Telegram Web Link
05/08/2017

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ተማሪዎች ማህበር (JCSA) በትላንትናው እለት በተካሄደው ደማቅ የክበባት አውደርዕይ ላይ ስራዎቹን አቀረበ ።

በርካታ ክበባት ተሳታፊ የሆኑበት የ2017 የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዙር የክበባት አውደርዕይ በትላንትናው እለት የዩንቨርስቲው አመራሮች እና ተማሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ።

በዚህ ደማቅ የክበባት አውደርዕይ ጀሲሳ እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች ለተገኙት አመራሮች እና ተማሪዎች አሳይቷል።

ማህበሩ በአውደርዕይው ላይ ስራዎቹን የሚያሳይበት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በመያዝ እና የተለያዩ አሳታፊ ጨዋታዎችን በማዘጋጀት ራሱን ማስተዋወቅ የቻለ ሲሆን ማህበሩ ተወዳዳሪ የሚያደርጉትን ተግባራት በማቅረብ በርካታ አባላትን ማፍራት ችሏል።

ማህበሩን የጎበኙ አመራሮች እና ተማሪዎችም በበኩላቸው አድናቆታቸውን ለማህበሩ ገልጸዋል።

ዘጋቢ: አይንአዲስ ታረቀኝ (የ4ተኛ አመት የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ተማሪ)

📌ጀሲሳ ለአውደርዕይው መሳካት ከቅድመ ዝግጅት እስከ ፍጻሜ ድረስ ተሳትፎ ላደረጉ የትምህርት ክፍላችን መምህራን እንዲሁም የማህበሩ ንቁ አባላት ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።🙏

እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

JC SA!
ቅዳሜ 4/7/2017 ዓ.ም

በትላንትናው እለት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በርካታ የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ክበባትን ያሳተፈ ደማቅ አውደርኢ ተካሂዷል ።

እኛም ታዲያ ከበጎ አድራጎት ጉዞ መልስ ቤታችንን ለማስተዋወቅ በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈናል ።

የዩንቨርስቲው አመራር አካላት በተገኙበት ስለስብስባችን ጠቅላላ ገፅታ ገለፃ ተደርጓል ።

ብዙ አዳዲስ ቤተሰቦችን አግኝተናል ። ከሎሎች ክበባትም ጋር አስተማሪ የልምድ ልውውጥ አርገናል።

🎹 በሙዚቃ እና በጨዋታ የታጀበ ደማቅ ቅዳሜ ከሰዓትን በጋራ አሳለፍን ።

🙏 እንደሁል ጊዜው ጎንበስ ቀና ብላችሁ ቤታችሁን ላደመቃችሁ እንዲሁም ላስተዋወቃችሁ በሙሉ ምስጋናችን ከልብ ነው ።

እንወዳችኋለን ❤️

☑️አድራሻችን Main Campus, Radio ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው
አዳራሽ።

🔘የቴሌግራም አድራሻዎቻችንን ላልተቀላቀላችሁ በታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።
👇👇👇👇

ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ!!

#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@RvcClub
@RvcClub
2025/09/19 19:04:45
Back to Top
HTML Embed Code: