Telegram Web Link
ወምድረኒ ትገብር ፋሲካ
<unknown>
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ/2/ 
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ /4/ 

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ምደር ጸዳች ሐሴት አደረገች /2/ 
በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች/4/

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
👍1
🦿ቅዱሳን ሥዕላት 📜
••●◉ ✞ ◉●••
🗣የተሃድሶ መናፍቃን ቅዱሳን ሥዕላትን አይቀበሉም፤ በሥዕል ፊትም አይጸልዩም፤ ጭራሽም ሥዕልን ማክበር ጣዖትን እንደ ማምለክ ይቆጥሩታል እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጽሐፍትን መሠረት አድርገን ለቅዱሳት ሥዕላት ተገቢውን ክብር እንሰጣለን።
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂በዘፀ 20፥3 ላይ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸውም፣ አታምልካቸውም የሚለውን ትእዛዝ የሰጠው እግዚአብሔር አምላክ በዘፀ 25፥16 ላይ ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ስራ ብሎ ሙሴን አዝዟል ይህም ቅዱሳት ሥዕላት ቁጥራቸው ከጣዖት እንዳልሆነ የሚያመለክት ነው እግዚአብሔር አምላካችን የሰው ልጅን ጣዖት እንዲሰራ አያዝምና ከዚህም በተጨማሪ እስራኤል በኃጢአታቸው ምክንያት በእባብ መንጋ ሲነደፉ በዘኁ 21፥8 ላይ እባብ ሰርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፣ የተነደፈውንም ሁሉ ሲያየው በሕይወት ይኖራል ሲል አዝዞት ነበረ ነገር ግን ይህ እንደ ጣዖት አምልኮ አልተቆጠረም እንዲያውም በዘኁ 21፥9 ላይ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ ተብሎ ተጽፏል ጌታችንም በዮሐ 3፥14 ላይ ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለው እባብ የእርሱ መሰቀል ምሳሌ መሆኑን አስተምሯል።
••●◉ ✞ ◉●••
🔊 ንጉሡ ሰሎሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በሠራ ጊዜ በ1ኛ ነገ 6፥23 ላይ እንደምናነበው በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆኑ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ በዚህ የተነሳ እግዚአብሔር መምለኬ ጣዖት ነህ አላለውም እንዲያውም በሌሊት ተገለጠለት እንጂ ንጉሥ ሰሎሞንም የኪሩቤልን ሥዕል ብቻ ሳይሆን ''የዘንባባ ዛፍ፣ የፈነዳም አበባ ምስል ቀርጾ ነበር'' /1ኛ ነገ 6፥29-35/ ነገር ግን ይህ እንኳን የጣዖት ምስል አስቀረፀ አላስባለውም።
••●◉ ✞ ◉●••
እኛ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና የአክብሮት ስግደት ይገባቸዋል እንላለን እንጂ አናመልካቸውም የአምልኮ መፈጸሚያዎች ናቸው እንላለን እንጂ የአምልኮ ስግደት አንሰግድላቸውም፤ ሥዕሎቹ በራሳቸው አንዳች ምስጢራዊ ኃይል ኖሯቸው ሳይሆን የሥዕሉ ባለቤት በሥዕሎቹ አማካኝነት ኃይሉን፣ ተአምሩን ይገልጣል ብለን ግን እናምናለን ሙሴ በበትሩ ባሕረ ኤርትራን ከፍሏል፣ ኤልሳዕ በኤልያስ ልብስ ዮርዳኖስን ከፍሎ ተሻግሯል፣ የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ ድውያንን ፈውሷል፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ አጋንንትን አውጥቷል... እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን በራሳቸው አንዳች ኃይል ኖሯቸው ሳይሆን የባለቤቱን ቅድስና ያስገኘላቸው ጸጋ ነው።
••●◉ ✞ ◉●••
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስተምረን እመቤታችን ጌታን እንደታቀፈች አድርጎ የመጀመሪያውን ሥዕል የሳለው ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው ይህም ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ሥዕላት በቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ቦታ ያመለክተናል ከዚህም በላይ በኢየሩሳሌም፣ በባዛንታይን፣ በኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በሌሎችም ሀገሮች የጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሾች በቁፋሮ ሲገኝ ቅዱሳን ሥዕላትም ይገኛሉ ይህም ሥዕሎችን ለመንፈሳዊ አገልግሎት መጠቀም ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ የነበረ መሆኑን ያሳያል።
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂በ7ኛው መ/ክ/ዘ ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ አሁን የተሃድሶ መናፍቃን የያዙትን ሃሳብ ይዘው የተነሱ ሰዎች ነበሩ እነዚያኞቹ ከዚያም አልፈው ቅዱሳት መጻሕፍትን ከምድረ ገጽ ለማጥፋትም ተነስተው ነበር እነዚህ ጸላዕያነ ሥዕላት "ኢኮኖማኺያ" በመባል ይታወቁ ነበር ትርጉሙም "ሥዕላትን የሚጠሉ" ማለት ነው ይህ አስተሳሰብ በ720 ዓ/ም አካባቢ ተነስቶ እስከ 843 ዓ/ም ድረስ ለአንድ መቶ አመታት ያህል ቤተ ክርስቲያንን ሲያወዛግብ ቆየ፤ ጉዳዩ የበለጠ እንዲሰፋ ያደሰገው ደግሞ ሥዕሉን ከባለ ሥዕሉ በላይ የሚያከብሩና የሚያመልኩ ክርስቲያኖቼ/ኢኮኖላትሪያ/ መፈጠራቸው ነው።
••●◉ ✞ ◉●••
🗣በዘመኑ የነበሩት ነገስታት የሥዕል አጥፊዎችን ሀሳብ በመደገፋቸው ለ700 ዓመታት የተሰበሰቡ አያሌ ጥንታውያን ሥዕሎች እንዲጠፉ ተደረገ ሁኔታው ግን ሊበርድ አልቻለም ሥዕሎች አማልክት አይደሉም፣ ነገር ግን ሊከበሩ ይገባቸዋል የሚለው ሃሳብ እያየለ መጣ በዚህም ምክንያት ችግሩ በተነሳበት በባዛንታይንና ሮሜ አካባቢ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በ787 ዓ/ም ጉባዔ አድርገው "ለቅዱሳት ሥዕላት ክብር እና ሰላምታ ይገባል፤ ለእነርሱ የሚደረግ ክብር እና ሰላምታ ሁሉ ለሥዕሉ ባለቤት የሚደረግ ነው እነርሱን የሚያከብር ሁሉ በሥዕሉ ላይ የተገለጠውን ነገር ማክበሩ ነው" በሚል ወሰኑ።
••●◉ ✞ ◉●••
👌ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን የአባቶቻችንን ስርአት ተከትላ ለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና የአክብሮት ስግደት ትሰጣለች እንጂ የተሃድሶ መናፍቃኑ በሀሰት እንደሚሉት የጣዖት አምልኮ አይደለም ስለዚህ ከተሃድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርት መጠንቀቅና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለማንኛውም ጥያቄ ምላሽ ያላት መሆኑን ልናውቅ ይገባል።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
💁‍♂አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ " አሉት።
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን።ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን ሰው ሁን ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው።ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።
••●◉ ✞ ◉●••
📜ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው። "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል
••●◉ ✞ ◉●••
🙏የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት ይባላል ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን
••●◉ ✞ ◉●••
👌በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን በፍጹም አይሆንም የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂አባ ጊዮርጊስ ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣ ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ ይል የለምን ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
💁‍♂አላመሰግንም ከየት የመጣ ነው
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አሰምታም እንዲህ አለች አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል የሰላምታሽ ድምጽ ወደኔ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ ዘሏልና ሉቃ ፩፥፳፰-፵፫
••●◉ ✞ ◉●••
🙌ልብ በሉ ሰላምታዋ መንፈስ ቅዱስን የሚሞላ ሴት እንዴት የተመረጠች ናትበመንፈስ ቅዱስ የተሞላች አረጋዊት ሴት አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የምትባል ሴት እንዴት አይነት መመረጥ ነው በኤልሳቤጥ ብቻ አይደለም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንኑ ቃል አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሏታል ምን አይነት መመረጥ ነው
••●◉ ✞ ◉●••
🧑‍💻ሰላምታዋን በሰማ ጊዜ በማሕጸን ያለ ጽንስ እንኳ በደስታ የዘለለ ምን አይነት ቅድስና ነው🤷ታዲያ በመንፈስ ቅዱስ ተመልታ ኤልሳቤጥ ካመሰገነች ድንግል ማርያምን ፕሮቴስታንት አላመሰግንም የሚል ምን ተሞልቶ ነው
••●◉ ✞ ◉●••
📖በመልአክ አንደበት ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንች ጋር ነውና፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የተባለችን እናት እኛም እንደመልአኩ እናመሰግናታለን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🔔እኛስ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ እመቤታችንን እንዳመሰገነቻት ኤልሳቤጥ እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እናመሰግናታለን መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን እንድትመሰ ን ሲያደርግ አይተናልና፡፡ የጌታዬ እናት እንላታለን በመንፈስ ቅዱስ ሆና የጌታዬ እናት አንች ወደኔ ትመጭ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል፤ አንች ከሰሰቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፤ የማህጸንሽ ፍሬ የተባረከ ነው.... እያልን እናመሰግናታለን ይህን ያናገሰ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በግልጽ አይተናልና፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🔊🔊🔊ሰማያዊ መልአክና ምድራዊት ሴት ተባብረው በአንድ ቃል በአንድ መንፈስ ቅዱስ ያመሰገኗትን አላመሰግንም የሚሉ በምን መንፈስ ሆነው ነው መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን አስመሰገነ እንጅ ሲከለክል አላየንም፡፡ አላመሰግንም የሚሉ ከምን እንዳገኙት እንኳ አይነግሩንም ሰይጣንና ክፉ የገንዘብ ፍቅር ክብሯን ሸፍኖባቸዋልና::
••●◉ ✞ ◉●••
📃 እኛ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተረዳነው እንደ መልአኩ ቅዱክ ገብርኤልና ቅድስት ኤልሳቤጥ እናመሰግናታለን፡፡ የአባቶቻችን አምላክ ፍቅሯን በልባችን ጣእመ ውዳሴዋል በከንደበታችን ያብዛልን።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 💒💒💒💒💒💒
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዶክተር ወዳጀነህ ምስክርነት ስለ ድንግል ማርያም ══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
🔊🔊🔊ምፅዋት በቅዱሱ መፅሐፍ
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሰው ወጥቶ ወርዶ ደክሞ ካገኘው ላይ የሚያደርገው በጎ ስጦታ ነው:: ምጽዋት ብልና ዝገት በማያበላሸው ሌቦችም በማይሰርቁት ስፍራ በሰማይ መዝገብ ማከማቸት ነው:: ምጽዋት ሲሰጡ ብድራትን ሁሉ የሚከፍል እግዚአብሔር መሆኑን አምነን ሊሆን ይገባል::
••●◉ ✞ ◉●••
📃ይህንም እላለሁ። በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።2ኛቆሮ 9፥6
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።ምሳ 19፥17
••●◉ ✞ ◉●••
📖የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ።ሉቃ 14፥12
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።ሮሜ 12፥8
••●◉ ✞ ◉●••
🔔ምጽዋት ሁሉም በአቅሙ ሊፈጽመው የሚገባ በጎ ተግባር ነው::
••●◉ ✞ ◉●••
📖ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር።ማር 12፥41
••●◉ ✞ ◉●••
📃በእምነት የሚፈጽሙት ምጽዋት ሰማያዊ ዋጋ ያለውና የተትረፈረፈ የእግዚአብሔርን በረከት የሚያስገኝ ነው::
••●◉ ✞ ◉●••
📃ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።ምሳ 11፥24
••●◉ ✞ ◉●••
📖ለድሀ የሚሰጥ አያጣም ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።ምሳ 28፥27
••●◉ ✞ ◉●••
🔊ዮአስም ካህናቱን። ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉ፥ካህናቱ እያንዳንዱ ሰው ከሚያመጣው ይውሰዱ በመቅደስም ውስጥ የተናዱትን ይጠግኑበት አላቸው።2ኛ ነገ 12፥5
••●◉ ✞ ◉●••
📖እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ። ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።ሐዋ 10፥4
••●◉ ✞ ◉●••
📃ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ማቴ 25፥34
••●◉ ✞ ◉●••
📖ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።መዝ 40፥1
••●◉ ✞ ◉●••
📃ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ ኃጢአትህንም በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት አስቀር።ዳን 4፥27
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
አበባየሆሽ
የአዲስ አመት መዝሙር
🌼🌼እንኳን ለ2014 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌼🌼
••●◉ ✞ ◉●••
📌 አዲሱ ዓመት እምነታችችን የሚያፀናልን ልብ ሰላምን /ጤና , ብልፅግና , እድገትን , መከባበር መተሳሰብ , አንድነትን የሚጠነክርበት ዓመት እዲሆንልን እመኛለው !
  ••●◉ ✞ ◉●••
እንዲሁም የጥላቻ , የዘረኝነት , የግጭት ስሜት የምናስወግድበት ዓመት ይሁንልን
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 💒💒💒💒💒💒
​​​​🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🗣በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
📖በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።መዝ 64፥11-12
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🔔እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን🔊
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💁‍♂መልካም አዲስ ዓመት🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን 🌼
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒@Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
Audio
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🔔እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን🔊
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💁‍♂መልካም አዲስ ዓመት🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
💁‍♂ይሔን የቤተክርስቲያን የቆየ መዝሙር ተጋበዙልኝ🙏
🌼 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን 🌼
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒@Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💁‍♂ከጠላቶችህ ጋር በሰላም ኑር ነገር ግን ይህን የምልህ ከግል ጠላቶች ጋር ነው እንጂ ከእግዚሐብሔር እና ከቤተክርስቲያን ጠላቶች ጋር አይደለም ።
  ••●◉ ✞ ◉●••
አቡነ ገርጎርዮስ ካልዕ
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒@Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
📃ስግደት🔊
  ••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ስግደት በሁለት ይከፈላል እነዚህም የባህርይና የፀጋ ተብለው ይከፈላሉ። የባህርይ ወይም የአምልኮት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ ሲሆን ፈጥረህናል ትገዛናለህ ለወደፊቱም ተስፋ መንግስተ ሰማይን ታወርስናለህ ብለን የምንሰግድለት ነው። የፀጋ ወይም የአክብሮት፥ ለእመቤታችን ለቅዱሳን ለጻድቃን፥ ለመላእክት ሁሉ እግዚአብሔር መርጦአቸዋል አክብሮአችሁማል፥ እኛም እናከብራችሁለን ብለን የምናቀርበው ነው::
══════◄✣••✥••✣►══════
🧑‍💻ለቤተክርስቲያን ወይም ለታቦት መስገድ ተገቢ ስለመሆኑ
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር።ዘፀ 33፥10
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።ኢያሱ 7፥6
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፥ ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ።2ኛሳሙ 12፥20
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።መዝ 5፥7
  ••●◉ ✞ ◉●••
በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ።መዝ 95፥9
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።መዝ 131፥7
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ።መዝ 137፥2
  ••●◉ ✞ ◉●••
🗣የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።መዝ 28፥2
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦....አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ።ሕዝ 46፥1
══════◄✣••✥••✣►══════
💁‍♂ለመላዕክት የፀጋ ስግደት እንደሚገባ ሁለቱም መላእክት
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ዘፍ 19፥1-2
  ••●◉ ✞ ◉●••
🗣እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።ዘኁ 22፥31
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።ኢያሱ 5፥13
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃ዳዊትም ዓይኖቹን አነሣ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፉ።1ኛዜና 21፥16
  ••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ።እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ።ዳን 8፥15
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ።መሳ 13፥20
══════◄✣••✥••✣►══════
ለቅዱሳን መስገድ ተገቢ ስለመሆኑ
  ••●◉ ✞ ◉●••
🔔ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ አወቀ፥ በፊቱም ተጐነበሰ፥ በምድርም ላይ እጅ ነሣ።1ኛሳሙ 28፥14
  ••●◉ ✞ ◉●••
🗣ከኢያሪኮም መጥተው በአንጻሩ የነበሩት የነቢያት ልጆች ባዩት ጊዜ። የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎአል አሉ። ሊገናኙትም መጥተው በፊቱ ወደ ምድር ተደፉ።2ኛ ነገ 2፥15
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ተመልክቶ ዳዊትን አየ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፋ።1ኛዜና 21፥21
  ••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር በግምባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል ሰገደለት፥ዳን 2፥46
  ••●◉ ✞ ◉●••
🧑‍💻በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሳኦል ሰፈር አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ።2ኛ ሳሙ 1፥1
  ••●◉ ✞ ◉●••
📖ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ፥እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው፥...ሴቶች ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀርበው ሰገዱ ከዚያም በኋላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ።ዘፍ 33፥1-8
  ••●◉ ✞ ◉●••
📃ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት።ሐዋ 10፥25
  ••●◉ ✞ ◉●••
🗣እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹዘንድ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።ራዕ 3፥9
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒@Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
👍1
🗣​​በተለይ ለኦርቶዶክሳውያን
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂አምልኮ/ምስጋና/ ማለት ክርስቶስ ራስ ለኾነላት ቤተ ክርስቲያን ለተባለችው አንዲት አካል ብልት ለመኾን የምንጋደልበት ሰማያዊ ሥርዓት ነው። ኦርቶዶክሳውያን በአምልኮ ጊዜ እርስ በእርሳችን ብቻ ሳይኾን ከመላእክትም ጋር ረቂቅ አንድነት አለን። በሰላም ማሠሪያ (ይህን) የመንፈስ አንድነት ለመጠበቅ እንድንተጋም ታዘናል። ኤፌ 4÷3
••●◉ ✞ ◉●••
📖ወደዚህ ሰማያዊ ኅብረት ይመጡ ዘንድም ለዓለም ኹሉ እንደ ሐዋርያቱ እንጮኃለን፤ ወደ ክርስቶስ ኅብረት በሃይማኖት ኑ እንላለን። እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው እንዲል(1ኛ ዮሐ 1÷3)
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ይህን በማድረግ ፈንታ ግን በማይመች አካሔድ ከማያምኑ ጋር መሰለፍ በሃይማኖታችን አይፈቀድም። ስለዚህ ማንም ኦርቶዶክሳዊ በሌላ ማኅበረሰባዊ ጉዳይ እንጂ በሃይማኖት ከማያምኑ ጋር ቢተባበር ራሱን ለካህን ያሳይ፣ በንስሐ ይመለስ‼️
••●◉ ✞ ◉●••
🔔ወንጌላችንም የሚለው የሚከተለውን ነው:-ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው2ኛ ቆሮ 6÷14-15)
••●◉ ✞ ◉●••
እኔም እላለሁ - ኦርቶዶክሳዊ ከኢሬቻ/ዋቄፈና ጋር ምን ኅብረት አለው
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💁‍♂ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ📖
••●◉ ✞ ◉●••
📃እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ ይላል (ኢያሱ 5÷13-15)፡፡ ይህን ጥቅስ ልብ ብለን ብናጤነው ለሌላው ሁሉ መርህ ይሆናልና ጥቂት ለማብራራት እንሞክራለን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱ ለኢያሱ በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆነው እንዲሁ ካንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውህም፡፡ (ኢያሱ 1÷1-9) በማለት ምን ያህል እንዳከበረው ያስረዳል፡፡ እስራኤላውያን አሞራውያንን በወጉ ጊዜ ቀኑ ስለመሸባቸው ከመደበኛው የተፈጥሮ ሕግ ውጭ ቀኑ እንደማይጨልምና መዓልቱ እንዲረዝም ኢያሱ በጸሎት ፈጣሪውን ስለጠየቀ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ቀኑን አስረዝሞ ከሰማይ በረድ አዝንሞ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት የፈጸመውን አስደናቂ ተአምር እንዲህ ብሎ ጸፏል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል (ልመና) የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም›› (ኢያ 10÷12-14) በማለት ተገልጿል፡፡ በጠቅላላው ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ የአሕዛብ ምሽጐችን አፍርሶ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሰ ኢያሱ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ይህ የእስራኤል መሪ በእጅ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጸለት ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን አላወቀም፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም ከመልአኩ የተሰጠው መልስ ታላቅ መሪና ነቢይ የሆነውን የኢያሱን አስተሳሰብ ለወጠው፡፡ ይኸውም ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ የሚለውን ቃል ሲሰማ ኢያሱ በፊቱ የቆመው ተራ ወታደር ሳይሆን የመላእክት ሠራዊት አለቃ ከሙሴ ሳይለይ የእስራኤልን ሕዝብ የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ አንተ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ለኢያሱ የምትነግረኝ ምንድነውበማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም መላእክት ጌቶች ይባላሉ፡፡ ጌትነታቸውም የጸጋ ጌትነት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛማ ኃጢአተኞች ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ…በማለት የአክብሮት (የጸጋ) ስግደት በመስገድ ብንለምነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጭ አልወጣንም፡፡ የፈጣሪን ክብር ለፍጡር አልሰጠንም፡፡ ተሳስታችኋል የሚለን ሰው ቢኖር እኛ አብነት ያደረግነው የእግዚአብሔር ወዳጅ ኢያሱን ስለሆነ ኢያሱም ተሳስተሃል ይባል፡፡ መልአኩም ኢያሱ ያቀረበለትን የአክብሮት ስግደትና ጥያቄ በመቀበል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን መልእክት ነገረው፡፡ ኢያሱም ትእዛዙን ፈጸመ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🙏ኦርቶዶክሳውያን ተወዳጆች እንኳን ለሰኔ 12,የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት ለቀየረበት በአል በሰላም አደረሰን
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
👍1
Forwarded from ፍቅረ ማርያም
2.በተምረ ማርያም መግቢያ ላይ ፍጥረት ሁሉ እመቤታችን ለማመስገን ነው የተፈጠረ ይላል ምን ማለት ነው።
🔔ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ አዳምና ሔዋንም እመቤታችን ከነሱ ልትወለድ ተፈጠሩ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂የተአምረ ማርያም መቅድም ቁጥር 7 ፡- ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ አዳምና ሔዋንም እመቤታችን ከነሱ ልትወለድ ተፈጠሩ፡፡አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ የማንረዳው ከሆነ እርሱ የወለዳቸውን አዋልድ መጻሕፍት አንረዳቸውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በራሱ ትርጓሜ ያሻዋል።አለበለዚያ እርስ በራሱ ይጋጫል፤ የራቀውን አቅርበው የረቀቀውን አጉልተው ለሰው አዕምሮ በሚስማማ መልኩ የሚያቀርቡት ደግሞ የትርጓሜ መጻሕፍት ናቸው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ለዚህም ነው በሐዋርያት ሥራ ላይ የተጻፈው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሚተረጉምልኝ ሳይኖር እንዴት እረዳለሁ ያለው፡፡በተለይ ደግሞ ተአምረ ማርያምን ለመረዳት በቂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት ያስፈልጋል።አለበለዚያ በተአምሯ ላይ የተጻፉትን አንዳንድ ምሥጢር አዘል መልዕክቶች ሲታዩ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
📃ተአምረ ማርያም ቁጥር ሰባት ላይ ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ይላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የዚህን መልዕክት ትርጉም በአግባቡ ካለመረዳት ፍጥረት የተፈጠረው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው እንጂ መቼ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ብለው ይከራከራሉ።እርግጥ ነው አመስጋኝ ፍጥረቶች ሰውና መላእክት ናቸው፤ እነርሱም የተፈጠሩት እግዚአብሔርን አመስግነው ክብሩን ለመውረስ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሰውና መላእክት ቢያመሰግኑት ክብር የሚጨምሩለት ባያመሰግኑት ክብር የሚጎድልበት አይደለም።እርሱ በባሕሪው ምስጉን ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
📖እምቅድመ ይፍጥር መላእክተ ለቅዳሴ አኮ ስብሐቲሁ ዘተጸርአ አላ ምሉዕ ውእቱ ስብሐተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፡፡ መላእክትን ለቅዳሴ ሳይፈጥር በፊት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምስጋና አልታጎለም እንዲል ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት፡፡በባሕሪው ምስጉን የሆነ እግዚአብሔር ለቅዱሳን ይልቁንም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የጸጋ ምስጋና ሰጥቷል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
📖ቅዱስ ዳዊት ለቅኖች ምስጋና ይገባል እንዳለ ከቅኖች ሁሉ በላይ ቅን ለሆነችው ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል፡፡ በዘወትር የጸሎትና የምስጋና ጊዜያችን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ካልን በኃላ አምላክን ለወለደች ለእመቤራችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል የምንለው ለዚህ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🔔ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ማለት ታዲያ ምን ማለት ነው ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ ማለት ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን አያመሰግነውም ማለት አይደለም❗️ የእመቤታችን መመስገን የእግዚአብሔርን ምስጋና አያጠፋውም አያጎድለውም❗️ የተአምረ ማርያም መጸሐፍም እየተናገረ ያለው ስለእመቤታችን ምስጋና ስለተጣት ክብር እና እርሷን ስለሚገልጹ ነገሮች ነው እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር ስላላት ምስጋና እያወዳደረ አይደለም፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እንግዲህ ይህ የተአምር መጽሐፍ ማለትም ተአምረ ማርያም ምን ያህል የነገረ ማርያም ምስጢራትን እንደያዘ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ነገረ ማርያምን በአግባቡ ያልተረዳ አንድ ግለሰብ ነገረ ክርስቶስ በምንም መልኩ ሊገባው አይችልም፡፡ ነገረ ማርያምን ከምንረዳበት መንገድ ደግሞ አንዱ ተአምረ ማርያም ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ወደቀደመ ነገራችን ስንመለስ ፍጥረት እመቤታችንን ለማሰመስገን መፈጠሩ እግዚአብሔር ራሱ ስላመሰገናት ነው፡፡ ዕውቀት የባሕሪ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ዓለምን ሳይፈጥር በልቡናው አስቧት ስለነበር ኃላም አካላዊ ቃልን ለመቀበል በተገባ የተገኘች ስለሆነች ትመሰገናለች፡፡ በተጨማሪም የተሳሳተ ግንዛቤ የያዙት ሰዎች ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማምለክ ተፈጥረ የተባለ ይመስል የተሳሳተ ሃሳብ ይሰነዝራሉ፡፡ነገር ግን መጽሐፉ የሚለው ለማመስገን ነው። መመስገን ደግሞ ስንኳንስ እመቤታችን ትቅርና ሌላውም ይመሰገናል፡፡ እኛም እኮ ውለታ የዋለልንንና ማንኛውንም ሰው አመሰግንሃለው እንለዋለን፤ ታዲያ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በቀር ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የሆነ ማን አለ፡፡ ጌታን የወለድሽ ሆይ እናመሰግንሻለን፣ የምህረት አማላጅ ሆይ እናመሰግንሻለን፣ እግዚአብሔር አንቺን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶምና ገሞራ ሆነን ነበር ስለዚህ እናመሰግንሻለን፣ በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ የሚቀመጠውን ጌታ በማኅጸንሽ የተሸከምሽ እናትና ድንግል ሆይ እናመሰግንሻለን እያልን ብናመሰግናት ምን ጥፋት⁉️
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂በመቀጠልም አዳምና ሔዋንም እመቤታችን ከነሱ ልትወለድ ተፈጠሩ ይላል፡፡ ይህንን ለመረዳት ዓለም ሳይፈጠር እመቤታችን በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር እንደተባለ ከአዳምና ከሔዋን መፈጠር በፊት እግዚአብሔር እመቤታችንን ያውቃት ነበር፡፡ ሰውን ከምድር አፈር ያበጀውና በአፍንጫው የሕይወት እስትንፋስን እፍ ያለበት እግዚአብሔር ሰውን ከማክበሩ የተነሳ የፈጠረውም በአርዓያውና በአምሳሉ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በመልክና አርዓያ የሚመስል ፍጥረት ሰው ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳን ሰው እግዚአብሔርን በመልክና አርዓያ ቢመስለውም እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው ሰውም ሰው ነው ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
🔊ባሕሪያቸው ይለያያል ሰው ሦስት ባህሪያትን ብቻ ነበር ከእግዚአብሔር የወረሰው እነርሱም የነፍስ ባህሪያት ሲባሉ ለባዊነት( ማሰብ)፣ ነባቢነት (መናገር)፣ ሕያውነት (አለመሞት) ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ እግዚአብሔር ፈጣሪ ሰው ፍጡር ነው እንጂ ምንም ዝምድና አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ አምላክ ሰው ሆነ ሰውም አምላክ ሆነ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
💁‍♂ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 4 ላይ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ግዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፡፡ እንዳለ የክርስቶስ ከእመቤታችን መወለድ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ዝምድና ከመፍጠሩም በላይ ሰባቱ መስተጻርራን ማለትም እግዚአብሔር፣ ሰው ፣ መላእክት፣ሰማይ ፣ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ሆነዋል ተታርቀዋል፡፡ ስለዚህ አዳምና ሔዋን የተፈጠሩት እመቤታችንን ወልደው እመቤታችን ደግሞ ክርስቶስን ወልዳ አምላክ ሰው እንዲሆን ሰውም አምላክ እንዲሆን ነው፡፡ አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነውና በልዑሉ (እግዚአብሔር) ትሑት (ሰው) መሆን ትሑቱ (ሰው) ልዑል(እግዚአብሔር) ሆኖ በአንድነት እንዲቀደስ በሦስትነት እንዲሠለስ ምክንያት የሆነች የአማኑኤል እናት የመድኃኔዓለም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
👍1
📃ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
••●◉ ✞ ◉●••
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።
ማቴ 5፡42-48፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒@Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒@Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
መንፈሳዊ ለዉጥ
የገኃነም ደጆች አይችሏትም መንፈሳዊ ቻናል
🙏በጣም ደስ የሚል ስብከት🧎 ══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @eotc27 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
2025/10/24 17:02:45
Back to Top
HTML Embed Code: