አዎ ቁርኣን ፍጡር አይደለም!
~
የዐባሲያው ኸሊፋ መእሙን የጀመረው ፈተና በርካታ ዑለማኦችን በልቷል። ብዙዎች በእስር ማቀዋል። ከፊሎቹ ወህኒ ውስጥ እያሉ ሞተዋል። ኢማሙ አሕመድ ይህንን መከራ በፅናት ከተወጡት ዓሊሞች ውስጥ ቀዳሚ ናቸው። በዚህ ፅናታቸውም ነው ኢማሙ አህሊ ሱና ወልጀማዐ በሚል የሚታወቁት። አሕመድ በኸሊፋዎቹ የቀረበውን ፈተና እስከ ፈፃሜ ተቋቁመዋል። እስር፣ እንግልት፣ ድብደባ በያይነቱ ተፈራርቆባቸዋል። ቢሆንም አልተረቱም። ይሄ መከራና ፈተና በታሪክ በሰፊው የሚታወቅ ነው።
የፈተናው ሰበብ ምን ነበር? ኸሊፋው መእሙን "ቁርኣን ፍጡር ነው" የሚል አዲስ እምነት በግዳጅ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ መጫኑ ነበር። ከየት አመጣው? ከጀህሚያና ሙዕተዚላ አንጃዎች ወስዶ። የዘመኑ ዑለማኦች ምላሽ ምን ነበር? "ቁርኣን ፍጡር ነው የሚል ሰው ከኢስላም ወጥቷል" የሚል ነበር። "ቁርኣን ፍጡር ነው" የሚለውን የኸሊፋዎቹን አስገድዶ ማጥመቅ ባለመቀበላቸውም ነው እነዚያ ሁሉ ዓሊሞች የመከራ ዶፍ የወረደባቸው። ኸሊፋዎቹን ተጠቅመው ጥመታቸውን በጉልበት ህዝብ ላይ ሲጭኑ የነበሩት እንደ አሕመድ ብኑ አቢ ዱኣድ ያሉ የጀህሚያ ቁንጮዎች ናቸው። ይሄ ፅሁፉን ያያዝኩት አሕባሽ እና መሰሎቹ "ቁርኣን ፍጡር ነው " የሚሉት ብዙ ዐቂዳቸው ከጀህሚያ የተቀዳ ስለሆነ ነው። የአላህን ሲፋት ማስተባበል፣ ኢርጃእ፣ አህለ ሱናን ከሹማምንት ዘንድ ተለጥፎ ማስመታት፣ ... ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የጋራ በሽታቸው ነው።
ለማንኛውም ቁርኣን ፍጡር አይደለም። መረጃዎችን እጠቅሳለሁ።
1. መረጃ አንድ፦
ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
أَعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللَّهِ التَّامَّاتِ مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ.
"ፍፁም በሆኑት የአላህ ንግግሮች ከፈጠራቸው ፍጥረቶች ክፋት እጠበቃለሁ።" [ሙስሊም ፡ 2708]
ማስረጃ የሚሆነው እንዴት ነው? የአላህ ንግግሮች ፍጡር ቢሆኑ ኖሮ በነሱ ጥበቃን መጠየቅ አይቻልም ነበር። ምክንያቱም በፍጡር ጥበቃን መሻት ሺርክ ነውና።
2. መረጃ ሁለት፦
ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው። የአላህ ንግግር ሲፈቱ (መገለጫው) ነው። የአላህ ሲፋ ደግሞ ፍጡር ነው አይባልም። ልክ የአላህ እውቀቱ፣ ችሎታው፣ መሻቱ፣ ማየቱ፣ መስማቱ፣ ዐይኑ፣ ... ፍጡር እንደማይባለው መናገሩም ፍጡር ነው አይባልም። አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል። ሁሉን ማወቁ ፍጡር ነው ይባላል ወይ? በፍፁም! በተመሳሳይ መናገሩም ማለትም ንግግሩም ፍጡር ነው አይባልም። ቁርኣን የሱ ንግግር ስለሆነ ፍጡር ሳይሆን ሲፋው (መገለጫው) ነው።
3. መረጃ ሶስት - ኢጅማዕ፦
ከሸሪዐህ ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ ኢጅማዕ ነው፤ የኢስላም ሊቃውንት ወጥ ስምምነት። ቁርኣን ፍጡር እንዳልሆነ የሰለፎች ኢጅማዕ አለበት። ሰለፎች ቁርኣን ፍጡር ነው የሚል ሰው ሙስሊም እንዳልሆነ ደግመው ደጋግመው አስረግጠው ተናግረዋል። ለምሳሌ ያህል ጥቂት ልጥቀስ፦
* ኢብኑል ሙባረክ፦ "ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ ሰው ሙና ^ ፊق ነው" ብለዋል። [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ 1/111]
* አቡበክር ብኑ ዐያሽ:- "ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ ሰው በአላህ - ዐዘወጀለ - ላይ በርግጥም ቀጥፏል" ብለዋል። [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ 1/157]
* ሱፍያን ብኑ ዑየይነህ:- "ቁርኣን የአላህ - ዐዘወጀለ - ንግግር ነው። ፍጡር ነው ያለ ሰው ከሃዲ ነው። ክህደቱን የተጠራጠረም እርሱ ራሱ ከሃዲ ነው" ብለዋል። [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ 1/112]
* የዚድ ብኑ ሃሩን፦ ከሱ በቀር የሐቅ አምላክ በሌለው፣ የሩቅ የቅርቡን አዋቂ በሆነ ርህሩህና አዛኙ ጌታ ይሁንብኝ! ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ ሰው እሱ ሙና ^ ፊق ነው" ብለዋል። [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ 1/122]
* የሕያ ብኑ መዒን:- "ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ ሰው እሱ ከሃዲ ነው" ብለዋል። [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ 1/128]
* የሕያ ብኑ የሕያ:- "ከቁርኣን ውስጥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ከሱ አንድ አንቀጽ እንኳ ፍጡር ነች ያለ ሰው እሱ ከሃዲ ነው" ብለዋል። [አልሉው፣ አዘሀቢይ፡ 1/168]
* አሕመድ ብኑ ሐንበል፦ "ቁርኣን ፍጡር ነው ያለ ሰው እሱ ከሃዲ ነው" ብለዋል። [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ 1/102]
ዝርዝሩ ረጅም ነው። ምንጩ ታማኝ ዓሊሞች ናቸው። ለተጨማሪ የቡኻሪን "ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ" ኪታብ ይመልከቱ።
ስለዚህ ይሄ ጉዳይ የቀድምቶች ኢጅማዕ ያለበት ጉዳይ ነው ማለት ነው። አላለካኢይ ረሒመሁላህ ይህንን ዐቂዳ ያስተጋቡ ዓሊሞችን በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ እንዲህ ብለዋል፦
(... قالوا كُلُّهم: القُرْآنُ كَلامُ اللهِ غَيرُ مَخلوقٍ، ومن قال: مخلوقٌ، فهو كافِرٌ. فهؤلاء خَمسُمائةٍ وخَمسونَ نَفسًا أو أكثَرُ من التابعينَ وأتباعِ التَّابعين والأئمَّةِ المَرْضِيِّين سوى الصَّحابةِ الخَيِّرينَ على اختلافِ الأعصارِ ومُضِيِّ السِّنينَ والأعوامِ. وفيهم نحوٌ من مائةِ إمامٍ ممَّن أخذ النَّاسُ بقولِهم وتدَيَّنوا بمذاهِبِهم، ولو اشتَغَلْتُ بنَقلِ قَولِ المحَدِّثين لبلغَت أسماؤهم ألوفًا كثيرةً، لكنِّي اختصَرْتُ وحَذَفتُ الأسانيدَ للاختصارِ، ونَقَلْتُ عن هؤلاء عصرًا بعد عصرٍ لا يُنكِرُ عليهم مُنكِرٌ، ومن أنكر قولَهم استتابوه، أو أمَروا بقَتْلِه أو نَفْيِه أو صَلْبِهـ) .
"ሁላቸውም ቁርኣን የአላህ ንግግር እንጂ ፍጡር አይደለም ብለዋል። ፍጡር ነው ያለ ሰው ከሃዲ ነው። እነዚህ ከሶሓቦች በኋላ የመጡ ከታቢዒዮች፣ አትባዑ ታቢዒን፣ ቅቡልነት ያላቸው ሊቃውንት የሆኑ አምስት መቶ ሃምሳ (550) ዓሊሞች ወይም ከዚያ የበዛ በተለያዩ ክፍለ ዘመናት እና አመታት የኖሩ ናቸው። ከነሱ ውስጥ ሰዎች ንግግሮቻቸውን የወሰዱላቸው እና በመዝሀባቸው የተከተሏቸው መቶ አካባቢ ታላላቅ ሊቃውንት አሉ። የሐዲሥ ሊቃውንት ንግግሮችን በመዘርዘር ላይ ብጠመድ ስሞቻቸው ብዙ ሺዎችን ያልፉ ነበር። ነገር ግን አሳጥሬዋለሁ። ሰንሰለቶቹንም አስቀርቻለሁ። ከነዚህ ውስጥ ከየዘመኑ ወስጃለሁ። የሚቃወም ተቃዋሚ አልነበረም። የተቃውመን ተውበት እንዲያደርግ ያስገድዱት አለያ ደግሞ እንዲገ ^ ደል ወይም ከሃገር እንዲባረር ወይም እንዲሰ ^ ቀል ያዝዙ ነበር።" [ሸርሑ ኡሱሊ ኢስቲቃዲ አህሊ ሱና ወልጀማዐህ ፡ 2/344]
የዑለማኡ ሱና አካሄድ እና እምነት ከጥንት እስከ ዛሬ ይሄ ነው። የጀህሚያን (የአሕባሽን) ዐቂዳ ማወቅ የፈለገ ደግሞ ያያያዝኩት ልጥፍ አንድ ማሳያ ነው። ሰውየው በአላህ ሲፋት ላይ የሚሳለቅ፣ ተውሒድን የሚዋጋ፣ በጠራራ ፀሐይ ወደ ወለድ የሚጣራ፣ አሁን ደግሞ "ቁርኣን ፍጡር ካልሆነ ፈጣሪ ሊሆን ነው ወይ?" እያለ በድንቁ ^ ርናው የሚኮፈስ፣ አለማወቁን እንኳ የማያውቅ ጃሂል መባል የሚበዛበት ኸቢث ፍጡር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

Forwarded from قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh Muhammed Zain Adam - ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም (عبد السلام عبد الله)
ኢብኑ ዐብዲል በር እንዲህ ይላሉ፦
"አስተዋይ የሆነ ሙእሚን ከበጎ ስራ ውስጥ የትኛውንም ሊንቅ አይገባም። ምናልባትም በትንሹ ምህረትን ሊያገኝ ይችል ይሆናልና።"
[አተምሂድ ፡ 13/539]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
"አስተዋይ የሆነ ሙእሚን ከበጎ ስራ ውስጥ የትኛውንም ሊንቅ አይገባም። ምናልባትም በትንሹ ምህረትን ሊያገኝ ይችል ይሆናልና።"
[አተምሂድ ፡ 13/539]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለሴቶች!
~
ሰበብ እየፈለጉ ያለ ቤተሰብ እውቅና በየመንደሩ የድብቅ ኒካሕ ከሚያስሩ ጎረምሶች፣ ደረሳዎች፣ የዱዓት ጭንብል ካጠለቁ ዱርየዎች ተጠንቀቁ! ጋብቻችሁም አይሰምርም። መለያየታችሁም አያምርም። የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«لا نِكَاحَ إِلّا بِوَليٍّ»
"ያለ ወሊይ ኒካሕ የለም።"
አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1537]
በሆነ ሸሪዐዊ ምክንያት አባትን መጠቀም ካልተቻለ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ሌሎችን መጠቀም እንጂ ሰበብ እየፈለጉ ከወሊይ እውቅና ውጭ የድብቅ ጋብቻ መፈፀም ተቀባይነት የለውም። በዲንና በደዕዋ ስም ስማቸውን ከተከሉ፣ ታማኝነትን ካገኙ በኋላ ብዙ ጥፋት የሚፈፅሙ አሉ።

ሃብት እና ትዳር
~
ለትዳር ሃብት ያለውን ወይም ያላትን መምረጥ ምንም የሚያስወቅስ ነገር የለውም። የሚያስወቅሰው ሃብትን ብቻ በማየት የማይሆን ሰው ማግባት ነው። "ባለ ዲኗን ምረጥ" የሚለው ሐዲሥ መልእክቱ ከዚህ አንፃር የሚታይ ነው።
ስለዚህ ሴቷ ተውሒድ ያለው፣ ሶላት የሚሰግድ፣ አላህን የሚፈራ እስከሆነ ድረስ ሃብት ያለውን ብትመርጥ ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰነችው። ሃብት አይታ ሄደች ተብላ የምትወቀስበት ምንም አይነት ውሃ የሚያነሳ ምክንያት የለም።
ወንዱም ላይ ተመሳሳይ ነገር ማለት ይቻላል። የእውነት ትዳር ፈላጊ እስከሆነ ድረስ ገንዘቤን ፈልጎ ሊሆን ይችላል የመጣው እያልሽ አትመልሺ። ወይም ከገባሽ በኋላ ትዳርሽን በአጉል ስሜት አትበጥብጪ። ሃብትሽ ለትዳርሽ ፈተና አይሁንብሽ። ትዳር ጌጥ ነው። ትዳር መከበሪያ ነው። ትዳር ዱንያ ብቻ ሳይሆን ዲንም ነው። እንዲያውም አላህ ሃብት ሰጥቶሽ ከሆነ ሁነኛ ሰው አፈላልገሽ ጥሩ ትዳር ለመመስረት ተጠቀሚበት። "በሃብቷ ልትጫነኝ ትፈልጋለች" የሚል ስሜት አድሮበት ሳይሳቀቅ ቤቴ ብሎ ዘና ብሎ በርትቶ ስራ ላይ እንዲሰማራ አድርጊው። የኸዲጃን - ረዲየላሁ ዐንሃ - ታሪክ አስታውሺ። በሃብታቸው ጥሩ ትዳር የመሰረቱ ብልጥ ሴቶችን እናውቃለን። ሃብታቸው ፈተና ሆኖባቸው ምን የመሰለ ትዳራቸውን አፍርሰው የተፀፀቱ ሴቶችንም እናውቃለን።
በሌላ በኩል ከገንዘብ ውጭ ለትዳር ቦታ የሌለው፣ ስግብግብ ወንድም ያጋጥማል። ሰው እንደ አገዳ ተነክሶ አይለይም። አስተውሎ፣ ሰው አማክሮ ዲኑ እና ስነ ምግባሩ ያማረ የሆነውን መምረጥ፣ ዱዓእ ማድረግ፣ በአላህ ላይ መውወከል፣ በራስ በኩል ያለን ኃላፊነት እስከ ጥግ መወጣት ለዘላቂ ትዳር ሁነኛ ሰበቦች ናቸው።

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ከጠቢባን አንደበት
~
ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ - አንድን ሰው እየመከሩ እንዲህ ይላሉ፦
✅ "በማያገባህ ላይ አትናገር።
✅ ጠላትህን ራቅ።
✅ ታማኝ ካልሆነ በስተቀር ወዳጅህን ተጠንቀቅ። አላህን - 0ዘ ወጀለ - የሚፈራና የሚታዘዝ ካልሆነ በስተቀር ወዳጅ ሁሉ ታማኝ አይደለም።
✅ ከባለ ጌ ጋር አትጓዝ። ከብልግናው ያስተምርሃልና። ምስጢርህንም አታሳውቀው።
✅ አላህን ለሚፈሩ ካልሆነ በስተቀር በጉዳይህ ላይ ማንንም አታማክር።"
[አልኣዳቡ ሸርዒያህ፡ 4/223]
#ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
የቴሌግራም ቻናል፦

የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 214፣ باب النذر
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 214፣ باب النذر
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Forwarded from Wolkite University Muslim students jeme'a official channel (Fereh)
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
በአላህ ፈቃድ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 16/09/2017 ለተመራቂ ተማሪዎች የሽኝት (Well Go) ፕሮግራም ስለተዘጋጀ ከወዲሁ እቅዳችንን adjust በማድረግ የሙሀደራ ድግሱን አብረን እንድናሳልፍ ጋብዘናችኃል። መረጃውን ለሌሎች ማድረስና በጊዜ መገኘት ከሁላችን የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው። አላህ ይወፍቀን!
● ተጋባዥ እንግዶች
1. ኡስታዝ ዐብዱናሲር መኑር (ከአዲስ አበባ)
2. ኡስታዝ ሁሰይን ሱለይማን (ከቡታጅራ)
🏠 አድራሻ : ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኢብኑ ዓባስ መስጂድ
⌚️ ሰዓት : 2:30-7:00
📎 ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ቀን : ቅዳሜ 16/09/2017 ኢትዮ

ጌታህ ረሺ አይደለም!
~
በበዳይ ሰው ልብ ላይ ቀስት የሆነች፣ በተበዳይ ሰው ልብ ላይ ደግሞ ፈውስ የሆነች አንዲት የቁርኣን አንቀፅ!
{ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِیࣰّا }
"ጌታህም ረሺ አይደለም።" [መርየም፡ 64]
.
ኮፒ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
በበዳይ ሰው ልብ ላይ ቀስት የሆነች፣ በተበዳይ ሰው ልብ ላይ ደግሞ ፈውስ የሆነች አንዲት የቁርኣን አንቀፅ!
{ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِیࣰّا }
"ጌታህም ረሺ አይደለም።" [መርየም፡ 64]
.
ኮፒ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #50
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-5️⃣ 0️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 214፣ باب النذر
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 214፣ باب النذر
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሙሳ ሰዎች ቂሷ ለዑዝር ቢል ጀህል ማስረጃ
~
አላዋቂ ሰው ጥፋት ቢፈፅም ወንጀለኛ አይደለም። ሰው ወንጀለኛ የሚሆነው ሆነ ብሎ በሚፈፅመው ጥፋት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{وَلَیۡسَ عَلَیۡكُمۡ جُنَاحࣱ فِیمَاۤ أَخۡطَأۡتُم بِهِۦ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتۡ قُلُوبُكُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمًا}
"በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ሃጢአት የለባችሁም። ግን ልቦቻችሁ አውቀው በሠሩት (ሃጢአት አለባችሁ)። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" [አልአሕዛብ፡ 5]
ይሄ ሁሉንም የዲን ርእሶች የሚያካትት መሰረታዊ የሸሪዐ ህግ ነው። "ዐቂዳ ሲቀር"፣ "ኡሉሂያ ሲቀር" የሚለው የአንዳንዶች 'ኢስቲሥናእ' ጠንካራ መሠረት ላይ ያልቆመ ውሃ የማያነሳ ሙግት ነው።
ስለዚህ አንድ ሙስሊም ባለማወቅ ሺርክ ቢፈፅም ከኢስላም አይወጣም። ይህንን ከሚያስይዙ ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ የሙሳ ሰዎች ታሪክ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿وَجَـٰوَزۡنَا بِبَنِیۤ إِسۡرَ ٰۤءِیلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتَوۡا۟ عَلَىٰ قَوۡمࣲ یَعۡكُفُونَ عَلَىٰۤ أَصۡنَامࣲ لَّهُمۡۚ قَالُوا۟ یَـٰمُوسَى ٱجۡعَل لَّنَاۤ إِلَـٰهࣰا كَمَا لَهُمۡ ءَالِهَةࣱۚ قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمࣱ تَجۡهَلُونَ﴾
''የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው፡፡ በጣዖቶቻቸው (ማምለክ) ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ዘንድም አለፉ፡፡ 'ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' አሉት፡፡ 'እናንተ የማታውቁ ሕዝቦች ናችሁ' አላቸው።" [አልአዕራፍ ፡ 138]
* ታሪኩ ምን ያስይዛል? እነዚህ የሙሳ ሰዎች፡
1ኛ፦ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ላይ ያዩትን የሺርክ ተግባር ለመፈፀም ጠይቀው እንደነበር፣
2ኛ፦ የጠየቁት ጉዳይ ከኢስላም የሚያስወጣ መሆኑን ባለማወቅ እንደሆነ፣
3ኛ፦ ባለማወቃቸውም የተነሳ ከኢስላም እንዳልወጡ እንወስዳለን።
ስለዚህ ባለማወቅ ሺርክ ወይም ኩ * f ር የፈፀመ ሰው ከኢስላም እንደማይወጣ ከታሪኩ እንረዳለን። ይህንን ሃሳብ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ረሒመሁላህ በከሽፉ ሹቡሃት ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል። የቀረበበት ጭብጥ ምንድነው?
የበኑ ኢስራኢል ሰዎች "አምላክ አድርግልን" ከማለታቸው ጋር ከኢስላም አልወጡም። በተመሳሳይ ሙታን የሚጣሩ ሰዎችም በተግባራቸው ቢቀጥሉም ከኢስላም አይወጡም የሚል ሙግት ለሚያቀርቡ አካላት እነሱ ሲነገራቸው ከመፈፀም ታቅበዋል። ከተነገራቸው በኋላ ቢቀጥሉ ኖሮ ከኢስላም ይወጡ ነበር የሚል ነው ባ'ጭሩ።
ከሽፉ ሹቡሃትን ሸርሕ ያደረጉ ሌሎች ዓሊሞችም የሸይኹን ሃሳብ አርመው ሳይሆን አጠናክረው ነው የፃፉት።
የአንቀጿ አጭር ተፍሲር
-
በቅድሚያ እዚህ ላይ የማቀርባቸው ማብራሪያዎች በሙሉ ከቀደምት የተፍሲር ሊቃውንት የተወሰዱ እንደሆኑ ይሰመርልኝ። የዓሊሞቹን ሙሉ ትንታኔያቸውን የሚፈልግ ሰው ከምጠቅሳቸው ምንጮች ይመልከት። እኔ ለማሳጠር ስል ለማስረጃ በቂ ናቸው የምላቸው ነጥቦች ላይ ብቻ ነው የማነጣጥረው።
1. ኢብኑ ጀሪር አጦበሪይ (310 ሂ.):-
" ... اجعل لنا" يا موسى "إلهًا"، يقول: مثالا نعبده وصنما نتخذُه إلهًا، كما لهؤلاء القوم أصنامٌ يعبدونها. ولا تنبغي العبادة لشيء سوى الله الواحد القهار. وقال موسى صلوات الله عليه: إنكم أيها القوم قوم تجهلون عظمة الله وواجبَ حقه عليكم، ولا تعلمون أنه لا تجوز العبادة لشيء سوى الله الذي له ملك السموات والأرض.
" 'ሙሳ ሆይ! አምላክ አድርግልን' አሉ። 'የምንገዛው ሃውልት፣ አምላክ አድርገን የምን ይዘው ጣዖት። ልክ ለነዚያ ሰዎች የሚያመልኳቸው ጣዖቶች እንዳሏቸው 'ማለታቸው ነው። ከአንድየውና አሸናፊው አላህ ውጭ ለማንም አምልኮት አይገባም። ሙሳ - የአላህ ሶለዋት በሱ ላይ ይሁንና - 'እናንተ የአላህን ልቅና እና በናንተ ላይ ያለውን የግዴታ ሐቁን አታውቁም፤ አምልኮት ለዚያ የሰማያትና የምድር ባለቤት ከሆነው ውጭ ለምንም እንደማይገባም አታውቁም ' አላቸው።" [ተፍሲር አጦበሪ]
2. መኪይ ብኑ አቢ ጧሊብ (437 ሂ.):-
فقال لهم موسى: عليه السلام: ﴿إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ﴾. أي: تجهلون نعمة الله عز وجل، عليكم وحقه، وتجهلون أنه لا تجوز العبادة إلا لله، سبحانه.
"ሙሳ - ዐለይሂ ሰላም - ለነሱ፡ 'እናንተ የማታውቁ ሕዝቦች ናችሁ' አላቸው። ማለትም፡ አላህ - ዐዘ ወጀለ - በናንተ ላይ ያለውን ፀጋ እና ሐቁን ትዘነጋላችሁ። ከአላህ - ሱብሓነህ - በስተቀር ለሌላ አምልኮት እንደማይፈቀድ ትዘነጋላችሁ።" [ተፍሲር መኪይ አቢ ጧሊብ]
3. አሰምዓኒይ (489 ሂ.):-
﴿قَالُوا يَا مُوسَى اجْعَل لنا إِلَهًا كَمَا لَهُم آلِهَة﴾ وَلم يكن ذَلِك من بني إِسْرَائِيل شكا فِي وحدانية الله - تَعَالَى - وَإِنَّمَا مَعْنَاهُ: اجْعَل لنا شَيْئا نعظمه ونتقرب بتعظيمه إِلَى الله - تَعَالَى - وظنوا أَن ذَلِك لَا يضر الدّيانَة، وَكَانَ ذَلِك من شدَّة جهلهم.
" 'ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' አሉት፡፡ የበኑ ኢስራኢል ሰዎች ይህን ሲሉ የላቀውን አላህ አንድነት በመጠራጠር አይደለም። ይልቁንም 'ለኛ የምናልቀው እና እሱን በማላቅ ወደ አላህ - ተዓላ - የምንቃረብበት አድርግልን' ማለታቸው ነው። ይሄ እምነትን የማይጎዳ መስሏቸዋል። ይሄ በመሀይምነታቸው ክፋት የተነሳ ነው።" [ተፍሲር አሰምዓኒይ]
4. ኢብኑ ዐጢያ (546 ሂ.):-
ቃዲ አቡ ሙሐመድ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፦
والظاهِرُ مِن مَقالَةِ بَنِي إسْرائِيلَ لِمُوسى: ﴿اجْعَلْ لَنا إلَهًا كَما لَهم آلِهَةٌ﴾ أنَّهُمُ اسْتَحْسَنُوا ما رَأوهُ مِن آلِهَةِ أُولَئِكَ القَوْمِ، فَأرادُوا أنْ يَكُونَ ذَلِكَ في شَرْعِ مُوسى وفي جُمْلَةِ ما يَتَقَرَّبُ بِهِ إلى اللهِ، وإلّا فَبَعِيدٌ أنْ يَقُولُوا لِمُوسى: اجْعَلْ لَنا صَنَمًا نُفْرِدُهُ بِالعِبادَةِ ونَكْفُرُ بِرَبِّكَ. فَعَرَّفَهم مُوسى عَلَيْهِ السَلامُ أنَّ هَذا جَهْلٌ مِنهم إذْ سَألُوا أمْرًا حَرامًا فِيهِ الإشْراكُ في العِبادَةِ
"የኢስራኢል ልጆች ለሙሳ፡ 'ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' ሲሉ ጉልህ መልእክቱ የሚያስይዘው እነሱ ከነዚያዎቹ ሰዎች አማልኮት ከተመለከቱት በመነሳት መልካም ነገር አድርገው አስበውታል፡፡ በዚህ የተነሳ ይሄ ተግባር በሙሳ ሸሪዐ ውስጥ እንዲካተት እና ወደ አላህ ከሚቃረቡባቸው ተግባራት ውስጥ እንዲሆን ፈልገዋል። እንጂ ለሙሳ 'በጌታህ ክደን በአምልኮት ብቸኛ አድርገን የምን ይዘው ጣዖት አድርግል' ሊሉት አይችሉም። ሙሳ - ዐለይሂ ወሰለም - ይሄ የነሱ

ነገር አለማወቅ እንደሆነ አሳወቋቸው። በአምልኮ ማጋራት ያለበት ክልክል ነገር ነውና የጠየቁት።" [አልሙሐረሩል ወጂዝ፣ ኢብኑ ዐጢያ]
5. ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ .)
وهذا إخبار عن عظيم جهلهم حيث توهموا جواز عبادة غير الله ، بعد ما رأوا الآيات".
"ይሄ አለማወቃቸው ምንኛ የራቀ እንደሆነ መናገር ነው፤ እነዚያን ሁላ ተአምራት ካዩ በኋላ ከአላህ ውጭ ያለን ማምለክ እንደሚቻል ገምተዋልና።'' [ዛዱል መሲር፡ 2/150]
6. ኢብኑ ከሢር (774 ሂ.):-
يُخْبِرُ تَعَالَى عَمَّا قَالَهُ جَهَلَةُ بَنِي إِسْرَائِيلَ لِمُوسَى، عَلَيْهِ السَّلَامُ، ... فَقَالُوا: ﴿يَا مُوسَى اجْعَلْ لَنَا إِلَهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ﴾ أَيْ: تَجْهَلُونَ عَظَمَةَ اللَّهِ وَجَلَالَهُ، وَمَا يَجِبُ أَنْ يُنَزَّهَ عَنْهُ مِنَ الشَّرِيكِ وَالْمَثِيلِ
"የላቀው አላህ መሀይማን በኑ ኢስራኢል ለሙሳ - ዐለይሂ ወሰለም - ያሉትን አስመልክቶ ይነግረናል። ... 'ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' አሉት፡፡ ይህም 'እናንተ የማታውቁ ሕዝቦች ናችሁ' አላቸው። የአላህን ልቅና እና ክብር እንዲሁም ከተጋሪና ከአምሳያ ሊያጠሩት እንደሚገባ የማታወቁ ናችሁ' ማለት ነው።" [ተፍሲር ኢብኒ ከሢር]
ብዥታዎች
-
ይሄ የሙሳ ሰዎች ቂሷ ማስረጃ ሆኖ ሲቀርብ የሚነሱ የተለመዱ ብዥታዎች አሉ። እንያቸው።
#ብዥታ_አንድ፦ "እነሱ ጥያቄ ጠየቁ እንጂ ሺርክ አልሰሩም" የሚሉ አሉ።
°
ምን ማለታቸው ነው? የሙሳ ሰዎች ጥያቄ ነው የጠየቁት። እንደማይቻል ሲነገራቸው ቆመዋል። ሁኔታቸው ሺርክ ከሚፈፅሙ ሰዎች ይለያል የሚል ነው።
ምላሽ፦
ሀ - ጥያቄያቸው'ኮ በራሱ ሺርክ ነው!
የሙሳ ሰዎች ጥያቄያቸው "ይቻላል ወይስ አይቻልም?" ወይም "ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም?" የሚል አይደለም። ጥያቄያቸው "ወደ አላህ መቃረቢያ እንዲሆነን የምናመልከው አምላክ አድርግልን" የሚል ነው። ይሄ ግልፅ ሺርክ ነው። ከላይ ያሰፈርኳቸውን የዓሊሞቹን ንግግር ተመልከቱ። ጥያቄያቸው ሺርክ እንደሆነ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ እንዲህ ሲሉ አስረግጠው ይናገራሉ፦
وتفيد أيضا أن المسلم المجتهد إذا تكلم بكلام كفر وهو لا يدري فنبه على ذلك فتاب من ساعته أنه لا يكفر كما فعل بنو إسرائيل
"ታሪኩ በተጨማሪ አንድ ለሐቅ ፍለጋ የሚጥር ሙስሊም ሳያውቅ #የክህደት ንግግር ቢናገር እና በዚያ ላይ ማስገንዘቢያ ተሰጥቶት ወዲያው ከተመለሰ ከኢስላም አይወጣም፤ ልክ በኑ ኢስራኢል እንዳደረጉት ማለት ነው።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 45]
ልብ በሉ! "የክህ .ደት ንግግር" ብለው ነው የገለፁት። እነዚህ ግን "ጥያቄ" ብለው ያሉታል።
ለ - "ያላወቀ አልገባም" የሚለው ህጋችሁ የት ገባ?
እነዚህ ዑዝር ቢልጀህል የለም የሚሉ ሰዎች "የኡሉሂያ ጉዳይ በዐቅል የሚታወቅ ነው። ላ ኢላሀ ኢለላህን እና አፍራሿን ያላወቀ ሰው ከነጭራሹ ወደ ኢስላም አልገባም" የሚሉ ናቸው። እንዲህ አይነት አቋም የሚያራምድ አካል የሙሳ ሰዎችን "ጠየቁ እንጂ መቼ ፈፀሙት?" ሊል አይገባም። በራሱ ህግ መሰረት ከነ ጭራሹ ወደ ኢስላም አልገቡምና።
#ብዥታ_ሁለት፦ "የሰዎቹ ጥፋት ትንሹ ሺርክ ነው" የሚሉም አሉ።
ምላሽ፦
የነዚህ ሰዎች አላማ በጥፋታቸው ከኢስላም ያልወጡት የፈፀሙት ትንሹ ሺርክ በመሆኑ ነው የሚል ነው። ይሄ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። "አምላክ አድርግልን" ማለት በምን ስሌት ነው ትንሹ ሺርክ የሚሆነው? ቀድመው አቋም ይዘው ስለሚዘጉ እንጂ ይሄ ሐቂቃ ለማንም የሚሰወር አልነበረም። ለማንኛውም ከላይ ያሰፈርኳቸውን የሙፈሲሮቹን ትንታኔ አስተውሉ።
* ሰምዓኒይ :- "ለኛ የምናልቀው እና እሱን በማላቅ ወደ አላህ - ተዓላ - የምንቃረብበት አድርግልን" እንዳሉ ገልፀዋል። የመቃረቢያ ሺርክ ጥንት የቁረይሾች ዛሬ ደግሞ የብዙ ሱፊዎች ሺርክ ነው፤ ትልቁ ሺርክ።
* ኢብኑ ዐጢያ፦ "ይሄ ተግባር በሙሳ ሸሪዐ ውስጥ እንዲካተት እና ወደ አላህ ከሚቃረቡባቸው ተግባራት ውስጥ እንዲሆን ፈልገዋል። ... በአምልኮ ማጋራት ያለበት ክልክል ነገር ነው የጠየቁት" ብለዋል።
እና ይሄ ትንሹ ሺርክ ነው? አላህን ፍሩ። ህሊናችሁንም አክብሩ። "አምላክ አድርግልን" የሚለው ንግግር ትልቁ ሺርክ እንደሆነ የማያውቅ ሰው ዑዝር ቢል ጀህል ባይኖር ኖሮ ሙስሊም አይሆንም ነበር።
#ብዥታ_ሶስት፦ "በአንቀጿ ውስጥ የተጠቀሰው ጀህል አለማወቅ ሳይሆን አውቆ ማጥፋት ነው። ሰዎቹ በፈፀሙት ሺርክ ከኢስላም ወጥተዋል" የሚሉም አሉ።
ምላሽ፦
ይሄም የተሳሳተ ድምዳሜ ነው። ምክንያቱም
ሀ - ሰዎቹ አውቆ አጥፊ ሳይሆኑ ባለማወቅ የጠየቁ እንደሆነ ከላይ ያሳለፍኳቸውን ስድስት ተፍሲሮች አስተውሉ። ጉዳዩ ኢንሷፍ ብቻ ነው የሚፈልገው።
ለ - እነዚህ የሙሳ ሰዎች ጥያቄያቸው ባለማወቅ እንደሆነ እና በዚህም የተነሳ ከኢስላም እንዳልወጡ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ደጋግመው ተናግረዋል። ይሄውና፦
1- ومن الدليل على ذلك أيضا ما حكى الله عن بني إسرائيل مع إسلامهم وعلمهم وصلاحهم، أنهم قالوا لموسى: اجعل لنا إلها كما لهم آلهة
"በዚህ ላይ ከሚነሱ ማስረጃዎች ውስጥ ደግሞ ሌላው አላህ ስለ በኑ ኢስራኢል የገለፀው ነው። ሙስሊሞች ከመሆናቸው ጋር፣ ዒልም ያላቸው እና ደጋጎች ከመሆናቸው ጋር ለሙሳ፡ 'ለእነርሱ አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን' ብለዋል፡፡" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 43]
ልብ በሉ! ሸይኹ እነዚህን የሙሳን ሰዎች ሙስሊሞች፣ ኧረ እንዲያውም ዓሊሞች፣ አልፎም ደጋጎች ብለው ነው የገለጿቸው። ልጨምር!
2- ولا خلاف أن بني إسرائيل لو فعلوا ذلك لكف .روا.
"የበኑ ኢስራኢል ሰዎች ያንን (የጠየቁትን) ቢሰሩት ኖሮ ከኢስላም ይወጡ እንደነበር በዑሉማእ መካከል ልዩነት የለም።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 44]
ልብ በሉ! ሰዎች ሙስሊሞች ባይሆኑ ኖሮ ከኢስላም ይወጡ ነበር አይሉም። ካ fi ር ከመነሻውም ከኢስላም ውጭ ነውና። ልቀጥል፦
3- هذه القصة تفيد أن المسلم بل العالم قد يقع في أنواع من الشرك لا يدري عنها
"ይህቺ ታሪክ አንድ ሙስሊም ኧረ እንዲያውም ዓሊም የሆነ ሰው ሳያውቀው የሺርክ አይነቶች ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ትጠቁማለች።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 45]
ልብ በሉ! ሰዎቹን ሙስሊሞች እንደሆኑና የወደቁበትንም ጥፋት ባለማወቅ እንደሆነ እየጠቆሙ ነው። ተጨማሪ!
4- وتفيد أيضا أن المسلم المجتهد إذا تكلم بكلام كف .ر وهو لا يدري فنبه على ذلك فتاب من ساعته أنه لا يكف . ر كما فعل بنو إسرائيل
"ታሪኩ በተጨማሪ አንድ ለሐቅ ፍለጋ የሚጥር ሙስሊም ሳያውቅ የክህደት ንግግር ቢናገር እና በዚያ ላይ ማስገንዘቢያ ተሰጥቶት ወዲያው ከተመለሰ ከኢስላም አይወጣም፤ ልክ በኑ ኢስራኢል እንዳደረጉት ማለት ነው።" [ከሽፉ ሹቡሃት፡ 45]

እዚህም ላይ ሰዎቹ ሙስሊሞች መሆናቸውን እየጠቆሙ ነው። ተመሳሳይ ሁኔታ ያለው ሰው ከኢስላም እንደማይወጣ የሚገልፀው ንፅፅራቸው ከዚህ ውጭ ሌላ ትርጉም የለውም።
ማሳሰቢያ፦
-
ሃሳብ ወይም እርምት አለኝ ለሚል ሰው በሩ ክፍት ነው። ባይሆን
1. በአደብ ይሁን።
2. ነጥብ ይጠበቅ። ስለ "ዛቱ አንዋጥ" ቂሷ አላወራሁም። የፃፍኩት ስለ ሙሳ ሰዎች ቂሷ ብቻ ነው።
3. ሙሉውን ያላነበበ ሃሳብ እንዳይሰጥ።
4. "ይህን የሚፈፅሙ፣ ያን የሚያደርጉ ሰዎችን ሙስሊሞች ናቸው ልትል ነው ወይ?" አይነት ከደሊል የተራቆተ ስሜት ኮርኳሪ፣ ሽብር ፈጣሪ ሙግት አልቀበልልም። እችላለሁ የሚል ሰው ዒልሚይ የሆነ ሃሳብ መሰንዘር ይችላል።
ባግባቡ የማይመጣን ሃሳብ ልሰርዝ እችላለሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 15/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ማሳሰቢያ፦
-
ሃሳብ ወይም እርምት አለኝ ለሚል ሰው በሩ ክፍት ነው። ባይሆን
1. በአደብ ይሁን።
2. ነጥብ ይጠበቅ። ስለ "ዛቱ አንዋጥ" ቂሷ አላወራሁም። የፃፍኩት ስለ ሙሳ ሰዎች ቂሷ ብቻ ነው።
3. ሙሉውን ያላነበበ ሃሳብ እንዳይሰጥ።
4. "ይህን የሚፈፅሙ፣ ያን የሚያደርጉ ሰዎችን ሙስሊሞች ናቸው ልትል ነው ወይ?" አይነት ከደሊል የተራቆተ ስሜት ኮርኳሪ፣ ሽብር ፈጣሪ ሙግት አልቀበልልም። እችላለሁ የሚል ሰው ዒልሚይ የሆነ ሃሳብ መሰንዘር ይችላል።
ባግባቡ የማይመጣን ሃሳብ ልሰርዝ እችላለሁ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 15/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
የዑምደቱል አሕካም ደርስ
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
• ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የዛሬ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #51
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-5️⃣ 1️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:-
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 217፣ ሐዲሥ ቁ. 366
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM