በህወሓት አመራሮች ላይ ክስ ተመሰረተ‼️
18 ከፍተኛ የትግራይ አመራሮችን ጨምሮ በዘር ማጥፋት ወንጀል 64 ሰዎች ተከሰሱ!
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ 18 ከፍተኛ የትግራይ የፖለቲካ እና የጦር መሪዎች በፌደራል መንግስት በተሾሙ 64 የጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ከጥቅምት 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም ድረስ በነበረው የትግራይ ደም አፋሳሽ ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ሚያዝያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለጠቅላይ የምርመራ መምሪያ የቀረበው የጽሁፍ ክስ እንዳመለከተው የተጠቀሱት ተከሳሾች በጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል።
ክሱ የቀረበው በአቶ አበራ ንጉስ የተባሉ የህግ ምሁር እና ጠበቃ እንዲሁም ከጥቅምት እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም በፌደራል መንግስት በተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉ ግለሰብ ናቸው።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽንን ልትቀላቀል ነው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (AFC) መቋቋሚያ ስምምነት ላይ ተወያይቶ ለማጽደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
ይህ ኮርፖሬሽን በመሠረተ ልማት፣ በተፈጥሮ ሀብትና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለግል አልሚዎችና ለመንግሥት አካላት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ ነው።
ኢትዮጵያ የዚህ ተቋም አባል በመሆን ለግሉ ዘርፍ ተጨማሪ የፋይናንስ አማራጮችን ታገኛለች። ይህም የግሉ ዘርፍ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን አንቀሳቃሽነት ሚና በማሳደግ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠንና ድህነትን ለመቀነስ ጠቃሚ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
አፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ልማት ለማፋጠን የተቋቋመ የፓን-አፍሪካ የፋይናንስ ተቋም ነው። ኮርፖሬሽኑ በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ፣ የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠትና የፋይናንስ መፍትሄዎችን በመቅረብ የአፍሪካን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ያለመ ነው።

ጣሊያንና የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ድጋፍ አደረጉ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጣሊያን መንግሥት ያገኘውን 11.5 ሚሊዮን ዩሮ ለአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም ከዓለም ባንክ ያገኘውን 38.1 ሚሊዮን ኤስ.ዲ.አር ለመማር ማስተማር ማጎልበቻ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውሉ የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶችን አጽድቋል።
ሁለቱም ብድሮች ምቹ የክፍያ ጊዜ ያላቸውና ያለወለድ በመሆናቸው ምክር ቤቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል።

ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና የዕቃዎች ቀረጥ ቅናሽ ደንብ ጸደቀ
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ለማስፈጸም የቀረበው የዕቃዎች ቀረጥ ምጣኔ ቅነሳ ደንብ በምክር ቤቱ ጸድቋል።
ይህ ደንብ በአባል ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን የሚያሳልጥና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንን የሚያበረታታ በመሆኑ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል።

በትራንስፖርትና ሲቪል ማህበረሰብ አገልግሎቶች የአገልግሎት ክፍያ ተወሰነ
ምክር ቤቱ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረቡ ሁለት ረቂቅ ደንቦችን አጽድቋል።
ክፍያው ተቋማቱ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡና የዜጎችን ተደራሽነት ባገናዘበ መልኩ እንዲሆን ታስቧል።

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሊኖራቸዉን ነው
የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
ይህ አሠራር የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የሪል ስቴት ዘርፉን ለማነቃቃት ይጠቅማል ተብሏል።

ከኦስትሪያ ጋር የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ሊጸድቅ ነው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከኦስትሪያ መንግሥት ጋር የተፈረመውን የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ለማጽደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
ይህ ስምምነት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከማጠናከሩም በላይ ለአየር መንገዳችን የገበያ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

በአዲስ አበባ ተማሪን በኃይል የደበደበች
መምህርት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች
በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰላም በር ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍል ተማሪን የቤት ስራ ባለመስራቷ ምክንያት በሌሎች ተማሪዎች እጅ አስይዛ ሽንቷ እስኪያመልጣት ድረስ የደበደበች መምህርት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ ይህን አሳዛኝ ድርጊት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን መምህሯን በቁጥጥር ስር አውሏል። በተጨማሪም መምህሯ ከትምህርት ቤቱ እንደሚባረሩ ምንጮች ጠቁመዋል።
የተማሪዋ ወላጆች ለደረሰባት የስነ ልቦና እና የጤና ጉዳት ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ምንም እንኳን አንዳንድ ወላጆች አስተማሪዎች ተማሪዎችን በመጠኑ የመገሰጽና የመቅጣት መብት እንዳላቸው ቢስማሙም፣ ይህ የተፈፀመው ድብደባ ግን ከልክ ያለፈና ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑን አውግዘዋል።
አስተማሪዎች የተማሪዎችን ስነ ምግባር የማስተካከል ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ ተማሪዎችን በኃይል ማከም በፍጹም ተገቢ አይደለም የሚል አስተያየት በህብረተሰቡ ውስጥ እየተሰነዘረ ይገኛል።
ይህ ክስተት በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሪዎችን ደህንነት መጠበቅና አስተማሪዎች በስነ ልቦና ላይ ጉዳት የማያደርስ የቅጣት ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል።
ፖሊስ ጉዳዩን በዝርዝር እያጣራ ሲሆን ተገቢው የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ (EIB) ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር አምብሮይዝ ፋዮል ጋር ተገናኝተው በልማትና ኢንቨስትመንት ትብብር ላይ ገንቢ ውይይት አካሄዱ።
ሚኒስትሩ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ (EIB) ለኢትዮጵያ በተለይም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ድጋፍ፣ የውሃ፣ የንጽህና እና የጤና አጠባበቅ እንዲሁም የሴቶች የስራ ፈጠራ ልማት ላደረገው ቀጣይነት ያለው እና ጽኑ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ ድጋፍ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገትና ማህበራዊ ልማት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ተናግረዋል።
የ EIB ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ባንኩ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ልማትና እድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች በኢትዮጵያ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህ ቁርጠኝነት ለአዲሱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት የፋይናንስ አማራጮችን መመርመርንም ያካትታል።
ሁለቱም ወገኖች የ EIB ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ወቅት ለቀጣይ ትብብር የሚሆኑ መስኮችና ዕድሎች ላይ ለመወያየት ተስማምተዋል።

በዓለም ላይ በየአመቱ ወደ 76ሺህ የሚጠጉ እናቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የደም ግፊት ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ
ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚከሰት የደም ግፊት በኢትዮጵያ ከከፍተኛ የደምም መፍሰስ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ የእናቶች ሞት መንስኤ መሆኑ ተገልጿል ።
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ምን ያህል እናቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ በደም ግፊት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተለይቶ የተቀመጠ ቁጥር ባይኖርም በዓለም ላይ በየዓመቱ 76ሺህ የሚጠጉ እናቶችና 500ሺህ ጨቅላ ህፃናት ህይወታቸዉን እንደሚያጡ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ጤና ቴክኒካል አድቫይዘር እና የፅንስና ማህፀን ስፔሻሊስት ዶክተር ሀሰን መሀመድ ተናግረዋል ።

ከዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን አንስቶ ብሄራዊ ባንክ የኤክስፖርት ቡና ፈቃድ መስጠት አቆመ።
አዲስ በሚተገረው አሰራር ባንኮች እና ቡና እና ሻይ ሃላፊነቱን ተረክበዋል።ከ27 አመታት በፊት ስራ ላይ ውሎ በነበረው የብሄራዊ ባንክ መመሪያ ኮንትራት ምዝገባ እና የጭነት ፍቃድ የሚሰጠው ማእከላዊ ባንኩ ብቻ እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም የኢኮኖሚ መከፈቱን ተከትሎ እየተተገበሩ ባሉ ለውጦች መሰረት የቡና ኮንትራት ምዝገባ ወደ ኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስስልጣን ተደርጓል።በተመሳሳይ ከዛሬ ጀምሮ የቡና ጭነት ፈቃድ በንግድ ባንኮች የሚሰራ ይሆናል።
በ1990 ዓም የወጣው የብሄራዊ ባንክ መመሪያ የንግድ ባንኮች እንደ ብሄራዊ ባንክ በመሆን ከቡና በስተቀር ለሁሉም ገቢ/ወጪ ምርቶች ፈቃድ እንዲሰጡ የሚፈቅድ ነው።
[ቅዳሜገበያ]

የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥን የሚፈቅድ አዲስ መመሪያ ጸደቀ
በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎችን የመለያ ቁጥር ሰሌዳዎች ለመቀየር የሚያስችል አዲስ መመሪያ በቁጥር 1050/2017 ጸደቀ። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ አቶ ከድልማግስት ኢብራሂም ለዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በሰጡት ማብራሪያ፣ የሰሌዳ ለውጡ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለማክበር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ከድልማግስት አክለውም ከዚህ ቀደም የነበረው የአሰራር ክፍተት፣ የሀብት ብክነት፣ የሲስተም ድጋፍ የሌለው አሰራር እንዲሁም የተላላፊ እና ቋሚ ሰሌዳዎች ለሐሰተኛ ሰሌዳ ስራ ተጋላጭ መሆን ለውጡ ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የተሽከርካሪ ሰሌዳ አመራረት፣ ስርጭት እና አወጋገድ ላይ የነበሩ ችግሮችም ለውጡ አስፈላጊ እንዲሆን እንዳደረጉ አመልክተዋል። እንደ ሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ አዲሱ መመሪያ እነዚህን ችግሮች እንደሚፈታ ይጠበቃል።

በአዲስ አበባ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ብስክሌቶች፤ ከተመረቱ ሁለት ዓመት ያላለፋቸው መሆን እንደሚገባ የሚያዝ ደንብ ተግባራዊ ሆነ
በአዲስ አበባ ከተማ በብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የስራ ፈቃድ የሚጠይቅ ሰው፤ 300 እና ከዚያ በላይ ብስክሌቶች ለአገልግሎት ማቅረብ የሚችል መሆን እንዳለበት የሚደነግግ ደንብ ስራ ላይ ዋለ።
ለአገልግሎት የሚቀርበው ብስክሌት ደረጃውን የጠበቀ ጂፔኤስ የተገጠለመት እና የተመረተበት ዘመን ከሁለት ዓመት ያልበለጠ መሆን አንዳለበትም አዲሱ ደንቡ ይደነግጋል።
“የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም” የተሰኘ መጠሪያ ያለው ይህ ደንብ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የጸደቀው ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ነበር። ደንቡን ማዘጋጀት ካስፈለገባቸው ምክንያቶች አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ የተሽከርካሪ ቁጥር “በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ” ምክንያት የሚፈጠረውን “የትራፊክ እንቅስቃሴ መጨናነቅን ለማቃለል” እንደሆነ ተገልጿል።
በስድስት ክፍሎች እና በ25 አንቀጾች የተከፋፈለው ይህ ደንብ የስራ ፈቃድ አሰጣጥን ጨምሮ ሌሎች ድንጋጌዎችን አካትቷል። አዲሱ ደንብ ማንኛውም በብስክሌት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመሰማራት የሚፈልግ ሰው፤ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የስራ ፈቃድ ማውጣት እንዳለበት ይደነግጋል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ኬንያ ከፈረቃ መብራት ለመዳን ከኢትዮጵያ ተጨማሪ የኤሌትሪክ ኃይል ልትጠይቅ ነው
እየጨመረ የመጣውን የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ለሟሟላት እና ሊከሰት የሚችል እጥረትን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ከ50 እስከ 100 ሜጋ ዋት ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተላለፍ ድርድር መጀመሩን ኬንያ ፓወር አስታውቋል።
ይህም ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ባለው ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ወቅት የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለማረጋጋት ያለመ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ 2022 በተፈረመው የ25 ዓመት ስምምነት መሠረት በኪሎ ዋት 6.5 ሳንቲም ዶላር እያስከፈለች ለኬንያ 200 ሜጋ ዋት ታቀርባለች።
ኬንያ የጠየቀችው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደሚገኝ ተዘግቧል። ስምምነቱ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ የኬንያ ሚዲያ ጨምሮ ገልጿል።

በስልጤ ወረዳ ባዶ የሬሳ ሳጥን ጭኖ አስክሬን ይዣለሁ በማለት ፖሊሶችን አታሎ ሊያልፍ የነበረ አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
👉 አሽከርካሪው የእንሰሳት መድኃኒት እና ማደለቢያ ይዞ ተገኝቷል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሆሳዕና ከተማ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 03 ሰሌዳ ቁጥር 15968 የሆነ አይሩፍ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከቀኑ 9፡30 ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ ባዶ የሬሳ ሳጥን ጭኖ አስክሬን ይዣለሁ በማለት የትራፊክ ፖሊሶችን አታሎ ለማለፍ ሲሞክር አሽከርካሪዉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስልጤ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
በተጨማሪም በተሽከርካሪው ውስጥ ተሳፋሪዎች እና የጫነው አስክሬን ነው ስትል የነበረች አንዲት እራሷን የፌዴራል ፖሊስ አባል ነኝ የምትል ግለሰብ ከአሽከርካሪው ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ተሽከርካሪው ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች በተጨማሪ በቁጥር ብዛት ያለው እና የጥራት ደረጃው ያልታወቀ ሁለት ማዳበሪያ እና አንድ ባሊ ሙሉ የእንሰሳት መድሃኒት እና ማደለቢያ መገኘቱ ተገልጿል።እንደዚህ አይነት የማጭበርበር እና የማታለል ዘዴን ተጠቅመዉ የወንጀል ተግባራት የሚፈፅሙ አካላትን ህብረተሰቡ ሊጋልጥ ይገባል ሲሉ ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፦
መንግሥት ሀገራዊ ተቋማትን ለማጠናከር ያለው ቁርጠኝነት የጸና ነው።
ከዚህ በፊት አንዳንድ ወገኖች በፈጠሩት ችግር የተነሣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባኤ ለመሳተፍ ላልቻሉ ሦስት አባቶች ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን መንግሥት ያሳውቃል።
ሀገራዊ ተቋማት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን የላቀ ሚና መንግሥት ስለሚረዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዲፈታ መንግሥት የመሪነቱን ሚና መጫወቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ የነበራትንና የሚኖራትን ሚና በመገንዘብ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሲሰጥ ቆይቷል። በዚህ አቋሙም ይቀጥላል።
ይሄንን ያልተረዱ አንዳንድ አካላት ችግሮችን ፈጥረው የነበረ ቢሆንም እንኳን፣ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያንዋ እና ለምእመንዋ ሲል በሆደ ሰፊነት ለማለፍ ወስኗል። ይሄም ከግለሰቦች ችግር ይልቅ የቤተ ክርስቲያንዋን አስተዋጽዖ ስለሚመለከት ነው።
መንግሥት ችግሩ እንዲፈታ ሲኖዶሱ ያቀረበውን ጥያቄ ተቀብሏል። በሂደቱም ተቀራርቦ መነጋገር ከሁሉም የተሻለ የመፍትሔ መንገድ መሆኑ ታይቷል።
ስለዚህም ሲኖዶሱ መንግሥት ነገሩን በሆደ ሰፊነት እንዲመለከተው በጠየቀው መሠረት፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ.ር)፣ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ.ር) እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በሲኖዶሱ ስብሰባ ለመገኘት እንዲችሉ ከመንግሥት የሚጠበቀውን ሁሉ እንደሚያደርግ ይገጻጣል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ/ም

የ2025 የአለም የፕሬስ ነፃነት ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡ ሪፖርተርስ ሳን ፍሮንቴ ባወጣው በዚህ ሪፖርት መሰረት በአለማችን ላይ ከፍተኛ የፕሬስ ነፃነት ያለባት በሚል በግንባር ቀደምነት የተቀመጠችው ኖርዌይ ናት፡፡
180 አገራትን ባካተተው በዚህ ዝርዝር የመጨረሻውን ደረጃ ያገኘችው ወይንም 180ኛ ላይ የተቀመጠችው ደግሞ ኤርትራ ናት፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ሪፖርት ላይ የ145ተኛን ደረጃ ስትይዝ አሜሪካ ደግሞ በ57ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ሪፖርተር ሳንፍሮንቴ በሪፖርቱ በያዝነው ዓመት ማለት በ2025 በአለማችን ከምንጊዜውም በላይ የፕሬስ ነፃነት አደጋ ውስጥ የወቀደበት አመት መሆኑን አስታውቋል፡፡ በዘንድሮው ሪፖርት ከአለማችን አገራት በግማሹ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሬስ ነፃነት መጥፎ የሚባል ደረጃ ውስጥ እንደሚገኝም አስረድቷል፡፡
የፕሬስ ነፃነት ሙሉ በሙሉ በሚከበርባቸው አገራት የሚኖሩ ህዝቦች ከአለማችን ከአንድ ፐርሰንት በታች የሚሆነውን ብቻ እንደሚሸፍኑም ጠቅሷል፡፡