Telegram Web Link
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)

...ገብረ ጉንዳን...

✍️ ትጋት የሚገኘው ትጋት ካላቸው ነገሮች ጥበብን ከመማር ወይም ከመቅሰም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የትጋትን ጥበብ ለማግኘት ትጋት ካላቸው እንደ ጉንዳን ካሉ ፍጥረታት እንድንማር ይመክረናል።
ጉንዳኖች የትጋት ምሳሌ ሲሆኑ የእነርሱን መንገድ በጥንቃቄ በማጥናት ከፍተኛ የሆነ የትጋትን ጥበብ መቅሰም እንችላለን።

ምሳሌ 6
⁶ አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። ⁷ አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት፤ ⁸ መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች።

በዚህ ክፍል ውስጥ ከጉንዳን የምንቀስመው ነገሮች፦

የመጀመሪያው: መልካም የሥራ ባህልን እንማራለን። ማለትም ማንም ሳይጎተጉተን ያለ አለቃና ገዢ የመስራት ጥበብ ነው። በዚህም ጠንካራ የሥራ ባህል በምድር ላይ ኃያልና ጠንካራ እንሆናለን።

ሁለተኛው: ጉንዳኖች በስሜት ሳይሆን በአላማ ይመራሉ። አላማቸውም ቡድኑን ምግብ ማብላት ነው። አላማ ልንደርስበት የምንችልበት ግብ ሲሆን ግልጽ አቅጣጫን የሚቃኝ ነው።

ሦስተኛው: በሕብረት እና በጋራ ይሰራሉ። ማለትም ትልቅን ነገር ለመፈጸም በጋራ እና በሕብረት በመስራት የሚታወቁ ናቸው። ከሰውአልይ ሰው መንፈስ ተላቀን ተባብረን የምንሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት ያመጣል።

አራተኛው: ጉንዳኖች የሚሰሩበት ጊዜ አላቸው። ማለትም ጉንዳኖች ትልቁ ጥበባቸው ትንሽነታቸውን አውቀው በጋራ ሆነው ለጋራ ግብ መሥራታቸው ነው።

አምስተኛ: ጉንዳኖች ምግብን የመሰብሰብ ጥበብ ተምረዋል። ማለትም ምግብ ወሳኝ እንደሆነ በሚገባ ተገንዝበዋል። እኛም መንፈሳዊ ምግብ መሰብሰብ እንዳለብን ትምህርትን ሰጪ ነው።

ስድስተኛ የሚሰሩበትና የሚያርፉበት ጊዜ አላቸው። ማለትም በማረፊያ ጊዜ መስራት በመስራት ጊዜ ማረፍ እንደሌለባቸው ያውቃሉ።

ሰባተኛ: ኃይላቸው ትንሽ ቢሆንም ጥበባቸው ግን ትልቅ ነው።

ስምንተኛ: እጅግ የተደራጁ ናቸው ማለትም የተሰጣቸውን ስራ ተቀናጅተው ያደርጋሉ።

ዘጠነኛ: እና የመጨረሻው ከራሳቸው ክብደት በላይ መሸከማቸው ሲሆን፤ ይህም ማለት ነገሮችን ለመፈጸም ከአቅማችን አልፈን በመሄድ ማድረግ እንዳለብን እንማራለን ። ትጋትን እንቅሰም!

ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 26/12/2016
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!

Join Us:-

Telegram
https://www.tg-me.com/GospelTvEthiopia

Youtube
https://youtube.com/@gospeltvethiopiaofficial9652...

Facebook
https://www.facebook.com/RevTezerayared?mibextid=ZbWKwL

WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029VaLnNNJDzgTDJ6BrLl1A
63👍10🔥10
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
ሽሎም ቅዱሳን! የዛሬውን የአዲስ አመት ዋዜማ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ለመከታተል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው አብረውን ይሁኑ!
https://youtube.com/live/aflef-DmsQQ?feature=share
47👍6🔥4
2025/10/31 04:59:38
Back to Top
HTML Embed Code: