ናቸው። እንደወለደች ጠርጥሬ ነበር። የፈረደባት እህቷ ጋር በዚያራ ሰበብ ደወልኩ። እንደለመደባት ሳልጠይቃት መለሰችልኝ። ወልዳለች። ኑሮዋም ዱባይ ሆኗል።
ዛሬ ከስራ መልስ ወደ ቤት ስገባ ቤቴ ውስጥ የቲላዋ ድምፅ እየተስተጋባ ነው። ወደ ፎቅ ስወጣ ድምፁ የሴት መሆኑን ለየሁ። መኝታ ቤቴን ከኪፋያ ውጪ ማንም ስለማይረግጠው እሷ እንደሆነች ገባኝ። አፏ በጣም ይጣፍጣል። ስገባ ቁምሳጥኑ ፊት ቆማ ልብሶቼን እያስተካከለች በቃሏ ትቀራለች። የምትቀራውን ምዕራፍ በጣም እወደዋለሁ። የዩሱፍ ምዕራፍ ነበር። በሩ ጋር ስደርስ ቀጣዩን የቁርዓን አንቀፅ አነበበች።
«وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ነፍሴንም (ከስሕተት) አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (አለ)፡፡»
«ድገሚው ....»
«ደገመችው!»
አቀራሯ ልብን ይሰረስራል። አልጋው ላይ ተቀምጬ ማልቀስ ጀመርኩ። እያለቀስኩ መሆኑን ስታይ ዝም አለች። እንድትቀጥል ጠየቅኳት። እየቀራች አቅፋ ታባብለኝ ጀመር። የተቀባችው ሽቶ ጠረኑ ደስ ይላል። አቀራሯን መሳም ፈልጌ ይሁን ባላውቅም ከንፈሯን በከንፈሬ ከደንኩት። ፊቷ ቀላ። ዝም አለች። ደነገጥኩ።
«ሀፊዝ ነሽ እንዴ?»
«ሲያስተዋውቁን ነግረውህ ነበር።»
«አልሰማኋቸውም።»
«ጠዋት ጠዋት የት እንደምታደርሰኝስ ታውቃለህ?»
«አላውቅም!»
«ለምን ቸልተኛ መሆንን መረጥክ?»
«ተሰብሬ ይሆን?»
«የበለጠ መሰበር ትፈልጋለህ?»
«አልፈልግም?»
«እኔ አዝኜብህ ድንገት ብሞትስ?»
«አዝነሽብኛል?»
«ባሌ እንድትሆን እንጂ የተጋባነው እንደ አባቴ ለመንከባከብ ከሆነማ አባት እኮ አለኝ።»
«ምን ላድርግልሽ?»
«ፈገግ በልልኝ! እንደድሮው ተጫዋች ሁን!»
«ድሮ ታውቂኛለሽ?»
«ባባ ከጋሼ ጋር ጓደኛ አይደል። አዎ! ሳታገባ በፊት ቤታችሁ እመጣ ነበር!»
«ይሆናል።»
«ያኔ በጣም ተጫዋች ነበርክ። ደስ ትለኝ ነበር።»
«ይገርማል።»
«ስታገባ አልቅሼ ነበር። ልጅ ነበርኩ ያኔ .... 19 ዓመት ቢሆነኝ ነው።»
«ለምን?»
«ደስ ትለኝ ነበር!»
«የምርሽን ነው?»
«አዎ አሁን ደግሞ በጣም እወድሀለሁ።» ሳመችኝ። 500 ዋት ትራንስፎርመር መያዝ በሉት። ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ።
«ጠዋት ጠዋት የት ነው የማደርስሽ?»
«መድረሳ ነው። ሂፍዝ አስቀራለሁ።»
አዛን አለ። ግንባሬን ስማኝ ተነሳች። መስጂድ ሄድኩ። ቤት እስክመለስ ድረስ ናፈቀኝ። ሳትደሰትብኝ የምትሞት መስሎኝ ፈራሁ። አዲስ ስሜት ነው። ከኢሻ በኋላ አበባ እና ብዙ ቸኮሌት ገዝቼ ገባሁ። እንደሁልጊዜው ቤቱን ድምቅ አድርጋ እየጠበቀችኝ ነበር። ስገባ እጄ ላይ የነበረውን አይታ ማልቀስ ጀመረች።
«ምን ሆንሽ?»
«ወላሂ አውቅ ነበር!»
«ምኑን?»
«አላህ ልብህን ወደኔ እንደሚያዘነብልልኝ! ኪፋያህ እንደምሆን!»
«ትዕግስትሽ ግን ይገርማል።»
«ዱዓ የማይቀይረው ነገር እንደሌለ ስለማውቅ!»
«ከፈይተኒ ኪፋያቲ!»
አበባውን ተቀበለችኝና ወደ መኝታ ቤት ገባች። ቴሌቭዥኑን ከፈትኩት። ዩትዩብ ከፈትኩ። አይኔን ወደ መኝታ ቤቱ ስመልስ ልቤ ትርክክ አለ። ኪፋያ! ሰውነቷ ብርሀን ይረጫል። ታፋዋ ላይ የቀረ የመኝታ ልብስ ለብሳ ወደኔ ተጠጋች። ከቴሌቭዥኑ የፈሪሀን ኢሜይል ዘግቼ ወጣሁ። ድጋሚ ስለሷ ላልከታተል Sign out አልኩት። ታፋዬ ላይ ተቀመጠች።
«አላህ ምን እንደሚል ታውቃለህ?»
«ምን ይላል?»
ውቡ ድምጿ መስረቅረቅ ጀመረ።
«وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡»
«እናስ?»
«እናማ እርካብኝ .... የአላህን አስደናቂ ተዓምር አስተንትንብኝ። ሀላልህ አይደለሁ።» ሳመችኝ።
ከአፌ ዚክር ወጣ።
«بِسْمِ اللَّـهِ، اللَّهُمَّ جَنِّـبْنَا الشَّيْطَانَ، وَجَنِّبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنَا
በአላህ ስም፣ አሏህ ሆይ ሸይጧንን ከልለን፤ የምትለግሰንንም ከሸይጧን ከልልን።»
ከዚህ በኋላ የሆነውን መናገሩ የላጤን ሆድ ያስብሳል። ባለትዳርን ላልታቀደ ልጅ ያነሳሳል። መች ወደ መኝታ ክፍል እንደገባን አላውቅም። ጀለቢያ ከሱሪ አንፃር በቀላሉ እንደሚወልቅ ገብቶኛል። የሆነው ሆነ። እቅፍ አድርጌያት አሸለብኩ።
ለሊት ላይ በላብ እንደተጠመቅኩ ድንገት «አላህ! አላህ!» እያልኩ ከእንቅልፌ ባነንኩ። ኪፋያ አቅፋኝ መቅራት ጀመረች።
እንደተረጋጋሁ አቀፍኳት።
«ምን ሆንክ?» አለችኝ።
«ሰሚሬን አየሁት።»
«ማሻአላህ። በመልካም አየኸው?»
«በሁላችንም ምኞት ላይ!»
«ንገረኛ!»
«ጀነት ውስጥ አየሁት።»
«አላሁአክበር! ምን አለህ?»
«እየደጋገመ እንዲህ ይል ነበር።
بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ الْمُكْرَمِينَ
ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»
«ያ ራህማን!» ማልቀስ ጀመረች።
«ሰው የሚያውቅህ በመልካም አይደለም። ጌታህ እንዴት ማረህ አልኩት።»
«እና ምን አለህ?»
«ወደ አላህ ሳልመለስ የተኛሁበት ምሽት .... ከወንጀሌ ለማምለጥ ያላለቀስኩበት ለሊት የለም። ቀን እወነጅለዋለሁ። ማታ አለቅሳለሁ። ሀጢዓትን በሰራሁ ጊዜ መልካም ነገርን አስከትላለሁ። ድብቅ ሰደቃን አበዛለሁ። ለሙስሊም ወንድም እህቶቼ የተቻለኝን መልካም አደርጋለሁ። የአልቃሾችን እንባ አብሳለሁ። ደካሞችን እከላከላለሁ። አላህ ፀፀቴን ወደደው። እዝነቱ የሰፋው ጌታዬ ማረኝ። አለኝ።»
ኪፋያ መንሰቅሰቅ ጀመረች።
«ዛሬ ደስታዬ ነው .... ምን ያስለቅስሻል?»
«ፉአዴ .... ሰሚር እያነበበው ከነበረው የቁርዓን አያ በፊት ያለውን አንቀፅ ታውቀዋለህ?»
«ምንድነው?» እያለቀሰች መቅራት ጀመረች።
«قِيلَ ادْخُلِ الْجَنَّةَ ۖ قَالَ يَا لَيْتَ قَوْمِي يَعْلَمُونَ
«ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡»
ማልቀስ ጀመርኩ። ሰሚሬም ጀነት መግባቱን ዱንያ ያለነው እንድናውቅ ፈለገ። በዱንያ እያለ የጀሀነም ነው ብለው የተጠቋቆሙበት እጆች መሳሳታቸውን እንዲረዱ ተመኘ። ጌታውም አደረገለት። የጌታውን ምህረት ተጎናፅፎ ጀነት ገባ። ጀነት መግባቱንም አወቅን። «እስኪ አንቀፆቹን እየደጋገምሽ አንብቢልኝ።» አልኳት። እየደጋገመች ማንበብ ጀመረች።
«قِيلَ ادْخُلِ الْجَنَّةَ ۖ قَالَ يَا لَيْتَ قَوْمِي يَعْلَمُونَ● بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ الْمُكْرَمِينَ

👍124❤57🥰8😁4🔥2
የልብ ነገር ሲደመደም
(ፉአድ ሙና)
***
የልብ ነገር የእኛ ታሪክ ነው። በሌሎች ስጋ ውስጥ ተቀርፆ የቀረበ የእኛ የሁላችንም ታሪክ! «እኛ እኮ!» እያልን ራሳችንን ከሰቀልንበት የውሸት ብፅዕና አውርዶ የደረስንበትን የወንጀል ውድቀት የሚያሳይ የአኗኗራችን ነፀብራቅ ነው። ዛሬ የፃፍኩትን ይህን ታሪክ ከ5 አመታት በፊት ተፅፎ ባነበው ተጋነነ ብለው ከሚከራከሩት ውስጥ በሆንኩ ነበር። በዕድሜያችን ልክ የማወቅ ተጋላጭነቱ የሚኖሩንን አኗኗሮች አሉ። የልብ ነገር እንደዚያ ነው።
የልብ ነገር የወንጀልና የተውበት ጉዳይ ነው። ብዙዎቻችን እያለቀስንለት ያለው የእኛ ገመና ነው። እዝነቱና ሲትሩ ፅንፍ የሌለው ጌታችን ምስጋና ይገባው። ቆመን እንሄዳለን። ሲትሩ ባልነበረ ለራሳችን ማዘን የምንችል አልነበርንም። አላህ ካለንበት የወንጀል ትብታብ ነፃ ይበለን። ከመረጣቸው ባሮቹም ያድርገን።
ይህን ፅሁፍ ስፅፍ ከጎኔ የነበራችሁትን አንባቢዎቼን ከልብ አመሰግናለሁ። ያለእናንተ ድጋፍ መፅናቱ ከባድ ነበር። ለፅሁፉ ያላችሁ ጉጉት እኔም ማቋረጥን እንድፈራና 25 ቀናትን ያለማቋረጥ በኸልዋ እንድቆይ አድርጎኛል።
የልብ ነገር Live Fiction ነበር። እንደከዚህ ቀደሙ ተፅፎ አልቆ እየተፖሰተ የነበረ ሳይሆን፤ በየቀኑ እየተፃፈ የሚለቀቅ ነበር። ይህ ለደራሲው እጅግ ፈታኝ የሆነ አፃፃፍ ነው። ወደ ኋላ ተመልሼ ላስተካክል ቢል አንባቢ ጋር ደርሷልና ምንም ማስተካከል አይችልም። እስካሁን ካስነበብኳችሁ ድርሰቶች በዚህ የLive fiction ዘውግ የተፃፉት ነጫጭ ጥቁረቶችና የልብ ነገር ናቸው። ለእኔ ቢከብድም አሪፍ ትግል ነበር።
አላህ ሳይቆይ ከዚህ በተሻለ ልብወለድ የምንገናኝ ያድርገን!
በቀጣይ አስተያየት የምትፅፉበት ፅሁፍ እለቃለሁ።
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu

❤180👍49👏17🥰6😁5
አስተያየት መዘርገፊያ
***
ሁሌም የምለው አንድ ነገር አለ። የእኔ አንባቢዎች ቁጥሮች አይደሉም። ቤተሰቦች ናቸው። በርካታ ኸይር ስራ ላይ በአጅር የተሳሰሩ፤ በተለያዩ ፅሁፎች የተጋመዱ ቤተሰቦቼ ናቸው።
እንደሁልጊዜው ስለ የልብ ነገር የተሰማችሁን ለቀጣይ የሚጠቅም አስተያየትና ቢመለስልን የምትሉትን ጥያቄ ፃፉልኝ። ስትፅፉ ብትችሉ በአማርኛ ታይፕ ቢሆን መልካም ነው። ካልሆነም ግልፅ በሆነ መልኩ ክተቡት። የሁላችሁንም አነባለሁ። አንብቤም ፖስት በማድረግ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ላይ ምላሽ እሰጣለሁ።
የኛ እውነታ የሌሎችን ስጋ ሲለብስ!

👍58❤36❤🔥2
ስለአስተያየትዎቻችሁ
(ፉአድ ሙና)
***
የሁላችሁንም አስተያየት አንብቤያለሁ። ሁላቹንም ለአስተያየትዎቻችሁ ከልብ አመሰግናለሁ። በተደጋጋሚ የተጠየቁና ቢመለሱ ተገቢ ናቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ጥያቄዎች ከዚህ እንደሚከተለው መልሻለሁ።
¤ እውነተኛ ታሪክ ነው?
ፅሁፉ የእውነት ነፀብራቅ ነው። በቀጥታ ከአንድ ግለሰብ የህይወት ማህደር የተቀዳ ግን አይደለም። የብዙ ትዝብቶች ጥርቅም ነው። ልብወለድ ነው።
¤ በገሀዱ አለም ሴት ልጅ ሳትጋበዝ ይህን ያህል ወንድን ለማማለል ትሞክራለች?
አዎን! በደንብ! ልብወለዱ ላይ ከተጠቀሰውም በላይ የሚሄዱ አሉ።
¤ የራስህ ታሪክ ነው?
የሁላችንም ታሪክ እንደመሆኑ የእኔም ታሪክ ከመሆን አያመልጥም። ታሪኩ በቀጥታ ከኔ ህይወት የተገለበጠ ግን አይደለም።
¤ የሙተነቂቦችን ነገር
ከልብወለዱ በፊት ያሉ ስራዎቼን እንዲሁም መፅሀፌን ያነበበ ለሙተነቂቦች ያለኝን ስሜት ይረዳል። የወከልኩበት መንገድ ስህተት አይታየኝም። ከዚያ ይልቅ ለሁላችንም የማንቂያ ደወል የሚሆን ይመስለኛል። በዚህ ድፍረት ውክልናውን ስጠቀም በእውነት አለም ተመሳሳይ ነገሮች መብዛታቸውን ትረዱኛላችሁ ብዬ እገምታለሁ።
¤ የSexual ነገር ገለፃ ለምን በዛ?
በዚህ ለረበሽኳችሁ በመጀመሪያ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ፅሁፉን እንዲያነብ የተፈለገ ቡድን ስላለ እሱን ቡድን fish ለማድረግ ተግባራዊ የተደረገ ነው። ስልቱ እንደሚረብሻችሁ እንዲሁም የነገሩን ጉዳት በደንብ እረዳዋለሁ። ግን ይህ ልብወለድ እንዲያነበው የተፈለገ Target audience ስላለ እሱን ለማግኘት የተደረገ ነው።
¤ ለምን ፋአድ ሙና የሚባል ገፀ ባህሪ አስፈለገ ?
የልብ ነገር የሁላችንም ታሪክ ነው። ትረካው በአንደኛ መደብ እንደመተረኩ አንባቢው እኔን እያሰበ እንዲያነበው እና የበለጠ Closness እንዲኖረው ለማድረግ የተደረገ ነው። ይኼ በሌሎች ፀሀፍት ዘንድም የተለመደ ነው።
¤ ሁሉም ለምን ስኬታማ ሆኑ? በተለይ ኢክራም እና ሰሚራ?
ኢክራም ስኬታማ መሆን አለመሆኗ አልተገለፀም። ግን የወደደችውን አጥታለች። ሰሚራ ወደ አላህ ለመመለስ የሚሞክር ልብ የነበራት እንስት ናት። በዚህ ሂደት ላይ ላሉ ሁሉ ከሀራም እና ሀላሉ የቱ እንደሚሻል ንፅፅር እንዲሰሩበት የሆነ ነው። ተውበት ካደለን ሁሉም ቆንጆ ይሆናል። ኢንሻአላህ!
¤ ሙና ስለሚባለው የነገርከን እውነት ነው?
እሱ እውነት ቢሆንማ ፈሪሀ የምትባል የቀድሞ ሚስት፣ ኢክራም የምትባል ex እና ኪፋያ የምትባል ማረፊያ በኖረኝ ነበር። ሰው ለታሪኩ ቅርበት እንዲኖረው የገባ ነው። ገለፃው የተፈበረከ ነው።
¤ በየቀኑ የሚሰጡህ አስተያየቶች የታሪኩ ይዘት ላይ ተፅዕኖ ነበራቸው?
የታሪኩ መዋቅር ቀድሞ የተጣለ ስለነበር የሚሰጡት አስተያየቶች ያመጡት ለውጥ አልነበረም። ሆኖም በጣም ለመፃፍ የሚያነሳሱ ነበሩ።
¤ ፈሪሀ "የኔ ጌታ" ብላ ባሏን መግለጿ እንዴት ይታያል?
የኔ ጌታ የሚለው ቃል አስተዳዳሪነትን የሚጠቁም ነው። በሀገራችንም ተግባራዊ የሆነ፤ በቋንቋ ስርዓታችን ውስጥ የነበረ ቃል ነው። አንዳንድ ሰፈር የተውሂድ ዳዕዋ የማህበረሰቡን ተጨባጭ ሳይረዳ ወደ ሀይማኖታዊ ትርጓሜ ወስዶት ይመስለኛል። በአረብኛውም ይህ አጠቃቀም አለ። ክፍለሀገር ሄደህ ከብቶች እያሳዩህ «የዚህ ጌታ ማነው?» ብለው ቢጠይቁህ «አላህ!» ብለህ አትመልስም። ምክንያቱም ጥያቄያቸው ባለቤቱ ማነው? የሚል ነው። የፈሪሀም ከዚህ አንግል ነው። የተውሂድ ጥያቄም የሚነሳበት አይደለም።
¤ ዘፈኖቹን ከየት አወቅካቸው? ለምንስ ገቡ!
የዘፈኖቹን ግጥሞች ያስገባሁት አንባቢ relate እንዲያደርግ ነው። በዚህ ወንጀል ውስጥ ያሉ ሰዎች ሲያነቡት በደንብ ወደ ራሳቸው ህይወት ያቀርባቸዋል። እኔ የፃፍኩት ከፅሁፉ ጋር የሚሄዱ ዘፈኖችን ሰርች በማድረግ ግጥሞቹን ከአንዳንድ ሳይቶች በማግኘት እንዲሁም በዚያ መልኩ ያላገኘኋቸውን እየሰማሁ በመገልበጥ ጭምር ነው። ዜማቸውን ለማያውቅ ግጥም ናቸው። ለሚያውቅ ዘፈን ናቸው።
ከአስተያየትዎቻችሁ ተደጋጋሚዎቹን መልሻለሁ። ቅዳሜ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በቴሌግራም ቻናሌ ላይ ባለኝ ላይቭ መሰናዶ ላይ ሌሎች ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ይቻላል። በሰፊውም ለመመለስ ይመቸኛል።
ቅዳሜ 3:00 ላይቭ እንገናኝ! ኢንሻአላህ!

👍138❤25👏17😁2
አጀብ አጀብ!
ቀኑ ቅዳሜ ነው! ቅዳሜ ምሽት 3:00 ደግሞ ፈገግታ መጅሊስ አለ። የዛሬው ፈገግታ መጅሊሳችን ደግሞ በዚህ ሳምንት በተፈፀመው የልብ ነገር ልብወለድ ላይ ያተኩራል።
ሀሳባችሁን፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችሁን ሌላም ሌላም ሸክፋችሁ ኑ! እየተዝናናን እናወጋለን!
ስነፅሁፍ፣ ቁርዓንና ሀዲስ ሪፍሌክሽን እና ቲላዋ ደግሞ እንደተለመደው ይቻላል።
ማታ 3:00 ላይ በዚሁ ቻናል ላይ እንገናኛለን! ኢንሻአላህ!
የልብ ነገርን ያነበቡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ጋብዙ!

👍50🥰9❤5🫡3🔥2
ሰቀቀን
(ፉአድ ሙና)
***
ጠብ አለ እንባዋ
መቻል አቃታት፣ ዘረገፈችው፣
እርቃን ገላዋን
ፀፀት ገረፈው፣ አይኔን አየችው።
እንደሁልጊዜው
ተንሰቀሰቀች፣ ዳግም ወንጅላ፣
የስሜት እቶን
መንገድ አስቶን፣ በፍቅር ጥላ።
እርቃን እንዳለች ....
አለም ቢያየው
የሚሞትለት፣ ገላዋ ፈጥጦ፣
ከፊቴ ቆመች
ጥያቄ የሞላው፣ ፊቷ አፍጥጦ።
«አይለምደንም አይደል?»
ተንሰቀሰቀች
ይገርፋት ጀመር፣ የፀፀት ጅራፍ፣
ምን ነበር እንደው
በኒካህ ጠርታ፣ ከስቃዬ ባርፍ!
እንዳላገባት ....
ቤተሰብ ይሉት፣
ዘግቶታል ደጄን፣ ሆኖኝ ደንቃራ፣
የኛን መታመም
ስቃያችንን፣ አ‘ርጎታል ተራ።
እወዳታለሁ
ፈገግታዋ ነው፣ ልቤን ‘ሚያሰራው፣
አነባችብኝ
እንጃልኝ እኔ፣ እንዳልሞት ፈራሁ።
ሳታወልቅ በፊት ....
ያኔ ቶብተን
ከፍም ገላዋ፣ የፆምኩ ለታ፣
ታወራኝ ነበር
ከተውበት ኪታብ፣ ስለ አላህ ማርታ!
«ተው ግን እንጋባ!»
ህመም ሆኖባት
የሞት ጥሩምባ፣ ቢቀድመኝ ብላ፣
የድመት ተውበት
እየሆነባት፣ በመውደቅ ዝላ፣
ለምናኝ ነበር
እንድሰብርላት፣ የሀላልን በር፣
ምን አቅም አለኝ
እወዳታለሁ፣ ግን እንዴት ልድፈር?
አመል ሲደግመን ...
ለምደናልና
ጠረን ለጠረን፣ ስንነፋፈቅ፣
ፀፀት ተረስቶ
ስንገባበዝ፣ ዳግም ለማውለቅ፣
የናፍቆት እሳት
ሲለበልበን ላይሳካልን፣ ማሸነፍ ከቶ፣
ቀን ስንወስን
ከአንዳችን አፍ፣ ግብዣው ተጠርቶ፣
የስሜት ጉልበት
ፍፁም ሽሮልን፣ የአምናውን ለቅሶ፣
በስሜት ነዳድ
ዳግም ተጠበስን፣ ስቃዩ ብሶ!
ማንባት ድጋሚ ....
ደግሞ መንሰቅሰቅ
«አግባኝ» ትላለች፣ ከፊቴ ቆማ፣
በደገመችው
በሀጢዓቷ፣ ክፉኛ ታማ፣
«ተው ግን አለሜ፣
ኒካህ እንሰር፣ የታል ውዴታ፣
ታፈቅረኝ የለ
የአባትህን ህግ፣ በጉልበት ፍታ!»
ልቧን አሟታል
ለሀላል እምቢ፣ ሀራም በሞቴ፣
መቻል ደክሟታል
እየተነሳች፣ ትውደቀው ስንቴ!
በየረመዳኑ ....
አማኝ በአንድነት
ሲለምን ድሎት፣ ተሀጁድ ቆሞ፣
የኛ ማረን ነው
የኛ አፅዳን ነው፣ ልባችን ታሞ።
እንዲሉ ሀቢብ ...
ለተዋደደ
መድሀኒት የለው፣ ትዳር ነው እንጂ፣
የሀሴት አለም
ነብስ የሚጠግን፣ የፍቅር ፈንጂ!
ቤተሰብ ከፍቶ
ታምሜ እያየኝ፣ ልቤ እያደፈ፣
መድሀኒት ሳለኝ
ትንሽ ቆይ ሲለኝ፣ ጅስሜ ረገፈ።
ከኒቃቧ ውስጥ
እኔ የማውቀው፣ አለ እርቃኗ፣
ከሒፍዜ ወዲህ
እሷ የምታየኝ ፣ አለሁ ሚስኪኗ።
በወንጀል ትብታብ
ተገፍተን ሳለን፣ ከሀላል መደብ፣
ሞት ከቀጠፈን
ሳይረጋ ቀርቶ፣ የአመፅ ወደብ፣
አያልቅስልን
የያዘን ሁሉ፣ ከሀላል ጋርዶ፣
አሁን ካልሆነ
ካለፍንስ ወዲያ፣ ጥቅሙ ባዶ!
አሁን ተውበት
ኋላ ራቁት፣
ይህን ልቤን
ምንድን ይሉት?
እዝነትህን ጌታዬ!
***
በብዙ እውነተኛ ታሪኮች ላይ የተመረኮዘ
***
@Fuadmu
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
***
ጠብ አለ እንባዋ
መቻል አቃታት፣ ዘረገፈችው፣
እርቃን ገላዋን
ፀፀት ገረፈው፣ አይኔን አየችው።
እንደሁልጊዜው
ተንሰቀሰቀች፣ ዳግም ወንጅላ፣
የስሜት እቶን
መንገድ አስቶን፣ በፍቅር ጥላ።
እርቃን እንዳለች ....
አለም ቢያየው
የሚሞትለት፣ ገላዋ ፈጥጦ፣
ከፊቴ ቆመች
ጥያቄ የሞላው፣ ፊቷ አፍጥጦ።
«አይለምደንም አይደል?»
ተንሰቀሰቀች
ይገርፋት ጀመር፣ የፀፀት ጅራፍ፣
ምን ነበር እንደው
በኒካህ ጠርታ፣ ከስቃዬ ባርፍ!
እንዳላገባት ....
ቤተሰብ ይሉት፣
ዘግቶታል ደጄን፣ ሆኖኝ ደንቃራ፣
የኛን መታመም
ስቃያችንን፣ አ‘ርጎታል ተራ።
እወዳታለሁ
ፈገግታዋ ነው፣ ልቤን ‘ሚያሰራው፣
አነባችብኝ
እንጃልኝ እኔ፣ እንዳልሞት ፈራሁ።
ሳታወልቅ በፊት ....
ያኔ ቶብተን
ከፍም ገላዋ፣ የፆምኩ ለታ፣
ታወራኝ ነበር
ከተውበት ኪታብ፣ ስለ አላህ ማርታ!
«ተው ግን እንጋባ!»
ህመም ሆኖባት
የሞት ጥሩምባ፣ ቢቀድመኝ ብላ፣
የድመት ተውበት
እየሆነባት፣ በመውደቅ ዝላ፣
ለምናኝ ነበር
እንድሰብርላት፣ የሀላልን በር፣
ምን አቅም አለኝ
እወዳታለሁ፣ ግን እንዴት ልድፈር?
አመል ሲደግመን ...
ለምደናልና
ጠረን ለጠረን፣ ስንነፋፈቅ፣
ፀፀት ተረስቶ
ስንገባበዝ፣ ዳግም ለማውለቅ፣
የናፍቆት እሳት
ሲለበልበን ላይሳካልን፣ ማሸነፍ ከቶ፣
ቀን ስንወስን
ከአንዳችን አፍ፣ ግብዣው ተጠርቶ፣
የስሜት ጉልበት
ፍፁም ሽሮልን፣ የአምናውን ለቅሶ፣
በስሜት ነዳድ
ዳግም ተጠበስን፣ ስቃዩ ብሶ!
ማንባት ድጋሚ ....
ደግሞ መንሰቅሰቅ
«አግባኝ» ትላለች፣ ከፊቴ ቆማ፣
በደገመችው
በሀጢዓቷ፣ ክፉኛ ታማ፣
«ተው ግን አለሜ፣
ኒካህ እንሰር፣ የታል ውዴታ፣
ታፈቅረኝ የለ
የአባትህን ህግ፣ በጉልበት ፍታ!»
ልቧን አሟታል
ለሀላል እምቢ፣ ሀራም በሞቴ፣
መቻል ደክሟታል
እየተነሳች፣ ትውደቀው ስንቴ!
በየረመዳኑ ....
አማኝ በአንድነት
ሲለምን ድሎት፣ ተሀጁድ ቆሞ፣
የኛ ማረን ነው
የኛ አፅዳን ነው፣ ልባችን ታሞ።
እንዲሉ ሀቢብ ...
ለተዋደደ
መድሀኒት የለው፣ ትዳር ነው እንጂ፣
የሀሴት አለም
ነብስ የሚጠግን፣ የፍቅር ፈንጂ!
ቤተሰብ ከፍቶ
ታምሜ እያየኝ፣ ልቤ እያደፈ፣
መድሀኒት ሳለኝ
ትንሽ ቆይ ሲለኝ፣ ጅስሜ ረገፈ።
ከኒቃቧ ውስጥ
እኔ የማውቀው፣ አለ እርቃኗ፣
ከሒፍዜ ወዲህ
እሷ የምታየኝ ፣ አለሁ ሚስኪኗ።
በወንጀል ትብታብ
ተገፍተን ሳለን፣ ከሀላል መደብ፣
ሞት ከቀጠፈን
ሳይረጋ ቀርቶ፣ የአመፅ ወደብ፣
አያልቅስልን
የያዘን ሁሉ፣ ከሀላል ጋርዶ፣
አሁን ካልሆነ
ካለፍንስ ወዲያ፣ ጥቅሙ ባዶ!
አሁን ተውበት
ኋላ ራቁት፣
ይህን ልቤን
ምንድን ይሉት?
እዝነትህን ጌታዬ!
***
በብዙ እውነተኛ ታሪኮች ላይ የተመረኮዘ
***
@Fuadmu
@Fuadmu
👍119💔68❤17😭10🔥7❤🔥6👏2😍1
ብዥዥዥታ!
(ፉአድ ሙና)
***
«ቆንጆ ባልሆን ይሻል ነበር!»
«ምንሽ ተነካ?»
አየችኝ። ዝም ብላ አየችኝ።
«እያት እስኪ ያቺን ...» ካፌው ውስጥ ተቀምጣ የነበረች ፉንጋ አሳየችኝ።
«እና?»
«አሁን እሷን ስንት ሰው የሚጨቀጭቃት ይመስልሀል?»
«ያንቺን ያህል አይሆንም።»
«አየህ ትኩረቷ አይበጠበጥም! ምናልባትም ቶሎ ታገባለች ምርጫ አያደናግራትም!»
«እና ምን ላድርግሽ እኔ?»
«ተወኝ! አፈቀርኩሽ የሚል ሰው ሰለቸኝ! ልማርበት ተወኝ! ልቅራበት ተወኝ! ሰው ልሁንበት አትጥለፈኝ! በቃኝ!» እየተንሰቀሰቀች ማልቀስ ጀመረች።
ከወንበሬ እየተነሳሁ «ፈተና ይዞ የማይመጣ ኒዕማ የለም!» አልኳት።
ከዚህ በኋላ አላገኘኋትም! ምናልባት አንድ ፈተናዋ ከተቀነስኩላት .... ብዬ!

🥰86👍42😁25😢19❤13🔥6👏3🤯1
🤔50😁32👍21🔥3❤2
ትዝታ ትዝታ ትዝታ
ዛሬ አንድ የከርሞ ሰው አግኝቼ ትዝታዬን ጫረው፤ ከአመታት በፊት ታወሩኝ የነበራችሁ ወዳጆች ግን የት ደረሳችሁ? አገባችሁ? ወለዳችሁ? ምን ላይ ናችሁ?

🤷♀44😁20👍6🤔2
👍131❤42🔥7
ከመክበር በር ላይ!
(ፉአድ ሙና)
.
ጊዜው በረታ ..... የአይናቸው ማረፊያ ኸዲጃን እና ከለላ አጎታቸውን አቡ ጧሊብን ቀበሩ። የመካ ሰዎች ነገር ከቀን ወደ ቀን ቢጠናቸው፤ ነብይ በሀገሩ አይከበርምና የሌላ ቀዬ ሰዎች ከተመለሱልኝ ብለው ወደ ጧዒፍ ከዘይድ ኢብኑ ሀሪሳ ጋር ተጓዙ።
ከጧዒፍ ቀዬ ቆሙ .... እኒያ የልቀት ልክ ... ለአይን የሚታፈሩ ነብይ .... ለተላኩበት ጥሪ ሲሉ የጧዒፍ መሪዎችን ተዋደቁ። እናንተ የጧዒፍ ሰዎች ሆይ የምታመልኳቸውን ጣዖቶች ወዲያ በሉና የአላህን አንድነት አውጁ ሲሉ ለፈፉ። የጧዒፍ ሰዎች በእጄ የሚሉ አይነት አልነበሩም። ይልቁንስ የተከበረውን ነብይ እና ዘይድ ኢብኑ ሀሪሳን በድንጋይ ይወግሯቸው ገቡ። ህፃናት እና እብዶቻቸውን አሰማሩባቸው። ከውዱ ነብይ ገላ ደም ፈሰሰ። ጫማቸው በደም ሞላ። ዘይድ በቻለው አቅም ከለላ ሊሆናቸው ይሞክራል። በዚህ መልኩ ከጧዒፍ ከተማ ለቀው ወጡ። ተደብድበው .... ተዋርደው .... ጧዒፍን ለቀቁ።
ከጧዒፍ ወጣ እንዳሉ መልዕክተኛው በተሰበረ ልብ ወደ ጌታቸው ተጣሩ።
«اللهم إليك أشكو ضعف قوتي، وقلة حيلتي، وهواني على الناس، يا أرحم الراحمين، أنت رب المستضعفين، وأنت ربي، اللهم إلى من تكلني؟ إلى بعيد يتجهمني، أم إلى عدو ملكته أمري؟ إن لم يكن بك غضب علي فلا أبالي، غير أن عافيتك أوسع لي، أعوذ بنور وجهك الذي أشرقت به الظلمات، وصلح عليه أمر الدنيا والآخرة، أن ينزل بي سخطك، أو يحل علي غضبك، لك العتبى حتى ترضى ولا حول ولا قوة إلا بالله
አላህ ሆይ! የአቅሜን ደካማነት፣ የዘዴዬን ማነስ፣ በሰዎች ዘንድ መዋረዴን ወደ አንተ አቤት እላለሁ! አንተ የአዛኞች አዛኝ የሆንክ ጌታ ነህ! አንተ የደካማዎች ጌታ ነህ! አንተ ጌታዬ ነህ! አላህ ሆይ ወደማን ታስጠጋኛለህ? ፊቱን ወደሚያጨፈግግብኝ ባዕድ ወይስ በጉዳዬ ላይ ስልጣን ለሰጠኸው ጠላት? አንተ ካልተቆጣህብኝ ግድ የለም። ግን ከአንተ የሆነ ጤንነት እና ደህንነት ለኔ በጣም ሰፊ ነው። የአንተ ቁጣ እንዳይወርድብኝ ጨለማዎች በበሩበትና በሱ ላይ የአዱንያና የአኼራ ጉዳዮች በተበጁበት በፊትህ ብርሀን እጠበቃለሁ። እስከምትወድልኝና እስከምትቀበለኝ ድረስ ስሞታዬን ለአንተ አቀርባለሁ። በአንተ እንጂ ዘዴም ሆነ ኃይል የለም።»
ከዚህ ዱዓ በኋላ የአላህ መልዕክተኛና ባልደረባቸው ወደ መካ ጉዟቸውን ቀጠሉ። መልዓኩ ጂብሪል (ዓሰ) ወደ ነብያችን በመምጣት «ሙሀመድ ሆይ ህዝቦችህ ያሉህን ጌታህ ሰማ፣ ማስተባበላቸውንም አየ! ጌታህ የተራራ መልዓክትን የምታዛቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ወዳንተ ልኳል!» አላቸው።
የእዝነት ተምሳሌቱ ነብይም «ከልጅ ልጆቻቸው እንኳን ቢሆን አላህን በብቸኝነት የሚገዛ ይወጣ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ።» ሲሉ የእልቂቱን ደመና አነሱ። ላደማቸው .... ለደበደባቸው .... ላዋረዳቸው ህዝብ ምላሻቸው ይህ ነበር። የአላህ ሰላት እና ሰላም በእዝነተ ሰፊው ነብይ ላይ ይሁን!
ወደ መካ ሲደርሱ በሀገሩ ከለላ የላቸውምና ቁረይሾች እንደሚገድሏቸው ገባቸው። በጃሂሊያ ጊዜ የነበረ ውብ ባህል ነበራቸው። ከለላ መስጠት! የአለሙ ጌጥ ከለላ ይሰጧቸው ዘንድ ሶስት ሰዎች ጋር መልዕክት ላኩ። ሁለቱ አሻፈረኝ ቢሉም ሙጥዒም ኢብኑ አዲይ ጥሪውን መለሰ። ልጆቹን አስታጥቆ ውዱን ነብይ አጅቦ ወደ መካ አስገባ። ነብያችን የበድርን ጦርነት ካሸነፉ በኋላ ይህን ሰው አውስተዋል። «ሙጥዒም በጠየቀኝ ምርኮኛዎችን ሁሉ በፈታሁለት ነበር!» ብለዋል። ነገር ግን ሙጥዒም ከበድር በፊት ወደማይቀርበት ወደ ቀጣዩ አለም ተጉዞ ነበር።
ከጭንቅ በኋላ ብስራት እንዳለ ለዓለም ትምህርት ይሆን ዘንድ፤ አላህ (ሱወ) በረጀብ በ27ኛው ለሊት የኢስራዕ ወል ሚዕራጅን ድግስ አሰናዳላቸው። ምድር ላይ በሰው ከተዋረዱ በኋላ ሰማይ ላይ ወስዶ አከበራቸው። ቡራቅን ተጭነው «ሀዬ» እያሉ ከጅብሪል ጋር በምድር ወደ መስጂደል አቅሳ ጋለቡ። ቡራቅ የሚሉት ጉድ አይኑ ማየት የሚችለውን ያህል በብርሀን ፍጥነት ይራመድ ነበር። አላህም በኢስራዕ ምዕራፍ ገድሉን ዘከረ።
«سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡»
(ኢስራዕ፣ 1)
ጧዒፍ ላይ በድንጋይ የተደበደቡት ነብይ በተቀደሰው ቤት ነብያትን ኢማም ሆነው አሰገዱ። ከዚያም ሚዕራጅ ተከተለ። ከጅብሪል ጋር ጉዞ ወደ ሰማይ ቤት! በየሰማዩ የተለያዩ ነብያትን እያገኙ ወደ ሲድረተል ሙንተሀ አቀኑ።
«مَا كَذَبَ الْفُؤَادُ مَا رَأَى๏أَفَتُمَارُونَهُ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ๏ وَلَقَدْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ๏ عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ๏ عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ๏ إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَىٰ๏ مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ๏ لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَىٰ
(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም። ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡»
(ነጅም 11 –18)
በዚህ ጉዞ ሲድረተል ሙንተሀ ላይ ሲደርሱ ጅብሪልን በተፈጠረበት ቅርፅ ተመልክተውታል። ከጌታቸው ጋር አውግተውም ሰላትን እና የላሚቷን ምዕራፍ የመጨረሻ አንቀፆች ተቀብለዋል።
ውዱ ነብይ ወደ ምድር እንደተመለሱ ይህንን ተዓምር ተናገሩ። ሰው ይሳለቅ ገባ። ጭራሽ በአንድ ለሊት ከመካ በይተል መቅዲስ ድረስ ዘለቅኩ፤ ወደ ሰማይም አረግኩ አለ ብለው ተሳለቁ። ይህ ወሬ የአቡበከር ጆሮ ደረሰ። «እርሱ ይህን ብሏል?» ሲሉ ጠየቁ። «አዎን ብሏል!» የሚል ምላሽን አገኙ። «እንግዲያማ ብሎ እንደሆን እውነቱን ነው።» ሲሉ ተቀበሉ። ሲዲቅ የተባለውን ማዕረግ ያስገኛቸው ይህ ነበር። «ከሰማይ መልዕክት ይመጣልኛል ሲለኝ ያመንኩትን ሰው ወደ ሰማይ ሄድኩ ቢለኝ ምን ይገርመኛል።» ሲሉ እምነታቸውን አረጋገጡ።
ከነብዩ የኢስራዕ ወል ሚዕራጅ ጉዞ አንድ ትልቅ ትምህርት እንማራለን። ከችግር በኋላ በእርግጥ ድሎት አለ።
«ምንድን ቢከፋህ
የበደል በትር፣ ቢያሳጣህ አቅም፣
አደራ አስታውስ
ከሚዕራጅ በፊት፣ የጧዒፍ በደል እንደሚቀድም! »
በአለማቱ ጌጥ .... በክብራችን መሰረት .... በእዝነቱ ቁንጮ .... በመወደድ ሚዛን .... በድሀው ነብይ ላይ የጌታው ሰላት እና ሰላም ይውረድ!

🥰67❤43👍34😢6👏3
Fuad Muna (Fuya)
ከመክበር በር ላይ! (ፉአድ ሙና) . ጊዜው በረታ ..... የአይናቸው ማረፊያ ኸዲጃን እና ከለላ አጎታቸውን አቡ ጧሊብን ቀበሩ። የመካ ሰዎች ነገር ከቀን ወደ ቀን ቢጠናቸው፤ ነብይ በሀገሩ አይከበርምና የሌላ ቀዬ ሰዎች ከተመለሱልኝ ብለው ወደ ጧዒፍ ከዘይድ ኢብኑ ሀሪሳ ጋር ተጓዙ። ከጧዒፍ ቀዬ ቆሙ .... እኒያ የልቀት ልክ ... ለአይን የሚታፈሩ ነብይ .... ለተላኩበት ጥሪ ሲሉ የጧዒፍ መሪዎችን…
ከመክበር በር ላይ Fuad muna
AudioLab
❤82👍12😢11🔥6😁3🙏1
Sekeken Final_
<unknown>
❤52💔20👍14😭7😢5👎4😁3🔥2🥰2