Telegram Web Link
ግብፅ ከደቡብ ኮሪያ 100 FA-50 የተሰኙ የጦር አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው።

በሴኡል የግብፅ አምባሳደር የሆኑት ካሊድ አብድራህማን ሀገሪቱ ከደቡብ ኮሪያ ለምትገጻው የጦር አውሮፕላን ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ግብፅ በመጀመሪያው ዙርም 36 የጦር አውሮፕላኖችን እንደምትረከብ ይጠበቃል።

FA-50 የተሰኘው የጦር አውሮፕላን በሰዓት እስከ 1800 ኪሎሜትሮችን መጓዝ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን ግዢው የግብፅን ወታደራዊ አቅም ለማሳደግ ታቅዶ እንደሆነ ተገልጿል።

Source: The Defense post
ሰርቢያ ከኬንያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች።

የሰርቢያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኬንያ ለኮሶቮ የሰጠችው የሃገር ዕውቅናን ተቃውሟል።

በ2008 ከሰርቢያ ነፃ የወጣችው ኮሶቮ አሜሪካን ጨምሮ በብዙ ሃገራት ዕውቅናን ያገኘች ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ በሃያላኑ ሩሲያ እና ቻይና ዕውቅናን አላገኘችም።

የሰርቢያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የዊሊያም ሩቶ መንግስት የግዛት አንድነትን የሚደግፈውን የተመድ ቻርተር ጥሰዋል ያለ ሲሆን ሰርቢያ ከኬንያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧንም አስታውቀዋል።

ሰርቢያ ጨምራም ኬንያ የአለም አቀፍን ህግ ጥሳለች ያለች ሲሆን ተገቢው የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ እርምጃም እወስዳለሁ ብላለች። በተጨማሪ የግዛት አንድነቷን ለመጠበቅ ማንኛውንም ነገር እንደምታደርግ አስታውቃለች።
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል የሚውል የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር ወይም የ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ተፈራርመዋል፡፡
👎1
ምክር ቤቱ ነገ የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም 22ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የፌደራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ፑቲን ከትራምፕ ጋር ለመነጋገር በራቸዉ ክፍት ነዉ አለ ክሬምሊን

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር በራቸዉ ክፍት ነዉ ሲል ክሬምሊን አስታወቀ።

ይህ የክሬምሊን ምላሽ የተሰማዉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲን «ተናድጃለሁ» ማለታቸዉን ተከትሎ ነዉ።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮፍ ዛሬ እንዳሉት፣ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ አቻቸው ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ዉይይታቸዉን ይቀጥላሉ፤ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስልክ ጥሪ ሊደረግ ይችላል፤ የፑቲን በር ለትራምፕ ክፍት ነዉ ብለዋል።

በሌላ በኩል የሩሲያ ከርሰ መድር ሀብት ድርጅት ኃላፊ ኪሪል ዲሚትሪየቭ፣ ሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ እምብዛም ባልተለመዱ የከርሰመድር ፕሮጀክቶች ላይ ሊደረግ ስለሚችለው ትብብር እየተወያዩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ ለሁለተኛው ሌሊት በተከታታይ በሰሜን ምሥራቅ ዩክሬን በምትገኘው በሃርከፍ ከተማ ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።
👍1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ከባንክ ፕሬዝደንቶች ጋር መወያየቱን ገለፀ።
የውይይቱን ውጤት፣ አሉ ያሏቸውን ብዥታዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከማስተካከል አንፃር የማእከላዊ ባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ያነሷቸው አበይት ነጥቦች
– በውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ረገድ በህብረተሰቡ በነጋዴ እንዲሁም ባንኮች ረገድ አልፎ አልፎ ብዥታ መኖሩን ባንኩ ተገንዝቧል።

–የባንኩ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ የለውጥ ትግበራ ከተጀመረበት ሀምሌ 2016 አንስቶ በ200 በመቶ ጨምሯል፤

–ይሄም በበጀት አመቱ መጨረሻ ይደረስበታል ተብሎ ከተቀመጠው እቅድ አንፃር ያለፈ ነው።

–ዛሬ ከባንክ መሪዎች ጋር በነበረው ውይይት በአፈፃፀም የሚታዩ ችግሮች እንዲታረሙ፣ የውጭ ምንዛሬ መመሪያ በጥብቅ እንዲተገበር  ብሄራዊ ባንክ አዟል።

–በተጨማሪ ባንኮች ለውጭ ምንዛሬ ግብይት የሚያስከፍሉት ኮሚሽን እና የአገልግሎት ክፍያ ተመጣጣኝ እንዲያደርጉ ታዘዋል።

–ብሄራዊ ባንኩ የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ቢያንስ እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ በየ 15 ቀኑ የውጭ ምንዛሬ ለባንኮች በጨረታ ይሸጣል።

–ባንኩ ቴክኖሎጂ እና አጋር ተቋማትን በመተቀም ጭምር በህገወጦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ገዥው የጠቀሱት

–በተለይ ከባንክ ውጭ ያሉ ሀዋላ የሚሰሩ፣ ገንዘብ ወደ ውጭ የሚያሸሹ እና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር/ላውንደሪ የሚያረጉ ላይ ነው ማስጠንቀቂያ የተሰጠው

–የሀዋላ ኩባንያዎችም የባንኩን ህግ አክብረው እንዲሰሩ ነው ማሳሰቢያ የተሰጠው

ወደዚህ እንዴት ተደረሰ

የብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገው ግምገማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስቦ ነበር። ከሳምንታት በፊት ባንኩ 60 ሚሊየን ዶላር ለባንኮች ለመሸጥ ባወጣው ጨረታ ለአንድ ዶላር በአማካኝ 135 ብር ከ62 ሳንቲም ቀርቦ ነበር።
ይሄም በባንኮች ከሚሸጥበት ዋጋ በ10 ብር ገደማ የጨመረ በመሆኑ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። (የኮሚቴውን ውሳኔ ተከተወሎ በጉዳዩ ላይ ባሳለፍነው ረቡዕ መጋቢት 17/March 26 ቀን በቅዳሜ ገበያ የሬድዮ ቆይታ ሰፋ ያለ ሃሳብ ያቀረብን በመሆኑ ከማህበራዊ ገፆቻችን ውይይቱን ማድመጥ ይቻላል)

–ባንኮች የግምታዊ ገብይት ውስጥ መግባት፣ የአገልግሎት ክፍያን የማናር፣ የውጭ ምንዛሬውን ሌላ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ እና ሌሎች መላ ምቶች ለምንዛሬ መጠን መናር በባለሞያዎች በምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው።

–በህገወጥ የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር ከ 150 ብር በላይ እንደሚመነዘር ነው ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች ለቅዳሜ ገበያ የገለፁት።
👍2
ብሄራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በአማካኝ አንድ ዶላር 131 ነጥብ 70 ብር ተሸጠ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።ባንኩ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር ማስታወቁን ተከትሎ፤ በዛሬው ዕለት 50 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ለባንኮች በጨረታ አቅርቧል፡፡

በዚህም ጨረታ ላይ 12 ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን መከፋፈል መቻላቸውን ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።በዚህም አማካኝ የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር 131 ነጥብ 7095 ብር ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል።

ባንኩ ከአንድ ወር በፊት 60 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፤ በአማካኝ 135 ነጥብ 6 ብር ለአንድ ዶላር መግዣ ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል።በዚህም ዛሬ በወጣው ጨረታ የቀረበው አማካኝ ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲስተያይ፤ የ3 በመቶ አካባቢ ቅናሽ ታይቶበታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መሰል ጨረታዎች ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት በየሁለት ሳምንቱ እንደሚካሄዱ ያስታወቀ ሲሆን፤ ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ግብን ማሳካት ነው ብሏል፡፡
👍1
#AddisAbaba

" የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው ማግኘት ይቻለል " - የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ከመጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ መፈቀዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ በመንጃ ፈቃዱ ላይ ወደ ተገለጸው እና ፋይሉ ወዳለበት ክፍለ ከተማ (የመታወቂያ አድራሻ) የሚገኝ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ቢሮ መሄድ ግድ ይል ነበር።

ከነገ በኃላ ግን በየትኛውም አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ መንጃ ፈቃድ ማሳደስ ይቻላል ተብሏል።

ተገልጋዮች በሚቀርባቸው ቅርንጫፍ ፋይላቸው ያለበት ቅርንጫፍ ሳይጠየቅ የጤና ምርመራ ሰርተፍኬትን በመያዝ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እንዲያገኙ መወሰኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።
👍1
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ አዲስ ምልክት አጸደቀ

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የሚሆን አዲስ የደረጃ ምልክት አጽድቋል።

ይህ ምልክት ከዉጪ የሚገቡና የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶች ከሀገር ውስጥ ምርቶች ለመለየት ያስችላል ተብሏል።

በገበያ ላይ ፍትሃዊ የሆነ ውድድር እንዲኖር እንደሚያደርግ እና ሸማቾች የውጭ ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው መምጣታቸውን እንዲያውቁ እንደሚረዳ ተገልጿል።

Capital Newspaper
Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ ጣሉ፤ ኢትዮጵያም 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባታል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ የታሪፍ እርምጃ ወሰዱ። ረቡዕ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ከ20 በላይ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ተዘግቧል ።
የክልል ጊዜያዊ አስተዳደሮች የቆይታ ጊዜ እስከ ሁለት ዓመት እንዲራዘም የሚያስችል አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሎች የሚቋቋም ጊዜያዊ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን፤ለሁለት ጊዜ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲራዘም የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያን አጸደቀ።

የአዋጁ ማሻሻያ፤ ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣን የነበረውን የክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቆይታ ጊዜን የማራዘም ኃላፊነት፤ለምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የሰጠ ነው።

አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚተካ ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ መጽደቁ ተገልጿል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ 23/2017 ዓ. ም. ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ የሥልጣን ዘመኑ የተጠናቀቀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ ዓመት እንዲራዘም የሚያስችል ነው።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጊዜያዊ አስተዳደር የተመሰረተው በ2015 ዓ. ም. የወጣውን ማቋቋሚያ ደንብ መሠረት አድርጎ ነው።

ጊዜያዊ አስተዳደሩን ያቋቋመው ደንብ ደግሞ መሠረት ያደረገው ከ22 ዓመት ገደማ በፊት የጸደቀውን የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግግ አዋጅ ነው።
ይህ አዋጅ የፌደራል መንግሥት በሦስት ሁኔታዎች በክልሎች ውስጥ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ደንግጓል።

በቀዳሚነት የተጠቀሰው ምክንያት በክልሉ ውስጥ የሚፈጠር የጸጥታ መደፍረስ ሲሆን በዚህ ጊዜ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል።
በክልሉ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከተፈጸም እና የክልሉ መንግሥት ድርጊቱን በቁጥጥሩ ሥር ማዋል ካልቻለም ፌደራል መንግሥት ጣልቃ ይገባል።

በአዋጁ ላይ የተጠቀሰው ሦስተኛ ሁኔታ፤ እንደ "በትጥቅ የተደገፈ የአመጽ እንቅስቃሴ" ያሉ ድርጊቶች በሚፈጸሙበት ወቅት የሚከሰት "የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት አደጋ ላይ መውደቅ" ነው።

በእነዚህ ሁኔታዎች መከሰት ምክንያት ወደ በክልሎች ጣልቃ የሚገባው የፌደራል መንግሥት ሊያከናውን ከሚችላቸው ጉዳዮች መካከል "የክልሉን ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል በማገድ ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር" ማቋቋም የሚለው ይገኝበታል።
በዚህ መልኩ የሚቋቋም ጊዜያዊ አስተዳደር የሚቆየው ከሁለት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እንደሆነ አዋጁ ደንግጓል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጊዜያዊ አስተዳደሩን የቆይታ ጊዜ ማራዘም "አስፈላጊ ሆኖ" ካገኘው "ከስድስት ወር ላልበለጠ ጊዜ" ሊያራዝመው እንደሚችልም በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ያጸደቀው አዋጅ፤ በክልሎች ውስጥ የሚመሠረት የጊዜያዊ አስተዳደር የቆይታ ጊዜ ሁለት ጊዜ እንዲራዘም ያስችላል።

"በክልሉ ውስጥ የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ መግባት አስፈላጊ ካደረገው ሁኔታ ውስብስብነት አኳያ አስፈላጊ ሆኖ" ከተገኘ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ እስከ አንድ ዓመት እንዲራዘም ሊደረግ እንደሚችል በአዋጁ ላይ ተጠቅሷል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲራዘም የሚያስፈልግ ከሆነም በድጋሚ "ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እንዲራዘም" ሊደረግ እንደሚችል አዲስ በጸደቀው አዋጅ ላይ ተቀምጧል።

በሥራ ላይ ባለው አዋጅ በክልሎች ውስጥ የሚመሠረት ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ሥልጣን ፌዴሬሽንም ምክር ቤት እንደሆነ ደንግጓል።
አዲሱ ማሻሻያ ረቂቅ በበኩሉ ይህንን ሥልጣን ወደ ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አዘዋውሯል።

አዋጁ የጊዜያዊ አስተዳደርን ቆይታ ጊዜ የማራዘም ሥልጣንን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቢሰጥም፤ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ወቅት ውሳኔው ቀርቦ መጽደቅ እንዳለበት ይደነግጋል።
ምክር ቤት የሚቀርብለትን የቆይታ ጊዜ ማራዘም ውሳኔ ካልተቀበለው፤ "ውሳኔው ውድቅ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ ተደርጎ መደበኛ የክልል መንግሥት አስተዳደር መመሥረት" እንደሚኖርበት በአዋጁ ላይ ተካትቷል።
ጊዜያዊ አስተዳደር በተመለከተ በአፈ ጉባኤው በሚተላለፍ ወይም በምክር ቤቱ በሚጸድቅ ውሳኔ ውስጥ "ጊዜያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ሊመላከቱ" እንደሚችሉ አዋጁ ያስረዳል።

እነዚህ ጉዳዮች "ለፌደራል መንግሥት ጣልቃ መግባት ምክንያት የሆነውን ሁኔታ በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማጽናት አስፈላጊ የሆኑ" ተግባራት እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።
👍1
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
#ደቡብ_ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር (ዶር) በጁባ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፓርቲያቸው የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የረጅም ጊዜ ተፎካካሪ የሆኑት ማቻር "20 ከባድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች" በተሳተፉበት ኦፕሬሽን ከቤታቸው ተወስደዋል ሲል ፓርቲያቸው ኤስፒኤልኤም-አይኦ (SPLM-IO) አስታውቋል።

ፓርቲው የፀጥታ ኃላፊዎች "ኢ-ሕገመንግስታዊ ድርጊት" ፈጸመዋል ሲል ድርጊቱን አውግዟል። በተጨማሪም ሪክ ማቻር በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት "ግልፅ አለመሆኑንም" ገልጿል።

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ እስሩ ሀገሪቷን ወደ አዲስ ግጭት እንዳያስገባ አስጠንቅቋል። የድርጅቱ ኃላፊ ኒኮላስ ሃይሶም መሪዎቹ ወደ ሰፊ ግጭት መመለስን ለማስወገድ ራሳቸውን መቆጣጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው፤ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለኪር እና ለማቻር ታማኝ በሆኑ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል። የተፈጠረው ውጥረትም እያየለ ባለበት ወቅት #ኖርዌይ እና #ጀርመን ኤምባሲዎቻቸውን ለጊዜው ዘግተዋል።

ካለፈው ወር ጀምሮ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ከእላኛው ናይል አካባቢ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል ሲል የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።
👍1
የእስራኤል አምባሳደር ከሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ላይ በአፍሪካ ህብረት ተባረሩ

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት አብርሃም ንጉሴ፣ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተካሄደው 31ኛዉ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት እንዲወጡ ተደረገ።

ይህ የሆነው በርካታ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሩ በዚሁ የሐዘን ስነ-ስርዓት ላይ መገኘታቸውን በመቃወማቸው መሆኑ ተዘግቧል ።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦረን ማርሞርስቴይን ድርጊቱን "አሳፋሪ" እና "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ በጽኑ አውግዘዋል።

"በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል አምባሳደር በተጋበዙበት፣ በሩዋንዳ የቱትሲ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ፀረ-እስራኤላዊ የፖለቲካ አመለካከቶችን ማስተዋወቃቸው እጅግ አሳፋሪ ነው" ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ማርሞርስቴይን አክለውም፣ "ይህ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት በመጀመሪያ ደረጃ የተገደሉትን ትውስታ የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ የሩዋንዳ ህዝብን እና የአይሁድ ህዝብን ታሪክ መሠረታዊ ግንዛቤ ማጣቱን ያሳያል።"

የእስራኤል ሚዲያ የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሰዉ እንደዘገቡት ይህ ክስተት በአፍሪካ ህብረት ውስጥ የእስራኤልን አቋምና ከአባል ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ ያለውን ቀጣይ ውጥረት የሚያሳይ ነው ሲሉም አስፍረዋል።
👍2
ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ

በፍቅረኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ግድያ ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ታዋቂው የኦሮምኛ ቋንቋ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሲቀርብ ፖሊስ በተሰጡት ባለፉት 12 ቀናት አከናወንኩ ያላቸውን የምርመራ ስራዎች ለችሎት አቅርቧል፡፡

ፖሊስ በእነዚህ ቀናት ተጨማሪ የ15 ምስክሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ የ28 ሰዎች የምስክር ቃል ማሰባሰቡን ዛሬ አሳውቋል፡፡ ከመኖሪያ ቤታቸው በተወሰደ ምንጣፍ እና ናሙና ላይ ለፌዴራል ፖሊስ የተላከ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤትና በተጠርጣሪው ስልክ ላይ በብሔራዊ መረጃ ደህንነት በኩል የሚደረጉ የምርመራ ውጤቶች አሁንም ድረስ እንዳልደረሱለት ያሳወቀው ፖሊስ የሆስፒታሎች ማስረጃዎችን በእነዚህ ጊዜያት ማሰባሰብ ቢችልም የባለሙያ ትንተና እና የታክቲክና ቴክኒክ ምርመራዎች እንደሚቀሩት ገልጿል፡፡ በመሆኑም ተጨማሪ የሰውና ሰነድ ማስረጃዎችን ለማጠናከር የ14 ቀናት የምርመራ ቀናት እንደሚያስፈልገው መርማሪ ፖሊስ ችሎቱን ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል የተጠርጣሪው አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጠበቃ “ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜያትን እየጠየቀ ያለው ከዚህ በፊት ካቀረባቸው ምክንያቶች ተመሳሳይ ነው” በማለት “ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ መጠየቁን” በመቃወም ከዚህ በፊት ተገኘ የተባለው የሆስፒታል ምርመራ “ተጠርጣሪዋ ከከፍታ ቦታ ወድቃ ህይወቷ ማለፉ ከመገለጹ ውጪ በሰውነቷ ላይ የተገኘ የተቦጫጨረ ነገር አለመኖሩ እራሷን ለማጥፋቷ ማሳያ በመሆኑ የተጠርጣሪው የዋስትና መብት ሊጠበቅ ይገባል” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ጠበቃው “ከሟች የግል ማህደር መረዳት እንደተቻለው ከዚህ በፊት ከመጠን በላይ የመድኃኒት ዶዝ መውሰድን ጨምሮ እራሷን ለማጥፋት ብዙ ሞክራለች” በማለት ይህንኑ ለጓደኞቿ መግለጿን እና ህልፈቷም ከዚሁ ራስን ከማጥፋት ጋር ልያያዝ እንደምችል ለችሎት አብራርተዋል፡፡ ጠበቃው “አርቲስቱ ከእስር ወጥቶ ለፋሲካ በዓል የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ማቀዱን በመግለጽ” የችሎት ሂደቱን አዛብተው ያልተባለውን እንደተባለ አድርገው “ስም በማጥፋት ላይ ተሰማርተው ለሚዘግቡ” መገናኛ ብዙኃን ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

ችሎቱ በፖሊስ እና ጠበቃ በኩል የቀረቡትን ሃሳቦች መርምሮ ብይን ለመስጠት ለነገ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ጠዋት 3፡30 ቀጥሯል፡፡
👍4
#update

ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በይፋ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሆኑ

ሹመቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያጋሩት መልእክት ሙሉ ይዘት ከስር ተያይዟል።

ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነት እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል:: የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ግዝያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል::

ዛሬ በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩን እና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል። ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው:: ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው:: አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምነት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።
በትግራይ ክልል ከአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ዳኞች ጫና እየበረታባቸው ነው ሲል ማህበሩ አስታወቀ

በትግራይ ክልል ከአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ዳኞች እየደረሰባቸው ያለው ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫናዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፣ አሳሳቢ ሁነዋል ሲል የትግራይ የዳኞች ማህበር መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

“በአሁኑ ወቅት በተለይም ደግሞ ባለፉት ሁለት አመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በትግራይ በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር እና ግድያዎች ተበራክተዋል” ሰል ማህበሩ በመግለጫው ጠቁሟል።

“እነዚህን ወንጀሎች በፈጸሙ ተጠርጣሪዎች እና ከሳሾች ዙሪያ ያሉትን ጉዳዮች የሚሰሙ ዳኞች ከፍርድ ሂደቱ በኋላም ሆነ በፍርድ ሂደቱ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል” ሲል አሳስቧል፤ “ለደህንነታቸው በመስጋት አንሰራም ሊሉ ስለሚችሉ የሚመለከተው አካል ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ጋር ልዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ እንዲሰራ” ጠይቋል።  
👍1😁1
ቃል የተገቡባቸው ነጥቦች።

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያው አስተዳደር ፕሬዚደንት ሆነው ሲሾሙ በስልጣን ቆይታቸው ከላይ የተያያዙትን ነጥቦች ለማስፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አቶ ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በፊርማቸው ቃል ገብተዋል።
2025/07/09 23:31:45
Back to Top
HTML Embed Code: