Telegram Web Link
በህወሓት እና ሻዕቢያ መካከል የተፈጠረው ጥምረትና ግንኙነት በፌደራል መንግሥቱ መቋረጥ አለበት ሲሉ የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ!

በቅርቡ ህወሓትና ሻዕቢያ ጥመረት እየፈጠረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ የሁለቱ አካላት ጥምረት በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሊቋረጥ ይገባል ሲሉ የቀድሞ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አሳስበዋል፡፡የቀድሞዋ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፤ "ይህንን ለጦርነት የተደረገ ጥምረት መንግሥት ሊያቋርጠው ይገባል" ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላው የቀድሞ የድርጅቱ አባልና ከፍተኛ አመራር እንዲሁም የዲሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ መስራች ውስጥ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት በበኩላቸው፤ "የሁለቱ አካላት ጥምረት ዓላማ ግልፅ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ህወሐትና የኤርትራ መንግሥት ጥምረት መፍጠር ለጦርነት ዓላማ የተደረገ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል።

በተጨማሪም በትግርኛ "ፅምዶ" ወይንም "ጥምረት ለሀቀኛ ሰላም ለትግራይ እና ኤርትራ" በሚል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እየተደረገ መሆኑንም መመልከት ተችሏል።ይህንን ጥምረት በሚመለከት ሀሳባቸውን የሰጡት የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም "በግልፅ ለጦርነት የተደረገ ጥምረት ነው" ብለዋል።

"ሕዝብን ከተደቀነበት ጦርነት ማዳን ላይ መስራት አለብን" ያሉ ሲሆን፤ ጦርነቱ የማይቀር እንኳን ቢሆን ዱላው ሕዝብ ላይ እንዳያርፍ መስራት አለብን" ሲሉም ገልጸዋል።"አሁን ላይ በግልፅም ይሁን በድብቅ ጥምረቱ ይታያል" ያሉት ወይዘሮ ኬሪያ፤ "ይህንን ማስቆምና መቁረጥ ያለበት የትግራይ ሊሂቃንና ፌደራል መንግሥት ነው በማለት ሀሳባቸውን" ሰጥተዋል።

ሌላው ሀሳባቸውን ለአሐዱ የሰጡት የቀድሞ የህወሕት አባልና ከፍተኛ አመራር ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፤ "በአንድ ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ ከሌላ ሀገር ጋር ማን ግንኙነት መፍጠር እንዳለበት ይታወቃል" ብለዋል፡፡"ሕገ-ወጥ ግነኙነት ሲኖር ደግሞ ማስቆም ያለበት ማን እንደሆነም ግልፅ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።"ይሁን እንጂ ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት ያልጠራ ነው፤ ነገር ግን ግንኙነቱ በመርህ ላይ ካልተመሰረተ ትክክል አይለም" ሲሉም ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህ ጥምረት ዙሪያ የፌደራል መንግሥት በግልፅ ያስታወቀው ነገር ባይኖርም፤ ባለፈው ሳምንት አርብ በትግራይ ሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ የሚጠይቅ ወይይት ተካሂዶ ነበር።የፌደራል መንግሥት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከልን በመወከል የተገኙት አቶ መለሰ አለሙ፤ "የፌደራል መንግሥት ኃላፊነት እንዳለ ሆኖ የትግራይ ፖለቲከኞችም ለሰላም ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል።"የድንበር ጉዳይን በተመለከተ መንግሥት ሉዓላዊነቱን በፍፁም አሳልፎ አይሰጥም" ያሉም ሲሆን፤ የውስጥ ችግሮች ከተፈቱ ሌላውን ማስተካከል እንደሚቻል ተናግረዋል።

Via Ahadu
ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ተወሰነ!

ሦስተኛ ስብሰባውን ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ያካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ዛሬ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውስኔዎችን አሳልፏል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ያሳለፈው ወሳኔ ተጠቃሽ ነው።

"አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል።

ኮሚቴው ያመነበት ይህ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ሌሎች ለብሔራዊ ባንክ ቦርድ ቀርቦ መጽደቁንም መግለጫው አመልክቷል።ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ በሚያስገድደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ባንኮች መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 2022 ጀምሮ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ብድራቸው አምስት በመቶ የሚሆነውን ለዚህ የቦንድ ግዥ ሲያውሉ ቆይተዋል። በዚህ መመሪያ መሠረት የገዙት ቦንድ የሚመለሰው (ለቦንድ ግዢ ያዋሉት ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው) ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ ሲሆን ፣ ባንኮቹ መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ወር አንስቶ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2024 ድረስ የገዙት የቦንድ መጠን 94 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት ዕዳ መግለጫ ያመለክታል።

በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ያሳለፈው ሌላኛው ውሳኔ በባንኮች ላይ የተጣለውን የብድር ዕቀባ የተመለከተ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት በባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ጣሪያ እስከ መጪው መስከረም 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጠል ኮሚቴው ወስኗል።ለዚህም የሰጠው ምክንያት አሁን ላይ የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ እየተስተዋለ ቢሆንም ይህንን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በባንኮች ላይ የተጣለው የብድር ዕድገት ጣሪያ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልጽ ነው።

Via Reporter
"በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ አፍሪካ በማዳበሪያ እራሷን ትችላለች"- አሊኮ ዳንጎቴ

ናይጄሪያዊው የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ አፍሪካ በመጪዎቹ 40 ወራት ውስጥ በማዳበሪያ ምርት እራሷን ትችላለች አሉ።

ዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካው ላይ የ2.5 ቢሊየን ዶላር ማስፋፊያ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህም አፍሪካ ከውጪ የምታስገባውን ምርት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።

ቢሊየነሩ" አፍሪካ ከ40 ወራት በኋላ ከየትኛውም ቦታ ማዳበሪያ አታስገባም፤ 40 ወራት ብቻ ስጡኝ፥ ዳንጎቴ ከኳታር የበለጠ የዩራያ አምራች እንዲሆን እናደርገዋለን" ብለዋል።

አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ከ6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በላይ በአመት ከሌላው አለም እያስገባች ሲሆን አሁን ያለው የዳንጎቴ ፋብሪካ በአመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም ገንብቷል።

የዳንጎቴ ፋብሪካ የድርጅቱን 37 በመቶ ምርት ለአሜሪካ ገበያ እያቀረበ መሆኑን ጠቅሶ ከማስፋፊያው በኋላ ምርቱን በእጥፍ በመጨመር የአፍሪካን ፍላጎት ያሟላል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ግዙፉ የአፍሪካ ኤግዚም ባንክ ሪፖርት አፍሪካ በ2021 ከማዳበሪያ ሽያጭ 8.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ስታገኝ ትልቁን ድርሻ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ይይዛሉ ተብሏል።

ሞሮኮ እና ግብፅ 70 በመቶ የአፍሪካን የማዳበሪያ ሽያጭ ሲይዙ በድምሩ 6.23 ቢሊየን ዶላር አግኝተዋል።

ምንም እንኳን የተወሰኑ ሃገራት በማዳበሪያ እራሳቸውን የቻሉ ቢሆንም አብዛኞቹ አሁንም ከውጪ በሚገባ ምርት ላይ ጥገኛ ናቸው።

የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሚቀጥሉት ሁለት አመታትም በቀን 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ቢሊየነሩ ገልፀዋል።

በ2022 ስራውን የጀመረው የሌጎሱ የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በናይጄሪያ የምግብ እጥረትን ለመቀነስ በዝቅተኛ ዋጋ እየሸጠ ሲሆን የናይጄሪያን የ1.5 ሚሊየን ቶን አመታዊ የማዳበሪያ ፍጆታም ለመሸፈን እየሰራ ነው።

በአመት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስመጣው የማዳበሪያ ፋብሪካው የናይጄሪያን የውጪ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።

የአፍሪካ የማዳበሪያ ዋጋ ከ15 ቢሊየን ዶላር የተሻገረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 20 ቢሊየን እንደሚያድግ ይገመታል።

በምግብ እጥረት እና በውጪ ምንዛሬ ለምትፈተነው አፍሪካ የዳንጎቴ ፋብሪካ ሁነኛ መፍትሄ እንደሚሆን ሲጠቆም ቢሊየነሩ ዳንጎቴ የአህጉሪቱ መሪዎች የአህጉሪቱን ሃብትና ኢንቨስትመንት ባማከለ መልኩ አፍሪካን ተቀዳሚ አድርገው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት መስማማታቸው በቅርቡ ይፋ መደረጉም ይታወሳል።

Source: Reuters, Africa Fertilizer Watch
“በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስራት እየተፈጸመ ነው” - ሂዩማን ራይት ፈርስት

ሂዩማን ራይትስ ፈርስት የተሰኘ የሃገር ውስጥ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች በከተማዋ ባለስለጣናት ኢላማ ተደርገው፣ ያለምንም መደበኛ ክስ እና ፍርድ ሂደት በማንነታቸው ምክንያት “የዘፈቀደ እስራት” እየተፈጸመባቸው ነው” ሲል ክስ አቀረበ።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ትላንት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በፀጥታ ሃይሎች በዘፈቀደ እየታፈሱ እና በህገወጥ መንገድ እየታሰሩ እንደሚገኙ ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል።

ለእስር ተዳርገው በኋላ ላይ መፈታታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ያስታወቁ አንድ በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ለምን እንደታሰርን ስንጠይቃቸው ምንም አይነት ማብራሪያ አልሰጡንም ብለዋል፤ “ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ ነው” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን፤ ክስ አልተመሰረተብንም፣ ፍርድ ቤትም አለቀረብንም” ብለዋል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) እንዲሁም ሂዩማን ራይት ፈርስት “ዜጎችን ስማቸውን ወይም ብሄራቸውን መሰረት በማድረግ ለእስር መዳረግ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ህግጋትን የሚጻረር እና መጣስ ነው” ሲል በመኮነን “ያለ ፍርድ ሂደት ለእስር የታዳረጉት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” ሲሉ በተናጠል ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።
የቻይና ሰላዮች በአሜሪካ

በአሜሪካ ውስጥ ለቻይና ሲሰልሉ የነበሩ 2 የቻይና ዜግነት ያላቸውን ሠዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአሜሪካን የባህር ሃይል ጣቢያን ፎቶግራፍ በማንሳት፣ አመጽ በገንዘብ በመደገፍና በማስተባበር እንዲሁም የተለያዩ የስለላ ስራዎችን በመስራት በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የሳን ፍራንሲስኮ የፌደራል ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ እንደገለጹት ፣ የቻይና መንግስት ስለ አሜሪካ ወታደራዊ አቅም በድብቅ መረጃ ለመሰብሰብ የቻይና መንግስት የማያቋርጥ ጥረቶች ማሣያ ነው በማለት አብራርተዋል።

አክለውም "ይህ ጉዳይ የቻይና መንግስት ወታደሮቻችንን ሰርጎ ለመግባት እና ብሄራዊ ደህንነታችንን ከውስጥ ለማዳከም የሚያደርገውን ያልተቋረጠ ጥረት አጉልቶ ያሳያል" ሲሉ ተናግረዋል።

"የውጭ ተላላኪዎችን እናጋልጣለን ፣ወኪሎቻቸውን እናያለን እና የአሜሪካን ህዝብ በብሄራዊ ደህንነታችን ላይ ከሚደርሱ ስውር አደጋዎች እንጠብቃለንም" ብለዋል።

እ.ኤ.አ በ2015 ወደ አሜሪካ የገቡት ሠላዮቹ ዩያንስ ቼን እና ሊረን ራያን በመባል ይጠራሉ። የቻይና መንግስት ደህንነት ሚኒስቴርን ወክለው ሚስጥራዊ የስለላ ስራዎችን ለመከታተል የተደረገው ጥረት አካል እንደሆኑም ገልጸዋል።

በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሊዩ ፔንግዩ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀው፣ ነገር ግን በቻይና ላይ የተከሰሱ ውንጀላዎች ምንም ዓይነት ማስረጃ የላቸውም እንዲሁም አሜሪካ በቻይና ላይ የምታደርገውን የስለላ ተግባር አላቆመችም ማለታቸውን ኤፒ ዘግቧል።
ባልታዛር ተፈረደበት

የቀድሞው የኢኳቶሪያል ጊኒ የብሄራዊ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ባልታዛር ኢንጎንጋ ከበርካታ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የህዝብን ገንዘብ በማጭበርበር ወንጀል ተከሰው የ18 አመት እስራት ተፈረደባቸው።

ባልታዛር ባለፈው አመት መስከረም ወር ላይ ከበርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የህዝብን ገንዘብ በማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ማረሚያ ቤት ታስረው ነበር።

የቀድሞ ብሄራዊ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ባልታዛር ኢንጎንጋ የፋይናንስ ወንጀሎችን ፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሙስናን የመከላከል ትልቅ ስልጣን ነበራቸው ።

ባልታዛር ኢንጎንጋ ከባለስልጣናቱ ጋር 1ቢሊዮን ፍራንክ ከመንግስት ካዝና አጭበርብረዋል ።

ባልታሳር ኢንጎንጋ ወደ ኪሳቸው 910 ፍራንክ እንዳስገቡ ተገልጿል ።

ከባልታዛር ጋር አገር ሲዘርፉ በነበሩት በሌሎች ባለስልጣናት ላይም ፍርዱ እንደሚቀጥል ተገልጿል
ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የወባ በሽታ ጉዳዮችን ሪፖርት አደረገች

በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥርም 8.4 ሚሊዮን ደርሷል

የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሰረት፣ ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ብቻ 520,782 የወባ በሽታ ጉዳዮችን ሪፖርት አድርጋለች። ይህ ቁጥር አሳሳቢ ሲሆን፣ በ2024 በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገበው የወባ በሽታ ጉዳይ ደግሞ ከ8.4 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ተገልጿል፤ ይህም እስካሁን ከተመዘገበው ሁሉ ከፍተኛው ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የጤና ክላስተር ቡለቲን ሪፖርቱ ላይ እንዳብራራው፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከወባ በተጨማሪ እንደ ኮሌራ፣ ኩፍኝ እና ኤምፖክስ (mpox) የመሳሰሉ በርካታ በሽታዎችን እየተቋቋመች ትገኛለች።

በተለይም በአገሪቱ እየተካሄዱ ያሉት ግጭቶች በህዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ ሲሆን፣ ብዙ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ እጦትና የተገደበ የጤና አገልግሎት በሚያገኙባቸው አካባቢዎች ተይዘው ይገኛሉ።

ወባ በኢትዮጵያ ከባህር ወለል በላይ በ2,000 ሜትር ከፍታ በታች ባሉ አካባቢዎች በስፋት የሚታይ በሽታ ነው። እነዚህ አካባቢዎች የአገሪቱን የመሬት ስፋት ሶስት አራተኛውን የሚሸፍኑ ሲሆን፣ በእነዚህ ስፍራዎች ከሚኖሩት የአገሪቱ ህዝብ ውስጥ 69 በመቶ የሚሆነው በበሽታው የመያዝ ስጋት ተጋርጦበታል።

የወባ በሽታ ስርጭት በተለምዶ ከዋናው የዝናብ ወቅት በኋላ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት፣ እና ከሁለተኛው የዝናብ ወቅት በኋላ ከሚያዝያ እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ይጨምራል።

Capital
ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ገቢ ምደባ ዝርዝር ዉጪ መሆኗ ተገለፀ

የ2025 የበጀት ዓመት ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ተብላ የተመደበችው ኢትዮጵያ፣ ለ2026 የበጀት ዓመት የዓለም ባንክ የገቢ ምደባ ዝርዝር ውስጥ አለመካተቷ ካፒታል ተመልክቷል።

የዓለም ባንክ በየዓመቱ ሐምሌ 1 ቀን በሚያወጣው የሀገራት ገቢ ምደባ፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት "ጊዜያዊ ምደባ አልተሰጣትም" ተብሏል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ በዝቅተኛ ገቢ ወይም ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ሀገራት ምድብ ውስጥ አልተካተተችም ማለት ነው።

ያልተመደቡ አገሮችን በተመለከተ መረጃው እንደሚያረጋግጠው :- ቬንዙዌላ እስከ 2021 ድረስ የከፍተኛ መካከለኛ ገቢ አገር የነበረች ቢሆንም፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መረጃ ባለመኖሩ ምክንያት ከምደባ ውጭ ሆናለች። ኢትዮጵያም በአሁኑ ወቅት ለ 2026 በጀት በጊዜያዊነት ከምደባ ውጭ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።

የዓለም ባንክ የ2025 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ዝርዝር በ2023 የአንድ ሰው አጠቃላይ አገራዊ ገቢ (GNI) 1,195 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከዚያ በታች የሆኑ አገሮችን ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ አንደኛው ነበረች።

ምንም እንኳን የዚህ ምደባ አለመስጠት ትክክለኛ ምክንያቶች ግልጽ ባይሆኑም፣ የሀገር ገቢ ምድብ ለውጦች በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይገለጻል ።

"በአትላስ" ዘዴ በሚሰላው የነፍስ ወከፍ GNI ላይ በሚከሰቱ ለውጦች (ለምሳሌ የኢኮኖሚ እድገት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሪ ተመን እና የህዝብ ብዛት መጨመር ወይም በምደባ ወሰኖቹ ላይ በሚደረጉ ማስተካከያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
Capital newspaper
ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ለመጀመሪያ ጊዜ የፊታችን መስከረም ወር ላይ ለገበያ ታቀርባለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር

ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት የፊታችን መስከረም ወር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ ታቀርባለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም በለውጡ መንግስት ጋዝ ለማምረት ፋብሪካዎች ለመትከል ስምምነት ተደርጎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ጋዝና አካባቢ የሚመጡ የግል ድርጅቶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነበራቸው ፍላጎት ፈቃድ መውሰድና በዛ ፈቃድ ብር መፈለግ ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ አካሄድና መንገድ አያዋጣም ብለን የነበሩትን በመሰረዝ አዳዲስ ኩባንያዎች ወደ ዘርፉ እንዲገቡ አድርገናል ነው ያሉት፡፡
ይህን ተከትሎም ምናልባትም የምክር ቤት አባላት ከእረፍት ሲመለሱ የፊታችን መስከረም ወር ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዝ ምርት ለገበያ ታቀርባለች ብለዋል፡፡
ኦፌኮ ከተመድ የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ተወያየ፤ የምርጫ ቦርድ እንደገና ማዋቀርን ጨምሮ ቁልፍ ጥያቄዎችን አቀረበ!

የኦሮሞ ፌዴራላሲት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በ2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ዙርያ ውይይት ማድረጉን አስታወቀ።

በኦፌኮ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም የተገኙ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር የሆኑት አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን ጨምሮ አራት አባላትን የያዘ ልዑክ መገኘቱን ከፓርቲው ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኦፌኮ በስብሰባው ላይ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ መንግስት ሊያሟላቸው የሚገቡ "መሰረታዊ" ጥያቄዎችን ማቅረቡ ተጠቁሟል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ላይ መሳተፉ ሙሉ በሙሉ "በመሠረታዊ እና በተጨባጭ ለውጦች" ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

"ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ቴክኒካዊ ሂደት ብቻ አይደለም፤ የዲሞክራሲያዊ ሂደት ውጤት ነው" ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ "ይህ ሂደት ዛሬ በኢትዮጵያ የለም። በጦርነት እና በፖለቲካ ስደት ውስጥ ተአማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ አይቻልም" ሲሉ አክለዋል።

ኦፌኮ በ2018 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ መሠረታዊ ተቋማዊ እና ህጋዊ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የጠየቀ ሲሆን የምርጫ ቦርድን እንደገና ማዋቀርን ጨምሮ የምርጫ ስርዓት ማሻሸያ እንዲደረግ እና ከምርጫ በፊት በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ግልጽ የሆነ ፍኖተ ካርታ ላይ ለመስማማት የሚያስችል ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም በኦሮሚያና በመላ ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም፣ የኦፌኮ አባላት፣ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ጨምሮ በመላ አገሪቱ የታሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ማስፈራራት፣ ወከባና እስራት እንዲቆም እና የጸጥታ ሀይሎች በፖለቲካው ሂደት ውስጥ ገለልተኛ የሚሆኑበት ስምምነት እንዲፈረም ጠይቋል።
ዜና: "የኃይሌ ኃይሎች" የተሰኘና በአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የስኬት ሚስጥሮች ዙርያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለምርቃት ሊበቃ ነው

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም 'Dissecting Haile' የተሰኘና በአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የህይወት ስኬት ሚስጥሮች ዙርያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለምርቃት ሊበቃ መሆኑ ተገለጸ።

የመጽሐፉን ምረቃ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ መርሀግብር ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሄዷል።

በመርሀግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የመጽሐፉ ደራሲ እና የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ልጅ ሜላት ኃይሌ መጽሐፉ ስለ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የህይወት ፍልስፍናዎች የሚዳስስ መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም መከራን ወደ ተጽዕኖ ለመለወጥ ለሚፈልጉ ሰዎች ምሳሌ የሚሆን እና ከሀይሌ ገብረስላሴ የህይወት ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ተናግረዋል።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በመርሀግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን "ብቻን ሆኖ ጀግና መሆን አይቻልም: እኔም ከቤተሰብ ጀምሮ የማህበረሰቤ ውጤት ነኝ" ብለዋል።

አክለውም በመጽሐፉ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰዎች ምስጋና አቅርበዋል።

"የኃይሌ ኃይሎች" /Dissecting Haile/ በ12 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

መጽሐፉ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በኤሌክትሮኒክስ እና በሀርድ ኮፒ አማራጮች በይፋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
ቶምቦላ እጣ ወጥቷል

ቶምቦላ ሎተሪ 2017 ዕጣ ዛሬ  ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል።
አል-ፋሽጋ ዳግም በኢትዮጵያውያን እጅ ገባ

ለዘመናት የኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የእርሻና የኑሮ መሰረት የነበረው ለም መሬት፣ አል-ፋሽጋ፣ ዳግም ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ ተመልሷል።

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙትን የመተማና የቋራ ወረዳ ለም መሬቶችን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር።

በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ መንግሥትም ችግሩን በዲፕሎማሲና በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ የሱዳን ወረራ ወቅት ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከእርሻቸው ከመፈናቀላቸውም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብልና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው አይዘነጋም፡፡

የሱዳን ባለሥልጣናት ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው ሲሉ መክሰሳቸው ተዘግቦ ነበር፡፡
የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ ግብይት ሊጀምር ነው

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ( ስቶክ ገበያ) በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል። ይህ እርምጃ ለአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ታውቋል።

ገበያዉ በኖቬምበር 2023 በተደረገ የካፒታል ማሰባሰቢያ ዘመቻ 1.5 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ ከታሰበው ግብ በ631% በልጧል። ይህ ገንዘብ ከ48 የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተገኘ መሆኑ ይታወቃል።

በሕዝብና በግል ሽርክና የሚሰራው አዲሱ የበይነመረብ ንግድ ልዉዉጥ መድረክን መንግሥት 25%፣ የግል ዘርፍ ደግሞ 75% ድርሻ አላቸዉ። አሁን ላይ ገዳ ባንክ አ.ማ. እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ. በገበያው ላይ ከተመዘገቡት ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ እስከ 50 ኩባንያዎችን፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ደግሞ ከ90 በላይ ንግዶችን ለማካተት አቅዷል። ይህ ልውውጥ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማዘመን፣ ግልጽነትን ለማሳደግ እና ለንግዶች ካፒታል ማሰባሰቢያ አዳዲስ አማራጮችን ለመስጠት ያለመ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያነቃቃም ይጠበቃል።

ዝርዝሩን ያንብቡ
በህዳሴው ግድብ ምርቃት ላይ ፕሬዝደንት ፑቲን ሊጋበዙ ነው

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በመጪው መስከረም ወር በሚደረገው የህዳሴ ግድብ ምርቃት ስነስርአት እንዲገኙ ግብዣ ሊላክላቸው መሆኑ ተሰማ፡፡

ስፑትኒክ የተሰኘው የሩሲያ ሚዲያ ዛሬ እንደዘገበው በግድቡ መክፈቻ ስነስርአት ላይ ፑቲን እንዲገኙ የኢትዮጵያ መንግስት ግብዣ ሊላክላቸው ይችላል፡፡ ይሁንና ግብዣው ቢላክ ፕሬዝደንቱ ለመገኘት ፈቃደኛ ስለመሆንና አለመሆናቸው ያለው ነገር የለም፡፡ የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በቀረበባቸው ክስ የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ወቅት በብራዚል እየተካሄደ ባለው የብሪክስ የመሪዎች ስብሰባ ላይ በአካል ያልተገኙትም ለዚህ ነው፡፡ ስለጉዳዩ የተጠየቁት የክሬሚሊን አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ‹‹ከአይሲሲ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ፕሬዝደንት ፑቲን በአካል ብራዚል ለመገኘት አይችሉም›› ሲሉ ባለፈው ሳምንት ተናግረው ነበር፡፡

በመሆኑም በስብሰባው ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደሚሳተፉ ማስታወቃቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት(አይሲሲ) አባል አይደለችም፡፡ በሮም ፍርድ ቤቱን በተመለከተ የተፈረመውን ስምምነት ባለመፈረሟ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ የማስፈፀም ግዴታ እንደሌለባት ዘገባዎች ገልፀዋል፡፡
10 ሀገራት የብሪክስ አጋር ሀገር ሆነው ተቀላቀሉ

ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተወጣጡ 10 ሀገራት ለብሪክስ እንደ አጋር ሀገር ሆነው ተቀላቅለዋል። ኢንዶኔዢያ ደግሞ የብሪክስ አባል ሀገር ሆና ተቀላቅላለች።

ብሪክስን አጋር ሆነው የተቀላቀሉት ሀገራት የሚከተሉት ናቸው፥

1.ቤላሩስ 🇧🇾
2.ቦሊቪያ 🇧🇴
3.ካዛኪስታን 🇰🇿
4.ኩባ 🇨🇺
5.ናይጄሪያ 🇳🇬
6.ማሌዢያ 🇲🇾
7.ታይላንድ 🇹🇭
8.ቪየትናም 🇻🇳
9.ዩጋንዳ 🇺🇬
10.ኡዝቤኪስታን 🇺🇿
በመዲናዋ ለ2018 የትምህርት ዘመን የነባር እና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ እንዲሁም የመፀሀፍ ስርጭት የሚካሄደው ከሐምሌ 1 እስከ ነሃሴ 23/2017 ዓ/ም መሆኑ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ/ም የትምህርት ቀናትን ዛሬ ይፋ አድርጓል ለ11ዱም ክ/ከተማ የትምህርት ፅ/ቤቶች ልኳል።

በዚሁ ካላንደር መሰረት ምዝገባ ከሃምሌ 1 እስከ ነሔሴ 23 /2017 ዓ/ም ይካሄዳል።

መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት የሚያደርጉበት እንዲሁም አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ የሚደረገው ነሃሴ 28 እና ነሃሴ 29/2017 ዓ/ም እንደሆነ ተመላክቷል።

ከነሃሴ 24 እስከ ጳጉሜ 5/2017 ዓ/ም ደግሞ የ7ኛና የ9ኛ ክፍል ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ አዲስ ተመዝጋቢዎች ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል።

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ  (day one class one) እንደሆነ ይፋ ተደርጓል።

በ2018 ዓ/ም የሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እንደሚሰጥ በትምህርት ካላንደሩ ላይ ታሳቢ ተደርጓል።

(ሙሉውን ከላይ ይመለከቱ)
2025/07/08 10:09:40
Back to Top
HTML Embed Code: