በአሜሪካ ድምፅ ጣቢያ (VOA) ላይ ያነጣጠረዉ የትራምፕ አስተዳደር የቁጠባ ፖሊሲ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የዓርብ ዕለት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝን ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስገዳጅ እረፍት ላይ ይገኛሉ።
ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ ሁሉም የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስተዳደራዊ ፈቃድ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መልዕክት ደርሷቿዋል። ይሄው ለሠራተኞች የደረሰዉ ደብዳቤ "ሌላ የተለየ መመርያ እስከሚመጣ ድረስ ደሞዛቸው እየተከፈላቸው እንደሚቆይ ገልጾ፣ ማንኛውንም የተቋሙን ንብረቶች መጠቀም እንደማይችሉና፣ ስልክና ኮምፒዩተር የመሳሰሉ ንብረቶችንም በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ያዛል።
እንደ የአሜሪካ ድምጽ ዳይሬክተር ማይክል አብራሞዊትዝ ከሆነ በአጠቃላይ 1,300 የሚጠጉ ጋዜጠኞች ፣አዘጋጆች እና ረዳቶች ሰራተኞቻቸው አስገዳጅ ዕረፍት ላይ ይገኛሉ።

ፈረስ ታክሲ የመነሻ ዋጋን በ30 ብር ጨመረ
በከተማዋ በስፋት አገልግሎት የሚሰጠው ፈረስ ታክሲ የመነሻ ዋጋውን በ30 ብር መጨመሩ ተሰማ። ይህ ጭማሪ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሆነ ሲሆን፣ የመነሻ ዋጋው ከ100 ብር ወደ 130 ብር ከፍ ብሏል።
የፈረስ ታክሲ አሽከርካሪዎች ለዚህ የዋጋ ጭማሪ ምክንያቱ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።
አሽከርካሪዎቹ ለረጅም ጊዜ ለሚመለከታቸው አካላት የዋጋ ማሻሻያ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ በመቅረታቸው በርካታ አሽከርካሪዎች ወደ ሌሎች ተመሳሳይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች መሄዳቸው ተጠቁሟል።
Capital

👍2😁2
☄️ከምሽቱ 3 ሰአት ተኩል በፊት የንግድ ተቋምን መዝጋት 10 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 94 መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡
በደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ንግድ ቤቶች እና ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች እስከ ምሽት ሶስት ተኩል እና አራት ሰዓት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸዉ፡፡
በተጨማሪም በምሽት ክፍለ ጊዜ የመግቢያ በሩን ዝግ በማድረግ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ፤የንግድ ተቋሙ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የሚያሳይ በመብራት የሚሰራ ምልክት በግልጽ በሚታይ ቦታ ላይ ማስቀመጥ እንደሚኖርበት በደንቡ ላይ ሰፍሯል ፡፡
ይህን ደንብ በመተላለፍ የንግድ ተቋሙን ከ 3 ሰአት ተኩል በፊት የዘጋ ለአንድ ጊዜ የጥፋት መጠን የ 10 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል ፡፡
በተጨማሪም ከምሽቱ 4 ሰዓት በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ማቋረጥ፣ከስምሪት መውጣት አልያም የስምሪትን መስመር ማቆራረጥ 5 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ተገልጿል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ በላይ ተሳፋሪውን ማስከፈልም በተመሳሳይ የ 5ሺህ ብር ቅጣት እንዳለዉ ነዉ የሰማነዉ፡፡

ሕገወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ቅጣት የሚያስጥል አዋጅ ተግባራዊ ተደረገ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ያጸደቀው የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት አዋጅ ከመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
ይህ አዋጅ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እና የእስራት እርምጃዎችን ያስቀምጣል።
አዲሱ የነዳጅ ውጤቶቾ ግብይት አዋጅ 1363/2017 በተለይም በሕገወጥ የነዳጅ ግብይት ተዋናዮች ላይ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጥል ተገልጿል።
የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ያከማቸ ወይም ያለ አግባብ ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ሰው፣ የተያዘው ነዳጅ ተወርሶ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።
በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የነዳጅ ውጤቶችን ከመንግስት ከተመነው በላይ የሸጠ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያጠፋ ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር፣ በተደጋጋሚ ሲያጠፋ ደግሞ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።
ከዚህ በተጨማሪ የነዳጅ ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች ያለ ፈቃድ ነዳጅ ሲሸጥ የተገኘ ሰው፣ ነዳጁ ተወርሶ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ እንደሚቀጣ ነው ካፒታል ያገኘው መረጃ የሚያመለክተዉ።
ቀደም ሲል የነበረው አዋጅ 838/2006 በነዳጅ ውጤቶች ቁጥጥር ላይ ክፍተቶች እንደነበሩበት የተገለጸ ሲሆን አዲሱ አዋጅ እነዚህን ክፍተቶች ለመቅረፍ ያለመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ መጋቢት 11 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ነው ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡት።

የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና ክትትል ሊያገኝ መቻሉን አስታወቀ፡፡
ሪጅኑ በ196 ሺሕ ደንበኞች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል 13 በስማርት ቆጣሪዎች፣ 69 በቅድመ ነጠላና ባለሦስት ፌዝ ቆጣሪዎች እና በ29 የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ላይ ስርቆቱ መፈጸሙን ገልጿል፡፡
ዘመናዊ ቆጣሪዎች (ስማርት ) ላይ የተደረገው ስርቆት የታወቀው ቆጣሪዎቹ ወደ መረጃ ቋት በሚልኩት መረጃ መሆኑን የሸገር ሪጅን ኢነርጂ ማኔጅመንት ማናጀር አቶ ግርማ ወግበላ አስታውቀዋል፡፡
ማናጀሩ የኃይል ስርቆት በፈፀሙ ደንበኞች ላይ ከ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ እንዲከፍሉ በማድረግ ሊባክን የነበረ ከ17 ሚሊየን በላይ ኪዋት ሰዓት ከብክነት ታድገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የኃይል ስርቆት ሲፈጽሙ በተገኙ ደንበኞች ላይ ክስ የተመሰረተ መሆኑን አቶ ግርማ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኃይል ስርቆት መፈፀም በወንጀል የሚያስከስ ሲሆን እስከ አምስት ዓመት ድረስ በእስራት እንዲሁም እስከ 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ነው፡፡

75% የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት አላገኘም
75 በመቶ የሚሆኑ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በሙያ ብቃት በሌላቸው ሰዎች የሚዘጋጅ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል ።
ቢሮው ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት፣ በጥቅምት ወር በተካሄደው ቅድመ ኦዲት 25 በመቶ ያህሉ ነጋዴዎች ብቻ የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል።
የተቋሙ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ እንደገለጹት፣ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ በባንክ ሂሳባቸው ከሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ጋር የማይጣጣም ነው። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ላይ ቢታይም፣ በሂሳብ መዝገባቸው ላይ ምንም ትርፍ እንዳላገኙ ያሳያሉ።
አንዳንዶቹ ደግሞ ገንዘቡን በህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ወጪ አድርገው ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም የተባለ ሲሆን የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ፕሮፌሽናል ባልሆኑ ሰዎች እየተዘጋጀ ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑም ተገልጿል ።
Capital Newspaper

አል ዐይን አማርኛ ሥራ ሊያቆም መሆኑን ተገለፀ❗❗
ባለቤትነቱ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት የሆነው አል ዐይን አማርኛ የበይነ መረብ የዜና ማሠራጫ፤ ሥራ ሊያቆም መሆኑን ዋዜማ ዘግቧል፡፡
የዜና ማሠራጫው በአማርኛ ቋንቋ ዜናዎችንና ዘገባዎችን የሚያዘጋጁ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎቹን የቅጥር ውል ማቋረጡን ዘገባው አረጋግጧል፡፡
ዘጋቢዎቹ ሥራቸውን እየሠሩ ባሉበት ወቅት ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቂያ ሳይደርሳቸው፣ በድንገት የሥራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልዕክት በኢሜይል እንደደረሳቸው ተዘግቧል፡፡
ተቋሙ የሠራተኞቹን ውል ያቋረጠው፤ የአማርኛ ዜና አገልግሎቱን አቁሞ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ለመውጣት በማሰቡ መሆኑን የዜና ምንጩ ተረድቻለው በሏል፡፡
ዋዜማ

የዋልያዎቹ አሰላለፍ ታውቋል !
ሌሊት 6:00 ሰዓት ላይ ግብፅን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ አምስተኛ ጨዋታውን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ለጨዋታው በቋሚ 11 የሚሰለፉ ተጫዋቾች ቋሚ አሰላለፍ ታውቋል።
በዚህም መሰረት :-
ግብ ጠባቂ :- አቡበከር ኑራ
ተከላካዮች :- አማኑኤል ተርፉ ፣ ራምኬል ጄምስ ፣ ብርሀኑ በቀለ
አማካዮች :- ብሩክ ማርቆስ ፣ ያሬድ ካሳዬ ፣ አማኑኤል ዮሐንስ
አጥቂ :- አቡበከር ናስር ፣ ቸርነት ጉግሳ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ
በመሆን ወደ ሜዳ ይገባሉ።
መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን 🇪🇹

❤1
አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች “በሽብር ወንጀል” ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞችን፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌደራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮውን የጠየቀው፤ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ስራ “በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት” በሚል ነው። ከስምንቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ባለፈው ሳምንት እሁድ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ ዝግጅት ላይ “የሀሰት ታሪኳ” ቀርቧል የተባለው ብርቱካን ተመስገን ትገኝበታለች።
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የመገናኛ ብዙሃኑ አንዱ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ነብዩ ጥዑመልሳንም በተጠርጣሪነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በቴሌቭዥን ጣቢያው በፕሮግራም ዳይሬክተርነት የሚሰራው ጋዜጠኛ ታሪኩ ኃይሌ፣ የስቱዲዩ ዳይሬክተሩ አቶ ንጥር ደረጀ፣ ረዳት የፕሮግራም አዘጋጇ ህሊና ታረቀኝ እና የካሜራ ባለሙያ የሆነው ቶማስ ደመቀም ፍርድ ቤት ቀርበው የዛሬውን ሂደት ተከታትለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ዲሽ እና ዲኮደር መጠቀም ሳያስፈልግ የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚቻልበት ስርዓት ይፋ ተደረገ።
ኢትዮቴሌኮም እና መልቲቾይስ አፍሪካ የቴሌኮምን አገልግሎት ከመዝናኛ ጋር ያጣመረውን የ"ዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል"ን ይፋ አድርገዋል።የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል የኢትዮ ቴሌኮምን የፊክስድ ብሮድባንድና የሞባይል ኢንተርኔት ዳታ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከጠበቁት የዲኤስቲቪ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች ጋር በአንድ ያዋሃደ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ትብብሩ ኢትዮ ቴሌኮም የደረሰበትን ሁሉንም አይነት አገልግሎት ዲጂታላይዝ የማድረግ ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ገሊላ ገ/ሚካኤል ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ ያለው ፋይበር ኔትዎርክ የሚጠቀም ደንበኛ ከዲኤስቲቪ አገልግሎት በላቀ መልኩ የኦንላይን ትምህርት እንዲሁም ስራዎችን ጨምሮ ለደንበኞች ህይወትን ሊያቀሉ የሚችሉ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።
ዲኤስቲቪ እና ኢትዮቴሌኮም ለዚህ የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል ከመደበኛው አገልግሎታቸው ክፍያዎች በተለየ መልኩ ልዩ ቅናሽ ያደረጉበት ሲሆን ደንበኞች የስትሪሚንግ አገልግሎቱን በመመዝገብ ብቻ ዲሽና ዲኮደር ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ መጠቀም ያስችላቸዋል።ይህም ደንበኞች በፈለጉት ዓይነት ዲቫይስ ወይም በስልክ፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕና ቴሌቪዥን ቦታ እና ግዜ ሳይገድባቸው ከ70በላይ ይዘቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
Via Arts TV

👍3
Forwarded from Capitalethiopia
YouTube
Capital: የማዳበሪያ ግዢ ቅሬታ አስነሳ | መንግስት በእንድ ማዕከል አደረገ | የማር አምራቾች ተግዳሮት
ኢትዮጵያ የማር ምርት ለማሳደግ ጉዞ ላይ ብትገኝም የገበያ ተግዳሮቶች እንቅፋት ሆነዋል l የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዘርፍ የመረጃ እና የሰው ኃይል እጥረቶች ገጥመውታል l ኮርፕሬሽኑ ለማዳበሪያ ግዥ ጨረታ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ቅሬታ አስነሳ l ኢትዮጵያ የመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደርን ለማሻሻል ትሬዠሪ ነጠላ አካውንት (TSA) ተግባራዊ እያደረገች ነው
24 የተሽከርካሪ ዓመታዊ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ ርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ተቋማትን በመገምገም ነው የጎላ ክፍተት የተገኘባቸው 24 ተቋማት ላይ ርምጃ የወሰደው፡፡
በዚህ መሰረትም 2 የምርመራ ተቋማት ፈቃዳቸው የተሰረዘ ሲሆን÷ 4 ተቋማት ደግሞ ለሶስት ወራት ታግደው ክፍተታቸውን እንዲያርሙ ተወስኗል፡፡
በተጨማሪም 6 ተቋማት ለአንድ ወር ሥራ እንዲያቆሙ እንዲሁም 12 ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በቁርጠኝት እንደሚሰራም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ትራምፕ ኢራን በኒውክሌር ድርድር ካልተስማማች በቦምብ ድምጥማጧን አጠፋለሁ አሉ
በጉዳዩ ዙሪያ ስምምነት ላይ ካልደረሱ የቦምብ ጥቃት እፈጽማለሁ ጥቃቱም ከዚህ በፊት አይተውት የማያውቁት ይሆናል ብለዋል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ከዋሽንግተን ጋር ለመደራደር ካልተስማማች ታይቶ የማይታወቅ የቦምብ ጥቃት ይደርስባታል ብለዋል፤
ይህም በጥር ወር ስልጣን ከያዙ በኋላ ስለሚወስዱት ወታደራዊ እርምጃ በጣም ግልፅ የሆነ ማስጠንቀቂያ የሰጡበት ነዉ ተብሏል፡፡
ባለፈው እሁድ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ቴህራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን ቀጥተኛ ድርድር ውድቅ እንዳደረገች በመግለጽ፤ኢራን ቀጥተኛ ምላሽ የሚያስፈልገዉን ከዶናልድ ትራምፕ የመጣ ደብዳቤ ለጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔ መላኳን አስታዉቀዋል፡፡
ይሁን እንጂ በተዘዋዋሪ ድርድር የማካሄድ እድልን ግን ክፍት አድርገዋል።
ትራምፕ ኢራን በቀጥታ ንግግሮች ላይ እንድትሳተፍ ለወራት በይፋ ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ቴህራን የውሳኔ ሃሳቡን ውድቅ ካደረገች በጣም መጥፎ ምላሽ እንደሚከተላት ፍንጭ ሰጥተዉ ነበር፡፡
በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ፤የአለም ኃያላን እና ኢራን የጋራ አጠቃላይ የድርጊት መርሃ ግብር በመባል ከሚታወቀው የኒውክሌር ስምምነት ራሳቸዉን በማግለል በቴህራን ላይ ከፍተኛ ማዕቀብ መጣላቸዉ ይታወሳል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

👍2
የኬንያ መንግስት በማይናማር እና ታይላንድ ለሚኖሩ ዜጎች ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
የኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በመሬት መንቀጥቀጡ ዜጎቻቸውን ካጡት ማይናማር እና ታይላንድ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በማይናማር ያሉ የኬንያ ዜጎች ደህንነት እንዳሳሰበውም ገልጿል።
በመሬት መንቀጥቀጡ በተጠቁ አካባቢዎች የሚኖሩ የኬንያ ዜጎችም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎችን በአግባቡ እንዲከታተሉ ከማሳሰቡ በተጨማሪ ኬንያ ለጊዜው ዜጎቿ አላስፈላጊ ጉዞዎችን እንዳያደርጉ አስጠንቅቃለች።
የኬንያ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጨምሮም በሃገራቱ የሚኖሩ ዜጎቹ ካልተመዘገቡ በባንኮክ በሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ እና የምስራቅ አፍሪካ ማዕበረሰብ ዲፕሎማቲክ ተልዕኮ መረጃቸውን ማስመዘገብ እንዳለባቸው ያሳሰበ ሲሆን ለዚህም የሚሆን የኢሜል እና የስልክ አድራሻን አስቀምጧል።
የኬንያ መንግስት አክሎም ዜጎች ከአመራሮች የሚሰጠውን መመሪያ እንዲተገብሩ አሳስቦ ለዜጎቹ እርስ በእርሳቸው በተለይም ተማሪዎችን እና አቅም የሌላቸውን የሃገራቸውን ሰዎች እንዲያዩ እና እንዲደጋገፉ ጥሪ አቅርቧል።