Telegram Web Link
Forwarded from Prestige Addis
ፕሪስቴጅ አዲስ ከአሜሪካ ኢምባሲ አዲስ አበባ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው 'Beyond The Screen, መድረክ ላይ ተዋናይት እና የፈርጀ ብዙ ባለሙያ የሆነችውን አርቲስት መቅደስ ፀጋዬን በመጋበዝ የማይረሳ ጊዜን አሳልፏል።

በዕለቱም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈችው አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ ከሙያ እና ከሕይዎት ተሞክሮችዋ ለወጣቶች ልምዷን ያካፈለች ሲሆን በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ወጣቶችም የተነሱላትን ጥያቄዎች ምላሽና ምክሮን ሰጣለች። በBeyond The Screen መድረክም እጅግ አስደሳች አስተማሪና አዝናኝ ቆይታን አድርጋለች።

ይሄንና መሰል ዝግጅቶቻችንን ለመከታተል እንዲሁም በአካል ለመታደም የማህበራዊ ገፆቻችንን ይከታተሉን።

@prestigeaddis
የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም በቅርቡ እንደሚለቀቅ ድምጻዊው በማህበራዊ ገፁ ካሰራጨው መረጃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ትሰስር ገፆቹ ከደቂቃዎች በፊት "ውድ ወዳጆቼ በቅርቡ በአዲስ አልበም እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በደስታ ነው" ብሏል።

ለተጨማሪ መረጃ : @firtunamedia
ስራ ልታቆም ነው...

ዝነኛዋ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አቅራቢ ዳናይት መክብብ ከያዝነው ክረምት በኋላ ከቃና ጋር እንደማትቀጥል ተሰምቷል።

ለስራ ማቆሟ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ተጠይቃ ስታስረዳ ፥
ከክፍያ እና ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ ችግር ሳይሆን በግሏ ጉዳይ መሆኑን ገልፃ ፥ ሌላ ቴሌቭዥን ጣቢያ ላይም የመስራት ፍላጎት እንደሌላት አረጋግጣለች።

ለምትሰራበት ቃና ቴሌቭዥን ጣቢያም የሁለት ወር ግዜን የሚሰጥ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቷን ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

ምንጭ፦ ኢትዮፒካሊንክ

@firtunamedia
Creative Connect Presents: Artist Nebyou Indris 🎭

Join us for an exciting episode of Creative Connect featuring the talented actor Nebyou Indris! Get an exclusive look into his journey, experiences, and insights from the world of acting.

📅 Date: Friday, August 23, 2024
🕙 Time: 4:00 PM
📍 Venue: Goethe-Institut, Addis Ababa
🎟️ Entrance: Free

Don’t miss this opportunity to connect with one of the brightest stars in the entertainment industry. Be inspired, ask questions, and immerse yourself in a night of creative conversation!

RSVP now and follow us for updates. See you there!

#CreativeConnect #nebyouindris #goetheinstitut #addisabeba #entertainment #actor #behindthescenes

@firtunamedia
Forwarded from Prestige Addis
What Would You Ask Netsanet Workneh?

Get ready for the incredible Netsanet Workneh—one of Ethiopia's most celebrated film actors, writers, directors, TV hosts, and producers—at our upcoming event! We want to hear from YOU: What questions would you like to ask Netsanet? Whether it's about his multifaceted career or personal interests, drop your burning questions below!

Let’s make this event unforgettable with your insightful inquiries. Stay tuned for more updates!

@prestigeaddis
CREATIVE CONNECT፡ ከ አርቲስት ነብዩ እንድሪስ ጋር 🎭

በCREATIVE CONNECT ዝግጅታችን ተወዳጁ የፊልም ተዋናይ ነብዩ እንድሪስን በእንግድነት የጋበዝን ሲሆን  በዚህም መድረክ ላይ ነብዩ የህይወት ተሞክሮውን እና ልምዱን ለወጣቶች ያካፍላል ስለሆንም በዝግጅቱ ላይ እንድትገኙ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

አርቲስት ነብዩ እንድሪስ በቅርቡ ለእይታ የበቁቱን 6:00 ከሌሊቱ፣ ጃናሞራ ፊልሞችን ጨምሮ በሌሎችም በበርካታ ፊልሞች ተሳትፏል።


📅 ቀን፡ አርብ  ነሃሴ 17,2016

🕙 ሰአት፥10 ሰአት

📍 ቦታ፡  Goethe-Institute, Addis Ababa - 6 kilo አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወደ ሽሮሜዳ በሚወስደው መንገድ

🎟 መግቢያ፡ ነፃ



ለበለጠ መረጃ @firtunamedia
📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሙዚቀኞች ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ ለሙዚቀኞች ጥሪውን አቅርቧል።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ "ክቡራን መንገደኞቹ አዝናኝ የበረራ ቆይታ ይኖራቸው ዘንድ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን የሚያቀርበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሙዚቃ ስራዎች 140 ወደሚጠጉ ዓለም-አቀፍ መዳረሻዎቹ ለሚጓዙ መንገደኞቹ ተደራሽ የሚሆኑበትን አማራጭ ይዞ ብቅ ብሏል።

በመሆኑም የሙዚቃ ስራዎቻችሁ አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ የምትፈልጉ የጥበብ ባለሙያዎች በሙሉ ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሙዚቃዎቻችሁን ይዛችሁ በመቅረብ የዕድሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥሮቻችን 0115178079 እና 0115178097 ይደውሉ። አሊያም በኢሜል አድራሻዎቻችን [email protected] ወይም  
[email protected] ይፃፉልን " ብሏል።

ለተጨማሪው : @firtunamedia
📌የወጣቱ ድምጻዊት ሔለን አበራ የሙዚቃ ድግስ!

ወጣቷ ድምጻዊት ሔለን አበራ በመድረክ ላይ በቀጥታ የሙዚቃ ስራዎቿን የምታቀርብበት የሙዚቃ ድግስ ነገ ነሐሴ 19 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው ተምሳሌት ኪቺን ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ልዩ ልዩ የሙዚቃ  ስራዎችን እንደምታቀርብ ድምጻዊት አስታውቃለች።

ድምጻዊት ሔልን አበራ በአዲሱ ዓመት የጃዝ ጣዕም ያለው የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች እንደምታደርስ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ የተናገረች ሲሆን ነገ የሚካሄደው የሙዚቃ ዝግጅትም የአልበሟ መደረሻ እንደሆነ ገልጻለች።

@firtunamedia
በርካታ ፊልሞች ላይ የምናውቀው ባቡጅ ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።ለቤተሠቡና ለአድናቂዎቹ መፅናናቱት ይሰጥልን።

ለባቡጂ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና አድናቂዎች፣ መጽናናትን ይመኛል።

@firtunamedia
አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ አረፈ

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በተከታታይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎችን ጨምሮ በተለያዩ ቴአትሮች እና ፊልሞች ላይ ተሳትፏል፡፡

የዝናቧ እመቤት፣ የገንፎ ተራራ፣ የጨረቃ ቤት፣ ዓይነ ሞራ፣ ንጉሥ ሊር፣ ጥሎሽ፣ ጣውንቶቹ፣ ከራስ በላይ ራስ፣ የሸክላ ጌጥ፣ የጫጉላ ሽርሽርና ቅርጫው አርቲስት ኩራባቸው ከተሳተፈባቸው የመድረክ ቴአትሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ከተዋናይነት ባለፈም ቴአትሮችን በመጻፍ በማዘጋጀት ለኪነ ጥበቡ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
አርቲስት ኩራባቸው በ1957 ዓ.ም በሐረር ከተማ ልዩ ስሙ ሸንኮር ተብሎ በሚጠራው መንደር ነበር የተወለደው፡፡

አርቲስቱ ባለትዳር እና የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጆች አባት እንደነበር ከቅርብ ወዳጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በቀጨኔ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ተመላክቷል፡፡

@firtunamedia
ተፈጸመ
ደህና ሁን! ~ የክብር ሽኝት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት

የአርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የቀብር ስነ-ስርዓት በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በተከታታይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎችን ጨምሮ በተለያዩ ቴአትሮች እና ፊልሞች ላይ ተሳትፏል፡፡

የዝናቧ እመቤት፣ የገንፎ ተራራ፣ የጨረቃ ቤት፣ ዓይነ ሞራ፣ ንጉሥ ሊር፣ ጥሎሽ፣ ጣውንቶቹ፣ ከራስ በላይ ራስ፣ የሸክላ ጌጥ፣ የጫጉላ ሽርሽርና ቅርጫው አርቲስት ኩራባቸው ከተሳተፈባቸው የመድረክ ቴአትሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ከተዋናይነት ባለፈም ቴአትሮችን በመጻፍ በማዘጋጀት ለኪነ ጥበቡ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን÷ የቀብር ስነስርዓቱ ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በቀጨኔ መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡

አርቲስቱ ባለትዳር እና የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጆች አባት ነበር፡፡

@firtunamedia
📌ካናል-ፕላስ የኢትዮጵያን ገበያ ለቆ ሊወጣ ነው

የፈረንሳዩ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ካናል ፕላስ (Canal +) የኢትዮጵያ ገበያን ለቆ ሊወጣ መሆኑን መሠረት ሚድያ ዘግቧል።

ከሶስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቻናሉ ለበርካታ ተጠቃሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ቢቆይም በበቂ ሁኔታ ገበያውን ተቀላቅሎ ትርፍ ማግኘት ስላልቻለ ውሳኔው ላይ እንደደረሰ ታውቋል።የስፖርት ቻናሉ ከተቋረጠ በርካታ ግዜም ተቆጥሯል።

"የስፖርት ቻናሉ መቋረጥን ተከትሎ ሌሎቹ ቻናሎች በቅርብ ሳምንታት ይቋረጣሉ። ይህም ማለት ኤጀንት ከነበረው ብሩህ Plc ጋር ያለውን ስራውን ያቆማል" ብሎ አንድ ጉዳዩን የሚያውቅ ምንጭ መረጃ ሰጥቷል።

አክሎም "ዋናው እና ግልፁ ምክንያት ገበያውን በደንብ ሰብሮ መግባት አለመቻሉ ነው" ብሏል።

ካናል ፕላስ የኢትዮጵያ ስራውን የጀመረው ከኢዩቴልሳት ጋር ስምምነት ተፈራርሞ የነበረ ሲሆን ስርጭቶቹንም በኢዩቴልሳት 7ሲ ቻናሎች ላይ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከስታር ታይምስ እና ዲ ኤስ ቲቪ ቀጥሎ ሶስተኛው የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል መሆን ችሎ ነበር።

📍መረጃው የመሰረት ሚዲያ ነው።

ለተጨማሪው @firtunamedia
📌የአንደኛው "ሚዲያ አዋርድ" ተሸላሚዎች !

አንደኛው "የሚዲያ አዋርድ" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ካዛንቺስ በሚገኘው በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ተከናውኗል።

በዚህ መሰረት የተሸላሚዎች ዝርዝርም ታውቋል።

በምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም ሴት አቅራቢ: አስካለ ተስፋዬ

በምርጥ ዜና ዘጋቢ ዘርፍ: ግርማ ፍሰሃ

ምርጥ የስፖርት ጋዜጠኛ: መንሱር አብዱልቀኒ

በምርጥ ዶክመንተሪ አዘጋጅ: አክሊሉ ሲራጅ

በምርጥ የሬድዮ ሴት ዜና አንባቢ: ለምለም ዮሐንስ

በምርጥ የሬድዮ ወንድ ዜና አንባቢ: ሶዶ ለማ

በምርጥ የቴሌቪዥን ሴት የዜና አንባቢ: የሸዋ ማስረሻ

በምርጥ የቴሌቪዥን ወንድ የዜና አንባቢ: ሠለሞን ኃይለኢየሱስ

በምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም ወንድ አቅራቢ :ሀብተማርያም መንግስቴ

በምርጥ የአምድ ፀሃፊ:አክሲያ ኢታሎ

በምርጥ የምርመራ ዘገባ: ክብረት ካህሳይ

በምርጥ ዲጄ : ዲጄ ኪንግስተን (ወዝወዝ አዲስ)

ልዩ ተሸላሚ: የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ዳኜ አበራ

ምርጥ የትምህርት ፕሮግራም: የእርቅ ማዕድ የሬድዮ ፕሮግራም

ምርጥ የሬድዮ ፕሮግራም: ታዲያስ አዲስ

በህዝብ ድምፅ ብቻ የተመረጠ የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ: አንዋር ጀማል

የህይወት ዘመን ተሸላሚ: መዓዛ ብሩ

ለተጨማሪው @firtunamedia
📌ተዋናይት ፍናን ህድሩ እና ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ

ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ተዋናይት ፍናን ህድሩን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በሐያት ሪንጀሲ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የአንድ ዓመት ቆይታ አለው የተባለ ሲሆን ኢንፊንክስ ኢትዮጵያ ተዋናይት ፍናን ከብራንዱ ጋር በቅርበት በመስራት በተለይም ወጣቱን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ የራሷን ድርሻ ትወጣለች ብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

ተዋናይት ፍናን በፊልሙ ኢንደስትሪ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ያገኘችውን ተቀባይነት እና ያላት የፈጠራ ችሎታ ከኢንፊኒከስ ብራንድ ጋር አብሮ ለመስራት ምቹ እንደሚያደርገው የተገለፀ ሲሆን ኢንፊኒከስ ከሚታወቅበት የስልክ ገበያ በተጨማሪ ወደ ቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ዋች፣ ኤር ፖድ እና መሰል ምርቶችን ወደ ገበያው ለማቅረብ ያለውን ዓላማ በመደገፍ ረገድ ጉልህ ተሳትፎ ይኖራታል ተብሏል።

ኢንፊኒከስ ዓለም አቀፍ የኤሌከትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሲሆን በተለይም በሚያመርታቸው የስማርት ስልኮች አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘ ብራንድ ነው::

በምርቶቹ አዳዲስ ቴከኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ የሚተወቀው ኢንፊኒከስ አሁን ደግሞ በቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ዋች፣ ኤር ፖድ እና የመሳሰሉት ምርቶቹ ወደ ገበያው እየመጣ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪው : @firtunamedia
📌የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ አልበም ተለቀቀ

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" የተሰኘ አልበም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በራሷ በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደተለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" አልበም 12 የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ሲሆን አልበሙ ላይ በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ፣አቡዲ እና ሱራፌል የሺጥላ ተሳትፈዋል በተጨማሪም በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፤አዲስ ፍቃዱ፣ አብርሃም ኪዳኔ ፣ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሠለሞን ኃ/ማሪያም ተሳትፈውበታል።

አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ያሉት ሲሆን ክሊፑ በአሜሪካ አትላንታ መሠራቱን ተነግሯል።

ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ ተደርጓል።

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ በ160,000 ዶላር በመላው ዓለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል፡፡

ለተጨማሪው :@firtunamedia
📌 ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ እና ሐበሻ ቢራ

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ "የእልል ያልኩ ሐበሻ" የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ።

ወጣቱ ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ በሐበሻ ቢራ ፋብሪካ እንደተመረጠ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

በ"የኔ ዜማ" አልበም እና በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው  ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል ተብሏል።

"እልል ያልኩ ሀበሻ "በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት ዛሬ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በቃና ዌርሀውስ ለየት ያለ ፕሮግራም የተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያዊያን ባህል፤ ዕሴት ፣ ማንነት እና ወግ ላይ ያተኮሩ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ተካሄደዋል።

በዚህም ዝግጅት በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባህላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

የዛሬው የዝግጅት ዓላማ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ማድረግ እና እነዚህ ሁነቶች ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ጎን ለጎን ራሳቸውንም እንዲያስተዋውቁ መደገፍ  እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪ @firtunamedia
2025/07/14 17:52:49
Back to Top
HTML Embed Code: