Telegram Web Link
ዘወትር እሁድ በሑዘይፋህ መስጂድ የሚሰጠው ደርሳችን እንደተጠበቀ ነው ኢንሻአላህ። የመንሃጁ ሳሊኪን ኪታብ የደርስ መነሻ የሚከተለው ርእስ ነው :-
باب المحرمات في النكاح
Live stream finished (1 hour)
ከሰው ፊት Vs ከጌታ ፊት መቆም
~
ወጣ ያለ'ለት ከጓዳ
ለንግግር ቢሰናዳ
ቃላቱ የተመረጠ
አለባበሱ ያጌጠ
ፕሮቶኮሉን የጠበቀ
ሁለ ነገሩ ያሸበረቀ
.
.
.
ሶላት ላይ ግን
.
ከጌታው ፊት የዘነጋ
አስር ጊዜ የሚያዛጋ
ላሰጋገዱ አይሰጋ
በድብርት የሚላጋ
እዚህ መቁነጥነጥ እዚያ ማከክ
ሁለ ነገሩ ዝርክርክ።
ግራ አጋቢ ነው የኛ ነገር
አይቦካ አይጋገር።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
በዚህ አመት ሐጅ ላልተሳካለት
~
ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–

★ በዐረፋ መቆም ላልቻለ ከአላህ ወሰኖች ዘንድ ይቁም።
★ በሙዝደሊፋ ማደር ላልቻለ ወደ አላህ ያቃርበው ዘንድ ለትእዛዙ ይደር።
★ ሀድዩን ሚና ላይ ማረድ ያልቻለ ከምኞቱ ይደርስ ዘንድ ስሜቱን ይረድ።
★እሩቅ በመሆኑ ቤቱ (በይተል ሐራም) መድረስ ያልቻለ የቤቱን ባለቤት ያስብ። ወደሱ ከደም ጋኑ የቀረበ ነውና።"

(ለጧኢፉል መዓሪፍ: 633)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Menhaju salikin #50
Ibnu Munewor
ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 5️⃣0️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
አንድ ሰው እህትማማቾችን ማግባት አይችልም። ከአንዷ በሞት ወይም በፍቺ ከተለየ ሌላኛዋን ማግባት ይችላል። ሁለቱንም መያዝ ግን አይቻልም። እንኳን የስጋ እህትማማቾችን በጥቢ የሚገናኙ ሴቶችንም በአንድ ላይ መያዝ አይፈቀድም። አላህ በቁርኣኑ ወንዶች ሊያገቧቸው የማይፈቀዱ ሴቶችን ሲዘረዝር አንዱ የጠቀሰው ይህንን ነው።

{ وَأَن تَجۡمَعُوا۟ بَیۡنَ ٱلۡأُخۡتَیۡنِ }
"በሁለት እህትማማቾችም መካከል መሰብሰብ (እንደዚሁ እርም ነው)።" [አኒሳእ፡ 23]

ከተከስተስ?

ይህንን ማስታወሻ እንድፅፍ ያደረገኝም እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ሁለት እህትማማች ሴቶችን ያገባ ሰው እንዳለ መስማቴ ነው። ይሄ ሰው ባስቸኳይ አንዷን መፍታት ግድ ይለዋል። ፈይሩዝ አደይለሚይ ረዲየላሁ ዐንሁ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሄጄ
" 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ ሰልሜያለሁ። ሁለት እህትማማቾች ከስሬ አሉ' ስላቸው የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም 'ከሁለቱ አንዷን ፍታ!' አሉኝ " ብሏል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1587]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ቀደም ብሎ በተጠቀሰው ተመሳሳይ አንድ ሰው አንዲትን ሴት እና አክስቷን ወይም የሹማዋን ጨምሮ ማግባት አይፈቀድም። [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም]

አንድ ሰው አብሮ ሊያገባቸው የማይፈቅድለት ወይም በተመሳሳይ ወቅት በአንድ ሰው ስር መሆን የማይፈቀዱ ሴቶች የትኞቹ ናቸው?

የሁለት ሴቶች የዝምድናቸው ቅርበት ለምሳሌ ያህል አንዳቸው ወንድ ሌላቸው ሴት ቢሆኑና መጋባት በማይፈቀላቸው መጠን ቅርበት ካላቸው እነዚያን ሴቶች አንድ ሰው ሁለቱንም ሊያገባቸው አይፈቀድለትም። ለምሳሌ፦ እናትና ልጅ፣ እህትና እህት፣ አንዲትን ሴት ከወንድሟ ወይም ከእህቷ ልጅ ጋር፣ ወዘተ.
ቅርበታቸው የዝምድና ሳይሆን የጥቢ ቢሆንም ተመሳሳይ ሑክም ነው ያለው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ የኸይር ስራ ጥሪ ለአማኞች በሙሉ ሸር አድርጉልን ወረባቦ ወረዳ 018 ቀበሌ ላይ ምሺንጋ በግፈኞች የተቃጠለብንን መስጂድ በቦታው መልሱልን አቅማችሁ የፈቀደውን አነሰ በዛ ሳትሉ አግዙን የወንድሞቻችንን የተሰበረ ልብ ጠግኑልን @highlight

አካውንት
1000701270097
Ali Shiferaw , Abdu Ali & Yimam Mohammed
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ዒድ እና ጁሙዐ ሲገናኙ ጁሙዐ/ እና ዙህርን ምን እናድርግ?
~
ዒድ በጁሙዐ ቀን ላይ ሲውል ሁለት በዓል በአንድ ቀን ገጠመ ማለት ነው። አመታዊው ዒደል ፊጥር ወይም ዒደል አድሓ እና ሳምንታዊው ዒድ፣ ጁሙዐ። በዚህን ጊዜ የሚኖረውን የዒድና የጁሙዐ ሶላት በተመለከተ በዑለማዎች የተለያዩ ሀሳቦች የተሰነዘሩ ሲሆን ጥቅል መልእክት ለሚፈልግ የሳዑዲ ዑለማ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ፈትዋ ጨመቅ አድርጌ አስቀድማለሁ። ዒድን የሰገደ ሰው ጁሙዐን የመተው ምርጫ እንዳለው የሚጠቁሙትን ሐዲሦችና የቀደምቶችን ንግግሮች ከዘረዘሩ በኋላ የሚከተሉትን ነጥቦች አስፍረዋል፡-

1. የዒድን ሶላትን የሰገደ የጁሙዐ ሶላት ላይ ያለመገኘት ፈቃድ አለው። በዙህር ወቅት ላይ ዙህርን ይሰግዳል። ከሰዎች ጋር ጁሙዐን ቢሰግድ ለሱ በላጭ ነው።
2. ዒድ ሶላትን ያልተካፈለ ማግራሪያው አይመለከተውም። ስለሆነም የጁሙዐ ግዴታነት አይወርድለትም። እናም ለጁሙዐ ሶላት መስጂድ የመሄድ ግዴታ አለበት።
3. ጁሙዐ በሚሰገድበት መስጂድ ላይ ኢማም የሆነ ሰው ላይ በእለቱ የጁሙዐ ሶላትን የማሰገድ ግዴታ አለበት። ይህም መስገድ የሚፈልግ ሰው እንዲሰግድ፣ ዒድን ያልሰገደም እንዲሁ እንዲሰግድ ነው። ጁሙዐ ሶላት የሚያሰግድ ብዛት ከተገኘ እሰየው። ካልሆነ ግን ዙህር ይሰገዳል።
4. የዒድ ሶላትን በመስገዱ ጁሙዐ ያልተካፈለ ሰው የዙህር ወቅት ሲገባ ዙህርን ሊሰግድ ይገባል።
5. ..
6. ዒድ ሶላትን የተካፈለ ሰው በእለቱ የጁሙዐም የዙህርም ሶላት ይወድቅለታል የሚለው እይታ ልክ ያልሆነ እይታ ነው። ለዚህም ነው ዑለማዎች ያገለሉትና ስህተትና እንግዳ እንደሆነም የበየኑበት።...” [ፈትዋውን የሰጡት ዐብዱል ዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ፣ ዐብደላህ አልጉደያን፣ በክር አቡ ዘይድ እና ፈውዛን ናቸው።]

ስለ ጉዳዩ ጥቅል መረጃ ብቻ ለሚሻ ሰው እስከዚህ ያለው ማጠቃለያ በቂው ነው። በጉዳዩ ላይ ውዝግብ ያስተዋለ ወይም ዝርዝር ዳሰሳ የሚሻ ቀሪውን ክፍል ይከታተል።

በጉዳዩ ላይ ከተሰነዘሩ ሃሳቦች ውስጥ አንዱ፡-

ዒድ የሰገደ ሰው ከነጭራሹ ጁሙዐም ሆነ ዙህር መስገድ አይጠበቅበትም። ይልቁንም እስከ ዐስር ሶላት ድረስ ሳይሰግድ ይቆያል የሚል ነው። ይሄ ሀሳብ በጣም በጥቂቶች ብቻ የተንፀባረቀ ከመሆኑም ባለፈ ማስረጃ ፈፅሞ የማይደግፈውና ወጣ ያለ እይታ ነው።
ይህን ፅሑፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ይህንን አቋም ስራዬ ብሎ አመት እየጠበቀ የሚያራግብ ሰው መኖሩ ሲሆን ዘንድሮም እንደተለመደው አድርጓል። በጣም የደነቀኝ እነ ኢብኑ ዑሠይሚንን ጭምር ባልዋሉበት ደጋፊ አድርጎ ማጣቀሱ ነው። በርእሱ ላይ የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ አባል ዑለማዎች ፈትዋ ሲነገረው “እነሱ ሳዑዲ ናቸው” ብሎ ማጣጣሉንም ሰምቻለሁ። ዐጂብ! እና የሳዑዲ ስለሆኑ ምን? ይሄ ምን የሚሉት መለከፍ ነው? የየት ሃገር ዐሊም ነው ማጣቀስ የሚቻለው? ደግሞስ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን በሐሰት ሲያጣቅስስ ምነው ሳዑዲያዊ መሆናቸውን ዘነጋ?
ወደ ርእሱ ስመለስ በመጀመሪያ ደረጃ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር ጥቂትም ቢሆኑ ይህንን አቋም ያስተጋቡ ዐሊሞች በተጨባጭ አጋጥመዋል። ለምሳሌ ሸውካኒይ። ይሄ ግን እንዳሻን እንፈነጭ ዘንድ አረንጓዴ መብራት አይሰጥም። ሸውካኒይ የተናገሩት ሁሉ ልክ ነው የሚል ጤነኛ ጭንቅላት ምድር ላይ የለም። ይልቁንም “ሌሎችስ ምን ይላሉ?” ብሎ መመልከት በላጭ ብቻም ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው።

~ ብዥታዎች ~

የዚህ “ዒድ የሰገደ ሰው ጁሙዐም ዙህርም መስገድ አይጠበቅበትም” የሚል አቋም አራማጆች ቀጥተኛና ግልፅ (ሶሪሕ) ማስረጃ እንደሌላቸው ይሰመርበት። ይህ ግን የሚመዟቸው ብዥታዎች የሉም ማለት አይደለም። ለምሳሌ፡-

[ብዥታ አንድ]፡-

የአላህ መልእክተኛﷺ “በዚህ ቀናችሁ ሁለት ዒዶች ተገናኝተዋል። የፈለገ (ዒዱ) ከጁሙዐ ያብቃቃዋል። እኛ ኢንሻአላህ ጁሙዐን እንሰግዳለን” ብለዋል። [ኢብኑ ማጃህ፡ 1311] አቡ ዳውድና ሌሎችም የዘገቧቸው ተመሳሳይ መልእክት የያዙ ዘገባዎችም አሉ።

መልስ፡-

በአንክሮ ያስተውሉ። ሐዲሡ በእለቱ ዒድን ለሰገደ ሰው ጁሙዐ የመስገድ ግዴታ እንደሌለበት ከመጠቆም ባለፈ ጭራሽ ዙህርንም ይተው የሚል መልእክት የለውም። ጁሙዐን የመተው አማራጭ ተሰጠ ማለት ጭራሽ ዙህርንም መተው ይቻላል ማለት አይደለም። እንዲህ የሚል ካለ ጁሙዐ መስገድ ግዴታ የማይሆንባቸው ሴቶች፣ ህመምተኞች፣ መንገደኞችና ባሪያዎች በጁሙዐ ቀን ዙህርንም የመተው ምርጫ አላቸው የሚል ይይዘዋል። ዒድ የሰገደ ሰው ሁኔታው ከህመምተኛና መንገደኛ የባሰ አይደለም። ታዲያ ከዒድም ከጁሙዐም ቀድሞ ከአመታት በፊት የተደነገገው የዙህር ሶላት እንዴት ተብሎ ነው ትክክለኛና ቀጥተኛ ማስረጃ በሌለበት ሳይሰገድ የሚዋለው?

የሐዲሡ መልክት በእለቱ ለዒድ ሶላት ሰው ከያቅጣጫው ይመጣል። ሶላት ሰግዶና ኹጥባ አዳምጦ ወደቤቱ የተመለሰ ሰው ለጁሙዐ ዳግም መውጣቱ ሊከብደው ይችላል። በተለይም ከሩቅ የመጣ ከሆነ። አስታውሱ በነብዩ ﷺ ዘመን እንደዛሬው በየቦታው ጁሙዐ የሚሰገድበት ብዙ መስጂድ አልነበረም። ስለዚህ ይህን ታሳቢ በማድረግ መልእክተኛው ﷺ ህዝብ እንዳይቸገር ዒድ የሰገደ ሰው ዳግም ወደሳቸው ዘንድ በመምጣት ጁሙዐ ላይ የመገኘት ግዴታ እንደሌለበት ተናገሩ። “ይህን ግንዛቤ ከየት ወሰድከው?” ከተባለ

1ኛ፡- ከጊዜው ነባራዊ ሁኔታ። ያኔ የጁሙዐ መስገጃ እንደዛሬው የበዛ ባለመሆኑ ታዳሚዎች ከግማሽ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሁለት ጊዜ ከቤታቸው ርቀው መሄዳቸው አድካሚ ነበር።
2ኛ፡- “ሰዎች ሆይ! በዚህ ቀናችሁ ሁለት ዒዶች ተገናኝተዋል። ከዐዋሊ አካባቢ የሆነ ሰው ጁሙዐን መጠባበቅ የወደደ ይጠባበቅ። መመለስ የፈለገ ይመለስ” የሚለው የዑሥማን ብኑ ዐፋን ረዲየላሁ ዐንሁ ንግግርም ይህን የሚያጠናክር ነው፡- [ቡኻሪ፣ ተዕሊቅ፡ 5572] ዐዋሊ በጊዜው በመዲና ዳርቻ ያሉ መንደሮች ነበሩ። የዐዋሊ ነዋሪዎች ከመስጂደ ነበዊይ ሩቅ ስለሆኑ ጁሙዐም አይወጅብባቸውም ይላሉ ዐሊሞች። [ሙኽተሶሩ ኢኽቲላፊል ዑለማእ ሊጦሓዊ፡ 1/347] የዑሥማንን ንግግር ያለ አግባብ የሚለጥጥ እንዳይመጣ ነው ይህን የማነሳው። እንዲያውም ዑሥማን በቅርብ ላሉ ነዋሪዎች አማራጭ አልሰጡም። ዛሬ በዐዋሊና በመስጂድ ነበዊ መካከል ቀርቶ ዐዋሊ ውስጥ እራሱ ብዙ መስጂዶች አሉ!

[ብዥታ ሁለት]፡-

በኢብኑ ዙበይር ዘመን ሁለቱ ዒዶች በአንድ ቀን ተገናኙ። ኢብኑ ዙበይርም ረዲየላሁ ዐንሁማ ሁለቱን አንድ አድርገው ሰበሰቧቸው። እናም በጁሙዐ ቀን ረፋድ ላይ የዒደል ፊጥርን ሶላት ሰገዱ። ከዚያ ዐስርን እስከሚሰግዱ ድረስ አልጨመሩም።” [ሱነኑ አቢ ዳውድ፡ 1072] በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል መጥቷል፡- “በኢብኑ ዙበይር ዘመን ሁለት ዒዶች ተገናኙ። ቀኑ ከፍ እስከሚል መውጣትን አዘገዩ። ከዚያም ኹጥባ አደረጉ። ኹጥባውንም አስረዘሙ። ከዚያም ወርደው ሰገዱ። ያን እለት ሰዎችን ጁሙዐ አላሰገዱም።” [ሱነኑ ነሳኢይ፡ 1592]

መልስ:-

ኢብኑ ዙበይር ዙህርን ላለመስገዳቸው በቁርጥ አይታወቅም። የመጀመሪያውን ዘገባ ያስተላለፉት ዐጣእ ናቸው። በሌላ ዘገባ ግን ራሳቸው ዐጣእ እንዲህ ብለዋል፡- “ኢብዙ ዙበይር በዒድ ቀን ጁሙዐ ቀን ጧት ላይ ሰገዱ። ከዚያም ለጁሙዐ ስንሄድ ወደኛ አልወጣም። በተናጠል ሰገድን። ኢብኑ ዐባስ ጧኢፍ ነበሩና ሲመጡ ስንነግራቸው ሱናውን አግኝቷል አሉ።” [አቡ ዳውድ፡ 1071]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አስተውሉ! እዚህ ላይ የኢብኑ ዙበይር ለጁሙዐ አለመምጣት እንጂ አለመስገድ አልተጠቀሰም። ይሄ ደግሞ እቤታቸውም ዙህርን አልሰገዱም የሚል መረጃ አይሰጠንም። ስለዚህ ቀደም ብሎ ያለፈው “ኢብኑ ዙበይር እስከ ዐስር ድረስ አልሰገዱም” የሚለው የዐጣእ ንግግር እዚህ ላይ ከተናገሩት ጋር ስናያይዘው መስጂድ መጥተው ጁሙዐ አለመስገዳቸውን እንጂ የሚጠቁመው በቤታቸው ዙህርን አለመስገዳቸውን አይደለም። ዙህርንማ ይሄው የታሪኩ ዘጋቢ ዐጣእ በተናጠል እንደሰገዱ እየነገሩን ነው። መቼስ በተናጠል የሰገዱት ጁሙዐ ነው አይባል ነገር። ሶንዓኒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ኢብኑ ዙበይር ለጁሙዐ ሶላት እንዳልወጡ ዐጣእ መናገራቸው አይሰወርም። ይህ ግን እቤታቸው ውስጥ ዙህር ላለመስገዳቸው ቆራጭ መረጃ አይደለም። እናም ይህን ዘገባ መነሻ አድርጎ ዒድ በጁሙዐ ቀን ሲሆን ዒድን በሰገደ ላይ ዙህር ይወርደለታል የሚለው የኢብኑ ዙበይር መዝሀብ እንደሆነ መደምደም ትክክል አይደለም። እቤቱ ሰግዶ ሊሆን ይችላልና። እንዲያውም ዐጣእ ብቻ ብቻቸውን - ዙህርን - እንደሰገዱ መናገሩ ይህን እንደማይል ይጠቁማል። መቼስ ጁሙዐን ብቻ ለብቻ ሰገዱ አይባልም። በጀማዐ እንጂ እንደማይሰገድ ኢጅማዕ አለና። ደግሞም በጁሙዐ ቀን መነሻው (አስሉ) የጁሙዐ ሶላት ነው። ዙህር የሱ ምትክ ነው የሚለው አቋም ሚዛን የቀለለው ነው። ይልቁንም የኢስራእ ሌሊት ጊዜ የተደነገገው ዙህር ነው ቀዳሚው ግዴታ። ጁሙዐ ዘግይቶ ነው የተደነገገው። ደግሞም ጁሙዐ ሲያልፍ ዙህር ይሰገዳል። ይሄ አጅማዕ ያለበት ነው። ስለዚህ እሱ ነው ለሱ (ለዙህር) ምትክ የሆነው።” [ሱቡሉ ሰላም፡ 1/408]

እንዲያውም ኢስሓቅ ብኑ መንሱር፣ ኸጧቢይ፣ በሳምና ሌሎችም ኢብኑ ዙበይር የሰገዱት ጁሙዐን ነው። ዒድን በዚያው ታሳቢ በማድረግ ነው ያለፈው እስከማለት ደርሰዋል። [መዓሊሙ ሱነን፡ 1/246] አሰጋገዳቸውም እንደዚያ ነው የሚመስለው። ሶላቱን ቀኑ እስከሚረፍድ ማዘግየትና ኹጥባውን ከሶላቱ ማስቀደም የጁሙዐ እንጂ የዒድ ሶላት አፈፃፀም አይደለም። ስለዚህ ጁሙዐ አልሰገዱም የሚለው ዳግም ይህን ከእኩለ ቀን በፊት የተሰገደውን ሶላት ዒድንም፣ ጁሙዐንም፣ ዙህርንም ለማብቃቃት ተጠቅመውበታል ማለት ነው። ኋላ ለጁሙዐ አልወጡም የተባለው የሰገዱበት ጊዜ ከወትሮው የጁሙዐ ወቅት ቀደም ያለ በመሆኑ ሰዎች የዒድ ሶላት መስሏቸው ዳግም ለጁሙዐ መውጣታቸውን በመጠባበቃቸው ሊሆን ይችላል።
“የለም ይሄ ስህተት ነው። የሰገዱት ዒድ ነው” የሚል ካለ “ወቅቱን ማስረፈዳቸውንና ኹጥባውን ማስቀደማቸውን ምን ትላለህ?” እንለዋልን። “እዚያ ላይ ተሳስተዋል” ካለ ጁሙዐንም ዙህርንም አለመስገዳቸውም ስህተት ነው ስንል ሊጎረብጠው አይገባም። ያውም ቤታቸው ላለመስገዳቸው ቆራጭ ነገር ካለመኖሩም ጋር።

[ብዥታ ሶስት]፡-

ዐጣእ እንዲህ ብለዋል፡- “ጁሙዐ እና (ዒደል) ፊጥር በአንድ ቀን ከተገናኙ ይሰብስባቸውና ሁለት ረከዐ ብቻ ይስገድ። ይህም ፊጥርን ብቻ መስገድ ነው። እስከ ዐስር እሷው ትበቃዋለች።” አክለውም ከላይ የተጠቀሰውን የኢብኑ ዙበይርን ድርጊት አውስተዋል። [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 5725]

መልስ፡-

ዐጣእ እዚህ ላይ ይህን ቢሉም ኢብኑ ዙበይር ከመስጂድ ሲቀሩ ግን ብቻ ብቻችንን ሰገድን ብለዋል። ከአንድ ዘጋቢ ንግግሮች ውስጥ ስሜታችን ጋር የሚሄደውን እየገነጠልን እንውሰድ ካልተባለ በስተቀር በእንዲህ አይነት ዘገባዎች ላይ ተንተርሶ በወቅት የተደነገገውን የዙህር ሶላት መተው የሚከብድ ነው።
በጥቅሉ የኢብኑ ዙበይርም ሆነ የዐጣእ ንግግርና ድርጊት በተለያዩ ዘገባዎች ላይ የተለያየ ይዘት ስላላቸው ብቻቸውን ቆራጭ አይደሉም። ሰለፎችን መከተል ማለትም እንዲህ እየነጠሉ መምዘዝ አይደለም።
ደግሞም ሰለፎች’ኮ በተናጠል ፍፁማን አይደሉም። በዚያን ዘመን የወለድን አይነት፣ የሙትዐን ኒካሕ፣ ዘፈንን፣… የፈቀደ አጋጥሟል። ጤነኛ ሰው እነዚያን እንግዳ ዘገባዎች እየመዘዘ ወለድንና የሙትዐ ኒካሕን ይፈቅዳልን? በፍፁም! በአንድ የፊቅህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች ከተለያዩ ሶሐቦች ተላልፈዋል። ያኔ ምንድን ነው የምናደርገው? ማስረጃዎቹን ሰብስቦ ማጥናትና ከሌሎች ማስረጃዎችና ከሸሪዐው መርሆዎች ጋር በማያያዝ ብይን ላይ መድረስ እንጂ እንዲሁ በስሜት ብቻ ከብዙሃኑ የተለየ አቋም ማሳደድ ጎሽ አያስብልም። ይልቁንም እንግዳ ርእሶችን እየመረጡ ማሳደድ የአፈንጋጮች መታወቂያ ነው።

እንዲያውም ብዙሃኑ ዑለማዎች በዒድ ሶላት ምክንያት እንኳን ዙህር ሊወድቅና የጁሙዐ ግዴታነትም አይወርድም ነው የሚሉት። በዚህኛው ሀሳብ መሰረት “ዒድ ስለሰገድኩ ጁሙዐን እተዋለሁ” ማለት አይቻልም። መረጃ የሚያደርጉትም በእለቱ ጁሙዐን ለመተው የሚቀርቡት ሐዲሦች ደካማ ናቸው የሚል ነው። ስለሆነም በደካማ ሐዲሦች ላይ ተንተርሶ አመቱን ሙሉ ግዴታ የነበረው የጁሙዐ ሶላት በዚህ ቀን በተለየ ከግዴታነቱ አይወርድም የሚል ነው። ይሄ የብዙሃን ዑለማዎች እይታ እንደሆነ ኢብኑ ቁዳማ ገልፀዋል። [አልሙግኒ፡ 2/265]

የእውነትም ዒድና ጁሙዐ አንድ ቀን ሲሆኑ ጁሙዐን የመተው ምርጫ እንዳለ የሚጠቁሙት ሐዲሦች በበርካታ ሙሐዲሦች ጥንካሬያቸው ላይ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል። ዝርዝር የፈለገ ይህቺን “አልሉምዐ ቢበያኒ አንነ ሶላተል ዒዲ ላቱጅዚኡ ዐን ሶላቲል ጁሙዐ” የተሰኘች አጭር ሪሳላ ቢመለከት መጠነኛ ሀሳብ ያገኛል። “በሐዲሥ ምሁራን አንድ እንኳን ነቀፌታ ያልተሰነዘረበት ሐዲሥ በሌለበት በነዚህ ሐዲሦች ተመርኩዞ አንድ ሙስሊም የጁሙዐን ድንጋጌ ግዴታ ከሆነበት ላይ ሊጥል አይገባውም” የሚለውን የታላቁን ዐሊም ብኑ ዐብዲል በር ንግግር እዚህ ላይ ማሰብ ይገባል። ኢብኑ ሐዝምም ዒድም ጁሙዐም ሊሰገዱ ይገባል። የሚጠቀሱት ማስረጃዎች ሶሒሕ አይደሉም ይላሉ። [አልሙሐላ፡ 3/303] ኢብኑ ሙንዚርም እንዲሁ። [አልአውሰጥ፡ 4/334]

ብዙሃኑ የዘመናችን የሐዲሥ አጥኚዎች ግን ሐዲሦቹ ተደጋግፈው ሶሒሕ ደረጃ ይደርሳሉ ይላሉ። ሲጠቃለል ምን እንበል?

ስለዚህ፡-
ዘገባዎችን ስንመረምር በእለቱ ዒድን የሰገደ ሰው ጁሙዐን ቢሰግድ ለሱ በላጭ ከመሆኑ ጋር ጁሙዐ ላይ የመገኘት ግዴታ የለበትም። ጁሙዐ ላይ ካልተገኘ ግን ዙህርን የመስገድ ግዴታ አለበት። ይህንን ሀሳብ ካንፀባረቁ ዑለማዎች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው:-

1. አልኸጧቢይ፡- “ዒድን መስገድ ከፈለገ ከጁሙዐ ያብቃቃዋል እንጂ ዙህር አይወርድለትም” ብለዋል። [መዓሊሙ ሱነን፡ 1/246]
2. ኢብኑ ተይሚያ:- ዒድና ጁሙዐ ሲገጥም ዒድን ለሰገደ ሰው ጁሙዐን የመስገድም የመተውም ምርጫ እንዳለው ካወሱ በኋላ “ከዚያም ጁሙዐ ላይ ካልተገኘ ዙህርን ይሰግዳል። ዙህርም በወቅቱ ይሆናል” ብለዋል። [መጅሙዑል ፈታል፡ 2/365]
3. ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- “ዒድ ከጁሙዐ ቀን ጋር ከገጠመ ዒዱን ለተካፈለ ሰው ጁሙዐንም ሆነ ዙህርን (ከሁለት አንዱን) ሊሰግድ ይፈቀድለታል። … ነገር ግን የዙህርን ሶላት አይተውም። በላጩ ከሰዎች ጋር ጁሙዐን መስገዱ ነው። ጁሙዐን ካልሰገደ ግን ዙህርን ይሰግዳል።” [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብኒ ባዝ፡ 13/13]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
4. ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ጁሙዐና ዒድ ሲገጥም ዙህር ይወድቃል ወይስ አይወድቅም ተብለው ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፡- “በዚህ ላይ ትክክለኛው በሱ ላይ ወይ ከኢማሙ ጋር ጁሙዐን መስገድ ነው። ወይ ደግሞ ዙህርን መስገድ ግዴታ ይሆንበታል። … በዙህር መውደቅ ላይ ማስረጃ የለም።” ቀንጭቤ ነው ያቀረብኩት።
እንዲህም ብለዋል፡- “የዒድ ቀን በጁሙዐ ቀን ጋር ከገጠመ የግድ የዒድ ሶላትም የጁሙዐ ሶላትም ሊፈፀም ይገባል። ልክ ነብዩ ﷺ ሲያደርጉት እንደነበሩት። ከዚያም የዒድ ሶላትን የተካፈለ ሰው ጁሙዐን የመካፈል ግዴታው ይነሳለታል። ነገር ግን ዙህርን መስገድ ግዴታው ነው። ምክንያቱም ዙህር የወቅቱ ግዴታ ነውና ሊተው አይቻልም።” [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 16/169፣ 171]
ወላሁ አዕለም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፡ ሰኔ 7/2010)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለመጅሊስ
~
የሐጅ ጉዞ ላይ አስተባባሪዎች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ አድርጉ። በተለይም 10ኛው ቀን ላይ ብዙዎች የሚፈተኑበት እለት በቅጡ የሚያስተናግድ ቀርቶ መንገድ የሚመራ ፣ ምልክት የሚያሳይ አስተባባሪ መጥፋት ትልቅ ችግር ይፈጥራል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለሑጃጅ ማስታወሻ ( 1 )
~
* ትኩረታችሁ ከሐጃችሁ ይበልጥ ለመጠቀም ፣ አጅር ለመሸመት ይሁን። ሶላትን በተቻለ መጠን በሐረም ስገዱ። ታሪካዊ ቦታ ጉብኝት እያላችሁ ሐረም ከመስገድ እንዳትዘናጉ።
* የየእለቱን ተግባር ቀድማችሁ አጥኑ። እርስ በርስ ተጠያየቁ።
* ኢኽላስን ከሚፈትኑ አጉል ስሜቶችና ተግባራ ራቁ። በቀረፃ አትጠመጡ።
* ከማህበራዊ መገናኛዎች ራቁ ወይም ቀንሱ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለሑጃጅ ማስታወሻ ( 2 )
~
8ኛው ቀን ላይ ወደ ሚና ሄዳችሁ ማረፊያ ድንኳናችሁ ስታርፉ google map በመጠቀም ሎኬሽኑን ያዙ። 10ኛው ቀን ላይ ስትመለሱ ቦታው ቢጠፋባቸሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለተወሰነ ጊዜ
1. የአርበዒን
2. የመንሃጁ ሳሊኪን እና
3. የዑምደቱል አሕካም ኪታቦች ደርስ አይኖርም። ሲጀመር አሳውቃለሁ ኢንሻአላህ።
ኡዱሒያ የምታርዱ ከኡዱሒያው ለምስኪኖች መስጠትን አትርሱ።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
2025/07/13 22:29:14
Back to Top
HTML Embed Code: