Telegram Web Link
▫️ዐምር ኢብነል ጀሙህ ረድየላሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~2

በሚቀጥለው ለሊት እነኚህ ወጣቶች ከቦታው በመውሰድ ያንኑ ድርጊት በድጋሚ ፈፀሙ። ዐምር ፈለገ በቆሻሻ ተጨማልቃ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ውስጥ አገኛት። አነሳት አጥቦ ሽቶ አርከፍክፎ ወደ ቀድሞ ቦታዋ መለሳት። ወጣቶች በየቀኑ ይህን ድርጊት ይደጋግማሉ። ግራ ተጋባ ዐምር። ከመተኛቱ በፊት በአንቷ ላይ ሰይፍ አንጠለጠለባት በመናት አንገት። የሚተናኮላትን እንድትሰይፍበት።
«መናት ሆይ! ማን እንደሚተናኮልሽ በትክክል አላወቅኩም። አቅሙ ካለሽ እራስሽን ተከላከይ።» አላትና ወደ መኝታው ሄደ። ዐምር ጥልቅ እንቅልፍ ወስዶታል። ወጣቶች ወደ መናት በመሄድ ሰይፉን ከአንገቷ አውርደው ይዘው ወጡ። ከሞተው ውሻ ጋር በገመድ በማቆራኘትም ቆሻሻ ውሃ ከሚጠራቀምበት ጉድጓድ ውስጥ ጨመሯት።

ሽማግሌው ዐምር ከመኝታው ተነስቶ መናትን ከቦታዋ አጣት። ፍለጋ ጀመረ። ከቆሻሻ ጉድጓድ ውስጥ በግንባሯ ተደፍታ ከሞተ ውሻ ጋር ተቆራኝታ አገኛት። ሰይፍ በአንገቷ ላይ አልነበረም። ከጉድጓድ ውስጥ አላወጣትም። «አምላክ ብትሆኚ ኖሮ ከሞተ ውሻ ጋር ከቆሻሻ መጣያው ተቆራኝተሽ ባልተገኘሽ ነበር።» በማለት ትቷት ሄደ። ብዙም ሳይቆይ ኢስላምን ተቀበለ።

•••✿❒🌹❒✿•••

ዐምር ኢብኑ ጀሙህ የኢማንን ልዩ ለዛ አጣጣመ። በሽርክ ያሳለፋት እያንዳንዷ ከንቱ ደቂቃ ትቆጨው ጀመረ። መላ እሱነቱ ለአዲሱ እምነት (ለኢስላም) አስረከበ። አካሉን፣ መንፈሱን፣ ገንዘቡን፣ ልጆቹን ኢስላምን ለማገልገል ተግባር አዋለ። አላህን እና ረሱልም ﷺ ለመታዘዝና ለማርካት ጥረት ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ የእሁድ ዘመቻ ተከሰተ። ሶስቱ ልጆቹ የአላህን ጠላት ለመፋለም ዝግጅት ላይ ናቸው። ሸሂድ ለመሆን አላህን በማርካት ለስኬት ለመብቃት ጓጉተዋል። ውስጣዊ ስሜቱን ቀሰቀሱበት። በረሱል ﷺ አመራር ስር ኡሁድ የፍልሚያ መስክ ላይ ለመገኘት ቆረጠ። ልጆቹ ግን ተቃወሙት። አባታቸው ሽማግሌ ነው እድሜው በጣም ገፍቷል። አንድ እግሩም ሽባ ነው። አላህ ጂሃድን ግዴታ አላደረገበትም። ስለዚህ ባይዘምት ይመረጣል።ነገር ግን በአቋማቸው ፀኑ። « አባታችን ሆይ! አላህ ጂሃድን በአንተ ላይ ግዴታ አላደረገብህም ለምን እራስህን ታስጨንቃለህ?» ዐምር በልጆቹ ውሳኔ በእጅጉ ተቆጣ። ከረሱል ﷺ ዘንድ በመሄድ ስሞታውን ተናገረ።
«የአላህ ነብይ ﷺ ሆይ! እነኚህ ልጆቼ ከዚህ በጎ ነገር ሊያቅቡኝ ይሻሉ። ሽባ ነህና ጂሃድ አትሂድም ይሉኛል። በአላህ ይሁንብኝ በዚች ሽባ እግሬ ጀነትን መርገጥ እፈልጋለሁኝ።» አላቸው።
«ይዝመት ምናልባትም አላህ ሰመእት የመሆን ታላቅ እድል ይሰጠው ይሆናል።» አሉ መልዕክተኛው ﷺ ለልጆቹ። ልጆቹ የረሱልን ﷺ ትዕዛዝ አከበሩ።

የኡሁድ ዘመቻ ወቅት ደርሷል። ዐምር ኢብኑ ጀሙህ ባለቤቱን ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናበተ። ከዚያም ወደ ቂብላ በመዞር ፊቱን ወደ ሰማይ አቅንቶ፦ «አላህ ሆይ! ሸሂድ የመሆንን እድል ለግሰኝ። ወደ ቤተሰቦቼ ከነህይወቴ እንዳትመልሰኝ።» ሲል ዱዓ አደረገ። በሶስቱ ልጆቹና በበርካታ የአንሷር ተዋጊዎች ተከቦ ወደ ዘመቻ ሄደ።

•••✿❒🌹❒✿•••

ጦርነቱ ተጋግሟል። ሰዎች ﷺ ጎን እየራቁ ነው። ዐምር ኢብነል ጀሙህ ከረሱል ﷺ ጎን ቆሟል። በደህናው እግሩ እየዘዘለ ይፋለማል። «ጀነትን ለመጎናፀፍ በእጅጉ ጓጉቻለው ይላል።» ከበስተጀርባው ልጁ ኸልላድ ነበረ። አምርና ልጁ ነብዩ ሙሃመድ ﷺ በፅናት ይከላከላሉ። ዐምር የሚችለውን ሁሉ ካደረገ በኋላ ተመቶ ወደቀ። ሸሂድም ለመሆን በቃ። ብዙም ሳይቆይ ልጁም ተከተለው። አባትና ልጅ የክብር ሞት ለመሞት ታደሉ።

ጦርነቱ ተጠናቋል። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የእሁድ ሸሂዶች ለመቅበር ተዘጋጅተዋል። «ከነደማቸውና ቁስላቸው ተዋቸው። እኔ መስካሪያቸው ነኝ።» ካሉ በኋላ፦ «በአላህ መንገድ ላይ የሚቆስል ሙስሊም የቂያማ ቀን ደሙ የሚፈስ ሆኖ ይመጣል። የደሙ ቀለም አበባ ይመስላል። ሽታው እንደሚስክ ይሸታል።» አሉ። በመቀጠልም፦ «ዐምር ኢብነል ጀሙህ እና አብደሏህ ኢብኑ ዐምርን ጎን ለጎን ቅበሯቸው። በህይወት እያሉ እጅግ ይፋቀሩ ነበረ።» አሉ።

•••✿❒🌹❒✿•••

ለአምር ኢብነል ጀሙህ እና ለሌሎች የኡሁድ ሰማእት ጀግኖች የአላህ እዝነት ይስፈንባቸው። ቀብራቸውን አላህ ብርሃን ያድርግላቸው።

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
Forwarded from Deleted Account
🌱ጅማ ዩኒሸርሲቲ ለተመደባችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የአላህ ፍቃድ ሆኖ ከረጅም ግዜ በኅላ የ12ተኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተናችሁን ተፈትናቹ አልፋችኅል (الحمد لله)። ከዚህም አልፎ አላህ ፈልጋችሁም ሆነ ሳትፈልጉ ጅማ ዪኒሸርሲቲን በመወፈቅ እድላችሁን አሳምሮላችኅል በድጋሚ (الحمد لله)። ታድያ በዚህ ጊዜ ሁሉም አዲስ ተማሪዎች ጊቢ ከመግባታቸው በፊት ጊቢ ሲገቡ ምንም ነገር እንዳይደርስባቸው በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ተማሪን ለመተዋወቅ ይጨነቃሉ ። ታድያ በዚህ ምክንያት ብዙ አህቶች አና ወንድሞች በማያውቁት ወይም በአጉል ሰው እጅ ውድቀው ከተፈጠሩለትና ከመጡለት አላማ ውጭ ሆነው ከመስጅድ እና ከሙስሊሞች ጀመአ ርቀው በአጉል ቦታ ወድቀው ይታያሉ። እናም ይህ ችግር በአዲስ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እንዳይደርስ በሚል የጅማ ዪኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ, አዲስ ጅማ ዪኒቨርሲቲ የተመደቡ ሙስሊም ተማሪዎችን ለመቀበል ምቹ ሁኔታን ፈጥሮ እየጠበቃችሁ ይገኛል። ከዚህ ዝግጅት ውስጥ አንዱ እናንተ በምትመጡበት ወቅት የጀመአው አሚሮች እናንተን እንዲቀበሉ የተመደቡ ልጆች ብቻ እንዲቀበሏችሁ ማድረግ ነው። ይህም እናንተ ወደ ቂርኣት, ወደ መስጅድ እና ወደ ጀመኣ እንድትቀርቡ እና በማንም መጥፎ ተንኮል እንዳትተነኮሎ ያግዛችኅል። ታድያ ይህን ስራ ለመስራት ከእናንተ የሚጠበቀው ጀመአው ከናንተ የሚፈልገውን ኢንፎርሜሽን በተዘጋጀው ቴሌግራም ቦት መሙላት ብቻ ነው። ከዚህም በዘለለ ማወቅ የምትፈልጉትን ኢንፎርሜሽን ሁላ በተዘጋጀው የአሚሮች ቁጥር በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።
#Register by Clicking here👇
@kjumj_official_bot
🌼#For_More_info. .Call_Now 👇
🇸🇦Main Campus Amir
+251 92 216 8415
🇸🇦 Agriculture and Veternary Campus Amir
+251 93 047 4983
🇸🇦Business and Economics Campus
+251 94 776 9852
🇸🇦Institute of Technology Campus
+251 91 077 0081
#Share and forward to Ur Brothers and Sisters.
👌To get Female Amirs Phone No. Ask Male Amirs

[🌸🌸"አላህ በሰላም ያገናኘን"🌸🌸 ]
.......... {💐💐 "ትናፍቁናላችሁ"💐💐}.......

💎Join ur Channel prepared for 1st year students only Now👇
@JUMJ2013
▫️አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም

▪️ክፍል~1

«አይነ ስዉር ነዉ። እርሱን በተመለከተ አላህ ቁርኣን ዉስጥ 16 አንቀፆችን አስፍሯል። እስካሁን ድረስ ይነበባል። ወደፊትም እንዲሁ»
(የቁርኣን ምሁራን።)

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም ረዲየላሁ ዐንሁ የሙኢሚኖች እናት የነበሩት የኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየላሁ ዐንሃ ፥የአጎት ልጅ ነበር። አባቱ ቀይስ ይባላሉ እናቱ ደግሞ ዐቃቲህ ቢንት አብደላህ ነበሩ። እናቱ ኡሙ ሠክቱም ማለትም "የተጋረደዉ ልጅ እናት" ተብለዉ ይጠሩ ነበር። አይነ ስዉር ልጅ በመዉለዳቸዉ።

አብደላህ የኢስላምን በመካ መነሳት አይቷል። ኢስላምን በመጀመሪያ ከተቀበሉት ሰዎች መካከል ዉስጥ አንዱ ሲሆን የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሀባዎች የደረሰባቸዉን ስቃይ ሁሉ ተቀብሏል። ልክ እንደነሱ ቆራጥ ፣ ታማኝ ፣ አይበገሬና ለመስዋዕትነት ዝግጁ ነበር። የቁረይሽ የከፋ ጥቃት ከዓላማ ፅናቱም ሆነ ከእምነቱ አላደከመዉም። በእርግጥም ይህ ሁሉ የአላህን « ዲን» እንደያዘ ለመቆየት የነበረዉን ቁርጠኝነትና ለመልእክተኛዉ የነበረዉን ታማኝነት የበለጠ አጠንክሮት ነበር።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

አብደላህ ለተከበሩት ነቢይ ﷺ ታዛዥ ነበር። ቁርኣንን በአዕምሮዉ ለማንጠንጠን ከፍተኛ ጉጉት ነበረዉ። የልቡን ፍላጎት ለማሟላት ሲል አንዲትም አጋጣሚ አያሳልፍም። ነብዩ ﷺ የቁረይሽ ታዋቂ ሰዎችን በማስተማር ሙስሊሞች እንዲሆኑላቸዉ ከፍተኛ ምኞት ነበራቸዉ።
በዚህ መሠረት አንድ ቀን ከኡትባህ ኢብን ረቢእ እና ከወንድሙ- ሸይባ፥ ከአምር ኢብን ሂሻም (አቡጃህል በመባል ይታወቃል) ፥ ከዑሙያህ ኢብን ኸለፍና ወሊድ ኢብን ሙጊራ (የኻሊድ ኢብን ወሊድ አባት) ጋር ተገናኙ። ስለ ኢስላም መናገርና ከእነሱም ጋር መወያየት ጀመሩ። አዎንታዊ መልስ እንዲሰጣቸዉ ፥ ኢስላምን እንዲቀበሉ ወይንም ቢያንስ በሙስሊሞች ላይ የሚያደርሱትን ስቃይ እንዲያቆሙ በፅኑ ተመኙ። በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም ረዲየላሁ ዐንሁ መጣና አንዲት የቁርኣን አንቀፅ እንዲያነቡለት ጠየቃቸዉ። «አላህ ካስተማረዎት መካከል ለእኔም አስተምሩኝ።» አላቸዉ።

ነብዩም ﷺ ግንባራቸዉን ጨፍግገዉ ከእሱ ዞር አሉ። እሳቸዉም የቁረይሽ ሹማምንት ይሰልሙ ይሆናል፣ ኢስላምን በመቀበላቸዉ ደግሞ የአላህን «ዲን» ያልቃሉ፥ የእሳቸዉንም መልዕክት ያጠነክራሉ ብለዉ ተስፋ በማድረግ ትኩረታቸዉን ከሱ ይልቅ ለነሱ ሰጡ። የጀመሩትን ለመጨረስ ሀሳባቸዉን ወደ ቁረይሽ ባላባቶች አዞሩ። ለነሱ መናገራቸዉን ጨረሱና ተሰናበቱ። በድንገት ያለመረጋጋት ስሜት ይሰማቸዉ ጀመር። ራሳቸዉም ተበጠበጠ። የሚከተለዉም «ወህይ» ወረደ ላቸዉ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

《"ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፤ ዕዉሩ ስለ መጣዉ።ምን ያሳዉቅሃል? (ከኃጢአቶቹ) ሲጥራራ ይከጀላል።ወይም ሲገሠጽ፥ ግሣጼይቱም ልትጠቅመዉ (ይከጀላል) ። የተብቃቃዉ ሰዉማ፤ አንተ ለርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ ፤ ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፤ እየገሰገሠ የመጣህ ሰዉማ፤ እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ አንተ ከርሱ ትዘናጋለህ ። ተከልከል፤ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት። የሻም ሰዉ (ቁርኣኑን) ያስታዉሰዋል። በተከበሩ ጽሑፎች ዉስጥ፤ ከፍ በተደረገች፥ ንፁህ በተደረገች፥ (ጽሑፍ ዉስጥ ነዉ) ። በጸሐፊዎቹ (መልእክት) እጆች፥(ንጹሕ የተደረገች)። የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት፤ (ጸሐፊዎች እጆች) ።》 {ዐበሰ ፥1-16}

እነዚህ አሥራ ስድስት አንቀጾች ነበሩ ስለ አብደላህ ኢብን ኡሙ መኽቱም ለነብዩ ﷺ የወረዱት።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ እየተነበቡ ናቸዉ። ወደፊትም ይነበባሉ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ነብዩ ﷺ አብደላህ ኢብን ኡሙ መኽቱምን ጉዳዩን ከመጠየቅ ፍላጎቶቹን ከማሟላት እና በቀረባቸዉ ጊዜም ከማማከር አላቆሙም።
በእርግጥም ከዚያ በኃላ ባሉ አመታት ለኢብኑ ኡም መኽቱም ሰላምታ የሰጡት፦ «መጠጊያዬ በሆነዉ ፈጣሪዬ እንድገሰፅ ያበቃኸኝ እንኳን ደህና መጣህ» በሚል ራስን ዝቅ በሚያደርግ ሐረግ ነበር።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ቁረይሽ፥ ከነቢዩና ከእርሳቸዉ ጋር ባመኑት ላይ ይደረስ የነበረዉን ስቃይ ባጠነከሩ ጊዜ፥ አላህ እንዲሰደዱ (መካን ለቀዉ እንዲሄዱ) ፍቃድ ሰጣቸዉ። የአብደላህ ምላሽ ፈጣን ነበር። ከሶሃባዎች መጀመሪያ መዲና የደረሱት እሱ እና ሙስዓብ ኢብን ዑመይር ረዲየላ ሁዐንሁ ነበሩ።

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️አብደላህ ኢብን ኡሙ መኽቱም

▪️ክፍል~2

እሱና ሙስዓብ ልክ የስሪብ እንደደሱ ከህዝቡ ጋር መወያየት፥ የአላህን «ዲን» ማስተማር ጀመሩ ። ነብዩ ﷺ ልክ መዲና እንደረሱ አብደላህ እና ቢላል ኢብን ረባህን ረዲየላሁ ዐንሁ ለሙስሊሞች «ሙዓዚን» ነት ሾሟቸዉ። ስለዚህ በቀን አምስት ጊዜ የአላህን አንድነት በማስተጋባት ከበጎ ነገሮች ሁሉ ወደተወደደዉና በድል ወደሚያበቃዉ ድሬጊት-ሶላት - ሰዎችን መጣራት ጀመሩ።

ቢላል ለስግደት (ለሶላት) አዛን (ጥሪ) ሲያደርግ አብደላህ ኢብን ኡሙ መኽቱም ረዲየላሁ ዐንሁ ደግሞ ሶላት ሊጀመር መሆኑን የሚያበ ስረዉን የመጨረሻ አዛን (ኢቃማ) ያሰማ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በመቀያየር ያደርጉ ነበር። በረመዷን ጊዜ የተለየ መደበኛ ሥራ ነበራቸዉ። አንዳቸዉ ሰዉን ከእንቅልፉ በማንቃት ጾም ከመጀመሩ በፊት እንዲመገብ ለመቀስቀስ አዛን (ጥሪ) ሲያደርጉ ሌላኛዉ ደግሞ መንጋቱን፥ ለማብሰር፥ "አዛን" ያሰማል። ሕዝቡን የሚያነቃዉን ጥሪ የሚያደርገዉ ቢላል ሲሆን ፥ መንጋቱን የሚያበስረዉ ደግሞ አብደላህ ነበር።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ነብዩ ﷺ ለአብደላህ ኢብን ኡሙ መኽቱም ረዲየላሁ ዐንሁ ሰጥተዉት ከነበረዉ ኃላፊነቶች መካከል እሳቸዉ በማይኖሩበት ጊዜ የመዲና አስተዳዳሪ ሆኖ መሥራት ነበር። ይህ ከአሥር ጊዜ በላይ የተደረገ ሲሆን ከነዚህም አንዱ መካን ነጻ ለማዉጣት በሄዱበት ወቅት ይገኝበታል።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከበድር ጦርነት በኃላ ነብዩ ﷺ ሙጃሂዲን (ሙስሊም ተዋጊዎች) ያላቸዉን ደረጃ ከፍ የሚያደርግና እቤታቸዉ ሳይንቀሳቀሱ ከቀሩት የሚያልቅ «ወህይ» ተቀበሉ።
ይህም የሆነዉ ሙጃሂዶችን የበለጠ ለማበረታትና ከጂሃድ የሚያፈገፍጉትን ደግሞ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነበር። ይህ «ወሕይ» ኢብን ኡሙ መኽቱምን ክፉኛ ነካዉ።

ከታላቅ ደረጃ መገለሉ ተሰምቶት ነበርና እንዲህ አለ፦ «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ጂሃድ መሄድ ብችል ኖሮ ያለጥርጥር እወጣ ነበር።» በማለት ሀዘኑን ገለጸ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም በአካለ ስንኩልነታቸዉ የተነሳ ወታደራዊ ዘመቻ ለመሄድ ያልቻሉ ሰዎች አምላክ ራዕይ (ወሕይ) እንዲያወርድላቸዉ በፅኑ ተማፀነ። ዱዓዉም ምላሽ አገኘ። አካለ ስንኩ ልነትያለባቸዉ ሰዎች ከመጀመሪያዉ አንቀፅ ነፃ እንደሆኑ የሚገልፅ ተጨማሪ ሐረግ ለነብዩ ﷺ ወረደላቸዉ።

ሙሉ አንቀፅ እንዲህ ይነበባል፦ 《ከምዕመናን የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር ተቀማጮቹና፥ በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸዉና በነፍሶቻቸዉ የሚታገሉት አይስተካከሉም፥. ..》 [አል- ኒሳእ፥ 95]

በዚህ ዓይነት አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም ረዲየላሁ ዐንሁ ከጂሀድ ነፃ ቢደረግም፥ ዘመቻዉ እየተባባሰ ባለበት ወቅት እቤት ዉስጥ ከሚዉሉት ጋር መቆየቱን አዕምሮዉ መቀበል አቃተዉ። ታላቅ አዕምሮዎች ከታላቅ ወቅታዊ ጉዳዮች ተነጥለዉ መቅረት አያረካቸዉም።
እሱም አንዳችም ዘመቻ እንዳያመልጠዉ ወሠነ። በጦር ሜዳ ዉስጥ እሱ ሊጫወት የሚችለዉ አንድ ሚና አቀደ። «በሁለት ረድፎች መካከል አድርጉኝና ባንዲራዉን ስጡኝ። እኔ እይዝላችኀለሁ፤ እጠብቅላችኀለሁም። ምክንያቱም እኔ አይነስዉር ስለሆንኩ መሮጥ አልችልም» ይል ነበር። ከሂጅራ በኃላ በአስራ አራተኛዉ ዓመተ፥ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የፋርስን መንግስት ለመጣልና ለሙስሊም ኃይሎች መንገድ ለመክፈት ፥ ከባድ ጥቃት ለመክፈት ወሰኑ። ለአገረ ገዥዎቻቸዉ፦ « የጦር መሳሪያ ወይም ፈረስ ያለዉን ወይንም ለኔ ማንኛዉንም አይነት እርዳታ ማድረግ የሚችል ማንኛዉንም ሰዉ በፍጥነት ላኩልኝ፣» በማለት ደብዳቤ ፃፉላቸዉ።
መላዉ ሙስሊም የዑመርን ረዲየላሁ ዐንሁ ጥሪ በመቀበል በመዲና ተሰባሰበ። ከነዚህም መካከል አይነስዉሩ ሙጃሂድ፥ አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም ረዲየላሁ ዐንሁ ይገኝበት ነበር። ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ፥ ሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስን ረዲየላሁ ዐንሁ የጦር መሪ አድርገዉ ሾመዉ ትዕዛዝ ከሰጡት በኃላ አሰናበቱት።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ሠራዊቱ ቃዲሲያ በደረሰበት ጊዜ አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም የጦር መከላከያ ጥሩር ለብሶና በደንብ ተዘጋጅቶ በግንባር ቀደምትነት ይታይ ነበር። የሙስሊሞችን ባንዲራ ለመያዝና ለመጠበቅ ወይም በሂደቱ ላይ እያለ ለመገደል ቃል ገብቶ ነበር። ሁለቱ ሠራዊቶች ተገናኝተዉ ለሦስት ቀናት ተዋጉ። ጦርነቱ በሙስሊሞች የፍልሚያ ታሪክ ዉስጥ ኃይለኛና መራራ እንደነበር ይታወሳል። በሦስተኛዉ ቀን፥ በዓለም ላይ ከነበሩት ታላላቅ ግዛቶች (ኢምፓየርስ) መካከል አንዱ የሆነዉ ተገርስሶና እጅግ ጥብቅ የነበረዉ ዙፋኑ ወድቆ ሙስሊሞች ወደር የለሽ ድል ተቀናጁ።

በጣዖት አምላኪዎች ምድር ላይ ከሺርክ (ከብክለት) የፀዳ እምነት ባንዲራ ተተከለ። ይህ ድል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት የደም ዋጋ ጠይቋል። ከነዚያም መካከል አብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም ረዲየላሁ ዐንሁ ይገኝበታል። በጦር ሜዳ ዉስጥ የሙስሊሞችን ባንዲራ እንደ ያዘ ነበር ሞቶ የተገኘዉ።

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲደላሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~1

«የኢብን ዑመርን ያህል የነብዩን ፈለግ (ሱናን) የተከተለ ማንም የለም» {አዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ}

በመዲና እና በኡሁድ መካከል ባለዉ መንገድ ላይ በምትገኘዉ ሻይኻን፥ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይመራ የነበረዉ አንድ ሺህ የሙስሊም ጦር ለሶላት ቆመ። ፀሃይ በአድማስ በታች መጥለቅ ጀምራለች።ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳክብ ከተባለዉ ፈረሳቸዉ ላይ ወረዱ። የተሞላ የዉጊያ ልብስ አድርገዋል። በብረት ቆባቸዉ ላይ ጥምጣም ታስሯል። የደረት መከላከያ ልብስ (ጡሩር) አጥልቀዋል። ከሥሩ ደግሞ የሰይፋቸዉ ማንገቻ የታሠ ረበት የሆድ ዕቃ መከላከያ የብረት ልብስ (ጡሩር) አለ። በጀርባቸዉ ላይ አንድ ጋሻ ተሸክመዋል። ሰይፋቸዉ ከጎናቸዉ በኩል ተንጠልጥሏል። ፀሐይ እንደጠለቀች ቢላል አዛን አደረገና ሰገዱ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወታደሮቻቸዉን ለሁለተኛ ጊዜ ተዘዋዉረዉ ተመለከቱ። ምንም እንኳ ዕድሜያቸዉ አነስተኛ ቢሆንም በዉጊያዉ ላይ ለመካፈል የተመኙ ስምንት ልጆች በመካከላቸዉ መኖራቸዉን የተገነዘቡት በዚህ ጊዜ ነበር። ከእነሱ መካከል የዘይድ ልጅ ዑሳማህና የ ዑመር ልጅ አብደላህ ይገኙበት ነበር። ሁለቱንም የአስራ ሶስት ዓመት ልጆች ነበሩ። ሁሉም በአስቸኳይ ወደየቤታቸዉ እንዲመለሱ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አዘዙዋቸዉ ። ከልጆቹ መካከል ሁለቱ ብቃት ያላቸዉ ተዋጊዎች መሆናቸዉን ስላሳዩ ወደ ኡሁድ ዉጊያ ከሚያመራዉ ጦር ሠራዊት ጋር አብረዉ እንዲሄዱ ሲፈቀድላቸዉ፥ ሌሎቹ ግን ወደየቤተሶቦቻቸዉ ተላኩ።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ገና በልጅነት ዕድሜዉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነበሩባቸዉ ግዳጆች ሁሉ ላለመለየት የነበራቸዉን ከፍተኛ ጉጉት ያሳዬዉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ነበር። ኢስላምንም የተቀበለዉ ገና አሥር አመት ሳይሞላዉ ነበር።
ከአባቱና የኀላኃላ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችዉ ሃፍሷህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከተባለች እህቱ ጋር ሂጅራህ አድርጓል (ተሰደዋል)።
ከኡሁድ በፊት ከበድር ጦርነትም እንዲ መለስ ተደርጎ ነበር። እሱና ኡሳማህ በዚያን ጊዜ ሁለቱም የአሥራ አምስት ዓመት ልጆች ሆነዋል።እንዲሁም በእነሱ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሌሎች ልጆች ለምሽግ ቁፋሮ ብቻ ሳይሆን ጊዜዉ ሲደርስ ለዉጊያም ጭምር ከሌሎቹ ሰዎች ረድፍ እንዲቀላቀሉ እስከ ምሽጉ ጦርነት ድረስ አልተፈቀደላቸዉም ነበር።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ሂጂራ ካደረገት ጊዜ አንስቶ ከ 70 ዓመት በላይ ቆይቶ እስከ ሞተበት ዕለት ድረስ ኢስላምን በማገልገል አቻ የለሽ ክብር ተጎና ጽፏል።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

አቡ ሙሳ አል-አሺዐሪይ እንዳሉት ከሆነ 《አብደላህ በሙስሊሞ ች ዘንድ «ጥሩና የጥሩ ሰዉ ልጅ »ተደርጎ ይታይ ነበር። በዕዉቀቱ ፣ በትህትናዉ ፣ በቸርነቱ፣ በመልካም ፀባዩ፣ በሃቀኝቱ፣ ከንቅዘት የፀዳ በመሆኑ እና በዒባዳዎች ላይ በነበረዉ ጽናቱ ይታወቃል። ከታላቁና እጅግ ከተከበሩ አባቱ ከዑመር ብዙ ተምሯል። ሁለቱም ከሁሉም በላይ ታላቅ መምህር ከነበሩት የአላህ መልእክተኛ-ሙሐመድ -የመማር ዕድል ተጠቃሚዎች ሆነዋል።

ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በተለያዩ ሁኔታዎች ያደረጉት የነበረዉን እያንዳንዱ ንግግር ወይም ይፈፅሙት የነበረዉን ድርጊት አብደላህ በቅርብ ሆኖ ይከታተላል።
የተከታተለዉንም በትጋት ተግባራዊ ያደርግ ነበር። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ሶላት ሲሰግዱ አይቶ ከሆነ፥ የኀላ ኀላ አብደላህ በዚያችዉ ቦታ ላይ ይሰግድባት ነበር። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁመዉ ዱዓ (ፀሎት) ሲያደርጉ አይቶ ከሆነ እሱም ቁሞ ዱዓ ያደርጋል።

በመንገድ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከግመላቸዉ ላይ ወርደዉ ሁለት ረከዓ ሶላት ሲሰግዱ አይቶና በዚያዉ መንገድ የመሄድ ዕድል አጋጥሞት ከሆነ እዚያችዉ ቦታ ላይ ቆሞ ሁለት ረከዓ ይሰግዳል። አንድ ጊዜ መካ ዉስጥ በአንድ ቦታ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከግመላቸዉ ላይ ወርደዉ ሁለት ረከዓ ከመስገዳቸዉ በፊት ግመሏ ሁለት ጊዜ ተሽከርክራ (ዞራ) ስትቆም ይመለከታል። በርግጥ ግመሏ ያንን ያደረገችዉን በአጋጣሚ ሊሆን ይችላል። አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ በሌላ ጊዜ እዚያ ቦታ የመገኘት እድል ሲገጥመዉ ግን ግመሉ ተንበርክካላት ከመዉረዱ በፊት ሁለት ጊ ዜ እንድትሽከረከር ነበር ያደረጋት።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ከዚያም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲያደርጉ ባየዉ ሁኔታ ዝንፍ ሳይል ሁለት ረከዓ ሰገደ። አዓሻ ረዲየላሁ ዐንሃ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩ ሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፈለግ ለመከተልና ለመተግበር አቻ እንደማ ይገኝለት መስክራለች።

አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባራት በቅርብ ሆኖ ሲከታተል የነበረ ይሁን እንጂ የእሳቸዉን ንግግሮች ሲዘግብ ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ከማድረግ አልፎ ይፈራም ነበር። አንዲት ሐዲሥ ይናገር የነበረዉ ቃል በቃል እንደሚያስተዉሳት ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ከሆነ ብቻ ነበር። «ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሃባዎች (ባልደረቦች) መካከል፣ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲስ ላይ ላለመጨመር ወይም ላለመቀነስ ከአብደላህ ኢብን ዑመር የበለጠ ጠንቃቃ ሰዉ ማንም አልነ በረም።» ሲል ከእሱ ዘመን ሰዎች መካከል አንደኛዉ መስክሮለታል።

ሕጋዊ ፍርድ (ፈትዋ) ለመስጠትም የዚያኑ ያህል ሲበዛ ጠንቃቃና የማይዳፈር ሰዉ ነበር። አንድ ጊዜ አንድ ሰዉ መጥቶ በአንድ በተወሰነ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጠዉ ይጠይቀዋል። በዚህ ጊዜ አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ «ስለ ጠየቅኸዉ ነገር ምንም ዕዉቀት የለኝም።» ሲል መለሰለት። ሰዉየዉ በመጣበት ተመልሶ ሄደ ። አብደላህ በደስታ እጆቹን እያጨ በጨበ ለራሱ «የዑመር ልጅ ስለ ማያዉቀዉ ነገር ተጠይቆ አላዉቅም አለ።» በማለት ተናገረ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ምንም እንኳ ቃዲ (ዳኛ) ለመሆን የሚያስችል ብቃት ቢኖረዉ እሱ ግን ለመሆን የሚሻ አልነበረም። የቃዲ ደረጃ በሙስሊሙ ኅብረተሰብና መንግሥት ዉስጥ ካሉት እጅግ ጠቃሚና የተከበሩ ሥልጣናት አንዱ በመሆኑ ክብርና አድናቆት የሚያስገኝ ቢሆንም ይህ ሹመት በኸሊፋዉ ዑስማን ረዲየላሁ ዐንሁ በተሰጠዉ ጊዜ ሳይቀበለዉ ቀርተዋል። ለዚህ የነበረዉ ምክንያት የቃዲን ሥልጣን አስፈላጊነት በመናቁ ሳይሆን ከኢስላም ጋር በሚያያዙ ጉዳዮች ላይ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ስህተቶችን እንዳይፈፅም ከነበረዉ ሥጋት በመነጨ ነዉ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ዑስማን የዳኞችንና የሕግ ስራ በሚያከናወኑ በርካታ ሌሎች የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሃባዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳድር ይሆናል በሚል አብደላህ የሚሰጠዉን የራሱን ዉሳኔ ለሰዎች እንዳይናገር አግባብተዉት ነበር።

አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ «የጨለማዉ ወንድም» ለመባልም በቅቷል። ሌሊቱን ሶላት በመስገድ እያለቀሰ የአላህ ምህረት ይለምናል። ቁርኣን ሲያነብ ያድራል። ለዚህ ያበቃዉ አጋጣሚ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለእህቱ ሀፍሷ ቢንት ዑመር «አብደላህ ምን የተባረከ ሰዉ ነዉ። የሌሊት ሶላት ቢሰግድ ደግሞ ከዚህ በበለጠ ይባረካል።» ብለዉ ነግረዋት ነበር።

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
▫️አብደላህ ኢብን ዑመር ረዲደላሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~2

ከዚያ ቀን ወዲህ አብደላህ ቤትም ዉስጥ ሆነ ወይም በመንገድ ላይ የሌሊት ሶላት መስገድ አልተወም። በሌሊት ፀጥታ አምላክን ብዙ ማስታወስ፣ ሶላት መስገድና ቁርኣን ማንበቡን ተያያዘዉ-እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ። በተለይ ደግሞ የቁርኣን የማስጠንቀቂያ አንቀጾችን በሚሰማ ጊዜ ልክ እንደ አባቱ ሁሉ የእሱም አይኖች በእምባ ይሞሉ ነበር።

ዑበይድ ረዲየላሁ ዐንሁ አንድ ቀን የሚከተሉትን አንቀጾች ለአብደላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ባነበበ ጊዜ የሆነዉን ይናገራል።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

«ከህዝቦችም ሁሉ መስካሪን ባመጣን ጊዜ፥ አንተንም በነዚህ ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊ ዜ (የከሓዲዮች ኹኔታ) እንዴት ይኾን? በዚያ ቀን እነዚያ የካዱትና መልእክተኛዉን ያልታዘዙት በነሱ ምድር ብትደፋባቸዉ ይመኛሉ፤ ከአላህ ወሬን አይደብቁም።» (አል-ኒሳ እ፥ 41-42)

አብደላህ እነዚህን አንቀጾች በሰማ ጊዜ ጺሙ በእንባ እስከሚርስ ድረስ አለቀሰ። አንድ ቀን ከአንዳንድ ቅርብ ጎደኞቹ ጋር ተቀምጦ ሳለ እ ንዲህ ሲል አነበበ፦ «ለሰላቢዎች ወዮዉላቸዉ፤ ለነዚያ ከሰዎች ባሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ ፤ ለነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ፥ ወይም በመዘኑላቸዉ ጊዜ የሚያጓድሉ (ለኾኑት) እነዚያ እነሱ ተቀስቃሾች መኾናቸዉን አያዉቁምን? በታላቁ ቀን፤ ሰዎች ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) ፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸዉን)፡፡» (አል-ሙጦ ፊፊን፥ 1-6)
በዚህ ላይ «ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ) ፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መሆናቸዉን)» የሚለዉን ሐረግ እየመላለሰ ሕሊናዉን እስኪስት ድረስ መደጋገምና ማልቀስ ቀጠለ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ለአላህ ተገዥነት፣ ገራገርነትና ቸርነት በአንድነት ተዋህዶ አብደላህ በሶሃባዎችና ከነሱ በኃላ በመጡትም ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ የተከበረ ሰዉ አድርገዉታል። ከመጠን ያለፈ ቸርነቱ ድህነትን ያለብሰኛል ብሎም አልፈራም።
ሕይወቱን ሙሉ ታታሪና ታማኝ ነጋዴ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ከበይተ ልማል (ግምጃ ቤት) በርከት ያለ ደሞዝ የነበረዉ ቢሆንም ይህንን ብዙዉን ጊዜ ለድሆችና ለችግረኞች ነበር የሚሰጠዉ።
ስለእሱ ቸርነት አዩብ ኢብን ወይል አርራሲ አንዲህ ሲል ይናገራል፦
«አንድ ቀን፣ኢብን ዑመር አራት ሺህ ዲርሃምና አንድ ባለ ለስላሳ ፀጉራም ብርድልብስ ተቀብሎ ነበር። ይሁንና በሚቀጥለዉ ቀን ለግመሉ ምግብ በዱቤ ሲገዛ አየሁት። ከዚያም ወደ አብደላህ ቤተሰቦች በመሄድ «አቡ አብድራህማን (አብደላህ ኢብን ዑ መር) ትላንት አራት ሺህ ዲርሃምና አንድ ብርድ ልብስ አላገኘምን?» ስል ጠየኳቸዉ።

እነሱም «ኧረ አግኝቷል! ትላንት ከመጨለሙ በፊት ከቤት ወጣ። ሲመለስም ምንም ይዞ አልመጣም። ገንዘቡን የት እንዳገባዉ ጠየቅነዉ ለአንድ ድሃ እንደሰጠዉ ነገረን» ሲሉ መለሱ- ቤተሰቦቹ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ለአብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ሃብ ት አገልጋይ እንጂ አለቃዉ አይደለም። የሕይወት መሠረታዊ ፍላጎቶች ማሟያ መንገድ እንጂ የቅንጦት መሣሪያ አልነበረም። በዚህ ዘንባሌዉ በመብቃቃትና በቀላል አኗኗሩ ይታገዝ ነበር። አንድ ጊዜ ከጎደኞቹ መካከል አንደኛዉ በኹራሳን በጣም ምርጥና ዉብ የሆነ ጨርቅ አመጣለት።
«ይህንን ልብስ ከኹራሳን አመጣሁልህ በርግጥ ለዓይኖችህ (ልብስ ) እርካታ ይሰጣል። እነዚህ የለበስካቸዉን ሻካራ ልብሶች አዉጥተህ ጣልና ይህንን ቆንጆ ልብስ እንድትለ ብስ እመክርሃለሁ» አለዉ።

«እሺ እስኪ አሳየኝ» አለ አብደ ላረዲየላሁ ዐንሁ።
«ለመሆኑ ሃር ነዉ?» ሲል ጠየቀ።
ጎደኛዉም «የለም ጥጥ ነዉ» ሲል መለሰ ለት።
ለጥቂት ጊዜ ያህል አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ተደሰተ።
ከዚያ በኃላ ግን ልብሱን በቀኝ እጁ ገፋ አድርጎለት፥
«የለም! ለራሴዉ ስል ነዉ የፈራሁት። ቀብራራና ጉረኛ ያደርጋል ብዬ እሰጋለሁ። አላህ ደግሞ ቀብራ ራና ጉረኛን አይወድም።» አለዉ።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

መይሙን ኢብን መህራንም የሚከተለዉን ይነግሩናል፦ «ከኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ቤት ገባሁ። አልጋዉን፣ ብርድልብሱን ፣ ምንጣፉንና በዉስጡ ያለዉን ነገር ሁሉ በገንዘብ ገመትኩት። መቶ ዲርሃም የሚያወጣ ሆኖ ነዉ ያገኘሁት። »

ያ የሆነበት ምክንያት ግን አብድላህ ኢብን ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ድሃ ስለነበር አይደለም። በርግጥም ሃብታም ነበር። ቆንቋና ሆኖም አልነበረም። በርግጥ ቸርና ለጋስ ነበር። ግና ያገኘዉን ንብረት ሁሉ ለኢስላምና ለሙስሊሞች ደህንነት ሲል ወጭ ስለሚያደርግ ነዉ።

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ታሪክ

ታሪክ የአንድ ህዝብ የማስታወስ ክህሎት መገለጫ ነው፡፡ ታሪክን የረሳ ህዝብ ዛሬን ብቻ የሚኖር ...የዛሬ እሱነቱን የሚገነባበት ያለፈ ማንነት የሌለው ማለት ነው፡፡ አብዛኞቹ የታሪክን ክብደት አያውቁትም፡፡ በጥንቃቄና በጥልቀት አይፈትሹትም፡፡
ታሪካዊ ክስተቶችን በቅደም ተከተል በአዕምሮ መሸምደድ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ከታሪክ ትምህርት የሚገኘው ውስጡን በጥልቀት በመመርመርና ትምህርት በመቅሰም ነው። በምድር ላይ በመጓዝ የህዝቦችን ውርስና ቅርፅ የማየት ጠቀሜታው በዓይን ማየቱና ታሪኩን በጆሮ መስማቱ ብቻ ሳይሆን ..ዋናውና ተፈላጊው ነገር የልቦና ማስተዋል ነው፡፡
እንደ አንድ ሙስሊም ማህበረሰብ ያለፉ ጀግኖችን የድልና የኃያልነት የዕድገትም ሆነ የውድቀት ታሪክ ካልተማረና ትምህርት ካልወሰደ እንደነሱ ጀግና ሊሆንም ሆነ የሰሩትን ስህተት ላለመደገሙ ዋስትና የለውም፡፡
የታሪክ ክስተቶች በጣም ይደጋገማሉ፡፡ ምክንያቱም ከበስተጀርባቸው እነርሱን የሚያንቀሳቅሱና የሚቀርፁ ፅኑና የማይለወጡ የተፈጥሮ ህግጋት ስላሉ ነው፡፡ ታሪክን የመረመረ ከሌሎች ስህተት ይማራል፡፡ ከእነርሱ ውድቀት ራሱን ይመክራል፡፡ እድለኛ ማለት ከሌሎች ስህተት የተማረና በጎ ጎናቸውን የቀሰመ ነው፡፡ ታሪክን አድበስብሰን ካለፍን የምንማርባቸው በርካታ ነጥቦች ያልፉናል፡፡ የታሪክ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ክስተቶችን በማወቅና በመማር በጀግንነት መንፈስ አንድነታችንን አስጠብቀን ያ የኃያልነታችንን ጉዞ ዳግም ለመመለስ በጋራ መስራት ካልቻልን ሁሌም አንድ ቦታ ላይ መቆማችን አይቀርም፡፡

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️"አላሁ አክበር እርስዎ ቢሆኑ ይሞክሩት ነበርን⁉️ " የእውነት አሸናፊነት "

# ነገሩ እንዲህ ነው፦
፨ ሼህ አስራር ረሺድ የሚባሉ ታዋቂ እንግሊዛዊ ዳዒና ዓሊም በአንድ
የሀይማኖታዊ ውይይት መድረክ ላይ ከሌላኛው ክርስቲያን ተከራካሪ ወገን ለሸሁ
እንዲህ የሚል ጥያቄ ያቀርብላቸዋል።

"የናንተ ነቢይ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አጅዋ የተባለውን የቴምር ፍሬ የበላ
ሰው መርዝ እንኳን ቢበላ ወይም ቢጠጣ ቴምሩን ከበላ መርዙን
ያረክሰዋል፣"ይላል እናም እርስዎ ይህንን በተግባር ያረጋግጡልናልን?"በማለት
በውይይት መድረኩ ላይ ጥያቄውን ያቀርብላቸዋል።

ሼህ አስራር አላንገራገሩም የአይጥ መርዝ እንዲመጣላቸው ካስደረጉ በሗላ
እዛው የውይይት መድረኩ ላይ ህዝብ በተሰበሰበበት መርዙን ግጥም አድርገው
ጠጥተው አጅዋ ቴምሩን አስከተሉ ሱብሀነላህ! አጂብ!በሚገርም ሁኔታ መርዙ
ሳይነካቸው በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
አጂብ! ምን ዓይነት የቂን ምን ዓይነት ተወኩል? ይሞክራሉ?

©ጀማል ዳውድ

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️መግቢያ

ታሪክን ማወቅ ለአንድ ማህበረሰብ ትልቅ ህልውና ነው። ቀደምት ማንነቱን ያልተረዳ ማህበረሰብ ሁሌም አላማ ቢስና የዋለለ ነው። በተለይም እንደ ሙስሊሙ ዓለም አንገትን ቀና፣ ደረትን ነፋ የሚያስደርግ አኩሪ ታሪክ ያለው ህዝብ ታሪኩን አለማወቁ ሁሌ የውርደትን ኑሮ፣ የሽንፈትንና የበታችነትን ካባ ለማጥለቅ ይገደዳል። ለዚህም ነው ታሪካችንን እንወቅ የምንለው። በነገራችን ላይ የኛ ታሪክ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ ብቻ አይደለም ይልቁንስ ኢስላማዊው ታሪክ ያዳረሰው፣ የኢስላም አሻራ ያረፈበት ታሪክ ሁሉ ታሪካችንና ኩራታችን ነው።

በአለም ታሪክ ውስጥ የሀይል አሰላለፍን በመቀየር ጉልህ ሚና ከነበራቸው የታሪክ ዓምዶች ውስጥ የቆስጠንጢንያ ድል ቁጥር አንድ ተጠቃሽ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለዚህ ታላቅ ድል እንዲህ ብለዋል፡፡ "የትኛዋ ከተማ ቀድማ ትከፈታለች ቆስጠንጢኒያ ወይስ ሩሚያ?" ተባሉ የአላህ መልእክተኛ “የሂረቅል ከተማ ቀድማ ትከፈታለች” አሉ፡፡ የሂረቅል ከተማ የተባለችው ቆስጠንጢኒያ ናት፡፡ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህም ብለዋል "ቆስጠንጢያን ትከፍታላችሁ ምንኛ ያማረ አሚር ነው አሚሯ ምንኛ ያማረ ጦር ነው ጦሯስ!"

እነሆ ለዚህ ታላቅ ድል የታጩት ቱርኮች ማናቸው? ኣመጣጣቸውስ ከየት ነው? የዑስማንያ ቱርክ ሥርወመንግሥት የተባለውስ እንዴት ተጀመረ? የዑስማንዮች ፉቱሐት / ሀገር የማቅናት/ ወታደራዊ ንቅናቄስ ምን ይመስል ነበር? በመጨረሻም ከላይ በሐዲሱ የተወሳችው ቆስጠንጢያ እንደምን ተከፈተች?

📚" ከሰይፎች ጥላ ስር " ከሚለው የአማን አሰፋ መፅሐፍ የተወሰደ
ሰዎች ሊረዱት በሚመች መልኩ በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል ኢንሻ አላህ!

وبيجوت Tube
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~1

📕ቱርኮች አመጣጣቸው ከየት ነው?

የቱርኮች መነሻ በማዕከላዊ ኢስያ ቱርኪስታን የምትባለው ሀገር ናት፡፡ ቱርኪስታን ዛሬ-ቃዛቂዝስታን፣ ቱርክማኒስታን፣ ጣጂኪስታን፣ ቂርጊዝሥታን፣ ዑዝቤኪስታን እና በቻይና ቅኝ አገዛዝ ሥር የምትገኘውን ምሥራቃዊ ቱርኪስታን /ቱርኪስታን ሸርቂያ/ የሚባሉትን ሀገራት ታጠቃልላለች፡፡

ምሥራቃዊ ቱርኪስታን ማለት ቻይና ቅኝ ግዛት አድርጋ ከያዘቻት በኋላ የራሷ አካል በማድረግ ሲኪያንግ ዊላያ ጀዲዳ ወይም /አዲሲቷ ክፍለ ሀገር/ በማለት ሰይማታለች፡፡ የቱርኪስታን ሌላው ግዛት ቀድሞ ኹራሳን ይባል የነበረ ሲሆን ዛሬ ግን በኢራን፣ በአፍጋኒስታንና በቀድሞዋ ቱርክማኒስታን ሶስት ቦታ ተከፋፍሎ ይገኛል፡፡

ቱርኮች በመሠረቱ ከሞጎል ነገድ ናቸው፡፡ ቢጫ ህዝቦች ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ወይም የያፌት ቢን ኑሕ ልጆች ናቸው፡፡ ቱርኮች በጦረኝነት ይታወቃሉ፡፡ ከኢስላም በፊት እነሱም እንደተቀሩት ዘመዶቻቸው እንደሞጎሎችና ተታሮችም ሁሉ አውሳንና ከዋኪብ አምላኪ ነበሩ፡፡

ሐቁ ይህ ከሆነ እንግዲህ! የቱርክ ጎሳዎች እንዴት ወደ ዛሬዋ ቱርክ መጡ? ነው ጥያቄው፡፡ በነገራችን ላይ የዛሬዋ ቱርክ ወይም (ቱርኪያ) ቀድሞ አናዶል ወይም አናቶሊያ እንደሚባል ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ አካባቢው በእጅጉ ተራራማ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የቱርኪስታን ሀገራት ከኢስላም የተዋወቁት በበኒ ኡመያ ኺላፈት ዘመን ነበር፡፡ ዳዕዋው የደረሳቸው ያን ጊዜ አለምን የማቅናት ዘመቻን በመሩት ምርጥ የመጀመሪያ ትውልድ አባላት ነበር፡፡ ቁተይባ ቢን ሙስሊም ባህሊይ ዐሊ መህለብ በተለይ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በነዚህ ለኢስላም በታመኑ መሪዎች ተጋድሉ ቱርኪስታን ቱርኮች ኢስላምን በጀምላ ተቀብለዋል አላህ ዐዝዘ ወጀልም በነሱ ዲንን ከፍ አድርጓል፡፡

ቱርኮችን ወደ ዛሬዋ ቱርክ ከቲርጊዝስታንና ከኹራሳን ቀበሌዎች አምጥተው እዚያ ያሰፈሯቸው የዐብባሲያ ኹለፎች ናቸው፡፡ አምጥተው ያሰፈራቸው ሙስሞሊችንና ክርስቲያን ሩሞችን በሚለየው ተራራማ ወረዳ መሀል እንደመከላከያ ቀጠና /buffor zone/ እንዲሆኑ በማሰብ ነበር፡፡ በተራራማዎቹ የኣናቶሊን ወረዳዎች የሰፈሩት ቱርኮች ቁጥር በመእሙንና በሙዕተሲም ኸሊፋነት ዘመን ይበልጥ ጨምሯል፡፡ በሙተወኪል የኸሊፋነት ዘመንማ ቱርኮች የጦር ሠራዊቱ አብላጫ ክፍልና ተፅዕኖ ፈጣሪ እስከመሆን ደርሰው አናቶሊያን ያስተዳድሩም ነበር፡፡

አንዳንዴ ድጋፋቸውን ለዐብባሲያ ኸሊፌት ይሰጣሉ፡፡ ሌላ ጊዜ ደሞ መቀመጫቸውን ሱሪያ ሐለብ ላደረጉት ሐምዳይን ይታዘዛሉ፡፡ ሲላቸው ደሞ ግብፅ ለሚገኘት ጠውለውኒይን ያድራሉ፡፡ ይሄ ልዩነት እንዳለ ሁኖ በሩምና በሙስሊሞች መካከል በሚደረው ውጊያው የድል ሚዛነ ተዘዋዋሪ እየሆነ ቀጥሏል፡፡ ባጭሩ እንግዲህ! የቱርኮች ወደ አናቶሊያ አመጣጥ ታሪክ ይሄን ይመስላል፡፡

ባንድ ወቅት የዐብባሲይን ኺላፈት መዳከም ተከትሎ ሰልጁቆች ተነሱ፡፡ ሰልጁቆች በመሰረቱ ከአትራክ ነገድ ናቸው፡፡ ቱርኮች ናቸው። መንበረ መንግሥት ተቆጣጠሩና በራሳቸው ገዥ ሁነው ብቅ አሉ። የሰልጁቅ መንግሥት /ደውለቱ ሰልጁቅ/ በመባል ታወቁ፡፡ ከሩሞች ሁሌም ይዋጉ ነበር፡፡ እውቅ እውቅ ጦረኛ መሪዎች ነበሯቸው፡፡ ከነዚህ አንዱና አብረዙ አለብ አርሰላን ነበር፡፡ በ463 ሂጅሪያ ከሩሞች ተዋግቶ በነሱ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅቷል፡፡
ሰልጁቆች ከተጠቃሹ ድል በኋላ ብዙ ኢማራቶችን እና አናሳ መንግሥታትን መሰረቱ፡፡ አናቶሊያ ውስጥ በኃይል በመስፋፋት ቀደም ሲል ሩሞች ከሙስሊሞች የወሰዱትን መሬት አስመልሰዋል፡፡ ተጨማሪ መሬቶችንም ይዘዋል፡፡ ይበልጡን ደሞ በመሊክ ሻህ ቢን አርስላን ዘመን ግዛት አስፍተዋል፡፡ አናቶሊያም እንደተቀሩት የሙስሊም ግዛቶች በሙስሊሞችና በኢስላም ጠላቶች ጠንሳሽነት የደረሰው ዓይነት የርስ በርስ ጦርነት በተለይም በስፔንና ሞንጎልች ይዞታዎች ሥር በተፈሩቅ ምክንያት የተከሰተው ግጭት ሊደርስባት ምንም አልቀራትም ነበር።

ምክንያቱም ሰልጁቆች እርስ በርስ የሚፎካከሩ በጣም ብዙ አናሳ መንግሥታትን በየጎጡ እያቋቋሙ ነበርና ነው፡፡ እነዚህ ጎጠኛ መንግሥታት ጊዜው እንደሚጠይቀው አንድ ልብና አንድ እጅ ሁነው ሩሞችን ከመዋጋት ይልቅ አንዱ ሌላውን በማሸነፍ ግዛት ማስፋፋትን ነበር ሥራዬ ብለው የያዙት፡፡ አላህ ዓዝዘ ወጀል ግን አንድ የሚያደርጓቸውን ዑስማኒዮችን አመጣላቸው፡፡

📕የዑስማኒያ ሥርወ-መንግሥት አጀማመር

የኢስላም ምሥራቃዊ ከተሞች ላይ የሞጎሎች ጫና እየበረታ ሲመጣ ብዙ ጎሳች ከሞጎል አረመኔያዊ ድርጊት እየሸሹ ወደ ምዕራባዊ የኢስላም ግዛቶች ይመጣሉ፡፡ ከነዚህ ጎሳዎች አንዱ ካይ ቱርክማኒያ ነበሩ፡፡ እየመራ ወደ ምዕራቡ የኢስላም መሬት አጎዳኝቶ ያመጣቸው አሚራቸው ሱለይማን ሻህ ቢን ቂያ አለብ ይባላል፡፡ ይሁንና ሱለይማን የሞጎል የጦር ጫና ረገብ የማለቱን ዜና ሲሰማ ወደ ትውልድ ሀገሩ ለመመለስ ናፈቀ፡፡ ቤተ ዘመዱን ይዞ በመመለስ ላይ እንዳለ ፉራት ወንዝ ውስጥ ሰጠመ፡፡

አራት ወንዶች ልጆቹ ወዴት ማምራት እንዳለባቸው በሃሳብ ተወዛገቡ፡፡ ሶንጎርትኪን እና ጎንዶግዱ እንደ አባታቸው ምኞች ወደ አባታቸው ሀገር መሄድን መረጡ፡፡ አርጦግሩል እና ዶንዳር ወደ ሰሜን ተቅጣጩ፡፡ አርጦግሩል በአናቶሊያ በቀረ አንድ የጎሳው ክፍል ላይ በመሪነትን ተሾመ፡፡ አርጦግሩል ዓላኡዲን ሰልጁቂን ለጎሳዎቹ መሥፈሪያን የሚሆን መሬት እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡ ዓላኡዲን ሰልጁቂይ በጊዜው የሰልጁቅ ሩም ሱልጣን ነበር።

ይህ በንዲህ እንዳለ አርጦግሩል ሁለት ጦሮች እየተፋለሙ ያገኛቸዋል፡፡ አንደኛው ወገን ሙስሊም ጦር ሲሆን የመዳከምና የመሸነፍ ምልክት ይታይበታል፡፡ ሌላው ወገን ባዘንታይን ክርስቲያን ሲሆን የማሸነፍ ምልክት ይታይበታል፡፡ አርጦግሩል ኢስላማዊ ስሜቱ አይሎበት ሙስሊሙን ጦር ለመርዳት ገባ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
🕋ሳኡድ አረቢያ የዘንድሮውን የሀጅ ስነ ስርአት ክንውን ምክንያት በማድረግ የተከበረውን የካእባን ልብስ የመቀየር ፕሮግራም ጀመረች።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~2

ባለፈው ክፍል አርጦግሩል የሙስሊሞች ጦርና የባዛንታይን ክርሰቲያኖች ጦር እየተፋለሙ እንዳገኛቸውና ኢስላማዊ ስሜቱ አይሎበት ሙስሊሙን ጦር ለመርዳት እንደገባ አይተን ነበር፡፡ እንቀጥል

አርጦግሩል ወደ ጦርነቱ ሲገባ የአሸናፊነት ሚዛኑ ተቀየረ። በአላህ እገዛ የሙስሊሙን ጦር ከተሸናፊነት አዘቅት ወደ ኣሸናፊነት ከፍታ አወጣው፡፡ እንደአጋጣሚ ሁኖ ሙስሊሙን ጦር ሲመራ የነበረው ዓላኡዲን ነበረ፡፡ ዓላኡዲን አርጦግሩል ስላደረገለት ትብብር የሚሻውን መሬት ባዘንታይን ሩም ድንበር ላይ ሰጠው። እግረ-መንገዱን የነሱን ተደጋጋሚ ወረራ እንዲመክትና እነሱም ላይ ወረራ እንዲያደርግ ብሎ ድንበር ላይ አሰፈረው፡፡ አርጦግሩል በሚያገኛቸው ድሎች ሁሉ ተጨማሪ መሬቶችን እየያዘ ግዛቱን እያሰፋ መጣ፡፡

አርጦግሩል ዑስማን የሚባል ልጅ ነበረው። ዑስማን ከአንድ ሷሊህ ሰው ዘንድ እያዘወተረ ይወዳጃል፡፡ እሱን ለመጎብኘት በሚሄድባቸው ጊዜያት የምታምር ልጅ እንዳለችው ያያል፡፡ በውበቷ ይማረካል፡፡ እንዲድርለት ይጠይቀዋል፡፡ ሰውዬው ግን ሊድርለት አልፈለገም፡፡ ዑስማን ስሜቱ ተጎዳ፡፡ በጣምም አዘነ፡፡ በዚህ ህመም እየተንገላታ ባለበት አንድ ለሊት በጥልቅ የእንቅልፍ ባህር ውስጥ ሁኖ ህልም ያያል፡፡ ያየውን ህልም ወደ ሷሊሑ ወዳጁ ሄዶ ያወራለታል፡፡ ሰውዬው ህልሙን ሰምቶ ሲያበቃ ልጅቱን እንደሚድርለት ነገረው፡፡

ህልሙ እንዲህ ነበረ:- “ሷሊሑ ሰውዬ ደረት ላይ ጨረቃ ትወጣለች፡፡ እያደገች ትመጣና ሙሉ ጨረቃ ትሆናለች፡፡ ከዚያም ዑስማን ደረት ላይ ትወርዳለች፡፡ ከዚያም ዑስማን ጀርባ ላይ ዛፍ ታቆጠቁጣለች፡፡ እያደገችም ትመጣና በአካባቢው ሁሉ ላይ ጥላዋን ታጠላለች፡፡ የቀውቃዝ፣ የበልቃን፣ የጠውሩስ እና የአጥለስ ተራሮች ሁሉ በጥላዋ ሥር ይኾናሉ፡፡ ከሥሮቿ ደሞ የጢግሮስ ፣ኤፍራጥስ፣ የአባይ እና የጠውኑህ /በልቃን ግዛት አውሮጳ ምድር/ የሚገኙ ወንዞች ይፈሳሉ፡፡ የዛፊቱ ቅጠሎችም ሠይፎችን እየኾኑ ወደ ቆስጠንጢኒያ አቅጣጫ ንፋስ እያበረረ ሲወስዳቸው ያያል። ሷሊሑ ሰውዬ ህልሙን ሰምቶ በጥሩ ፈታው፡፡ ልጅቱንም ሰጠውህ አለው፡፡ የዑስማን የዘር ዘሮች ዓለምን እንደሚገዙም አበስረው፡፡

📕ሱልጣን ጋዚ ዑስማን ቀዳማዊ

አርጦግሩል በ687 ሂጅሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በቦታው ልጁ ዑስማን ተተካ፡፡ የጎሳውን መሬት በሰልጁቁ ሱልጣን ዓላኡዲን ቀዳማዊ ስምምነት መሰረት ማስፋፋትን ቀጠለ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በ699 ሂጅሪያ ሞጎሎች የሰጁቅን ሱልጣን ወረሩ፡፡ ዓላኡዲን ሶስተኛ ተሸንፎ ወደ ባዘንታይን ግዛት ሸሸ፡፡ በዚሁ ዓመት ሞተ፡፡ ከሱ መሞት በኋላ ልጁ መስዑድ ሶስተኛ ሥልጣን ያዘ፡፡ ይሁንና እሱም በሞጎሎች እጅ ተገደለ፡፡ አሁን ነገሮች ለዑስማን ተመቻቸለት፡፡ በሥሩ ያለውን ሀገር ነፃነት ለማስከበርና በሥሙ የሚጠራበትን የዑስማኒያ መንግሥት /ደውላ ዑስማኒያን/ መሰረተ፡፡ ቀድሞ “እስኪ ሸሂር” ትባለ የነበረችውን ከተማ /የኒ ሸሂር/ አዲሲቷ ከተማ በማለት እንደ መናገሻ ከተማ አድርጎ ቆረቆረ፡፡ እስካሁንም ድረስ የቱርክ ብሔራዊ መለያ የሆነውን ባንዲራ አበጀ፡፡ ቀጥሎም በአናቶሊያ ለነበሩ የሩም ባለሥልጣናት እስልምናን እንዲቀበለ ጥሪ አደረገላቸው፡፡ እስልምናን ካልተቀበለ ጂዝያ እንዱከፍሉ፡፡ ሁሉንም አማራጭ አሻፈረኝ ካሉ ጦርነት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቀ፡፡

የሩም ባለሥልጣናት በአናቶሊያ ያላቸውን ግዛት እንዳያጡ ፈሩ፡፡ እስልምናን መቀበልም አልፈለጉም፡፡ ዑስማንን መግጠምም አልቻሉም፡፡ ስለዚህ በሱ ላይ በሞንጎሎች እየታገዙ መዋጋትን መረጡ፡፡ ዑስማንም አስቀድሞ ዝግጁ ባደረገውን ጦር በሁለተኛ ሌጁ በአይሩኻን መሪነት ሞንጎሎች ላይ አዘመተ፡፡ “ፈሸተተ ሸምለሁም” ብትንትናቸው ወጣ፡፡ ህብረታቸው ፈረሰ፡፡ ከዚያም ዑስማን የጦር ንቅናቄውን ቀጥሎ በውሩስ የተሰኘችውን ታዋቂ ከተማ ከፈተ፡፡ ነዋሪዎቿን አረጋጋ፡፡ መልካም አያያዜ አደረገላቸው፡፡ የከተማው ህዝቦች ደስ ተሰኙበት፡፡ ለጦሩ ማጠናከሪያ 30,000 የወርቅ ዱናር ሰጡት፡፡ የከተማዋ ገዢም አፍሩኑስ እስልምናን ተቀበለ፡፡ ከከፍተኛ የጦር መሪዎች እንደ አንድ ሆነ፡፡ ከዚያም ዑስማን በ726 ሂጅሪያ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ከሱ በኋላ ልጁ አይሩኻን እንዲተካው ተናዞለት ሞተ። ጀናዛውም ራሱ በከፈታት በበውሩስ ከተማ በክብር አረፈ፡፡ እነሆ በውሩስ ከዚህ በኋላ የዑስማን ቤተሰቦች ሲሞቱ መቀበሪያ ሥፍራ ሁና ቀጥላለች፡፡

ዑስማን በዘመኑ ጋዚ መባልን የተቀፀል የመጀመሪያው ሱልጣን ነው፡፡ ጋዚ ማለት ሙጃሂድ ማለት ሲኾን እንደመሪ ቃልም “ኢማ ጋዚን ወኢማ ሸሂድ” ማለትን መመሪያው በማድረግ አስተዋውቋል፡፡ አብዛኛው የዑስማንያ ሱልጣኖችም የሱን ፈለግ በመከተል ጋዚ መባልን ተቀጽለዋል፡፡ እንደመሪ ቃልም ሺዓር አድርገው ይዘውታል- ኢማ ጋዚን ወኢማ ሸሂድ-ይላሉ።

📕ሱልጣን ጋዚ አይሩኻን ቀዳማዊ

አይሩኻን የዑስማን ሁለተኛ ልጁ ነበር፡፡ የላቀ ሂማና ሹጃዓነት ስለነበረው አባቱ ዑስማን ሥልጣኑን እንዲተካው መርጦታል፡፡ ታላቅ ወንድሙ አላኡዲን የመገለልና የፈሪሃ-አላህ ዝንባላ ስለነበረው የአባቱን ኑዛዜ አልተቃወመም፡፡ አይሩኻን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ለታላቅ ወንድሙ ስለተሰጠው በዋናነት ግዛት የማስፋቱን የውጭ ጉዳይ ሃላፊነትን ያዘ፡፡ የመንግሥቱን ዋና ከተማም ከየኒ-ሸሂር ወደ በውሩስ አዘዋወረ፡፡ ዓላኡዲን በበኩሉ እንደ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሃላፊነቱ የብርና የወርቅ መገበያያ ገንዘብ አስቀረጸ፡፡ አዲስ የጦር ህግ በማርቀቅም የቋሚ ሠራዊት ግንባታ አስጀመረ፡፡ በፊት ሠራዊቱ በጦርነት ጊዜ ብቻ ሲጠራ ነበር የሚሰባሰበው፡፡

ወታደሩ በየትውልድ ጎጡ ተሰግስጎ በየራሱ ጎሣ ሊፈረግጥ ይችላል የሚለውን ሥጋት ለማስቀረት አንድ የተዋሀደ ቋሚ ሠራዊት እንዲኖር አድርጓል፡፡ ከዚህ የቋሚ ሠራዊት ግንባታ ጋር በተያያዘ ዑስማኒያ ቱርኮች በአውሮጳ መስቀላውያን የሚብጠለጠልበት ነጥብ ቢኖር ከሩሞች ጋር ሲደረግ በነበረው የተራዘመ ጦርነት ወላጆቻቸውን ያጡ ተፈናቃይ ሕፃናትን በመያዝና በወታደራዊ ሰፈሮች በማጎር፣ ከጂሃድ ፊ ሰቢሊላህ ውጪ ሌላ አንዲትም ሐርፍ የማያውቁ እስከሚሆኑ ድረስ፣ እንዲሁም ከቅርብ አዛዣቸው ሱልጣን ውጪ ማንንም የማይሰሙ እስከሚሆኑ ድረስ የውጊያ ትምህርት /ፈኑል ቂታል/ እያስተማሩ ያዋጓዋቸዋል የሚለው የሐሰት ወሬ ይገኝበታል፡፡ ሐቁ ግን እነዚህ ልጆች ኢስላማዊ ተርቢያ ይወስዳሉ፣ ከዚያም ከጠላት ፊት የሚቆሙ የኢስላም ተከላካይ ኃይሎች ይኾናሉ፡፡ የኒ ተሽር ወይም “አዲሱ ጦር” ይሰኛል፡፡ በዓረበኛ ኢንኪሻሪያ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ዑስማኒያ ቱርኮች ወደ አውሮጳ አህጉር ባደረጉት የፈቱሀት ዘመቻ ውስጥ የላቀ ድርሻ ነበራቸው፡፡

ኋላ ግን የሥልጣን ገደባቸውን እያለፉ ባስተዳደር ጉዳዮች ጣልቃ መግባት በመጀመራቸው በሙሐመድ ሁለተኛው ኸሊፋነት ዘመን በ1242 ሂጅሪያ እንዲበተኑ ተደርጓል፡፡ -አይሩኻን በሀገር ግንባታ ሥራው ብዙ መድረሳዎችን ከፍቷል። የሀገር ውስጥ ደህንነት አጠባበቅ ስርዓት ዘርግቷል። መሳጂዶችን ብዙ ገንብቷል ለዑለማዕና ለሹዓራእ ይለግስም ነበር።

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~3

📕የአይሩኻን ፉቱሐት

አይሩኻን ፉቱሐቱን ቀጥሎ ኢዝሚር፣ ኢዝኒቅ… የተሰኙና በቱርክ አናቶሊያ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሬቶችን በመያዝ የዑስማኒያ ኺላፋ ግዛትን እያሰፋው መጣ፡፡ አይሩኻንም አንድን ከተማ ሲከፍት በነዋሪዎች ላይ ገራም ንግግርን ይናገራል ያዝንላቸዋል። የዲናቸውን ትዕዛዛት ከመፈፀም አያግዳቸውም። ሀገሩን ለቆ መሄድን ለሚሻ ተንቀሳቃሽ ንብረቱን ይዞ ቋሚውን ሽጦ መሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡ አይሩኻን የውጭ ሀገር ሴት የማግባትን የመቀራረብ ስልት ይጠቀማል። ግሪካዊት ክርስቲያን ሴት አግብቷል። ነገሮች በዑስማኒያ ሱልጣኖች ዘንድ በጣም የተለመደ እስከሚመስል ድረስ ከአውሮፓ ነሳራ ሴቶች መጋባትና ከሩም ባዛንታይን ነገስታት ጋር በጋብቻ የመተሳሰር ልምድ የዳበረበት ሁኔታ ነበር።

አይሩኻን የባዘንታይን መንግሥት እንደመድከም ማለቱን ባስተዋለ ጊዜ ተዋጊ ጦሩን ወደ አውሮጳ አህጉር እንዲሻገር ወሰነ፡፡ ከቆስጠንጢኒያ በስተምዕራብ በመዝለቅ የወደፊት የከተማዋ መከፈት ወታደራዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን መሬት ያዘ፡፡ ይህ የአይሩኻን ከቁስጢንጢኒያ በስተ-ምዕራብ ያነጣጠረ ንቅናቄ ያለምክንያት የታሰበ አልነበረም፡፡ ከቱርኮች በፊት ቆስጠንጢኒያን መክፈት የሞከሩ ሙስሊም ሰራዊቶች ሁሉ ሙከራቸውን ያደረጉት በከተማዋ ምሥራቃዊ ጠረፍ በኩል ነበር፡፡፡ ሁሉም ግን ግባቸውን አላሳኩም፡፡ ስለዚህ አይሩኻን በአንጋፋ ልጁ ሱለይማን አማካኝነት ምርጥ የተሰኙ አርባ ተዋጊዎችን ይዞ የአውሮጳን የባህር ዳርቻ ተሻገሩ፡፡ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን መሬቶች ተቆጣጠሩ፡፡ ይሁንና በ760 ሂጅሪያ የአይሩኻን አልጋ ወራሽ እና የጦሩ አዛዥ የነበረው ሱለይማን ከጦር ፈረሱ ላይ ወድቆ ባገኘው ጉዳት ሰበብ ሞተ፡፡ በዓመቱ አይሩኻንም ራሱ አረፈ። ስልጣኑን ሁለተኛ ልጁ ሙራደል አወል ተረከበ፡፡

📕ሡልጣን ጋዚ ሙራድ ቀዳማዊ

ሙራድ ቀዳማዊ በትረ-መንግሥቱን እንደጨበጠ የቀርማን /የከርማን/ ልዑል ዓላእዲን አሊ ቤይ በጠላትነት ተነሳበት፡፡ በአናቶሊያ የነበሩና የየራሳቸውን ግዛት ተቆጣጥረው ለየብቻ ይገዙ የነበሩ ኡመራዎችን በዑስማንያ መንግሥት ላይ አስተባበረ፡፡ ሡልጣን ሙራድም ጦሩን አስጠግቶ የቀርማን ርዕስ ከተማ የሆነችውን አንቀራን በኃይል መግባት ቻለ። ዓላእዲን አንቀራን ለዑስማኒዮች እንዲያስረክብና ከዛ እንዲወገድ ተገደደ፡፡ የተቀረ መሬቱን ግን ይዞ መቆየት ተፈቀደለት። ሴት ልጁንም እንደመልካም ግንኙነት ተምሳሌት ቀዳማዊ ሙራድ አገባት።

ይሁንና ዓላእዲን ቀልብ ውስጥ የበቀል እሳት ጨርሶ አልከሰመችም፡፡ ምቹ አጋጣሚ ጠብቆ የጦር ዝግጅት አደረገ፡፡ ከዑስማኒያ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ነፃ የአናቶሊያ መንግሥታትን አስተባብሮ አንድ ላይ ዑስማኒዮችን ለመውጋት ወጡ፡፡ በ787 ሂጅሪያ ቀዳማዊ ሙራድ በበኩሉ ጦር ላከባቸው፡፡ ድል ተመቱ፡፡ ችግር ፈጣሪው ዓላእ ዲን ተማረከ፡፡ ይሁንና ሡልጣን ሙራድ ባገባት ልጁ ምልጃ ይቀርታ አደረገለት፡፡ ሱልጣኑ በግዛቱም ላይ ተወው፡፡ ነገር ግን ዓመታዊ ግብር ቀጥ ብሎ እንዲከፍል ግዳጅ ጣለበት፡፡

📕የሡልጣን ሙራድ ቀዳማዊ የአውሮፓ ጂሀድ

የሱልጣን ሙራድ ቀዳማዊ የውጭ ጉዳይ መርሁ በአናቶሊያ ግንባርም ሆነ በአውሮጳ ግንባር. የዑስማኒያ መንግሥትን ግዛት በማስፋፋት ላይ ያለመ ነበር። በቅድሚያ ኢስላማዊ የአናቶሊያ ግዛት አሚሮችን ወደ ውህደት ማምጣት ነበረበት፡፡ ይህንኑ አላማ በመልካም ግንኙነትና በጋብቻ ጭምር ሊያበጀው ሞክሯል። በዚሁ አያያዝ የዚድ የተባለውን ወንድ ልጁን ከከርማያን አሚር ሴት ልጅ ጋር አጋባ። የልጅቱ አባት ‹ኩተሂያ› የተባለችውን ከተማ የሡልጣኑን ልጅ ላገባች ልጁ ሸለማት፡፡ እሷም ከተማዋን ከዑስማኒያ መንግሥት ግዛት ጋር በሰላም ቀላቀለች፡፡

ሱልጣን ጋዚ ሙራድ ቀዳማዊ መታዘብ እንደቻለው ሙስሊም ወታደሮች አናቶሊያ ምድር ላይ ከመዋጋት ይልቅ ወደ አውሮጳ ዘልቆ ለመዋጋት ይበልጥ ተነሳሽነት ነበራቸውና የኢስላምን ጠላቶች ለማሸነፍ የሙስሊሞች አንድነት አስፈላጊነቱ ግልጽ ነበረ፡፡ በ762 ሂጅሪያ ዑስማኒዮች ወደ አውሮጳ አህጉር ዘልቀው በመግባት አደረኑህ ከተማን ከፈቱ፡፡ ከተማዋ ከቆስጠንጢኒያ በስተምዕራብ ራቅ ብላ ትገኛለች፡፡ ሱልጣን ሙራድም በአውሮጳ ምድር በቀጣይ ለሚደረገው የጦር ንቅናቄና ጂሃድ ወታደራዊ ማዕከል እንድትሆን በማሰብ ዋና ከተማውን ወደሷ አዞረ፡፡ ይቺ ከተማ በ857 ሂጅሪያ ቆስጠንጢኒያ እስከምትከፈት ድረስ የዑስማኒዮች ርዕሰ ከተማ ሆና ቀጥላለች፡፡ ከዛሬዋ ደቡብ ቡልጋሪያ “የፊሊቢን” ከተማ፣ ከልጃሚና፣ “ውርዳር” የመሳሰሉትን ከተሞች ከፈቱ፡፡ ይህ በመከናወኑም ቆስጠንጢኒያ በአውሮጳ ግንባር በሁሉም አቅጣጫ የከበባ ቀለበት ውስጥ ገባች፡፡

የአውሮጳ ነገሥታት ከዑስማኒያ መንግሥት መከሰት አንስቶ ዑስማኒዮችን በመዋጋት ተጠምደው የሰነበቱ ከመሆናቸው አንፃር ያሁኑ የዑስማኒያ ጦር የድል ግሥጋሴ እያሳሰባቸው መጣ፡፡ ወደ ዋናው ሊቀ-ጳጳሱ የጦር ዝግጅት እንዲያስጀምሯቸው ተፃፃፈ፡፡ የቆስጠንጢኒያ ንጉሥ ራሱ ተነስቶ ወደ ሉቀ-ጳጳሱ ሄደ፡፡ ከፊታቸው አጎነበሰ፡፡ እጆቻቸውንና ጉልበታቸውን ጨብጦ ተንበረከከ፡፡ እርዳታን ተማጸነ፡፡ ንጉሡ የኦርቶዶክስ ተከታይ ነበረ፡፡ ጳጳሱ ግን የካቶሊክ አማኝ ናቸው፡፡ በሁለቱ መካከል ልዩነትና ጠላትነት ቢኖርም በኢስሊም ላይ ሲሆን ግን እርስ በርስ ይተባበራሉ፡፡ አንድ ይኾናሉ፡፡ ሊቀ-ጳጳሱ ለአውሮጳ ነገሥታት ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ኢስላም ወደ አውሮጳ የሚያደርገውን ግስጋሴ ለመግታት ሁሉም ለመስቀል ጦርነት ዝግጅት እንዲያደርጉ በማሳሰብ ላኩባቸው፡፡ የሰርቡ ንጉሥ ግን የጳጳሱን እርዳታ መጠበቅ አልፈለገም፡፡ የራሱን ኃይል አሰለፎ ከቦስኒያና ከደቡብ ሩማንያ ንጉሦች ጋር ትግግዝ ፈጥሮ፣ የሀንጋሪያ ፈረሰኞችን ጨምሮ በቀጥታ የዑስማኒዮች ርዕሰ-ከተማ ወደኾነችው ወደ አድረኑህ ዘመቱ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~4

ባለፈው ክፍል ኢስላም ወደ አውሮጳ የሚያደርገውን ግስጋሴ ለመግታት ሁሉም ለመስቀል ጦርነት ዝግጅት እንዲያደርጉ ጳጳሱ እንዳሳሰቡ እና የሰርቢያው ንጉሥ የጳጳሱን እርዳታ እስኪመጣለት መታገስ ተስኖት የራሱን ኃይል አሰልፎ ከቦስኒያና ከደቡብ ሩማንያ ንጉሦች ጋር ተጋግዞ የዑስማኒዮች ርዕሰ-ከተማ ወደኾነችው ወደ አድረኑህ እንደዘመቱ አይተን ነበር ያቆምነው፡፡ እንቀጥል...

መስቀለኞች ሱልጣኑ በዋናው የቱርክ ግማደ-መሬት በአናቶሊያ ውስጥ በአንዳንድ ውጊያዎች ተጠምዶ የነበረ መሆኑን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ቆጥረውታል፡፡ የዑስማኒዮች ጦር ሠራዊት በአድረኑህ ከተማ በሚያልፈው የማርተሪዝ ወንዝ አካባቢ ደረሰባቸው፡፡ በከባድ ጦር ተመተው ጀርባ አዞሩ፡፡ በአድሪያቲክ ባህር ከባቢያዊ ምድር ላይ የነበረችው የራጅዊዝ ነፃ ግዛት የዑስማኒዮችን ኃይል በመፍራት ድርድር ጠይቃ ከዑስማኒያ መንግሥት ጋር ሠላም ፈጠረች፡፡ በዓመት 500 ዱካን ወርቅ የሚመጥን ጂዝያ(ግብር) ለመክፈል ፈረመች፡፡

የሰርብ ንጉሥ ላዚር እና የቡልጋሪያው ልዑል ስይስማን በጋራ ዑስማኒዮችን ለመፋለም ተስማሙ፡፡ ነገር ግን ከዑስማኒዮች ጋር ካደረጓት አነስተኛ መቆራቆስ በኋላ ልካቸውን አውቀው ዓመታዊ ጂዝያ ለመክፈል ተገደው ተስማሙ፡፡ ሱልጣኑም የቡሌጋሪያን ሌዑል ሴት ልጅ አገባ፡፡ ይሁንና ሰርብና ቡልጋሮች ጂዝያውን በወቅቱ ከመክፈል ሆን ብለው በመዘግየታቸው የተነሳ የዑስማኒያ ወታደሮች ዘመቱባቸውና የሰርቢያን የተወሰኑ ከተሞች ወደ ኢስላማዊ ግዛት አጠቃለሉ፡፡ ቀጠለና በመቄዶኒያ የሰሎንቄን ከተማ /ዛሬ በግሪክ ትገኛለች/ ሙሉ በሙሉ ከፈቱ።

📕የኮሶቮ ጦርነት 791 ሂጅሪያ

ሰርቦች አንድ ነገር አስተውለዋል፡፡ ዑስማኒዮች በአናቶሊያ ውስጥ ዓላኡዲን የተሰኘውን የስልጣን ጥመኛ በመዋጋት ላይ መጠመዳቸውን አይተዋል፡፡ በቡልጋሪያው ልዑል ስይስማን አበረታችነት ተገፋፍተው በደቡብ ሰርቢያ አንዳንድ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ነገር ግን የዑስማኒያ ጦር ሲመጣበት ስይስማን ወደ ነይኩውበሉይ ከተማ ሸሸ፡፡ እዚያም ሁኖ ከተቀሩት ጦሩ ጋር በመቀናጀት በዑስማኒያ ኃይሎች ላይ ጥቃት ሰነዘረ፡፡ ይሁንና ጦሩ ክፈኛ ተመታበትና እሱም ተማረከ፡፡ እንደዚህም ሁኖ ሱልጣኑ ገራለት፡፡ ግማሽ ግዛቱን እንዲያስተዳድር ተወው፡፡ የተቀረውን ግማሽ ወደ ዑስማኒያ መንግሥት አጠቃለለው፡፡ የሰርቡ ንጉሥ የጦር ተጓዳኙ በነበረው በስይስማን ላይ ምን እንደደረሰበት ባወቀ ጊዜ ከነጦሩ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ርቆ ጥግ ያዘ፡፡ የዑስማኒያ ሰራዊቶች ግን ተከታትለው ኮሶቮ መሬት ሊይ ደረሱበት፡፡ (ኮሶቮ-ከቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ነፃነቷን ያገኘች ሀገር ስትሆን ነዋሪዎቿ በአብላጫው የአልባኒያ ሙስሊሞች ናቸው)፡፡ በሁለቱ ኃይሎች መካከል የውጊያ ሚዚኑ ተዘዋዋሪ ሁኖ ቀጥሎ ባለበት የንጉሥ ላዛር አማች በሥሩ የነበረውን 10,000 ተዋጊ ጦር አስከድቶ ወደ ሙስሊሞች ወገን ሲሰለፍ የውጊያ ሚዛኑ ተቀየረ፡፡ ንጉሥ ላዛር ተሸነፈ፡፡ ቀደም ሲል በሙስሊም ምርኮኞች ላይ ስለፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት መስሊሞች ተበቀሉት፡፡ ገደሉት፡፡ ገደሉት፡፡

ይህንን ጦርነት ባሸናፊነት ሞገስ የመራው ሡልጣን ሙራድ ቀዳማዊ በዓውደ ውጊያው ላይ የተገደሉትን የሰርብ ወታደሮች ሬሳ ተዘዋውሮ እየቆጠረ ባለበት ከጀናዛዎቹ መሐል አድፍጦ የቆየ ወታደር አንደ ድንገት ተነሳና በያዘው ጩቤ ወግቶ ጣለው፡፡ የዑስማኒያ ወታደሮችም ሰርቡን ወድያው አጣድፈው ገደሉት፡፡ በዚህ መዕረካ ከሚዘከሩ ነገሮች በመዕረካው ዋዜማ እንደትናንቱ ለሊቱን ሡልጣን ሙራድ ቀዳማዊ ያደረገው ዱዓ ነው

"አምላኬ ሆይ! በአሸናፊነትህና በልቅናህ እምላለሁ - በዚህ በማደርገው ጂሃዳ ይቺን ከንቱ ዓለም አልሻበትም። ይልቁንም ያንተን ውዴታና ውዴታ ብቻ እከጅልበታለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ! ባንተ መንገድ ወደ ሚደረግ ጂሃድ በመምራት እንዳከበርከኝ ሁሉ ባንተ መንገድ በሚደረግ ጂሃድ ላይ የመሞትን ክብርም ጨምርልኝ ..."

📕ሡልጣን ጋዚ ባየዚድ ቀዳማዊ

ሡልጣን ጋዚ ባየዚድ ቀዳማዊ ስልጣኑን ሲይዝ የ30 ዓመት ሰው ነበረ፡፡ ለጂሃድ የነበረው ፍላጎትና ለኢስላምም ያለው ሐማስ የላቀ ነው፡፡ በጠላት ላይ በድንገት እንደ መቅሰፍት እየወረደ በሚፈፅመው አጣዳፊ ጥቃት “ያልድረም” መባልን ተቀፅሏል፡፡ ሡልጣን ባየዚድ እሱም እንደ ተቀደሙት ሡልጣኖች ሁሉ ዓይኑ ወደ አውሮጳ በሚደረገው ጂሃድና በቁስጢንጢኒያ መከፈት ላይ ነበረ፡፡ በመሆኑም በአናቶሊያ ውስጥ የጀርባው መሬት ከተቃዋሚ ኃይሎች መጽዳት ስለነበረባት በተናጠል የነበሩ በርካታ ከተሞችን እየተቆጣጠረ በዑስማኒያ መንግሥት ሥር አዋሀደ፡፡ ሙስሊሞች ከሩሞች ጋር በፊት ለፊት ግንባር ተጠምደው በሚዋጉበት ወቅት ከበስተኋላ እየወጋች ሠላም ትነሳቸው የነበረችው የካርማን ኢማራትም በሱ እጅ ፍፃሜዋን አገኘች፡፡ በ794 ሂጅሪያ ወደ ቆስጠንጢኒያ በመቅጣጨት ከበባት፡፡ ሡልጣን ጋዚ ባየዚድ ቀዳማዊ ከዑስማኒያ ሡልጣኖች ቁስጠንጢኒያን ለመክበብ የመጀመሪያው መሪ ሆነ፡፡ ቆስጠንጢኒያ በከባድ ከበባ ውስጥ እንዳለች እሱ ወደ ሩማኒያ አቀና፡፡ ለሩማኒያው ልዑል በላከው መልእክት በዑስማኒያ ጥበቃ ሥር ሁኖ ግዛት ሀገሩ ላይ መቆየት ከፈለገ ዓመታዊ ጂዝያ እንዲከፍል አስማማው፡፡

በሰርቢያ ላይም አስቲፈን ላዛርን ንጉሥ አድርጎ ሾመ፡፡ ሹመቱ ግን በሁለት ቅድመ ሁኔታዎች የታጠረ ነበር፡፡ ዓመታዊ ጂዝያ በመክፈል በግዛት ሀገሩ ላይ ነፃ መሆንና በተጠየቀ ጊዜ ደሞ እሱና ወታደሮቹ በማንኛውም ወቅት ታዛዥ ሁነው ከዑስማኒዮች ጎን እንዲቆሙ የሚል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሡልጣን ጋዚ ባየዚድ ቀዳማዊ የእስቲፈንን እህት ኡሉፈር የምትባለውን ተዘወጀ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~5

የዑስማኒያ ሡልጣናዊ መንግሥት ተከታታይ ድሎች በአውሮጳ ቀልብ ውስጥ የማይሰክን ፍርሐት እየለቀቀባቸው መጣ፡፡ የሀንጋሪው ንጉሥ በጳጳሱና በአውሮጳ ክርስቲያናት እየታገዘ ተነሳ፡፡ ጳጳሱም ለይቶላቸው በዑስማኒዮች ላይ የመስቀል ጦርነት ዓወጁ፡፡ ምሥራቅ ፈረንሳይ፣ እና ደቡብ ጀርመን ለጥሪው ምላሽ ሰጡ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ፈረሰኛ ጦርም ሁነው ተሰባሰቡና በ798 ሂጅሪያ በዑስማኒያ ቁጥጥር ሥር የነበረችውንና በሰሜን ቡልጋሪያ የምትገኘውን የነይኮውብሊይን ከተማ ከበቡ፡፡ ለዑስማኒያ መንግሥት የታመኑ ብዙ ክርስቲያኖችና የዑስማኒያ ወታደሮች የተካተቱበት የዑስማኒዮች ጦር በሰርቡ ልዑል በኢስቲፈን አዛዥነት እየተመራ ወጣ፡፡ ሁለቱ ጦሮች ተገናኙ፡፡ ተጋጠሙ፡፡ የመስቀል ጦረኞች አይሸነፍ ሽንፈት ተሸነፉ፡፡ በዚህ መዕረካ ብዙ የአውሮጳ የጦር አለቆችም ተማረኩ፡፡ ከነሱ መሐል የቦርጎኒያው ዱክ ይገኝበታል፡፡ ከፍተኛ ክፍያ ከፍሎ ነፍሱን ከሞት ታደገ፡፡ ሡልጣኑ ፊት ቆሞ በሕይወት እስካለ ድረስ ዳግመኛ እንደማይዋጋ ምሎ ተናገረ፡፡

ቀዳማዊ ጋዚ ባየዚድ ግን እንዲህ አለው:- “እኔ ይሄን መሐላህን እንዳትጠብቅ ፈቅጄልሃለሁ፡፡ አንተ እኔን መልሰህ መዋጋት ሐላል አድርጌልሀለው፡፡ መላውን የአውሮጳ ክርስቲያን ተዋግቶ በነሱ ላይ ድል ከመቀዳጀት የበለጠ ምንም ነገር እኔ ዘንድ ተወዳጅ አይደለም።” ከዚህ ከፍተኛ የጦር ድል በኋላ የባዘንታይን ንጉሠ ነገሥት በቁስጠንጢኒያ ላይ የተጣለው ከበባ ይነሳላቸው ዘንድ 10,000 የወርቅ ዲናር ከፈለ፡፡ በተጨማሪም ከተማዋ ውስጥ ለሙስሊሞች መስጂድ ለማቆም ቃል ገባ፡፡ ሡልጣን ጋዚ ባየዚድ ቀዳማዊ ከሞንጎሎች ጋር በተደረገ ውጊያ ላይ ተማርኮ በእስር ጥበቃ ሥር እንዳለ በ805 ሂጅሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ተጨባጭ ታሪካቸው እንደሚያስረዳው የሞንጎል ሙስሊሞች ከኢስላም ሥሙን ብቻ እንጂ ተግባሩን አልያዙም፡፡ በኢስላም ከተሞች ላይ እየተነሱ በሚፈጽሙት የጭካኔ እርምጃ ኢስላም ከነሱ ድርጊት የፀዳ የኾነበትን አስከፊ ድርጊት ሲፈጽሙ ኖረዋል፡፡ በርግጥ ከሞንጎሎች መከሰት ከ35 ዓመት በኋላ እንደ በርኬ ኻን ያሉ መሪዎች ከውስጣቸው እንደሰለሙና ለዲኑ ዘብ ቆመው እንደተዋጉ ታይቷል፡፡ ይሁንና ሞንጎሎች ቱርክ አናቶሊያ ድረስ ዘልቀው ወረራዎችን በመፈጸም የዑስማኒያ ሡልጣኖች አውሮጳ ላይ በሚያካሄደው ጂሃድና ቁስጢንጢኒያን ለመክፈት የሚደረገውን ጥረት ይረዳ ዘንድ እንደምንም ብለው ያዋሐዷቸውን ከተሞች እንደገና በመከፋፈል በቀዳሚው የዑስማኒያ ግንባር ላይ የበስተኋላ ችግር እየፈጠሩ ያስቸግራሉ፡፡

በአናቶሉያ የተቀረውን የዑስማኒያ ግዛት ሁሉ ሞንጎሎች ተቆጣጠሩት፡፡ በዑስማኒያ አገዛዝ ሥር የነበሩት የአውሮጳ ግዛቶችም የዑስማኒያ መንግሥት ከበስተጀርባ የገጠመውን እክል በማየትና እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ነፃነታቸውን አወጁ፡፡ ቡልጋሪያ፣ ሰርቢያና ሩማኒያ ከዑስማኒያ መንግሥት ነፃ ነን አሉ፡፡ በዚህ ላይ የሡልጣን ባየዚድ ልጆች ሌላውን ጉዳይ ችላ ብለው ሥልጣን ፉክክር ውስጥ መዘፈቃቸው ችግሩን አወሳሰበው፡፡ ሱለይማን የተባለው የሡልጣኑ ልጅ የተወሰነውን የአውሮጳ የዑስማኒያ ግዛትና ርዕሰ ከተማ አድረኑህን ጨምሮ - የራሱ አድርጎ በመያዝ ተነጠለ፡፡ በተቀሩት የሥጋ ወንድሞቹ ላይ እገዛ ያደርግለት ዘንድ ከዳግማዊ አማኑኤል የባዘንታይን ንጉሠ ነገሥት ጋር ተዋዋለ፡፡ በዚህም እንደመቀራረቢያ የሰልነቄን ከተማና የጥቁር ባህርን የተወሰነ ጠረፋማ ዳርቻ በከፊሉ ሰጠው፡፡ የንጉሡ የቅርብ ዘመድ ከኾነች ሴት ጋርም ጋብቻ ፈጸመ፡፡ ሌላውና ዒሳ የተባለው ወንድሙ በሟች አባቱ ቦታ ራሱን ሱልጣን ብሎ አወጀ። በአናቶሊያ ሙሀመድ ደግሞ የሞንጎሎች ጫና ረገብ ሲልለት ከቅርብ ታማኝ ወታደሮቹ ጋር በመሆን የተቀሩትን ሞንጎሎች ተዋግቶ ቀደም ሲል ከአባታቸው ከባየዚድ ጋር በሞንጎሎች እጅ ምርኮ ተወስዶ የነበረውን ሙሣ የተባለ ወንድሙን ከምርኮ አስለቀቀው፡፡ ከዚያ ግን የተቀሩት ወንድሞቹን መጋደል ቀጠለ።

ከብዙ ትግሎች በኋላ ሙሀመድ በወንድሙ ዒሳ ላይ ድል ቀናው። ዒሳ ተገደለ። ከዚያም በወንድሙ በሙሳ መሪነት ሌላውን ወንድማቸውን ለመዋጋት ጦር ላከ። ሙሳ በመጀመሪያው ግጥሚያ ድል አልቀናውም። ተስፋ ሳይቆርጥ በሠነዘረው ድጋሚ ጥቃት ድል ቀናው፡፡ ሡለይማንም በ813 ሂጅሪያ በአድረኑህ በር ላይ ተገደለ፡፡ ቀጥሎም ሙሣ በሞንጎሎች ወረራ ወቅት ሰርቦች ስለፈፀሙት የክህደት ተግባር በቅጣት ሊበቀላቸው ዘመተ፡፡ ሰርቦች በሀንጋሪያ ንጉሥ እየተረዱ ተዋጉና ሙሣ ተሸነፈ፡፡

ሙሣ በአውሮጳ የዑስማኒያ ግዛትን ለብቻው ተቆጣጥሮ የራሱ አድርጎ በመያዝ ከዋናው የዑስማኒያ መንግሥት መገንጠል አማረው፡፡ ቅድሚያ ግን ቆስጠንጢኒያ ላይ ከበባ አካሄደ፡፡ የቆስጠንጢኒያ ንጉሥና የሰርብ ንጉሥ ከሙሐመድ ጋር በማበር በሙሣ ላይ ተነሱ፡፡ እነዚህ የቃል ኪዳን ቡድኖች ድል አደረጉና አሚር ሙሣ ተገደለ፡፡ ሙሐመድ ከዚህ በኋላ ብቸኛው የሥልጣን ባለቤት መሆኑን አረጋገጠ።

📕ሡልጣን ጋዚ ሙሀመድ ቀዳማዊ

ሡልጣን ሙሐመድ ሶስት ወንድሞቹን ዒሳን ሙሣንና ሱለይማንን መግደሉ ተሰምቶታል፡፡ ከዚህ የህሊና ወቀሳ ለመላቀቅ የፈለገ ይመስል ከዚህያ በኋላ ይቅር ሲል ተስተውሏል፡፡ የቀርማኑ አሚር በጦርነት ተሸንፎ ለሱልጣኑ እንደሚታዘዝ ከማለለት በኋላ ይቅር ብሎ አሰናብቶቷል፡፡ እንደገናም ግን ተመልሶ በሡልጣኑ ላይ አመፀ፡፡ እንደገናም ሡልጣኑ ተዋግቶ ካሸነፈው በኋላ መልሶ በይቅርታ አልፎታል፡፡ የኢዝሚርን አሚርም እንደዛው ድል ካደረገው በኋላ ይቅር ብሎት- እንደውም ነይኩብሊይ ከተማ ላይ ሹሞታል፡፡ ሙስጠፋ ቢን ሡልጣን ባየዚድ በተራው የሥልጣን ተቀናቃኝ ሁኖ ከተነሳበትና ኋላም ድል ተመትቶ ወደ ባዛንታይን ንጉሠ ነገሥት ከሸሸ በኋላም ይቅር ሊለው ፈልጎ ነበር፡፡ በሌላ ወገን ግን በድረዲን ቢ ሐረካት የተባለ ሌላ አፈንጋጭ የኢሽትራኪያ ርዕዮት አቀንቃኝ ተነስቶ ከሌሎች ዲያናት ድጋፍ ባሰባሰበ ጊዜ ተዋግቶ አሸንፎ ገድሎታል፡፡ በ824 ሂጅሪያ ሡልጣን ሙሐመድ ሞተ፡፡ ሥልጣኑን ከሱ በኋላ ለልጁ ለሙራድ ተናዟል፡፡ በዑስማኒያ ዘመን በመሃሉ የተከሰተው ይህ የወንድማማቾች በሥልጣን ፉክክር መጠፋፋት ጥቁር ነጥብ ጥሎ እንዳለፈ ይገነዘቧል፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጢንያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~6

📕ሡልጣን ጋዚ ሙራዱ ሣኒ

ዳግማዊ ሙራድ በ824 ሂጅሪያ በትረ ሥልጣኑን ሲጨብጥ ዕድሜው ገና ከ18 ዓመት አልዘለለም፡፡ በአናቶሊያ የሚገኙ ብዙ ግዛቶች ያኔ በሞንጎሎች ወረራ ሰበብ ምስቅልቅል ብለዋል፡፡ እነሱን እንደገና በደንብ ማዋቀሩ በአውሮጳ ለሚደረገው ጂሃድ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ሡልጣን ሙራድ ዳግማዊ ይሄንኑ በፍጥነት ማስተካከል ነበረበት፡፡ እስከዛው ድረስ አውሮጳን በዲፕሎማሲ አግባብ መያዝ ነበረበትና ከሀንጋሪ ንጉሥ ጋር ለአምስት ዓመት የሚፀና የተኩስ አቁም መፈራረም አቅዶ ከወዲሁ እክሎች ገጠሙት፡፡

የባዛንታይን ንጉሥ ተነሳና ከሙራድ በኩል ቆስጠንጢኒያ ላይ ወረራ ያለመፈጸም ውል እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡ ከዚሁ ጋር አብሮ ግን ለውሉ ማስጠበቂያ ሁለት ወንድሞቹን በመያዣነት እንዲሰጠው ፈለገ፡፡ የሱን ቅድመ ሁኔታ የማይቀበል ከሆነ ሮም እሱ ዘንድ ሽሽቶ በጥገኝነት የሚገኘውን አጎቱን /ሙስጠፋን/ ፈትቶ እንደሚለቅበት አስጠነቀቀ፡፡ ሡልጣኑ ግን ጥያቄውንም ቅድመ ሁኔታውንም ውድቅ አደረገበት፡፡ የባዛንታይን ንጉሥ እንደዛተው ለሙስጠፋ ስንቅና ትጥቅ ጭኖ ለቀቀው፡፡ እሱም የጋሊዮብሊ ከተማን ከብቦ አጠቃ፡፡ ይሁንና የከተማዋን ጠንካራ ምሽግ መስበር አልቻለም፡፡ ከዚያም ሙስጠፋ ወደ አድረኑህ ከተማ አመራ፡፡ የዑስማኒያ ቃኢድ የነበረውን ባየዚድ በሻህን ገደለ፡፡ ቀጥሎም የወንድሙን ልጅ /ሡልጣን ሙራድ ዳግማዊ/ ለመግጠም ሲጓዝ ከራሱ የጦር ሠልፍ አዛዦች መካከል ክህደት ተፈጽሞበት ከዚያ ጥሎ ወደ ጋሊዮብሊ ከተማ ሲሸሽ ተይዞ በሞት ፍርድ ተቀጣ፡፡ ሡልጣን ሙራድ ዳግማዊ የባዛንታይን ንጉሥ ስለፈጸመው ድርጊት ሊበቀለው አስቦ በ825 ሂጅሪያ ቆስጠንጢኒያ ላይ ከበባ ጣለ፡፡ ይሁንና ሊከፍታት አልቻለም፡፡

📕ሁለተኛው የኮሶቮ ጦርነት

ሙስሊሞች ለሁለተኛ ጊዜ እዚህ መስክ ላይ ከክርስቲያን አውሮጳ ጦር ይገናኛሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን የሀንጋሪ ጦር የከዚህ ቀደም ሽንፈቱን በሙስሊሞች ላይ ለመበቀል ከአውሮጳ ጦር ጋር በተደራቢነት ተገኝቷል፡፡ ሙስሊሞች ግን በሀንጋሪ ጦር ላይ ከፍተኛ ድልን ተቀዳጁ፡፡ ሡልጣን ሙራድ ዳግማዊ በ855 ሂጅሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በመንበረ ሥልጣኑ ላይ ልጁ ሙሐመድ ዳግማዊ ተቀመጠ፡፡ እነሆ ቆስጠንጢኒያን የመክፈትን የድል ዘውድ በራሱ ላይ እንዲጭን ወደተመረጠው ሰው መጥተናል፡፡ ጉዞው ግን በሁሉም የዑስማኒያ ሡልጣኖች ድካምና ደም እየታጀበ እዚህ መድረሱን አይተናል፡፡ ለመጨረሻው ወሳኝ ጥቃት መንገዱን የደለደሉ እነሱ ናቸው፡፡ ሡልጣን ጋዚ ሙሐመድ ዳግማዊ አልፋቲሕ/ 855-866 ሂጅሪያ በትረ ሥልጣኑን ሲጨብጥ ዕድሜው 22 ዓመት ነበረ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️የቆስጠንጠኒያ ድል ከመሰረቱ

▪️ክፍል~7

📕ፈትሑል ቆስጠንጢኒያ

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተጠየቁ - “የትኛዋ ከተማ ቀድማ ትከፈታለች- ቆስጠንጢኒያ ወይስ ሩም? ተባሉ፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) “የሂረቅል ከተማ ቀድማ ትከፈታለች” አሉ፡፡ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው የሂረቅል ከተማ የተሰኘችው ቆስጠንጢኒያ ናት፡፡ እነሆ በዚህ የረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሐዲስ አበራች ዓላማ ከዑስማኒዮች በፊትም ኑረው ያለፉ ሙስሊሞች ሁሉ ቆስጠንጢኒያን ለመክፈት ተሽቀዳድመዋል፡፡ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡ በዚህ ረገድ በተለይ ኡመዊዮች ይጠቀሳሉ፡፡ ዐብባሲያዎችም አልቦዘኑም፡፡ ከሁሉም ግን የዑስማኒያ ቱርኮች የጦር ንቅናቄ ቆስጠንጢኒያን የመክፈት ዓላማ ያነገበ እንደነበረ አይተናል፡፡ እንደዛውም ሁሉ ሡልጣን ሙሐመድ ዳግማዊ ለቆስጠንጢኒያ መከፈት የጦር መሰናዶውን አደረገ፡፡

በአውሮጳ ምድር የጦር ምሽግ ግንባታ ጀመረ፡፡ በተለይም ከቦስፈር የባሕር ወሽመጥ ጋር በተያያዘ የጦር እቅዱን አስተካከለ፡፡ በአስያ ምድር ደሞ ቀደም ሲል ለተመሳሳይ ግብ በሡልጣን ባየዚድ ቀዳማዊ ተገንብቶ የነበረውን የጦር ምሽግ እንዳዲስ አጠናከረ፡፡ ይኸውም - የቦስፈርን የባህር መሽመጥ በመቆጣጠር ለቆስጠንጢኒያ ምንም ዓይነት የጦር ድጋፍ /የስንቅና ትጥቅ አቅርቦት/ እንዳይደርስላት ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

የቆስጠንጢኒያ ንጉሠ ነገሥት የሡልጣኑን የመክፈት አቅም ከወዲሁ በመገመት ዓመታዊ ጂዚያ በመክፈል የከተማይቱን መወረር ለማስቀረት ጥያቄ አቀረበ፡፡ ሡልጣኑ ግን ጥያቄውን ውድቅ አደረገበት፡፡ ከዚያም ወደ ክርስቲያን አውሮጳ የጦር አገሮች ንጉሡ ተጣራ፡፡ ጀኖአ /በጊዜው ነፃ መንግሥት ነበረች/ 80 የጦር መርከቦችን ላከችለት፡፡ የጦር መርከቦቹ የተላኩት ዑስማኒዮች በቆስጠንጢኒያ ላይ ጦር ከበባቸውን በሁሉም አቅጣጫ እያጠነከሩ ባሉበት ወቅት ነበር፡፡ ጨከዑስማኒያ ባሕር ኃይል ጋር ፊለፊት ተገጣጠሙ። ይሁንና ጂኖአዎች ወደ ወርቃማው ቀንድ ያቀርን ዘሃቢይ/ ሠርገው መግባት ቻሉ፡፡ ዑስማኒዮች ሊገናኟቸው ሲቀዝፉ ጂኖአዎች ወደ ቀርን ዘሃቢይ እንደገቡ ወዲያው ሰንሰለቱ እያዩት ተዘጋ፡፡

ከተማዋን በምድር የከበበው የዑስማኒያ ወታደሮች ቁጥር 250,000 ገደማ ሲሆን በባሕር ደሞ 180 የጦር መርከቦች የውጊያ ቁመና ይዘዋል፡፡ የጠቅላላውን ጦር አሰላለፍ ካስተካከለ በኋላ ሙሐመድ ዳግማዊ ከፍተኛ የጦር አዛዦችን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦
“የቆስጠንጢኒያ መከፈት ከተሳካልን የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሐዲስና ከሙዕጂዛዎቻቸው አንዱ ሙዕጂዛቸው የኾነው በኛ ውስጥ ተረጋገጠልን ማለት ነው፡፡ በሐዲሱ የተመለከተው ነገርም ከድርሻችን ይኾናል፡፡ ለወታደሮቹ ልጆቻችን አንድ ባንድ አድርሱ፣ እየተጠባበቅን ያለነው ታላቅ ድል ለኢስላም ኃይልና ከበሬታን ይጨምርለታል፡፡ በያንዳንዱ ወታደር ላይ የሸሪዓችንን አስተምህሮ እንደዓይኑ መጠበቅ ይወጅብበታል፡፡ ከነሱ አንዱም ይሄን አስተምህሮ የሚያመክን ነገር መፍቀድ የለበትም፡፡ ከአብያተክርስቲያናትና ከቤተ-አምልኮዎች ይጠንቀቁ፡፡ በክፉ እንዳይደርሱባቸው፣ ቀሳውስትን፣ ድኩማንና አዕሩግን- እነዚያ የማይጋደሉ የኾኑትን ሁላ ዳዕዋ ያድርጉላቸው”

ከዚህ በኋላ ዑስማኒዮች በሁሉም ግንባር /በምድርና በባሕር፣ በምዕራብና በምሥራቅ/ ቆስጠንጢኒያ ላይ የከበባ ቀለበቱን እያጠበቡ መጡ፡፡ የቦስፈርን ወሽመጥ /መዲቀል ቦስፈር/ በባሕር ኃይል ተዋጊ ጀልባዎች ጥርቅም አድርገው ዘጉት፡፡ ከዚያም በኋላ የቁስጠንጢኒያን ግንቦች ከሁሉም አቅጣጫ በመድፍ ይደኩት ያዙ፡፡ ከተማዋ ይሄን ውርጅብኝ ተቋቁማ መዝለቅ አልቻለችም፡፡ እነሆ ዑስማኒዮች በወርኃ ጁማደል ኡውላ 15ኛ ቀን ማለዳ 857 ሂጅሪያ ነቢያዊው ሐዲስ ከተነገረ ከ850 ዓመት በኋላ የቆስጠንጢኒያን ከተማ በድል አድራጊነት ገቧት፡፡ ንጉሠ ነገሥቷ በመዕረካው ውስጥ ተገደለ፡፡ ዑስማኒዮች ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሯት፡፡ ሙሐመድ ዳግማዊ አልፋቲሕ መባልን በሥሙ ላይ ተቀፀለ፡፡ የከተማዋን ሥምም ቀየረ፡፡ አዲስ ሥም አወጣላት፡፡ ኢስላም ቡል አላት፡፡ የኢስላም ከተማ መዲነቱል ኢስላም/ ማለት ነው፡፡ የዑስማኒያ ሥርወ-መንግሥት ርዕሰ ከተማዋም አደረጋት፡፡ ኋላም የኢስላማዊው ኺላፈት ዋና ከተማ ሁና እስከ ኺላፈቱ ፍፃሜ ድረስ ትዘልቃለች፡፡ እነሆ በቆስጠንጢኒያ መከፈት የሙስሊሞች አንድ ቁጥር ጠላት የነበረው የባዛንታይን መንግሥት ከ8 ክፍለ ዘመናት ያልተቋረጠ ተጋድሎ በኋላ ተፈጸመ። ሡልጣን ጋዚ ሙሐመድ አልፋቲሕ የከተማዋን ክርስቲያን ነዋሪዎች በዲናቸው ላይ ነፃነትን ሰጣቸው፡፡ በመዲናዋ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት ግማሾችን ገዝቶ ወደ መሳጂድ ቀየራቸው፡፡ የተቀሩትን ግማሾች ለህዝበ-ክርስቲያን መገልገያነት ተወላቸው፡፡

ሙስሊሞች ቆስጠንጢኒያን ከበው እየተዋጉ ባሉበት ሰዓት እንደ ድንገት ጀሊሉ ሰሐቢይ አቢ አዩብ አል-አንሷሪ ቀብር ላይ መጡ፡፡ ጀሊሉ ሰሐቢይ አቢ አዩብ አል-አንሷሪ በየዚድ ቢን ሙዓዊያ ዘመን ቁስጠንጢኒያን ለመክፈት በተካሄደው የመጀመሪያ ዘመቻ ወቅት ከተማዋ ላይ ተጥሎ በነበረው ከበባ ወቅት እዚህ ተሰውቶ ተቀብሯል። ከቁስጠንጢኒያ በድል መከፈት በኋላ ሥፍራው ላይ መስጂድ ተገነባ፡፡ ከዚህም በኋላ ሡልጣኖች መንበረ ሥልጣኑን በሚረከቡበት ጊዜያት ሁሉ የዑስማኒያ ሥርወ-መንግሥት መሥራች የኾነውን የዑስማን ኤርትሩልን ሠይፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት የሚፈፅሙበት ዋና መስጂድ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
2024/05/15 22:48:06
Back to Top
HTML Embed Code: