Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
17👍4
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
...እግዚአብሔር እንዳለ...
“ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።”
— ዕብራውያን 11፥6
✍️ ክርስትናችን የተመሰረተው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እውቀትና መገለጥ ላይ ነው፤ ክርስቶስ ኢየሱስም እግዚአብሔር አምላክን መኖሩን በሚገባ ተርኮልናል።
ሁልጊዜ ክርስትና ከባድ የሚሆነው እግዚአብሔር አምላክን በክርስቶስ ካለማወቅ የተነሳ ነው፤ ለዛም ነው ሁልጊዜ ጥማታችን እና ፍላጎታችን እርሱ መኖሩን ማወቅ መሆን ያለበት።
ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን መኖር በሚገባ አውቀው እና አምነው የእምነት ሕይወትን ኖረዋል።
አቤል እግዚአብሔር መኖሩን በማመን መስዋዕት ማቅረቡ፣ ሄኖክ እግዚአብሔር መኖሩን በማመን አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ሞትን ላለማየት በእምነቱ እግዚአብሔርን አስደሰተ፣ ኖኅ እግዚአብሔር መኖሩን በማመን የማይታየውን ነገር እንዲመጣ አምኖ ከጥፋት ውኃ አመለጠ እንዲሁም አብርሀም እግዚአብሔር መኖሩን በማመን እንደነገረውም በማመን ተከተለው።
በአዲስ ኪዳንም መጥምቁ ዮሐንስ በእምነት የኢየሱስን መምጣት፣ የጌታ እናት ማርያምም በእምነት ኢየሱስን በመጸነስ፣ ጌታ ኢየሱስ እንደ ሰው በእምነት በመመላለስ ለደቀመዛሙርቱ ማስተማር እንዲሁም ሐዋርያት የእምነት ሰዎች ሆነው እየፈወሱና ወንጌሉን እየሰበኩ እምነትን በግልጥ ኖረውታል።
በመጨረሻም ሕያው የሆነውን እግዚአብሔርን የምናስደስተው በእምነት ሲሆን የእምነቱ አይነት ደግሞ እግዚአብሔር መኖሩን ማመን እንዲሁም ለሚፈልጉት ዋጋ ወይንም ሽልማት እንደሚሰጥ ማመን ነው። እኛም ያው አንዱ የእምነት መንፈስ አለን ስለዚህ እናምናለን እናገራለን!
“ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤”
— 2ኛ ቆሮ 4፥13
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 26/01/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!
Join Us:-
Telegram
https://www.tg-me.com/GospelTvEthiopia
Youtube
https://youtube.com/@gospeltvethiopiaofficial9652...
Facebook
https://www.facebook.com/RevTezerayared?mibextid=ZbWKwL
WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029VaLnNNJDzgTDJ6BrLl1A
50👍7🔥5
*: "በእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር የተፈጠርን ነን እናም ያንን እስካልተረዳን ድረስ ሕይወት ፈጽሞ ትርጉም አይሰጠንም." ሪክ ዋረን*

"You were made by God and for God, and until you understand that, life will never make sense."*
Rick Warren*
👍30🔥207
2025/10/27 06:53:05
Back to Top
HTML Embed Code: