═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
አላህን (ሱ.ወ) መፍራት እውቀትን እንድንወድ የሚያደርግ ሲሆን አላህን (ሱ.ወ) መዳፈር ወደ ድንቁርና ይወስዳል፡፡
                ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ሞት ከሱ በኋላ ካሉ ነገሮች ሁሉ በጣም ቀላሉ ሲሆን ከባዱ ነገር ደግሞ ከሱ በፊት ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡
                ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
እድሜህ እያለፈ አንተ ግን አንዳችም መልካም ነገር አለማድረግህን ባወቅ ጊዜ የዛን ቀን አልቅስ፡፡
            ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ለማንም ሰው ምክር ሲሰጡ አላህን በመፍራት ላይ የተመሰረተ መሆን አለብዎት፡፡
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
አንድ ሰው ራሱን ወደላይ በጣም ቀና ካላደረገ በስተቀር አንገት ውስጥ የሚሰማ የህመም እድል ሊኖረው አይችልም፡፡
           .   ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
የአንድ ሙስሊም ወንድ ከሁሉ የበለጠ ቅዱስነት/ንጹህነት፣ ምላሱን፣ ወሲባዊ አካሉን እና አስተያየቱን ሲጠብቅ ነው፡፡
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ለአላህ ተብሎ መነጠል በአላህ ዘንድ በጣም የተወደደ ነው፡፡
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ታላቅነትን ራቀው፤ ታላቅነትን በራቀው ቁጥር ይከተልሃልና።
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ለሁሉም ችግሮች ሁሉ መሰረቱ ንግግሩ ነው፡፡
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
▫️ ስደት ወደ ሐበሻ ▫️
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

በጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ መሪነት ወደ አቢሲኒያ (ኢትዬጵያ) የመጀመሪያው ስደት ተደረገ። በፍትሀዊው የኢትዮጵያ ንጉስ ነጃሺ ጥላ ስር በመሆን ሃይማኖታ ቸውን በነፃነት በመተግበር አላህን የመገዛትን ጣዕም ሊቀምሱ ቻሉ። የስደተኞቹ በሰላም መኖር የእግር እሳት የሆነባቸው የቁረይሽ ሹማምንት ወደ መካ የሚመልሱባቸውን መንገድ ያውጠ ነጥኑ ጀመር።

ለዚህ ተግባር የቁረይሽ ግፈኞች #አምር ኢብን አልአስና #አብዱላህ ኢብን አቢ ራቢያን በመወከል ከበርካታ ስጦታወች ጋር ወደ ንጉሱና ጳጳሳቱ ላኩዋቸው።

ኢትዮጵያ እንደደረሱ ለስጦታ ያመጧቸውን ንብረቶች ለጳጳሳቱ በመለገስ «በንጉሱ መሬት የሚንቀሳቀሱ አመፀኛ ወጣቶች አሉ። በአባቶቻቸው ሀይማኖት ላይ ያፌዛሉ፣ ይኮንኑታልም። በህዝባችን መካከል ሁከትና መከፋፈልን ፈጥረዋል። ንጉሱን ስናነጋግር ስለ ሃይማኖታቸው ምንነት ሳይጠይቋቸው እንዲያስረክቡን ጎትጉቱልን። የተከበሩት የህዝባችን መሪወች ስለ እነሱም ሆነ ስለ ሀይማኖታቸው ከሁሉም በላይ ያውቃሉ» አሏቸው። ጳጳሶቹም ተስማሙ።

📦 አምርና ዐብደላህ ብስጦታቸው ለተደሰተው ነጃሽ 《ንጉስ ሆይ! ርኩሳን ወጣቶች ከኛ አምልጠው ወደ ግዛተዎ መጥተዋል። እኛም እርሶም የማናውቀውን ሃይማኖት ይከተላሉ። በወላጆቻቸው እና በህዝባቸው ላይ ያመፁ አፈንጋጮች እንድትመልሱልን የተከበሩ መሪዎቻችን ልከውናል።» ሲሏቸው ንጉሱ ወደ ጳጳሳቱ ዞር ብለው ሲመለከቷቸው።

«ንጉስ ሆይ! እውነታቸውን ነው የተንናገሩት። በህዝባቸው ላይ ምን ፈፅመው እንደመጡ ስለሚያውቁ ለፍትሀዊ ፍርድ ወደነርሱ ይላኩዋቸው» አሉ።

🎙 በአስተያየታቸው የተቆጡት ንጉስ ነጃሽ «በፈጣሪ ይሁንብኝ! ለምን እንደተወነጀሉ እራሴ ሳላጣራ አሳልፌ አላስረክባቸወም። እነዚህ ሁለት ሰዎች የሚሉት እውነት ከሆነ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ካልሆነ ግን የእኔን ጥበቃ እስከፈለጉ ድረስ በኔ ምድር ይኖራሉ።» በማለት አስደነገጧቸው።

ንጉሱ ሙስሊሞቹ ለችሎት እንዲቀርቡ
አዘዙ። ሙስሊሞቹ ከመሄዳቸው በፊት እነሱን ወክሎ #ጀዕፈር ኢብኑ አቢ-ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ብቻ እንዲናገር ተስማሙ በንጉሱ ቤተ መንግስት ጳጳሳቱ የሚያምር አረንጓዴ ልብስና ማራኪ ቆብ ደፍተው ከንጉሱ ወንበር ግራና ቀኝ ቁጭ ብለዋል ሙስሊሞቹ ሲገቡ ቁረይሾቹ ቦታቸውን ይዘው ነበር። ንጉሱ መጡ።

ቀሳውስት፣ ጳጳሳት፣ ቁረይሽ ወዘተ.. ከሙስሊሞች በስተቀር ሁሉም ለንጉሱ አጎነበሱ።

ንጉሱ ሙስሊሞቹን ለምን የክብር ሰላምታ እንዳልሰጡ ሲጠይቋቸው

🎤 «እኛ ለአላህ እንጅ ለሌላ የማናጎነብስ ህዝቦች ነን። »በማለት ነበር በታሪክ የማይረሳውን ቃል ጀዕፋር ረዲየሏሁ ዐንሁ የመለሱት።

🎙 ንጉሱ በመገረም «ለመሆኑ ከህዝቦቻችሁ ጋር ሆድና ጀርባ ያደረጋችሁ እምነት ምን አይነት ነው? ወደ እኔ ወይም ወደ ሌላ ህዝቦች ሃይማኖት ለምን አልገባችሁም?» በማለት ጠየቁ።

ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ ወደፊት ቀረብ በማለት በቅን ልሳን የመካ ሰውን ሁኔታ፣ የኢስላምንና የረሱልን ﷺ ሚና ቁልጭ አድርጎ አቀረበ።


🎤 እንዲህ ነበር ያለቸው፦ «ንጉስ ሆይ! በድንቁርናና በምግባረ ብልሹነት የተዘፈቀን፣ ጣዖት አምላኪ፣ የሞተ እንስሳ ተመጋቢ፣ አሰቃቂ እና አፀያፊ ስራወችን የምንፈፅም፣ ዝምድናን የምንቆርጥ፣ እንግዳ የምናስከፋ ህዝቦች ነበርን። ኃይለኛውም ደካማውን የሚበዘብዝ በት ሁኔታ ነበር። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን አላህ ማንነቱን፣ ቤተሰቡንና እውነተኝነቱን የማንክደው መልእክተኛ ላከልን።
እሱም ፦ እውነትን ብቻ እንድንናገር፣ ውለታችንን እንድናከብር፣ ለዘመድ መልካም እንድንውል፣ ጎረቤቶቻችንን እንድንረዳ፣ ከተከለከሉ ነገሮች ሁሉ እድንርቅ፣ ያለ አግባብ ደም ከማፍሰስ እንድንታገድ፣ ከብልግና ተግባሮች እንድንርቅ፣ በውሸት እንዳንመሰክር፣ የሙት ልጅ ሀብት አጭበ ርብረን እንዳንወስድ፣ የንፁህ ሴቶችን ስም እንዳናጠፋና በሀሜት እንዳንለውስ፣ በአላህ ሳናጋራ እሱን ብቻ እንድናመልክ፣ ሶላት እንድንሰ ግድ...አዘዘን። ያዘዘንን በመስራት፥ ከከለከለን ነገር በመከልከል ከእሱና ከአላህ በመጣልን መልዕክት አመን።»

« ክቡር ንጉስ ሆይ! ህዝባችን አሰቃየን ሃይማኖታችንን ክደን ወደድሮው አስፀያፊ ጣዖት አመልኮት እንድንመለስ ለማድረግ አሰቃቂ ቅጣቶች ፈፀመብን። ጨቆነን። ህይወታችንን መምራት አቃተን።የእምነታ ችንን ግዴታወች ማከናወን ተሳነን ለዚህ ነው ሀገራችንን ጥለን በመሰደድ ከሁሉም በፊት እርሰወን መርጠን በመሬትዎ በፍትህና በሰላም ለመኖር የመጣነው።»

▫️ንጉሱ በገለፃው ተማርከዋል። ቢሆንም ነገሩ በዚህ አልተገታም


በሚቀጥለው ቀን ብልጣ ብልጡ ዐምር «ንጉስ ሆይ! እነዚህ መሸሸጊያና መጠለያ የሰጠሀቸው ሙስሊሞች ስለ ማሪያም ልጅ እየሱስ አስከፊ ነገር ይናገራሉ። አስጠርተው ይጠይቋቸው አለ።

🎙ንጉሱ ለሁለተኛ ጊዜ አስጠራቸው። « ስለ ማርያም ልጅ ኢየሱስ እምነታችሁ ምን ይላል?» በማለት ጠየቃቸው።

🎤 ጀዕፈር ረ.ዐ አጭር መልስ ሰጡ፦ «ኢየሱስ የአላህ ባርያ አገልጋዩና መልእክተኛው ነው ወደ ማርያም የተላከ የአላህ የሁን ቃልና መንፈስ እንደሆነ ተምረናል።»

🎤 ጃዕፋር ረዲየሏሁ ዐንሁ፦ ጣእም ባለው አንደበት ስለ ኢየሱስ እና ማርያም የሚያወሳውን ከሱራ መርየም የመጀመሪ ያውን ክፍል ቀሩ።
የቁርኣን አንቀፅ ከልቡ የሰረፀው ንጉስ እንባው #የአይኖቹን ግድብ ጥሶ በጉንጮቹ ላይ እየተንከባለሉ ወደ ሙስሊሞቹ ዞር በማለት
«የነብያችሁ እና የኢየሱስ መልእክት ከአንድ ምንጭ ነው!»
ሲላቸው አምርና ጓደኛውን ደግሞ «ዘወር በሉልኝ! በፈጣሪ እምላለሁ ለናንተ አላስረክባቸውም!» አላቸው።

🎙 ንጉሱ «እየሱስ በትክክል ነብያችሁ እንደነገራችሁ ነው!» አላቸው።

በጀዕፈር መልስ የተናደዱት ጳጳሳት በማኩረፋቸው ንጉሡን ክፉኛ ነቅፈዋል። ንጉሥ ነጃሽ ሙስሊሞችን «ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ናችሁ በመንገዳችሁ መሰናክል የሚሆን ዋጋውን ይቀምሳል። የተቃወማችሁን ሁሉ እቀጣዋለሁ። በፈጣሪ ይሁንብኝ! አንዳችሁ ከምትጎዱብኝ የወርቅ ተራራ ባጣ ይሻለኛል።» አሉ።

በሌላ በኩል አምርና ጓደኛው ስጦታቸው ተመልሶላቸው ውርደት እና ሀፍረትን ተከናንበው ኢትዬጵያን ለቀው ወደ መካ ተመለሱ። ሙስሊሞችም በደስታ ይኖሩ ጀመር።

ጀዕፈር እና ሚስቱ አስማ ረዲየሏሁ ዐንሁም በኢትዬጵያ ለአስር አመታት ኖሩ። #አብዱላህ#ሙሀመድ እና #አውን የሚባሉ ልጆችም ወለዱ።

               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
አንዳንድ ጊዜ ወንጀለኛን ይቅር ማለት ወንጀለኛውን የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል።
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ገደብ የለሽ ፍላጎቱን ተከትሎ የሚሮጥ ሰው የውድመት እና የሞት አደጋ ይደርስበታል፡፡
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
════════ ∘◦❁◦∘ ═════════
ወረተኛ አትሁን
◕———✷_✿_✷———◕

አሽ-ሸብሊ በአንድ ወቅት፦ "#ከረጀብና #ከሸዕባን የሚበልጠው የትኛው ነው?" የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። እርሳቸውም፦ "ሁሌም አላህን #የምታመልኩ ሰዎች ሁኑ እንጂ #ወረተኛ አትሁኑ።" ሲሉ መለሱ።

ይህ ንግግራቸው ጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚያመልክ፣ ሸዕባን ወር ላይ አላህን ተገዝቶ ቀሪውን ወራት አላህን የሚረሳን ሰው ለማሳሰብ ነው። #በረመዳን ወር እንባውን ሲያፈስ የነበረንና ከረመዷን ውጭ ባሉት ወራት እንባው #የደረቀውን ሰውም ይመለከታል።

ሁሉም የህይወት ዘመናቸው #ረመዷን የሆነላቸው የአላህ ምርጥ ባሮች ከወረተኞች ምንኛ የላቀ ደረጃ ላይ ናቸው?! የሌሊት ግዚያቸው #በሶላት ያልፋል፤ ቀናቸው በፆምና በዒባዳ።

#ወንድሜ_ሆይ! የአላህን መልትክኛ (ሰ.ዕ.ወ) ኮቴ ተከተል። ውድድርህን እስከምታጠናቅቅ ሥራህ ያለመቋረጥ ይቀጥል። በዚህ ሁኔታ ሆነህ ወደ #አኺራ ተጓዝ። የህይወትህ ፍጻሜ ይሁን።

"እውነትም (ሞት) እስኪመጣ ድረስ ጌታህን ተገዛ።" (አል-ሒጅር ፡99)

               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
════════ ∘◦❁◦∘ ═════════
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
ለሙታን ያለቅሳል እራሱን ዘንግቶ፣
የዕድሜውን መርዘም ከልቡ ሞግቶ፣
አዕምሮ ቢኖረው የሚያስተውል ፈጣን፣
እንባው ለራሱ እንጂ ባልሆነ ለሙታን።

ወንድሜ...
ዱንያ ህልም ናት፣ አኺራ ደግሞ ከእንቅልፍ መንቂያ ነው፤ በሁለቱም መካከል ሞት ይገኛል፤ እኛ አሁን ያለነው ቅዥት ውስጥ ነው።
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሚመለከተው ሁሉ!

ረመዳን ቀርቧል

በሀይድ፣ በወሊድ ፣ በህመም፣ በጉዞ ምክንያቶች ያለፈዉ ረመዳን ቀዳ ያለባቹ ሙስሊም ወንድም እህቶች በቀሩት ቀናቶች ቀዳቹን አዉጡ!


ጊዜዉ ገና ነዉ በማለት ተዘናግተን ሲያልፈን ፈትዋ ለመጠየቅ እንዳንሮጥ!
ያ ረብ ረመዷንን በሰላም አድርሰን ደርሰውም ከሚጠቀሙት አድርገን አሚንንንን...
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌾ሰባቱ የሙስሊም ባሕሪያት

የአንድ ሙስሊም ሕይወት በሰባት መሠረቶች ላይ ይቆማል። እነዚህም፦ በአላህ መፅሐፍ ሲመራ፣ የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሱናን ሲከተል፣ ሐላል የሆነ ምግብ ሲመገብ፣ ሌሎችን ከሚጎዱ ተግባራት ሲታቀብ፤ ከኃጢአቶች ሲርቅ፤ በየጊዜው ተውበት ሲያደርግ እና የሌሎች ሰዎችን መብቶች ሲያከብር። የጥንትም ሆኑ የዚህ ዘመን ታላላቅ ዑለማእ ይህን መስክረዋል። እያንዳንዱ ሙስሊም እነዚህን ሰባት መርሆዎች እንዲተገብር ይመክራል።
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️ልብህ በህይወት ውጣ-ወረድ
ሲጨልምብህ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ
ሰለዋት ማውረድን በማብዛት ብርሃናማ
አድርጋት ።
               ♻️ይቀላቀሉን♻️
@Halal_2Tube
═══════ ∘◦❁◦∘ ════════
2024/05/15 02:31:37
Back to Top
HTML Embed Code: