Telegram Web Link
ነፃ መፅሀፍ 1
አዳማ

አሁን ያለነው መብራት ጋር ያለው ማፊ ሬስቶራንት ነው። ቀድሞ አንድ እስክሪፕቶ ይዞ የመጣ አንባቢ መፅሀፉን ይወስዳል ። በሰው የተላከ መሆን የለበትም።

ምልክት
3 ግማሽ ሊትር የውሀ ሀይላንዶች
2 ወንድ እና 1 ሴት
.
@Fuadmu
😁15👍5🔥2👏1
አልተወሰደም እስካሁን ....
እየጠበቅን ነው።
😁10👍2
በሚቀጥለው 5 ደቂቃ ውስጥ የሚመጣ ከሌለ ቦታ እንቀይራለን።
👍4🦄1
ተወስዷል።
👍3😁1
መፅሀፍ  1

አዳማ

ተወስዷል።

ቀጣይ ቦታ ከጥቂት ቆይታ በኋላ እንፖስታለን።

.
@Fuadmu
@Fuadmu
5👍4
ነፃ መፅሀፍ 2
አዳማ

አሁን ከአስቱ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት ያለው ስካይ ሲቲ ሆቴል ግራውንድ ላይ ያለው ኮፊ ሀውስ ነን። ቀድሞ እስክሪፕቶ ይዞ የመጣ አንባቢ መፅሀፉን ይወስዳል ። በሰው የተላከ መሆን የለበትም።

ምልክት
2  ወንድ እና 1 ሴት
.
@Fuadmu
👍41
ተወስዷል!
መፅሀፍ  2

አዳማ

ተወስዷል።

ቀጣይ ቦታ ከጥቂት ቆይታ በኋላ እንፖስታለን።

.
@Fuadmu
@Fuadmu
👍3
ነፃ መፅሀፍ 3
አዳማ

አሁንም ድጋሚ ከአስቱ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት ያለው ስካይ ሲቲ ሆቴል ግራውንድ ላይ ያለው ኮፊ ሀውስ ነን። ቀድሞ እስክሪፕቶ ይዞ የመጣ አንባቢ መፅሀፉን ይወስዳል ። በሰው የተላከ መሆን የለበትም።

ምልክት
2  ወንድ እና 1 ሴት
.
@Fuadmu
👍6
ተወስዷል!
መፅሀፍ  3

አዳማ

ተወስዷል።

ለዛሬው በዚሁ እናበቃለን።

.
@Fuadmu
@Fuadmu
👍11😢8🥰1
በዛሬው ፈገግታ መጅሊሳችን

የስነ ፅሁፍ ስራዎች
የቁርዓን እና ሀዲስ ሪፍሌክሽን
ቲላዋ

በእናንተው ወደ እናንተው ይቀርባል።

ከምሽቱ 3:00 ሲል እንገናኝ!
.
@Fuadmu
👍26
Live stream started
Live stream finished (2 hours)
ንፍቅና እና እዝነት
(ፉአድ ሙና)
***
በበኒል ሙስጠሊቅ ዘመቻ ወቅት ነበር። ጃቢር ኢብኑ አብዱላህ ይናገራል። ምዕመናን ከምድራችን ጌጥ ከነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ጋር በጦር ሜዳ ላይ ሰፍረዋል። አንድ ሙሀጂር አንሷር ወንድሙ ላይ ጥቃት ሰነዘረ። የተመታው አንሷር ወገኖቹ ይደርሱለት ዘንድ «አንሷሮች ሆይ!» ሲል ተጣራ። ጥቃቱን ሰንዛሪው ስደተኛም «ሙሀጂሮች ሆይ!» ሲል ጥሪውን አቀለጠው። ይህ ጥሪ የአላህ መልዕክተኛ ጆሮ ደረሰ። የሰሙትን ነገር ያልወደዱት ነብይም «ምን አይነት የጃሂሊያ ጥሪ ነው? አስቀያሚ ነውና ተውት!» ሲሉ አስጠነቀቁ። የአንሷሩ መመታት ከጆሮው የደረሰው የመናፍቃን አባወራ ይህንን እድል ማስመለጥን አልወደደም። እንደተለመደው የጥፋት ምላሱን ዘረጋ። «እነዚህ ሙሀጂሮች ይህንን አደረጉ? በአላህ ይሁንብኝ ወደ መዲና ስንመለስ የተከበረው ወራዳውን ያስወጣል!» ሲል ዛተ።

በእርግጥ የአብዱላህ ኢብኑ ሰሉል መርዛማ ድርጊት እና ቃላት ለሙስሊሞች አይን እና ጆሮ አዲስ አልነበሩም። ኢብኑ ሰሉል ማለት በርካታ ሰሀባዎች በተጨፈጨፉበት የእሁድ ዘመቻ ላይ 300 ወታደሮችን ከጦር ሜዳ ይዞ የሸሸ የክህደት ቀንዲል ነው። ጠላት ብለው እንዳይጋደሉት ሙስሊምነቱን አውጇል። ወዳጅ ነው ብለው አይተውት የስራው ዋጋ ከፍቷል። ይህ ግለሰብ ከምድራችን ኑር ጋር የልብ ቁርሾውን የጀመረው እግራቸው መዲናን ከረገጠበት ቀን ጀምሮ ነው። ያልሸረበባቸው የሴራ አይነት አልነበረም። አቡ ጃህል በመካ፤ ኢብኑሰሉል በመዲና እስኪባልለት ድረስ ወዳጅ እየመሰለ የሙስሊሞችን አንድነት ለመበተን ያገኘውን ድንጋይ ሁሉ ሲፈነቅል ኖሯል። እናታችን አዒሻን በዝሙት በማነወር ሙዕሚኖች እንኳን ባሰራጨው ወሬ ፈተና ውስጥ እስኪገቡ ድረስ የቻለውን ያህል በመልዕክተኛው ክብር ላይ ተረማምዷል። ታዲያ ይኸው ሰው በይዓቱል ዓቀባ ላይ ተገኝቶ ከነብያችን ጋር ቃል ተጋብቷል። ጠላት ብለው እንዳይነጥሉት ያልተመቸ፤ ወዳጅ አድርገው እንዳይዙት የከበደ ጉድ ነበር።

ታዲያ አላህ ጥበቡን ሊያሳይ ወደደ። በፊርዓውን ቤት ሙሳ (ዐሰን) ያሳደገው ጌታ፤ ከዚህ ሙናፊቅ የዘር ፍሬ አብዱላህ ኢብኑ አብዱላህ የተሰኘ ልጁን አበጀ።

يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ

ሕያውን ከሙት ያወጣል፡፡ ሙታንም ከሕያው ያወጣል፡፡ (ሩም፣ 19)

ህያውን ከሙት የሚያወጣው ጌታ፤ ኢብኑ ሰሉልን ከመሰለ ጨለማ ውስጥ አብዱላህን የመሰለ ብርሀንን ፈለቀቀ። አብዱላህ እምነቱ ላይ የጠነከረ ሙጃሂድ ነበር።

በበኒ ሙስጠሊቅ ዘመቻ ወቅት የተነሳውን ቁርሾ መጠቀም የፈለገው ኢብኑ ሰሉል ያወጣው «የተከበረው ወራዳውን ያስወጣል!» የሚል ቃል ወደ አለሙ እዝነት ጆሮ ደረሰ። በወቅቱ የእስልምና እና የመልዕክተኛው ክብር ላይ ትዕግስት የማይችለው ኡመር (ረዐ) ከአዛኙ ነብይ ጎን ተቀምጦ ነበር። ደምስሮቹ ተወጠሩ። «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የዚህን መናፍቅ አንገት እቀነጥሰው ዘንድ ይፍቀዱልኝ!» ሲል ጠየቀ።
ከስሜታቸው የማይናገሩት ነብይ
«فكيف يا عمر إذا تحدث الناس أن محمدا يقتل أصحابه

ኡመር ሆይ! ሙሀመድ ባልደረባዎቹን ይገላል እንዲባል ትፈልጋለህን!» አሉ።

የንፍቅና ራስ የሆነው ኢብኑ ሰሉል ንግግሩ ከተፈቃሪው ነብይ ጆሮ እንደደረሰ ሲገባው ከፊታቸው ቀርቦ በፍፁም እንዲህ ያለ ፀያፍ ነገር ከአንደበቱ እንደማይወጣ ተናገረ። በርካታ ሰሀቦች አንገቱን ለመቀንጠስ ቢመኙም ጥበበኛው ነብይ አልፈቀዱም። ባልተለመደ ሰዓት ጦራቸው እንዲንቀሳቀስ አዘዙ። ወደ መዲና እየተመለሱ ባሉበት ከኡሰይድ ኢብኑ ሁደይር ጋር ተገጣጠሙ። ኡሰይድ ግራ በመጋባት «ምነው ባልተለመደ ወቅት መጓዝን መረጡ?» ሲል መልዕክተኛውን ጠየቀ።
መልዕክተኛውም
« أوما بلغك ما قال صاحبكم عبد الله بن أبي ؟ زعم إن رجع إلى المدينة أخرج الأعز منها الأذل

የጓደኛህ የኢብኑ ኡበይ ወሬ አልደረሰህምን? ወደ መዲና ስንመለስ የተከበረው ወራዳውን እንደሚያስወጣ ዝቷል!» አሉት።
ኡሰይድም «በርግጥ የተከበሩት እርስዎ ነዎት አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! ወራዳው ደግሞ እርሱ ነው!» አለ። ቀጥሎም «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የእርሱን ነገር ተውት! እርስዎ ወደ መዲና በመጡበት ወቅት እርሱን በእኛ ላይ ንጉስ አድርገን ልንሾመው ዘውዱን የምናበጅበት ሉል እየሰበሰብን ነበር። የእርስዎ መምጣት ንግስናውን እንደነጠቀው ያስባል።» አላቸው። 

የአላህ መልዕክተኛ ጉዟቸውን ቀጥለው ምሽት ላይ ጦራቸውን አሳረፉ። ጦራቸው ባሸለበበት ወቅት መልዓኩ ጅብሪል የመናፍቃንን ምዕራፍ ይዞ ከተፍ አለ። ኢብኑ ሰሉል  ያስተባበላቸው ነገሮች በሙሉ እውነት መሆናቸው እውን ሆነ።

«يَقُولُونَ لَئِن رَّجَعْنَا إِلَى الْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ الْأَعَزُّ مِنْهَا الْأَذَلَّ ۚ وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ

«ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያወጣል» ይላሉ፡፡ አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡» (ሙናፊቁን፣ 8)

የአባቱ የንፍቅና ወሬ ከአብዱላህ ጆሮ ደረሰ። አብዱሏህ አባቱን በማክበር በአንሷሮች ዘንድ የታወቀ ነው። ሆኖም ጉዳዩ የሀይማኖት ነውና እምነቱ ዝምድናውን አሸነፈ። በመዲና መግቢያ በር ላይ ሰይፉን እያውለበለበ አባቱን መጠበቅ ጀመረ። አባቱ ሲደርስ አስቆመው።
«በአላህ ይሁንብኝ የአላህ መልዕክተኛ ካልፈቀዱልህ በስተቀር በዚህ አታልፍም። እርሱ የተከበረ አንተ ደግሞ ወራዳ ነህና!» አለው።
አብዱላህ ኢብኑ ኡበይ ኢብኑ ሰሉል የተፈጠረውን ወደ አላህ መልዕክተኛ ሄዶ ተናገረ። የአላህ መልዕክተኛም እንዲገባ ፈቃድ ሰጡ። ልጁ አብዱላህም «አሁን ግባ የአላህ መልዕክተኛ ፈቅደውልሀል።» ሲል አሳለፈው።

የአላህ መልዕክተኛ ሲደርሱም አብዱላህ ጠጋ ብሎ «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አባቴ እንዲገደል መወሰንዎን ሰማሁ። በእውነት በላከዎት ጌታ ይሁንብኝ አባቴን ከማክበሬ የተነሳ በሙሉ አይኔ አይቼው አላውቅም። ግን እርስዎ ከፈለጉ ጭንቅላቱን ይዤልዎት እመጣለሁ። ምክንያቱም የአባቴን ገዳይ መመልከትን እጠላለሁ።» አላቸው።

አዛኙ ነብይ ግን አሁንም የግድያ ትዕዛዝ አላስተላለፉም። የሚያደርስባቸውን መከራ ችለው መኖርን መረጡ። ኃይሉ እየላቸው፣ አቅም ሳይከዳቸው መቻልን አስቀደሙ። የሰው ልጅ እድሜ የተቆጠረ ነውና የመናፍቃን ቁንጮ የምድር ቆይታ ተጠናቀቀ። ሙጃሂዱ ልጁ ወደ ነብያችን ጠጋ ብሎ አባቱ እንደሞተ አሳውቆ ልብሳቸውን ለጀናዛው መጠቅለያ እንዲሰጡት ጠየቃቸው። የመናፍቃን ራስ እንዲጠቀለለው ልብሳቸውን አውልቀው ሰጡ። ቱፍታቸውንም አልነፈጉትም። የጀናዛ ስግደት እንዲሰግዱበት ሲጠይቃቸውም ጀናዛው ሲዘጋጅ እንዲጠሯቸው ተናገሩ። የእውነት ጉዳይ የሚያንገበግባቸው ኡመር (ረዐ) «እንዴት ለዚህ መናፍቅ?» ብለው ተቃወሙ። አዛኙ ነብይ ግን ከመስገድ አልተወገዱም።
27👍12🔥2🤯1
«اسْتَغْفِرْ لَهُمْ أَوْ لَا تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ إِن تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ سَبْعِينَ مَرَّةً فَلَن يَغْفِرَ اللَّهُ لَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَفَرُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ

ለእነርሱ ምሕረትን ለምንላቸው፤ ወይም ለእነሱ ምሕረትን አትለምንላቸው (እኩል ነው)፡፡ ለእነሱ ሰባ ጊዜ ምሕረትን ብትለምንላቸው አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም፡፡ ይህ እነርሱ አላህና መልክተኛውን በመካዳቸው ነው፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አያቀናም፡፡ (ተውባ፣ 80)

የእዝነቱ ቀንዲል ተጠየቁ። «መናፍቅ ሆኖ ሳለ በእርሱ ላይ ትሰግድበታለህን?»
«አላህ ያለው ሰባ ጊዜ ምህረትን ብትለምንላቸው እንኳን ነው። እኔ ደግሞ ሰባ ጊዜ ድጋሚ ሰባ ጊዜ፣ ድጋሚ ሰባ ጊዜ እጠይቅለታለሁ።» አሉ።  ይህንን እዝነት ምን ትሉታላችሁ?
በኋላ ላይ ግን ቁርዓን ከዚህ በኋላ ለመናፍቃን ምህረትን እንዳይለምኑ አስጠነቀቀ።

«وَلَا تُصَلِّ عَلَىٰ أَحَدٍ مِّنْهُم مَّاتَ أَبَدًا وَلَا تَقُمْ عَلَىٰ قَبْرِهِ ۖ إِنَّهُمْ كَفَرُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَمَاتُوا وَهُمْ فَاسِقُونَ

ከእነሱም በአንድም በሞተ ሰው ላይ ፈጽሞ አትስገድ፡፡ በመቃብሩም ላይ አትቁም፡፡ እነሱ አላህንና መልክተኛውን ክደዋልና፡፡ እነሱም አመጸኞች ኾነው ሞተዋልና፡፡» (ተውባ፣ 84)

ይህ የነብዩ (ሰዐ) የእዝነት ትዕይንት በሺህ የሚቆጠሩ መናፍቃንን ወደ አማኝነት መለሰ። ከዚህ ታሪክ ከቤተሰባችን እምነታችንን ማስቀደምን እና መልካም ለዋለልን ብቻ ሳይሆን ለበደለንም መልካምን መዋልን እንማራለን።  እየተበደሉ የሚችሉ፤ ለጎዳቸው እዝነትን የሚሞሉ ውድ ነብይ!

በአዛኙ ነብይ፣ በባለእዳው መልዕክተኛ፣ በይቅር ባዩ ተዓምር፣ በምድር በሰማይ ጌጥ ላይ የአላህ ሰላት እና ሰላም ይውረድ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
56👍10🔥4😢4🥰2👏1
Live stream started
Live stream finished (3 hours)
2025/07/14 20:59:31
Back to Top
HTML Embed Code: