Telegram Web Link
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ግን ከእግዚአብሔር አይደለም!!!
“የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ግን ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ይህ ነው፤ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።”
1 ዮሐንስ 4 : 2 - 3 NASV
መልካም ቀን!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
63👍9🔥3
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
ኢየሱስም፣ “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም ደግሞ እሠራለሁ” አላቸው።

“አይሁድም፣ በሰንበት ቀን እነዚህን ድርጊቶች በመፈጸሙ፣ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር። ኢየሱስም፣ “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም ደግሞ እሠራለሁ” አላቸው። እንግዲህ አይሁድ፣ ኢየሱስ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቱ በማድረግ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር እኩል በማድረጉ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉት ነበር።”
ዮሐንስ 5 : 16 - 18 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
65🔥9👍3
…እኔ ነኝ’ ወደ እናንተ ልኮኛል” በላቸው!!!
“ሙሴም “እኔ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሄጄ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ በምላቸው ጊዜ እነርሱ ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እመልስላቸዋለሁ?” አለ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ ‘ያለሁና የምኖር ነኝ፤’ ስለዚህም ‘እኔ ነኝ’ ወደ እናንተ ልኮኛል” በላቸው፤ እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።”. ኦሪት ዘጸአት 3 : 13 - 15 አማ05
"Jesus is the great 'I AM THAT I AM' of Exodus 3:14, manifested in the flesh!"
“ኢየሱስም “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ፤ አሁንም፥ ወደፊትም አለሁ።” አላቸው።”
የዮሐንስ ወንጌል 8 : 58 አማ05

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
82👍15🔥11
“እንደገናም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ እኔን የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል፤ በጨለማም አይመላለስም” ሲል ተናገራቸው።”
የዮሐንስ ወንጌል 8 : 12 አማ05

….ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ!!! ሲል እያለን ያለው ( ምሪትና እውነትን የምሰጥ ነኝ ማለቱ ነው) የሕይወት ብርሀን ያለው ሰው በዚህ ጨለማ አለም ውስጥ ያለ ግራ መጋባት ይመላለሳል። አሜን

መልካም ቀን!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
73🔥16👍12
ትንሳኤ ስብእና አለው ስሙም ኢየሱስ ይባላል።
“ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?””
ዮሐንስ 11 : 25 - 26 NASV
መልካም በዓል!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
70👍16🥰11🔥9
“ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም፤”
ዮሐንስ 15 : 13 NASV
መልካም ምሽት!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
67🔥8👍2
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
....በርግጥ ከሙታን ተነሥቷል።

“አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁንና የተቀበላችሁትን፣ ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል ላሳስባችሁ እወድዳለሁ፤ የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው። እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤”
1 ቆሮንቶስ 15 : 1 - 4 NASV

የጌታችን እና የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ማለት የወንጌል አንዱ ክፍል ብቻ ሳይሆን የክርስትናችን ዋናና ማዕከላዊ ደግሞም ወሳኝ መልእክት ነው፡፡
ኢየሱስ ከሞት ባይነሳ ኖሮ የተናገራቸው እና ያስተማራቸው ነገሮች ዋጋ የሌላቸው ሌላ ሰማእት ብቻ ይሆን ነበር።

“ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቷል።”
1 ቆሮንቶስ 15 : 20 NASV

በትንሣኤው ምክንያት - ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በኃይል ተረጋግጧል፤ እንዲሁም አዳኝ፣ የሞትና የሲኦል የኃጢአትም አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
“በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በኀይል ስለ ተገለጠው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
ሮሜ 1 : 4 NASV

መልካም የትንሳኤ በአል ይሁንላችሁ!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ እና ቤተሰቡ
80👍17🔥9🥰8
….እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም!!!
“ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።”
የዮሐንስ ራእይ 3 : 7 አማ05
እርሱ የከፈተልልን በር ማንም ሊዘጋብን አይችልም ስለዚህ እርሱን ጥብቅ አድርገን እንያዘው።

መልካም የተከፈተ በር ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
98🔥21👍8🥰4
2025/10/22 17:09:44
Back to Top
HTML Embed Code: