Telegram Web Link
✍️ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለን ሀኪሞች  መካከል ያለው የታካሚዎች ሽኝትና ቅብብል (referral) ስርአት ለብዙዎች የእንግልት ምክንያት በሚሆኑ ሽንቁሮች የተሞላ ነውና ተባብረን ብናርመው ሸጋ ነው።

✍️ ታካሚዎች ለወራት ሲታከሙ ከቆዩበት እና የ እትዬ ሌሌ ያህል ምርመራዎች ካሰሩበት የግልም ሆነ የመንግስት የህክምና ተቋም ኪሎ ሜትሮች አቋርጠው ለተሻለ ህክምና የደረት ኪሳቸው ውስጥ ሻጥ ባደረጓት የብጣሽ ወረቀት ብቻ የሚከሰቱበት ሁናቴ ከመርህ አንጻርም ልክ ስላልሆነ ማስተካከል የምንችልበትን ሁኔታ ብንፈልግ መልካም ነው። (ከዓመታት በፊት ከስራ ማሰናበቻ የነበረችው ብጣሽ ወረቀት እንኳን ግልባጭ ሲበዛባት አሁን ሦስት ገጽ ሆናለች አሉ!)

✍️ ተለቅ ባሉ የህክምና ተቋማት የተሻለ ምርመራ ማድረግ እና በአንጻሩ ከፍ ያለ ህክምና መስጠት የሚቻል ቢሆንም አስቀድሞ በመጀመሪያ በላኪው የጤና ተቋም ሀኪሞች የተደረጉ የታካሚ እይታዎች (evaluations ) እንዲሁም አጠቃላይ ምርመራዎች (Investigations) አስተዋጽኦ በreferral Hospitals ለምንሰጠው ቀጣይ ህክምና የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል .. ባልልም  ቢያንስ የነብር እና የአጋዘንን ድርሻ አያጣም። 

I think all of us recall this particular conversation ... " ጋሼ ምን አይተው ነበር  የሳንባ መድሀኒት ሐኪሞቹ የጀመሩሎት?" .. " አይ ምን እንዳዩ እንኳን እንጃ .." .. " "እሺ አክተው ላይ ቲቢ አለ ብለው ነበር ወይስ ራጅ ብቻ ነው የተነሱት ጋሼ?" ... " አክታ ወስደው ነበር ብለህ ነው ልጄ ?.. ትዝ አይለኝም .." የሚሉ የመላምት ትንበያዎች ካለፈው የመኸር አመት ጋር ሲነፃፀሩ ቁጥራቸው እየጨመረ ይገኛል! ምን ተሻለ ጎበዝ ? ... ምርመራውን አንደግመው ነገር..  የአክታ ምንጩ ደርቋል .. መድሀኒቱን አንቀጥለዉ ነገር ከመንፈቅ እስከ ዓመት ሆነ ህክምናዉ 🤔(እነዚህንና መሰል ምርመራዎችና ውጤቶች ትኩረት ተሰጥቷቸው አብረው ቢላኩ !!)

✍️ ብሽሸት ወይም አንገት ላይ አንድ ለናቷ የወጣች ንፍፊት አስወግዶ .. መርምሮ .. በስመ ጥር ወይም ታዋቂ የስነ ደዌ ስፔሻሊስት አስገምግሞ እና comment  አስደርጎ ካበቁ በኋላ ውጤቱን ፋይል አድርጎ በአንድ መስመር መደምደሚያ " እመኑኝ ከምር Lymphoma ነው .." የምትል ማስታወሻ እንደ ግርጌ መግለጫ ከትቦ ታካሚን ክልል ማሻገር አጉል እያደረገን ይገኛል! ምርመራውን አንደግመው ነገር ..  ንፍፊቱ ጠፍቶ .. ብሽሽቱም ገጥሟል!  ቢኖር እና እንመርምረው ቢባል እንኳን ታካሚው በወሰዳቸው መድሀኒቶች ምክንያት ንፍፊቶቹ ወይ ንፍፊታዊ ማንነታቸው ተቀሽቧል .. ወይም ደግሞ ከተማ ላይ ለሳምንታት አልጋ ይዞ ምርመራ የማሰራት  እና ውጤት የመጠበቅ አቅም ያለው ሰዉ ይጠፋል!

✍️ በርካታ ተመሳሳይ ምሳሌዎችን መስጠት ይቻላል .. ከባድ ህመምን ያዘሉና ደግሞ ለመስራትም የሚያሳቅቁ የአጥንት መቅኔ መጠጣ (Bone marrow aspiration)  እና የአጥንት መቅኔ ስላሽ (Bone marrow biopsy) ናሙናዎች ፥ ከዋጋቸው መናር አንጻር ብዙ ጊዜ በብድርና በልመና የሚሰሩ የCT እና MRI CDዎች እና ንባቦች .. ተሟልተው ያለመላክ እና ያለመገኘት ላላስፈላጊ ወጪ፥ ምሬትና እንግልት እየዳረገን ነውና ቢታሰብበት! ታካሚዎችም ቢሆኑ አጥንትና ንፍፊትን የሚያክል ነገር ተሰርስረው የተሰሩ ምርመራዎች ሀኪሞች ከስራ ብዛት ዘንግተው ባይሰጧቸው እንኳን አስታውሰው ተቀብለው ይዞ መምጣት ይገባቸዋል.. "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም" ነውና !...

✍️ ከጤና ተቋሞቻችን ከባድ የመሠረተ ምርመራ አቅም  ቁጥብነት አንፃር መስራት የምንችላቸው ምርመራዎች  ውስን ሆነው ሳለ እነርሱንም በአግባቡ ካልተቀባበልን በእንቅርት ላይ Toxic Adenoma መሆኑ ነው 🤷

፤ በ referral ወረቀት ላይ ሁሌም አሻራዋ ማይጠፋው "?..quiry ?" .. የማትደመሰሰው እና በየ ተኝቶ ታካሚ ቅኝቱ (round) ላይ ከሀኪም ሀኪም አፍ እንደ አፈ ታሪክ ለመዝለልዋ መነሻ እንደነዚህ በየደረጃው ያሉ የታካሚ ሁኔታ መግለጫ (evaluations ) እና ምርመራዎች (Investigations ) ቅብብሎሽ ድዊነት አንዱ ምክንያት ይመስለኛል!

✍️ የዱላ ቅብብል ሩጫን በማሸነፉ ሂደት ውስጥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተሳተፉ አራቱም ሯጮች ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። ነገር ግን አንዱ ሯጭ በመሃል ዱላዋን በትክክል ካላቀበለ ተቀባዩ Usain Boltም ቢሆን ሲጥላው አይተናል ..

The situation is much worse when people's lives are at stake. እንደው ከዕለት እለት እሮሮው ቢበዛብን ነው ይህችን ለመጣፍ የተገደድኩት ! 

ሂሳችንን እንዋጥ 🍚 .. እንደጋገፍ ..🤞በተሻለ እንቀባበል✍️🤝 ! አንድ እንሁን☝️ !

         ክፍተቱ ይቀልበስ
        "?..quiry"ን ለመደምሰስ!

በቀጣዩ referral እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት 👋🙏

Ephrem Hailey G.: MD, Internist, Adult Clinical Hematologist, Assistant professor of Internal Medicine, AAU, SOM, TASH

@HakimEthio
62👍12👏2
Meet Dr. Robel Gebrewahd, the gold medalist from Aksum University's medicine class of 2025, with a CGPA of 3.95.

@HakimEthio
94👏48👍12
The Orthopedic residents and senior staff of Jimma University Medical Center (JUMC) held a farewell dinner in honor of Dr. Tolosa Dibisa, former Head of the Orthopedic Department, as he departs to pursue an international fellowship program.

The event also served to warmly welcome Dr. Yohannes Shugie as the new Head of Department.

We extend our heartfelt gratitude to Dr. Tolosa for his years of dedicated service, leadership, and mentorship, and wish him success in his future endeavors.

At the same time, we are proud to welcome Dr. Yohannes, whose experience and vision are set to guide the department into its next chapter of growth and excellence.

@HakimEthio
👍2317
🔎 Discover the power of early detection with our state-of-the-art serum tumor marker test, available at ONCO Advanced Diagnostic Center. Our advanced technology and expert team provide accurate and reliable results, helping to identify potential cancerous growths and monitor treatment effectiveness.

Visit our branches

📍Enkulal fabrica beside Noc Gas Station

📍Around Alert hospital, In front of Abune Aregawi Church


  📞0945606969| 0949065555| 0949045555
#HealthCare
#OncoAdvancedDiagnostics #Open24Hours #HealthcareExcellence
👍31
የሽንት ቧንቧ ጫፍ ከተፈጥሮው ቦታ በታች መሆን | Ujummoo fincaanii caafii hin ga’iin hafe | Hypospadiasis
Amharic | Afaan Oromoo

"ዶ/ር ልጄ የተወለደው በተፈጥሮ ተገርዞ ነው። የማርያም ግርዛት አለው: የሽንት ቧንቧው ከተፈጥሮው ቦታ በታች ነው። ሲሸና ሽንቱ ልብሱን ይነካል። መፍትሄ አለው? መፍትሄው ምንድነው?” በስራ ቦታዬ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመኝ ጥያቄ ነው።

ይህ ችግር ምንድን ነው?

ይህ ችግር በተፈጥሮ የሚከሰት እና በህክምና ቋንቋ 'ሃይፖስፓዳይስስ' በመባል ይታወቃል። በተለምዶ 'የማርያም ጊሪዛት' በመባል ይታወቃል:: የፊኛው ጫፍ ከብልቱ ጫፍ በታች ወደፊት ይገኛል ማለት ነው።

እንዴት ነው የምፈጠረው?

የፊኛው ጫፍ በተፈጥሮው በወንድ ብልት ጫፍ ላይ ይገኛል:: ፊኛው ይህንን ቅርጽ የሚይዘው ህጻኑ በማህፀን ውስጥ እያለ ነው:: ይህ የሚሆነው የሽንት ቱቦው እስከ ብልት ጫፍ ድረስ ካላደገ ነው::

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

የፊኛ ጫፍ ከብልቱ ጫፍ በታች ሊሆን ይችላል፣ ብልቱ ወደ ታች መታጠፍ፣ ወደ ፊት ቀጥ ብሎ መሽናት አለመቻል፣ ሽንት በሚሸናበት ጊዜ ጨርቁን ሊነካ ይችላል፣ አልፎ አልፎም ብልቱ የወንድ ልጅ ላይመስል ይችላል።

ቤተሰቡ በልጁ ላይ እነዚህን ባህሪያት ካገኙ ምን ማድረግ አለባቸው? ልጁ መገረዝ የለበትም:: ምርመራ ለማድረግ ልጁን ወደ ሐኪም ይውሰዱት::

ሕክምና፡- ችግሩ በራሱ አይፈታም ስለዚህ የቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል

ሃይፖስፓዲያን ለመጠገን ትክክለኛው ዕድሜ ስንት ነው? በተወለደበት ጊዜ ከታወቀ ከ6-12 ወራት ውስጥ ቀዶ ጥገናውን ማድረግ የተሻለ ነው:: በኋላ ላይ ከታወቀ ቀዶ ጥገናው ከታወቀ በኋላ ወዲያውኑ መደረግ አለበት::

ሕክምና ካልተደረገለት ምን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል?

ü ሽንት ልብሶችን ያበላሻሉ እና የንጽህና ችግሮችን ያስከትላል

ü በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው

ü የስነ-ልቦና ተፅእኖ ያስከትላል

ü የፊኛ ጫፍ በጣም ከኋላ በሚወርድበት (proximal hypospadiasis) ላይ በሚገኙ ሕፃናት ላይ የመካንነት ችግርን ሊያስከትል ይችላል::

v ስለዚህ, ይህ ችግር ልምድ ባለው ባለሙያ በጊዜው መታከም አለበት::

“Doctor, mucaan koo uumamaan dhaqna qabatee dhalate. Karaan fincaansaa ittiin fincaa’u bakka uumamaa irraa gad siqee jira. Yeroo fincaan fincaa’u, fincaansaa kofoo/surree isaa tuttuqa. Falli isaa maali?” Kun gaaffii yeroo baay’ee lafa hojii kootti na quunnamuudha.

Rakkoon kun maali?

Rakkoon kun uumamaan kan uumamu yoo ta’u afaan medikaalaan ‘Hypospadiasis’ jedhamee beekama. Innis fiixeen ujummoo fincaanii fiixee qama saalaa gaditti gara fulduraatti gad bu’ee argamuu jechuudha.

Akkamiin uumama?

Fiixeen ujummoo fincaanii uumamaan fiixee qaama saalaa irratti argama. Ujummoon fincaanii kun bifa kana kan qabaatu osoo daa’imni garaa haadhasaa keessa jiruuti. Rakkoon kun kan uumamu yoo ujummoon fincaanii kun guddatee fiixee osoo hin gahiin hafeedha.

Mallattoon isaa maali?

Fiixeen ujummoo fincaanii fiixee qaama salaa gad ta’uu, gad jallachuu qaama saalaa, dhaabbatanii fulduratti fincaa’uu dadhabuu, yeroo fincaa’an fincaan huccuu tuttuquu fi darbee darbee qaamni saalaa kan ijoollee dhiiraa fakkaachuu dhabuu mala.

Maatiin daa’ima mallattoo akkanaa qabuu maal gochuu qabu? Daa’imicha daqna qabuu dhiisuu. Ogeessa yaalaa bira geessuun ilaalchisuu qabu.

Yaallisaa maali?

Yoom yaalamuu qaba? Daa’imni tokko akka dhalateen rakkoo kana qabaachuun isaa yoo beekame, umuriin isaa yeroo ji’a 6-12 gidduutti osoo yaala baqaqsanii yaaluu argatee ni filatama. Umirii sana booda warren jiran immoo akkuma rakkichi barameen osoo yaalamanii gaariidha.

Yoo hin yaalamne rakkoo akkamii geessisuu danda’a?

ü Fincaan huccuu waan xuquuf rakkoo qulqullina qaamaa ni fida

ü Carraan infekshinii ujummoo fincaaniin qabamuu isaanii ni dabala

ü Xinsammuun miidhamuu daa’immanii ni fida

ü Namoota fiixeen ujummoo fincaanii baay’ee gad bu’ee (proximal hypospadiasis) jiru irratti rakkoo dhala dhabuu fiduu danda’a.

Kanaaf rakkoon kun ogeessa muuxannoo qabuun yaala yeroo isaa eeggate argachuu qaba.

Dr. Tafese Gudissa
Pediatric surgeon/ የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም/ Ispeshaalistii baqaqsanii yaaluu daa’immanii.

📞 +251919399329

@HakimEthio
24👍6
Today the new Orthopedic ward was inaugurated at Filtu General Hospital. The inauguration ceremony was attended by Hospital, Zonal and Woreda administrators.

This development underscores Filtu General Hospital ongoing efforts to expand infrastructure and provide accessible, high quality health care to Liben Zone community, Borena, Guji Zones of Oromia and South Kenya.

The ward is equipped with 40 beds and was built by the participation of Liben Zone community. Credit goes to Hospital CEO, Dr. Feisal Mowlid, Zonal, Woreda Administrators and the community at large.

Compiled by Eyob Mamuye, MPH

@HakimEthio
23
2025/07/14 13:41:30
Back to Top
HTML Embed Code: