Telegram Web Link
የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች ማኅበር (JCSA) እና የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትሬሲ ክበብ (MILC) አዳዲስ አመራሮችን ሾሙ

***

በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የተመሰረቱት ሁለቱ የተማሪዎች ማኅበራት በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት በየዓመቱ በሚደረግ ምርጫ አዳዲስ አመራሮችን የሚሰይሙ ሲሆን ትናንት በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሄደ ምርጫ ነው አዳዲስ አመራሮቻቸውን የሾሙት።

በምርጫ ሂደቱ ሁለቱን ክበባት በፕሬዚዳንትነት፣ በምክትል ፕሬዚዳንትነት እና በጸሐፊነት ለመምራት ለአያንዳንዳቸው አምስት ዕጩ ተማሪዎች ቀርበው በአባላትና በመምህራን ፊት ዕቅዶቻቸውን በማቅረብ የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገዋል።

በአባላትና በመምህራን በሚስጥር በተሰጠ ድመጽ አብላጫ ድምጽ ያገኙ ተማሪዎቸ ተለይተው አዲሱን ሀላፊነት ተረክበዋል።

በዚሁ መሠረት JCSAን ለመምራት ተማሪ #ሚዴቅሳ_መንግስቱ_ፕሬዝዳንት፣ ተማሪ #አብዱላሂ_ዓለሙ ምክትል ፕሬዝዳንት እዲሁም ተማሪ #ሐዊ_ቤዛው ጸሐፊ ሆነው ሲመረጡ፤

በተመሳሳይ ለሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትሬሲ ክበበብ (MILC) ተማሪ #ፍርዶስ_መሐመድ_ፕሬዝዳንት፣ ተማሪ #ቴዎድሮስ_ታከለ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ተማሪ #ሐና_ደረሰ ጸሐፊ በመሆን ተመርጠው ሀላፊነት ተረክበዋል።

የትምህርት ክፍሉ መምህራንም ለተመረጡት አዳዲስ አመራሮች መልካም የስራ ዘመን ተመኝተው ለቀድሞ የማኅበሩና የክበቡ አመራሮች ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ የዕውቅና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

via:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083448233574

HU JCSA!
1
2025/07/14 02:53:21
Back to Top
HTML Embed Code: