Telegram Web Link
ዲሽ እና ዲኮደር መጠቀም ሳያስፈልግ የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚቻልበት ስርዓት ይፋ ተደረገ።

ኢትዮቴሌኮም እና መልቲቾይስ አፍሪካ የቴሌኮምን አገልግሎት ከመዝናኛ ጋር ያጣመረውን የ"ዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል"ን ይፋ አድርገዋል።የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል የኢትዮ ቴሌኮምን የፊክስድ ብሮድባንድና የሞባይል ኢንተርኔት ዳታ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከጠበቁት የዲኤስቲቪ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች ጋር በአንድ ያዋሃደ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ትብብሩ ኢትዮ ቴሌኮም የደረሰበትን ሁሉንም አይነት አገልግሎት ዲጂታላይዝ የማድረግ ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ገሊላ ገ/ሚካኤል ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ ያለው ፋይበር ኔትዎርክ የሚጠቀም ደንበኛ ከዲኤስቲቪ አገልግሎት በላቀ መልኩ የኦንላይን ትምህርት እንዲሁም ስራዎችን ጨምሮ ለደንበኞች ህይወትን ሊያቀሉ የሚችሉ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።

ዲኤስቲቪ እና ኢትዮቴሌኮም ለዚህ የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል ከመደበኛው አገልግሎታቸው ክፍያዎች በተለየ መልኩ ልዩ ቅናሽ ያደረጉበት ሲሆን ደንበኞች የስትሪሚንግ አገልግሎቱን በመመዝገብ ብቻ ዲሽና ዲኮደር ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ መጠቀም ያስችላቸዋል።ይህም ደንበኞች በፈለጉት ዓይነት ዲቫይስ ወይም በስልክ፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕና ቴሌቪዥን ቦታ እና ግዜ ሳይገድባቸው ከ70በላይ ይዘቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via Arts TV
👍3
ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል

የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ቅዳሜ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መደበኛና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ ነው‼️
24 የተሽከርካሪ ዓመታዊ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ ርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ተቋማትን በመገምገም ነው የጎላ ክፍተት የተገኘባቸው 24 ተቋማት ላይ ርምጃ የወሰደው፡፡

በዚህ መሰረትም 2 የምርመራ ተቋማት ፈቃዳቸው የተሰረዘ ሲሆን÷ 4 ተቋማት ደግሞ ለሶስት ወራት ታግደው ክፍተታቸውን እንዲያርሙ ተወስኗል፡፡

በተጨማሪም 6 ተቋማት ለአንድ ወር ሥራ እንዲያቆሙ እንዲሁም 12 ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በቁርጠኝት እንደሚሰራም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ኢራን በኒውክሌር ድርድር ካልተስማማች በቦምብ ድምጥማጧን አጠፋለሁ አሉ

በጉዳዩ ዙሪያ ስምምነት ላይ ካልደረሱ የቦምብ ጥቃት እፈጽማለሁ ጥቃቱም ከዚህ በፊት አይተውት የማያውቁት ይሆናል ብለዋል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ከዋሽንግተን ጋር ለመደራደር ካልተስማማች ታይቶ የማይታወቅ የቦምብ ጥቃት ይደርስባታል ብለዋል፤

ይህም በጥር ወር ስልጣን ከያዙ በኋላ ስለሚወስዱት ወታደራዊ እርምጃ በጣም ግልፅ የሆነ ማስጠንቀቂያ የሰጡበት ነዉ ተብሏል፡፡

ባለፈው እሁድ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ቴህራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን ቀጥተኛ ድርድር ውድቅ እንዳደረገች በመግለጽ፤ኢራን ቀጥተኛ ምላሽ የሚያስፈልገዉን ከዶናልድ ትራምፕ የመጣ ደብዳቤ ለጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔ መላኳን አስታዉቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተዘዋዋሪ ድርድር የማካሄድ እድልን ግን ክፍት አድርገዋል።

ትራምፕ ኢራን በቀጥታ ንግግሮች ላይ እንድትሳተፍ ለወራት በይፋ ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ቴህራን የውሳኔ ሃሳቡን ውድቅ ካደረገች በጣም መጥፎ ምላሽ እንደሚከተላት ፍንጭ ሰጥተዉ ነበር፡፡

በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ፤የአለም ኃያላን እና ኢራን የጋራ አጠቃላይ የድርጊት መርሃ ግብር በመባል ከሚታወቀው የኒውክሌር ስምምነት ራሳቸዉን በማግለል በቴህራን ላይ ከፍተኛ ማዕቀብ መጣላቸዉ ይታወሳል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
👍2
የኬንያ መንግስት በማይናማር እና ታይላንድ ለሚኖሩ ዜጎች ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በመሬት መንቀጥቀጡ ዜጎቻቸውን ካጡት ማይናማር እና ታይላንድ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በማይናማር ያሉ የኬንያ ዜጎች ደህንነት እንዳሳሰበውም ገልጿል።

በመሬት መንቀጥቀጡ በተጠቁ አካባቢዎች የሚኖሩ የኬንያ ዜጎችም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎችን በአግባቡ እንዲከታተሉ ከማሳሰቡ በተጨማሪ ኬንያ ለጊዜው ዜጎቿ አላስፈላጊ ጉዞዎችን እንዳያደርጉ አስጠንቅቃለች።

የኬንያ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጨምሮም በሃገራቱ የሚኖሩ ዜጎቹ ካልተመዘገቡ በባንኮክ በሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ እና የምስራቅ አፍሪካ ማዕበረሰብ ዲፕሎማቲክ ተልዕኮ መረጃቸውን ማስመዘገብ እንዳለባቸው ያሳሰበ ሲሆን ለዚህም የሚሆን የኢሜል እና የስልክ አድራሻን አስቀምጧል።

የኬንያ መንግስት አክሎም ዜጎች ከአመራሮች የሚሰጠውን መመሪያ እንዲተገብሩ አሳስቦ ለዜጎቹ እርስ በእርሳቸው በተለይም ተማሪዎችን እና አቅም የሌላቸውን የሃገራቸውን ሰዎች እንዲያዩ እና እንዲደጋገፉ ጥሪ አቅርቧል።
1
ግብፅ ከደቡብ ኮሪያ 100 FA-50 የተሰኙ የጦር አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው።

በሴኡል የግብፅ አምባሳደር የሆኑት ካሊድ አብድራህማን ሀገሪቱ ከደቡብ ኮሪያ ለምትገጻው የጦር አውሮፕላን ድርድሩ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ግብፅ በመጀመሪያው ዙርም 36 የጦር አውሮፕላኖችን እንደምትረከብ ይጠበቃል።

FA-50 የተሰኘው የጦር አውሮፕላን በሰዓት እስከ 1800 ኪሎሜትሮችን መጓዝ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን ግዢው የግብፅን ወታደራዊ አቅም ለማሳደግ ታቅዶ እንደሆነ ተገልጿል።

Source: The Defense post
ሰርቢያ ከኬንያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች።

የሰርቢያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኬንያ ለኮሶቮ የሰጠችው የሃገር ዕውቅናን ተቃውሟል።

በ2008 ከሰርቢያ ነፃ የወጣችው ኮሶቮ አሜሪካን ጨምሮ በብዙ ሃገራት ዕውቅናን ያገኘች ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ በሃያላኑ ሩሲያ እና ቻይና ዕውቅናን አላገኘችም።

የሰርቢያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የዊሊያም ሩቶ መንግስት የግዛት አንድነትን የሚደግፈውን የተመድ ቻርተር ጥሰዋል ያለ ሲሆን ሰርቢያ ከኬንያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧንም አስታውቀዋል።

ሰርቢያ ጨምራም ኬንያ የአለም አቀፍን ህግ ጥሳለች ያለች ሲሆን ተገቢው የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ እርምጃም እወስዳለሁ ብላለች። በተጨማሪ የግዛት አንድነቷን ለመጠበቅ ማንኛውንም ነገር እንደምታደርግ አስታውቃለች።
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል የሚውል የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር ወይም የ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ተፈራርመዋል፡፡
👎1
ምክር ቤቱ ነገ የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም 22ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የፌደራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ፑቲን ከትራምፕ ጋር ለመነጋገር በራቸዉ ክፍት ነዉ አለ ክሬምሊን

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመነጋገር በራቸዉ ክፍት ነዉ ሲል ክሬምሊን አስታወቀ።

ይህ የክሬምሊን ምላሽ የተሰማዉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲን «ተናድጃለሁ» ማለታቸዉን ተከትሎ ነዉ።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮፍ ዛሬ እንዳሉት፣ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ አቻቸው ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ዉይይታቸዉን ይቀጥላሉ፤ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስልክ ጥሪ ሊደረግ ይችላል፤ የፑቲን በር ለትራምፕ ክፍት ነዉ ብለዋል።

በሌላ በኩል የሩሲያ ከርሰ መድር ሀብት ድርጅት ኃላፊ ኪሪል ዲሚትሪየቭ፣ ሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ እምብዛም ባልተለመዱ የከርሰመድር ፕሮጀክቶች ላይ ሊደረግ ስለሚችለው ትብብር እየተወያዩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ ለሁለተኛው ሌሊት በተከታታይ በሰሜን ምሥራቅ ዩክሬን በምትገኘው በሃርከፍ ከተማ ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።
👍1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ከባንክ ፕሬዝደንቶች ጋር መወያየቱን ገለፀ።
የውይይቱን ውጤት፣ አሉ ያሏቸውን ብዥታዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከማስተካከል አንፃር የማእከላዊ ባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ያነሷቸው አበይት ነጥቦች
– በውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ረገድ በህብረተሰቡ በነጋዴ እንዲሁም ባንኮች ረገድ አልፎ አልፎ ብዥታ መኖሩን ባንኩ ተገንዝቧል።

–የባንኩ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ የለውጥ ትግበራ ከተጀመረበት ሀምሌ 2016 አንስቶ በ200 በመቶ ጨምሯል፤

–ይሄም በበጀት አመቱ መጨረሻ ይደረስበታል ተብሎ ከተቀመጠው እቅድ አንፃር ያለፈ ነው።

–ዛሬ ከባንክ መሪዎች ጋር በነበረው ውይይት በአፈፃፀም የሚታዩ ችግሮች እንዲታረሙ፣ የውጭ ምንዛሬ መመሪያ በጥብቅ እንዲተገበር  ብሄራዊ ባንክ አዟል።

–በተጨማሪ ባንኮች ለውጭ ምንዛሬ ግብይት የሚያስከፍሉት ኮሚሽን እና የአገልግሎት ክፍያ ተመጣጣኝ እንዲያደርጉ ታዘዋል።

–ብሄራዊ ባንኩ የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ቢያንስ እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ በየ 15 ቀኑ የውጭ ምንዛሬ ለባንኮች በጨረታ ይሸጣል።

–ባንኩ ቴክኖሎጂ እና አጋር ተቋማትን በመተቀም ጭምር በህገወጦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ገዥው የጠቀሱት

–በተለይ ከባንክ ውጭ ያሉ ሀዋላ የሚሰሩ፣ ገንዘብ ወደ ውጭ የሚያሸሹ እና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር/ላውንደሪ የሚያረጉ ላይ ነው ማስጠንቀቂያ የተሰጠው

–የሀዋላ ኩባንያዎችም የባንኩን ህግ አክብረው እንዲሰሩ ነው ማሳሰቢያ የተሰጠው

ወደዚህ እንዴት ተደረሰ

የብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገው ግምገማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስቦ ነበር። ከሳምንታት በፊት ባንኩ 60 ሚሊየን ዶላር ለባንኮች ለመሸጥ ባወጣው ጨረታ ለአንድ ዶላር በአማካኝ 135 ብር ከ62 ሳንቲም ቀርቦ ነበር።
ይሄም በባንኮች ከሚሸጥበት ዋጋ በ10 ብር ገደማ የጨመረ በመሆኑ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። (የኮሚቴውን ውሳኔ ተከተወሎ በጉዳዩ ላይ ባሳለፍነው ረቡዕ መጋቢት 17/March 26 ቀን በቅዳሜ ገበያ የሬድዮ ቆይታ ሰፋ ያለ ሃሳብ ያቀረብን በመሆኑ ከማህበራዊ ገፆቻችን ውይይቱን ማድመጥ ይቻላል)

–ባንኮች የግምታዊ ገብይት ውስጥ መግባት፣ የአገልግሎት ክፍያን የማናር፣ የውጭ ምንዛሬውን ሌላ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ እና ሌሎች መላ ምቶች ለምንዛሬ መጠን መናር በባለሞያዎች በምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው።

–በህገወጥ የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር ከ 150 ብር በላይ እንደሚመነዘር ነው ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች ለቅዳሜ ገበያ የገለፁት።
👍2
ብሄራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በአማካኝ አንድ ዶላር 131 ነጥብ 70 ብር ተሸጠ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።ባንኩ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር ማስታወቁን ተከትሎ፤ በዛሬው ዕለት 50 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ለባንኮች በጨረታ አቅርቧል፡፡

በዚህም ጨረታ ላይ 12 ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን መከፋፈል መቻላቸውን ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።በዚህም አማካኝ የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር 131 ነጥብ 7095 ብር ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል።

ባንኩ ከአንድ ወር በፊት 60 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፤ በአማካኝ 135 ነጥብ 6 ብር ለአንድ ዶላር መግዣ ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል።በዚህም ዛሬ በወጣው ጨረታ የቀረበው አማካኝ ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲስተያይ፤ የ3 በመቶ አካባቢ ቅናሽ ታይቶበታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መሰል ጨረታዎች ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት በየሁለት ሳምንቱ እንደሚካሄዱ ያስታወቀ ሲሆን፤ ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ግብን ማሳካት ነው ብሏል፡፡
👍1
#AddisAbaba

" የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው ማግኘት ይቻለል " - የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ከመጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ መፈቀዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ በመንጃ ፈቃዱ ላይ ወደ ተገለጸው እና ፋይሉ ወዳለበት ክፍለ ከተማ (የመታወቂያ አድራሻ) የሚገኝ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ቢሮ መሄድ ግድ ይል ነበር።

ከነገ በኃላ ግን በየትኛውም አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ መንጃ ፈቃድ ማሳደስ ይቻላል ተብሏል።

ተገልጋዮች በሚቀርባቸው ቅርንጫፍ ፋይላቸው ያለበት ቅርንጫፍ ሳይጠየቅ የጤና ምርመራ ሰርተፍኬትን በመያዝ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እንዲያገኙ መወሰኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።
👍1
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ አዲስ ምልክት አጸደቀ

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የሚሆን አዲስ የደረጃ ምልክት አጽድቋል።

ይህ ምልክት ከዉጪ የሚገቡና የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶች ከሀገር ውስጥ ምርቶች ለመለየት ያስችላል ተብሏል።

በገበያ ላይ ፍትሃዊ የሆነ ውድድር እንዲኖር እንደሚያደርግ እና ሸማቾች የውጭ ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው መምጣታቸውን እንዲያውቁ እንደሚረዳ ተገልጿል።

Capital Newspaper
Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ ጣሉ፤ ኢትዮጵያም 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባታል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ የታሪፍ እርምጃ ወሰዱ። ረቡዕ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ከ20 በላይ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ተዘግቧል ።
የክልል ጊዜያዊ አስተዳደሮች የቆይታ ጊዜ እስከ ሁለት ዓመት እንዲራዘም የሚያስችል አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሎች የሚቋቋም ጊዜያዊ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን፤ለሁለት ጊዜ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲራዘም የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያን አጸደቀ።

የአዋጁ ማሻሻያ፤ ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣን የነበረውን የክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቆይታ ጊዜን የማራዘም ኃላፊነት፤ለምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የሰጠ ነው።

አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚተካ ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ መጽደቁ ተገልጿል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ 23/2017 ዓ. ም. ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ የሥልጣን ዘመኑ የተጠናቀቀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን ለተጨማሪ ዓመት እንዲራዘም የሚያስችል ነው።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጊዜያዊ አስተዳደር የተመሰረተው በ2015 ዓ. ም. የወጣውን ማቋቋሚያ ደንብ መሠረት አድርጎ ነው።

ጊዜያዊ አስተዳደሩን ያቋቋመው ደንብ ደግሞ መሠረት ያደረገው ከ22 ዓመት ገደማ በፊት የጸደቀውን የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግግ አዋጅ ነው።
ይህ አዋጅ የፌደራል መንግሥት በሦስት ሁኔታዎች በክልሎች ውስጥ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ደንግጓል።

በቀዳሚነት የተጠቀሰው ምክንያት በክልሉ ውስጥ የሚፈጠር የጸጥታ መደፍረስ ሲሆን በዚህ ጊዜ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል።
በክልሉ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከተፈጸም እና የክልሉ መንግሥት ድርጊቱን በቁጥጥሩ ሥር ማዋል ካልቻለም ፌደራል መንግሥት ጣልቃ ይገባል።

በአዋጁ ላይ የተጠቀሰው ሦስተኛ ሁኔታ፤ እንደ "በትጥቅ የተደገፈ የአመጽ እንቅስቃሴ" ያሉ ድርጊቶች በሚፈጸሙበት ወቅት የሚከሰት "የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት አደጋ ላይ መውደቅ" ነው።

በእነዚህ ሁኔታዎች መከሰት ምክንያት ወደ በክልሎች ጣልቃ የሚገባው የፌደራል መንግሥት ሊያከናውን ከሚችላቸው ጉዳዮች መካከል "የክልሉን ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል በማገድ ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር" ማቋቋም የሚለው ይገኝበታል።
በዚህ መልኩ የሚቋቋም ጊዜያዊ አስተዳደር የሚቆየው ከሁለት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እንደሆነ አዋጁ ደንግጓል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጊዜያዊ አስተዳደሩን የቆይታ ጊዜ ማራዘም "አስፈላጊ ሆኖ" ካገኘው "ከስድስት ወር ላልበለጠ ጊዜ" ሊያራዝመው እንደሚችልም በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ያጸደቀው አዋጅ፤ በክልሎች ውስጥ የሚመሠረት የጊዜያዊ አስተዳደር የቆይታ ጊዜ ሁለት ጊዜ እንዲራዘም ያስችላል።

"በክልሉ ውስጥ የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ መግባት አስፈላጊ ካደረገው ሁኔታ ውስብስብነት አኳያ አስፈላጊ ሆኖ" ከተገኘ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ እስከ አንድ ዓመት እንዲራዘም ሊደረግ እንደሚችል በአዋጁ ላይ ተጠቅሷል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲራዘም የሚያስፈልግ ከሆነም በድጋሚ "ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እንዲራዘም" ሊደረግ እንደሚችል አዲስ በጸደቀው አዋጅ ላይ ተቀምጧል።

በሥራ ላይ ባለው አዋጅ በክልሎች ውስጥ የሚመሠረት ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ሥልጣን ፌዴሬሽንም ምክር ቤት እንደሆነ ደንግጓል።
አዲሱ ማሻሻያ ረቂቅ በበኩሉ ይህንን ሥልጣን ወደ ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አዘዋውሯል።

አዋጁ የጊዜያዊ አስተዳደርን ቆይታ ጊዜ የማራዘም ሥልጣንን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቢሰጥም፤ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ወቅት ውሳኔው ቀርቦ መጽደቅ እንዳለበት ይደነግጋል።
ምክር ቤት የሚቀርብለትን የቆይታ ጊዜ ማራዘም ውሳኔ ካልተቀበለው፤ "ውሳኔው ውድቅ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ ተደርጎ መደበኛ የክልል መንግሥት አስተዳደር መመሥረት" እንደሚኖርበት በአዋጁ ላይ ተካትቷል።
ጊዜያዊ አስተዳደር በተመለከተ በአፈ ጉባኤው በሚተላለፍ ወይም በምክር ቤቱ በሚጸድቅ ውሳኔ ውስጥ "ጊዜያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ሊመላከቱ" እንደሚችሉ አዋጁ ያስረዳል።

እነዚህ ጉዳዮች "ለፌደራል መንግሥት ጣልቃ መግባት ምክንያት የሆነውን ሁኔታ በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማጽናት አስፈላጊ የሆኑ" ተግባራት እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።
👍1
2025/07/09 15:31:54
Back to Top
HTML Embed Code: