ሁለተኛው ''ቢላል የክብር እውቅና'' ስነስርዓት ተከናወነ
............

የተመሰረተበትን 25ኛ አመት የብር ኢዩቤልዩን በተለያዩ ስራዎች በማክበር ላይ የሚገኘው ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር  አመታዊውን ''የቢላል የክብር እውቅና'' ስነስርዓት በዛሬው እለት አከናወነ።

በተለያዩ ዘርፎች ለሙስሊሙ እና ለሃገር ውለታ የዋሉ፣ በሙያቸው፣ እውቀታቸው እና በተሰማሩበት ዘርፍ ተፅእኖ የፈጠሩ እንዲሁም ለትውልዱ አርአያ ተደርገው የሚጠቀሱ ግለሰቦችን በታሪክ ገፅ ላይ ህያው ለማድረግ  እና በሰፊው ለማስተዋወቅ የሚያስችለው የቢላል የክብር እውቅና በዛሬው እለት በደመቀ መልኩ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።

በክብር እውቅና መርሃግብሩ ላይ  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ትላልቅ ኡለማዎች፣ ምሁራን፣ የክብር እውቅና ተሸላሚ ግለሰቦች ቤተሰቦች ፣የቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር አባላትን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ እና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተገኝተዋል ።

በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ  በልዩ ተመስጋኝ ዘርፍ ለተመረጡት ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የተዘጋጀውን ሽልማት ያበረከቱት የቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር የበላይ ጠባቂ ሸይኽ መሀመድ ጀማል አጎናፍር ባደረጉት ንግግር  የቢላሉል ሐበሺ የ 25ኛ አመት የብር እዩቤልዩ በአል የመዝጊያ ፕሮግራም ህዳር 21 በሚሊንየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ገልፀው ለፕሮግራሙ ታዳሚያን በመዝጊያ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በዛሬው እለት የቢላል የክብር እውቅና በተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ግለሰቦችን ህይወት እና አበርክቶ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን ይህም ተመስጋኝ ባለውለታዎችን ለትውልዱ ለማስተዋወቅ እና አርአያ ለማድረግ ትልቅ አቅም የፈጠረ ሆኖ አልፍል።

በዛሬው ፕሮግራም የቢላል የክብር  እውቅና በ 6 ዘርፎች የተበረከተ ሲሆን እነዚህም :-

🔵በልዩ ተመስጋኝ ዘርፍ ለክቡር ሸይኽ ሙሐመድ ሑሴን ዓሊ አል-አሙዲ  የተሰጠ ሲሆን የተመረጡበትም ምክንያት  ለአገራችን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ባከናወኗቸው መጠነ ሰፊ የልማትና የኢንቨስትመንት ሥራዎች፣ እንዲሁም ለዜጎች ሕይወት መሻሻል በደግነት በፈፀሟቸው አያሌ በጎ ተግባራት ላሳዩት የላቀ የአገር ወዳድነት እና ላበረከቱት ወደር የለሽ አገራዊ አስተዋጽዖ  መሆኑ  ተገልጿል።

🔵በታሪክ እና በስነ ጽሁፍ ዘርፍ ለክቡር አቶ ወልደ ገብርኤል አሰጌ የተበረከተ ሲሆን የተመረጡበትም ምክንያት ስለ እስልምና ሃይማኖት ብዙም አይታወቅ በነበረበት በ1960ዎቹ አጋማሽ፣ እርሳቸው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ሆነው ሳለ፣ የነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) አጭር ታሪክ የሚል ርዕስ ያለው ምጥን መጽሐፍ በግል ጥረታቸው አዘጋጅተው በማሳተም፣ ለሕዝቦች መተዋወቅና መቀራረብ በቅን ልቦና ላበረከቱት አስተዋጽዖ መሆኑ ተገልጿል።

🔵 በአመራር ዘርፍ ለሸይኽ ሆጀሌ አል-ሐሰን ሙሐመድ የተመረጡ ሲሆን የተመረጡበትም ምክንያት
''በሕይወት ዘመናቸው በተግባር ያሳዩትን የዲኘሎማሲና የአመራር ጥበብ፣ ለፈፀሟቸውን በጎ ተግባራት እና ለአገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋጽዖ''  መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

🔵በጥናትና ምርምር ዘርፍ ፕሮፌሰር  ጀማል አብዱልቃድር የተመረጡ ሲሆን የተመረጡበትም ምክንያት ''በሕይወት ዘመናቸው በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሕክምና ጥናትና ምርምር መስክ ላደረጉት ከፍተኛ ምሁራዊ አስተዋጽዖ እና ለብዙ ዓመታት ለወገናቸው በትጋት ለሰጡት ሙያዊ አገልግሎት መሆኑ ተገልጿል።

🔵 በንግድና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለክቡር ሐጂ ሙሐመድ አብዱላሂ ኦክሰዴ የተሰጠ ሲሆን ይህም የሆነው ክቡር ሐጂ ሙሐመድ አብዱላሂ ኦክስዴ በህይወት ዘመናቸው ለአገራችን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ባከናወኗቸው መጠነ ሰፊ ሥራዎች፣ እንዲሁም ለዜጎች ሕይወት መሻሻል በፈፀሟቸው አያሌ በጎ ተግባራት ላሳዩት የላቀ የአገር ወዳድነት እና ላበረከቱት አገራዊ አስተዋጽዖ መሆኑ ተገልጿል።

🔵በበጎ አድራጎት ዘርፍ ለሐጂ አዳነ ማሙዬ የተመረጡ ሲሆን የተመረጡበትም ምክንያት በሕይወት ዘመናቸው  በተግባር ያሳዩትን የአገርና የወገን ወዳድነት፣ ለፈፀሟቸውን የልማትና የበጎ ተግባራት መሆኑ ተመላክቷል ።

የተዘጋጀውን የክብር እውቅና የ2ኛው የቢላል የክብር እውቅና ተሸላሚ ቤተሰቦች እና ተወካዮች ከክብር እንግዶች እና የቢላሉል ሐበሺ የበላይ ጠባቂ እና የቦርድ አመራሮች እጅ ተቀብለዋል።

መድረኩ ከክብር ሽልማቶቹ ባለፈ የተለያዩ የጥበብ ስራዎች እና የቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ጉዞ እና ስራዎች የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልምም የቀረበበት ሆኖ አልፏል ።
19👍4👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሐሙስ ምሽት ከ 2፡30 ጀምሮ
ለይለተል ጁሙዓ በዚህ ሳምንት
17
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለይለተል ጁሙዓ ፕሮግራማችን በዚህ ሳምንት ...........
የቢላሉል ሐበሺ ልማትና መረዳጃ እድር መስራች እና የበላይ ጠባቂ ከሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍር ጋር ቆይታ አድርገናል ።
በቆይታችን ከሸይኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍር የህይወት ልምድ እስከ ቢላሉል ሐበሺ የ 25 አመት ጉዞ ዳሰናል ።
ነገ ሐሙስ ምሽት ከ 2፡30 ጀምሮ በሐሪማ ቴሌቭዥን እና ዩቲውብ ይጠብቁን ..

ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍር ስለ ሐበሻ ዑለማዎች ስብዕና ካካፈሉን ውስጥ በጥቂቱ እነሆ ....
24
የደጋጎች ሰብሳቢ
...........................
ብዙ ሰዎች በዝምታቸው ያውቋቸዋል። ሌሎች እርጋታ በተሞላው አነጋገራቸው ይወዷቸዋል።መላው ህይወታቸውን በዳዕዋ እና ዲን ኺድማ አሳልፈዋል ሸይክ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍር።

ከዛሬ 25 አመት በፊት በዙሪያቸው የነበሩ ደጋግ ሰዎችን በማስተባበር ድጋፍ እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎችን የመደገፍ እና የመርዳት ስራዎችን ይሰሩ ነበር ። ይህ በደጋግ ግለሰቦች ተነሳሽነት የተጀመረው መልካም ስራ አድጎ ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር በመባል ተቋማዊ በሆነ መንገድ መጓዝ ከጀመረ እነሆ 25 አመታትን ደፍኗል ።

ቢላሉል ሐበሺ ባለፉት 25 አመት ውስጥ በርካታ የቲሞችን አስተምረዋል፣ የታመሙትን አሳክመዋል፣ በዚዎች ሚቆጠሩ ሰዎችን ከ መዋዕለ ህጻናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት እና ሙያ ትምህርቶች አስተምረዋል በማስተማር ላይ ይገኛሉ። የቀብር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የደጋጎች ሰብሳቢ እና የቢላሉል ሐበሺ መስራች እና የበላይ ጠባቂ የሆኑትን ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍርን በዛሬው ለይለተል ጁሙዓ ፕሮግራማችን እንግዳችን አድርገናቸዋል።

ከምሽቱ 2፡30 ጀምሮ በሐሪማ ቴሌቭዥን እና ዩቲውብ ይከታተሉ
28👍2
የደጋጎች ሰብሳቢ ከሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍ ጋር በለይለተል ጁሙዓ ፕሮግራማችን ያደረግነውን ቆይታ ከ 2፡30 ጀምሮ
በሐሪማ ቴሌቭዥን
___________________
በኢትዮ-ሳት
Frequency - 11545
Symbol rate - 45000
Polarisation - H

ወይም በዩቲውብ
https://youtu.be/5tIAJnNUlEU

ይከታተሉ
11👍8
ለይለተል ጁመዓ ዛሬ ምሽት 2፡30 ጀምሮ
18🥰18
🙏51😭2518💔7👍4
2025/10/19 05:54:26
Back to Top
HTML Embed Code: