Telegram Web Link
🗣ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል‼️🗣
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም::ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ::ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ (ኢሳ 38:5)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነውበደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን ይላል መሐሪው (ሕዝ 18፥23)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
🗣በማርያም ማመን ይገባልን
የተቃዋዋሚዎች ጥያቄ ነው
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ተወዳጆች ሆይ የአምልኮ ስግደት ለምናመልከው ጌታ ለመመድኀኒታችን ለእየሱስ ክርሰቶስ የፀጋ ደግሞ ፀጋን ለተሞላችው ለእመ ብርሀን እንሰግዳለን ሳንሠለችም በትክክል እናምናለን፡፡ ነገር ግን ምን ብለን ማመን እንደሚገባን መለየትና ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
የአዳም ዘር መሆኗን እናምናለን
ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ መሆኗን እናምናለን
ከሴቶች መካከል የተባረከች መሆኗን እናምናለን
አማላጅነቷን እናምናለን
ዘላለማዊ ድንግልናዋን እናምናለን
የእግዚአብሔር እናት መሆኗን እናምናለን
የውርስ ኃጢአት ያላገኛት ንጽህት
መሆኗን እናምናለን
የመዳናችን ምክኒያት መሆኗን እናመናለን
የሕይወት መገኛ መሆኗን እናምናለን
እመ አምላክ፣ እመ ብርሃን መሆኗን እናምናለን

┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💯ልብ ይበሉ ተወደጆች‼️ነገር ግን ፈጣሪ ናት፣ አምላክ ናት፣ እንዲሁም በመስቀል ተሰቅላ አድናናለች ብለን ግን አናምንም❗️አምነንም አናውቅም❗️ ወደፊትም አናምንም❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ተወደጆቸ ይሄንን ልል የቻልኩት አንዳንዶች በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ በማርያምም ማመን አይገባም ስለሚሉ ነው፡፡ዝም ብሎ ማመን የለም❗️ምን ብሎ ማመንም እንደሚገባ ማወቅም ያስፈልጋል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስም እኮ የምናምነው፦ እግዚአብሔር መሆኑን፣ የባህርይ አምላክ መሆኑን፣ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ፣ የአማልክት አምላክ፣ የስጋም የነብስም ፈጣሪ፣ አልፋና ኦሜጋ ፈራጅ ዳኛ፣አማላጅ ያይደለ ተማላጅ መሆኑን፣ ፀሎት ሰሚ ጉዳይ ፈጻሚ አምላክ መሆኑን ነው ፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣በድጋሚ ልብ ይበሉ፦ነገር ግን የግል አዳኝ ነው፣ የፀጋ አምላክ ነው፣ አማላጅ ነው፣ ከአብ በስልጣን ያነሰ ነው፣ ፍጡር ነው ብለን ግን አናምንም፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ....ቅዱሳት መፅሐፍት እንዲህ ይላሉ።
••●◉ ✞ ◉●••
📖የሰው ልጅን(ክርስቶስ) ወልዳለችና ትውልድ ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ፥ ልጆቿም እናታቸው ደስ ይላቸው ዘንድ ስለ እሷ በመጸሐፍት ይሰብኳቸዋል። መዝ86(87)፥4-7
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ይህ ቃሉ ትዕዛዝ ነውና እሷ ያልሰበከ ያለመሰገነ በእሷ ዘወትር ደስ ያላለው የቃሉ ተቃዋሚ አውሬ ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ታላቁ የመዳን ሥራ ሰርቶብኛልና ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይለኛል።ሉቃ1፥48-49
••●◉ ✞ ◉●••
🤷‍♂ይህ ማለት እኮ ትውልድ ሁሉ ፤ማርያም ይሰብካል ማለት ነው፡፡ብፅዕት ማለት እኮ የተመሰገኝሽ ማለት ነው፡፡ካልሰበኳት ቃሉ እንዴት ይፈጽማል⁉️በሆዱ እያመሰገነ ነውን⁉️ ትውልድስ ተብሎ እንዴት ይድናሉ⁉️
••●◉ ✞ ◉●••
📖እንኳን ሰማያዊቷ ኪዳን እናታችን ማርያም ቅድስት ቢታንያ እና ነብዩ ሙሴ እንኳን በምድር በሰማይ እንደ ሚሰበኩ ተጽፏል።ሐዋ 15፥21፣ራዕ 15፥3
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ግን ክርስቶስ በመስቀሉ የሰጠን እናታችን ናት።ገላ 4፥26-27፣ዮሐ19፥27
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ፤ይላል ኢትዮጲያንም ከሷ ተወልደዋልና እናታችን ይሏታል።መዝ 86(87)፥4-5
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እንዲህ ተብሎ የተጻፈው እኮ እኛ ኢትዮጲያውያን በእስራኤል ሐገር ተወልደን አይደለም ፤የማርያም ልጆች ስለሆንን እንጂ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በሰማይ በምድር ሌላ የመዳኛ ምልክት አትፈልጉ ፤ አምላክ የሰጣችው የመዳን ምልክት አማኑኤልን የወለደችውን ድንግልን ነው።ኢሳ 7፥10-14፣ራዕ 12፥1
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ኢየሱስ ከሐዋሪያት ዮሐንስን ከፍጥረት እናቱን ይወዳል የወደዳቸውም ሰልጣን ሰጥቷቸው ሰማይ ዙፋን አንግሷቸዋል። ዮሐ19፥26፣ራዕ 3፥21፣ራዕ 20፥4
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ለእነሱም እንሰግድ ዘንድ አዝዞናል። ኢየሱስ የሚወድ መገለጫው ጌታ ሆይ❗️ጌታ ሆይ❗️ማብዛት ሳይሆን ትዕዛዙን መፈጸም ነውና ትዕዛዙን አክብረን ሰማያዊ ዙፋን ላስቀመጣቸው ስልጣናት ትዕዛዙ ነውና በማክበር ብቻ ሳይሆን በፍቅር እንሰግዳለን።ራዕ 3፥9፣ሮሜ 13፥1-7 ፣ዮሐ 14፥15-16
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ማንም ድል የነሳ፥ የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም የማርያም ስም ይታተምበታል።ራዕ 3፥12፣ገላ 4፥26-27
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
የቤተ ክርስቲያን ደጆች እንዳይዘጉ.mp4
2.7 MB
🗣የማንቂያው ደወል በጃንሜዳ ከአዲስ አበባ ጎልማሶችና ማኀበራት ሕብረት ጋር በመተባበር የካቲት 21/2013 ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ይደወላል🔊
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ይሰበካል በዛ ቀን እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል። ከግማሽ ሚሊየን ህዝበ ክርስቲያን በላይ በሚሳተፍበት በዚህ ጉባኤ ላይ የተዋህዶ ልጆች ታሪክ ለመስራት ተዘጋጁ።
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂በእውነት የተዋህዶ ልጅ ሆኖ ይህንን መልዕክት ሼር የማያደርግ ክርስቲያን ይኖር ይሆን በሉ በፍጥነት ሼር_አድርጉት።

••●◉ ✞ ◉●••
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
🕊የማንቂያ ደወል ድምፅ 🕊
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
🤷‍♂አንዳንዶች ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን
••●◉ ✞ ◉●••
🙈ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን
••●◉ ✞ ◉●••
🙏ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም❗️
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ለምታውቋቸው ሁሉ አጋሩ።እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ❗️
••●◉ ✞ ◉●••
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
🕊የማንቂያ ደወል ድምፅ 🕊
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
የእምነት አባቶቻችን የጌታ ደቀመዛሙርት ህይወታቸው እንዴት አለፈ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ማርቆስ:- እስኪሞት ድረስ በአሌክሳንድርያ ግብፅ ጎዳናዎች በፈረስ ታስሮ እየተጎተተ ሰማዕት ሆኗል።
💁‍♂ሉቃስ:- በግሪክ ሰቅለውት ህይወቱ አልፋለች።
🔊ማቲዎስ:-በቆንጨራ ተቆርጦ ሰማዕት ሆኗል።
🔊ዮሐንስ:- በፈላ ዘይት ውስጥ ተቀቅሎ ሰማዕት ሆኗል።
😱ጴጥሮስ:-ተዘቅዝቆ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሰማዕት ሆኗል።
😱ቶማስ:- በህንድ በጦር ተወግቶ ሰማዕት ሆኗል።
ጳውሎስ:-በአሰቃቂ ሁኔታ ተገርፎ አንገቱ ተቆርጦ ሰማዕት ሆኗል።
🗣ስምዖን:-ግማሽ ለግማሽ ተቆርጦ ሰማዕት ሆኗል።
🗣ማቲያስ:-በድንጋይ ተወግሮና አንገቱ ተቆርጦ ሰማዕት ሆኗል።
💁‍♂እንድርያስ:-በስቅላት ሰማዕት ሆኗል።
💁‍♂ያዕቆብ:-በእየሩሳሎም አደባባይ አንገቱ ተቆርጦ ሰማዕት ሆኗል።
🙏በርተለሚዎስ:-በግርፋት ሰማዕት ሆኗል።

┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ሁሉም መልካሙን ገድል ተጋደሉ። ክርስቶስን ካዱ ሲባል አይሆንም ብለው አንገታቸውን ለካራ ሰውነታቸውን በዘይት ለመቀቀል፣ለግርፋት፣ለስቅላት አሳልፈው ሰጡ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🤷‍♂እርስዎስ በአሁኑ ሰዓት ስለምን እያማረሩ ይሆንበላይ ያለው ክብር ይበልጣል። ይኸኛው አላፊ ጠፊ ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖አሁንም ይላል እግዚአብሔር በፍፁም ልባችሁ በፆም በልቅሶ እና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ❗️እዮ 2፥12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
በምድር ያበበ በሰማይ ይረግፍል...በምድር የተጎሳቀለ ያለቀሰ በሰማይ ምህርትን ያገኛል ....
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
🙈ምንፍቅና በቅዱስ ቃሉ ሲፋቅ❗️
መናፍቃን የሚያነሱትን ጥያቄ ቀለል ባለ
መንገድ ስንመልስ
‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣የእስራኤል መስፍን የሆነው ኢያሱ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን ብሎ እንዳላለ ❗️ኢያ 5፥13።እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኘ አሁን መጥቻለሁ አለ፤ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፤ጌታየ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው አለው፤የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ አለው።የምታመልኩትን ምረጡ ያለው ኢያሱ ለመልአኩ በስህተት ሰገደ ብለን አናምንም❗️ለመልአኩ በግንባሩ መደፋቱም መልአኩን ለማክበር እንጅ ለማምለክ እንዳልሆነ እናውቃለን‼️ዛሬም ኢያሱን ተከትለን እንዲሁ ስናደርግ አምላክን ከመልአክ ለይተን ነው‼️የአንዱን ላንዱ ሳንሰጥ፣ሳንቀላቅል‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ወንጌላዊው ዮሐንስ በመልአኩ እግር ፊት ሰገድኩለት እሱ ግን አትስገድልኝ፣ ሁለታችንም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን አለኝ….(ራዕ 19፥10፣22፥8) የሚለውን ጥሬ ንባብ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት መናፍቃን ያቀርባሉ።ተሳስተዋል❗️ልብ በሉማ
••●◉ ✞ ◉●••
ወንጌሉን፣መልእክታቱን፣ራእዩን የጻፈው ዮሐንስ ለመልአኩ የሰገደው ባለማወቅ ነው ማለት ይሄን ሁሉ የጻፈውን ዮሐንስ ለማን መስገድ እንዳለበት እንኩዋ የማያውቅ አዲስ ምእመን ማስመሰል ነው❗️ዮሐንስ የሰገደው መስገድ ስለሚገባው ነው❗️
••●◉ ✞ ◉●••
መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ስግደት የበላይና የበታች መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ዮሐንስ በክብር እደተስተካከለው አውቆ ነው።ለትህትና‼️
••●◉ ✞ ◉●••
መልአኩ በምእራፍ 19 ቁ 10 እንደተገለጸው ዮሐንስን አትስገድልኝ ቢለውም ዮሐንስ ግን በምእራፍ 22 ቁ 8 ም ዳግመኛ ለመልአኩ ሲሰግድ እናገኘዋለን❗️ዮሐንስን ያህል የጌታ ወዳጅ(ፍቁረ-እግዚእ) ተብሎ የተነገረለትና በጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ የወረደበት አባት ለመልአክ መስገድ ስህተት መሆኑ ጠፍቶ፣ እየተነገረው ጭምር ከአንዴም ሁለቴ ሰገደ ማለት ቅድስናውን መጠራጠር ይሆናል።ስለሆነም መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ለትህትና ነው ስንል እናምናለን
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂የሞቱ ቅዱሳን ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም የምትሉ ሰዎች አላችሁ😂።እሺ ቅዱሳኑስ ይሁኑ ታዲያ መላእክት እኮ አይሞቱም። ስለታናናሾች የአብን ፊት ያያሉ እንጅ ማቴ 18፥10 እንደተጻፈው❗️በዘካ 1፥13 የመልአኩ ምልጃ እንዲህ ተጽፉዋል።አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ 70 አመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተማዎች የማትምራቸው እስከመቼ ነው አለው እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው ታዲያ ሳንለምነው እንዲህ የሚማልድልን መልአክ ብንለምነውማ ምን ያህል ይማልድልን⁉️ሰአሉ ለነ ሚካኤል ወገብርኤል እንበላቸውማ‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር በመንፈስ እንደሚገናኙ ደግሞ ይሄው።ያረፋ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነሱ እንደማያፍር በዕብ 11፥16 ተጽፉዋል።ያረፋ ቅዱሳን አላዋቂዎች ሳይሆኑ ወደፍጹምነት የተሸጋገሩ ፍጹማን መሆናቸው በዕብ 12፥22 ሰፍሮልናል‼️ጌታም ከአመታት በፊት በሞት የተለዩትን አብርሃምን ይስሀቅንና ያዕቆብን ጠቅሶ ፤የህያዋን አምላክ ነኝ ሲል በማቴ 22፥32 ተናግሯል ❗️ጌታችን በስጋ ስለሞተው አብርሃም በዮሐ 8፥56 ሲናገር አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴትን አደረገ፤አየም ደስ አለው ይላል።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣በአጸደ ነፍስ ያለው አብርሃም የጌታን ቀን አይቶ የተደሰተው በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር ካለነው ጋር ህብረት ስላላቸው ነው❗️ዮሐንስ በራዕዩ 8፥3 የዕጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚብሔር ፊት ወጣ ይለናል።መላእክት ጸሎታችንን ያሳርጋሉ‼️አእርጉ ጸሎተነ የምንላቸውም ለዚሁ ነው።ሙሴ በዘፀ 32፥13 በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ይስሀቅንና እስራኤልን አስብ ብሎ በአጸደነፍስ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ስም ጌታውን ሲማጸን ከሞቱ ቅዱሳን ህብረት ስላለን አይደለምን⁉️ነው እንጅ❗️
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ይሄን ሁሉ ስንል ባለቤቱን ረስተን አይደለም።በቀጥታም እሱን ማረን እንለዋለን።
እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በምህላ፤መሀረነ አብ በማስታኮት‼️ስማን፣ተማለደን፣ታረቀን እንለዋለን።ግን እንደሌሎቹ አማልደን አንለውም😳ሌሎች የሚያማልደን ጌታ ነው እያሉ ቤዛነቱን እንደአማላጅነት ስለሚወስዱት ነው እኛ ቅዱሳንን አማልዱን ስንል አምላክ ያደረግናቸው የሚመስላቸው‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
አምላካችን አንድ ነው❗️የሃይማኖታችን መሰረትም እሱ ለዚህም ነው ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን ስንል የሃይማኖት ጸሎታችንን የምንጀምረው‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🗣የማንቂያው ደወል በጃንሜዳ።ሥፍራ ጠበበ እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በምን ቃል ልግለጽሽ እኔ ቃል የለኝም። በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታሪክ እየተሰራ ነው። እግዚአብሔር በትውልዱ ላይ ሊሰራ ያሰበው መለኮታዊ አጀንዳ እየተፈጸመ ነው። ዓለም ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እየተመመ ነው።የኢትዮጵያም የትንሳኤ ጊዜ የተቃረበ ይመስላል። ብቻ እየሆነ ያለው ነገር በእግዚአብሔር እንጂ በሰው ጉልበት አይደለም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔊የማንቂያ ደወል ! በበኩረ ሰባኪያን መምህር ምህረተአብ አሰፋ በጃንሜዳ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
የማንቂያ ደወል ድምፅ

┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
🔥1
Forwarded from Emebet A
Selam lenante yhun fkadachhu kehone azegajoch sle slet mawek efelgalehu bnasker bnset ena lelochnm .....egzabher ystlgn
🗣ስእለት በቅዱሱ መፅሐፍ 📖
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
የኔ ተወዳጆች ስእለት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ፥ ሰው በፈቃዱ ለመስጠት ቃል የሚገባው ነገርና ለአምላካችን ምስክርነት የሚሰጥበት ነው ::ሰው ራሱን ከችግር ከመከራ ለማራቅ ለእግዚአብሔር ይሳላል ሆኖም የምንሳለውን ማወቅ አለብን።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ተወዳጆቸ ተስለን ከሆነ ከመፈጸም አንሽሽ፥ ሰው ስእለቱን ባይፈጽም ኃጢአት ነውና::
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘገይ። ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም።በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።ዘዳ 23፥21-23
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉ ዕጣን ዘቢብ ጥላ ጣፍና የመሳሰሉትን ብንሳል ጥሩ ነው:: እንዲሁም በጎ ሥራ ለመፈጸም እንደ ዝክር ጸበል ጻዲቅ ነዳያንን መመገብ የመሳሰሉት ያጸድቁናል::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ስእለትን በተመለከተ ማስረጃ📖
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ። ዘፍ 28፥20-22
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂እስራኤልም ለእግዚአብሔር፦ እነዚህን አሳልፈህ በእጄ ብትሰጣቸው ከተሞቻቸውን እርም ብዬ አጠፋለሁ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ዘኁ 21፥2
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ዮፍታሔም። በእውነት የአሞንን ልጆች በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ።ዮፍታሔም ሊዋጋቸው ወደ አሞን ልጆች አለፈ፥ እግዚአብሔርም በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው። መሣፍ 11፥30
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች። 1ኛሳሙ 1፥11
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ ።መዝ 49፥14
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ በዙሪያው ያሉ ሁሉ እጅ መንሻን ለሚያስፈራው ያገባሉ።መዝ 75፥11
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሰው በችኰላ። ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው።ምሳ 20፥25
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔርi ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውን ፈጽመው።መክ 5፥4
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።ዮና 2፥10
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል። ናሆ 1፥15
••●◉ ✞ ◉●••
📖ከዚህም በኋላ ጳውሎስ እጅግ ቀን ተቀምጦ ወንድሞቹንም ተሰናብቶ በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ፤ ስእለትም ነበረበትና ራሱን በክንክራኦስ ተላጨ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ።ሐዋ 18፥18

┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
👌ቤተክርስቲያን ባሕረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት።የሲኦል ደጆች አይችሏትም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ቤተክርስቲያን የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን አሜን
‼️
❖✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
አንድ ጌታ፣ አንድ ሀይማኖት ፣ አንዲት ጥምቀት።ኤፌ 4፥4-5
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✍🏽 ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ነገር ግን በፍርሃትና በየዋህነት ይሁን።1ኛ ጴጥ 3፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✍🏽 ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም።1ኛ ቆሮ 8፥2
❖✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @efr21
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @eotc27 🔔 @eotc27
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
🗣ሐይማኖት ያድናል ወይስ አያድንምሐይማኖት ምንድነውሐይማኖት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም ሐይማኖት ይወረሳል ወይስ አይወረስም
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ሐይማኖት፦ የሚለው ቃል ሃይመነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው።ትርጉሙም፦ማመን፣መታመን፣አማኝነት፣አመኔታ ማለት ሲሆን መቀበል ተስፋ ማድረግ ፣አለመጠራጠር፣ያዩትን እና የሰሙትን እንዲሁም ያመኑትን እውነት በማያምኑት ፊት መመስከር ማለት ነው።ሮሜ 10÷9፣ቆላ2÷6-7፣የሐ 14÷1
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሐይማኖት ምንጩና ባለቤቱ ኃያሉ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።ሐይማኖት የሰው ልጆች ከእውቀት ማነስ ወይም ከፍርሃትና ከድንጋጤ ያመጡት አይደለም።ከፍልስፍና እና ከመራቀቅም የተገኘ ሳይሆን እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሰጣቸው ውድ ስጦታ ነው።ይሁዳ 1÷3
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሐይማኖት አንዲት ናት።ሁለተኛና ሦስተኛ የላትም።ፈጣሪና ፍጡራን የሚገናኙባት ረቂቅ መንገድ ናት።ኤፌ 4÷5 ፣ኤር 6÷16፣ማቴ፣7÷13-14
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ሐይማኖት ሲባል ሰዎች የፈጠሩት ሳይሆን እግዚአብሔር በራሱ ፍቃድ እናውቀው ዘንድ ስለ ራሱ የገለጠው መገለጥ ነው።ስለሆነም ሐይማኖት እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ያሳየበት
መንገድ እና የሰው ልጅ ሊቀበለው በሚችለው መጠን ስለ ራሱ ማንነት ለእኛ የገለጠው እውነታ ነው።ስለዚህ ከዚህ እውነታ በመነሳት

••●◉ ✞ ◉●••
🙋ጥያቄ1፦ሐይማኖት ያድናል ወይስ አያድንም
🙋‍♀ጥያቄ 2፦ሐይማኖት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም
🙋‍♂ጥያቄ 3፦ ሐይማኖት ይወረሳል ወይስ አይወረስም
ለሚሉ ጥያቄዎች የማያዳግም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መልስ እንሰጥበታለን።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙋ጥያቄ 1፦በአንዲት እውነተኛ ሐይማኖት ውስጥ ያለ አንድ ሰው እና ምንም ሐይማኖት የሌለውን ሌላ ሰው ብናነፃፅር የመዳን ወይም እግዚአብሔርን የማወቅ ሰፊ እድል ያለው የትኛው ሰው ነውስለዚህ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዲት ተብላ የተጠቀሰችው ሐይማኖት ሰዎች ከተጠቀሙባት መዳን በውስጧ አለ ታድናለች።
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ምክንያቱም የእግዚአብሔር አንድነትና ልዩ የሦስትነት ሚስጥር፤ጌታችን አምላካችን አባታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፤የመስቀሉ ድንቅ ሥራው እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የገለጠበት ዋና መንገድ ሐይማኖት በመሆኑ ሰው ለመዳን የግድ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተሰጠች ሐይማኖት ውስጥ ገብቶ ትምህርት ሐይማኖትን መማርና ማወቅ አለበት።ካልተማረ የእግዚአብሔርን መኖርና የእግዚአብሔርን ፍቃድና አላማ እንዴት ያውቃል ካላወቀ እንዴት ያምናል ካላመነ እንዴት ሊድን ይችላል 🤷‍♂
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ለዚያ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደተቀበላችሁ በእርሱ ተመላለሱ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነፁ እንደተማራችሁም በሐይማኖት ፅኑ ምስጋና ይብዛላችሁ።ቆላ፡ 2÷6-7
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ስለዚህ ሰው በሐይማኖት መኖር አለበት።በሐይማኖ መኖር ብቻም አይደለም።ሐይማኖት የሚያዘውን ትዕዛዝ እየፈፀመ መኖር አለበት።ለዚህም በሐይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው ተብሎ የተፃፈው።ቲቶ 1÷13
••●◉ ✞ ◉●••
🔊ሐይማኖትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው ተብሎ የተፃፈውም ሰው ሐይማኖቱን የሚከዳ ወይም በሐይማኖት የማይኖር ከሆነ ሊድን እንደማይችል የሚያስረዳ ቃል ነው።1ኛ ጢሞ 5÷8።ምክንያቱም ሐይማኖትን መካድ ወይም ከሐይማኖት መውጣት ከማያምን ሰው ይልቅ የሚከፋ ከሆነ በሌላ አነጋገር ሐይማኖትን የሚከዳ ሰው አይድንም ወይም ከማያምን ሰው ይልቅ ተጠያቂ ይሆናል ማለቱ እንደሆነ ማወቅ አለብን።
••●◉ ✞ ◉●••
👑የፅድቅ አክሊል ከሚያጎናፅፈን አንዱ እና ዋናው ሐይማኖትን መጠበቅ መሆኑን ተናግሯል፦ መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ሩጫውን ጨርሻለው፣ሐይማኖትን ጠብቄያለሁ።ስለዚህ የፅድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ። 2ኛ ጢሞ 4÷8
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙋‍♂ጥያቄ 2፦ ሃይማኖት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም መናፍቃን እና ተሐድሶዎች ፓስተሮቻቸውም ጭምር ሐይማኖት አያስፈልግም ሲሉ እንሰማቸዋለን።ለመሆኑ ሐይማኖት
የማያስፈልግ ከሆነ ለምን የፕሮቴስታንት ሐይማኖት ተከታይሆኑ
ለምንስ ከአንዱ ሐይማኖት ወደ ሌላው ሐይማኖት ይዟዟራሉ ሐይማኖት የማያስፈልግ ከሆነ ለምን የማንም ሃይማኖት ተከታይ ሳይሆኑ አይኖሩም ነበር 🤷
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ሲጀመር በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማያስፈልግ ነገር አይፃፍም።ቅዱስ ጳውሎስም ሐይማኖት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያውቅ ብዙ ቦታ ላይ ስለ ሐይማኖት ሰብኳል።ለምሳሌ በሐይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ።2ኛ ቆሮ 13÷5፣ንቁ በሐይማኖት ቁሙ።1ኛ ቆሮ 16÷13 ፣አንዲት ሐይማኖት ኤፌ 4÷5፣ሐይማኖትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።1ኛቲሞ 5÷8
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙋ጥያቄ 3 ፦ሐይማኖት ይወረሳል ወይስ አይወረስም የእውነት የሆነ ሐይማኖት ይወረሳል።ትውልድ አልፎ ትውልድ በመጣ ቁጥር ሐይማኖት ይወረሳል እንጂ እየታደሰ እየተፈጠረ አይሄድም።ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጣቸው ሐይማኖት በትውልድ ቅብብሎሽ እኛ ዘመን ላይ ደርሳለች። አባቶቻችን ከሐዋርያት የተቀበሏት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖትን ለእኛ አውርሰውናል እኛ ደግሞ ለልጆቻችን እናወርሳቸዋለን፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
📖በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን ፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን ፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል።የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 7፥21-26
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🙈ዓይኔን ጨፍኜ ብጸልይስ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣አይንን ጨፍኖ መፀለይ የጨለማ
ምልክት ነው፤ጨለማ ደግሞ የሲዖል ምልክት ነው፡፡የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምእመናን የምንጸልየው ዓይኖቻችነንን ከፍተን ወደላይ ወደሰማይ አቅንተን ነው።ምክንያቱም እንዲህ መጸለይ የቅዱሳን አበው ስርዓት ነውና። ይህንን በተመለከተ ልብ አምላክ ዳዊት
ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አንሳሁ ብሏል፡፡መዝ120፥1
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂በተጨማሪም በሰማይ የምትኖር ሆይ አይኖቼን ወደ ተራሮች አነሳሁ እነሆ የሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እንዲሆኑ የባሪያቱም ዓይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሆነ እንዲሁም እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚያብሔር ነው ብሏል፡፡መዝ 123፥1-2)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ያስተማረው ዓይንን ከፍቶ ወደ ሰማይ አቅንቶ መፀለይ ነው፡፡ዮሐ11፥41 ከዚህም የተነሳ የሐዲስ ኪዳን ምእመናን ሁሉ የሚከተሉት ይህንን የጸሎት ስርዓት ነው።ለምሳሌ ቅ/ ስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ በድንጋይ እየተወገረ እርሱ ግን አይኑን ከፍቶ ወደ ሰማይ አቅንቶ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል እያለ ሲጸልይ እና ይህንን ሐጥያት አትቁጠርባቸው እያለ ያማልድ ነበር።የሐዋ 7፥54
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ከላይ በአጭሩ ለመግለጽ እንሞከርኩት መሰረታዊው ነገር ይህ ሲሆን ዓይንን ጨፍኖ ግን ለመጸለይ የሚቀርበው ምክንያት ሀሳቤን ይሰበሰብልኛል፤ ልቦናዬን ያረጋጋልኛል የሚል ነው፡፡ነገር ግን አይን ስለተጨፈነ አሳብ አይሰበሰብም ልቦናም አይረጋጋም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👌ምክንያቱም አይንን በመጨፈን አሳብ የሚሰበስብ ቢሆን ኖሮ ዓይኖቻቸው የጠፋባቸው ወገኖች ሁሉ ለጸሎት በሚነሱበት ጊዜ ልቦናቸው አይበትንባቸውም ያስብል ነበር፡፡ምን አልባት ነገር በአይን ስለሚገባልንል እንችል ይሆናል።ዳሩ ግን በጆር የሚገባውንስስንጸልይ ጆሮኣችንን በጥጥ ልንወትፈው ነውነገር እኮ ከልቦና ይመነጫል።ይህንንስ እንዴት ልናደርገው ነው
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👍ተወዳጆች እኛ በስሜታዊነት በአንድ ጊዜ ከመንፈሳዊነት ሕይወት ጫፍ ላይ ለመውጣት በአንድ ጊዜ ከፍጹም ማዕረግ ለመድረስ ስለምንፈልግ እንጂ አሳብን ሰብስቦ በተረጋጋ መንፈስ መጸለይ በአንድ ጊዜ የሚደረስበት ጸጋ አይደለም፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ምክንያቱም መንፈሳዊ ህይወት ደረጃ አለው በመሆኑም በብዙ ገድል ከአንድ ደረጃ ወደሌላ ደረጃ በእግዚያብሔር ቸርነት እያደጉ ይደረስብታል እንጂ ቁጭ ተብሎ ስለፈለጉ ብቻ የሚገኝ አይደለም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ስለዚህ በምንጸልይበት ጊዜ የሚረብሹን ብዙ የሀሳብ ውጣ ውረዶች ቢኖሩ ከእነርሱ ጋር በእምነት እየተጋደልን እስከመጨረሻው መጽናት አለብን፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙈እንደ አሁኖቹ ፕሮቴስታንቶችም ሆነ ሌላ የእምነት ድርጅቶች ውስጥ አይንን ጨፍኖ መጸለይ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም፤መፅሐፍ ቅዱስም አይደግፈውም እና በምንጸልይበት ጊዜ አይናችንን ወደ ሰማይ አምላክ በመግለጥ መጸለይ እንዳለብን መጽሀፍ ያስረዳል፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🔔ወጣት ተጠንቀቅ እራስህን ጠብቅ ታላቁ ጾም ሊገባ ነው።ታዲያ ሰይጣን ይህን ግዜ በጆሮህ ኃጥያትን ሹክ ይልሀል። 🚷
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔔ሰኞ ጾም ሊገባ አይደል ያውም ረጅም ጾም ስለዚህ ከመገባቱ በፊት ከሴት/ፍቅረኛ/ ጋር አብረህ እደር❗️(ከትዳር በፊት)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣እያለ የዝሙት ሀሳብን በልብህ ይዘራል ምርጫው ያንተ/ቺ ነው❗️ ኦርቶዶክሳዊ/ት ወጣት ጾምን በንስሐ እንጂ በዝሙት አይጀምርም(አትጀምርም)❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙈ለጽድቅ ያልነው ኩነኔ እንዳይሆንብን፤ጾሙን እግዚአብሔር አምላክን በማስቀየም እንዳንጀምረው፤የሰይጣን የጦር እቃ እንዳንሆን እንጠንቀቅ❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✉️ይህን መልዕክት ሳይረፍድ ለወጣቱ በሙሉ አድርሱ❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
እንኳን አደረሰን አደረሰዎ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
📩በጥንት የተላከ ደብዳቤ📄
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📄በእኛ ዘንድ የጌታችንን እናት ለማየት የሚሹ ብዙ ሴቶች አሉ።ዘወትርም ወደ አንተ ለመምጣት ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በታቀፈች እጆቿ መዳሰስ እንዲሁም ከእርሷ መማርን ይናፍቃሉ።🙈
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📑እመቤታችንን የአምላክ እናት እንደሆነች ንጽህት ቅድስት ዘላለማዊት ድንግል እንደሆነች በማመን ከፍ ከፍ እናደርጋታለን።በመከራና በመሳደድ ደስተኛ እንደሆነች በማጣትና በችግር እንደማታዝን በሚነሱባትም ሁሉ እንደማትቆጣ ብቻ ሳይሆን መልካም እንደምታደርግላቸዉም በእኛ ዘንድ የታመነ ነዉ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📑እመቤታችን ለድሆች እንደምትራራና በሁሉ እንደምትረዳቸዉ በደስታም ጊዜ በዝግታ የምትኖር መሆኑን እናዉቃለን።ነገር ግን እምነቷን (ሀይማኖቷን) የሚጻረሩትን በጽኑ ትቃወማቸዋለች።እምቤታችን ለሚያምኑ ሁሉ የመልካም ስራ መሪ የጽናት ፣የትግስትና የትህትና መምህር ናት።ከሁሉ አብልጣ ትሁታን ትወዳለች።እርሷም ለሁሉ ትሁት ናትና።የአይሁድ ህግ አዋቂወችና ፈሪሳዉያን በተሳለቁባት ጊዜ በትህትና መቀበሏ የሚገርም ነዉ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📄የምናምናቸዉ ሰዎች በጌታችን እናት በማርያም ንጽህና የተነሳ የሰዉ ብህሪይ የመላእክትን በህሪይ እንደመሰለ ነግረዉናል።በዚህ ሁሉን የተነሳ በልባችን ያለዉ እመቤታችንን የማየትና ድምጿን የመስማት ፍላጎት ልናገር ክምንችለዉ በላይ ሆኖብናል።የሚቻለኝ ቢሆን ወደ ኢየሩሳሌም ልምጣና በዚያ የተሰበሰቡትን ክርስቲያኖች ላያቸዉ እናፍቃለሁ።ይልቁንም የጌታችንን እናት ለማየት እናፍቃለሁ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📃ብዙወች እርሷ ን ያዩ ክብርት መሆኗን ከዚሁም ጋር ትሁታን በርጋት የምትናገር ደስ የምታሰኝ እንደሆነች ነግረዉናል።ይህም በፈጠረብን መደነቅ ሁላችንም ልናያት እንናፍቃለን።ግን ሰማያዊ አምላክ በሆዷ የያዘችዉን በድንግልናም የወለደችዉን ቅድስት ድንግል ማርያም ለማየት የማይሻ ማን ይኖራል።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗞ቅዱስ አግናጥዮስ ለወንጌላዊ ዮሐንስ ከጻፈለት ድብዳቤዎች የተወሰደ
(ምንጭ፦THE ASSUMPTION OF OUR MOST HOLY LADY ,THE MOTHER OF GOD AND VERGIN MARY 1990

══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
ሞትን የማይፈራ ትውልድ ❗️❗️

┈┈┈••●◉ ✞ #join @geb19 ✞◉●••┈┈┈

🗣አባ አጋቶን በክርስቶስ ዙፋን ፊት እቆማለሁና እፈራለሁ ይሉ ነበር።ከእርድእቶቹ አንዱ አባታችን ሞትን አንተም ትፈራለህ አሉዋቸው፡፡ አባ አጋቶንም እኔስ እንደ ተቻለኝ ሠራሁ እላሉ፣ነገር ግን የጌታ ፍርድ ሌላ የሰው ፍርድ ሌላ፣አላውቅህም ቢለኝ ምን እላለሁ፣በእለተ ሞትና በእለተ ምጻት ከፍርሃት ከጥርጥር የሚድን የለም አሉ፡፡

┈┈┈••●◉ ✞ #join @geb19 ✞◉●••┈┈┈

💁‍♂አባቶቻችን ጽድቅ ሠርተው ተጋድለው በተጋድሎቸው ፈጣሪያቸውን አስደስተው ሞትንና የሰማይ ቤት ፍርድን ይፈራሉ፡፡ እኛ ግን የነፍሳችንን ስነቅ ሳንሰንቅ፣በኃጢአት ስንጨማለቅ ኖረን ሞትን አንፈራም፡፡ኃጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል፤እግዚአብሔር በበደላችን ሲታገሰን የሌለ ይመስለናል፡፡ በዚህም የሰማይ ቤት ፍርድ እና ክብር ተረት የሚመስለን አለን፡፡

┈┈┈••●◉ ✞ #join @geb19 ✞◉●••┈┈┈

🤷‍♂ጽድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ሆኖ፣ በእግዚአብሔር ቸርነት ተከድኖ እየኖርን ሞትን መርሳታችን ንስሐን እንቢኝ ማለታችን ይገርማል፡፡ሞትን የማንፈራ ትውልድ መሆናችንን የምናውቀው በሞት መንገድ በኃጢአት ጎዳና መመላለሳችን ነው፡፡ ሞትንና ሰማያዊ ፍርድን የምንፈራብንሆንማ ንስሐ ገብተን በቅዱስ ቁርባን ተወስነን በቅድስና ጎዳና እንጓዝ ነበር፡፡

┈┈┈••●◉ ✞ #join @geb19 ✞◉●••┈┈┈

🗣ሁላችንም ሞትን እንደ ልብሳችን የምናወልቀው ሳይሆን ተሸክመነው የምንዞረው የምንኖረው ነው፡፡ ሞት እራሱ ሞትን ያደፋፍረናል፡፡ሰው ሲሞት ላየ ሞት ምኑም አይደለም፡፡ለክርስትያን ግን የሥጋ ሞት ሳይሆን የነፍስ ሞትና ሰማያዊ ፍርድ ስላለ እሱን ነው እንደ አባ አጋቶን መፍራት ያለብን፡፡

┈┈┈••●◉ ✞ #join @geb19 ✞◉●••┈┈┈
በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
┈┈┈••●◉ ✞ #join @geb19 ✞◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🗣ተሀድሶ አንዱ የማስረሳት ዘዴ ❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ማስረሳት ማለት፦እነዚህ ሰዎች ድንግል ማርያም ታማልዳለች ብለው በአደባባይ አይናገሩም❗️ ጾም አያስፈልግም ብለው አይናገሩም❗️ጸሎት አያስፈልግም ብለው አይናገሩም❗️ውዳሴ ማርያም አትድገሙ፤ሰዓታት አትቁሙ፤ማሕሌት አትቁሙ አይሉም።ግን በተቃራኒው ማሕሌት ቁሙም አይሉም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
አሁን ብዙ ምዕመናን የሚሸወዱት በዚህ ነው።መች ድንግል ማርያም አታማልድም እኮ አይሉም ይላሉ፡፡በነገራችን ላይ ምዕመናን ተሐድሶዎቹ ድንግል ማርያምም እኮ ታማልዳለች አይሉም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🤷‍♂እኛ እኮ ክፉ ሰው ወይም መናፍቅ የምንለው ድንግል ማርያም አታማልድም የሚለውን ብቻም አይደለም።ታማልዳለች የማይለውንም ጭምር ነው።ይሄ ማስረሳት ነው።ስለ ጾም አያስተምሩም፤ ስለጸሎት አያስተምሩም ስለጸሎት አይዘምሩም ተሐድሶዎቹ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂እስቲ እንደው ከአስር አመት በፊት የነበሩትን መዝሙሮች እና ከአስር አመት በኋላ የወጡትን መዝሙሮች እናነጻጽራቸው ስለ ጸሎት ፤ ስለ ጾም ፤ ስለ ሥግደት ፤ ስለ ማሕሌት ፤ ስለ ሰዓታት ፤ ስለ ቅዱሳን የሚዘመሩ መዝሙሮች እኮ እየጠፉ ነው።

┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙊ጸልዩ የሚሉ ፤ ዳዊት ድገሙ የሚሉ ፤ ውዳሴ ማርያም ድገሙ የሚሉ ፤ ማሕሌት ቁሙ የሚሉ ፤ ቅዳሴ ቀድሱ የሚሉ መዝሙሮች እየጠፉ ነው የመጡት ለምንድን ነው እየጠፉ የመጡት አላማው ማስረሳት ስለሆነ ነው። በተለይ ወጣቱ ትውልድ እንዲረሳው ማድረግ እነዚህን ነገሮች እንዲዘነጋ ማድረግ ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
Forwarded from Deleted Account
ሀይማኖት ለስው ልጅ ብቻ ነው?
መላእክት ሃይማኖት አላቸው ?
Forwarded from Deleted Account
መንፈስ ቅዱስ የተሳደበ ሃፂያቱ አይስረይለትም ? የተዋህዶ ልጅ ናኝ እነኝ ጥያቄ ስላልገቡኝ ነው
😞ስርየት የሌለው ኃጢዓት🗣
══════◄✣••✥••✣►══════
📖ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም ።ማቴ 12፥31-32
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እውነት እላችኳለሁ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን ለዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።ማር 3፥28 - 30
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ፍቅር ማቃለል፣የክርስቶስን የማዳን ስራ መቃወም፣የመንፈስ ቅዱስን የምህረትና የይቅርታ ጸጋ መሳደብ ስለሆነ ዲያብሎስ ከፈፀመው ኃጢአት እጅግ የከፋ መሆኑን መናገር ነው።ለእንደዚህ ዓይነቱ ኃጢአት ስርየት የለም።ከዚህ ከተጠቀሰው በስተቀር ለማንኛውም በደል ይቅርታ ይደረጋል።በሰው ልጅ ላይ እንኳን ቃል የሚናገር ይሰረይለታል ተብሏልና‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙊መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ኃጢአት የሚፈጸመው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል (በእግዚአብሔር ጣት) የተሰራውን ሥራ ፈውስ፣ ተዓምራት ሆን ብለው ስም ለማጥፋትና እያወቁ በሰይጣን ኃይል እንደተደረገ ሲቆጠርና ሲነገር ነው፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
💁‍♂ሃይማኖት ምንድን ነው
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሃይማኖት ወይም እምነት ማለት ማመን፤ መታመን፤ የፈጣሪን ሕልውና ማወቅ፤ ከሃሊነቱን፣ መግቦቱንና ቸርነቱን መረዳት፤ መለኮታዊ እውነታዎችን በትክክል መቀበል፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ፈጽሞ አለመጠራጠር፤ ጥርጥርን ከኅሊና ማስወገድ፤ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ጽኑ ተስፋ ማድረግ በሚሉ አገላለጾች ይተረጐማል።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሃይማኖት በረቂቅ ሐሳብ፣ በልብ ሰሌዳነት፣ የሚጻፍ የአእምሮ መጽሔት ነው። ሃይማኖት የኅሊና መሰላል በመሆኑ የዓለምን አስቸጋሪ ዳገት ይወጡበታል። ሃይማኖት የሕይወት መርከብ በመሆኑ ገፊውን ማዕበል ተቋቁመው ባሕሩን ይሻገሩበታል። ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል። ዕብ ፲፩፥፮። ልክና መጠን፣ ወሰንና ዳርቻ የሌለው መለኮታዊ ባሕርይ የሚታየው፣ ሕልውናው ከሃሊነቱና መግቦቱ የሚታወቀው በሃይማኖት ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ቅዱስ ጳውሎስ የሃይማኖትን ኃይል ሲተረጉም እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው። ይልና በመቀጠልም ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን። ብሎአል። ዕብ 11፥1-3

ሃይማኖት ፍጡርን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ የኅሊና መሰላል በመሆኑ ፍጡር የሃይማኖት መሰላሉና ድልድዩ ከተሰበረበት ወደ ፈጣሪው መድረስ ይሳነዋል፤ ሌላ መድረሻ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለውም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👌ስለዚህ ቅዱሳን መላእክት ደግም እግዚአብሔር በፈጠረልንና እንድንረዳ አቅሙን በሰጠን በቀጥታ ከላይ በወረደችው በቀጥተኘዋ ሃይማኖት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ ውስጥ ያሉ በመሆናቸው ሃይማኖት አላቸው።ስለዚህ ሰው ብቻ ሳይሆን መላእክትም ሃይማኖት አላቸው።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
2025/10/26 03:44:53
Back to Top
HTML Embed Code: