ፈገግታ መጅሊስ የረመዷን መቀበያ 16/06/16
Fuad Muna (Fuya)
የትናንት ምሽት የፈገግታ መጅሊስ የረመዳን መቀበያ መሰናዷችንን ጋበዝናችሁ!
በኢፋዳ የሀድራ ትስስር የተዘጋጀ ነበር። ወደ ሀድራ ትስስሩ ለመግባት የምትፈልጉ ኮሜንት ላይ ባለው ሊንክ ትራንዚት ማድረጊያ ግሩፑን መቀላቀል ትችላላችሁ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
በኢፋዳ የሀድራ ትስስር የተዘጋጀ ነበር። ወደ ሀድራ ትስስሩ ለመግባት የምትፈልጉ ኮሜንት ላይ ባለው ሊንክ ትራንዚት ማድረጊያ ግሩፑን መቀላቀል ትችላላችሁ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
❤20👍17
ኢፋዳ በልዩ ቅናሽ!
.
ከአሁን ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ኢፋዳን @ifadasales ላይ ወይም በአካል በመሄድ ለምትገዙ የ20% ቅናሽ ያደረግን ሲሆን በ400 ብር ብቻ መፅሀፉን መሸመት ትችላላችሁ።
መልካም ሸመታ!
.
@Fuadmu
.
ከአሁን ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ኢፋዳን @ifadasales ላይ ወይም በአካል በመሄድ ለምትገዙ የ20% ቅናሽ ያደረግን ሲሆን በ400 ብር ብቻ መፅሀፉን መሸመት ትችላላችሁ።
መልካም ሸመታ!
.
@Fuadmu
👍21🔥5
ልቻል በይ ቻዪው!
(ፉአድ ሙና)
***
እንደው በምድር
የምስለውን፣ አይኖርም ብዬ፣
ከምን ቢያበጅሽ
አመል ከግብርሽ፣ ተውቦ ታዬ?
ስብራት አጥፎት
ዳግም ሊያፈቅር፣ ሲገግም ልቤ፣
በምን ጥበብሽ
ፈገግታሽ ብቻ፣ ሆነ ቀለቤ?
የእውነት መውደድ
ማስመሰል አልባ፣ የፍቅር ገንቦ፣
ደረቁ ልቤ
ባንቺ እንደሚረጥብ፣ መቼ አስቦ!
ግን ረጠበ ....
አገኘሁ አንቺን
የቀን አውራዴን፣ የልቤን ደሊል፣
ቀልቤን ገራሽው
የትም ብትወስጂው፣ መርሀባ እንዲል!
አገኘሁ አንቺን
የሸውቄን ጌታ፣ ሙተከሊሜን፣
አመት ብትሰብኪኝ
እንጃልኝ እኔ፣ በቃኝ ማለቴን!
አገኘሁ እኔ
የቡርዳን ቅመም፣ አሚር የልቤን፣
ጨፍኛለሁኝ
ወዳሻሽ ቦታ፣ ውሰጃት ነፍሴን!
አግኝቻለሁኝ
‘ስቲግፋር ተቀማጭ፣ ለውዷ ሀጃ፣
ሳላይሽ ባድር
ሰው መሆኔንም፣ አላውቅም እንጃ!
እናም አለሜ ...
ዘውትር ጆሮዬን
የሚባርከው፣ ሳወራሽ አህዋል፣
የጀነት ዜማሽ
የሚከብድበት፣ የፆም ወር መጥቷል።
በድምፅ በሳቅሽ
የሚከፈተው፣ የቀኔ ደስታ፣
እንዴት ይሆናል
በወሬሽ ረሀብ፣ ሸህሩን ሲመታ?
እንጃልኝ እኔ
አልተወው ነገር፣ አዞኛል ጌታሽ፣
እወድሻለሁ
ፍቅሬ አልጎደለም፣ ስጋት አይግባሽ!
በትዳር አፋፍ
ስንዞር ጠርዙን፣ ባንችል መቆጠብ፣
አመቱን ባከን
ለረመዷኑ፣ በይ እንሰብሰብ!
አዎ እንሰብሰብ ...
ምን ቢከብደኝም
ድምፅሽን መራብ፣ ለአንዲት ደቂቃ፣
ወሩን ልታገስ
የአመፁ መንገድ፣ ቁረጪ ይብቃ!
አይናፍቀኝም
ምግብ መጠጡ፣ አይኔ ላይ መጥቶ፣
አላህ ቢኩለን
ካንቺ መፆሜን፣ ስራዬን አይቶ።
የረመዳኑን
ድርብርብ ምንዳ፣ ላታጪ ብዬ፣
ካንቺ ልፆም ነው
«መርሀባ» በዪኝ፣ «አብሽር ፍቅርዬ!»
አልችልምና
በርታ ካላልሽኝ፣ አይቆርጥም ልቤ፣
ጥርስሽ ይብራልኝ
እንዳልመለስ፣ ኸይሩን አስቤ!
እሺ ካልሽ ወዲያ ...
አጥብቀሽ ያዢው
በረመዷኑ፣ የዱዓን ወገብ፣
በሸዋል ለሊት
ጎናችን እንዲያርፍ፣ ከአንድ መደብ!
ያ ራህማን በይው
ዱዓን ተቀባይ፣ ሰሚውን ጌታ፣
ነብሳችን ትረፍ
መብሩክ መባልን፣ ደጋግማ ሰምታ!
ኪራይ አለም ላይ
ፋታ እንዳናጣ፣ በዱንያ ሀጃ፣
ያንን ውብ አለም
ፈታ እንድንል፣ በነቢ ምልጃ፣
ይቅርብን ዛሬን
ሰማይ ቢነካም፣ ናፍቆትሽ ጥጉ፣
ልማል አልልም
ላንቺ አይጠፋሽም፣ የመውደድ ወጉ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
***
እንደው በምድር
የምስለውን፣ አይኖርም ብዬ፣
ከምን ቢያበጅሽ
አመል ከግብርሽ፣ ተውቦ ታዬ?
ስብራት አጥፎት
ዳግም ሊያፈቅር፣ ሲገግም ልቤ፣
በምን ጥበብሽ
ፈገግታሽ ብቻ፣ ሆነ ቀለቤ?
የእውነት መውደድ
ማስመሰል አልባ፣ የፍቅር ገንቦ፣
ደረቁ ልቤ
ባንቺ እንደሚረጥብ፣ መቼ አስቦ!
ግን ረጠበ ....
አገኘሁ አንቺን
የቀን አውራዴን፣ የልቤን ደሊል፣
ቀልቤን ገራሽው
የትም ብትወስጂው፣ መርሀባ እንዲል!
አገኘሁ አንቺን
የሸውቄን ጌታ፣ ሙተከሊሜን፣
አመት ብትሰብኪኝ
እንጃልኝ እኔ፣ በቃኝ ማለቴን!
አገኘሁ እኔ
የቡርዳን ቅመም፣ አሚር የልቤን፣
ጨፍኛለሁኝ
ወዳሻሽ ቦታ፣ ውሰጃት ነፍሴን!
አግኝቻለሁኝ
‘ስቲግፋር ተቀማጭ፣ ለውዷ ሀጃ፣
ሳላይሽ ባድር
ሰው መሆኔንም፣ አላውቅም እንጃ!
እናም አለሜ ...
ዘውትር ጆሮዬን
የሚባርከው፣ ሳወራሽ አህዋል፣
የጀነት ዜማሽ
የሚከብድበት፣ የፆም ወር መጥቷል።
በድምፅ በሳቅሽ
የሚከፈተው፣ የቀኔ ደስታ፣
እንዴት ይሆናል
በወሬሽ ረሀብ፣ ሸህሩን ሲመታ?
እንጃልኝ እኔ
አልተወው ነገር፣ አዞኛል ጌታሽ፣
እወድሻለሁ
ፍቅሬ አልጎደለም፣ ስጋት አይግባሽ!
በትዳር አፋፍ
ስንዞር ጠርዙን፣ ባንችል መቆጠብ፣
አመቱን ባከን
ለረመዷኑ፣ በይ እንሰብሰብ!
አዎ እንሰብሰብ ...
ምን ቢከብደኝም
ድምፅሽን መራብ፣ ለአንዲት ደቂቃ፣
ወሩን ልታገስ
የአመፁ መንገድ፣ ቁረጪ ይብቃ!
አይናፍቀኝም
ምግብ መጠጡ፣ አይኔ ላይ መጥቶ፣
አላህ ቢኩለን
ካንቺ መፆሜን፣ ስራዬን አይቶ።
የረመዳኑን
ድርብርብ ምንዳ፣ ላታጪ ብዬ፣
ካንቺ ልፆም ነው
«መርሀባ» በዪኝ፣ «አብሽር ፍቅርዬ!»
አልችልምና
በርታ ካላልሽኝ፣ አይቆርጥም ልቤ፣
ጥርስሽ ይብራልኝ
እንዳልመለስ፣ ኸይሩን አስቤ!
እሺ ካልሽ ወዲያ ...
አጥብቀሽ ያዢው
በረመዷኑ፣ የዱዓን ወገብ፣
በሸዋል ለሊት
ጎናችን እንዲያርፍ፣ ከአንድ መደብ!
ያ ራህማን በይው
ዱዓን ተቀባይ፣ ሰሚውን ጌታ፣
ነብሳችን ትረፍ
መብሩክ መባልን፣ ደጋግማ ሰምታ!
ኪራይ አለም ላይ
ፋታ እንዳናጣ፣ በዱንያ ሀጃ፣
ያንን ውብ አለም
ፈታ እንድንል፣ በነቢ ምልጃ፣
ይቅርብን ዛሬን
ሰማይ ቢነካም፣ ናፍቆትሽ ጥጉ፣
ልማል አልልም
ላንቺ አይጠፋሽም፣ የመውደድ ወጉ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
❤101👍41🥰24👎7
ኢፋዳ በልዩ ቅናሽ!
.
ከአሁን ጀምሮ እስከ ነገ ምሽት ድረስ ኢፋዳን @ifadasales ላይ ወይም በአካል በመሄድ ለምትገዙ የ20% የረመዳን ቅናሽ ያደረግን ሲሆን በ400 ብር ብቻ መፅሀፉን መሸመት ትችላላችሁ።
መልካም ሸመታ!
.
@Fuadmu
.
ከአሁን ጀምሮ እስከ ነገ ምሽት ድረስ ኢፋዳን @ifadasales ላይ ወይም በአካል በመሄድ ለምትገዙ የ20% የረመዳን ቅናሽ ያደረግን ሲሆን በ400 ብር ብቻ መፅሀፉን መሸመት ትችላላችሁ።
መልካም ሸመታ!
.
@Fuadmu
👍8
ኢፋዳ በልዩ ቅናሽ!
.
ከአሁን ጀምሮ እስከ ነገ ምሽት ድረስ ኢፋዳን @ifadasales ላይ ወይም በአካል በመሄድ ለምትገዙ የ20% የረመዳን ቅናሽ ያደረግን ሲሆን በ400 ብር ብቻ መፅሀፉን መሸመት ትችላላችሁ።
መልካም ሸመታ!
.
@Fuadmu
.
ከአሁን ጀምሮ እስከ ነገ ምሽት ድረስ ኢፋዳን @ifadasales ላይ ወይም በአካል በመሄድ ለምትገዙ የ20% የረመዳን ቅናሽ ያደረግን ሲሆን በ400 ብር ብቻ መፅሀፉን መሸመት ትችላላችሁ።
መልካም ሸመታ!
.
@Fuadmu
👍7
ኢፋዳን በክልል ከተሞች!
.
★ወራቤ
ወራቤ ከቴሌ ጎን(ፓርክ ሆቴል ፊትለፊት) አቅሷ የኪታብ መሸጫ መደብር
★ሀዋሳ
ሀዋሳ ፒያሳ ኬርአውድ ሆቴል ፊትለፊት ሁሴን ሞል ሳኒ ሞባይል አክሰሰሪ ሱቅ ቁ.29
★ጅማ
ጅማ +251944842429 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።
★ደሴ
ደሴ +251982674095 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።
★አዳማ
ፖስታ ቤት ወደ ፒኮክ በሚወስደው አስፓልት በኩል አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ አሰብ አዳማ የገበያ ማዕከል መግቢያ ላይ በሚገኘው ፖስታ ስቴሽነሪ
★ድሬዳዋ
ድሬዳዋ አሸዋ በሚገኘው ሲትራ ሱፐርማርኬት
ቦታው ከጠፋችሁ+251929065110 ደውሉ
★ሀረር
ሀረር ሲጋፋ ተራ kim Cafe ፊትለፊት መካ ኤሌክትሮኒክስ
ቦታው ከጠፋችሁ +251968209420 ይደውሉ።
.
#Ifadasales
.
★ወራቤ
ወራቤ ከቴሌ ጎን(ፓርክ ሆቴል ፊትለፊት) አቅሷ የኪታብ መሸጫ መደብር
★ሀዋሳ
ሀዋሳ ፒያሳ ኬርአውድ ሆቴል ፊትለፊት ሁሴን ሞል ሳኒ ሞባይል አክሰሰሪ ሱቅ ቁ.29
★ጅማ
ጅማ +251944842429 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።
★ደሴ
ደሴ +251982674095 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።
★አዳማ
ፖስታ ቤት ወደ ፒኮክ በሚወስደው አስፓልት በኩል አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ አሰብ አዳማ የገበያ ማዕከል መግቢያ ላይ በሚገኘው ፖስታ ስቴሽነሪ
★ድሬዳዋ
ድሬዳዋ አሸዋ በሚገኘው ሲትራ ሱፐርማርኬት
ቦታው ከጠፋችሁ+251929065110 ደውሉ
★ሀረር
ሀረር ሲጋፋ ተራ kim Cafe ፊትለፊት መካ ኤሌክትሮኒክስ
ቦታው ከጠፋችሁ +251968209420 ይደውሉ።
.
#Ifadasales
👍4😁2
አዲስ አበባ ካሉን ፒካፕ ሎኬሽኖች በሚቀርብዎ ቦታ
★ብስራተ ገብርኤል
አዶት መልቲፕሌክስ ሱቅ ቁጥር 40
★ፒያሳ
ኤልያና ሞል ምድር ላይ ዋዋ ኮስሞቲክስ
★መገናኛ
ማራቶን የንግድ ማዕከል ምድር ላይ ሶፊ ሞባይል
★ቤተል
ቤተል ከአደባባዩ ዝቅ ብሎ ከፊዩቸር ሞል አጠገብ ባለው AJ Mall G 02 የስፖርት ቁሳቁስ መሸጫ
★ጀሞ
ጀሞ ሰይድ ያሲን ህንፃ አንደኛ ፎቅ 135 አሊፍ በጎ አድራጎት ቢሮ
★ኮልፌ
አጠና ተራ በሚገኘው እፎይታ የገበያ ማዕከል ኢትዮ ፋሽን ግራውንድ BBSB 102
የኢፋዳ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
#Ifadasales
★ብስራተ ገብርኤል
አዶት መልቲፕሌክስ ሱቅ ቁጥር 40
★ፒያሳ
ኤልያና ሞል ምድር ላይ ዋዋ ኮስሞቲክስ
★መገናኛ
ማራቶን የንግድ ማዕከል ምድር ላይ ሶፊ ሞባይል
★ቤተል
ቤተል ከአደባባዩ ዝቅ ብሎ ከፊዩቸር ሞል አጠገብ ባለው AJ Mall G 02 የስፖርት ቁሳቁስ መሸጫ
★ጀሞ
ጀሞ ሰይድ ያሲን ህንፃ አንደኛ ፎቅ 135 አሊፍ በጎ አድራጎት ቢሮ
★ኮልፌ
አጠና ተራ በሚገኘው እፎይታ የገበያ ማዕከል ኢትዮ ፋሽን ግራውንድ BBSB 102
የኢፋዳ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
#Ifadasales
👍18❤1😘1
አልመሰክርም
(ፉአድ ሙና)
(ማርች 8 አስመልክቶ ድጋሚ የተፖሰተ)
.
ለሴቶች ቀን ብለሽ
የላክሽው አበባ፣ ደርሶኛል ጠውልጎ፣
ምስክር ሁን ብለሽ
ከፃፍሽው ብሶት ጋር፣ አንድ ላይ ታሽጎ።
የላክሽው አበባ ፣ ለምን ገረጀፈ?
ጠውልጎ እስኪወድቅ ፣ ለምንድን ታለፈ?
እሱም እንዳንቺው ነው?
እንቡጥ ነኝ እያለ
ለ'ንቡጥ መብት ሲታገል፣ ሀረግነት ሽቶ፣
ፅጌረዳነቱ ከላዩ የተነሳ ፣ ከእድሜው ተጣልቶ?!
እሱም አንቺነት ነው?
.
ሀረግ መሆን መስሎት
የነፃነት ድካው፣ ታላቅነት ስሙ፣
ከክብሩ ተነስቶ
ስጦታነት አልፎት ፣ እንደዚህ መድከሙ?
እሱም እንዳንቺው ነው?
አዎን እንዳንቺው ነው
እኩል እና መምሰል የተደናገረው፣
ሴትነቱን ያጣ ወንድነት ሲያምረው!
ሀረግ ነው ‘ሚመስለው።
እሱም አንቺነት ነው!!!
.
ከፃፍሽልኝ ብሶት
ሴትነቴን አክብር፣ ያልሽው ታየኝ ጎልቶ፣
ወንድ ከሆንሽ ወዲያ
ሴትነት ሊከበር፣ ከወዴት ተገኝቶ?!
ሀፍረትሽ ተገፎ
ገላሽ ተሸቅጦ ፣ ከአንቺነት ተገፍተሽ፣
ጡት እና ዳሌ እንጂ
ሴትነት ጠቋሚ ፣ ምን አለ የቀረሽ?
ሴትነት የት ታይቶ?
ከወዴት ተገኝቶ?
ምንህን እናክብር አንቺነትህ ጠፍቶ?!!
.
ከፃፍሽልኝ ብሶት
ሴትነቴን መስክር ያልሽው አሳዘነኝ፣
ሴትነትሽን ‘ሚገልፅ
የኩሩነት ጌጥሽ ለአፍታ ታወሰኝ።
ሴትነትሽ ገዝፎ
ጨዋነት ተላብሶ ፣ ለአንቺነትሽ በቅተሽ፣
የነበረሽ ውበት
ከአይኔ ይታየኛል ፣መሆን አንቺ እያለሽ።
አለመሆን ሲገዝፍ ፣ መስክር ማለት መጣ፣
ያለመሆን ዳገት በመምሰል ሊወጣ።
መስክር ማለት መጣ!
.
እንኳን አደረሰሽ
ብዬ ለመመለስ ከበዳት ብዕሬ፣
የሴትነት ድካው
ወንድነት ነው ብለሽ ፣ ስላሰብሽ አፍሬ።
ከጀመርኩት አይቀር ፣ሀቁን ልናገራ፣
ሴትነት አይልቅም ፣ ከወንድነት ተራ።
የሴትነት ልቀት
በሴትነት ሲታሽ ፣ ሴትነት ሲፈርደው፣
ተከብሮ የሚኖር
በከለለው ሜዳ ፣ ሲፈነጭ የሚያምረው፣
ሴትነት እንዲያ ነው!!
እንዲያም ነው ‘ሚያምረው!!
.
ተጨማሪ ግጥሞችን ለማንበብ ቻናሉን ይቀላቀሉ!
👇
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
(ማርች 8 አስመልክቶ ድጋሚ የተፖሰተ)
.
ለሴቶች ቀን ብለሽ
የላክሽው አበባ፣ ደርሶኛል ጠውልጎ፣
ምስክር ሁን ብለሽ
ከፃፍሽው ብሶት ጋር፣ አንድ ላይ ታሽጎ።
የላክሽው አበባ ፣ ለምን ገረጀፈ?
ጠውልጎ እስኪወድቅ ፣ ለምንድን ታለፈ?
እሱም እንዳንቺው ነው?
እንቡጥ ነኝ እያለ
ለ'ንቡጥ መብት ሲታገል፣ ሀረግነት ሽቶ፣
ፅጌረዳነቱ ከላዩ የተነሳ ፣ ከእድሜው ተጣልቶ?!
እሱም አንቺነት ነው?
.
ሀረግ መሆን መስሎት
የነፃነት ድካው፣ ታላቅነት ስሙ፣
ከክብሩ ተነስቶ
ስጦታነት አልፎት ፣ እንደዚህ መድከሙ?
እሱም እንዳንቺው ነው?
አዎን እንዳንቺው ነው
እኩል እና መምሰል የተደናገረው፣
ሴትነቱን ያጣ ወንድነት ሲያምረው!
ሀረግ ነው ‘ሚመስለው።
እሱም አንቺነት ነው!!!
.
ከፃፍሽልኝ ብሶት
ሴትነቴን አክብር፣ ያልሽው ታየኝ ጎልቶ፣
ወንድ ከሆንሽ ወዲያ
ሴትነት ሊከበር፣ ከወዴት ተገኝቶ?!
ሀፍረትሽ ተገፎ
ገላሽ ተሸቅጦ ፣ ከአንቺነት ተገፍተሽ፣
ጡት እና ዳሌ እንጂ
ሴትነት ጠቋሚ ፣ ምን አለ የቀረሽ?
ሴትነት የት ታይቶ?
ከወዴት ተገኝቶ?
ምንህን እናክብር አንቺነትህ ጠፍቶ?!!
.
ከፃፍሽልኝ ብሶት
ሴትነቴን መስክር ያልሽው አሳዘነኝ፣
ሴትነትሽን ‘ሚገልፅ
የኩሩነት ጌጥሽ ለአፍታ ታወሰኝ።
ሴትነትሽ ገዝፎ
ጨዋነት ተላብሶ ፣ ለአንቺነትሽ በቅተሽ፣
የነበረሽ ውበት
ከአይኔ ይታየኛል ፣መሆን አንቺ እያለሽ።
አለመሆን ሲገዝፍ ፣ መስክር ማለት መጣ፣
ያለመሆን ዳገት በመምሰል ሊወጣ።
መስክር ማለት መጣ!
.
እንኳን አደረሰሽ
ብዬ ለመመለስ ከበዳት ብዕሬ፣
የሴትነት ድካው
ወንድነት ነው ብለሽ ፣ ስላሰብሽ አፍሬ።
ከጀመርኩት አይቀር ፣ሀቁን ልናገራ፣
ሴትነት አይልቅም ፣ ከወንድነት ተራ።
የሴትነት ልቀት
በሴትነት ሲታሽ ፣ ሴትነት ሲፈርደው፣
ተከብሮ የሚኖር
በከለለው ሜዳ ፣ ሲፈነጭ የሚያምረው፣
ሴትነት እንዲያ ነው!!
እንዲያም ነው ‘ሚያምረው!!
.
ተጨማሪ ግጥሞችን ለማንበብ ቻናሉን ይቀላቀሉ!
👇
@Fuadmu
👍65❤33👎5👌3😭3👏1😘1
ረመዳን መጥቶላችኋል!
(ፉአድ ሙና)
***
እናንተ አማኞች ሆይ!
ረመዳን መጣላችሁ!
የፍጥረተ አለሙ ስርዓት የሚለወጥበት የፀጋ ወር ደረሳችሁ!
በዚህ ወር ጌታችሁ የክብር ቃሉን አወረደ!
የነብዩሏሂ ኢብራሒም (ዐሰ) ሱሁፍ፣
የነብዩሏሂ ሙሳ (ዐሰ) ተውራት፣
የነብዩሏሂ ኢሳ (ዐሰ) ኢንጂል እና
የአለማቱ ፈርጥ፣ የነብዮች ኢማም፣ የሸፋዓው እጣ የነብያችን (ሰዐወ) ቁርዓን በዚህ ታላቅ ወር ተወረደ።
የደረሳችሁት ወር ...
የጀሀነም ደጃፎች ይከረቸሙበታል።
የጀነት በሮች ይከፋፈቱበታል።
ከሰይጣናትም ትላልቆቹ ይታሰሩበታል።
በውስጡ አንዲት ምሽት አለች
ከሺህ ምሽቶች ትልቃለች!
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ ረመዳን መጣላችሁ!
የረመዳን የመጀመሪያው ምሽት ላይ ተጣሪ ይጣራል!
«አንተ መልካም ፈላጊ ሆይ ግፋ!
አንተ ክፉ ፈላጊ ሆይ ታቀብ!» ይባላል!
ጌታችሁ ለመልካም ስራ የክፍያ ስኬል አለው!
መልካም ስራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ ድረስ ይከፈላል።
ፆም ሲቀር! የፆም ዋጋ የእኔ ነው!
እኔም እመነዳዋለሁ ሲል ሸሽጎታል።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ ረመዳን መጣላችሁ!
በረመዳን በሁሉም ምሽቶች
አላህ ከጀሀነም የሚያወጣቸው ባሪያዎች አሉት!
የእነዚህ ሰዎች ነፃ መውጣት
ሰው የገደለ ሰው የሟቹ ቤተሰቦች አውፍ ቢሉት ሳይቀጣ እንደሚተርፈው እንደዚያ ምሳሌ ነው!
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ ረመዳን መጣላችሁ!
በውስጡ ብዙ ትሩፋቶች አሉት!
ኸይሯን የተከለከለ በእርግጥ ተከልክሏል!
ረመዳንን ለአላህ ብሎ በአግባቡ የፆመ
ያለፈው ወንጀሉ በሙሉ ይታበሳል!
አያያዟን ያላወቀበት በትንሳዔ ቀን በእርግጥ ይቆጫል።
ያወቀበት በአዕላፍ ደስታዎች ውስጥ ይፈነጫል።
ረያን የሚሉትን የጀነት በር አልፎ የስኬት ሽቶ ይረጫል።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ!
ይህን ታላቅ እንግዳ እንደ ባለጌ ወይስ እንደ ጨዋ ታስተናግዱታላችሁ?
የተቆጠሩ ቀናት ናቸው!
የ
ተ
ቆ
ጠ
ሩ
ቀናት!!!
እናንተ አማኞች ሆይ ረመዳን እኮ መጥቶላችኋል!!!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
***
እናንተ አማኞች ሆይ!
ረመዳን መጣላችሁ!
የፍጥረተ አለሙ ስርዓት የሚለወጥበት የፀጋ ወር ደረሳችሁ!
በዚህ ወር ጌታችሁ የክብር ቃሉን አወረደ!
የነብዩሏሂ ኢብራሒም (ዐሰ) ሱሁፍ፣
የነብዩሏሂ ሙሳ (ዐሰ) ተውራት፣
የነብዩሏሂ ኢሳ (ዐሰ) ኢንጂል እና
የአለማቱ ፈርጥ፣ የነብዮች ኢማም፣ የሸፋዓው እጣ የነብያችን (ሰዐወ) ቁርዓን በዚህ ታላቅ ወር ተወረደ።
የደረሳችሁት ወር ...
የጀሀነም ደጃፎች ይከረቸሙበታል።
የጀነት በሮች ይከፋፈቱበታል።
ከሰይጣናትም ትላልቆቹ ይታሰሩበታል።
በውስጡ አንዲት ምሽት አለች
ከሺህ ምሽቶች ትልቃለች!
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ ረመዳን መጣላችሁ!
የረመዳን የመጀመሪያው ምሽት ላይ ተጣሪ ይጣራል!
«አንተ መልካም ፈላጊ ሆይ ግፋ!
አንተ ክፉ ፈላጊ ሆይ ታቀብ!» ይባላል!
ጌታችሁ ለመልካም ስራ የክፍያ ስኬል አለው!
መልካም ስራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ ድረስ ይከፈላል።
ፆም ሲቀር! የፆም ዋጋ የእኔ ነው!
እኔም እመነዳዋለሁ ሲል ሸሽጎታል።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ ረመዳን መጣላችሁ!
በረመዳን በሁሉም ምሽቶች
አላህ ከጀሀነም የሚያወጣቸው ባሪያዎች አሉት!
የእነዚህ ሰዎች ነፃ መውጣት
ሰው የገደለ ሰው የሟቹ ቤተሰቦች አውፍ ቢሉት ሳይቀጣ እንደሚተርፈው እንደዚያ ምሳሌ ነው!
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ ረመዳን መጣላችሁ!
በውስጡ ብዙ ትሩፋቶች አሉት!
ኸይሯን የተከለከለ በእርግጥ ተከልክሏል!
ረመዳንን ለአላህ ብሎ በአግባቡ የፆመ
ያለፈው ወንጀሉ በሙሉ ይታበሳል!
አያያዟን ያላወቀበት በትንሳዔ ቀን በእርግጥ ይቆጫል።
ያወቀበት በአዕላፍ ደስታዎች ውስጥ ይፈነጫል።
ረያን የሚሉትን የጀነት በር አልፎ የስኬት ሽቶ ይረጫል።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ!
ይህን ታላቅ እንግዳ እንደ ባለጌ ወይስ እንደ ጨዋ ታስተናግዱታላችሁ?
የተቆጠሩ ቀናት ናቸው!
የ
ተ
ቆ
ጠ
ሩ
ቀናት!!!
እናንተ አማኞች ሆይ ረመዳን እኮ መጥቶላችኋል!!!!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
❤70🥰10
ፈገግታ መጅሊስ ተጀምሯል። ገባ ገባ በሉ!
https://www.tg-me.com/fuadmu?livestream=bd9d811b647fd456b3
https://www.tg-me.com/fuadmu?livestream=bd9d811b647fd456b3
Telegram
Fuad Muna (Fuya)
የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!
ለአስተያየትዎ
@fuadmubot
ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com
❤2