Telegram Web Link
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
#ደቡብ_ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር (ዶር) በጁባ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፓርቲያቸው የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የረጅም ጊዜ ተፎካካሪ የሆኑት ማቻር "20 ከባድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች" በተሳተፉበት ኦፕሬሽን ከቤታቸው ተወስደዋል ሲል ፓርቲያቸው ኤስፒኤልኤም-አይኦ (SPLM-IO) አስታውቋል።

ፓርቲው የፀጥታ ኃላፊዎች "ኢ-ሕገመንግስታዊ ድርጊት" ፈጸመዋል ሲል ድርጊቱን አውግዟል። በተጨማሪም ሪክ ማቻር በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት "ግልፅ አለመሆኑንም" ገልጿል።

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ እስሩ ሀገሪቷን ወደ አዲስ ግጭት እንዳያስገባ አስጠንቅቋል። የድርጅቱ ኃላፊ ኒኮላስ ሃይሶም መሪዎቹ ወደ ሰፊ ግጭት መመለስን ለማስወገድ ራሳቸውን መቆጣጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው፤ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለኪር እና ለማቻር ታማኝ በሆኑ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል። የተፈጠረው ውጥረትም እያየለ ባለበት ወቅት #ኖርዌይ እና #ጀርመን ኤምባሲዎቻቸውን ለጊዜው ዘግተዋል።

ካለፈው ወር ጀምሮ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ከእላኛው ናይል አካባቢ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል ሲል የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።
👍1
የእስራኤል አምባሳደር ከሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ላይ በአፍሪካ ህብረት ተባረሩ

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት አብርሃም ንጉሴ፣ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተካሄደው 31ኛዉ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት እንዲወጡ ተደረገ።

ይህ የሆነው በርካታ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሩ በዚሁ የሐዘን ስነ-ስርዓት ላይ መገኘታቸውን በመቃወማቸው መሆኑ ተዘግቧል ።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦረን ማርሞርስቴይን ድርጊቱን "አሳፋሪ" እና "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ በጽኑ አውግዘዋል።

"በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል አምባሳደር በተጋበዙበት፣ በሩዋንዳ የቱትሲ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ፀረ-እስራኤላዊ የፖለቲካ አመለካከቶችን ማስተዋወቃቸው እጅግ አሳፋሪ ነው" ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ማርሞርስቴይን አክለውም፣ "ይህ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት በመጀመሪያ ደረጃ የተገደሉትን ትውስታ የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ የሩዋንዳ ህዝብን እና የአይሁድ ህዝብን ታሪክ መሠረታዊ ግንዛቤ ማጣቱን ያሳያል።"

የእስራኤል ሚዲያ የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሰዉ እንደዘገቡት ይህ ክስተት በአፍሪካ ህብረት ውስጥ የእስራኤልን አቋምና ከአባል ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ ያለውን ቀጣይ ውጥረት የሚያሳይ ነው ሲሉም አስፍረዋል።
👍2
ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ ዛሬ ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ

በፍቅረኛው ሞዴል ቀነኒ አዱኛ ግድያ ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ታዋቂው የኦሮምኛ ቋንቋ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሲቀርብ ፖሊስ በተሰጡት ባለፉት 12 ቀናት አከናወንኩ ያላቸውን የምርመራ ስራዎች ለችሎት አቅርቧል፡፡

ፖሊስ በእነዚህ ቀናት ተጨማሪ የ15 ምስክሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ የ28 ሰዎች የምስክር ቃል ማሰባሰቡን ዛሬ አሳውቋል፡፡ ከመኖሪያ ቤታቸው በተወሰደ ምንጣፍ እና ናሙና ላይ ለፌዴራል ፖሊስ የተላከ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤትና በተጠርጣሪው ስልክ ላይ በብሔራዊ መረጃ ደህንነት በኩል የሚደረጉ የምርመራ ውጤቶች አሁንም ድረስ እንዳልደረሱለት ያሳወቀው ፖሊስ የሆስፒታሎች ማስረጃዎችን በእነዚህ ጊዜያት ማሰባሰብ ቢችልም የባለሙያ ትንተና እና የታክቲክና ቴክኒክ ምርመራዎች እንደሚቀሩት ገልጿል፡፡ በመሆኑም ተጨማሪ የሰውና ሰነድ ማስረጃዎችን ለማጠናከር የ14 ቀናት የምርመራ ቀናት እንደሚያስፈልገው መርማሪ ፖሊስ ችሎቱን ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል የተጠርጣሪው አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጠበቃ “ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜያትን እየጠየቀ ያለው ከዚህ በፊት ካቀረባቸው ምክንያቶች ተመሳሳይ ነው” በማለት “ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ መጠየቁን” በመቃወም ከዚህ በፊት ተገኘ የተባለው የሆስፒታል ምርመራ “ተጠርጣሪዋ ከከፍታ ቦታ ወድቃ ህይወቷ ማለፉ ከመገለጹ ውጪ በሰውነቷ ላይ የተገኘ የተቦጫጨረ ነገር አለመኖሩ እራሷን ለማጥፋቷ ማሳያ በመሆኑ የተጠርጣሪው የዋስትና መብት ሊጠበቅ ይገባል” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ጠበቃው “ከሟች የግል ማህደር መረዳት እንደተቻለው ከዚህ በፊት ከመጠን በላይ የመድኃኒት ዶዝ መውሰድን ጨምሮ እራሷን ለማጥፋት ብዙ ሞክራለች” በማለት ይህንኑ ለጓደኞቿ መግለጿን እና ህልፈቷም ከዚሁ ራስን ከማጥፋት ጋር ልያያዝ እንደምችል ለችሎት አብራርተዋል፡፡ ጠበቃው “አርቲስቱ ከእስር ወጥቶ ለፋሲካ በዓል የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ማቀዱን በመግለጽ” የችሎት ሂደቱን አዛብተው ያልተባለውን እንደተባለ አድርገው “ስም በማጥፋት ላይ ተሰማርተው ለሚዘግቡ” መገናኛ ብዙኃን ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

ችሎቱ በፖሊስ እና ጠበቃ በኩል የቀረቡትን ሃሳቦች መርምሮ ብይን ለመስጠት ለነገ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ጠዋት 3፡30 ቀጥሯል፡፡
👍4
#update

ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በይፋ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሆኑ

ሹመቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያጋሩት መልእክት ሙሉ ይዘት ከስር ተያይዟል።

ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነት እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል:: የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ግዝያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል::

ዛሬ በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩን እና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል። ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው:: ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው:: አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምነት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።
በትግራይ ክልል ከአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ዳኞች ጫና እየበረታባቸው ነው ሲል ማህበሩ አስታወቀ

በትግራይ ክልል ከአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ዳኞች እየደረሰባቸው ያለው ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫናዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፣ አሳሳቢ ሁነዋል ሲል የትግራይ የዳኞች ማህበር መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

“በአሁኑ ወቅት በተለይም ደግሞ ባለፉት ሁለት አመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በትግራይ በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር እና ግድያዎች ተበራክተዋል” ሰል ማህበሩ በመግለጫው ጠቁሟል።

“እነዚህን ወንጀሎች በፈጸሙ ተጠርጣሪዎች እና ከሳሾች ዙሪያ ያሉትን ጉዳዮች የሚሰሙ ዳኞች ከፍርድ ሂደቱ በኋላም ሆነ በፍርድ ሂደቱ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል” ሲል አሳስቧል፤ “ለደህንነታቸው በመስጋት አንሰራም ሊሉ ስለሚችሉ የሚመለከተው አካል ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ጋር ልዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ እንዲሰራ” ጠይቋል።  
👍1😁1
ቃል የተገቡባቸው ነጥቦች።

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያው አስተዳደር ፕሬዚደንት ሆነው ሲሾሙ በስልጣን ቆይታቸው ከላይ የተያያዙትን ነጥቦች ለማስፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አቶ ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በፊርማቸው ቃል ገብተዋል።
በእንግሊዝ አንዲት ሴት በተተከለላት ማህፀን ተጠቅማ  ልጅ መውለዷ ተአምር ተብሏል

በእንግሊዝ የሕክምና ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አንዲት ሴት ከእህቷ ማህፀን ከተቀበለች በኋላ ጤናማ ሴት ልጅ ወልዳለች።

ግሬስ ዴቪድሰን (36 ዓመቷ) ማየር-ሮኪታንስኪ-ኩስተር-ሃውዘር  ሲንድረም የተባለ ያልተለመደ በሽታ ይዛ የተወለደች ሲሆን ይህም የሚሰራ ማህፀን እንዳይኖራት አድርጓታል። እ.ኤ.አ. በ2023፣ በኦክስፎርድ በሚገኘው ቸርችል ሆስፒታል ውስጥ ለ17 ሰአታት በፈጀ እና ታሪክ በሰበረ ቀዶ ጥገና የእህቷ ኤሚ ፑርዲ የለገሰችውን ማህፀን በተሳካ ሁኔታ ተቀበለች ።

ከአንድ አመት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ግሬስ የካቲት 27 ቀን በለንደን በሚገኘው ንግስት ሻርሎት እና ቼልሲ ሆስፒታል በቄሳሪያን ቀዶ ጥገና ኤሚ ኢዛቤል የተባለች ሴት ልጅ ወልዳለች።

ስሙ የሕፃኗን አክስት እና የማህፀን ለጋሽ የሆነችውን ኤሚን እንዲሁም የሕክምና ቡድኑን የመሩትን የትራንስፕላንት ቀዶ ሐኪም ኢዛቤል ኪሮጋን ያስታውሳል።
ግሬስ ሴት ልጇን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታቅፍ “እውን መሆኗን ማመን ከባድ ነበር።በጣም ድንቅ ነበር።” ብላለች።
👍1
ባለስልጣኑ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ለጋዜጠኞች የሙያ ማረጋገጫ የመስጠት ስልጣን የለዉም አለ
ፌደራል ፖሊስ በዮሃንስ ቧያሌውና ክርስቲያን ታደለ
ጉዳይ ስዩም ተሾመን ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ አለመቻሉን ገለፀ

“እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ"

አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና ክርስቲያን ታደለን በተመለከተ አቶ ስዩም ተሾመ “ባደረጉት ንግግር ተከሰው” ለችሎት እንዲያቀርባቸው በፍርድ ቤቱ የታዘዘው ፌዴራል ፖሊስ፤ “አድራሻው ስላልተገለፀልኝ ላቀርበው አልቻልኩም” የሚል ምላሽ መስጠቱን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

የተከሳሾች ጠበቃው፤ አቶ ስዩም ተሾመ የተባሉት ግለሰብ ትናንት መጋቢት 30 በተካሄደው ችሎት እንዲቀርቡ የታዘዘው፤ የሽብር ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙትን የአማራ ክልል የምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለውን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉን አቶ ክርስቲያን ታደለን ስም በመጥቀስ፣ መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በቻናላቸው ባስተላለፉት ፕሮግራም ምክንያት ነው ብለዋል።

አቶ ስዩም በፕሮግራሙ ተከሳሾቹ አቶ ዮሃንስ እና ክርስቲያን “ታጥቀው መንግስት እንገለብጣለን ብለዋል፣ የአማራን ወጣት አስፈጅተዋል፣ ድሽቃ መሣሪያ መግዣ ጠይቀዋል” የሚል ንግግር በማድረጋቸው፣ “በፍርድ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር በችሎት መድፈር” መከሰሳቸውን ጠበቃ ገዛኸኝ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ስዩም ተሾመን ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያቀርብ ለፌዴራል ፖሊስ ትዕዛዝ ቢሰጥም ሳይገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

በችሎቱ ላይ የቀረቡት አቶ ዮሐንስ ቧያሌው፤ “ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሼው ተቀጥቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው፤ ትምህርት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው አሁንም ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀመው” ብለዋል፤ ሲሉ ጠበቃቸው ተናግረዋል።

አቶ ዮሃንስ አክለውም፤ “መንግስት ቤት የሰጣቸው፣ ደሞዝ የሚከፍላቸውና መኪና የተሰጣቸው የመንግስት አክቲቪስት ናቸው። አማራ ሲሆን የትም ይገኛል። ደብል ስታንዳርድ ነው” በማለት የፌደራል ፖሊስ የሰጠውን መልስ “አሳማኝ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው ተከሳሽ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው፤ የፌዴራል ፖሊስ የአቶ ስዩም ተሾመ አድራሻቸውን አላውቀውም ማለቱ “ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም የሚለውን አባባል እውነተኝነት ያሳያል” ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም፤ “እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ። የመንግስት ሹመኛን የሚጠብቀው የፌደራል ፖሊስ አካል ነው። እኛን የህዝብ እንደራሴዎችን ከቤተሰባችን ፊት ደብድቦና አዋርዶ ለማምጣት ያልተቸገረው ፌዴራል ፖሊስ፣ ላገኛቸው አልቻልኩም ማለቱ ስላቅ ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

በመጨረሻም የተከሳሾች ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የተላለፈው ፕሮግራም ሕግን የተላለፈ መሆኑን ጠቅሰው፤ ፖሊስ ያለምንም ምክንያት አቶ ስዩም ተሾመን እንዲያቀርብ ይደረግልን ማለታቸውን ጠበቃው ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

ፍርድ ቤቱም በድጋሚ የፌደራል ፖሊስ ስዩም ተሾመን በችሎቱ እንዲያቀርብ ለሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ተመላክቷል።

አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስትያን ታደለን ጨምሮ 52 ግለሰቦች በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ውለው የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው በሆኑበት በዚህ የክስ መዝገብ ሥር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስትያን ታደለ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ካሳ ተሻገር፣ አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ ዘመነ ካሴ እና ዶክተር ጫኔ ከበደ ይገኙበታል።

ለተከሳሾችና ጠበቆቻቸው የደረሰው የክስ ዝርዝር ተከሳሾች “የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም” ተሰባስበው መምራት የሚል ክስ ነው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ክሱን አስመልክቶ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ግለሰቦቹ ክስ የተመሠረተባቸው “የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈጸም በማሰብ ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ጋር በመደራጀት” ነው።

“የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸዉን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስና አገር ‘በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት’ በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል” የሚል ሀሳብ በክሱ ውስጥ እንደተካተተም ቢሮው ማስታወቁ ይታወቃል።

(አዲስ ስታንዳርድ)
1👏1
ለአለም ገበያ ንቀቷን አሳይታለች ያሉት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና ላይ ወዲያው ተግባራዊ የሚደረግ የ125 በመቶ ታሪፍ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።

ቀደም ብሎ ቻይና በአሜሪካ ከኤፕሪል 2 ቀን አንስቶ ለተጣለባት የ34 በመቶ ተጨማሪ ቀረጥ/ታሪፍ ምላሽ እንዲሆን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በአሜሪካ እቃዎች ላይ የ34 በመቶ ታሪፍ መተግበር ጀምራ ነበር።

ሆኖም ፕሬዝደንት ትራምፕ ቻይና እቅዷን የማታጥፍ ከሆነ ተጨማሪ 50 በመቶ ታሪፍ እጥላለው ብለው ነበር።

ይሄም ባለፈው የካቲት ተጥሎ ከነበረው 20 በመቶ ጋር ሲደመር አሜሪካ ቻይና ላይ በሳምንታት ውስጥ የምትጥለው ቀረጥ 104 በመቶ እንደሚደርስ ሲገለፅ ነበር።

ሆኖም ፕሬዝደንት ትራም በማህበራዊ ገፃቸው ይፋ ባደረጉት አዲስ ውሳኔ ቀረጡ ወደ 125 በመቶ ከፍ ብሏል።

ለዚህም ቻይና የአለምን ገበያ ንቃለች ሲሉ ነው የተናገሩት።

በርግጥ ቻይና ከጣለችው አቻ የቀረጥ ምላሽ በተጨማሪ አንዳንድ የአሜሪካ ኩባንያዎችን ማገድ እንዲሆም ሌላ የፖሊሲ መላ መተግበሯ የአሜሪካውን መሪ ሲያበሳጭ የቆየ ጉዳይ ነው።

በተያያዘ ፕሬዝደንቱ ወደ 75 የሚሆኑ አገራት ለመደራደር ፍላጎታቸውን መግለፃቸውን የተናገሩ ሲሆን።

አሜሪካ ለጣለችው ታሪፍ መሰል ምላሽ አልሰጡም ላሏቸው አገራት ለመደራደር የ90 ቀን እፎይታ ሰጥቻለው ብለዋል።

በእፎይታው መሰረት ከቻይና በስተቀር ሁሉም አገራት የ10 በመቶ ታሪፍ ይተገበርባቸዋል።
ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት❗️

የኢንተርኔት አጠቃቀም በየቀኑ እየጨመረ በሄደበት በዚህ ዘመን፣ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችም እየተስፋፉ ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅርቡ በርካታ አደገኛ የኢንተርኔት አድራሻዎችን (URLs) መርምሮ፣ እነዚህ አድራሻዎች ለሀገራችን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በይበልጥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች አካውንቶችን በመንጠቅ ከፍተኛ ስጋት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አረጋግጧል።

ከተለያዩ አካላት በቴሌግራም የሚደርሱ ሊንኮች በርካታ አደጋዎችን የሚይዙ ሲሆን፣ የሚከተሉት አደጋዎች በዋናነት ይገኙበታል፡፡

👉የግል መረጃ መጠለፍ:- እንደ የባንክ መለያ ወይም የይለፍ ቃል ያሉ መረጃዎችን መሰረቅ፤

👉የማልዌር ስርጭት:- ስልኮችን ወይም ኮምፒውተሮችን የሚጎዱ ቫይረሶች፤

👉ማጭበርበሪያ:- ተጠቃሚዎችን በሀሰተኛ ተስፋዎች (እንደ ውርርድ ወይም ኢንቨስትመንት) መታለል፤

በመሆኑም ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባወጣው መረጃ አሳስቧል።

ሰሞኑን በቴሌግራም ከሚላኩና በፍጹም መከፈት የሌለባቸውን ሊንኮች አስተዳደሩ በምስል አጋርቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቴሌግራም አጠራጣሪ የሆኑ ሊንኮች ካጋጠሙ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ e-mail [email protected] እና 933 ነጻ የስልክ መስመር ማሳወቅ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
👍3
ጌታቸው ረዳ የቀድሞ የትግራይ አመራሮችንና የሕወሓትን የሥልጣን ጥማት ተቹ

የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ ለቢቢሲ ፎከስ ኦፍ አፍሪካ በሰጡት ቃለ ምልልስ የቀድሞ የክልሉ የጸጥታ ሃላፊና ምክትል ፕሬዝዳንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነቶች በአግባቡ መወጣት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ጌታቸው ጀኔራል ታደሠ ያከናወኗቸው ተግባራት በውድቀት የተሞሉ እንደነበሩ በመግለጽ በወቅቱ ከኃላፊነታቸው አለማንሳታቸው የገዛ ውድቀታቸው እንደሆነም አመልክተዋል።

በተጨማሪም ጌታቸው ሥልጣንን በጠቅላላ ለመቆጣጠር ከሚፈልገው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከሚመራው የሕወሓት አንጃ የሚመጣው ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የሥልጣን ጥማት ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ተግዳሮት ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጀኔራል ታደሠ ከሌሎች ሥልጣን ፈላጊ የሕወሓት ሰዎች የተሻሉ እንደሆኑ ለማሳመን እንደሞከሩና የሹመታቸውም ውሳኔ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደነበር ጌታቸው አስረድተዋል።

የትግራይን ፖለቲካ ይበልጥ አስቸጋሪ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል በመንግሥት ሥር መሆን የነበረበት ሠራዊት እስካሁን ድረስ ራሱን የቻለ አካል አድርጎ መቆጠሩ ዋነኛው ችግር እንደሆነ ጌታቸው አንስተዋል።

ኤርትራን በተመለከተም በእሳቸው አስተዳደር ውስጥ የነበሩ የተወሰኑ ግለሰቦች ከኤርትራ መንግሥት ጋር በሕገወጥ መንገድ ለመገናኘት ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር ጌታቸው ረዳ በቃለ ምልልሳቸው ላይ ገልጸዋል።
👍1
በዋስ የተለቀቀው ተጠርጣሪ ዳግም ታፈነ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ ለአሥር ወራት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቆየው ሚካኤል መላክ የተባለው ተከሳሽ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በ300 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ቢወሰንም፣ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ እንደገና መታፈኑን ቤተሰቦቹ ገለጹ።

ቤተሰቦቹ እና የዓይን እማኝ ነኝ ያሉ አንድ የቅርብ ሰው ለመሠረት ሚድያ እንደተናገሩት፣ ሚካኤል ዛሬ ከቂሊንጦ ሲፈታ ባልታወቁ ሰዎች በኃይል ወደ መኪና ተጭኖ ተወስዷል።

በተለይም የተከሳሹን ክስ የያዘው ዓቃቢ ሕግ ናትናኤል ስንታየሁ ከታጋቾቹ መካከል እንደነበር የዓይን እማኙ ተናግረዋል።

ቤተሰቦቹ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎችና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ ቤቶች ቢጠይቁም እስካሁን አድራሻውን ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

አቶ ሚካኤል መላክ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ታጣቂ ቡድን በሚዲያ ታግዛለህ በሚል ከሰኔ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአሥር ወራት በእስር ላይ ቆይቷል። ቀደም ሲልም በ2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጉዳይ ከዚህ በፊት ለወራት ታስሮ እንደነበር ይታወሳል ሲል የዘገበው መሰረት ሚዲያ ነዉ።
👍1
ሲፒጄ ኢትዮጵያ በኢቢኤስ ጋዜጠኞች ላይ የከፈተችውን ምርመራ እንድታቆም ጠየቀ

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግሥት በሰባት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ኢቢኤስ) የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ላይ የከፈተውን የሽብር ወንጀል ምርመራ በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪ አቀረበ።

ፖሊስ ጋዜጠኞቹ ግጭት ለመቀስቀስ፣ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማናጋት እንዲሁም በአማራ ክልል ከሚገኙ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር በመመሳጠር መንግሥትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል ክስ ጋዜጠኞቹ ነቢዩ ጥዑመልሳን፣ ታሪኩ ኃይሌ፣ ኅሊና ታረቀኝ፣ ንጥር ደረጀ፣ ግርማ ተፈራ፣ ኄኖክ አባተ እና ሐብታሙ ዓለማየሁን ማሰሩን ሲፒጄ በሰጠው መግለጫ አውግዟል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ቢሮ ሃላፊ ሙቶኪ ሙሞ በሰጡት አስተያየት፣ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በጣቢያው ላይ እርምጃ በወሰደበት ሁኔታ፣ በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ላይ ለታየ ግድፈት ጋዜጠኞችን በሽብር ወንጀል ማሰር ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ነው ብለዋል።

ሲፒጄ መንግሥት ጋዜጠኞቹን በአስቸኳይ እንዲፈታና ክሱን እንዲያቋርጥ አሳስቧል።
👍1
" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወታደሮችን ለፖለቲካ ካላስገዛ ወታደራዊ አገዛዝ ይሆናል" ገብሩ አሥራት

የቀድሞ ታጋይና የአረና ፖለቲካ ፓርቲ መስራች አቶ ገብሩ አሥራት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ወታደሮችንና ታጣቂዎችን ለፖለቲካው ሥልጣን ተገዢ ካላደረጉና አሮጌው አካሄድ ከቀጠለ ሥርዓቱ ወታደራዊ አገዛዝ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።

አቶ ገብሩ ይህንን አስተያየት የሰጡት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ከቆዩት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሥልጣን ርክክብ ማድረጋቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ነው። ሌተና ጄኔራል ታደሰ پیش از این የትግራይ ኃይሎችን ወክለው በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንትና የካቢኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሥልጣን ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፣ ይህ የሥልጣን ሽግግር በአዲስና ሰላማዊ መንገድ መከናወኑ አዲስ ባህል መሆኑን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ አቶ ገብሩ አሥራት አዲሱ ፕሬዚዳንት ወታደራዊ ኃይሎችን በፖለቲካ ቁጥጥር ሥር ካላዋሉ ሥርዓቱ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ሊያመራ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።
እስከ ምሽት 4 ሰዓት አገልግሎት ሳይሰጡና ከታሪፍ ውጪ የሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ እርምጃ ይወሰዳል

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት ሳይሰጡ የሚያቋርጡ እና ከተፈቀደው የታሪፍ ዋጋ ውጪ ህዝቡን የሚያስከፍሉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ቢሮው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በደንብ ቁጥር 185/2017 መሰረት ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅበት ገልጿል።

በተጨማሪም ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በፊት አገልግሎቱን ማቋረጥ፣ ከተፈቀደለት መስመር ውጪ መስራት፣ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ አለማድረስ እንዲሁም ቢሮው ከወሰነው ህጋዊ ታሪፍ ውጪ ማስከፈል እንደማይችል አሳስቧል።

በዚህ ደንብ ላይ የተቀመጡትን ክልከላዎች ተግባራዊ የማያደርጉ እና ከቢሮው መመሪያ ውጪ በህገ-ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ባለቤቶችና ሹፌሮች ላይ በደንቡ በተቀመጠው የቅጣት እርከን መሰረት የ5 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚጣል ተገልጿል።

ህብረተሰቡም አገልግሎቱን በሚያደናቅፉ ህገ-ወጥ አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥመው በነፃ የስልክ መስመር 9417 በመደወል ወይም በአቅራቢያው በሚገኝ የትራንስፖርት ቢሮ በመሄድ የተሽከርካሪውን ሰሌዳ ቁጥርና ሰዓት በመያዝ ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ቢሮው አሳውቋል።
👍1
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ነዳጅን ሙሉ በሙሉ በባቡር ለማጓጓዝ በዝግጅት ላይ ነው

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር በመጪው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅን ሙሉ በሙሉ በባቡር ለማጓጓዝ የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሙና አህመድ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጹት፣ በየጊዜው የሚታየውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ድርጅቱ በቀን አስር ጊዜ የባቡር ትራንስፖርት በመጠቀም ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ ዝግጁ ነው።

ነዳጁ ከጅቡቲ ከተጓጓዘ በኋላ አዋሽ በሚገኘው ማከማቻ ጣቢያ እንዲራገፍ ይደረጋል ተብሏል። በዚህም በዓመት እስከ 4.2 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ለማጓጓዝ እቅድ ተይዟል።

የባቡር መስመሩ ከአዋሽ እስከ ጅቡቲ ድረስ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ቢሆንም፣ ከጅቡቲ በኩል ያለው ግንባታ ሲጠናቀቅ በመጪው ዓመት ሙሉ በሙሉ ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ድርጅቱ የባቡር ጉዞውን በ18 ሰዓታት ውስጥ በማጠናቀቅ የታቀደውን የነዳጅ መጠን በዓመት ውስጥ ለማጓጓዝ አቅዷል።
2
የአማዞን አክሲዮን በቻይና ሻጮች የዋጋ ጭማሪ ማስፈራሪያ ምክንያት ቀንሷል

በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ምርቶች ላይ የጣለው "ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ" የታሪፍ ጭማሪን በመቃወም በአማዞን ላይ የሚሸጡ የቻይና ሻጮች ዋጋቸውን ለመጨመር ወይም ከአሜሪካ ገበያ ለመውጣት ማስፈራሪያ ከሰነዘሩ በኋላ የአማዞን አክሲዮን -5.17% ዛሬ ቀንሷል።

ሮይተርስ እንደዘገበው፣ በአማዞን ላይ ምርቶቻቸውን የሚሸጡ የቻይና ኩባንያዎች ለአሜሪካ ሸማቾች ዋጋቸውን ለመጨመር ወይም ሙሉ በሙሉ ከአሜሪካ ገበያ ለመውጣት እቅድ አላቸው።

አንዳንድ ሻጮች ቀድሞውንም ዋጋቸውን እስከ 30% ከፍ እንዳደረጉ እና በአማዞን ማስታወቂያ ላይ የሚያወጡትን ወጪ እንደቀነሱ ተዘግቧል። ሌሎች ገበያዎች ምርቶቻቸውን ሊቀይሩባቸው የሚችሉባቸው ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አውሮፓ ይገኙበታል።

ይህ እርምጃ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቻይና በስተቀር በሁሉም ሀገራት ላይ የጣሉትን የንግድ ታሪፍ ቆም ካደረጉ በኋላ የመጣ ሲሆን፣ ቻይና በአሁኑ ጊዜ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ 125% ከፍተኛ የታክስ መጠን እየገጠማት ነው። በሁለቱ የዓለም ትላልቅ ኢኮኖሚዎች መካከል ያለው የንግድ ግጭት ከዚህም የከፋ ሊሆን ይችላል።

የቻይና ትልቁ የኢ-ኮሜርስ ማህበር የሆነው የሼንዘን የድንበር ተሻጋሪ ኢ-ኮሜርስ ማህበር ኃላፊ ዋንግ ዢን ለሮይተርስ እንደተናገሩት የቻይና አቅራቢዎች "ጠቅላላ የዋጋ መዋቅር" ሙሉ በሙሉ እየተናጋ ነው።

ማህበሩ በጉምሩክ መዘግየት እና ከፍተኛ የሎጂስቲክስ እና የአቅርቦት ሰንሰለት ወጪዎች እየተጠቁ ያሉ ከ3,000 በላይ የአማዞን ሻጮችን ይወክላል።
Join Us @Hulaadiss
የአውሮፓ ህብረት በአሜሪካ እቃዎች ላይ የጣለውን ታሪፍ ለ90 ቀናት አገደ

የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ላይን ዶናልድ ትራምፕ በንግድ ጦርነታቸው ላይ ባሳዩት ድራማዊ ማሽቆልቆል ምክንያት በአሜሪካ እቃዎች ላይ የጣለውን የ25% የበቀል ታሪፍ ለ90 ቀናት ማገዱን አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እንዳሉት ህብረቱ ረቡዕ እለት በ21 ቢሊዮን ዩሮ (18 ቢሊዮን ፓውንድ) የአሜሪካ እቃዎች ላይ የጣለውን የ25% የመልሶ ማጥቃት ታሪፍ ለ90 ቀናት ያቆማል። "ድርድር እድል እንዲያገኝ እንፈልጋለን" ብለዋል። "ድርድሩ አጥጋቢ ካልሆነ፣ የመልሶ ማጥቃት እርምጃዎቻችን ተግባራዊ ይሆናሉ።"

ቀደም ሲል የአውሮፓ ህብረት የመልሶ ማጥቃት እርምጃዎችን ባልጠቀሰ መግለጫ ላይ ቮን ደር ላይን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከፍተኛ ታሪፋቸውን ለ90 ቀናት ማቆማቸውን በደስታ ተቀብለዋል፤ የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካ ጋር የንግድ ስምምነት ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ደግመው አረጋግጠዋል።

Join Us @Hulaadiss
2025/07/09 09:44:16
Back to Top
HTML Embed Code: