Telegram Web Link
🙈ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር😂
══════◄✣••✥••✣►══════
ወደ መልሱ እንሂድ እና ብዙ ጊዜ ሙስሊም ወገኖቻችን ለቅጥፈታቸው እንደመረጃ አድርገው ከሚያቀርቡት የሞኝ ፍልስፍና አንዱ ይህ ነው።
ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነው በማለት ብዙ ግዜ ሲናገሩ ይደመጣሉ።ነገር ግን እስልምና የተመሰረተው የዛሬ 1400 በአረብ ሰው ነው።እሱ ራሱ በቁርአኑ ላይ እኔ የእስልምና መስራች ነኝ ብሎል።ሱረት አል አንዓም 6፥14 ሱረት አል አንዓም 6፥163 ሱረት አል ዘሙር 39፥12 የመጀመርያ ሙስሊም እንድሆን ታዘዝኩ

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👉ስለዚህ በዚህ የቁርአን ማስረጃዎች የእስልምና መስራችና ጀማሪ መሀመድ የአረብ ሰው የግመል እረኛ ኢቢን አሚና ነው።ስለዚ መሀመድ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት እስልምና የሚባል ታሪክ የለም ይሄ ፍልስፍናቸው ፉርሽ ይሆናል።
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
እኛ ግን መልሳችን ሰው ሲወለድ ሙስሊም አይደለም።አንድ ሰው ሙስሊም የሚባለው አላህን አምላክ መሀመድን ነብይ ብሎ ካመነና ከተቀበለ በኋላ ነው ይህን ያላደረገ ማንኛውም ሰው ሙስሊም አይባልም።ሰው ሙስሊም የሚባለው ባለመጠመቁ ከሆነማ እኮ በአለም ላይ ሳይጠመቁ የየራሳቸው የእምነት ድርጅት መስርተው የሚኖሩ ብዙ አሉ።ለምሳሌ ያህል በህንድና በቻይና ሀገር ያሉ ሰዎችን መመልከት ብቻ በቂ ነው።
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
🤷ታድያ ስላልተጠመቁ ብቻ ሙስሊም የሚያስብላቸው ከሆነእነዚህ ህዝቦች ሙስሊሞች ናቸውንአይደሉም ለምን ይዋሻል
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
💒በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤላውያን ጥምቀት በ40 እና በ80 ቀናቸው አልነበራቸውም ግን እስራኤላውያን ሙስሊሞች ነበሩንአልነበሩም❗️
ታድያ ለምን ሙስሊም ወገኖቻችን ይዋሻሉ

══════◄✣••✥••✣►══════
👉እስራኤል ከአህዛብ የሚለዩበት በዘመነ ብሉይ ግዝረት ነበራቸው። የአብርሃም ልጆች ለመሆናቸው በተወለዱ በስምንተኛው ቀን ይገረዙ ነበር።ያ ግዝረት ደግሞ በሐዲስ ኪዳን በጥምቀት ተተክቷል።ክርስቶስ ተጠምቆ እኛንም እንድንጠመቅ አዝዞናል።ማር 16፥16
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
🖕ከአብርሃም በተቀበሉበት ሥርአት መሰረት እስራኤላውያን በመገረዝ እራሳቸውን ከአህዛብነት ለይተው የአብርሃም የጽድቅ ልጆች የተስፋው ወራሾች ተብለው እንደተጠሩት ሁሉ
እኛም ዛሬ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን የተጠራን በሙሉ የክርስቶስ ለመሆናችንና ፍፁም ድህነት አግንተን የመንግስቱ ወራሾች ለመሆን እንጠመቃለን እንጂ ገና ክርስትናን በጥምቀት ለመጀመር አይደለም። የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ነው።የሙስሊም ልጅም ሙስሊም ነው።

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👉አንድ ሙስሊም ከርስቲያን ለመሆን አብርሃም እራሱን ለእግዚአብሔር ከለየ በኋላ እንደተገረዘ ሁሉ እርሱም ለክርስቶስ ለመሆኑ ማህተሙ ጥምቀት ነው።መጠመቅ ያስፈልገዋል ሳይጠመቅ ድህነት ሊያገኝ የመንግሥቱ ወራሽ ሊሆን አይችልም።
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
👌ስለዚህ ሰው የሚጠመቀው ክርስቲያን ለመሆን ሳይሆን ለመዳን ነው የመዳን መንገድ አንዱ ክርስተቶስ ኢየሱስ የባህርይ አምላክ እንደሆነ አምኖ መጠመቅ ነው።መጠመቅ በራሱ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን መመስከር ነው።ይህን ለመመስከር ደግሞ የግድ መጠመቅ ያስፈልጋል። አንድ አምላክ በሆነው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ማቴ 28፥19
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
በመጨረሻም ተራ ተረት ተረት ወደሆነው ወደ ሙስሊም ወገኖቻችን ሀሳብ ስንሄድ እንኳን ሰው ሲወለድ ሙስሊም መሆን አይደለም ሰው ሲፈጠር የተፈጠረው ከተጠመቀ ዐፈር ነው።እንዲሁም የእግዚአብሔር መንፈስ ሰፎ ከነበረበት ውሃም ጭምር።ምክንያቱም መጽሐፍ እንዲህ ይላልናበመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።ዘፍ 1÷1
••●◉ ✞ ◉●••
👍ስለዚህ የሙስሊሞች ተረት ተረት ምንም ከተረትነትና ከሞኝነት ፍልስፍና ያለፈ ነገር ቁምነገር የለውም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
ሰው የዳነው እንዴት ነው
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
መዳናችን (ድኅነታችን) የተገኘው በእኛ ሥራ መልካምነት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋገረው እርሱን የሚያስደስትና እንዲያ እንዲያደርግለት የሚያበቃው የተቀደሰ ሕይወት ስለነበረው አይደለም፡፡ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ሰው የዳነው በእግዚአብሔር ቸርነት (ጸጋ) ነው፡፡ የሰው ድኅነት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ስጦታና ለሰው ያለው የማይለወጥ ፍቅር ውጤትና መገለጫ ነው፡፡ የእኛን የቀደመ ሁኔታና እግዚአብሔር እንዴት እንዳዳነን ሐዋርያው ግልጽ በሆነ ሁኔታ እንዲህ ሲል ያስተምረናልእኛ ሁላችን ደግሞ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፣ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን፡፡ እንደ ሌሎችም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጸጋ ስለሆነ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን፣ በጸጋ ድናችኋልና፡፡ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፡፡ኤፌ 2፥3-8

👉ሰው ሁሉ በአዳም በደል ምክንያት “የቁጣ ልጅ” ነበር፤ ሁሉም በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነበር፡፡ሮሜ 8፥10 አሁንም ይኸው ሐዋርያ ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገር ለደቀ መዝሙሩ ለቲቶ በላከው መልእክቱ እንዲህ አለእኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፤ የምንስት፤ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፣ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፤ የምንጣላ፤ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን፡፡ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው ጥምቀትና በመንፈስ መታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም፡፡ቲቶ 3፥3-5

ጌታችንና መድኃኒታችንም እግዚአብሔር ሰውን የወደደውና ያዳነው እንዲሁ በአባታዊ ፍቅሩ መሆኑን ሲገልጽ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን (ሰውን) እንዲሁ ወዷልና አለ፡፡ ዮሐ. 3:16

👌የወደደን እንዲሁ በቸርነቱ እንጂ እንዲወደን የሚያደርግ መልካም ሥራ ስለነበረን ወይም እኛ ስለ ወደድነው አይደለም፡፡ ሰውማ በራሱ ጥፋት ከአምላኩ ፊት የኮበለለ ነበር፡፡ ጌታችን በጠፋው በግ ምሳሌ እንደ ተናገረው የጠፋውን አዳምን “የሰውን ልጅ በሙሉ” ይፈልገውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ከሉዐላዊ መንበሩ ወርዶ ፈለገው፤ ባገኘውም ጊዜ ለመፈለግ በደከመው ድካም ሳይቆጣው፣ ሳይገርፈው፣ በእግርህ ሂድ ሳይለው በማግኘቱ ተደስቶ በጫንቃው ላይ ተሸከመው፡፡ በጠፋው ልጅ ምሳሌ እንደ ተናገረው ያጠፋውን ጥፋትና የበደለውን በደል ሳያሰብ አዘነለት፣ በፍጹም ፍቅር ተቀበለው፣ የሰባውን በማረድ (የራሱን ቅዱስ ሥጋውን በመቁረስና ክቡር ደሙን በማፍሰስ) በዓል አደረገለት፡፡ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኗል፣ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷልም፤ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል አለ፡፡ ሉቃ 15፥11-32

ቅዱስ ጳውሎስም ይህንኑ ሲገልጽ፡- እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፣ በፊት የተለያችሁትን፣ ክፉ ሥራንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞት በኩል አስታረቃችሁ አለ፡፡ ቆላ 1፥21-22 ይህን ሁሉ አጠቃልሎ ወሶበ እንዘ ጸሩ ንሕነ ለእግዚአብሔር ተሣሃለነ በሞተ ወልዱ - እግዚአብሔር ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት ታረቀን አለ፡፡ ሮሜ 5፥10

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፦እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፣ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ በማለት የዳንነው ክርስቶስ በቸርነቱ በተቀበለው ሕማምና መከራ መሆኑን ይነግረናል፡፡ 1 ጴጥ 2፥24

ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም እንዲህ ይላል፡-በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፤ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና፡፡ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተሥረይ ይሆን ዘንድ ልጁን አንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፡፡1ዮሐ 4፥9-10
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
የወደቀውንና የሞተውን የሰው ልጅ ያዳነው የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ የእርሱ ሥራ አይደለም፡፡ ሰው በሥራው ብቻ የሚጸድቅ ቢሆን ኖሮ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ደጋግ አባቶች ለመዳን ክርስቶስ ባላስፈለጋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳ በደጋግ ሥራቸው በኃጥአን ላይ የሚደርሰው መከራ ሙሉ በሙሉ ባይደርስባቸውም ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ በአዳም በደል ምክንያት የተዘጋችውን ገነት እስኪከፍታት ድረስ ከሲኦል መውጣትና ወደ ገነት መግባት አልቻሉም፡፡ በኃጢአት ምክንያት ከመጣው ፍዳ አንዷንም ፈቀቅ ማድረግ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ እኛን ያዳነን የክርስቶስ ቸርነት እንጂ ሥራችን አይደለም ማለት ነው፡፡ እንደ ሥራችንማ ቢሆን እግዚአብሔር ሰው ኾኖ ኃጥአን ለሆንነው ለእኛ መከራ ይቀበል ዘንድ የሚያበቃው የትኛው ሥራችን ነበር በእኛ ሥራ ቢሆንማ ኖሮ እንኳን ይህ ሁሉ ቸርነት ሊደረግልን ቀርቶ ከተደረገልን ቸርነት አንዷንም እንኳን ባላገኘን ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ በዋጋ የሚገዛ አይደለም፡፡

በኃጢአት ድካም ሳለን በቸርነቱ የወደደንና ያዳነን መሆኑን በማድነቅ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡-ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና፡፡ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡ሮሜ 5፥6-9
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ እንደ ገለጸው እኛ ጻድቃን ሆነን ክርስቶስ ቢሞትልን ኖሮ ምናልባት ብዙም ላይደንቅ ይችል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ለጻድቅ ሰው ተላልፎ የሚሞት ምናልባት ይገኝ ይሆናልና ነው፡፡ ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍጹም ፍቅርና የቸርነቱን ገናናነት ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ ለሞት የሚያበቃ ወንጀል ሠርቶ ሞት ለተፈረደበት ኃጢአተኛ ሰው “እኔ እሞትለታለሁ” ብሎ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ማን ነው ክርስቶስ ለእኛ ያደረገው ይህንን ነው፤ በኃጢአታችን ሞት የተፈረደብን “የሞት ሰዎች” ሳለን በፍጹም ፍቅሩ ስለ እኛ ራሱን ቤዛ አድርጎ ሰጠ፣ ሞተልን፤ በሞቱም ከሞት አዳነን፣ ሕይወትን ሰጠን፡፡ ይህ የእርሱ የጸጋ ስጦታ ብቻ ነው፡፡ ኢሳ 53፥4-6
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
💁ኢየሱስ ጌታ ነው❗️የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም!
••●◉ ✞ ◉●••
💁የዛሬ 2000 ዓመት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ እጅ መንሻ ይዛ ለተገኘች፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕፃንነቱ ሲሰደድ ለተቀበለች፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባረገ በዓመቱ በጃንደረባዋ በኩል በስሙ ለተጠመቀች፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁ከማንም በፊት ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን እምነት በንጉሥዋ በኢዛና በኩል በይፋ ለገለጠች፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁በዓለም ጥንታዊዉን በእጅ የተጻፈ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል በአባ ገሪማ ገዳም ለያዘች፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁በዓመት ከ1825 ጊዜ በላይ የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዲነበብ ሥርዓት ለሠራች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፡-ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም።ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል ሆኖ ነው እንጅ ነገሩ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
📖ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ...ዕብ ፭:
💒💒💒💒💒💒
ተወዳጆቸ እኔ ይሔን ጥያቄ በተመለከትኩ ጊዜ ፪ ጥያቄዎች ወደ ውስጤ ዘልቀው ገቡ።
••●◉ ✞ ◉●••
፩ኛ አኛ ኦርቶዶክሳውያን መፅሐፍ ቅዱስ የማንበብ ልማዳችን የት ድረስ ነው
፪ኛ አህዛብ፣በስህተት ጎዳና የሚገኙት ፕሮቴስታንት እህት ወንድሞቻችን ከንፍስና ሰከንዶች በፈጠኑበት ቅዱስን መፅሐፍ ባይረዱትም ቀን ከሌት በሚያነቡበት በዚህች ሰዓት የቤተ ክርስቲያኒቱ የቁርጥ ቀን ልጆች የት ነን 🤷
••●◉ ✞ ◉●••
🙏#እግዚአብሔር ጠላት በአማናዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ያጠላውን ክፍ የስንፍና መንፈስ በበረታው ክንዱ ይስበርልን።ለማንኛውም ወደ #አብዱራሐም ጥያቄ እንመለስ
══════◄✣••✥••✣►══════
📖እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ዕብ ፭÷፯
══════◄✣••✥••✣►══════
ይህ ጥቅስ በማያሻማ መንገድ የገለጸው ነገረ ሥጋዌ ነው:: ይኸውም ጌታችን ፍጹም አምላክ ቢሆንም ፍጹም ሰውም ነውና በሥጋው ወራት ከኃጢአት በቀር በሰው ያለውን ልማድ ሁሉ በሥጋዌ የፈጸመ ነው:: ለአብነትም እንደበላ እንደተኛ ለሞተ ሰው እንዳለቀሰ ተጽፏል::በለበሰውም ሥጋ ዳግማዊ አዳም ተብሎአል::
••●◉ ✞ ◉●••
📖ኢየሱስም...ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።ማቴ 8÷፳፪
••●◉ ✞ ◉●••
📖ኢየሱስም...በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።ማቴ ፳፮÷፳
••●◉ ✞ ◉●••
📖ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።ዮሐ ፲፩÷፴፭
••●◉ ✞ ◉●••
📖እንዲሁ ደግሞ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።1ቆሮ ፲፭÷፵፭
••●◉ ✞ ◉●••
📖ተንበርክኮም። አባት ሆይ፥ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።ሉቃ ፳፪÷፴፱-፵፮

••●◉ ✞ ◉●••
🗣ጌታችን ሊቀ ካህናት ተብሎ ነበርና በሥጋው ወራት እንደ ካህናተ ኦሪት የበግና የፍየል ደም ያቀረበ አይደለም:: ይልቁንም ጸሎትን እንደላም ልመናንም እንደ በግ አድርጎ አቀረበ:: አንድ ጊዜም ስለሆነ ያቀረበው ግዳጅ የሚፈጽም መሆኑን ሲያጠይቅ በፍጹም ኃዘንና በእንባ አቀረበ አለ:: ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ሲልም ሰው ሁሉ በአንዱ አዳም እንደ ሞተና በጌታም ቤዛነት እንደ ዳነ ስለ ምእመናን በጌታችን መናገሩ ነው::
••●◉ ✞ ◉●••
እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት የሚለው ወልድ በኩር ሆኖ ሳለ አምላክነት ገንዘቡ ሆኖ ሳለ ፍጹም ሰው በመሆኑ ስለ አዳም ያቀረበው ቁርጥ ልመናው ተሰማለት አምላክ ነኝ ልጸልይ አይገባኝም ሳይል ሰው በመሆኑ ታዟልና:: ስለ መታዘዙም እግዚአብሔርን ስለ መፍራቱም ቢል አንድ ነው በአዳም ተገብቶ ነው እንጂ ጌታችን ከመከራ መስቀል በኃላ የሚያማልድ ሆኖ አይደለም::
••●◉ ✞ ◉●••
ሁሉን ነገር ያደረገው እኛ በብርቱ ጩኸት ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን በእግዚአብሔር ፊት እንድናቀርብ ለአብነት ነው:: እግዚአብሔርን በመፍራት የምንጮኽው ጩኸት እንደሚሰማልን አርእያነቱን የሚያሳይ ቃል ነው::
••●◉ ✞ ◉●••
መልካም ዕለተ ሰንበት
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🗣🗣የትኘዋ ናት ሰንበት
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
📖ስድስት ቀን ስራ፣ተግባርህም ሁሉ አድርግ በሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፡፡እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን አርፏልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ዘፀ 20÷10-11
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው
••●◉ ✞ ◉●••
👉ሰንበት ማለት አቆመ፣አረፈ ማለት ነው፡፡ይህ ቀን የጌታ ዕረፍት የተባረከም ቀን ነው፡፡ከማንኛውም ሥጋዊ ሥራ ተቆጥበን የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስብበት ቀን ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሰው እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ የሰንበት ቀንም የተፈጠረው ለዚህ ነው፡፡ዘዳ 5÷14)፣ማር 2÷38።ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለእረፍት የተቀደሰው የተባረከው ዕለት ሰንበት ብቻ ነው፡፡ ስለሌሎች ቀናት የተነገረው ያ መልካም እንደሆነ አየ የተባለው ብቻ ነው፡፡ሰንበትን ግን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ዘፍ 1÷12፣ 18፡20፣25፡31
••●◉ ✞ ◉●••
🗣በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያን ሁለት ሰንበት አለዉ።ቀዳሚት ሰንበት
(ቅዳሜ) እና ሰንበተ ክርስቲያን(እሑድ
)
••●◉ ✞ ◉●••
👉ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) ጌታ ያረፈባት ለእስራኤል ዘሥጋ የታዘዘው ሰንበት ነው፡፡ይህ ቀን እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አምላክ ከግብፅ ባርነት ወደ እረፍት እንዳወጣቸው ያመለክታል፡፡ዘዳ 5÷2-16 በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ዘጸ 3÷17፣ሕዝ 20÷12፣ዘኁ 15÷32-36 ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር።ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተወቅሰዋል፡፡ማቴ 12፡14፣ሉቃ 4፡16
••●◉ ✞ ◉●••
👉በዘመነ ሐዲስ የክርስቲያኖች የቀዳሚት ሰንበት አከባበር እንደ አይሁድ ለሰው የሚከብድ እንዳይሆን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 ላይ ተገልጿል፡፡
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
••●◉ ✞ ◉●••
👉እሑድ ማለት አሐደ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን በመባል ትታወቃለች፡፡ዮሐንስም በራዕዩ የጌታ ቀን ያላት ናት።ራእይ 1፥10) ፡፡ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ዕለተ እግዚአብሔር የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች
••●◉ ✞ ◉●••
💁እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
••●◉ ✞ ◉●••
💁ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
••●◉ ✞ ◉●••
💁የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያኙባት ዕለት
••●◉ ✞ ◉●••
💁ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት
ዕለት ናት።1ኛ ቆሮ 16፥1

••●◉ ✞ ◉●••
💁የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (ሐዋ 20፥7)።በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር፡፡ ራዕ 1፥10
••●◉ ✞ ◉●••
💁በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ዕብ 4፥1-10
••●◉ ✞ ◉●••
መልካም ዕለተ ሰንበት
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
ሥራህን ሥራ (በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
══════◄✣••✥••✣►══════
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነዉ። ቢቻለዉ እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ። በእርግጥ ሥራዉን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን ኦንዲጠይቁህ እጅግ ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል።
••●◉ ✞ ◉●••
ጲላጦስ፥ሄሮድስ፥ሀናንያ፥ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በፀና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኽኝን ስራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።

••●◉ ✞ ◉●••
አባ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፩፱፫፪-፩፱፰፪ ዓ.ም
.
══════◄✣••✥••✣►══════
ብቻ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እደርስ ዘንድ ፍቀዱልኝ ፦
🗣ወደ እሳት ጣሉኝ
🗣በመስቀል ላይ ስቀሉኝ
🗣ወደተራቡ አናብስት ወርውሩኝ
🗣ብትፈልጉ ጀርባየን ስበሩት
🗣አጥንቴን ከስክሱት
🗣ሰውነቴ ሁሉ ይድቀቅ
••●◉ ✞ ◉●••
ብቻ ወደኢየሱስ ክርስቶስ እደርስ ዘንድ አትከልክሉኝ - - - ተውኝ - የእግዚአብሔር ስንዴ ልሁን - ስጋየም በአውሬዎች ንክሻ ደቅቆ እንደ ንጹህ ዳቦ በክርስቶስ ፊት ይቅረብልኝ
••●◉ ✞ ◉●••
ቅዱስ ሰማዕት አግናጢዎስ
ከአንጾኪያ ወደሮም ለሰማዕትነት በሚሄድበት ወቅት ለሮማ ክርስቲያኖች ከጻፈው መልዕክቱ
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🔊የክርስትና ስም ለምን ያስፈልጋል
══════◄✣••✥••✣►══════
ጥቂት የማንባል ሰዎች ከነ መሰየሙም የክርስትና ስማችንንም የማናስታውስ ልንኖር እንችላለን🤷
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂የክርስትና ስም አንድ የሚጠመቅ ሰው በሚያጠምቀው ካህን የሚሰጠው ወይም የሚጸድቅለት ስያሜ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ይህንን ስም ቤ/ክ ዝም ብላ ለህጻናቱ የምትለጥፍ የሚመስላቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ በጥምቀት ጊዜ ቤ/ክን ልጆቿን ስትቀበል እንዲሁ አይደለም ተገቢ ስም አውጥታ ከመንፈስ ቅዱስ በጥምቀት ዳግመኛ ወልዳ ቅበዐ ሜሮን ቀብታ የሚንከባከብ የክርስትና አባት እናት ሰይማ በመስቀሉ ቃል አስገብታ ቅዱስ ስጋና ደሙን መግባ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣የክርስትና ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ክርስቲያናዊ ትውፊት አለው፡፡ብዙ ነብያት እና ቅዱሳን ካላቸው መጠሪያ ሰም በተጨማሪ እራሱ አምላካችን አዳዲስ ስም ሲያወጣላቸው እናያለን ለምሳሌ
💁‍♂አብራምን 👉 አብርሃም
💁‍♂ያይቆብን 👉 እስራኤል
💁‍♂ስምዖንንን 👉 ጴጥሮስ
💁‍♂ሳኦልን 👉ጳውሎስ እያለ ሲጠራቸው ለምን በአዲስ ስም መጥራት እንደፈለገ አንዳች ነገር ልንገነዘብ ይገባል፡፡

══════◄✣••✥••✣►══════
👉ዓላማውስ ምንድን ነው
══════◄✣••✥••✣►══════

ቋሚ የቅዱሳን መታሰቢያ እንዲሆን፡-
••●◉ ✞ ◉●••
🗣በኢሳ 56፥5 አምላክ ለቅዱሳን የማይጠፋ ስም እና የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሰጣቸው እናነባለን፡፡ስለዚህ በተለያዩ ቅዱሳን ላይ የነበረውን ፀጋ እና በረከት ለመካፈልና እንዲሁም እንደነሱ የበረታን እንድንሆን በስማቸው እንሰየማለን።የጌታችንንም ስሙን ዘርፍ በማድረግ እንዲሁ እንጠቀምበታለን፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
ለተጠማቂውም በረከት እንዲሆንለት፡-
••●◉ ✞ ◉●••
🗣በምሳ 10፥6 የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ይላል፡፡ ስለዚህ በስማቸው በመሰየም ከላይ እንደገለጽነው መታሰቢያቸውን እና በረከታቸውን ለመካፈል ሲረዳን ይህን ጸጋ ለማግኘት በቅዱሳን ስም በመሰየም የክርስትና ስም ይወጣልናል፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
መጠሪያ ስም ነው፡-
••●◉ ✞ ◉●••
🗣በቀድሞው ስርአት የክርስትና ስም ለሁልጊዜውም መጠሪያ ነበር፡፡ ከግራኝ መሐመድ መነሳት አስቀድሞ የነበሩ ምዕመናን በክርስትና ስማቸው ነበር የሚጠሩት፡፡ነገር ግን መከራው ሲበዛባቸው ከርስታቸው ላለመሰደድ ሲሉ ተለዋጭ ስም በማውጣት መጠቀም ጀመሩ ከዛን ግዜ ጀምሮ ይህ ነገር እየተስፋፋ መጥቶ ከነ ጭራሹ ለመለወጥ በቃ❗️
••●◉ ✞ ◉●••
🔊የማይገባ የክርስትና ስም በአምላክ ስም በቀጥታ መጠራት አይገባም ለምሳሌ አማኑኤል፣ኤልሻዳይ፣ኢየሱስ እነዚህ ስሞች ለሠው ልጆች መጠናችን ስላልሆኑ መጠቀም የለብንም፡፡ በዚህ ምትክ ገብረ አምላክ፣ሣህለ ሥላሴ፣ፍቅርተ ክርስቶስ ፣ዘአማኑኤል በማለት መሰየም ይቻላል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
በቅዱሳንም ስም በቀጥታም ሆነ ዘርፍ እየተደረለት መሰየም ይቻላል፡፡ለምሳሌ፡- ዘማርያም፣ዘሚካኤል፣አጸደ ማርያም፣ ተክለ ሐይማኖት ወዘተ...
••●◉ ✞ ◉●••
ስለዚህ ስርአቱን በመጠቀም ከሚገኘው በረከት ተሳታፊዎች እንድንሆን አምላክ ይርዳን🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
Forwarded from Deleted Account
ከፕሮቴስታንቶች የተጠየቁን ጥያቄዎች እንደሚከተሉት ኣቀርባለው
1 ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ኣይደለም የጌቶች ጌታ ነው ብሎ የሰበከው ሐዋርያ ማን ነው?
2 ለምን ከሌሎች ጌቶች ጋር የእየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ታወዳድራላችሁ?
ኣመሰግናለው
💁ከከፍታ ማውረድ ለምን ይሆን 🤷
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ተወደጆቸ ኢየሱስ ብሎ መጥራት እውቀት የሚመስላቸው ነገር ግን ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ መጥራት ደግሞ ስህተት መስሎ የሚሰማቸውን ሰዎችን ምን ትሏቸዋላችሁኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ፣ የነገስታት ሁሉ ንጉስ ፣ የጌቶች ሁሉ ጌታ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስታስተምር የኖረችና የምትኖር ናት።
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም ከስሞች ሁሉ የሚበልጥ የተወደደ ስም ነው፥ የተወደደ አምላክ ጌታችን መድሃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በምድር የሚኖሩትን ፍጥረታት በጥበቡ የፈጠረ ነው ፤ እርሱ ለአብርሃም የተገለጠ ፣ ለሙሴ ህግን የሰጠ ፣ ቀይ ባህርን የከፈለ ፣ ዮርዳኖስን ያሻገረ ፣ ወደ ምድር የወረደ ፣ ወደ ሰማይም የወጣ ፣ ለመፍረድም የሚመጣ እርሱ ነው ፣ በእርሱ የሚያፍር ከሰይጣን በቀር ማንም የለም ፤ይህንንም ማንም ሳይሆን ተዋህዶ እናታችን አስተማረችን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ተወዳጆቸ ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ብቻ ከማለት ስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስላለችው ነውን ይሔ ሁሉ ጫጫታ ወይንስ አርዮሳዊ እንዲያፍር እግዚአብሄር ወልድ ቃል አምላክ ብላ ስለጠራችው ነውን ወይንስ አህዛብ እንዲያፍሩ ለሚጠራጠሩም ምስክር እንዲሆን ከሶስቱ አካል አንድ አካል አካላዊ ቃል መድህን አለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስላለችው ነውን ወይንስ ኢየሱስ ጌታ ነው ከማለት ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ የአማልክት አምላክ ስላለችው ነውን ወይንስ ኢየሱስ ማለት መድሃኒት ማለት እንደሆነ ይህም ስም በእስራኤላውያን ዘንድ የተለመደ እንደሆነ ክርስቶስ ማለት ግን መሲህ ይህም አንድ ብቻ እንደሆነ የእግዚአብሄር ልጅ አንድ እንደሆነ የሚገልፅ መሆኑን የሚያመለክት እንደመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንል መድሃኒት የሆነው መሲህ ፣ ስለ ሰወች ልጆች ሃጢአት የሞተው ትሁት ፣ ወደሰማያት ያረገው ገዥ ፣ ለመፍረድ የሚመጣ ፈራጅ እርሱ አንድ እንደሆነ እንደሚናገር እንዴት ረሱት ወይንስ ኢየሱስ ጌታ ነው ሲባል በአለም ብዙ ጌቶች እንዳሉ ስናውቅ ፣ ተዋህዶ ግን ይህን ሲባል ለመግለፅ የፈለግነው አንዱን ክርስቶስን እንደሆነ ለማጠየቅ የጌቶች ጌታ (የሁሉም ጌታ) ማለቷ ይህ ከዚያኛው አይበልጥምንወይንስ ማንን ደስ እንዲለው ነው የጌቶች ጌታ የሚል ጥቅስ ንገሩን የሚሉት🤷ችግር የለውም እንነግራችኋለን።
••●◉ ✞ ◉●••
🙊እኛስ ራሳቸውን ከፍ ከፍ እንደሚያደርጉ ፃፎችና ፈሪሳውያን የተወደደውን የአምላካችንን ስም እንደ ተራ ሰው ስም አድርገን አንጠራም።ተወዳጆች ሆይ እስኪ መልሱልኝ፦አንድን ንጉስ ንጉስ ከተባለ በኋላ ለንግስናው የተሰጠውን ማእረግ ሽራችሁ በስሙ ብቻ ካልጠራሁ ይባላልንይህንስ ካላላችሁ የነገስታት ንጉስ የሆነውን እንዴት ናቃችሁትወይንስ እናንተ ራሳችሁን መንፈሳዊ የምታደርጉ ለመንፈሳዊ አባቶቻችሁ የሰጣችሁትን ማእረግ ለአምላክ ትሽሩታላችሁን🤷
••●◉ ✞ ◉●••
ጥቅስ ጠቅሰህ የጌቶች ጌታ ያለ ሀዋሪያ ተናገር ስላላችሁ ቅዱስ ቃሉን የምትሸከሙበት ንፅህና ይዛችሁ ከቀረባችሁ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ አነሆ
••●◉ ✞ ◉●••
📖ብቻውን የሆነ ገዚ የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ 1ኛ ጢሞ6፥15
📖የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ የሚል ስም አለው ራዕ 19፥16
📖በጉም የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ ስለሆነ እርሱም ድል ይነሳል ራዕ 17፥14
📖ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ ነው-ዘዳ10፥16
📖ፈጥሮ የሚገዛን ጌታችን አማላካችን አንድ ጌታ ነው-ማር12፥29
📖ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፥ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባሀል እያሉ፥በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።ራይ 4፥10-11
📖ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።ዮሐ 1፥4
📖ቶማስ ጌታዬ አማላኬም ብሎ መለሰለት ዮሐ 20፥28
💁‍መንግስቱን እንዲያወርሰን በመናፈቅም ጌታችን ሆይ ና እንላለን 1ኛ ቆሮ16፤22።
💁‍በመላክትና በእኛ በሰዎች ዘውትር በቅዳሴ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብርክ ተሞልታለች እየተባለ ይሞገሳል ኢሳ6፤3፡፡

••●◉ ✞ ◉●••
🗣ቤተክርስቲያን......
ቅዳሴዋ ተጀምሮ እስኪፈጸም ለስሙ ጥልቅ የሆነ ክብር እና አምልኮ የትሰጥ ናት!እንግዲህ ይህችን ቤተክርስትያን የተሰቀለውን ክርስቶስን አትሰብክም ፣ኢየሱስ የሚለውን ስም አትጠረውም ለማለት ለምን ደፈሩያላመኑትን ቤተ አህዛብን እና ቤተ አይሁድን ለመውቀስ የተጻፈውን ለቤተክርስትያን ሰጥተው ለመናገርስ ለምን ደፈሩአዎን ነገሩ እንዲህ ነው
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍አጽራረ ቅዱሳን የሆኑት መናፍቃን ከቅዱሳን ጋር ያለንን ሕብረት ለማቋረጥ ያለው ብቸኛ አማራጭ
💁‍ስለቅዱሳን ሲወራ የክርስቶስ ስም ተሸፈነ ማለት፣
💁‍የክርስቶስ ስም አትጠራም በማለት ለስሙ የሚገባውን ተገቢ ክብር ማስቀረት
💁‍የኦርቶዶክሳዊ ትውፊትዊ አጠራርን ማጥፋትና ከመናፍቃኑ ጋር ማመሳሰል ቀስ በቅስም መቀላቀል እውነተኛውን ትምህርት መበረዝ፣
💁‍መጪው ትውልድ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊነቱን እንዲረሳ ማድረግና ግራ እንዲጋባ ከዚያም እውነታውን ፈልጎ እንዲያጣ ማድረግ

••●◉ ✞ ◉●••
🗣ፍጹም አምላክ ሲሆን ፍጹም ሰው በተዋህዶ የሆነውን አንዱን ክርስቶስን ለሁለት ከሚከፍሉት ከካቶሊካዊያን ጀምሮ ከክብሩ ዝቅ አርገው ዛሬም የምልጃን ስራ ይሰራል እስከሚሉት ፕሮቴስታንታዊያን ድረስ በክርስቶስ ጉዳይ ይህችን ክብሩን አሳምራ የምታውቀውን ቤተክርስትያን ሊወቅሳት የሚችል አንድስ እንኳን የለም።
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ደግሞ ጌትነቱን ለምን ታነፃፅራላችሁ ይሉናል እንዴ😂የምናነፃፀረው እኮ ጌትነቱን የምትገልፁበት መጠን ሰማይና ምድርን ያለ መሰረት ላቆመ የማይመጥን ሰለሆነብን እንዲያው መማሪያ ቢሆናችሁ ብለን ነዉ እኮ ነው አትፍረዱብን።ቤተ ክርስቲያንማ ጌትነቱን ዳግም እንደናንተ ላይወረድ ሰቅለዋለች። ጥቅስ መዘን የምንወስድ ከሆነ ሳራም ባለቤቷን አብርሃምን ጌታዬ ብለዋለች።ሳራ ባሏን ጌታ ካለችው ቃሉን ቀጥታ የምንወስድ ከሆነ ከፈጣሪ የጌትነት ትንታኔ ለይቶ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
ፈጣሪ የተጠራባቸውን ስሞችን ድግግሞሽ በመፅሀፍ ቅዱስ ያውቃሉ
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂እግዚአብሔር የሚለው ፩ሺ፯፬ (1074)
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ጌታ የሚለው ፮፻፶፮(646) ጊዜ፣
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂አምላክ የሚለው ፺፩(91) ጊዜ፣
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ወልድ ወይም ልጅ ወይም የሰው ልጅ የሚለው ፻፲፬(114) ጊዜ፣
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ኢየሱስ የሚለው ፮፻፱ (609) ጊዜ፣
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ክርስቶስ የሚለው ፪፻፴፬ (234) ጊዜ፣
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ፫፻፱ (309) ጊዜ፣
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ጌታ ኢየሱስየሚለው ፱(9) ጊዜ እና
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚለው ደግሞ ፲ (10) ጊዜ መጻፉን እንረዳለን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ከዚህ በተጨማሪ አማኑኤል የሚለው ስሙ በወንጌል አንድ ጊዜ የተጠቀሰ ሲኾን በትንቢተ ኢሳይያስ ደግሞ ሁለት ጊዜ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
ለዘተወልደ እምቅድስት
ሊቀ መዘመራን ይልማ ሐይሉ
ኦ ዘ መንክር ልደተ አምላክ እማርያም እምቅድስት ድንግል። አግመረቶ ለቃል ኢቀደሞ ዘርዕ ለልደቱ ወኢአማሰነ በልደቱ ድንግልናሃ። እምኀበ አብ ወፅአ ቃል ዘእንበለ ድካም ወእምድንግል ተወለደ ዘእንበለ ሕማም ። ሎቱ ሰገዱ ሰብአ ሰገል አምጽኡ ዕጣነ ከመ አምላክ ውእቱ። ወርቀ እስመ ንጉሥ ውእቱ ። ወከርቤ ዘይትወሀብ ለሞቱ ማሕየዊ በእንቲአነ ተወክፈ በፈቃዱ ። አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ኄር ወመፍቀሬ ሰብእ።
••●◉ ✞ ◉●••
ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅቃልን ወሰነችው ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠውም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት ንጉስም ነውና ወርቅ አመጡለት መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው።

••●◉ ✞ ◉●••
ቅዱስ ኤፍሬም
••●◉ ✞ ◉●••
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል
❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🗣እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መዳኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ ተወልዶላችኋልና።ሉቃ 2፥10-11
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።ማቴ 1፥23
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።ኢሳ 9፥6
••●◉ ✞ ◉●••
🗣When He had accomplished the full measure of nine months, the begetter of Adam…(የዘጠኙን ወራት ሙሉ ስፍራ በፈጸመ ጊዜ የአዳም ወላጅ (አስገኚ) የኾነው ርሱ በትክክለኛው ወግ መሠረት ለመወለድ ፈቀደ።
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ወጣቲቱ ርግብ በድንግልናዋ ውስጥ ጋደም አለች ወጣቱን ንስር ታላቁን ንጉሥ በታናሽ ዋሻ ውስጥ ልትወልደው፤ የተወደደችው ጊደር በወጣትነቷ ውስጥ ጋደም አለች። (መዝ 88፥31፤ ኢሳ 7፥21‐22)
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሥርዐተ ሰማይ ከማሁ ተሠርዐ በዲበ ምድር፤ ቤተልሔም ተመሰለት ከመ ሰማይ ህየንተ ፀሓይ ዘየዐርብ ሠረቀ በውስቴታ ፀሓየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘኢየዐርብ ወዘዘልፈ ያበርህ ዲበ ቅዱሳን … (የሰማይ ሥርዐት በምድር ላይ ተሠራ፤ ቤተልሔምም እንደ ሰማይ ተመሰለች፤ በሚጠልቅ ፀሓይም ፈንታ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ኅልፈት ጥልቀት የሌለበት አማናዊ ፀሓይ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጧ ወጣሚልክ 4፥2
••●◉ ✞ ◉●••
📖በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ኾነ። እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንግሥናውንም እጅ መንሻ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት አለቀሰ።
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
••●◉ ✞ ◉●••
📖ተወልደ እምአመቱ ወሰላመ ገብረ በልደቱ፤ ከአገልጋዩ ተወለደ፣ በልደቱም ሰላምን አደረገ።
ቅዱስ ያሬድ
••●◉ ✞ ◉●••
🔊O my beloved, ye God-fearing people, open ye the ears of your hearts,… (የምወድዳችኊ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሕዝቦች ሆይ የልቡናችኹን ዦሮዎች ከፍታችኊ የሴቶችን ኹሉ ንግሥት፣ በርሷም ውስጥ የአብ ልጅ በታላቅ ክብር የኖረ የእውነተኛዋን ሙሽራ የእግዚአብሔርን እናት ክብሯን ስሙ፤ መጥቶ በማሕፀኗ ለዘጠኝ ወራት ኖረ ስለእኛ መዳን በቤተ ልሔም ውስጥ ወለደችው በመናኛ የመታቀፊያ ኩታ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በከብቶች ማደሪያ በረት ውስጥ አኖረችው፤ እንስሳትም ርሱን ተመልክተው ዐውቀውት ተገዙለት (እስትንፋሳቸውን ገበሩለት)። ሉቃ 2፥6-7
💒💒💒💒💒💒
🗣🗣የአምላክን ልጅ ሰው መኾኑን በዓል እናድርግ የተሸከመችውን ማሕፀን እናመስግን፤ ላቀፉት ጉልበቶች እንስገድ፤ ላሳደጉት ጡቶች እንዘምር፤ የዳሰሱትን እጆች እናመስግን፤ ለሳሙት ከንፈሮች እናሸብሽብ፤ ከእረኞች ጋር ምስጋናን እናቅርብ፤ ከሰብአ ሰገልም ጋር እጅ እንንሣ፤ እንደ ዮሴፍ እናድንቅ እንደ ሰሎሜም እናገልግል በተኛበት በረት እንስገድ፤ በተጠቀለለበት በረት እንበርከክ፤ ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና ይኹን በምድርም ሰውን ለወደደ እንበል (ሉቃ 2፥14)፤ እግዚአብሔር ሰው ኾነ የሰው ልጅ ሴት ልጅም የእግዚአብሔር እናት ኾነች፤ ለርሱ ምስጋና ይኹን ለርሷም ስግደት ይገባል
💒💒💒💒💒💒
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ

🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
🕯🕯📖📖🕯🕯
💒💒💒💒💒💒
🗣ተወዳጆች ሆይ ፍቅር ተወልዶልናል
እንኳን አደረሳችሁ ❗️
••●◉ ✞ ◉●••
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🙊ያለመጠን የሚያስገርም ልደት❗️😳
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሕፃን ተወልዶልናል፣ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፣አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ፣ስሙም ድንቅ መካር፣ኃያል አምላክ ፣የዘለዓለም አባት፣የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።ኢሳ ፱፥፮
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እናቱን የፈጠረ ልጅ፤
🗣ፈጣሪዋን የወለደች እናት፤
🗣አባቱ የማይቀድመው ልጅ::

••●◉ ✞ ◉●••
🤷መልክን ከደም ግባት ፣ንፅህናን ከቅድስና አስተባብራ የያዘች እናት ማረፊያ አጥታ እንዴት በበረት ወለደች
🤷አለቅነት በጫንቃው የሆነ ጌታ አንዴት በበረት ተወለደ

••●◉ ✞ ◉●••
🗣አንደበቶች ሁሉ ስለ እርሱ በጐነት የሚያወሩለት ጉልበቶችም ሁሉ የሚንበረከኩለት የሁሉም ጌታ የሁሉም ሀኪም የሁሉም መድሐኒት የሆነው ጌታ የዛሬ 2013 በከብቶች በረት ከንፅህት ድንግል ተወለደልን❗️ይህ የፍቅሩ ጅማሬ ነው።ተወለደ ስንል ተወለድን ማለታችን ነው❗️
••●◉ ✞ ◉●••
በበረት የወደቁ ፣ጊዜ የከዳቸው፣የታሰሩ፣የተፈናቀሉ፣የተሰሳደዱ፣በመንገድና በቤት በችግር ያሉ አሉና እናስባቸው።
••●◉ ✞ ◉●••
በዚህ
ሰጪ ይፀድቅበታል፣ተቀባይ ያመሰግንበታል
ሰጥተን ለመፅደቅ፣ተቀብለን ለማመስገን ያብቃን ።

••●◉ ✞ ◉●••
🗣ተወዳጆች ሆይ ፍቅር ተወልዶልናል
እንኳን አደረሳችሁ ❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
📖ከተራ ምንድን ነው
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
👉ከተራ "ከበበ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🎚በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ-ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን(ዳስ) ይተክላል፡፡ የምንጭ ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል፣ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🎚በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🎚ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ ሲኾን፣ ካህናቱ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌ፣ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
📡የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። ኢያሱ ፫÷፫
••●◉ ✞ ◉●••
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
🕊 እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ 🕊
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
ቅዱስ ዮሐንስ ሌላውን ሰው በአንተ ስም፣ በባሕርይ አባትህ በአብ፣ በባሕርይ ሕይወትህ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለሁ።አንተን ግን በማን ስም /ምን እያልኩ/ አጠምቅሃለሁ አለው።
••●◉ ✞ ◉●••
ጌታችንም ወልዱ ለብሩክ ከሳቴ ብርሃን ተሣሀለነ …፣ እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለን።ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም እነሆ የዓለምን ሀጢአት የምታስወግድ የእግዚአብሔር በግ /መስዋዕቱ/ እያልክ አጥምቀኝ አለው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
📡የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። ኢያሱ ፫÷፫
••●◉ ✞ ◉●••
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
🕊 እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ 🕊
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🔊ተወዳጆቸ እንደምን ሰነበታችሁልኝበተደጋጋሚ በውስጥ መስመር የሚጠየቁ ጥያቄዎች መልስ ለእናንተ ለውድ ቤተሰቦቸ ይድረስልኝ።አሜን
••●◉ ✞ ◉●••
1 ሰው ከመጠመቁ በፊት ሐይማኖቱ ምንድን ነው
2 ሰው ሲፈጠር ሐይማኖቱ ምንድን ነው

💁‍♂ሁላችንም ከመጠመቃችን በፊት ሐይማኖታችን ኦርቶዶክስ ነው።ይህን ያልኩት እንዲሁ በደፈናው አይደለም ምክንያት አለኝ።ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው ትርጉሙ እውነተኛ ፣ ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት ማለት ነው።ተወዳጆቸ ማስረጃ ካላችሁኝ ኤር 6÷16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርስዋም ላይ ሒዱ ለነፍሳችሁም መድሐኒት ታገኛላቹ ይላል

🗣መንገድ ማለት ሐይማኖት ማለት ነው ማስረጃ ማቴ 7÷13 በጠባቢቱ በር ግቡ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር ሰፊ መንገድም አለችና ወደ እርስዋ የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገድዋም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው

🗣ኤርሚያስ የቀደመችውን መንገድ ጠይቁ አለ።በእርስዋ ለይም ተመላለሱ አለ።ክርስቶስም መጣ ወደ ጠበበው ደጅ ግቡ አለ በጠበበው መንገድ ላይ ወደ ሕይወት የሚወስደው እርሱ ነው ግቡ አለ።የጠበበው መንገድ የቱ ነው ብለህ ስትጠይቅ መልሱ ኦ....ር...ቶ...ዶ...ክ...ስ ነው።ጥበቱንም ፆም ፣ ስግደት ፣ ቀኖና ፣ ንስሐ ፣ ስጋ ወደሙን መቀበል ፣ቆሞ ማስቀደስ ፣ ፀበል መጠጣት ፣ መጠመቅ ........ እነዚህ ሁሉ የኦርቶዶክስን ደጅ ያጠቡታል

🗣ሰፊው መንገድስ ካላችሁኝ
እንደመንገዱ ስፋት ማንም የሚገባበትና የሚወጣበት የማይፆምበት፤ የማይሰገድበት የክርስቶስ ወዳጅ የሆኑ ቅዱሳንና ቅዱሳት የማይከበሩበት የክርስቶስ ስጋና ደሙ የማይፈተትበት፣ለአለባበስ፤ለአነጋገር እና ለአምልኮ ስርአት የሌላቸው ማንም ሰው እንደልብ የሚቦርቅበት የሚጨፍርበት። በአጠቃላይ ሉጋም የሌለበት መንገድ ሁሉ ሰፊው መንገድ ነው እላለው።


💁‍♂ኦርቶዶክስ ግን ሉጋም አላት።ይህም በፆም፦ገና ፆም ይገባል ነፍሳችንን እያበረታን ስጋችንን እናደክማለን።ከዚያም ይፈታል። ስጋ ሊበረታ ሲል እንደገና የነነዌ ፆም ይገባል ስጋችንን አድክመን ነፍሳችን እናበረታለን።ይፈታል ስጋ አረፍኩ ሲል አብይ ፆም ይገባና ስጋችን 0 ይሆናል። ነፍሳችን ትበረታለች ስጋ ሲዝል 50 ቀን ይፈልታ።50 ቀን ስጋችን ተደሰትኩ ሲል ሰኔ ፆም ይገልባል።ስጋ ይደክማል እንዲ እንዲያ እያልን ስጋን እያደከምን ነፍሳችንን ወደ ገ....ነ....ት ስለዛ ጠባቧና እውነተኛዋ መንገድ ኦ......ር....ቶ....ዶ...ክ..ስ.....ናት።ከአለም ሕዝብ እኛ ብቻ ልንፀድቅ ነው አላችሁ

🗣አዎና በደንብ ከአለም ሕዝብ እኮ 8 ሰው ብቻ ነው የዳነው።በኖህ መርከብ እኛ ከ 8 አንበልጥም እንዴ በእርስዋ ላይ ቁሙ ብዙ ሰው አይፈልጋትም አለ ክርስቶስ ስማችን ኦርቶዶክስ ነው ክርስቲያን ስማችን አልነበረም ያወጣልን ጠላት ነው።

🗣የሐዋ ሥራ 11÷26 ደቀመዛሙርቱም መጀመሪያ በአንፆኪያ ክርስቲያን ተብለው ተጠሩ" የክርስቶስ ተከታዮች ናቸውና በክርስቶስ አማካኝነት
ክርስቲያን ሲሏቸው እነርሱም "ይህ ስም ተስማምቶናል
አሉ ሞትን አሸንፎ የተነሳው እርሱ ስለሆነ በእርሱ ስም መጠራት ፈለጉ በመጠራታቸውም አላፈሩም።ህዝቡም ለማስታወስ እንዲመቻቸው በክርስቶስ አያያዙና ክርስቲያን አሏቸው።ከዚያም ክርስቲያን መባል መጣ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛቹ የሚባለውም ለዚሁ ነው።

🗣ሥማችን ኦርቶዶክስ ነበር የቀደመችዋ ቀጥተኛዋ መንገድ ይቺ ቀጥተኛ መንገድ ከማን መጣች ኦርቶዶክስ የማን ሐይማኖት ናት ካልችሁኝ ደግሞ ከአዳም ጀምሮ የመጣው ሐይማኖት ኦርቶዶክስ ነው እላለው።እንዴት አትሉኝም

💁‍♂ቆያ ላብራራላችሁ። ይኸውልህ ፦የአዳም ሐይማኖት ተጠምቆ መፈጠር ነው።ማስረጃው ዘፍ 1÷1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ።ምድርም ባዶ ነበረች አትታይም ነበር የተዘጋጀችም አልነበረችም ጨለማም በውሃ ላይ ነበር የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃ ላይ ይንሳፈፍ ነበር ይላል።ከውሃ ውስጥ የብሱ ይገለጥ ብሎ ምድርን ፈጠረ ( አፈርን ) ማለት ነው ከአፈር አዳምን ፈጠረ ከአዳም ሔዋንን ፈጠረ ከሔዋንና ከአዳም እኛ ተፈጠርን ሔዋን ከአዳም አዳም ከአፈር አፈር ከውሀ ያ ውሀ የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት የአዳም አባት አፈር አያቱ ውሃ ያ ውሃ የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት ስለዚያ አዳም በጥንት አያቱ ተጠምቆ የተፈጠረው የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተዘፍቆ ተፈጠረ ።አይደለም አዳምና ሔዋን የሰው ዘር ቀርቶ ሰማይና ምድር ጭምር በውሃ ተጠምቀው ነው የተፈጠሩት የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ።

🗣ምነው ገረማችሁ ልንገራችሁ 2ኛ ጴጥ 3÷5 ምን ይላል መሰላችሁ ነገር ግን እነዚያ ሰዎች ሰማያት ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው እንደሚኖሩ መሬትም በውሃ መካከልና በውሃ እንደተሰራች ሆን ብለው ይክዳሉ በዚያን ጊዜ የነበረው አለም በውሃ ሰጥሞ ጠፉ።በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች ለምን ጠፉ ቢባል ሰማይና ምድር ከውሃ እንደተፈጠሩ ሆን ብለው ይክዳሉ። ስለዚህ ጠፉ በውሃው ጥምቀት ያመኑ ኖህና ቤተሰቦቹ ዳኑ በውሃው ጥምቀት ያላመኑ የኖህ ዘመን ሕዝቦች ጠፉ በውሃው ጥምቀት ያመኑት እስራኤል ዘስጋ ዳኑ በውሃው ጥምቀት ያላመኑት ፈርኦንና ሰራዊቱ ጠፉ።1ኛ ቆሮ 10÷1 መስረጃ ወንድሞቻችን ሆይ አባቶቻችን ደመና እንደጋረዳቸው ሁሉም በባህር መካከል አልፈው እንደሔዱ ልታውቁ እወዳለሁ ሁሉንም ሙሴ በደመናና በባህር አጠመቃቸው

🙆‍♂ስለዚህ አይደለም አዳምና ሔዋን ሰማይና ምድርም የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተጠምቀው ነው የተፈጠሩት።የአዳም ሐይማኖት የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተጠምቆ መፈጠር ነው ።ያ ውሃ በሰይጣን ተበላሽቶ ተቋረጠ።ከዛም ክርስቶስ መጣ ለ ኒቆዲሞስ እንዲህ አለውዮሐ 3÷5 እውነት እውነት እልሀለሁ ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።ያ የድሮ ውሃ ተበላሽቶ ክርስቶስ መጣና ያንን ውሃ ቀደሰው።ስለዚህ ድጋሚ አዳም ከተወለደበት ውሃ ተወለዱ ከዛ ውሃ
ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስትን አያይምምምምም።

🗣ስለዚህ አሁን ኦርቶዶክሶች ስንጠመቅ በፊት አዳም ከተወለደበት ውሃ ተወልደናልና የእግዚአብሔርን የልጅነት ፀጋ ተቀብለን ወደ መንግስተ ሰማያት እንገባለንንንንንንን።የተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳል
ያልተጠመቀ ደግሞ አይወርስም ይህንንንም ጌታ ነው ያለው እኛ የተዋህዶ ልጆች የተጠመቅን ነን።መንግስቱ የኛ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቅን ብቻ ነው አርባ አራት ነጥብ።የተጠመቁ ብቻቻቻቻቻቻ።።።።።

••●◉ ✞ ◉●••
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
🗣ዕጣን ለቤተመቅደስ አገልግሎት ይውላል:: ሃያ አራቱ ካህነተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በ እግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለዓለም ድኅነት የሚለምኑበት ነው::
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂በቤተክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት፣በነግህ ጊዜ እና በቅዳሴ ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና ልመናውን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል::

══════◄✣••✥••✣►══════
ስለ ዕጣን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ
••●◉ ✞ ◉●••
📖የዕጣን መሠዊያውን ሥራ ከግራር እንጨት አድርገው።ዘፀ 30፥1
••●◉ ✞ ◉●••
📖እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ የሁሉም መጠን ትክክል ይሁን።ዘፀ 30፥34
••●◉ ✞ ◉●••
📖በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ፥ በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው።ዘፀ 30፥35
••●◉ ✞ ◉●••
📖ለዕጣንም የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፥ በማደሪያውም ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ትጋርዳለህ።ዘጸ 40፥5
••●◉ ✞ ◉●••
📖የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ዐጠነበት።ዘጸ 40፥27
••●◉ ✞ ◉●••
📖የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ።ዘሌ 10፥1
••●◉ ✞ ◉●••
📖በእግዚአብሔርም ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናውን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ ዕጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል።ዘሌ 16፥12
••●◉ ✞ ◉●••
📖ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ እጅግ አብዝታችኋል ብሎ ተናገራቸው።ዘኍ16፥7
••●◉ ✞ ◉●••
📖ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ይሠዋሉ።ዘዳ 33፥10
••●◉ ✞ ◉●••
📖ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ ወደ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ ዐጠነ።2ኛዜና 26፥16
••●◉ ✞ ◉●••
📖ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።መዝ 140፥2
••●◉ ✞ ◉●••
📖ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሚልክ 1፥11
••●◉ ✞ ◉●••
📖ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።ማቴ 2፥11
••●◉ ✞ ◉●••
📖በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።ሉቃ 1፥10
••●◉ ✞ ◉●••
📖መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።ራዕ 5፥8
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።ራዕ 8፥3
••●◉ ✞ ◉●••

መልካም ዕለተ ሰንበት
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🙈እነዚህ ሰዎች ተአምር እንዲያደርግ ሲጠይቁት እሺ ያለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ስትለምነው ይቆጣል ብለን እንዴት እንቀበል⁉️የአይሁድን ሽማግሌዎች እንኳን ያልተቆጣውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምን አንደበታችን እናቱን ተቆጣ ልንለው ይቻለናል⁉️
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ከሁሉ በላይ ቅዱስ ዳዊት ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን እንዳለው በረከሰ አንደበታችን፣ በሚወላውል ልባችን ፣ በሚባክን ሃሳባችን ወደ እርሱ የምንጸልየውን የእኛን የኃጢአተኞቹን ጸሎት ለምን ጸለያችሁ ብሎ ያልከለከለ አምላክ ንጽሕት እናቱ በፍጹም ትሕትና ለለመነችው ልመና የቁጣ ምላሽ ሠጠ ማለት እንዴት እንደፍራለን⁉️
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ዳዊት በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ ብሏል፤ እርሱ በልቡ በደል ስለሌለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማው በሃሳብዋ ድንግል የሆነች እናቱን እንዴት አልሰማትም እንላለን⁉️
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እመቤታችን የጠየቀችው ይህን ያህል የማይጠየቅ ነገር ነው እንዴየመንግሥትህን እኩሌታ የሥልጣንህን ፈንታ ሥጠኝ አላለችውም፤ የጠየቀችው ስለ ድሆቹ ሙሽሮች ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🙆‍♂እኛ በረባ ባልረባው ስንዘበዝበው የምንውለውና የምናድረው ታጋሽ አምላክ ለእናቱ ለእኛ የሠጠውን ነገር ይነሣል ማለት ፈጽሞ አይታሰብም❗️አብን አሳየንና ይበቃናል፣እሳት ከሰማይ ወርዶ ሕዝቡን ያጥፋቸው፣በግራ ቀኝህ አስቀምጠን የሚሉ ደቀ መዛሙርትን ታግሶ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ያስከተለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት እናቱ ተገቢ ልመና በተገቢ ሰዓት ስትለምነው ሊቆጣ አይችልም።እንደ ወንጌሉ ብቻ ከሔድን ደግሞ እመቤታችን ከዚህ በፊትና በኋላ ምንም ነገር ስትለምነው አልተጻፈም፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
📖በወንጌል ለተጻፈው ለዚህ ብቸኛ ልመናዋም መልሱ ቁጣ ነው ብለን አምነን መቀመጥ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ፈጽሞ የሚዋጥልን ሃሳብ አይደለም፤ በልጅነትዋ ወልዳው ለተሰደደችው ፣ በነፍስዋ የኀዘን ሰይፍ ላለፈባት እናቱ አንዴ ብትለምነው ተቆጣ ብለን እንዴት እንናገራለን⁉️
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሰርግ ቤት እንኳንስ እንዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚተረጉመው ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ የሚል የአክብሮት ንግግር ተናግሮ ቀርቶ ፤ ለእናቱ የተናገረው በቀጥታና በግልፅ የቁጣ ንግግር ቢሆን ኖሮ እንኳን ጾመን ጸልየን ፣ ወድቀን ተነሥተን ምሥጢራዊ ትርጉሙን እንፈልጋለን እንጂ ሰማይና ምድር ቢነዋወጥ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን ተቆጣ ብለን አናምንም።
••●◉ ✞ ◉●••
ምንጭ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
💁‍♂ቃና ዘገሊላ ገጽ 81
••●◉ ✞ ◉●••
መልካም ዕለተ ሰንበት
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
2025/10/27 14:41:53
Back to Top
HTML Embed Code: