Telegram Web Link
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የታሊባን መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዛሬ ማክሰኞ በሁለት የታሊባን ላይ መሪዎች የእስር ማዘዣ አውጥቷል ሲል ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ ባለሥልጣናቱ ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣው በአፍጋኒስታን በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ተከታታይ የጭቆና ያደርሳሉ በሚል መሆኑ ተነግሯል።

የአይሲሲ ዋና አቃቤ ህግ እንደገለፀው፣ ሂበቱላህ አክሁንዘዳህ የታሊባን የበላይ መሪ እና አብዱልሀኪም ሃቃኒ የጀማአቱል ኢስላሚያ ዋና ዳኛ በስርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ ጭቆና ያደርሳሉ በሚል ከኦገስት 15 2021 ጀምሮ በመፈጸም “በወንጀል ተጠያቂ” ናቸው ብሏል።

ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ተከታታይ የጭቆና እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርጓል ሲልም ወቅሷል።

"ታሊባን በአጠቃላይ በህዝቡ ላይ የተወሰኑ ህጎችን እና ክልከላዎችን ቢያደርግም በተለይ ልጃገረዶችን እና ሴቶችን በፆታቸው ምክንያት መሰረታዊ መብቶችን እና ነፃነቶችን ገፏል" ሲል አይሲሲ ተናግሯል ብሏል።
ግብጽ በድጋሚ የቀይ ባህር ደህንነት ላይ ትኩረት አደርጋለች፣ ከሶማሊያ ጋር ጠንካራ ወታደራዊ ግንኙነት ለመመስረት ቃል ገብታለች!

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ አሁንም በድጋሚ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ያተኮረ መልዕክት ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም አስተላልፈዋል፤ የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ግብጽ ለሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም ቃል ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን መልዕክት በድጋሚ ያስተላለፉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን በግብፅ የባህር ጠረፍ ከተማ ኤል አላሜይን ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፤ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸው ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል ተብሏል።

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በግብጽ በኩል የወጣው መግለጫ አንደሚያትተው መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል፣ በተለይም በሶማሊያ ደህንነት እና መረጋጋት ዙሪያ በዝርዝር ተነጋግረዋል ብሏል።

ፕሬዝዳንት አልሲሲ በተደጋጋሚ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር ደህንነት እና መረጋጋት ዙሪያ አስተያየት ሰጡ ወይንም ተወያዩ የሚሉ አገላለጾች መሰማት የጀመሩት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2024 መጀመሪያ ላይ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ ነው።

በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ከሁለቱም ወገኖች ምንም አይነት ድምጽ እየተሰማ ባይሆንም ኢትዮጵያውያ በቀጥታ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት አሁንም ከግብፅም ሆነ ከሶማሊያ በኩል በጥርጣሬ እና በስጋት የሚታይ ነው።

Via AS
1
አዲስ የግብር አወሳሰን ለአከራዮች እና የሙያ አገልግሎት ሰጪዎች ይፋ ተደረገ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የ2017 የግብር ዘመን አዲስ የአወሳሰን ስርዓት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረጉን አስታወቀ። ይህ አዲስ መመሪያ የመኖሪያ ቤት አከራዮችን፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪዎችን፣ እንዲሁም አንዳንድ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን ይመለከታል።

የንግድ ስራ ያልሆነ ገቢ ያላቸው የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፍቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች (እንደ ጠበቆችና ኢንሹራንስ ወኪሎች ያሉ) ከጠቅላላ ገቢያቸው 35 በመቶው እንደ ወጪ የሚቀነስ ሲሆን፣ ቀሪው 65 በመቶው ብቻ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ይሆናል።

ይህ አሰራር የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ ግዴታ ሳይኖርባቸው በግምት ገቢያቸው የሚሰላላቸውን ግብር ከፋዮች ጫና ለመቀነስ እና የግብር አሰባሰቡን ፍትሃዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ካፒታል ከመመሪያው ለመረዳት ችሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በህግ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ የሌለባቸው የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም በግል ኮድ 02 እና በንግድ ኮድ 03 የተመዘገቡ ተሽከርካሪ የኪራይ አገልግሎት ሰጪዎች ላይም አዲሱ መመሪያ ተፈፃሚ ይሆናል። ለእነዚህ ዘርፎች ግብሩ የሚሰላው በሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት መሆኑን ተገልጿል።

ከእነዚህ ዘርፎች ውጭ የሆኑ እና የሂሳብ መግለጫ የማቅረብ ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር ከፋዮች ግን ግብር ለመሸሽ በሚደረግ ተግባር እንደሚወገዱ ቢሮው አስጠንቅቋል። በዚህም መሰረት፣ የታክስ ጉዳቱ 40 በመቶ እና የታክሱ እጥፍ ቅጣት ሳይነሳ ገቢው እንደሚሰበሰብ ተገልጿል።

Capital Newspaper
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
አንድ የደጋ አጋዘን በ15 ሺህ ዶላር እየታደነ ነው

አንድ የደጋ አጋዘን በ15 ሺህ ዶላር እየታደነ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦና ያዴሳ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በክልሉ ደንን ማዕከል ያደረገ የአካባቢ ጥበቃ ስራ በስፋት ይሰራል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የነበረው አሰራር ደኖችን ለመጠበቅ ህዝብን ያሳተፈ አልነበረም ያሉት አቶ ቦና፤ ይህን አሰራር በመቀየር ህብረተሰቡ እንዲደራጅ በማድረግ ደኖችን እንዲከልልና በውስጡ ያሉ ሃብቶች እንዲጠብቅ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኘውን የደጋ አጋዘን ለውጪ ሀገር ዜጎች ለሕጋዊ አደን በማቅረብ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

የደጋ አጋዘን በአርሲ እና ባሌ ተራራማ ስፍራዎች እንዲሁም በምዕራብ ሀረርጌ በስፋት የሚገኝ ነው ብለው፤ የውጪ ሀገር ዜጎችም ለስፖርታዊ አደን የሚመርጡት ብርቅዬ እንስሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በአዳባ እና ዶዶላ አካባቢዎች ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ለውጪ ዜጎች የደጋ አጋዘንን ለአደንነት እንዲያቀርቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አደኑን የሚያደርጉት የውጪ ዜጎች ፈቃድ የሚሰጣቸው ሲሆን፤ በአካባቢው ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመሆን ያረጀ ወንድ የደጋ አጋዘን ተመርጦ እንዲያድኑ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

ማንኛውንም የደጋ አጋዘን ማደን ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንም አክለዋል፡፡

አንድ የውጪ ዜጎች ለአንድ አጋዘን ለማደን 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፍላል ያሉት አቶ ቦና፤ አዳኙ ያደነውን የደጋ አጋዘን ከአንገት በላይ ያለው አካል ይዞ መሄድ ይችላል ብለዋል፡፡

ከአደኑ የሚገኘው ገቢ 70 በመቶ የሚሆነው ለኢንተርፕራዞች የሚገባ መሆኑና 30 በመቶውን መንግስት እንደሚወሰድም ተናግረዋል፡፡
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
ለእናቱ ሕመም መፍትሔ ለመፈለግ የጀመረው ጥረት ከስኬት ያደረሰው ወጣት

"እናቴ በብዙ ርህሩህ ነበረች፤ ነገር ግን በድንገት ሳይታሰብ ታመመች" ይላል ለእናቱ ፈውስ ለመፈለግ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ዘንድሮ የተመረቀው ወጣት ቅዱስ ኤፍሬም።

እናቱ በድንገት ሰውነታቸው ፓራላይዝድ በመሆኑ እጃቸውም አልሠራ እንዳላቸው እና መናገርም እንደተሳናቸው ይገልጻል።

“ያም ሆኖ እያነከሰችም ቢሆን፣ እኔን ለማሳደግ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፋለች" ይላል ቅዱስ።

እኚህ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው ያሳደጉት እናቱ ታዲያ አንድ ቀን ሲያለቅሱ ያገኛቸዋል።

ምክንያቱ ደግሞ በአንድ የምርቃት ፕሮግራም ላይ በታደሙበት ወቅት በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ሲያናግሯቸው መልስ መመለስ ባለመቻላቸው ነበር።

“በወቅቱ እያነባች እንደምንም በዲፕሎማ ወደ ተመረቀችው ልጅ በመጠቆም ለማስረዳት ሞከረች” ይላል።

ነገሩ የገባው ልጅም ቁጭቱን በልቡ አድርጎ ለዚህ ሕመሟ መፍትሔ ለማግኘት እና እናቱን ለማስደሰት ቆረጠ።

“ከስምንት ዓመት በላይ በስትሮክ ሕመም የተጎዳችው እናቴን ለማስደሰት እና ለመርዳት ስል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን ለመማር ወሰንኩ” ሲል ቅዱስ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግሯል።

ቅዱስ ኤፍሬም የእናቱን ዕንባ ለማበስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪያል ዲዛይን ትምህርት ክፍልን ተቀላቀለ።

ለአራት ዓመታት ዓላማውን ለማሳካት ፈተናዎችን ተቋቁሞ በመማር ለእናቱ በአጠቃላይም ለስትሮክ ታማሚዎች መፍትሔ የሚሰጥ ለእጅ እንቅስቃሴ የሚረዳ መሣሪያ ‘rehabilitation glove’ ሠርቷል።

የመመረቂያ ዲዛይን ፕሮጀክቱን ለእናቱ መፍትሔ ለመስጠት እና ለማኅበረሰቡ ለመድረስ የሠራው ሲሆን፤ "የቤቴን ችግር ለመቅረፍ የተማርኩት ትምህርት ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ጉልህ ሚና እንዳለው በተለያዩ ኩባንያዎች አስተያየት እየተሰጠኝ ነው" ብሏል።

የስትሮክ ታማሚ እናቱን በማሰብ መሣሪያውን የሠራው ቅዱስ፣ እጃቸው ፓራላይዝድ የሆነ ሰዎች ሰውነታቸው መሥራት እንዲችል የሚረዳ መፍትሔ ሠርቶ ተመርቋል።

እናቱም የድጋፍ መሣሪያውን ተጠቅመው እጃቸውን ማንቀሳቀስ ችለዋል።

የሠራውን የድጋፍ መሣሪያ ያዩ መምህሮቹም "እናትህ ወለደችህ፤ አንተ ደግሞ እናትህን ወለድካት" የሚል አስተያየት ሰጥተውታል።

“ከተሠራ የማይቻል የለም፤ እግዚአብሔር ብዙ አስችሎኛል” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም፣ ከጎኑ በመሆን ለደገፉት ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

በሔለን ተስፋዬ
2
አራት የመጀመሪያ ዲግሪዎችን እና አንድ የዶክትሬት ዲግሪ ይዞ በሞተር መልዕክተኛ ስራ የሚሰራው ቻይናዊ

አንድ ቻይናዊ ሰው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተመረቀ በኋላ በአሁኑ ጊዜ በሳምንት 550 ዶላር የሚያስገኝለትን የመልዕከተኛ ስራን ይሰራል።

በ15 ዓመታት ውስጥ በቻይና፣ በሲንጋፖር እና በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር አራት የመጀመሪያ ዲግሪዎችን እና አንድ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝቷል።

"ፈተናዎትን ካላለፉ ተስፋ አይቁረጡ።" ወጣቶችን “ጥሩ ውጤት ካመጣችሁ ደግሞ የአብዛኞቹ ሰዎች ስራ ለውጥ እንደማያመጣ አስታውሱ” ሲል መክሯል።
Fidel post
በመዲናዋ ከ68 ሺ በላይ ደንብ ተላላፊ እግረኞች መቀጣታቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ ከ68 ሺህ በላይ ደንብ ተላላፊ እግረኞች መቀጣታቸውን፣ ኢፕድ የከተማዋ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ከበበው ሚዴቅሳ እንደገለጹት፤ በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ላይ በተደረገ ቁጥጥር 68 ሺህ 640 ደንብ ተላላፊ እግረኞች ተቀጥተዋል። ከዚህም 30 ሺህ 616 በገንዘብ እንዲሁም 37 ሺህ 790 እግረኞች የአገልግሎት ስራ እንዲሰሩ የተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ዜብራ ጠብቀው የማይሻገሩ፣ አደባባይ የሚያቋርጡ፣ እንዲሁም የትራፊክ መብራት የማያከብሩ እግረኞች መቀጣታቸውን ነው ን ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

ከ80 በመቶ በላይ የትራፊክ አደጋ ተጎጂ እግረኞች መሆናቸውን በመግለጽም፤ እግረኞች የትራፊክ ደህንነት ህጎችን በማክበር በተሽከርካሪ ከሚደርስ አደጋና ሞት እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
👍1
የመኪና አደጋው ምክንያት ምን ነበር ?

ከሳምንት በፊት የዲያጎ ጆታ እና ወንድሙን ህይወት የቀጠፈው የመኪና አደጋ የተፈጠረበትን ምክንያት የስፔን መንግሥት አስታውቋል።

የመኪና አደጋው የተፈጠረው ከተፈቀደው የፍጥነት መጠን በላይ በማሽከርከር ምክንያት መሆኑን የስፔን ሲቪል ጠባቂ ማረጋገጡን " AFP " አስነብቧል።

አደጋው በተከሰተበት ወቅት የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ መኪናውን ሲያሽከረክር እንደነበር ተገልጿል።
#TS
ኢትዮጵያ የራሷን ዋትስአፕ፣ ጂ-ሜይልና ቴሌግራም እያበለፀገች ነው ተባለ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አማካኝነት የተገነቡት የዲጂታል ቴክኖሎጂ መድረኮች የሳይበር ደህንነትን ለማሻሻልና ከኢትዮጵያ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውጪ በሆኑ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የታለሙ እንደሆኑ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ለጂሜይል አማራጭ ሆኖ የቀረበው “እርጋሜል” ከወዲሁ በመንግሥት ተቋማት ሥራ ላይ መዋል እንደጀመረ ተነግሯል፡፡ "ሰርኩትኒ" የዋትስአፕ እና ቴሌግራም ምትክ እንዲሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ገና በትግበራ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ለቨርቹዋል ግንኙነቶች ታስቦ በኢንሳ የበለፀገው “ደቦ” ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል፡፡
😁1
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የምትሰጠውን ቪዛ ቆይታ ወደ ሦስት ወር አሳጠረች

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታወቀ።
ኤምባሲው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም. በኤክስ ገፁ ባሰፈረው መረጃ፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ ባደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ገልጿል።

በአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲ መሠረት፤ "ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ" እንደሚኖረው አስታውቋል።
ኤምባሲው በዚሁ የኤክስ ገጽ ልጥፉ ላይ ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ገልጿል።
ለንግድ እና ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ "B1" እና "B2" በሚለው ምድብ ውስጥ ይካተታል።

እስካሁን በነበረው አሰራር በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ተጓዦች የሚያገኙት ቪዛ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነበር። በተጨማሪም የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ያስችል ነበር።

አሁን ይፋ የተደረገው ፖሊሲ የቪዛውን የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ከማሳጠር በተጨማሪ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትን ከልክሏል።
በአዲሱ ፖሊሲ ቪዛ የሚያገኙ ተጓዦች የቆይታ ጊዜ ባይጠናቀቅም እንኳ ከአሜሪካ ከወጡ በኋላ በዚያው ቪዛ ተመልሰው መግባት አይችሉም

አሜሪካ የቪዛ አሰጣጥ ፖሊሲዋን በመከለሷ ምክንያት ለጉብኝት፣ ለትምህርት እንዲሁም ለሥራ ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ መንገደኞች የሚያገኙት የሦስት ወር ቪዛ ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
ከዚህም በተጨማሪ የያዙት ቪዛ አንድ ግዜ ብቻ መግባት የሚያስችላቸው ይሆናል።

አሜሪካ የቪዛ ፖሊሲዋን ዳግም የከለሰችው የትራምፕ አስተዳደር እአአ ሰኔ 5/2025 የደህንነት ስጋት ናቸው ባሏቸው 12 አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ ክልከላ ማድረጓን ካስታወቀች በኋላ ነው።
ከእነዚህ 12 አገራት መካከል ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኤርትራ፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ይገኙበታል።

ከሳምንት በኋላም ኢትዮጵያን ጨምሮ የ36 አገራት ዜጎች አሜሪካ እንዳይገቡ ለማገድ ሃሳብ እንዳለው የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጣዊ ሰነድን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር።

ጋና፣ ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ እገዳው ሊጣልባቸው ይችላል ከተባሉ አገራት መካከል ተጠቅሰውም ነበር።

Via BBC
1
ሚስታቸውን የነዳጅ ማደያ ቦታ ረስተዋት ከ300 መቶ ኪሎ ሜትር በኃላ ያሳታወሷት ባል

ፈረንሳዊ የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው። ባለቤታቸውን በፈጣን ጎዳና ላይ ባለ አንድ የነዳጅ ማደያ ውስጥ እንደረሷቸው ደግሞም ማስታወስ እንዳልቻሉ አስገራሚው የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ይጠቁማል።

አዛወንቱ ሚስታቸውን ጥለው መክነፋቸውን የተረዱት ግን ከተነሱበት ማደያ 300 ኪሎ ሜትር ከራቁ በኃላ ነበር። በዚህም እርዳታን ፍለጋ ፖሊስ ዘንድ የእርዳታ ጥሪ ያደርጋሉ።

ነገሩ እንዲህ ነው። የፓሪስ ነዋሪ አዛውንት ጁላይ  5  ከባለቤታቸውና እና ሴት ልጃቸው ጋር ለእረፍት ወደ ሞሮኮ ያቀናሉ። በመንገዳቸውም ነዳጅ ለመቅዳት በርካታ ማደያዎች ላይ ይቆማሉ። ይሁንና አንዱ ማደያ በቆሙበት ጊዜ ግን አንድ የተለየ ክስተት ይፈጠራል።

ስማቸው በሚዲያ ያልተገለፀው ግለሰብ ንጋት 10:30 ላይ ነዳቸውን ሞልተው በጨረሱበት ሰዓት ሚስታቸውን እዛው ትተዋቸው መሄዳቸውን ሳያስታውሱ ወደፊት ይገሰግሳሉ።

ነገር ግን ባለቤታቸውን መርሳታቸው የተረዱት 300 ኪሎ ሜትር ርቀው ከተጓዙ በኃላ ነበር። አዛውንቱ ባለቤታቸውን የነዳጅ ማደያ ውስጥ እንደረሷቸው ሲረዱ እርዳታ ፍለጋ በፍጥነት ለእርዳታ የድንገተኛ ጥሪ ያደርጋሉ።

ሚስታቸውን ማደያ ቦታ መርሳታቸው፣ 300 ከራቁ በኃላ ማስታወሳቻው ጉድ በል ሊያስብል ይችላል፣ ነገር ግን የበለጠ አጃኢብ የሚያስብለው  ሚስታቸውን የትኛው የነዳጅ ማደያ እንደረሷቸው አለማስታወሳቸው ነው።

Fidel post
የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በሚመለከት የገባችዉን የቃል ማረጋገጫ በጽሑፍ ስምምነት እንድታጠናክር ግብፅ ጠየቀች

ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ  የሰጠቻቸውን የቃል ማረጋገጫዎች በጽሑፍ ስምምነት እንድትደግፍ ግብፅ ጠየቀች። ይህ ጥያቄ የመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግድቡ በመስከረም ወር እንደሚመረቅ ከገለጹ በኋላ ነው።

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ፣ በቅርቡ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ከአብይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

በብሪክስ ስብሰባ ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ግድቡን “ግብፅንና ሱዳንን ሳይጎዳ” የማጠናቀቅ እና ትብብርን የመቀጠል ፍላጎታቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ ማድቡሊ፣ እነዚህ የቃል ማረጋገጫዎች በሁለቱ ሀገራት ወይም በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ያለውን የወደፊት ግንኙነት በሚያደራጅ የጽሑፍ ሰነድ ውስጥ መተርጎም አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “የግብፅ አቋም በፍጹም አልተለወጠም፤ በአባይ ውሃ ድርሻዋ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዲደርስ አትፈቅድም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ግብፅ የልማት ተቃዋሚ ባትሆንም፣ በአባይ ውሃ ላይ ያላትን ህጋዊ መብት እንደምትጠብቅም አስረድተዋል።

Capita
l newspaper
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
ነጻ ዋይፋይ (Wi-Fi) ስንጠቀም ደህንነታችን ለምን አደጋ ላይ ይወድቃል?

አገልግሎት ሰጪዎች ደንበኞችን ለመሳብ ነጻ ዋይፋይ እንደ አማራጭ ያቀርባሉ።

ግለሰቦችም እየተዝናኑ እግረ መንገዳቸውን ነጻ የቀረበላቸዉን ዋይፋይ በመጠቀም አንዳንድ ጉዳዮችን መከወን የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል።

ይሁን እንጂ የህዝብ ዋይፋዮች ደህንነታቸዉ የተረጋገጠ አለመሆናቸዉን ተከትሎ ግለሰቦችን በተለያየ መልኩ ለሳይበር ጥቃት ያጋልጣሉ፤ ለመሆኑ ነጻ ወይም የሕዝብ ዋይፋይ (Wi-Fi) ለደህንነታችን ስጋት የሚሆንበት ምክንያቶች ምንድን ናቸው፦

• ብዙ የህዝብ ዋይፋይ ኔትዎርኮች ምንም ዓይነት ምስጠራ ስለማይተገብሩ ሚስጥራዊ መረጃዎቻችንን ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ያደርጉታል፤
• ሰርጎ ገቦች ባልተመሰጠሩ ኔትወርኮች ውስጥ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በቀላሉ የመጥለፍ እድል ስለሚፈጥርላቸዉ የግላዊ መረጃዎቻችንን በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል፤
• የሳይበር ወንጀለኞች ሀሰተኛ ዋይፋይ በማዘጋጀት ወይም አጥፊ ተልዕኮ ያላቸዉን ሶፍትዌሮች ወደ ህጋዊ ዋይፋይ በማስገባት ዲቫይሶቻችንን የመቆጣጠር አቅም ስለሚሰጣቸው፤
• የመረጃ መንታፊዎች የእኛን ግንኙነት ለመጥለፍ እና ለመቆጣጠር ከእኛ እውቅና ውጪ የምንጠቀምባቸዉን ዲቫይሶች ሰርገዉ በመግባት መረጃዎችን መስረቅ ስለሚያስችላቸዉ፤
• አንዳንድ የህዝብ ዋይፋይ አቅራቢዎች የመረጃ ፍለጋ እንቅስቃሴያችንን በመመዝገብ ሊሰልሉን ስለሚችሉ ግላዊና ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎቻችንን ለአደጋ ያጋልጡብናል፡፡

ነጻ ዋይፋይ (Wi-Fi) መጠቀም የግድ ከሆነ የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች እንውሰድ
• HTTPSን የሚጠቀሙ ድረ-ገጾች በመረጃ መፈለጊያው እና በድረ-ገጹ መካከል ያለውን ግንኙነት ስለሚያመሰጥሩ እነሱን ብቻ መጠቀም፤
• በህዝብ ዋይፋይ በመጠቀም የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን (የኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ግብይትን ወ.ዘ.ተ) ከመፈጸም ወይም ሚስጥራዊ መረጃን ከመለዋወጥ መቆጠብ፤
• ዲቫይሳችን ከማናውቀው የዋይፋይ አውታረ መረብ (Network) ጋር በራሱ እንዳይገናኝ አውቶማቲኩን ማጥፋት።
Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው

በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ መካተቱ ታውቋል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ (ለምሳሌ ከዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ እና ሌሎችም መድረኮች) ፣ በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች እንደሚሁም ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣ ከስፖንሰርሺፕ እና ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው “ሌሎች ገቢዎች” በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣኑ የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

በኢያሱ ዘካሪያስ
የኢትዮጵያ ብር በሩሲያ የባንክ ምንዛሬ ውስጥ ተካተተ

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሌሊት ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ የኢትዮጵያን ብር በምንዛሬ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።ይህም ማለት ብርን ወደ ሩብል እንዲሁም ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ዕድልን ይሰጣል።

በዚህም መሰረት ባንኩ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.5872  ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።

Via EBC
1
2025/07/14 11:38:30
Back to Top
HTML Embed Code: