ኬንያ ተጨማሪ 200 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ለመግዛት ልዑኳን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን አስታወቀች!
ኬንያ ተጨማሪ 200 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ለመግዛት ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳን አስታወቀች፤ የኬንያ የኢነርጂ እና ሃይል ሚኒስቴር የቴክኒክ ልዑካን በኤሌክትሪክ ግዢው ዙሪያ ለመደራደር ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ተጠቁሟል።
ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው የኬንያ ልዑክ በኤሌክትሪክ ሀይሉ የክፍያ ታሪፍ፣ አቅርቦቱ የሚከናወንበትን ግዜ፣ የማስተላለፊያዎቹ ደህንነት አጠባበቅ መንገዶች ዙሪያ የመጨረሻ ስምምነቱን እንደሚፈጽም ተገልጿል።ለኬንያ የሚቀርበው ተጨማሪ መጠባበቂያ ሀይል ከህዳሴ ግድብ ከሚመነጨው እንደሚሆን ከኬንያው ኬዲአርቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከሶስት አመታት በፊት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ለ25 አመታት የሚቆይ የሀይል ግዢ ስምምነት መፈጸማቸው የሚታወስ ሲሆን ኢትዮጵያ ለኬንያ ኤሌክትሪክ በማቅረብ በኪሎ ዋት ስድስት ነጥብ አምስት የአሜሪካን ሳንቲም እንደምታስከፍል ተቀምጧል፤ ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታስከፍላት የኬሎዋት ክፍያ ለማምረት ከምታወጣው ወጪ እጅግ ያነሰ ነው ተብሏል።
ኬንያ ከጂኦተርማል ኢነርጂ አንድ ኪሎ ዋት ለማመንጨት 20 የአሜሪካ ሳንቲም ወጪ እንደምታደርግ ተጠቁሟል። ኬንያ አጠቃላይ ከጎረቤቶቿ የምታስገባው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 400 ሜጋ ዋት ለማድረስ እየጣረች መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ይህም አመታዊ 10 ሚሊየን ዶላር እንድታድን ያደርጋታል ተብሏል።በአሁኑ ወቅት በኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ከፍተኛ በሚሆንበት ሰዓታት 283 ሜጋዋት እጥረት እንደሚያጋጥማት መረጃዎች አመላክተዋል።

የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት ያስፈልጋል ተባለ
በ #ኢትዮጵያ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ገለጹ።
የገንዝብ ሚኒስትር ደኤታው እዮብ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
የምክር ቤት አባላቱ በሀገሪቱ ለተጀመሩት የመንገድ ፕሮጀክቶች ትልቅ ማነቆ የሆነውን በጀት መፍታት የሚያስችል የብድር ስምምነቶችን ገንዘብ ሚኒስቴር ሊያመጣ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
በተጨማሪም የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ከአጋር የልማት ድርጅቶች ሀብት የማሰባሰብ ስራ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ በምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ከተለያዩ የብድር አቅራቢ ተቋማት በተገኘ ብድርና ከልማት አጋሮች በተገኘ ድጋፍ በርካታ መንገዶች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ሆኖም በምክር ቤቱ በቂ አይደለም የተባለውን በመውሰድ የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ እና ከልማት አጋሮች ሀብት ማሰባሰቡን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።
አጠቃላይ እንደሀገር የተጀመሩትን የመንገድ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ከአንድ ነጥብ ሶስት ትሪሊዮን እስከ አንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።
ችግሩን ለመፍታት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን አንስተው፤ ዘርፉን ለማሳደግ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያስፈልጋል ብለዋል።

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
“አደባባይ የወጣሁት ሕዝቤ እንዲደርስልኝ ነው”:- አትሌት ገለቴ ቡርቃ
******
በኢቲቪ ኦፋን ኦሮሞ ቴሌቪዥን ከሚቀርበው "ገመዳ ሾው" ጋር ቆይታ ያደረገችው አትሌት ገለቴ ቡርቃ "አደባባይ የወጣሁት ሕዝቤ ያለሁበትን አስቸጋሪ ሁኔታ አውቆ እንዲደርስልኝ ነው" ብላለች፡፡
ከ800 እስከ ማራቶን ኢትዮጵያን ወክላ በተለያዩ መድረኮች የተወዳደረችው አትሌት ገለቴ ሳላውቅ ትዳሬ እየፈረሰ ነውም ብላለች፡፡
"በሩጫ ባገኘሁት ገንዘብ ወደ ኢንቨስትመንት ልገባ ስል ችግር አጋጥሞኛል" የምትለው አትሌቷ.፣ ባለቤቷ በ2009 ዓ.ም ከቤት ጠፍቶ ስምንት ወር ከቆየ በኋላ ፍርድ ቤት እንዳቀረባት እና እስካሁን ክርክር ላይ እንዳሉ ተናግራለች፡፡
ዘጠኝ ዓመታት አብራ የቆየችው ባለቤቷ በ2009 ዓ.ም ለውድድር ከሀገር ውጭ ስትሄድ ከሸኛት በኋላ ውድድሯን ጨርሳ ስትመለስ ባዶ ቤት እንዳገኘች ገልጻለች፡፡
ፍለጋውን ጀምራ ለፖሊስ ስታስታውቅ "ደውሎ ለምን ስሜን ታጠፊያለሽ? አርፈሽ የማትቀመጪ ከሆነ እገድልሻለሁ" እንዳላት የተናገረችው ገለቴ በ2010 ዓ.ም በእርሱ በኩል የክስ መጥሪያ እንደደረሳት ጠቅሳለች፡፡
ፍርድ ቤት ስትቀርብም ባለቤቷ ጋብቻቸው እንዲፈርስ እንደጠየቀ እሷ ደግሞ የተጋቡት በእምነት ተቋም እንደሆነ እና እምነት ደግሞ ጋብቻ እንዲፈርስ እንደማይፈቅድ ጠቅሳ አላፈርስም እንዳለች ነገር ግን በጫና ጋብቻው እንደፈረሰ ትናገራለች፡፡
"ከዚያ ቀደም የወሰደውን ውክልና ተጠቅሞ ያለውን ንብረቴን ሸጦ ስለነበረ ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ንብረቴን ለማሳገድ ብንቀሳቀስም ከአንድ ቤት በስተቀር ሁሉም ስማቸው ዞሮ ነበር ያገኘሁት" ብላለች አትሌት ገለቴ፡፡
አንዷ የቀረችው ቤትም በ2008 ዓ.ም ውክልናው የተነሳባት ቤት እንደሆነ የጠቀሰችው አትሌቷ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አሥር ቤቶች፣ አራት መኪና እና ሌሎች በርካት ንብረቶችን ተሸጠውባት ባዶ እጇን መቅረቷን ተናግራለች፡፡
"እናቱ እንዲኖሩበት የሰጠሁትን መንግሥት የሰጠኝን ቤት እንኳን ለእናቱ ሸጧል" የምትለው ገለቴ፣ "ከጋብቻ በፊት ያፈራሁት ንብረቴም ሳይመለስ፣ ከጋብቻ በኋላ ያፈራነውንም ሳልካፈል አንዷን የቀረችውን ቤት ለመካፈል ፍርድ ቤት ወስኖብኛል" ስትል ተናግራለች፡፡
እሱ ቀድሞ ሁሉንም አቅዶበት ስለሄደበት ያላትን አቅም ሁሉ ተጠቅማ ፍርድ ቤት ብትከራከርም ውሳኔው ግን ከሷ በተቃራኒ እንደሆነ ተናግራለች፡፡
ከዚህ አልፎም እንደሚያስፋራራት ለፖሊስ ማልከቷን ጠቅሳ፣ ንብረቱም እንዳይገኝ አንድም ገንዘቡን በሱ ስም እንደማያስቀምጥ እንዲሁም ተሸጡ የተባሉ ንብረቶችም ከዋጋቸው እጅግ ባነሰ የተሸጡ መሆናቸው ጉዳዩን ውስብስብ እንዳደረገው ተናግራለች፡፡
ይህን ጉዳይ የማያውቀው የመንግሥት አካል እንደሌለ የጠቀሰችው አትሌት ገለቴ፣ "እስካሁን መፍትሄ ካለማግኘቴም በላይ ወደ ጎዳና ለመውጣት ከዚያም አልፎ ለሕይወቴ አስጊ ሁኔታ ላይ ስለምገኝ የሚመለከተው አካል ይድረስልኝ" ትላለች፡፡
"አደባባይ የወጣሁት ሕዝቤ እንዲደርስልኝ ነው" ያለችው ገለቴ፣ "ወጥቼ የምወደውን ስፖርት እንኳን እንዳልሠራ ማስፋራራት እየደረሰብኝ ቤት ውስጥ ተዘግቼ ተቀምጫለሁ፤ የአቅሜን ያበረከትኩላት ሀገሬ እና ሕዝብ ያለሁበትን ሁኔታ ይወቅልኝ" ብላለች፡፡
በለሚ ታደሰ ( EBC)

“አሜሪካ ብትሳተፍም ባትሳተፍም፣ እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት በሙሉ የማጥፋት አቅም አላት”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እንደተናገሩት፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሳተፉም ባይሳተፉም፣ እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት በሙሉ የማጥፋት አቅም አላት።
ኔታንያሁ ይህንን የተናገሩት ዋይት ሃውስ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጣልቃ መግባት አለመግባታቸውን ይወስናሉ ከማለቱ በፊት ነው።
የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች፣ እስራኤል የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዋነኛ ክፍል የሆነውን ፎርዶው የነዳጅ ማበልጸጊያ ፋብሪካን ለማጥፋት የአሜሪካ እገዛ ሊያስፈልጋት ይችላል ብለው ያምናሉ።
"በሁሉም ኢላማዎቻችንን፣ ሁሉንም የኒውክሌር ተቋሞቻቸውን የማስወገድ አቅም አለን ያሉት ኔታንያሁ፤ ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ለመቀላቀል ይፈልጉ እንደሆነ ወይም እንደማይፈልጉ የሚወስኑት እርሳቸው ናቸው ብለዋል።"
ኔታንያሁ አክለውም እርሱ (ትራምፕ) ለአሜሪካ የሚበጀውን ያደርጋል፣ እኔም ለእስራኤል መንግስት የሚበጀውን አደርጋለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከዛሬ ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል።
መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።
ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል።
ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ ባንኮችን፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፎችን ወይም የወኪል ቢሮዎችን ማቋቋም ይገኙበታል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት መሆኑን የገለፀ ሲሆን የውጭ ባንኮች እና ባለሀብቶችም ማመልከቻዎቻቸውን ከዛሬ ጀምሮ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።
Via Capital Newspaper

በቀጣይ አመት ማስተማር የማይችሉ ት/ቤቶች
በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉ የትምህርት ተቋማትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ይፋ አድርጓል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉና እውቅናቸው የተሰረዘ ትምህርት ቤቶችን አሳውቋል።
በ2016 ዓ.ም ማጠቃለያ ላይ በተደረገው የእድሳት ፍቃድ ምዘና ለ2017 የትምህርት ዘመን ካሳዩት ዝቅተኛ ውጤት መሻሻል እንዲያሳዩ እስከ 2017 ዓ.ም ታህሳስ ድረስ ዝግጅት እንዲያደርጉ ፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ላይ በማስጠንቀቂያ እንዲያስተምሩ ጊዜ ቢሰጣቸውም በታህሳስ 2017 በተደረገ የእድሳት ፍቃድ ምዘና ውጤታቸው መሻሻል ባለማሳየቱና ዝቅተኛና ከደረጃ በታች በመሆኑ ምክንያት በ2018 የት/ት ዘመን ማስተማር የማይችሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳውቋል።
በመሆኑም የትምህርት ማህበረሰቡ እና ወላጆች ይህን በማወቅ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እንድታከናውኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር አሳውቋል።

በታጣቂዎች ጥቃት 16 አሽከርካሪዎች መገደላቸው ተነገረ
"ተሳፋሪዎችና አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል"
በአማራ ክልል በጎንደር መተማ መንገድ ላይ "መቃ" በተባለች ሥፍራ ታጣቂዎች ሰኞ'ለት በፈጸሙት ጥቃት 16 አሽከርካሪዎች ተገድለው፣ በርካቶች መቁሰላቸውን ዋዜማ ምንጮችን ጠቅሳ ዘግባለች፡፡
በታጣቂዎቹ ከተገደሉት ሾፌሮች በተጨማሪ ተሳፋሪዎችና በርካታ አሽከርካሪዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
አብዛኞቹ አሽከርካሪዎች የተገደሉት፣ ከጥቃቱ ለማምለጥ ጥረት በማድረግ ላይ ሳሉ በእሩምታ ተኩስ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል፡፡
ዋዜማ የጥቃቱን ፈጻሚ ታጣቂዎች ማንነት ለጊዜው ባታረጋግጥም፣ የፋኖ ታጣቂዎች ሰሞኑን በመተማ ወረዳ ከቅማንት ብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ግን ምንጮች መናገራቸውን ጠቁማለች፡፡

አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት የኒውክሌር ማብላያ ይዞታዎችን እንዳላወደመ የአሜሪካ መከላከያ ማዕከል (ፔንታጎን) የደህንነት ግምገማ አሳየ።
ቅድመ ግምገማው፤ ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ምናልባትም በወራት ወደ ኋላ ሊመልሰው እንደሚችል ነው ያሳየው።
ኢራን ያበለጸገችው የዩራኒየም ክምችት አሜሪካ ቅዳሜ፣ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በፈጸመችው ጥቃት አለመውደሙን የአገሪቱ የመከላከያ ደህንነት ኤጀንሲ ግምገማን የሚያውቁ ምንጮች ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ተናግረዋል።
ዋይት ሃውስ በበኩሉ፤ "ይህ ፍጹም የተሳሳተ ግምገማ" በማይረባ የደህንንት ማህበረሰብ ሾልኮ የወጣ ነው" ሲል ውድቅ አድርጎታል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፤ የኢራን የኒውክሌር ይዞታዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል በማለት በድጋሚ አጽንኦት ሰጥተው፤ "በታሪክ ውስጥ ስኬታማ ከሆኑ ወታደራዊ ጥቃቶች መካከል አንዱ የሆነውን ለማዋረድ", በሚዲያዎች የሚደረግ ሙከራ ሲሉ ከሰዋል።
ነገር ግን የፔንታጎን የደህንነት ግምገማን የሚያውቁ ምንጮች በበኩላቸው፤ የኢራን ማብላያዎች በአብዛኛው እንዳልተነኩና የጥቃቱ ተጽእኖ ከመሬት በላይ ባለው ብቻ የተወሰነ ነው ይላሉ።
የሁለቱ ኒውክሌር ይዞታዎች መግቢያዎች ተዘግተው እንደነበር የጠቀሰው ግምገማው፣ አንዳንድ መሰረተ ልማቶች ቢወድሙም ወይም ቢጎዱም፤ ከመሬት ስር ያሉት አብዛኛዎቹ ይዞታዎች ግን ከፍንዳታው ቃጠሎ አምልጠዋል ብሏል።
እኚህ ማንነታቸው ያልተገለጹ ምንጮች ለአሜሪካ ሚዲያ እንደተናገሩት፤ ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በወራት ወደ ኋላ ሊመልሰው እንደሚችል መገመቱን ገልጸዋል።
የኢራን የመንግሥታዊ ሚዲያ ምክትል የፖለቲካ ዳይሬክተር ሃሰን አብደኒ በበኩላቸው፤ አሜሪካ ጥቃት ያደረሰችባቸው ሶስቱ የኒውክሌር ይዞታዎች፣ ከጥቃቱ ቀድሞ ክምችታቸው እንዲዛወር መደረጉን ተናግረዋል።
(ቢቢሲ)

በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ የተባሉ 3 የጦር መሪዎች የኢራን የድል በዓል ላይ ተገኙ
በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ የተባሉ 3 የኢራን ጦር መሪዎች የኢራን የድል በዓልን ከሕዝብ ጋር ሲያከብሩ መታየታቸውን አናዶሉ እና የኢራን የሀገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
እስራኤል ከሰኔ 13 ጀምሮ የኢራን የጦር ጀኔራሎችን መግደሏን ያስታወቀች ሲሆን፤ ሦስቱ የኢራን የጦር መሪዎች በትናንትናው ዕለት ኢራን የድል በዓሏን ስታከብር ከህዝቡ ጋር በመገኘት አክብረዋል ብለዋል ምንጮቹ።
ከዚህ ውስጥ አንዱ የሆኑት የእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፕስ ቁድስ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ኢስማኢል ቃኣኒ በዓሉን ከሕብ ጋር ማክበራቸውን የኢራቅ የሀገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
በኢራን ታስኒም የዜና አገልግሎት የተለጠፈ ቪዲዮ ቃአኒ በዝግጅቱ ላይ ከተሰበሰቡት መካከል አሳይቷል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ቃአኒ በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት የኢራን ጦር መሪዎች መካከል አንዱ እንደሆኑ ዘግቦ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በተመሳሳይ የወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር እና የአየር ኃይል አዛዥ የነበሩ ብርጋዴር ጄኔራል አዚዝ ናስርዛዴህ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በመከላከያ ሚኒስቴር ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ተገድለዋል ተብለው የነበረ ቢሆንም በሕይወት እንዳሉ እና አሁንም በስልጣን ላይ እንደሚገኙ ተስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።
የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ከፍተኛ አማካሪ እና የደህንነት ዋና አማካሪ አድሚራል አሊ ሻምካኒ እ.ኤ.አ ሰኔ 13 ቀን 2025 በእስራኤል የአየር ጥቃት መሞታቸው ከተነገሩት አንዱ የነበሩ ናቸው። አድሚራል አሊ ሻምካኒ በድል በዓሉ ላይ በመገኘት የድል በዓሉን አክብረዋል ሲሉ የኢራን የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።

ኢራን ጦርነቱን እንድታቆም ከአሜሪካ የ30 ቢሊየን ዶላር ጉርሻ ቀርቦላታል ተባለ
ኢራን ጦርነቱን እንድታቆም እና ወደ ድርድር እንድትመጣ አሜሪካ የ30 ቢሊዮን ዶላር ጉርሻ እና ማዕቀብ እንዲነሳላት ማድረጓን ሲኤን ኤን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዘገባው እንደሚለው አሜሪካ ቴህራንን ወደ ድርድር ጠረጴዛው ለመመለስ የተጠናከረ ሙከራ አድርጋለች።
ላለፉት ሁለት ሳምንታት በኢራን እና በእስራኤል ወታደራዊ ጥቃቶች እየተበራከቱ ባለበት ወቅት እንኳን ከመጋረጃው ጀርባ ከኢራናውያን ጋር መነጋገራቸውን ምንጮች ነግረውኛል ሲል ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል።
የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ እነዚያ ውይይቶች በዚህ ሳምንት ቀጥለዋል ብለዋል።
ኢራን ወደ ድርድር ብትመለስም ዩራኒየም ማበልፀግ ላይ የማይወላውል አቋም አሳይታለች ብሏል ዘገባው።
ለኢራን የቀረበው የ30 ቢሊዮን ዶላር ጉርሻ ለሲቪል የኒውክሌር መርሃ ግብር አገልግሎት የሚውል መሆኑን የትራምፕ አስተዳደር ባለስልጣናት እና ሃሳቡን የሚያውቁ ምንጮች ለሲ.ኤን.ኤን ተናግረዋል ብሏል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የጃምቦ ሪል እስቴት ብራንድ አምባሳደር በመሆን ለሦስት ዓመት በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ትላንት ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ከድርጅቱ ጋር ተፈራርሟል፡፡
የጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ሰይፉ በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው ዓመታዊ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጃምቦ ሪል ስቴትን ወክሎ በመሳተፍ የመጀመሪያውን የስራ እንቅስቃሴው እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡
ጃምቦ ሪል አስቴት በቅርቡ በተከበረው የጋዜጠኛው የ60ኛ ዓመት ልደት በዓል ላይ፣ ባለ ሦስት መኝታ ክፍል የመኖሪያ ቤት ስጦታ እንዳበረከተለት ይታወሳል፡፡ አንጋፋው ጋዜጠኛ በዕለቱ ከመኖሪያ ቤት በተጨማሪ የመኪና ስጦታ ከታሜሶል እንዲሁም መጠኑ ያልተገለጸ ገንዘብ ከወዳጆቹ እንደተበረከተለት ይታወቃል፡፡
በግራንድ ሃይሌ ሆቴል በተካሄደው የልደት በዓል ላይ ጋዜጠኛው ለጃምቦ ሪል ስቴት በብራንድ አምባሳደርነት መመረጡ መጠቀሱን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ የትላንትናው ሥነስርዓት ያስፈለገው ስምምነቱን ለህዝብ ይፋ ለማድረግና ለመፈራረም መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ጃምቦ ለምን ጋዜጠኛ ደረጄን በአምባሳደርነት እንደመረጠው ሲያብራሩም፤ "የመረጥነው በብዙ መስፈርቶች ነው፤ ጃምቦ ካለው ዓላማና እንቅስቃሴ ጋር ተመሳሳይና ትክክለኛ ዓላማ ያለው በመሆኑ ነው፤ ደሞም ምርጫችን ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠናል" ብለዋል።
"ደረጀ ለሥራው ያለው ፍቅር፣ ቁርጠኝነትና ሙያዊ ታማኝነት የድርጅታችን አምባሳደር እንዲሆን ለመምረጥ አስችሎናል" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ያለው ሰፊ ልምድ፣ እውቅናና ተቀባይነት ለጃምቦ ሪል ስቴት ብራንድ ግንባታና ለድርጅቱን ዕድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት እምነታቸውን ገልጸዋል።
እስከዛሬ ለጋዜጠኝነት ሙያና ለባለሙያዎቹ ትኩረት ሳይሰጣቸው መቆየቱን ያነሱት አቶ ደበበ ሰይፉ፤ "ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኛና የጋዜጠኝነት ሙያ ክብርና ዕውቅና በማግኘታቸው ትልቅ ኩራትና ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡፡
ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ በበኩሉ፣ በህይወት ዘመኑ ከጋዜጠኝነት ውጭ ሌላ ሥራ ሞክሮ እንደማያውቅና እንደማይችል ተናግሯል፡፡
"የምችለው ጋዜጠኝነትን ብቻ ነው። ጋዜጠኝነት አልከፈለኝም ብዬ አማርሬ ግን አላውቅም" ያለው ጋዜጠኛ ደረጄ ፤ ለተደረገለት ነገር ሁሉ ጃምቦ ሪል እስቴትን አመስግኗል።
ይህ በዚህ እንዳለ፣ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ በልደቱ ዕለት ቃል የተገባለትን BYD E2 መኪና በዛሬው ዕለት ከታሜሶል ኮሙኒኬሽንስ ተረክቧል፡፡ የመኪና ስጦታው 3.4 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ ታውቋል፡፡
ጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕ ከ29 ዓመታት በፊት በወንድማማቾቹ አቶ ደበበ ሰይፉና አቶ ወንድይራድ ሰይፉ አማካኝነት "ጃምቦ ኮንስትራክሽን" በሚል ስያሜ እንደተቋቋመ ይታወቃል። ድርጅቱ ከዚያ ጊዜ አንስቶ በግንባታ ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ በማካበትና በርካታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ገበያ ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ ሆኖ ዘልቋል፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ ታንዛኒያ 50 ሜጋ ዋት ኃይል የማስተላለፍ የሙከራ ሂደት በስኬት መከናወኑ ተገለፀ
የኬንያ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ሱስዋ-ኢሲንያ ማስተላለፊያ መስመር ከ225 ሜጋ ዋት እስከ 262 ሜጋ ዋት ማስተላለፉን የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ጆን ማትቪዮ ተናግረዋል፡፡
የማስተላለፊያ መሠረተ ልማት ግንባታው በኬንያ ግምጃ ቤት፣ በዓለም ባንክ፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለታል።
ከኢትዮጵያ ወደ ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተላለፍ የሚያስችል የሶስትዮሽ ስምምነት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ ባለፈው ጥር ወር መፈራረማቸው ይታወሳል።

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የትምህርት ቤት ፈተና ሲወስዱ የነበሩ 29 ህጻናት በአካባቢው በደረሰ ፍንዳታ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የአከባቢው ሆስፒታል ዳይሬክተር ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ፍንዳታው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማጠናቀቂያ ፈተና እየወሰዱ በሚገኙ ተማሪዎች ላይ የደረሰው በኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ላይ በገጠመው አዳጋ ነው።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፋውስቲን-አርቸንስ ቱዋዴራ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ተማሪዎችን ለማስታወስ ብሄራዊ የሐዘን ቀን ያወጁ ሲሆን፤ በአደጋው የቆሰሉት ከ280 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በሆስፒታል ነፃ ህክምና እንዲያገኙ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
አደጋው የደረሰው ከዋና ከተማው ከሚገኙ አምስት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች የባካሎሬት የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ለመውሰድ በተሰበሰቡበት አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።
የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ ፍንዳታው የተፈጠረው በዋናው ህንጻ ወለል ላይ በሚገኘው የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ላይ ጥገና ሲደረግለት የነበረው ኃይል ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ በመደረጉ ነው ብሏል።
የትምህርት ሚንስትሩ ኦሬሊን ሲምፕሊስ ኮንግቤሌት ዚምጋስ፤ በአደጋው ልጆቻቸውን ላጡ ወላጆች ሀዘናቸውን ገልፀው ተጨማሪ ፈተናዎች መቋረጣቸውን አስታውቋል።