Telegram Web Link
…. አምናችሁም!!!

“ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ብዙ ተአምር በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤ ነገር ግን ኢየሱስ መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድታምኑና፥ አምናችሁም በእርሱ ስም የዘለዓለም ሕይወትን እንድታገኙ ይህ ተጽፎአል።”
የዮሐንስ ወንጌል 20 : 30 - 31 አማ05

ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው ብለን እናምናለን??? ኢየሱስ መሲሕ ፥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድናምን መጽሐፍ ቅዱስ ያዘናል።

መልካም ቀን!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
129🔥7🥰2👏2
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)

"...ኢየሱስን ማወቅ..."

ፊልጵስዩስ 2:11 NASV
[11] ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

✍️ በዚህ ክፍል ውስጥ "ጌታ" የሚለውን "LORD" በግሪኩ ቃል "KYRIOS" "ኪርዩስ" ማለት ሲሆን በብሉይ ኪዳን "ያህዌ" የሚለው አቻ ቃል ነው። ይህም የሚያሳየን የኢየሱስ ስም ከስም ሁሉ በላይ የመሆኑን ምስጢር እና የኢየሱስን ያህዌነትን ነው።

ስለ ኢየሱስ ማንነት በሚገባ ማወቅ የሚያስፈልግበት ምክንያት ኢየሱስ አስተማሪ ወይም ነብይ ብቻ ሳይሆን እርሱ እግዚአብሔር ራሱ ስለሆነ ነው።

ማወቅ ያለብን ነገር ኢየሱስ ብቻ ነው ሕጻን ሆኖ ሳለ የተመለከ እና የከበረ ስጦታ የተቀበለው፤ ምንም እንኳን ደግሞ በስምኦን እጅ ታቅፎ ብናየውም መዳን የሆነና አለምን እና ያቀፉትን ሁሉ አቅፎ የያዘ ትልቅ አምላክ ነው።

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11

ጌትነቱ ሲወለድ የተጀመረ ወይንም ገና የሚሆነው ሳይሆን ጌታ የሆነ እንደተወለደ ግልጽ ነው።

በተጨማሪም ስለ ኢየሱስ ማንነት በሚገባ ማወቅ የሚያስፈልግበት ምክንያት መዳናችን የመጣው ከራሱ ከእግዚአብሔር ስለሆነ ነው።

“ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።”
— መዝሙር 3፥8

እንደሚል ቃሉ የመዳን በረከትን ያገኘነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ ነው። ይህ ኢየሱስን ማወቅ ያስፈለገበት ምክንያት ነው።
በመጨረሻም ስለ ኢየሱስ ማንነትና እንዲሁም ስለሰራው ስራ በሚገባ ማወቅ ወሳኝና ልንተጋበት የሚገባ ነገር ነው።

ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 17/09/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!
128👍19🔥10🥰6👏4
እግዚአብሔር እንዲህ አለ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም!

““ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደ ሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም። እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም። ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም። እኔ አምላክ እንደ ሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤”
ኢሳይያስ 43 : 10 - 12

ሬቨ ተዘራ ያሬድ
መልካም ቀን!!!
118👍8👏4🔥3
…..ይህን ተረድቻለሁ!!!

“ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣ ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።”
ሮሜ 8 : 37 - 39 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
156🔥23👍10🥰4
…..እኛም የርሱ ነን!!!

“እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤ በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ። እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የርሱ ነን፤ እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን። በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።”
መዝሙር 100 : 2 - 5 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
132🔥26👍10🥰7
“በሙያው ሥልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገሥታት ዘንድ ባለሟል ይሆናል፤ አልባሌ ሰዎችን አያገለግልም።”
ምሳሌ 22 : 29 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
125🔥21
‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበር ከእኔ ይልቃል’ ያልሁት እርሱ ነው!!!
“ዮሐንስ በማግስቱም፣ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፤ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበር ከእኔ ይልቃል’ ያልሁት እርሱ ነው፤ እኔ ራሴ አላወቅሁትም ነበር፤ በውሃ እያጠመቅሁ የመጣሁትም እርሱ በእስራኤል ዘንድ እንዲገለጥ ነው።””
ዮሐንስ 1 : 29 - 31 NASV
መልካም ሰንበት!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
111🔥10
“ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።”
ወደ ሮም ሰዎች 15 : 13 አማ05

ይህ ሳምንት በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ባረኳችሁ “ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።”

አሜን አሜን አሜን!!!

ሬቨ ተዘራ ያሬድ
መልካም ሳምንት
135🔥14🥰10👍9
…..የርኅራኄ አባት ይራራላችሁ!!!
“የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።”
2 ቆሮንቶስ 1 : 3 - 4 NASV
መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
175🥰18👍8🔥5
…..ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ!!!!

““እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው፣ ለእግዚአብሔር ያበደረ ከቶ ማን ነው?” ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ ነውና፤ ለርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን! አሜን።”
ሮሜ 11 : 35 - 36 NASV

በኛ ሕይወት የሆነው ሁሉ፣ ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ እንጂ ከእኛ በእኛ ለእኛ አይደለምና ክብር ለርሱ ይሁን በሉ!!!

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ
117🔥18👍10🥰3
2025/10/21 13:21:58
Back to Top
HTML Embed Code: