Telegram Web Link
#ለፈገግታ 😂

😍አፍቃሪው😘

ሚበላ በገንዘብ መግዛቱ ሲከብደኝ
           ኑሮ ጣራ ነክቶ

ባፌ እንደዚህ አልኩ ልቤ አንድ ነገር
          ድንገት ተመኝቶ።

'' ምናለ እንደድል

ባገኝ እንደነሱ የኔ ማቶንን ሴት
       የማፍቀሩን እድል

እሷን ካላገባው እህል ባፌ አይዞርም
     ከቶ አልበለም እንድል
።''

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ቤት ማንም ሳይኖር ብቻዬን ሳለሁኝ
ስራ ጨራርሼ ፋታ እንዳገኘሁኝ
ትንሽ መለስ ብዬ ትናንቴን ለማየት
ያለፈው ዘመኔን ጥቂት ለመጎብኘት
የትዝታን መዝገብ ጀመርኩኝ መቃኘት።

እልፍ ደስታ ንፁህ ፍቅር 
ሀሜት የለ እዛው ንግር
የጨዋታው ለዛ ጥርስ የማያስከድን
ልጅነት ይመስገን ያ መልካም ዘመን።

ደሞ እሱ አልፎ ታድጎ ተጎርምሶ
በንፁ ልቤ ላይ አለማወቅ ነግሶ
መልካም ስሜ ሆኖ ከግብሬ ወርጄ
ይሉኝታን ገድዬ ንቀትን ወልጄ
ታዘብኩት እራሴን ወደኋላ ሂጄ።

By ሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@paappii
ናፍቀሽኛል

ጊዜ ይሮጣል አሉ

ጊዜ ይበራል አሉ

አንደዚ በማለት ሚያወራ ሰው ሁሉ

ምናለ ቢያስረዱኝ ይህንን ከቻሉ
:
:
ለኔ ጊዜው አይሮጥም

በፍፁም አይበርም

እንደው ይባስ ብሎ መቁጠሩንም ትቷል

ካንቺ ከራቅኩ ወዲህ ቀኑ አመት ሆኗል

እናም ርዝማኔው አሁንስ ከብዶኛል

የውነቴን ነው ምልሽ በጣም ናፍቀሽኛል
:
:
ሀልጊዜም ቢሆን አንቺን ነው ማስብሽ

ከራሴ በላይ ነው እኔ የምወድሽ

በደስታ ቆዪልኝ በአካል እስካገኝሽ::


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

           ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem
ከርግቦች ትራስ ስር
(አሌክስ አብርሃም)

የላባን መከዳ አምነህ አትመቻች
ቂም በቀል ነው ከታች!
የመስዋዕት አንገት አግኝቶ እስኪመዘዝ
አንዳች የሚወገር አንዳች የሚወገዝ
"ከርግቦች" ትራስ ስር የዛገ ሰይፍ አለ
በፍቅር እየማለ!
ማነህ ባለሳምንት ማነህ ባለዝክር
ተሰልፏል ከሳሽ ተሰብቋል ምስክር
ብቻ እጣ ይውጣብህ ልክም ሁን ስህተት
አንተን ሞረድ አርጎ የተረሳው ሁሉ ይነቃል ከዝገት!

@getem
@getem
@paappii
የትናንቱ ትናንት

ትናንት ትዝታ አቃጠለኝ ናፍቆትሽ ገደለኝ ብዬ የፃፍኩልሽ

የትናንቱ ትናንት ፈፅሞ እንዳይመስልሽ

ትናንት አፈቀርኩሽ ሞትኩኝ አበድኩልሽ

ልሰበር ልቀንጠስ ገለመሌ ያልኩሽ

ይህ ያለፈው ትናንት ጭራሽ እንዳይመስልሽ

እወድሻለሁ ያልኩሽ አንዴ አይንሽን ልየው

ቶሎ ደርሰሽልኝ ከንፈርሽን ልሳመው

ናፍቆኝ የዋለውን ጠረንሽን ልማገው

ሙት ሚያስነሳውን ድምፅሽንም ልስማው

ብዬ ያልኩት ትናንት የትናንቱ ትናንት አይደለም ፈፅሞ

በፍቅር በናፍቆት በትናንቱ ትናንት ዉል አትይም ከርሞ

በድሮው ዛሬዬ ትናንት ብዬ ያልኩሽ

ትናንት የሆነ ዛሬ ስንት አለ መሰለሽ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@paappii
..       💗ድንቅ💗

በትርምስ መሀል ባለበት ጫጫታ

ትኩረቴን ሰብስቤ ስሄድ በዝግታ

የንፋስ ሽውታ

ያንቺን ስም አምጥቶ ከጆሮዬ ቢያደርስ
            ወዲያው ልቤ መታ
:
:

እንደበነራ ፋኖስ በድቅድቅ ጨለማ

ሀሴት ይሞላኛል ስምሽን ስሰማ

አሁን አሁንማ

ሳወድስ ሳሞካሽ ያንቺን መልክ ደም ግባት

ካምሮዬ አጣው ሚሆንሽን ቃላት
:
:
መልካሙ ልብሽን

ትሁት መሆንሽን

ምገልፅበት ነገር አስሼ ስፈልግ
         ከቃላቱ ደሴት

አንድ ድምፅ ሰማሁ ሳያቋርጥ እያለ
         ድንቅ ነሽ አንቺ ሴት::

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

           ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem
ሞት
.
ያ....ክፉ ነጣቂ፤
ከሥጋ ለይቶ እስትንፋስ ፈልቃቂ፤

ወሳጅ መልአከ ሞት በሰዎች ጀርባ ላይ፤
ተንጠልጥሎ ሚኖር በእድሜ ገደብ ጣይ፤

ቀናትና ወራት በቀመር ሲለኩ፤
ወራትና አመታት ፈጥነዉ ሲተካኩ፤

የሰዉ ልጅ ማለፊያዉ፤
የእስትንፋሱ ማብቂያው ፤

ከአይን ጥቅሻ እጅጉን ይቀርባል፤
ከአፈር እንደመጣ ከአፈር ይከተታል።
.....................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
🤰ውዷ እናቴ🤰

ሲከፋኝ ሚከፋሽ ስስቅ የምትስቂ

ስሳሳት ምትመክሪኝ አንቺ የኔ አዋቂ

የአምላክ ስጦታ ለአንዷ ህይወቴ

ምን ይውጠኝ ነበር ያላንቺ እናቴ
:
:
ጓደኛ ወዳጄ ከኔ ማትርቂ

ጉዳዬን ማዋይሽ ሚስጥሬን ጠባቂ

በማንም በምንም መተኪያ የሌለሽ

በደስታ ኑሪልኝ ሳለሽ በህይወትሽ

ሁሌም ወድሻለው እኔ ያንቺ ልጅሽ::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
..........ፍቅር እንደ Icarus.......

ካልጠፋ ከዋክብት ካልጠፋ
ጨረቃ ፀሐይን መዉደዴ
ፍቅርሽ አሸንፎኝ ተፈጥሮን
ስታገል ላውልሽ ከክንዴ
ስቀርብሽ ብቃጠል ስጠጋሽ ብነድድ
ፍቅር ሆነበትና ቢችልልኝ ሆዴ
ተቃጥዬም ቢሆን ከእቅፍሽ ልደር
አትከልክይኝ ዉዴ
ህልሜ አንቺን ማቀፍ ነው
ሞቼም ቢሆን ነይ ልሳምሽ አንዴ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
💗❤️ወድሀለው💗❤️

- ወደኔ ተራምደህ ቆመህ ካጠገቤ

- ድንገት አይኔ አይቶህ ሲደነግጥ ልቤ

- ሀሳቤን ሰብስቤ ከጎንህ እንዳለው

- ለመናገር ሀቁን አይንህን እያየው

- ውስጤን አሳወኩህ ብዬ ወድሀለው።
         :
         :
🎈 ሴቶች ለምትወዱት ወንድ ላኩለት
  
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️
@BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
💗❤️ወድሻለው💗❤️

- ወደኔ ተራምደሽ ቆመሽ ካጠገቤ

- ድንገት አይኔ አይቶሽ ሲደነግጥ ልቤ

- ሻል እንዳለኝ ወዲያው ከጎንሽ እንዳለው

- ለመናገር ሀቁን አይንሽን እያየው

- ውስጤን አሳወኩሽ ብዬ ወድሻለው።
         :
         :
🎈 ወንዶች ለምትወዷት ሴት ላኩላት

  📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
▪️▪️የውሸት ብርሀን🔸🔸

ዙሪያክ ገደል ቢሆን መሄጃው መንገዱ

ያመንካቸው ሰዎች አንተኑ ቢከዱ

ተንዶ ቢከስም የነበረክ ተስፋ

ያካበትከው ሀብትህ በሙሉ ቢጠፋ

አዝነህ እየተከፋ

ድቅድቁ ጨለማ ዙሪያህን ሲከበው

መውጫ ቀዳዳህን ጨንቆህ ስትፈልገው

ድንገት ምታያቸው

ብርሀኖች ሁሉ

እንዳያታልሉክ ተስፋ እየመሰሉ: :

ምክኒያቱም

ካላየኸው በቀር በጥሩ እይታ

የጅቦችም አይን ያበራል በማታ::


  📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
🤫🤫ዝምታ🤐🤐

🚫🧠ካላዋቂ ወሬ

🚫💶ከሌለበት ፍሬ፣

🚫🕐ጊዜን ከሚገድለው፣

🚫📚እውቀት ከማይሰጠው፣

🤥🗣ከውሸት ጋጋታ፣

👍🤐 ይበልጣል ዝምታ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤
ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤

የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤
መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤

ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤
ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤

ይድረስልኝ ላንቺ.........

ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤
ምን ፅልመት ቢከብሽ፤

ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤
አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል።
.............................................

በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
ስማኝ ወዳጄ

ሲያንቋሽሹህ--- አርገው አሳሳች

ሲያስቀምጡህ---- ከሰው በታች

ፊት ሲነሱህ---- ስታያቸው

ሲያጣጥሉህ---- በቃላቸው

በዝምታ ንቀህ አልፈህ

በፈገግታህ ግረፋቸው::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ስሚኝ እህቴ

ሲያንቋሽሹሽ---- አርገው አሳሳች

ሲያስቀምጡሽ-----ከሰው በታች

ፊት ሲነሱሽ----- ስታዪአቸው

ሲያጣጥሉሽ----- በቃላቸው

በዝምታ ንቀሽ አልፈሽ

በፈገግታሽ ግረፊያቸው::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
የማይጨንቀው ሲጨንቅ...
(በሳሙኤል አለሙ
.
በኩለ ቀንን አይባል
በኩለ ሌሊቱ አይባል
ሀብታም የውስኪ ፅዋውን ሲያጋጭ
ድሃ የቋጠረውን ዕንባውን ሲራጭ
"ተፈፀመ" ተብሎ ታይቶ ለሚጠፋው
ያፈጣል ከኩርሲው
ያፈጣል ከሶፋው
.
አንተስ ላይባሉት...
በኖረበት ሲያዝን
በኖረበት ሲደሰት መልሶ መላልሶ
ድራማው ህይወቱን አይቶ ጨርሶ
በድራማው ዓይኑ ቀልቶ ዓይኑን ያሻል
ይቀጥላልን ሲጠባበቅ ውሎ ያመሻል
።።።።።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@getem
@getem
ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤
ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤

የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤
መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤

ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤
ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤

ይድረስልኝ ላንቺ.........

ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤
ምን ፅልመት ቢከብሽ፤

ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤
አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል።
.............................................

በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.     👄አፍና ልብ❤️

🙅‍♂ አፌን አትመኝው አንዳንዴ ይዋሻል

🤥 በመግደርደር ብዛት እውነትን ያሸሻል

❤️ ልቤ ግን ሞኝ ነው ትንሽ ብትቀርቢው

            ሁሉም ይታይሻል

💓ከሌላ አብልጦ አንቺን እንደሚወድ

         በደንብ ይነግርሻል።❤️‍🔥

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ወሰን አልባው ደግነሽ
ለካ ልክ ኖሯል ሞኝነሽ
የዛሬ መሳዩ አዋቂ
መነሻ ነጥቡን ናቂ
ገፁ ሲታይ ጥበበኛ
ለራሱ ከራሱ ጠበኛ

By @Yidne567

@getem
@getem
@getem
2024/05/15 15:46:31
Back to Top
HTML Embed Code: