"አማኑኤል ሃብታሙን እናክብር "
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ "አማን በአሜሪካ የአንድ ሰው ቴአትር" በሚል ርዕስ በሀገረአሜሪካን ዝግጅቱን ሊያቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
በዚህ መርሐግብር ላይ"አማኑኤል ሀብታሙን እናክብር" በሚል ለአርቲስት አማኑኤል ስራዎቹ እውቅና የሚሰጥበት ሥነሥርዓትም ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ዝግጅቱም በአሜሪካ ሴልቨር ስፕሪንግ
ሴፕቴምበር 14 እና 15 2024 ይካሄዳል።
ለተጨማሪው: @firtunamedia

የድምጻዊ እሱባለው ይታየው አዲስ ሙዚቃ!
የድምጻዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) "የበርሽ አበባ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የበዓል ሙዚቃ ዛሬ ጳጉሜን 3 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም ድምጻዊ እሱባለው ይታየው "በመላው ዓለም የምትገኙ ሁሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያልኩ "የበርሽ አበባ" የተሰኘ ሙዚቃዬ የራሴ በሆነው በEsubalew Yitayew Yeshi የዩቱዩብ ቻናል ላይ ዛሬ ማታ ይለቀቃል ገብታችሁ ተጋበዙልኝ መልካም በዓል ሰላም ለዓለም" ብሏል።

"ፍቅር እስከ መቃብር" ድራማ ተለቀቀ
የደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ዘመን አይሽሬ መጽሐፍ የሆነው"ፍቅር እስከ መቃብር" መጽሐፍ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ተቀይሮ ዛሬ መስከረም 1 2017 ዓ.ም በቴለቪዥን መታየት የሚጀምር ሲሆን አስቀድሞ ትላንት ሌሊት በኢቢሲ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ተለቋል።
ተከታታይ ድራማው ከዩቲዩብ በተጨማሪም ዛሬ
በኢቢሲ ዜና ቻናል ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እና በመዝናኛ ቻናል ደግሞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ ይተላለፋል፡፡ እንዲሁም በድጋሚ ምሽት ከዜና በኋላ በሁለቱም ቻናሎች እንደሚተላለፍ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"የፍቅር እስከ መቃብር" የልብ ወለድ መጽሐፍን ‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በመቀየር በአራት ምዕራፍ፣ በ48 ክፍሎችና በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ እንዲኖረው ሆኖ እንዲሰራ ስምምነት ከኢቢሲ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
በተጨማሪም ውሉ ላይ ‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።

የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ የሆነው ሰላም ንዋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በጋብቻ ተሳስረው አሜሪካን አገር ለረጅም አመት የኖሩት ንዋይ ደበበና አይዳ ሀሰን ከቅርብ ዓመታት በፊት በይፋ መለያየታቸውን ቢገልፁም እንደቤተሰብ ብዙም አልተራራቁም።
በትዳር ሕይወታቸው ፅናት ንዋይ የተባለች ሴት ልጅና ሰላም ነዋይ የተባለ ወንድ ልጅ በጋራ ያፈሩት ንዋይና አይዳ ልጆቻቸውን ያሳደጉት ቨርጂንያ ውስጥ ሲሆን፣ ሰላም ከጊዜ በኋላ በገጠመው የጤናእክል የተነሳ ሕክምና ሲከታተል ቆይቷል።
በተለይ የኩላሊት ኢንፌክሽን ተጠቂ በነበረበት ሰዓት አንድ ኩላሊት እናቱ አይዳ ሰጥታው ንቅለ ተከላ ማድረጉ ይታወሳል።
ከልጅነቱ ጀምሮ ተጨዋች፣ ሳቂታ እና ቀልድ የሚወድ ተወዳጅ ልጅ ነበር ትምህርቱን ተከታትሎ ያጠናቀቀው እዚያው አሜሪካን አገር ሲሆን፣ ሲበዛ አዛኝ ልብ የነበረውና ሰዎችን መርዳት የሚያስደስተው ሰላም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ንዋይ ደበበ ዛሬ ማታ ወደ አሜሪካን ይጓዛል ተብሏል።
©️መረጃው የሁሉአዲስ ነው

"ሦስተኛው ዓይን" የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ
የሠዓሊ መሐሪ ተሾመ "ሦስተኛው ዓይን: The third eye" የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ቅዳሜ መስከረም 4 2017 ዓ.ም ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው አናፎራ የጥበብ ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ ከአንድ ወር በላይ በእይታ ይቆያል።
ለተጨማሪው: @firtunamedia
የሠዓሊ መሐሪ ተሾመ "ሦስተኛው ዓይን: The third eye" የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ቅዳሜ መስከረም 4 2017 ዓ.ም ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው አናፎራ የጥበብ ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አውደርዕይ ከአንድ ወር በላይ በእይታ ይቆያል።
ለተጨማሪው: @firtunamedia
የመዓዛ ወርቁ አዲስ ድራማ ሊጀምር ነው
ከዚህ ቀደም "ወፌ ቆመች" እና "ደርሶ መልስ" በተሰኙ የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድራማዎችን ጨምሮ በበርካታ የሬድዮና ቴሌቪዥን ድራማዎች የምናውቃት ደራሲ መዓዛ ወርቁ "አላውቅም አናውቅም" የተሰኘ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በቅርቡ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲዋ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተከታታይ ድራማው ከሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዲኤስትቪ አቦል ቻናል 465 ላይ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ መተላለፍ ይጀምራል ተብሏል።

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃ/ማርያም ማስታወሻ ዝግጅት የፊታችን እሁድ በወመዘክር ይካሄዳል።
የዛሬ 30 ዓመት ህይወቱ ያለፈው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም በሙያ ባልደረቦቹ የማስታወሻ ዝግጅት ሊደረግለት ነው፡፡
የፊታችን እሁድ መስከረም 12 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ በሚከናወነው በዚህ ዝግጅት፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ባልደረቦች ይታደማሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በማስታወሻ ዝግጅቱ ላይ፣ ስለ ጌታቸው ምስክርነት የሚሰጡት ጋዜጠኛ ሚሊዮን ተረፈ ፤ ጋዜጠኛ ዋጋዬ በቀለ እና ጋዜጠኛ ታዬ በላቸው ሲሆኑ በተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን የተዘጋጀ የ20 ደቂቃ የድምጽ ዘጋቢ ሥራም እንደሚደመጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የማስታወሻ ዝግጅቱ ሀሳብ አመንጪ እና አዘጋጅ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ሲሆን በዕለቱም ጋዜጠኝነትን የሚያጠኑ ተማሪዎች በመሰናዶው ላይ ይገኛሉ፡፡
አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ በጠቅላላው ከ 24 ዓመታት በላይ ያገለገለ ጋዜጠኛ ነበር፡፡ በተለይም በዜና አቀራረብ እና አንባቢነት ለብዙዎች አርአያ የሆነም የሚከበር ጋዜጠኛ ነበር፡፡
የሚድያ ሰው ጌታቸው ኃይለማርያም፣ አሁን በአንጋፋነታቸው እውቅና የተቸራቸውን እንደ ነጋሽ መሀመድ፣ አለምነህ ዋሴ፣ ንግስት ሰልፉ እና ብርቱካን ሀረገወይንን የመሰሉ ባለሙያዎች ለሙያዊ ብቃት እንዲደርሱ በማሰልጠን እና ልምዱን በማካፈል የበኩሉን የተወጣ ባለሙያ ነበር፡፡ ዜና ፋይል የተሰኘውን ፎርማት ለመጀመረያ ጊዜ እንዳስተዋወቀ እና እንደፈጠረ የሚነገርለት ይህ ሰው በብስራተ ወልጌል የሬድዮ ጣቢያም ሙያዊ አደራውን ሲወጣ ነበር፡፡
©️መረጃው የተወዳጅ ሚዲያ ነው

ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ እና ሌሎች ሶስት ሴት ኢትዮጵያዊያኖች በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው።
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር ተሸላሚዎች ታውቀዋል። ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ሥነስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው።አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት ተካሂዷል።
ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች አምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል፤ የዚህ አመት ተሸላሚዎች በሙሉ ሴቶች ናቸው። በስነ ጥበብ ዘርፍ ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀና አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ በስፖርቱ ዘርፍ የማራቶንና የ5000 ሜትር የአለማችን ክብረወሰን ባለቤቶች ትዕግስት አሰፋና ጉዳፍ ፀጋዬ እንዲሁም በቢዝነስ ዘርፍ ርብቃ ሀይሌ ተሸላሚዎች ይሆናሉ።
በዕለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረጋላቸው በርካታ እንግዶች ይገኛሉ፤ ተሸላሚዎቹ ከግዛቶቹና ከተማዎቹ ተወካዮች የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል።
በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የሙዚቃ ዝግጅት በወጣቷ ድምፃዊት ራሄል ጌቱና በታዋቂው መሳሪያ ተጫዋች ሰላም ስዩም የሚቀርብ ይሆናል።
የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል እሁድ ኦክቶበር 13/2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት ይካሄዳል።

📌 የድምፃዊ አንዷለም ጎሳ"አያንቱ" አልበም
የድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ "አያንቱ" የተሰኘው የአፋን ኦሮሞ የሙዚቃ አልበም መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ዩቲዩብን ጨምሮ በዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።
"አያንቱ" የሙዚቃ አልበም በውስጡ 16 ሙዚቃዎችን ያካተተ ሲሆን፣ 16ቱ የሙዚቃ ስራዎች የሀገራችንን የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን ተጠቅመው የቀረቡ ናቸው።
አልበሙ በርካታ ሙዚቀኞችን እና ባለሙያዎችን አሳትፏል ከእነዚህም መካከል ኤፍሬም ብርቅነህ፣ ሚኪ ጃኖ፣ እዮብ ባልቻ፣ አንተነ (አቡዝ) እና ኤንዲ ቤተ ዜማ በሙዚቃ ቅንብር ተሳትፈዋል።
እንዲሁም በታዋቂው የሙዚቃ ባለሙያ አበጋዝ ሾይታ ማስተር ተደርጓል።
በግጥም እና ዜማ ዘርፍ ላሊሳ ኢንድሪስ፣ አቦማ ማርጋ ፣ አርቲስት አቢራሂም መሀመድ፣ ሞቲ አባ ዳሌ እና ፋጤ አኒያ፣ ናሆም መኩሪያ፣ ኢፊረም ብርቅነህ፣ ዘርዓ ብሩክ እና ኢሳያስ ተሳትፈዋል።
አርቲስት አንዱአለም ጎሳ የሙዚቃ አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከ6 አመታት በላይ ፈጅቶበታል።

📌 የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ትዝታ" የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ይለቀቃል
የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ትዝታ" የተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል።
ሙዚቃው ላይ በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣በዜማ አንተነህ ወራሽ፣ በቅንብር አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ተሳትፈውበታል።የሙዚቃው ቪዲዮው ዳይሬክተር ኤዲተር እመቤት ካሣ ነች።ይህ የሙዚቃ ስራ "ማያዬ" ከተሰኘው የሙዚቃ አልበም ውስጥ የተካተተ ነው።
ለተጨማሪው: @firtunmedia

📌አርቲስት አዜብ ከግማሽ ቀን እስር በኃላ ተፈታለች
ሰሞኑን አርቲስት አዜብ ወርቁ "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዋ ካጋራች በኋላ ጽሁፉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ ይታወሳል።
በዚህ ጽሑፍ መነሻ ይሁን በሌላ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት አርቲስት አዜብ ወርቁ ዛሬ መስከረም 9 2017 ዓ.ም በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለግማሽ ቀን ያህል ታስራ እንደነበር ተሰምቷል።
ዛሬ በቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው አዜው ወርቁ ለግማሽ ቀን ያህል በእስር ከቆየች በኋላ መለቀቋን ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ቴዲ አፍሮ የቢቂላ ሽልማትን ተሸለመ
በሀገራችን እንቁ አትሌት የተሰየመው “ቢቂላ አዋርድ” ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሽልማት ተቋሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን እስካሁንም ለበርካታ የሀገር ባለውለታዎች እውቅናን በመስጠት ሲሸልም ቆይቷል። ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award) ከሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ከምንም አይነት ትርፍ እራሱን ባገለለ መልኩ በካናዳ ከ50 አመታት በላይ በኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው የተቋቋመው። ይህ ተቋም በትምህርታቸው፣ በንግዳቸው፣ በሙያቸው ብሎም በበጎ አድራጎት ስራ ተሰማርተው ልዩ ስኬት ያስመዘገቡ እና አርአያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ በመሸለም እውቅናን የሚሰጥ ትልቅ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።
በዚህ አመት አስረኛ (10) የምስረታ በአሉን ያከበረው የቢቂላ አዋርድ ተቋም፥ ትላንት ምሽት መስከረም 11 (21 September 2024) በተደረገው መርሃ ግብር ላይ በሙዚቃው ዘርፍ የዚህ አመት ተሸላሚ የሆነው የግጥምና የዜማ ደራሲ ብሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነውን የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን በዚህ ግዙፍ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሽልማቱን በደማቅ ስነስርዓት በክብር ተቀብሏል
Follow us on Social Medias
#share #like #follow
Telegram: https://www.tg-me.com/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/@firtunamedia
#firtuna
Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

የደራሲ እስከዳር ግርማይ "የፈረንጅ ሚስት" መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ተተረጎመ
የደራሲ እስከዳር ግርማይ "የፈረንጅ ሚስት" የተሰኘ መጽሐፍ "WHITE MAN'S WIFE"በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ እንደተተርጎመ ተወዳጅ ሚዲያ ዘግቧል።
የእስከዳር ግርማይ አዲሱ የእንግሊዝኛ መጽሀፏ እውነተኛ ታሪኮችን ይተርካል። በተለይም በተለያየ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶችንና የውጭ ሀገር ዜጋ ያገባ ኢትዮጵያዊ ወንድን ከምሳሌ እና ኹነቶች ጋር እያጣቀሰ የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን ያስቃኛል።
መጽሀፉ መጀመሪያ የተጻፈው ''የፈረንጅ ሚስት'' በሚል ርዕስ እንደመሆኑ ተደራሽነቱ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ማዕከል አድርጎ የተነሳ ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዜጎቻቸውን ሲያገቡ የሚያጋጥማቸውን እይታም ድንበር ተሻጋሪ እንደመሆኑ " WHITE MAN'S WIFE" ወደሚል ተተርጉሟል።
የመጽሀፍ ወደ እንግሊዝኛ መተርጎም የኢትዮጵያ ስነጽሁፍን ለአለምአቀፍ አንባቢያን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያዋጣ ይታመናል ተብሏል።
የፈረንጅ ሚስትን ወደ እንግሊዝኛ መጽሀፉን የተረጎመችው ራሷ ደራሲዋ ስትሆን፣ እንግሊዛዊው የሥነጽሁፍ ባለሙያው ክርስትያን ሀሪፎርድ መጽሀፉን በአርታኢነት ሲሠራው፣ አሳታሚው ጆርጅ ኦፍ ሚድልተን "ይህ የኢትዮጵያን ሴቶች ታሪክ ብቻ ሳይሆን ስለሁላችን እና ስለምርጫዎቻችን ነው" በማለት አስተያየታቸውን መግቢያው ላይ አስፍረውበታል።
ለተጨማሪ

"አንድ ቃል" የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ይለቀቃል
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከወር በፊት ከለቀቀው "አንድ ቃል" የሙዚቃ አልበም ውስጥ ለአልበሙ መጠሪያ ለሆነው "አንድ ቃል" ለተሰኘው ሙዚቃ የተሰራው የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ረቡዕ መስከረም 15 2017 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገፁም"ከአዲሱ አልበሜ አንድ ቃልን በቪዲዮ ረቡዕ ወደ እናንተ እንደማደርስ ስገልፅላችሁ በደስታ ነው" ብሏል።
#share #like #follow
Telegram: https://www.tg-me.com/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/@firtunamedia
#firtuna
Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከወር በፊት ከለቀቀው "አንድ ቃል" የሙዚቃ አልበም ውስጥ ለአልበሙ መጠሪያ ለሆነው "አንድ ቃል" ለተሰኘው ሙዚቃ የተሰራው የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ረቡዕ መስከረም 15 2017 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገፁም"ከአዲሱ አልበሜ አንድ ቃልን በቪዲዮ ረቡዕ ወደ እናንተ እንደማደርስ ስገልፅላችሁ በደስታ ነው" ብሏል።
#share #like #follow
Telegram: https://www.tg-me.com/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/@firtunamedia
#firtuna
Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ
🎵 ዘማሌ 🎵 በድምፃዊ አዲስ ሙላት ነገ ምሽት ይጠብቁን !
👉 ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ ) በሙዚቃ ቅንብሩ
👉አበጋዙ ክብረወርቅ (ሺዎታ ) ማስተሪንግ
👉እንዳሻው አለማየሁ (ፊታውራሪ ) በግጥም ተጣምረዋል።
👉በ16 ፊልም ኘሮዳክሽን ምስል ታጅቦ በ Addis Mulat Youtube በኩል ወደ እናንተ መጥቷል።
ከተሜውንና ባለ ሃገሬውን የተወሃደበት በከተሜው ባለ ሃገር ለዛ የተዋደደ ድንቅ ሥራ ይመልከቱት 💥
ፊታውራሪ እንዳሻው አለማየሁ ከሶዶ ሰማይ ስር