማሪዎች እና በዕለቱ ለሚታደሙ ታዳሚያን ሙያዊ ትንታኔ እና ሙያዊ ተሞክሮዎቹን እንደሚያካፍል ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከኮሌጁ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዚህ የፊልም ሞያ ውይይት መሰናዶው መግቢያ በነፃ እና በሰዓቱ መገኘት ነው ተብሏል ።

ለተጨማሪው: @firtunamedia
2025/10/04 17:32:31
Back to Top
HTML Embed Code: