Telegram Web Link
ኢትዮጵያ ድሮን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ገንብቻለሁ አለች!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) የሚያመርተውን የስካይ ዊን ኢንዱስትሪን መርቀው በከፈቱበት እንዳስታወቁት ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ ያሳድጋል ፡፡

ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ የሚያሳድጉ ናቸው ተብሏል፡፡ድሮኖቹ በከፍተኛ መልካዓ-ምድር ላይ በብቃት አገልግሎት የሚሰጡና ጸረ-ድሮን ጭምር የታጠቁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ኢንዱስትሪው ድሮኖችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም አለው ብለዋል ፡፡
👏1😁1
የሪፖርተር መረጃ የተሳሳተ ነው:-ተቋሙ
ምንም አይነት  አዲስ ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም

ከሚያዝያ ወር ጀምሮ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሆነ ተደርጎ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው።

ተቋሙ ከመስከረም  2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ4 ተከታታይ አመታት  በማኅበረሰቡ ላይ ጫና እንዳይፈጠር በየሩብ አመቱ ተከፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የታሪፍ ማስተካከያ  ከማስፈፀም ውጪ አዲስ ተግባራዊ ያደረገው የታሪፍ ማሻሻያ አለመኖሩን እንገልፃለን ብሏል።
👍1
የአፋር ክልል መንግስት የባቡር ፕሮጀክት ስርቆት ላይ ተሳትፈዋል ያላቸዉን ኃላፊዎች ከስራ አሰናበተ

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ላይ የተፈፀመውን የስርቆት ወንጀል በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታዉቋል።

ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25.7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር መዘረፉ የክልሉን መንግስት አሳዝኗል ብሏል።

በዚህ ክስተት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የወረዳ የስራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለወይን ብርሃነአሰፋ እንዳሉት፣ በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት በገቢረሱ ዞን በተፈፀመው ስርቆት ከ717 ሺህ ዶላር በላይ እና ከ25.3 ሚሊየን ብር በላይ ኪሳራ ተመዝግቧል።

የኤሌክትሪክ ኃይሉ የሰሜን ምስራቅ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው ሪጅኑ ሶስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ከ436 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የማስተላለፊያ መስመሮችን እንደሚያስተዳድር ገልፀዋል።

ተቋሙ ለህብረተሰቡ ኤሌክትሪክ ለማዳረስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችና የኮንዳክተር ሽቦ ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል ማነቆ እንደሆነ አስረድተዋል።

የዞንና የወረዳ እንዲሁም  የፀጥታ ዘርፍ አካላት በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ አለመቻላቸው በኃይል መሰረተ ልማቶቹ ላይ ከፍተኛ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈፀም በር ከፍቷል ተብሏል።

Capital Newspaper
መጋቢት 2/2017 ዓ፣ም ዐበይት ዜናዎች

1፤ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪው ፈንታው ከበደ ታጣቂዎች በፈጸሙባቸው ጥቃት እንደተገደሉ ዛሬ ከቀትር በኋላ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ከዋና አስተዳዳሪው በተጨማሪ የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊና ተወካይ የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አዲስዘመን ፍሰሃ እና የወረዳው ሹፌር ከበደ እንድሪስ ጭምር በጥቃቱ እንደተገደሉ የወረዳው አስተዳደር ገልጧል። የአስተዳደርና የፖሊስ ሃላፊዎቹ የተገደሉት፣ ለመስክ ሥራ በወጡበት ታጣቂዎቹ በፈጸሙባቸው የደፈጣ ጥቃት እንደኾነ የወረዳው አስተዳደር መረጃ ያመለክታል።

2፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሦስት የጸጥታ ኃይል አዛዦች ላይ የተላለፈው እገዳ ቢሮው የአንድ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ መኾኑን በተግባር አሳይቷል በማለት አውግዟል። ቢሮውን በመወከል መግለጫ ያወጡ አካላት አስቸኳይ እርምት ካልወሰዱ፣ ለሚመጣው ችግር ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው በማለት አስጠንቅቋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ የጀኔራሎቹ እገዳ ተቋማዊ አሠራርንና ሕግን ያልተከተለ ነው በማለት ቢሮው ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው። ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍም፣፣ እገዳው ሕገወጥና የክልሉን የጸጥታ ኃይል ለማፍረስ የሚካሄደው ሴራ አካል ነው በማለት ኮንኖታል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ የጸጥታ ኃይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ አልቻሉም በማለት የጸጥታ ኃይል አዛዦች የኾኑትን ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወልደጊዮርጊሰን፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነን እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ኃይለን ትናንት በጊዜያዊነት ማገዳቸው ይታወሳል።

3፤ በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የሕወሓት ክንፍ፣ በራሱ ሥልጣን ለአዲግራት ከተማ አስተዳደር ከንቲባነት የሾማቸው ረዳኢ ገብረ እግዚያብሄር ዛሬ ሥራ መጀመራቸውን አስታውቋል። የደብረጺዮን ክንፍ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች አንዳንድ አዛዦች በመታገዝ፣ በደቡባዊ፣ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቃዊ ዞኖች እንዲኹም በመቀሌ ከተማ የአካባቢ አስተዳደሮችን በኃይል ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረገ ነው በማለት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰሞኑን ክስ አሠምቶ እንደነበር አይዘነጋም።

4፤ ኢዜማ፣ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጉዳይ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ዜጎች "በውድም ኾነ በግድ" ለገዥው ፓርቲ ማጠናከሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ እየተደረጉ ይገኛሉ በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ ዜጎች የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት በሚሄዱባቸው መንግሥታዊ ተቋማት ለፓርቲ ማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ የመጠየቅ ወይም የማስገደድ ተግባር በፍጹም ሕገወጥ ተግባር ነው በማለት አውግዟል፡፡ በዚህ መልኩ መዋጮ ማሰባሰብ "የሕግም ኾነ የሞራል መሠረት" የለውም ያለው ኢዜማ፣ ድርጊቱ የገዥው ፓርቲ "የማናለብኝነት ስሜት" ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ማሳያ ይኾናል ብሏል፡፡ "በጠራራ ጸሐይ በፓርቲ መዋጮ ስም የሚፈጸም ዝርፊያ በቸልታ እንደማይታለፍና ገዥው ፓርቲ በዚህ አካሄዱ ከቀጠለ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ እንደሚኾን ኢዜማ ጠቅሷል። ምርጫ ቦርድ፣ ይህን ጉዳይ በማጣራት በአስቸኳይ እንዲያስቆመውና በፓርቲው ላይ የወሰደውን የእርምት እርምጃ ለሕዝብ በግልጽ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

5፤ ሴሌክታ ዋን የተባለ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በአበባና የፍራፍሬ ልማት ኢንቨስትመንት ተሠማርቶ የነበረው የጀርመን ኩባንያ ከክልሉ ጠቅልሎ በመውጣት ኢንቨስትመንቱን ወደ ኬንያ እና ኡጋንዳ ማዛወሩን በድረገጹ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ኩባንያው ከክልሉ ለመውጣት በምክንያትነት የጠቀሰው፣ በክልሉ ያለውን ያልተረጋጋ ፖለቲካዊ ኹኔታና ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲኹም የሠራተኞቹ ደኅንነት ሊጠበቅበት የሚችልበት ዋስትና ማግኘት አለመቻሉን ነው። ኩባንያው፣ በክልሉ በተሠማራበት ኢንቨስትመንት ባለፉት ኹለት ዓመታት ዋና ዋና የሎጂስቲክስ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ችግሮቹ በዘላቂነት ሊፈቱ ሳይችሉ እንደቀሩ ገልጧል። በዞኑ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ቁንዝላ ከሚገኘው የአበባና ፍራፍሬ ልማት ኢንቨስትመንቱን ጠቅልሎ የወጣው ኩባንያው፣ ኬንያና ኡጋንዳ ውስጥ ተመሳሳይ ምርቶችን ማምረት ጀምሬያለኹ ብሏል።

6፤ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ሰሞኑን የኦርቶዶክስና እስልምና ሃይማኖቶችን የአብሮነት እሴት በሚያንቋሽሽ መልኩ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚለቀቁ አንዳንድ አስተያየቶች እንዳሳዘኑት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ጉባኤው፣ በሃይማኖት ሽፋን አብሮነትን ሊሸረሽሩ የሚችሉና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ አካላትን በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጧል። በኹለቱ ሃይማኖቶች ላይ ክብረነክ መልዕክቶችን የሚያሠራጩ ግለሰቦች ሕገወጥነትን ከማስፋፋት እንዲታቀቡ የጠየቀው ጉባኤው፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትም አፋጣኝ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።

7፤ ኡጋንዳ፣ ለፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር መንግሥት ጥበቃ ለማድረግ ቁጥራቸው ያልተገለጡ ወታደሮቿን በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ አሰማርታለች። ኡጋንዳ ወታደሮቿን ያሠማራችው፣ በኋይት ናይል ግዛት የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትና የተቃዋሚው መሪ ሬክ ማቻር ታማኝ ናቸው የተባሉ አማጺ ኃይሎች በመንግሥት የጦር ሠፈር ላይ ጥቃት በሰነዘሩ ማግስት ነው። ኡጋንዳ፣ በደቡብ ሱዳን በኹለቱ ወገኖች መካከል ከዓመታት በፊት በተካሄደ የእርስበርስ ጦርነት ከሳልቫ ኪር ጋር ወግና ወታደሮቿን በጁባ ማሠማራቷ አይዘነጋም። [ዋዜማ]
በሟች ወ/ሪት ቀነኒ አዱኛ ዋቆ አሟሟት ዙሪያ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰንሻይን ቤቶች ፊት ለፊት ከሚገኘው ውዳሴ ህንፃ ላይ ነዋሪ የነበረችው ሟች ወ/ሮ ቀነኒ አዱኛ ዋቆ መጋቢት 01 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃው ከደረሰው በኋላ የምርመራ ቡድን በማዋቀርና ቦታው ድረስ በመሄድ ተገቢውን የቴክኒክና የታክቲክ መረጃዎችን ያሰባሰበ ሲሆን የሟችንም አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለተጨማሪ ምርመራ እንዲሄድ አድርጓል፡፡

ሟች ወ/ሮ ቀነኒ አዱኛ በወቅቱ ከበረዳ ላይ በወደቀችበት ሰዓት ፖሊስ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለም ጎሳን በቁጥጥር ስር በማዋልም ምርመራ እያጣራ ሲሆን በቀጣይ የመጨረሻውን የምርመራ ውጤትም ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ እያስታወቀ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ከፖሊስ የወንጀል ምርመራ ውጤት በፊት የሚናፈሱ መረጃዎች ተገቢነት የሌላቸው ከመሆኑም ባሻገር በምርምራ ሒደቱ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅህኖ በመገንዘብ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ እና የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን "ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክ" ሕገ-ወጥ ነዉ ሲል አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን "ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክ" በሚል ስም የሚንቀሳቀስ አካል ያለ ምንም ህጋዊ ፈቃድ የኢንቨስትመንት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ ይህ አካል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ነኝ ብሎ ድረ-ገጽ ከፍቶ ማስተዋወቁን ገልጿል።

ባለስልጣኑ ባወጣው መግለጫ መሰረት ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክ በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016 መሰረት ፈቃድ ሳያገኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው። በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የካፒታል ገበያ አገልግሎት እንዲሰጥ ያልተፈቀደለት አካል መሆኑን አሳስቧል።

በተጨማሪም ባለስልጣኑ የካፒታል ገበያ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡና ፈቃድ ያላቸው አካላት ብቻ መሆናቸውን አስገንዝቧል። ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከዚህ አካል ወይም ከሌሎች ፈቃድ ከሌላቸው "የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች" ጋር ማንኛውም አይነት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አሳስቧል።

Capital
"የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ እልቂት ሲገባ ዝም ብሎ ሊመለከት አይገባም" ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ

👉 አስተዳደሩ ፌደራል መንግስት አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርግም ጠይቋል


የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ዛሬ ረፋድ መግለጫ አውጥቷል። አስተዳደሩ የትግራይ ጦር አዛዦች ከተልኮ ወጭ የአንድ ጠባብ ቡድን የስልጣን ጥም ለማርካት በማለት ግልፅ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ቆይተዋል ያለ ሲሆን በዚህ ሳምንትም በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ግንባር አዛዦች እንቅስቃሴው በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።

አስተዳደሩ በመግለጫው ይህንን አደገኛ እንቅስቃሴ እንዲያስቆም ለአጠቃላይ ጦር አዛዡ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ትእዛዝ ቢሰጥም የጥፋት ድርጊቱ ማስቆም እንዳልቻለ አስታውቋል።

የጥፋት ድርጊቶቹ ተባብሰው በቀጠሉበት በአሁኑ ሰዓት በስቪሎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑንና ከላይ እስከታች ያለውን የመንግስት መዋቅር የማፍረስ እንቅስቃሴዎች ቀጥለዋል ማለቱንም ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው የትግራይ ጦር የበላይ አዛዦች የኃላ ቀሩን ቡዱን ፍላጎት ለማሟላት ሲሉ መንግስት እንዲፈርስ እንዲሁም የፕሪቶርያ ስምምነት በይፋ እንዲጣስ በማድረግ የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነት እያስገቡት ነውም ብሏል።

አስተዳደሩ በመጨረሻም " የፌደራል መንግስት በትግራይ የፀጥታ ሀይል ስም የሚንቀሳቀሱት አዛዦች የአንድ ኃላቀርና ወንጀለኛ ቡዱን ተላላኪዎች እንጂ የትግራይ ህዝብና ጊዝያዊ አስተዳደሩን እንደማይወክሉ በመረዳት አስፈላጊ እርዳት ማድረግ አለበት" ብሏል። ከዚህ ባሻገር የፕሪቶርያ ስምምነት እንዲ በይፋ ሲፈርስና የትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ እልቂት ሲገባ ዝም ብሎ ሊመለከት አይገባም ሲል የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ዛሬ ረፋድ ባወጣው መግለጫ አስታዉቋል።

#ዳጉ_ጆርናል
👍2
" ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው ' የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም ' በሚል ነው " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ጠዋት ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ድረስ ባላው ጊዜ ውስጥ ነው።

ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው ' የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም ' በሚል ምክንያት ነው።

አቶ ሽፈራው ረጋሳ የተባለ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ ግለሰቧን እና ከግለሰቧ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው በሚል የጠረጠረውን ሌላ ባልደረባውን በመግደል ራሱን አጥፍቷል።

ግለሰቡ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበላት ወይዘሪት ሃና ተስፋዬ የተባለች 32 ዓመት ወጣት እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለ የሥራ ባልደረቦቹን ነው በጥይት ተኩሶ የገደለው።

ወንጀሉን የፈፀመው የጥበቃ ሠራተኛ ካልተራው ሌላ ሠራተኛን ተክቶ በመግባት እና ከምሽት የጥበቃ ሠራተኞች የጦር መሳሪያ በመቀበል ነው ግድያውን የፈጸመው።

ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ወደ ዕለታዊ ሥራቸው እስኪገቡ ድረስ በመጠበቅ ነው።

መጀመሪያ አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለውን ግለሰብ በሁለት ጥይት መትቶ ገድሏል።

ባልደረባውን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ሌላኛዋን የጥቃቱ ሰለባን ከመግደሉ በፊት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቁን ነገር ግን ፈቃደኛ አልነበረም።

ግለሰቡ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ እና እጁን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፣ በዚህ መካከልም ወደ ባንኩ አንደኛ ፎቅ በማምራት የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበለችም ያላትን በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት መትቶ ገድሏል።

በሁለቱ ግድያዎች መካከል እስከ 15 ደቂቃ የሚሆን የጊዜ ክፍተት ነበር።

ግለሰቡ ሁለቱን ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ በያዘው መሳሪያ የእራሱንም ሕይወት አጥፍቷል።

በክስተቱ በአጠቃላይ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።

ሁለቱ ሟቾች ወ/ሪት ሃና ተስፋዬ እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁም ፎቶግራፎች ተገኝተዋል። ፖሊስ በምርመራው ስለግንኙነታቸው ያጣራል።

ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ሂደት ይቀጥላል። "

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

#tikvahethiopia
👍2
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ወቅታው ሁኔታ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ

የፌድራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ያቀረብነው ህጋዊ ጥያቄ የለም፣
ጊዜዊ አስተዳደሩ በፌድራል መንግስትና በህውሃት መካከል በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የተቋቋመ ነው፣
የፌድራል መንግስቱ በራሱ ፍቃድ የተቋቋመውን መንግስት አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ አደጋውን የመቀልበስ ግዴታ ይኖርበታል፣
አሁን ባለው የትግራይ ሁኔታ ተስብስቦ ጥያቄ ሊያቀርብ የሚችል ምክር ቤት የለም፣
በአሁኑ ሰዓት ትግራይ ውስጥ እየተፈጠረ ያለው ቀውስ የህግ ተቀባይነትን ያጣ አንድ የህውሃት አንጃ ደጋፊ የሚላቸውን የተወሰኑ ከፍተኛ መኮንኖች በመያዝ እየሰራ ነው፣
ሂደቱን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረጉ እንቅስቃሴ ውስጥ ጊዜዊ አስተዳደሩ ውስጡ ያለውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችለው እድልን እየተነፈገ መቷል፡፡

የፌድራል መንግስት አግባብነት ያለው እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ስንል ጦር አዝምቶ ጦርነት ይቀስቅስ እያልን አይደለም፡፡
የፌድራል መንግስት ወደ ጦርነት ለማስኬት   የሚያዣብብ ሂደትን  ለማስቆም የሚያስችል ሁሉንም አይነት እርምጃ መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን፡፡

እኔ እንደ ጊዜዊ አስተዳደሩ ዋናወቅ ራስ ምታቴ በአንድም በሌላም መንገድ ትግራይ ውስጥ ሌላ ጦርነት ተከፍቶ ህዝባችን ወደ መከራ የሚገባበትን ሁኔታ ማስቀረት እንጂ እንግጠም ብሎ መሟገት አይደለም፡፡

እንግጠም ያለ ያለን ኃይል አደብ ለማስገዛት ለፌድራል መንግስቱ የኔ ግብዣ ያስፈልገዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ምክንያቱም ጉዜዊ አስተዳደሩ የፌድራል መንግስት ውሳኔ አካል ነው፡፡

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት አንድ ሰራዊት ነው በክልሉ መኖር ያለበት፡፡ነገር ግን እጅግ ግዙፍ የሠራዊት አቅም በትግራይ ክልል ውስጥ አለ፡፡

የሰራዊት አቅሙ በሙሉ አይደለም አሁን ወደ ጥፋት እንቅስቃሴ ውስጥ የገባው በተወሰነ ደረጃ ጉባኤ አድርጌለው ከሚለው ቡድን ጋር የጥቅም ቁርኝት አለን የሚሉ የተወሰኑ ኃይል የመረበሽ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል፡፡

ፌድራል መንግስት በቂ የሚለውን ድጋፍ መስጠት አለበት የሚል እምነት አለን፡፡
የፌድራል ምንግስት በትግራይ ክልል ያሉ የመከላከያ ካምፖችን ለመረከብ የኔ ጥሪ አያስፈልገውም ፡፡
በገበያተኞች ላይ የወደቀ ዛፍ የ 7 ሰዎች ህይወት ቀጠፈ።

በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፌዴ ከተማ በሀሙስ ገበያ መሐል የነበረ ትልቅ ዛፍ በገበያተኛ ላይ ወድቆ የ 7 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በ8 ሰዎች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋ የደረሰባቸው ወገኖች በቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገዱ ወገኖችም ወደ ጅማ ሪፈር ተደርገዋል ሲል የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ፎቶ: ማኅበራዊ ሚዲያ
👍1
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ለ "ሶስት ተጨማሪ ኩባንያዎች" የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ፈቃድ ሰጠ

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ለማሳደግና የሎጅስቲክስ ዘርፉን ለማጠናከር በማለም ለሶስት ተጨማሪ ኩባንያዎች የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የስራ ፈቃድ ሰጠ።

ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች ኢትዮ ሬል ሎጅስቲክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር እና ገልፍ ኢንጎት ኤፍ ዜድ ሲ ኢንደስትሪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው።

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ እንደገለጹት (ዶ/ር) ፣ ተጨማሪ ኩባንያዎች ወደ ዘርፉ መግባታቸው በገበያው ውስጥ ፉክክርን በማነቃቃትና በትብብር በመስራት የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ለማሳደግ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ በበኩላቸው፣ የመልቲ ሞዳል አገልግሎት ወጪን በመቀነስ እና የገቢ ዕቃዎች ደህንነትን በመጠበቅ በፍጥነት ወደ ተፈለገው ቦታ እንዲደርሱ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ፣ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ዘርፉን የተቀላቀሉ ኦፕሬተሮች ቁጥር ወደ ሰባት አድጓል። በቅርቡ ዘርፉን የተቀላቀሉት ኦፕሬተሮች ፓናፍሪክ ግሎባል፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት እና ኮስሞስ መልቲ ሞዳል ኦፕሬሽን የተሰኙ ኩባንያዎች መሆናቸዉ ይታወቃል።

Capital
ሲዳማ ክልል ለውጥ ያስፈልገዋል በማለት የተቃወመች አርቲስት ኢትዮጵያ በቀለች ታሰረች።

ያለፉትን ሁለት ሳምንት ከአርቲስት #ቶኪቻው ጋር በመሆን የሲዳማ ህዝብ ለውጥ ይሻል በማለት ንቅናቄ በማድረግ የምትታወቀው አርቲስት #ኢትዮጵያ በቀለች ትላንት መጋቢት 5 በቁጥጥር ስር ውላለች።

ባለስልጣናት፣ ባለሃብቶች እንዲሁም የሀገር  ሽማግሌዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት በወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቧ መጋቢት 5 በህግ ቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን የሲዳማ ክልል የፀጥታ ግብረሀይል ገልጿል።
2025/07/12 21:43:01
Back to Top
HTML Embed Code: