Telegram Web Link
Forwarded from Deleted Account
ሰላም አንድ ጥያቄ ነበረኝ እሱም ሁሌ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከ boble ምንም ብትጠየቅ መልስ አላት ግን ይህ ሆኖ እያለ ለምን ትጠጣላችሁ? ቄሶች ለምን ይጠጣሉ? ሲሉኝ ሁሌም መልስ እፕጣለሁ ርና እስኪ አንዳንድ አገልጋዮች ለምን እንደሚሰክሩ እና ለምን እንደሚጠጡ ስለ መጠጥ በመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት በቂ መልስ ብትሰጡኝ ስለ እጠይቃለሁ🙏🙏🙏
🗣መጠጥ መጠጣት ኃጢአት ነውን
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏የኔ ተወደጆች በመጀመሪያ እናንተ ኦርቶዶክሶች ለምን ትጣላላችሁለሚለው ጥያቄ ቅድስት ቤተክርስቲያን መጠጥ ይጠጣ አይጠጣ ለሚለው ሀሳብ የምትሰጠውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ እንሆ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂መጠጥ አብዝተው ቢጠጡት ያሰክራል ፤ኃጢአትም ይሆናል።እህልም ቢበዛ ቁንጣን ያመጣል፤ፈትወት ይቀሰቅሳል፤ከእግዚአብሔር ጸጋ ይለያል።በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናገኛቸው አበው መሀከል መስፍኑ ሶምሶን፣ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የወይን ጠጅ፣ የሚያሰክርም መጠጥ ከአፋቸው ፈጽመው እንደማያቀርቡ (እንደማይቀምሱ) ተመዝግቦልን እናገኛለን።ሳሙ 13፥1-5፣ሉቃ 1፥15።ዛሬም ባህታውያን ወይን እንደማይጠጡ ይተወቃል።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👍ከምዕመናም ወገን ይህንን አብነት አድርገው መላ ዘመናቸውን ከውኃ በስተቀር ሌላ መጠጥ የማይጠጡ አሉ።ይህ በጎ ምግባር ነው ነገር ግን መጠጥ የማይጠጡት ወይን መጠጣት ኃጢአት ነው በሚል ሀሳብ ወይም ሥርዓት ባለው መንገድ የሚጠጡትን በመንቀፍ ሊሆን አይገባም።ለምሳሌ፦ሰዎች ምንኩስናን ሲመርጡ ጋብቻን አቃለው እንደ ርኩስ ቆጥረው ሊሆን አይገባም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🤷‍♂መጠጥ መጠጣት ኃጢአት ነው እንዳንል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዶኪማስ ሠርግ ቤት ውኃውን ወደ ወይን ከመለወጡም በላይ ወይን ጠጥቷል ስለዚህ ነገር ማንም ያስገደደው ሳይኖር በፈቃዱ ጠጣ በማለት በሃይማኖት አበው ላይ ገልጾልናል።በግብጽ ገዳማት ያሉ መነኮሳትም ወይንን መጠጣት ኃጢአት አለመሆኑን ለማስረዳት በዓመት አንድ ቀን ወይንን ይጠጣሉ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ቅዱስ ዳዊትም ወይን የሰውን ልቡና ያስደስታል መዝ 103፥15)፤ሲለን ልጁ ጠቢቡ ሰለሞንም ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድህነቱንም ይርሳ፤ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ አያስብ ብሏል።ምሳ 31፥7-8፤ቅዱስ ጳውሎስም ለደቀመዝሙሩ ለጢሞቴዎስ ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።1ጢሞ 5፥23 ብሎታል።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🖕ከላይ በተገለጸው መሰረት ቄሶችም ይሁኑ አገልጋዮች መጠጥ አለመጠጣታቸው የተሻለ ሲሆን ይህን መጠበቅ ያለተቻለው ግን ለኃጢአት በማያደርሰው መጠን ቢጠጣ አይከለከልም ወይም ኃጢአት አይሆንበትም።ይህ ሲባል ግን አልሰከርኩም ብሎ ብዙ መጠጣት አይፈቀድለትም።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ቄስም ይሁኑ መዘምር፣አገልጋይም ይሁን ሰንበት ተማሪ አብዝቶ ከመጠጣቱ የተነሳ በተለያዩ ኃጢአቶች ይማረካል።ጠቢቡ ሰለሞንም ዋይታ ለማነውኅዘን ለማን ነውጠብ ለማን ነውጩኸት ለማን ነው ያለ ምክንያት መቁሰል ለማን ነው የዓይን ቅላት ለማን ነው የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈተኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን እንዲል ሰው አብዝቶ በጠጣ ጊዜ አእምሮውን ያጣል።ምሳ 23፥29-35
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙈አስተዋይ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉትን ሐይለ ቃል ፍቻቸውን ማስረጃዎች ብቻ በመመልከት መጽሐፉ መጠጥ መጠጣትን ያይደለ ስካርን እንደሚያወግዝ ልብ ሊል ይገባል።ስካር የስጋ ሥራ ነው፤ገላ.5፥19።ስለ ስካር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው ልብስን የሚያስጥል <<የፈቃድ እብደት>> ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ስካር በማወቅ የሚደረግ ጥፋት በመሆኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅጣት ያመጣል።የስካር መዘዝ በምድር ብቻ አይወሰንም ንስሐ ካልገቡና ካልታረሙ ሰካራሞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤1ቆሮ.6፥10።ከዚህ በላይ የስካር ጉዳት ከየት ይመጣል። ወዬ ለሰካራሞች ወዮታ ይገባል።ኢሳ 28፥1-8 ፣ ምሳ 23፥29 ፣ ኢዮ 1፥5
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙅አብዝቶ መጠጣት ሱሰኛ ይልደርጋል ሱስ ደግሞ ኃጢአት ነው።ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባርያ ነው ይላል፤ዮሐ 8፥34።በመጠጥ ሱስ የተሸነፈ የስካር ባርያ ነው።በክርስቶስ ደም ነጻ የወጣ ክርስቲያን ግን እንኳን ለመጠጥ ለምንም ነገር ቢሆን ተገዥ መሆን የለበትም። ሰው በሁለት ጌታ መገዛት አለመቻሉ ግልጽ ነው።ማቴ 6፥24
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
😡ለመጠጥ የሚገዛ ሰው ለእግዚአብሔር ሊገዛ እንዴት ይችላል ማለትም፦ለመጾም፣ ለመጸለይ፣ ለመስገድ፣ ለመመጽወት፣ መንፈሳዊ በዓላትን ለማክበር ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ የመሳሰሉትን ማከናወን እንዴት ይችላል የመጠጥ ሱስ ፈተና ነውና በደስታና በመከፋት ሰዓት ወደ መጠጥ አትይ ተጠንቅቄ አደርገዋለው አትበል። ስካር በራሱ ኃጢአት ነውና። ሰው እየኝ አላየኝ እያልክም ተደብቀህ አትጠጣ ሰው ባያይህ እግዚአብሔር ያይኃልና‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂በመጨረሻም ስለ መጠጥ በምታስብበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እንግዲህ እንዲህ የምትሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውንም ነገር ብታደርጉ ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ በማለት የተንልገረውን ቃል አስብ።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
Forwarded from Efrata Nega
ለ ስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቃሉ ዳኑ ብሎ ማዳን ሲችል ከሰማይ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ለምን ያንን ሁሉ ስቃይ አይቶ አዳነን?
👌የኔ ተወደጅ ባለማህተብ የስንዱዋ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እግዚአብሔር ለምን ሰው ሆኖ መሰቃየትና የሞትን ፅዋ እንደቀመሰ፤ የእግዚአብሔርን ዕቅዱ በሙሉ መርምሮ የሚያውቅ ባይኖርም በቅዱሳት መጻሕፍት በተገለጠውና በሊቃውንት አስተምህሮ በተተነተነው መሠረት ምክንያቶቹም
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
የነብያቱ ትንቢት ይፈፀም ዘንድ
ቤዛ ለመሆን
አርአያ ለመሆን
አምላክ መኖሩን ለመግለጽ
ፍቅሩን ለመግለጥ
የሰይጣንን ጥበብ ለመሻር
እና የመሳሰሉት ናቸው።
══════◄✣••✥••✣►══════
🖕ከላይ የተገለፁት በቅዱሱ መፅሐፍ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩና ከተፈጠረም በኋላ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነው፡፡ የምድር ማዕከል በሆነች ቀራንዮም መድኃኒትን አደረገ።መዝ 73፥14
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ...እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ።ኢሳ 53፥4-12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።ኢሳ 64፥6
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በርሱ ላይ ነበረ፥በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ኢሳ 53፥5
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ዓለም ከተፈጠረ ዠምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር አኹን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኀጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧል።ዕብ 9፥26
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ከዚህም በረት ያልኾኑ ሌላዎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፥ድምፄንም ይሰማሉ፥አንድም መንጋ ይኾናሉ፥እረኛውም አንድ።ዮሐ 10፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ቁጣዬ ከርሱ ዘንድ ተመልሷልና ዐመፃቸውን እፈውሳለኹ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለኹ።ሆሴ 14፥4
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥በርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።1ኛ ዮሐ 4፥9
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ነገር ግን፥ገና ኀጢአተኛዎች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና፥እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።ሮሜ 5፥8
══════◄✣••✥••✣►══════
🗣ቀደምት አባቶችእግዚአብሔር ይሔን ያደረገበትን ሲናገሩ🔊
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ አምላክ ለምን ሰው መሆን እንዳስፈለገው ሲያስረዳ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከሕይወት የተገኘ ሕይወት፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን ወደዚህ ዓለም የላከው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የእኛን ባሕርይ ይዋሐድ ዘንድ ጌትነቱንም ወደማወቅ ያደርሰን ዘንድ ነው ብሏል፡፡ዮሐ 6፥55፣ ዮሐ 11፥25፣ ገላ 4፥4፣ ኤፌ 2፥16፣ ሐዋ 4፥12
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘአርማንያ 15፥2
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ቅዱስ እለእስክንድሮስም እግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም ይመጣ ዘንድ ከንጽሕት ድንግል ማርያም ሥጋን ይዋሐድ ዘንድ ምን አተጋው በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ፣ በበረት ይጣል ዘንድ፣ ከሴት (ከድንግል) ጡት ወተትን ይተባ ዘንድ፣ በዮርዳኖስ ይጠመቅ ዘንድ ምን አተጋው ሕግ አፍራሽ ጲላጦስ ይዘብትበት ዘንድ፣ በመስቀል ይሰቀል ዘንድ፣ በመቃብር ይቀበር ዘንድ፣ በሦስተኛው ቀን ይነሣ ዘንድ ምን አተጋው በፍዳ ተይዘን የነበርን እኛን ያድነን ዘንድ፣ ለእኛ ብሎ አይደለምንበማለት አምላክ ሰው የሆነበትን ምክንያት በአንክሮ ገልጾታል፡፡ ኢሳ 7፥14፣ፊል 2፥5-9፣1ኛ ቆሮ1፥21-25
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ እለእስክንድሮስ 16፥2-3
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🔔እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢሏችሁ አትመኑ🙅ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ።በማቴ 24፥24
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔊ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ🙅ማር 13፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📢ወንድሞች ሆይ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።ዕብ 3፥12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏እንደተማራችሁት በሃይማኖት ጽኑ፣ ልዩ ልዩ ዓይነት በሆኑ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፣ በዐመጸኖች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፣ ልጆች ሆይ መጨረሻው ሰዓት ነው የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደሰማችሁ 🙆አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቋዋሚዎች ተነሥተዋል፣ ስለዚህም የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን።ቆላ 2፥7 ፣ ዕብ 13፥7 ፣ 2ኛ ጴጥ 3፥6 ፣ 1ዮሐ 2፥18
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ🙅።ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን.......በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል።የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።ማቴዎስ 7፥13-23
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🤷‍♂ስለ እርስዋ አማላጅነት ሲነሣ ቁጭ ብድግ እያሉ የሚቃወሙ እኒህ ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶቻችን ፤ ይህን ጠላትነት ከዘንዶው ካልሆነ በቀር ከየት ሊያገኙት ይችላሉ በቃና ዘገሊላ ማማለዷን ሲቃወሙ የነበሩ ሰዎች፤ አሁን አሁን በሥጋ ሳለች ይሁን እንቀበለው አማልዳለች፤ አሁን ግን የለችም፣ አታማልድም ይሉናል‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🛎ልብ ልንል የሚገባው ሐዋርያትን እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ (ማቴ 28፥20) ያለው ጌታ አሁን እነርሱ በሥጋ ኖረው አይደለም፤ በነፍስ ስላልሞቱ አሁንም ከእርሱ ጋር ስላለ ነው፡፡ ከእመቤታችንም ጋር አብሮ ለመኖሩ በመልአክ አንደበት ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው (ሉቃ 1፥28) ካላት ከእርስዋ ጋር እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለመኖሩ ምን ጥያቄ አለው ⁉️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂እርስዋ በነቢዩ እንደ ተነገረው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች ተብላለችና (መዝ 44፥9) ማንም ከልባችን ሊያሳድዳት አይችልም‼️እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት (ራእይ 12፥14) የታላቁ ንሥር የተባለው አባቷ አብርሃም ነው‼️
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
🗣እኛ የተዋህዶ ልጆች በመዝ 48፥12 ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቍጠሩ በብርታቷ ልባችሁን አኑሩ አዳራሽዋን አስቡ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ እንደ ተባለን ጽዮን የተባለች እናታችን ማርያምን አንድም ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከብበን ንጹህ ነገር ሃይማኖትን በመማር ራሳችንን ከሚነፍሰው የጥርጥር ክህደት ከሚወረውርው የኑፋቄ ቀስት ከሚሰነዝረው የክህደት ፍላጻ ሁሉ መጠበቅ መቻል አለብን የትውልድ ባላደራዎች ነንና‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ 13፥9 ልዩ ልዩ በሆነ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘለዓለም ያው ነው በማለት እንዳስተማረን በአንዲት ርትዕት ሃይማኖት እንድንጓዝ እግዚአብሔር ይርዳን::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🤷‍♂ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንጂ የጌቶች ጌታ አይባልምንደግሞስ ኢየሱስ ክርስቶስ "ብቻውን" ጌታ ነው ማለት ቅዱሳን በፀጋ ጌታ አይባሉም ሊሉን ፈልገው ይሆን
══════◄✣••✥••✣►══════
📖መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራ‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂እመ ብዙኀን ሣራ ጌታዬ ፈጽሞ ሸምግሎአል ስትልኮ "ጌታዬ" ያለችው አብርሃምን ነው።ዘፍ 18፥12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ ጌታዬ ሙሴ ሆይ ከልክላቸው አለው።ዘኁ 11፥28
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ነብየ እግዚአብሔር ነብዩ ኢያሱ መምህሩን ሊቀ ነብያት ሙሴን "ጌታዬ" ብሎ የጠራው የእግዚአብሔርን ጌታነት ሳያቅ ቀርቶ ነውንደግሞስ "ጌታዬ" ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነውአለው ያለውስ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መልአከ እግዚአብሔር መሆኑን እያወቀ "ጌታዬ" ማለቱ ስሕተት ነውን ፈጽሞ። ኢያ 5፥14
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ስለሆነም አምላካችን እግዚአብሔር በባሕርዩ "ጌታ" መባሉ፤ ቅዱሳን ደሞ በጸጋ "ጌታ" መባላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👍እኛ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ግን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ ነው ብቻ ሳይሆን የጌቶች ጌታ፥ የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ብሎም እግዚአብሔር ነው ብለን እናምናለን፥ እንታመናለን።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ቃልም እግዚአብሔር ነበረ የሚለውንና በደምም የተረጨ ልብስ ተጎናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል ስለሚል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔር ማለታችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው።ዮሐ 1፥1፣ራዕ 19፥13
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🤷‍♂ኦርቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ ብቻ ሳይሆን "የጌቶች ጌታ፥ የነገስታት ንጉሥ" ስትል የተሐድሶ መናፍቃን ግን የጌቶች ጌታ ሳይሆን "ጌታ" ብቻ ነው የሚባለው ይላሉ።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል።1ኛ ጢሞ 6፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እነዚህ በጉን ይወጋሉ፥ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ። ራዕ 17፥14 ይሔን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ መከተላችን የተገባ ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ምንጭ:- ዘማርያም ዘለቀ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
📖ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።ዕብ 10፥24-25
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።ፊሊ 3፥20
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🛎🛎የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣በዓለም ፍጻሜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥአንን ደግሞ በግራው ለይቶ እንደየሥራችን ሊፈርድ ይመጣልና ምልክቶቹን እናውቅ ዘንድ በወንጌል ተጽፎልናል፡፡ጌታችን ኢየሱስም ክርስቶስም በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ በነበረበት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ስለዳግም ምጽአት ጥያቄ አቀረቡለት፤
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙋ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል የመምጣትህና የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነውጌታችንም ኢየሱስም ክርስቶስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ጦርነትን፥ የጦርነትንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠንቀቁ፤ አትደንግጡ፤ ነገር ግን ፍጻሜው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣሉ፤ በየሀገሩም ረኃብ፣ ቸነፈርም፣ የምድርም መናወጥም ይሆናል፡፡ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ ያን ጊዜም ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፡፡ ያንጊዜም ብዙዎች ሃይማኖታቸውን ይለውጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፡፡ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ከዐመጽም ብዛት የተነሣ ፍቅር ከብዙዎች ዘንድ ትጠፋለች፡፡ እስከ መጨረሻው የሚታገሥ ግን እርሱ ይድናል፡፡ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ምስክር ሊሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ያንጊዜም ፍጻሜ ይደርሳል።ማቴ 24፥3-14
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የነገራቸው የዓለም ፍጻሜ ምልክት ለደቀ መዝሙርቱ ቢሆንም ትንቢቱ ግን በእኛ ትውልድ እየተፈጸመ መሆኑን በሚገባ ልናውቅና ተረድተንም የሚጠበቅብንን ጥንቃቄ መፈጸም ያስፈልጋል፡፡🛎🛎
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
💖ፍቅር ካለ እግዚአብሔር አለ።እግዚአብሔር ካለ ደግሞ ሁሉ ነገር አለ። ፍቅር ማለት ፍጹም ሰው ፈልጎ ማግኘትና መውደድ ሳይሆን፣ ጎደሎውን ሰው ፍጹም አድርጎ መቀበል ነው።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሰማህ ወዳጄ እግዚአብሔር አምላክ ከኛ ለመሸሽ በቂ የሆነ ምክንያት እያለው፣የታገሰን፣በደላችን ደስ አሰኝቶት ሳይሆን ስለሚወደን ነው።ማንም ሰው፣ፀሐይን ያለችበት ድረስ ሄዶ ለመንካት ቢሞክር መቅለጡ ግድ ነው።ነገር ግን ያለንበት ድረስ መጥታ ታሞቀናለች። እግዚአብሔር አምላክንም፣ማንም፣በመለኮቱና በአምላክነቱ፣ ሊያየውና በግርማው ፊት ሊቆም አይችልም። ነገር ግን ላይ መሄድ ለማንችለው፣ታች ድረስ ሊፈልገን መጥቶ፣ በፍቅሩ ፀሐይ አሞቀን።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏መግደል የሚችለው ሞተ።ኃይልም ፍቅርም ያለው አምላክ ከኃይል ይልቅ በፍቅር ተደሰተ።ማንም የራሱን በደል ተሸክሞ ተጠያቂ መሆን በማይፈልግበት ዓለም ላይ ስለ የሁላችንን በደል ተሸክሞ ተጠያቂ ሆነልን።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🛎የማንቂያ ደወል ድምፅ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🛎አሕዛብ ሙስሊም ወገኖቻችን ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በአንደበቱ ‹እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ› ብሎ የተናገረበትን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሳዩን ›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ይደመጣሉ፡፡🙋በጥያቄያቸው መሠረት ራሱ ጌታችን በቃሉ እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ ብሎ እንደተናገረና ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ በደንብ እናሳያቸዋለን።
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ማታ ከ2 ሰዓት ጀምሮ ይጠብቁን❗️🏃‍♂
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
Forwarded from Efron
🛎🛎ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው❗️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👆የቀጠለ👆
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
6ኛ. ጌታችን እኔና አብ አንድ ነን ያለውንስ ቃል እንዴት ተናገረው ቢሉ ፊሊጶስ አብን አሳየንና ይበቃናል ስላለው ነው፡፡ ጌታችን ለዚህ የፊሊጶስ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እንዲህ ነው ያለው፡-አንተ ፊልጶስ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ አንተ ‹አብን አሳየን› ትላለህ› እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል፡፡ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ፡፡ ዮሐ 14፥8-10፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ ማለቱኮ ከአብ ጋር ፍጹም አንድ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ለመሆኑ ራሱ አምላክ ካልሆነ በቀር የትኛው ፍጡር ነው ራሱን ከአምላኩ ጋር አንድ አድርጎ እንዲህ ማለት የሚችል
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
7ኛ. አይሁድ ራሱን አምላክ አድርጓል የሚለውን ክሳቸው ይዘው ጌታችንን እያዳፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ከወሰዱት በኋላ ቀያፋም ማንነቱን ሲጠይቀው ጌታችን የሰጠው መልስ የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው አምላክ እንደሆንኩ ይኸው አንተም በአንደበትህ መሰከርክ የሚል ነበር፡፡ እንዲሁም ለፍርድ ስመጣ ታያላችሁ ነበር ያለው፡፡ሊቀ ካህናቱም ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው፡፡ ኢየሱስም አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው፡፡ በዚያን ጊዜ ሊቀካህናቱ ልብሱን ቀዶ ተሳድቧል፣ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ለምን ያስፈልጉናል አለ፡፡ ማቴ 26፥63-65፡፡ በዚህ ክፍለ ንባብ መሠረት ጌታችን ለሊቀ ካህናቱ የሰጠው መልስ እኔ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንሁ አንተም ራስህ እየመሰከርክ ነው የሚል ነው፡፡ በዚያውም ለፍርድ በታላቅ ግርማ ሆኖ እንደሚመጣ ነገረው፡፡ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ልብሱን ያስቀደደው ጉዳይ፣ አይሁድም ጌታችንን ለስቅላት ሞት ያበቁት ምክንያት ጌታችንን ራሱን አምላክ አድርጓል ብለው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
8ኛ. በዮሐ 1፥52 ላይ ጌታችን ለናትናኤል እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ ብሎታል፡፡ ይህም ማለት መላእክት የእግዚአብሔር እንደሆኑ እንደተናገረ እናነብባለን፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነውና የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ በማለት ጌታችን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ነገረን፡፡ ማቴ 13፥41፡፡እንግዲህ ጌታችን በቃሉ የእግዚአብሔር መላእክት ያላቸውን ነው በኋላ ላይ ለራሱ አድርጎ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል ያለው፡፡ ጌታችን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ እንዴት የእግዚአብሔር የባሕርይው የሆነውን ነገር ለራሱ ያደርጋል ቅዱስ ጳውሎስም በ2ኛ ተሰ 1፥6 ላይ ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ በማለት መላእክት የኢየሱስ ክርስቶስ መሆናቸውን ገልጦልናል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
9ኛ. በዮሐ 20፥28 ላይ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታዬ፣ አምላኬም ብሎ ጠርቶታል፡፡ ቶማስ ጌታዬ፣ አምላኬም ሲለው ጌታችን አምላክ ባይሆን ኖሮ አምላኬ ለምን ትለኛለህ ብሎ መሳሳቱን ነግሮ ያርመው ነበር፡፡ ነገር ግን ቶማስ የጌታችንን ትክክለኛ ማንነቱን ስለነገረው ጌታችን የሰጠው መልስ ስላየኸኝ አምነሃል፣ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው የሚል ነው፡፡ቀደም ብለን እንዳየነው በዮሐ 13፥13 ላይ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ፤ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ ብሎ እንተናገረው ሁሉ አሁንም ቶማስ ጌታዬ አምላኬ ሲለው ጌታችን ስላየኸኝ አምነሃል በማለት አምላክነቱን ሰዎች በማወቃቸው ይህን ዕውቀታቸውን አልተቃወመም፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
10ኛ. በዮሐ 10፥17 ላይ ጌታችን ስለራሱ ሲናገር ነፍሴን በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ብሏል፡፡ ማንም ንጹሕ አእምሮ ያለው ሰው ይህን እውነታ መቀበል አለበት-ማንም ቢሆን ከሰው ወገን የገዛ ነፍሱን በራሱ ሥልጣን ከሥጋው መለየት የሚችል ማንም የለም፣ ሊኖርም አይችልም፡፡ ነፍሱን በገዛ ፈቃዱ መለየት የሚችለው እርሱ የአዳምን ሥጋ የተዋሐደው ሰውም አምላክም የሆነው መድኅን ዓለም ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ወደዚህች ምድር የመጣበትንም ዓላማ ሁሉን ከፈጸመ በኋላ ተፈጸመ አለ፣ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ ተብሎ ነው የተጻፈው፡፡ ዮሐ 19፥30፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👌ሐዋርያትስ ስለ ጌታችን አምላክነት ምን አሉ የሚለውን ቀጥሎ እናያለን
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🛎🛎ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👆የቀጠለ👆
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ለመሆኑ በወቅቱ አብረውት በዋለበት ውለው ባደረበት አድረው በኋላም እርሱ ራሱን የገለጠላቸው የከበሩ ሐዋርያትስ ስለ ጌታችን አምላክነት ምን አሉ የሚለውን ቀጥሎ እናያለን
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
1ኛ. ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ ፈጣሪ እንደሆነ የሐዋርያት ምስክርነት
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል፡፡ ራዕ 4፥10

📖የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል፡፡ቆላ 1፥15-16።በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌ 2፥10
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
2ኛ. ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ የነቢያትና የሐዋርያት ምስክርነት
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ሐዋ 20፥28።ቤቴ የጸሎት ቤት ናት፡፡ ማቴ 21፥13፣ ማር 11፥17፣ ሉቃ 19፥46፡፡

💁‍♂በ1ኛ ቆሮ 15፡9 ላይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ በማለት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር እንደሆነች ሲገልጥልን፤ በተጨማሪም ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቴዎስ ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው በማለት መስክሯል፡፡ 1ኛ ጢሞ 3፥15፡፡

📖ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረታት ራሱ እግዚአብሔር ነውና በማቴ 16፡18 ላይ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም በማለት ቤተ ክርስቲያን የእርሱ እንደሆነች ነገረን፡፡ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጌታችን ቤተ ክርስቲያኔ ብሎ ጠራት፡፡ ለዚህም ነው በዓለም ሁሉ ያለችውን አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል በማለት የጻፈው፡፡ ሮሜ 16፡16፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🛎ቀጥሎ የተዘረዘሩት የሐዲስ ኪዳን ጥቅሶች ደግሞ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን ግልጽ አድርገው የሚናገሩ ናቸው፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ጌታ ሆይ❗️ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው። ዕብ 1፥10

📖ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል። ራዕ 1፥8

📖ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ። ዕብ 1፥6

📖ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ። ፊል 2፥10

📖እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። 1ኛ ዮሐ 5፥20

📖ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር ፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና። ዮሐ 2፥25፤ 1ኛ ቆሮ 4፥5

📖መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።ዮሐ 10፥11

📖ደግሞም ኢየሱስ ‹እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም› ብሎ ተናገራቸው።ዮሐ 8፥12

📖ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።ሉቃ 24፥51

📖ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል።የሐዋ 1፥11

📖እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።ማቴ 28፥6

📖ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።ዮሐ 5፥22

📖እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።ራዕ 22፥12

📖ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። ራዕ 1፥17-18

📖አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።ራዕ 2፥23

📖ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ 1ኛ ተሰ 3፥12)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👌ይቀጥላል‼️
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
🛎ለሙስሊሞች መልስ የመጨረሻ ክፍል❗️
💁‍♂የመሢሑን መወለድና የእስራኤልን መዳን በተስፋ ይጠባበቅ የነበረው አረጋዊው ስምዖን ጌታችን በተወለደ በ40 ቀኑ በቤተ መቅደስ እንዳገኘው ታቅፎ ይዞት ሣለ ስለ ሕፃኑ ክርስቶስ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናገረ እነሆ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሟል።ሉቃ 2፥44

🗣ይህ ትንቢት ከተነገረ ከ30 ዓመት በኋላ ትንቢቱን ጌታችንም ራሱ ደግሞ ሲናገረው የማያዩ እንዲያዩ፣የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ አለ ዮሐ 9፥39።ይህ የአረጋዊው ስምዖን እና የጌታችን ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው።መድኅን ዓለም ክርስቶስ ለብዙዎች ለመውደቃቸው ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ሆኖ ወደዚህች ምድር ለእውነተኛ ፍርድ መጥቷል።

🤷‍♂ይህን ከትውልዱ ማን አስተዋለ አሕዛብ ዐይነ ልቡናቸው ታውሮ እያዩ የማያዩ ሆኑ እንጂ የክርስቶስ አምላክነት ለመረዳት የራሳቸው መጽሐፍ ማለትም ቁርአናቸው በቂ መነሻ ይሆናቸው ነበር።እንደ እስልምና አስተምህሮ አላህ ዓለማትን በቃሉ ነው የፈጠረው። ልብ በሉ❗️አላህ ዓለማትን በቃሉ ፈጠረ።በቁርአኑ ሱረቱ መርየም 19፥34 ላይ ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፣ ያ በእርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ነው ይላል።በሌላም ቦታ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ መንፈስ ብቻ ነው ይላል ሱረቱ አል-ኒሳእ 4፥171፡፡ዒሳ የአላህ ቃል እንደሆነ ሁሉም ሙስሊሞች ያውቃሉ፡፡

💁‍♂እንግዲህ አላህ ዓለማትን በቃሉ ከፈጠረ ዒሳም የአላህ ቃል ከሆነ ዒሳ ማን ሆነ ማለት ነውግልጽ ነው ዒሳ ፈጣሪ ነው።የዒሳን ፈጣሪነት በተግባርም ከቁርአኑ ላይ ማየት እንችላለን።በሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፥110 ላይ ዒሳ በአላህ ፈቀድ ሙታንን እንዳሥነሣ፣ለምጻሞችን እንዳነጻ፣ዕውራንን እንዳበራ፣ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ሥውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ዐይን እንደፈጠረለት፣ከጭቃ የወፍ ቅርጽ ሠርቶ በላዩ ላይ እፍ እንዳለበትና ሕይወት እንደዘራባት ቁርአኑ ይጠቅሳል።

እዚህ ጋር ሁለቱን ነጥቦች በደንብ ማንሳት እፈልጋለሁ።ዒሳ በአላህ ፈቃድ ከአንደበቱ በወጣው እስትንፋስ ብቻ ሕይወትን ፈጥሯል።ሺህ ጊዜ በአላህ ፈቃድ ቢፈጸምም የትኛው ፍጡር ወይም ነቢይ ነው በእስትንፋሱ እፍ ብሎ ሕይወትን መፍጠር የሚችለውበአላህ ፈቃድ የሚለው ያስማማናል ችግር የለውም።በመጽሐፍ ቅዱስም በግልጽ እንደተጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቴን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁ ብሏል ዮሐ 6፥38።አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በፈቃድ አንድ ስለሆኑ የአብ ፈቃድ ማለት የራሱ የወልድ ፈቃድ ነው።

👌ስለዚህ በቁርኑ ላይ በአላህ ፈቃድ የሚለው አገላለጽ በእኛም ጋር ችግር የለውም።ሲጀመር እንደእስልምናው አስተምህሮ አላህ እንደ ፈጣሪነቱ ያለ እርሱ ፈቃድ የሚሆን ምንም ነገር የለም። ችግር አለው እያልን ያለነው ግን ዒሳ ነቢይ ነው ከተባለ እንዴት ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ሥውር ሆኖ ለተወለደው ሰው ዐይን ፈጠረለት ሺህ ጊዜ አላህ ቢፈቅድለት እንዴት ነቢይ በእስትንፋሱ እፍ ብሎ ሕይወትን መፍጠር ይችላል
አላህ የመፍጠርን ሥልጣን ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ የእርሱ ፈጣሪነት ላይ ነው በትልቁ ጥያቄ የሚነሳበት።ሕይወትን መፍጠር የሚችለው እርሱ አምላክ ብቻ ነው፡፡ነቢይ ጸጋ ከተሰጠው ተአምር ማድረግ ይችላል እንጂ የመፍጠር ሥልጣን ፈጽሞ ሊኖረው አይችልም።

👍አሕዛብ ማስተዋል ከቻሉ ቁርአናቸው በራሱ በቂ መነሻ ሊሆናቸው ይችላል። አላህ ዓለማትን በቃሉ ከፈጠረ፣ዒሳም የአላህ ቃል ከሆነ ዒሳ ዒሳ ፈጣሪ ነው❗️ ይህንንም የዒሳን ፈጣሪነት በቃልም በተግባርም ከቁርአኑ ላይ ማረጋገጥ ይቻላል።ያ ማለት ግን እኛ ክርስቲያኖች የክርስቶስን አምላክነት ለማወቅ የቁርአን ምስክርነት ያስፈልገናል እያልኩ አይደለም።ቁርአኑ በሌላም በኩል የክርስቶስን መሰቀልና ዓለምን ማዳን በመካድ ከራሳቸው ከሰቃዮቹ ከአይሁድ በላይ እኔ አውቃለሁ የሚል የሰይጣንንና የሰዎችን ከንቱ አስተሳሰብን ያየዘ መጽሐፍ ነው።ደግሞም በሌላ በኩል ቁርአኑ ስለ ኢየሱስ ሲናገር በሱረቱ መርየም 19፥33 ላይ ሰላምም በእኔ ላይ ነው፣በተወለድሁ ቀን በምሞትበትም ቀን ሕያው ሆኜ በምቀሰቀስበትም ቀን.. እያለ ሲወናበድ እናየዋለን፡፡

💁‍♂ወደ ማጠቃለያው ሀሳብ ልመለስና የአረጋዊው ስምዖን እና የጌታችን ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው።ክርስቶስ ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ሆኖ ወደዚህች ምድር ለእውነተኛ ፍርድ መጥቷል።ጌታችን የማያዩ እንዲያዩ፣ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ ነው ያለዉ ዮሐ 9፥39።እርሱም ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም (15፥13) እያለ ፍቅሩን በቃል ገለጸ፤እስከ መስቀል ሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ በመስጠትም ፍቅሩን በተግባር ገለጸ።

🗣ይህን ፍቅሩንና ውለታውን ማስተዋል ላልፈለገ ደግሞ በጊዜው ጊዜ ፍርዱንና ቁጣውን ይገልጻል።ይህን ከትውልዱ ማን አስተዋለየከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትም ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ፡፡እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል (1ኛ ጴጥ 2፥24)፣ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል (ሮሜ 5፥8)፣ፍቅርም እንደዚህ ነው፤እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም (1ኛ ዮሐ 4፥10) እያሉ የተናገሩትን ነገር ከትውልዱ ማን አስተዋለ እነሆ ቅዱሳን ነቢያትስ ከክርስቶስ መምጣት በፊት ስለእርሱ እንዲህ ሲሉ የተናገሩትን ትንቢት ከትውልዱ ማን አስተዋለ

📖የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፣ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፣እኛም አላከበርነውም፡፡በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው፡፡እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ስለ በደላችንም ደቀቀ፤የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን፡፡እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፣በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፣እንዲሁ አፉን አልከፈተም።በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፨ኢሳ 53፥1-12
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
📖ስለ ዓለም መበዥት ልጇ የተሰቀለባት የመጀመሪያም የመጨረሻም እናት
••●◉ ✞ ◉●••
ከሄሮድስ የሞት አዋጅ ታስጥለው ዘንድ ዓመታትን ስለእሱ ስትል ወደ በረሃ ተሰዳለች።ወንበዴዎች እንዳይነጥቋት፤ ዘራፊዎች እንዳይወስዱባት እልፍ ቀናትን በሰቀቀን አሳልፋለች።30 ዓመታትን ክርስቶስ የሚለውን ስም ከእርሷ ውጪ ማንም አያውቅም።ልጇ ታምራትን ሳያደርግ፤ሙት ሳያነሳ፤ሽባ ሳይተረትር ሰማያዊ መናን እና ፅዋን ከሰማይ አውርዶ ሳይመግብ በልቧ ያነገሰችው ውድ ልጇና ጌታዋ ነው።ዓለምን በመዳፏ የያዘውን ልጇን በጀርባዋ ተሽክማ ይዛ የተሰደደቸውን፤ ከበረሃ ወንበዴ በሰቀቀን የጠበቀችውን ልጇን ጲላጦስ በበርባን ምትክ ሞት ፈረደበት።በስስት የምትመለከተውን ገፁን በደም ለወሱት።
••●◉ ✞ ◉●••
በጀርባዋ ተሸክማው ዘመናትን የተሰደደችው አካሉ በሮም ወታደሮች ግርፋት ተበጣጠሰ።በእሱ ሞት ፍጥረት ነፃ ሲወጣ ድንግል ማርያም ግን በእናትነቷ አንጀቷ አነባች።የተከተሉት ሁሉ ሲበተኑ የወለደችው እናቱ ግን እስከመጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ ሽቅብ ልጇን ከተቸነከረበት መስቀል ሆኖ ተመለከተችው።ቅዱሱን ልጇን ርኩሳኑ ገደሉት።አንዳች በደል ሳይገኝበት በበደለኞች እጅ ተገረፈ።ሆሳዕና ብለው ያነገሱትን ጌታ ይስቀል ይሰቀል ይሰቀል ብለው ፈረዱበት።ፍርደኛውን አርነት ያወጣው ዘንድ እሱ ፍርድን ተቀበለ።በስስት ጥቂት በጥቂት ያሳደገችውን ብቸኛውን ልጇን ለህዝብ ሁሉ ድህነት ለሞት ተላልፎ ሲሰጥ ሞቱን በእንባ አጀበችው።
══════◄✣••✥••✣►══════
እንኳን ለቅዳሜ ስዑር በሰላም አደረሰን❗️
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
📖በትንሣኤሁ ቅድስት አግብኦ ለብእሲ ዳግመ ውስተ ገነት/ልዩ በሆነች መነሳቱ ሰውን እንደገና ወደ ገነትአገባው::ቅ/ ኤፍሬም
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ይግብሩ በዓለ ሰማያት ይግብሩ በዓለ ደመናት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሃጺባ በደመ ክርስቶስ።ቅ/ያሬድ
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሞቱን በሚመስል ሞት ከርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤዉን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡ ሮሜ 6፥5
••●◉ ✞ ◉●••
🙏በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንልን ፡፡እግዚአብሔር በህመም የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ምህረትን ይላክላቸው፡፡የጎደለንን እግዚአብሔር ይሙላልን።እንደ ሰደድ እሳት በአለም ዙሪያ የሰው ነፍስ እያጠፋ ያለውን የጊዜውን ክፍ መንፈስ በእግዚአብሔር በበረታው ክንዱ ተመቶ ከእግራችን ስር ያድርግልን።ስንዱዋን አመቤት እምዬ ተዋህዶ ቤታችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን።ባለ ቀሰተ ደመነዋ ሀገር ኢትዮጵያን ክፍዋን አያሳየን🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
2025/10/25 17:01:27
Back to Top
HTML Embed Code: