Telegram Web Link
የተውሒድን ወሳኝነት እና ህዝባችን በዚህ በኩል ያለበትን ክፍተት የሚያውቅ ሰው ተውሒድ የደዕዋችን ሁሉ ማዕከል ሊሆን እንደሚገባው አይሰወረውም። ይሄ ሐቂቃ ባለበት ሁኔታ መስጂድ ላይ በሚያስተምረውም ይሁን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሚያደርገው ደዕዋ ነክ ተሳትፎው ላይ የተውሒድን ርእስ #ከነጭራሹ የሚገፋ ዳዒያህ እውነተኛ ዳዒያህ ተብሎ ሊቆጠር አይችልም። በዚህ ጉዳይ ላይ ደንታ ቢስ የሆነ ዳዒያህ ለደዕዋው ሸክም ስለሚሆን ወይ ወደ መስመር ይገባ ዘንድ በጥልቀት መስራት ይገባል። መፍትሄ ከሌለው አርግፎ መተው ነው። እንዲህ አይነቱ ካለም አይቆጠርም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ሰዎች ለተውሒድ ትምህርት እንቅፋት ሲሆኑብን በቀላሉ ተሸንፎ እጅ መስጠት አይገባም። እስከ ደም ጠብታ ታገል። ተውሒድ ከሌለ ከዲንህ ምን ቀረህ? ለተውሒድ ካልተቆጨህ ለምን ልትቆጭ ነው? ምከር። ዝከር። ጣር። ታገል። መክፈል ያለበህን መስዋእትነት ሁሉ ክፈል። ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ።

ዙልቀዕዳህ 28/1446

ጅማ አባ ጅፋር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
በነገራችን ላይ ለቻለበት በአርበዑነ ነወዊየህ፣ በሪያዱ ሷሊሒን፣ ... ደርስ ተውሒድን ማስተማር የሚቻልባቸው ብዙ ተያያዥ ሐዲሦች / ርእሶች አሉ። ብቻ የእውነት ትኩረት ይኑርህ! ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም።

ስለዚህ በነፃነት ተውሒድን የምታስተምርበት መድረክ ስታጣ ተውሒድ ከለከሉኝ እያልክ አትነፋረቅ። ሁሉ አልተገኘ ተብሎ ሁሉ አይተውም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ተውሒድን ትተህ ''ሒክማ ገብቶታል"፣ "ሰፋ ያለ ነው"፣ "ፀባዬ ሸጋ ነው"፣ ... ከምትባል ፤ ተውሒድ ላይ ትኩረት አድርገህ ያሰኛቸውን ስም ይለጥፉልህ።
ስለ አቀራረብህ ደንታ ቢስ ሁን ማለቴ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
አሰላሙ ዐለይኩም
~
ዛሬ በዘህራእ መስጂድ የአርበዒን ደርስ መግባት አልችልም፤ 0ፍወን።
የደዕዋው ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ ሁሉ!
~
እውቀት ያለው በእውቀቱ፣
ሃብት ያለው በሀብቱ፣
በየትኛውም በምንችለው መንገድ ሁሉ ለደዕዋ አስተዋፅኦ ይኑረን። መስጂዶችን፣ ማህበራዊ መገናኛዎችን፣ ... ለደዕዋ እንደሚገባ እንጠቀማቸው። ካልሆነ የተጋረጡብንን አደጋዎች መቋቋም አንችልም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

"ጂብሪል ታላላቆችን እንዳስቀድሞ አዞኛል።"

[አሶሒሐ ፡ 1555]

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ከቀናት በፊት ከዑዝር ቢል ጀህል ጋር በተያያዘ የሙሳ ሰዎችን ቂሷ አንስቼ ለፃፍኩት ፅሁፍ በርከት ያሉ ኮመንቶች እንደተሰጡ አየሁኝ። ተረጋግቼ ቁጭ ስል ምላሽ እስከምሰጥበት ድረስ በሚል ትኩረት አላደረግኩበትም ነበር። ሀሳባችሁ ከኔ ድምዳሜ ጋር ገጠመም አልገጠመም በመልካም ኒያ ተሳትፎ ያደረጋችሁን ሁሉ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ልል እወዳለሁ።

በጉዳዩ ላይ ዑለማኦች የተለያየ አቋም የሰነዘሩበት መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ከልብ መቀበል ይገባል። ያ ሲሆን ነው ጉዳዩን በልኩ የምንይዘው። ይሄ ርእስ በምንም መልኩ ለመፈራረጅ የሚደርስ አልነበረም። ይሁን እንጂ እንደ ኢብኑ ተይሚያ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን ያሉ ታላላቅ ዑለማኦችን ሳይቀር ዑዝር በመስጠታቸው የተነሳ አንዴ በማ k ፈ ^ r ሌላ ጊዜ በኢርጃእ በመወረፍ የተጠመደ አካል እስካለ ድረስ ጉዳዩ በቀላል ሊታይ አይችልም። ስለዚህ በስርአት ለመነጋገር ዝግጁ ያልሆነውን እያስገለሉ መወያየቱ እና ብዥታ ማጥራቱ ይቀጥላል፣ ኢንሻአላህ።

መዝዘንጋት የሌለበት ነገር ቢኖር ዑዝር ቢል ጀህል የለም የሚሉ አካላት አይነታቸው ብዙ መሆኑን ነው። ለምሳሌ ያህል፦
- ዑዝር የማይሰጡበትን ርእስ በተመለከተ ከፊሎቹ በኡሉሂያ ጉዳይ ላይ ብቻ ሲገደቡ ፣ ሌሎቹ በአስማእ ወሲፋት ጭምር ያከ f ^ራሉ።
- ዑዝር የሚሰጡ አካላትን ከፊሉ በጅምላ ከኢስላም ሲያስወጡ፣ ከፊሎቹ ደግሞ በኢርጃእ ይወነጅላሉ። ሌሎቹ ችግራቸው እዚህ አይደርስም።
- ከፊሎቹ ለአዲስ ሰለምቴ እና ከእውቀት ርቆ ላለ ዑዝር ሲሰጡ ከፊሎቹ ማንንም አያስተርፉም።
- ከፊሎቹ እነ ፈውዛንን ደጋግመው ሲያጣቅሱ ሌሎቹ ደግሞ ፈውዛንን ጭምር ከኢስላም ያስወጣሉ።
- ከፊሎቹ የሙሳ ሰዎች ከኢስላም ወጥተዋል ብለው በድፍረት ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ "አይ" ይላሉ። በዚህ ነጥብ ብቻ አንድ የነበሩ ግን ለሁለት የተሰነጠቁ አካላት አሉ።
ወዘተ.

ማለት የፈለግኩት ምንድነው? አይነታቸውም ነገሮችን የሚይዙባቸውም መንገዶች የበዛ ስለሆነ ለአንዱ ብዥታ የሚስሰጠው ምላሽ ለሌላው ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ብዥታን ለማጥራት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጉዳዩን መመልከት ያስፈልጋል ማለት ነው። ስለሆነም በየቀኑ ሆኖ እንዳያሰለች አለፍ አለፍ እያልኩ መጠነኛ ዳሰሳ ለማድረግ እሞክራለሁ ኢንሻአላህ።

የተለየ ሀሳብ ላላችሁ!
-
የተለየ ሃሳብ መምጣቱን በቅሬታ አላይም። እንዲያውም በደስታ ነው የምቀበለው። ለቀጣይ ዳሰሳዬ እንደ ግብአት እጠቀመዋለሁ። መነሻ ሃሳብ ወይም ራሱን የቻለ ርእስ እወስድበታለሁ። አመጣጡ ጤነኛ ካልሆነ ግን አስወግደዋለሁ። "ተሳስተሃል" የሚል አካል በማስረጃ እንዲመጣ አደራ እላለሁ። ባይሆን ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም መዘጋጀት ደግ ነው። ለዛሬ ለመነሻ ያህል ይህን ካልኩ ይበቃኛል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የዙል ሒጃ ስምንቱን ቀናት መፆም
~
ነብያችን ﷺ የዙልሒጃን አስር ቀናት አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል፦

مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الأَيَّامِ الْعَشْرِ . فَقَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ، إِلا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ

''በውስጣቸው መልካም ስራ ከሚፈፀምባቸው ቀናት ውስጥ ከነዚህ አስር ቀናት በላይ አላህ ዘንድ የተወደደ የለም።" "በአላህ መንገድ መታገልም ቢሆን?" ብለው ሲጠይቋቸው የአላህ መልእክተኛ ﷺ "በአላህ መንገድ መታገልም ቢሆን! በነፍሱም፣ በገንዘቡም ወጥቶ ከዚህ ውስጥ ምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር" ብለው መለሱ። [አልቡኻሪይ፡ 969]

በዚህ መሰረት በነዚህ የተከበሩ ቀናት የተለያዩ ዒባዳዎችን መፈፀም በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ነው። ፆም ወደ አላህ መቃረቢያ ከሆኑ ዒባዳዎች ውስጥ አንዱ መሆኑ ግልፅ ነው። ከመሆኑም ጋር በያመቱ "የዙል ሒጃን አስር ቀናት መፆም ይቻላል ወይ?" የሚል ጥያቄ ሲነሳ ያጋጥማል። የግርታው መነሻ እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ "በነዚህ አስር ቀናት ውስጥ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ፈፅሞ ፆመው አላየሁም" ማለቷ ነው። [ሙስሊም፡ 1179]

ይሄ ግን ግርታ ሊፈጥር የሚገባው አይደለም። እንደሚታወቀው የነብዩ ﷺ ሱና በሶስት መንገድ ይተላለፋል።
1- በቃላቸው
2- በተግባራቸው እና
3- ሌሎች ሲፈፅሙ አይተው የሚሰጡት ይሁንታ (ኢቅራር)።

የዙል ሒጃን ስምንት ቀናት መፆም ከነዚህ ውስጥ በቃላቸው የተላለፈው ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል። ሐዲሡ አስተማማኝ፣ መልእክቱም ፆምን አካታች ነው። ከዚህ በኋላ የዓኢሻ ነብዩን ﷺ ሲፆሙ አለማየት የሳቸውን ጥቅል የቃል መልእክት ለመገደብ መነሻ መሆን የለበትም። ለዓኢሻ አለማየት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ደግሞ የሚገድብ መረጃ እስከሌለ ድረስ በጥቅል ቃላዊ መረጃ የተገኘው በቂ ነው።
ስለዚህ ሌሎች መረጃዎች ደካማዎች (ዶዒፎች) ቢሆኑ እንኳ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው ሐዲሥ በቂ ማስረጃ ነው።

ይሄ እንግዲህ ስምንቱን ቀናት በተመለከተ ነው።
* ዘጠነኛው ቀን የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያሳብስ አስተማማኝ መረጃ መጥቶበታል። [ሙስሊም፡ 1162] ስለዚህ ብዥታ የሚነሳበት አይደለም።
* አስረኛው ቀን በአል ስለሆነ አይፆምም።

ወሏሁ አዕለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ደርስ
~
* ኪታቡ፦ አልአርበዑነ ነውዊየህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር
* ቦታ፦ በአሸዋ ሜዳ፣ ዘህራ መስጂድ (ኮንደሚኒየም አጠገብ)
* ጊዜ፦ ሰኞ እና ማክሰኞ
* ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የምትችሉ ኪታቡን ገዝታችሁ ያዙ። የማትችሉ pdf ፋይል በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦ https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/7390
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (1 hour)
ብዙ ሰው ፆመኛ ስለሚሆን የዑምደቱል አሕካም ደርስ አይኖርም። ሲጀመር አሳውቃለሁ ኢንሻአላህ።
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

"በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው።" [አልቡኻሪይ ፡ 5027]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
መውደድ በልክ ነው፣ መጥላትም!
~
መዋደድና መጠላላት በዘመናት ውስጥ ሊፈራረቁ ይችላሉ፡። ዛሬ የጠሉት ነገ ወዳጅ ሊሆን ይችላል። በተቃራኒውም እንዲሁ። ሲጣሉ ልክ ማለፍ ሲታረቁ ያሳቅቃል። ሲዋደዱ አቅልን መሳት ሲራራቁ ይቆጫል። ሁሉም በልክ ሲሆን ያምራል። ይህንን ድንቅ ሐዲሥ እንመልከትማ፦
أحْبِبْ حبيبَكَ هوْنًا ما، عَسى أنْ يَكونَ بَغيضَكَ يومًا ما، و أبْغِضْ بغيضَكَ هوْنًا ما، عَسى أنْ يكونَ حبيبَكَ يومًا ما
"ወዳጅህን በልክ ሆነህ ውደድ። ምናልባት የሆነ ቀን የምትጠላው ይሆናል። የምትጠላውንም በልክ ሆነህ ጥላ። ምናልባትም የሆነ ቀን ወዳጅህ ሊሆን ይችላል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 178]
ልክ ሲያልፍ ግን ውዴታም ፈተና ይሆናል። ጥላቻም ገዳይ ይሆናል። ስንቶች አሉ በሆነ መነሻ የጠሉትን አካል ሞቱን የሚመኙ! ዘይድ ብኑ አስለም - ረሒመሁላህ - እንዳስተላለፉት ዑመር ብኑል ኸጧብን - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ብለዋል፦
لا يكُن حُبُّكَ كَلَفًا، ولا بُغضُكَ تَلَفًا
"ውዴታህ ፈተና አይሁን፤ ጥላቻህም ጥፋት አይሁን።"

"እንዴት ነው እሱ?" ስሏቸው ይህን አሉ፦
إذا أحبَبتَ كَلِفْتَ كَلَفَ الصَّبِيِّ، وإذا أبغضتَ أحببتَ لصاحبِك التَّلَفَ
"ስትወድ የህፃን አይነት ሙጭጭ ማለትን ሙጭጭ ልትል ነው። ስትጠላም ለጠላሀው አካል ሞቱን ልትወድ ነው።" [ሶሒሑል አደቢል ሙፍረድ፡ ቁ. 1322]

ልክ ባለፈ ፍቅር እና ጥላቻ ገደል የገቡ ብዙ አካላት አሉ። ሐሰኑል በስሪይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"أحبوا هونًا، وأبغضوا هونًا، فقد أفرط أقوامٌ في حب أقوام فهلكوا، وأفرط أقوام في بغض أقوام فهلكوا؛ فلا تفرط في حبك، ولا تفرط في بغضك"
"በልክ ውደዱ። በልክ ጥሉ። በውዴታ ልክ አልፈው የጠፉ ሰዎች አሉ። በጥላቻም ልክ አልፈው የጠፉ ሰዎች አሉ። በውዴታህ ድንበር አትለፍ። በጥላቻህም ድንበር አትለፍ።" [ሹዐቡል ኢማን፡ 5/261]

ልከኝነት ለሁሉም ኸይር አለው። በልክ ስትሆን ራስህን አትጎዳም። ለሌሎችም እዳ አትሆንም። ዐብዱላህ ብኑ ዐውን - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"كَانَ فِي بَعْضِ الْكُتُبِ الَّتِي كُنْتُ أَقْرَأُ عَلَى مُحَمَّدِ بْنِ سِيرِينَ : يا بُنَيَّ لَا تَكُنْ حُلْوًا فَتُبْتَلَعَ ، وَلَا مُرًّا فَتُلْفَظَ ، وَلَكِنْ بَيْنَ ذَلِكَ
"ሙሐመድ ብኑ ሲሪን ላይ የምቀራው ኪታብ ላይ እንዲህ የሚል ነበር፦ 'ልጄ ሆይ! ጣፋጭ አትሁን ትዋጣለህ። መራራም አትሁን ትተፍፋለህ። ይልቁንም በዚህ መሀል ሁን።" [አልጃሚዕ፣ ኢብኑ ወህብ፡ 475]

ስለዚህ ራሳችንንም ሌሎችንም እንዳንጎዳ፣ ኋላ ፀፀት እንዳይለበልበን ሁሉንም ነገር በልክ መያዝ ይገባል። ኢማሙ አሕመድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
لا تغلـو فـي كـل شـيء، حـتى الحـبّ و البغـض
"በየትኛውም ነገር ድንበር አትለፍ። በመውደድና በመጥላት እንኳ ቢሆን።" [አልኣዳቡ ሸርዒያህ፡ 1/98]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
Ibnu Munewor ፣ ዙል ቀዕዳህ 09/1444
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Audio
🔥🔥ሙስጠፋ ሙብተዲእ አይደለም 🔥🔥

💥 ለምትሉ 💥

በራሱ አንደበት ራሱ ላይ ሲበይን ስሙት ።
2025/07/13 15:30:48
Back to Top
HTML Embed Code: